Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እውነትሽን እኮ ነው የኔ እናት😭

@mahtot
እንደሚባለው ከሆነ በ6ኛው እና በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እዚ አረብ ምድር እና ሰሜን አፍሪካ አከባቢ፣ ሰዎች ሴት ልጅ ስትወለድላቸው አንዳንዱ በቢላ ይገድሏታል፤ በብዛት ግን በህይወት ይቀብሯታል። አንዳንዶች ገና እንደተወለደች ሲገድሉ፣ ቸር የሆኑት እስከተወሰነ እንድታድግ ይፈቅዱላት ነበር ይባላል። ይሄ ሁሉ ሴት ልጅ ከተወለደች ውርደት/disgraceful ነው ብለው ስለሚያስቡ ነበር።

አንድ እንዲ ልጅ የተወለደለት ሰው ተመሳሳይ ዕጣ ደረሰው- ሴት ልጅ ነበረች ከእናትየው ማሕፀን የወጣችው። እና በርህራሄም ይሁን በሌላ ምክንያት ትንሽ ከፍ ትላለች። ነገር ግን የማይቀረው ቀን ሲመጣ እንጠልጥሎ ይወስዳትና፤ ጉድጓድ ይቆፍርላታል። ጉድጓድ ሲቆፍር ጢሙ በአፈር ይቆሽሻል፣ እና ልጁ ከስሩ እየሄደች ከጹሙ ላይ አፈሩን ታብስለት እና ትለቅምለት ነበር። ከዛ ጉድጓዱን ቆፍሮ ሲጨርስ፣ ወደ ጉድጓዱ ወረወራትና፤ አፈሩን መልሶ ደምድሞ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

ህይወት እንዲህ ስትጨክንብህስ?

@mahtot
2025/07/05 20:25:50
Back to Top
HTML Embed Code: