የአንድነት ገዳማት ኅብረቱ መተዳደሪያ ደንብ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ በኩል ታይቶና ተመርምሮ እንዲቀርብ፣
በአጠቃላይ በአንድነት ገዳማት ኅብረት የቀረበው የገዳማውያንና ገዳማውያት ማረፊያ እና የገቢ ማስገኛ ሁለገብ ሕንጻ ግንባታ የትግበራ ዕቅድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል በዘርፉ ባለሙያዎች ታይቶና ተገምግሞ ከባለሙያ አስተያየቶችና የውሳኔ ሐሳብ ጋር ተጠንቶ ለግንቦት 2018 ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ እንዲቀርብ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡
9.በበዓላት አከባበር፣ በመንፈሳዊ አገልግሎት አፈጻጸም ዙሪያ የሚታዩ ግድፈቶች፣ ያልተገቡ እንቅስቃሴዎችና ከሥርዓት የወጡ የአገልግሎት አፈጻጸሞች መታረም ስላለባቸው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሚሰየሙ ሊቃውንትና ባለሙያዎች ለመመሪያና ለማስተማሪያ የሚሆን ሰነድ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተገቢውን ውሳኔ ያስተላለፈ መሆኑን እየገለጽን ያለጠባሳ የሚያድኑ ሐኪሞች፣ ያለቅሬታ የሚያስታርቁ ሽማግሌዎች በነበሩባትና ባሉባት ሀገር ተመካክሮ ችግርን አለመፍታት ተገቢ አይደለምና ሀገራችንን እንወዳለን፣ ሕዝባችንን እናከብራለን የምትሉ፣ የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባችሁ ሁሉ ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ እንዳይጠፋ፣ አካሉ እንዳይጐድል የሀገር ልማትና መልካም ገጽታ እንዳይበላሽ ጠላት መባባሉ ቀርቶ፣ የጦር መሣሪያ ትግል ተወግዶ፣ በእኩልነትና በመስማማት ሰላማዊ የችግር አፈታት መንገድን ተከትላችሁ በውይይትና በጥበብ ልዩነቶችን በመፍታት የተሟላ ሀገራዊ ሰላም እንዲሰፍን ታደርጉ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ከአደራ ጭምር ሐዋርያዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
በመጨረሻም የሀገራችን ኢትዮጵያና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሕልውና ስለማይነጣጠሉ፣ ሀገራችን በሉአላዊነቷ እንድትቀጥል የቤተ ክርስቲያናችን የአንድነት መዋቅሯ የበለጠ ተጠናክሮ፣ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮዋ ሰፍቶ፣ ለትውልድ እንድትሻገር፣ ሕዝባችን ደኅንነቱና ሰላሙ ተጠብቆ እንዲኖር ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን መምህራን፣ ካህናትና ሕዝባውያን፣ መነኰሳትና መነኰሳይያት በሙሉ በፍቅርና በአንድነት ዘወትር በመጸለይ ዘመኑ ከደረሰበት አሠራርና ጥበብ በላቀ ሁኔታ ከፍ ብለን ትውልዱን ለመዋጀት እንድንችል የበኩላችሁን እንድትወጡ በማሳሰብ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ፎቶ ከኢኦተቤክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

❤10👍2
ማኅበረ ቅዱሳን ከሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን፣ በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ በድርቅና በበረዶ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረገ
ጥቅምት ፲፯/፳፻፲፰ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውስ በተለያዩ ወገኖች ላይ እያስከተለ ያለውን ችግር ለማቅለል ባለፉት 7 ተከታታይ ዓመታት ሁለገብ ማኅበራዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህም በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ባጋጠመው ድርቅና በረዶ ከ22,221 በላይ ነዋሪዎች ከ7,570 ሄክታር በላይ ሰብል እንደወደመባቸው መረጃዎች ያሳያሉ። ስለሆነም ማኅበረ ቅዱሳን ከጥቅምት 11 እስከ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በቦታው በመገኘት ሰብላቸው ለወደመባቸው በድብቆ ቀበሌ ለሚገኙ 613 ለሚሆኑ ወገኖች 136 ኩንታል አስቸኳይ የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።
የዚህ ማኅበራዊ ቀውስ ተጎጅ የሆኑት ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም የ4ቱ ጉባኤያት የመጽሐፍት ትርጓሜ ቤት እና ዋልድቢት ቅድስት ማርያም ወአባ ሳሙኤል አንድነት ገዳምም የድጋፉ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ተደርጓል።
ለዚህ ድጋፍ በጠቅላላው 1,572,074 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ሰባ አራት) ብር ወጭ የተደረገ ሲሆን በድጋፍ ርክክብ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካን፣ የማኅበረ ቅዱሳን ላሊበላ ወረዳ ማእከል ተወካዮች፣ የወረዳው የግብርና ባለሙያዎችና የድጋፉ ተጠቃሚዎች በመገኘት ድጋፉን ለተጎጅዎች አስረክበዋል።

❤9🕊1
ድጋፉ የተደረገው የማኅበራዊ ፕሮጀክቶች በኩር አጋር ከሆነው ከሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን በተመሳሳይ ሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ማኅበራዊ ቀውሶች ለተጎዱና በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች ተደጋጋሚ ፣ ድጋፍ እንድናደርግ ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ የሚገኝ ቀዳሚው አጋራችን በመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ከፍ ያለ ምሥጋናውን ያቀርባል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ባለፈው 1 ዓመት ብቻ በማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ከ14 በላይ ተመሳሳይ ማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ አድርጓል። መሰል የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በ2018 ዓ.ም ለአዳዲስ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ መርሐ ግብር የእንጅባራ ማእከል የግቢ ጉባኤ አገልግሎት ማስተባበርያ አከናወነ
ጥቅምት ፲፰/፳፻፲፰ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን እንጅባራ ማእከል የግቢ ጉባኤ አገልግሎት ማስተባበርያ በ2018 ዓ.ም ለአዳዲስ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ መርሐ ግብር ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም አከናወኗል።
በመርሐ ግብሩ "ለነፃነት ተጠርታችኋል" (ገላ ፭፥፲፫) በሚል ርእስ በእንጅባራ ማእከል የግቢ ጉባኤ አስተባባሪ የሆኑት የኔታ ፍሬው ስሜነህ ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን ወረብ ፣ በኦሮምኛ ቋንቋ መዝሙር ፣ ቅኔና ሌሎች መርሐ ግብሮች መካሄዱ ተገልጿል።
በመጨረሻም በማእከሉ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመምህር መንግሥቱ ይርጋ የማኅበሩ መልእክት ቀርቧል።

🙏8❤4👍4
ለመመዝገብ እና የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ👉👉https://forms.gle/jkjeZnNBunzKHvp69 ማሳሰቢያ መጠይቆችን ሞልተው ሲጨርሱ Submit የሚለዉን መጫንዎን እንዳይረሱ
በሃሎ መምህር ፕላትፎርም ከ300 በላይ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠታቸው ተገለጸ
ጥቅምት ፲፱/፳፻፲፰ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ለሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ምላሽ ማግኘት በሚቻልበት በሃሎ መምህር ፕላትፎርም ከምእመናን ለተነሡ ከ300 በላይ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠታቸው ተገልጿል።
በሃሎ መምህር ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ጠይቀው ምላሽ እንዲያገኙ ምእመናን በሚመቻቸው ጊዜና ቦታ ሁሉ አገልግሎቱን ማግኘት የሚያስችል የቴክኖሎጂ መንገድ በመሆኑ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም ተጠቁሟል።
በማኅበረ ቅዱሳን የዋናው ማእከል መደበኛ መምህር ሊቀ ልሳናት ቀሲስ ክፍያለው ጥላሁን እንደገለጹት ከሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች በርካታ የስልክ ጥሪዎች የሚመጡ ሲሆን እንደየ አካባቢያቸው ጥያቄያቸውም የተለያየ መሆኑን ተናግረዋል።
ለሚነሡት ጥያቄዎችም ምላሽ እንደሚሰጥ የገለጹት ሊቀ ልሳናት ቀሲስ ክፍያለው ጥላሁን አክለውም ምእመኑ ከመጻሕፍት፣ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ከማኅበራት፣ ከመምህራን ተገናኝተው የበለጠ መማር፣ ማወቅ እንዲችሉ መንገድ የምናሳይበትም ነው ብለዋል።
በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት የስብከተ ወንጌልና ዕቅበተ እምነት ዋና ክፍል ምክትል ኃላፊ ዲያቆን ዐቢይ ጌታሁን በበኩላቸው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት የጠፉትን በመመለስ፣ ያላመኑትን በማሳመንንና ያመኑትን በማጽናት የስብከተ ወንጌል ተልእኮን ከግብ ለማድረስ አንደኛው መሣሪያ የሃሎ መምህር ፕላትፎርም ነው በማለት ገልጸዋል።
የስልክ አገልግሎቶቱ ከተጀመረ ስምንት ወር እንደሆነው አያይዘው የገለጹት ዲያቆን ዐቢይ ጌታሁን አክለውም ፕላትፎርሙን በመጠቀም ለተነሡ በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱንም አብራርተዋል።

በመጨረሻም ምክትል ኃላፊው የእምነቱ ተከታይ የሆነውም ያልሆነውም ሁሉም ምእመን በተዘጋጀላቸው የስልክ ፕላትፎርም ሃማኖታዊ ጥያቄዎችን ዘወትር ከሰኞ እስከ ዐርብ ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ደውለው በመጠየቅ ምላሽ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ገልጸዋል።
👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤9