ማሕቶት
❉❉❉ አራቱ የቡና ላይ ፈላስፋዎች ❉❉❉
.....on 𝚏𝚎𝚎𝚕𝚒𝚗𝚐𝚜, 𝚝𝚒𝚖𝚎 𝚊𝚗𝚍 𝚋𝚎𝚝𝚛𝚊𝚢𝚊𝚕
የጃዝ ሙዚቃ ቀሰስ ብሎ በኮፊ ባሩ እየፈሰሰ ነው። ሙዚቃው የሆነ ትዝታ ትዝታ ይላል- የምታውቁት 'ሚመስላችሁ ነገር ግን የማታውቁት አይነት። ከውጪ ካፍያው የቤቱን የመስታወት ግድግዳ አልፎ አልፎ ሿ ያደርገዋል። የመንገዱ ላይ መብራት ቀኑን ትኩስ ምሽት አስመስሎታል። ከውስጥ ሲኒ ሲጋጭ፣ ቡና ሲማሰል፣ አልፎ አልፎ የቡና ማሽኑ ሲጮህ ይሰማል።
ከፊት ለፊት ለባሩ ቡና ምትቀምም የቡና ኬሚስት አለች- ደንበኛው ነች። እሱ ባንኮኒው ላይ ተቀምጦ አልፎ አልፎ ጥግ ላይ የተሰቀለውን ቲቪ፣ አልፎ አልፎ እሷን ይመለከታል። ቡናውን ትክ ብሎ ካየ በኋላ አንስቶ ወደ አፍንጫው አስጠግቶ ከማገው በኋላ ፉት አለው።
"ይቀዘቅዛል ዛሬ አየሩ" አላት። በፎጣ ንኬሎችን ስታደራርቅ ለነበረችው ባሪስታ ወዳጁ።
"ትዳር ያዝ፣ ወይ ጥሩ ይሆንና ይሞቅሃል ካልሆነ በጭቅጭቅ ቢያንስ ውስጥህ ይሞቃል" ሁለቱም ፈገግ አሉ። ከወደበሩ ባለትዳር ጓደኞቹ ወደ ባሩ ገቡ። ሞቅ ያለ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ዝናብ ያራሰ ኮታቸውን እያወለቁ አሌክስ በቀኙ፣ ሚስቱ በግራው ተቀመጠች።
"ለብርድክ ፍቱን መፍትሄ" አለችው ባሪስታዋ "እንኳን መሃል አደረጋችሁት" ብላ ጨምራ ወደ ባለትዳሮቹ አየች።
እዚህ አያት ሬጀንሲ ሆቴል ነው ሁሉም የተዋወቁት። በግምት ሁለት አመት ያልፋል። በሳምንት 3 ወይ 4 ቀን ኮፊ ባር ውስጥ እየተገናኙ ክፉውንም ደጉንም ይጨዋወታሉ። አሌክስ እና ማያ ከመጋባታቸው በፊት ለሶስት በጓደኝነት አሳልፈዋል። አሁን የቀረው ልዋም ነው- ሲቀላለዱ " አንተ እና ሚሚ (ባሪስታዋ) ብትጋቡ ምርጥ ቡና በነጻ እንጠጣ ነበር" ይላሉ። ምናልባት ሁሌ ከእነሱ ቀደም ብሎ ሚመጣው ለዚ ይሆናል።
ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ከፍ ከፍ ባለ ጎልቦ የተለያየ ቡና በአልኮሆል ቀላቅለው የጦፈ ወሬ ውስጥ ገብተዋል።
ልዋም ከጭቅጭቁ መለስ አለና ሚሚ የሰራችለትን የቡና አረፋ ገለል ገለል አድርጎ " አንዳንዴ የሆነ ህመምን አልፈህ ራሱ፣ ህመሙ ከተረሳ በኋላ- የድሮው ሰው እንዳልሆንክ ያህል ተሰምቶህ ያ'ቃል?" ብሎ ጠየቀ። ማንን እንደጠየቀ እንጃ እንጂ።
ማያ ወደ አፏ እየሰደደች የነበረውን ንኬል መልሳ "የድሮው ሰው ስላልሆንክ ይሆናላ!" መለሰች ቀለል አድርጋ "ከባድ ጊዜዎችን ብታልፍ እና ጉዳቶችህ ቢሻሩ እንኳን ከድሮው ጋር አንድ አትሆንም" ብላ ጨመረች።
አሌክስ የሚስቱን አስተያየት በመገረም ሰምቶ እንደጨረሰ ለመቃወም ያህል "ትዝታ አደገኛ ነው ወዳጄ፣ ሁላ ማን እንደሆነ የማታውቀው በፍጥረት አለም ውስጥ የሌለን ሰው እንኳ ያስናፍቅሃል።"
ማያ ምኗ የዋዛ ነው "ወይም ደግሞ" አለች " ያለና የሄደብህን ሰው ያስናፍቅሃል። ያ ሰው ናፍቆህ ታዝናለህ።"
ሚሚ የተወሰነውን በጨረፍታ ሰምታ እየሳቀች " ለሁለት ደቂቃ ብሄፍድባችሁ ናፈቅሽን ምናምን ማለት ጀመራችሁ አይደል? ቂ ቂ" ሁሉንም ፈገግ ታስደርጋቸዋለች። ሚሚ ምንም ያህል ከባድ የሆነን ነገር ወደ ቀልድ የመለወጥ ምትሃታዊ ሃይል አላት- ለቅሶ ቤትን እንኳን። ነፍሷ አይማርም!
ትንሽ ዝምምም...ከወደ ውጪ ካፊያው ስላቆመ ሰዎች ወደ ባሩ በብዛት መምጣት ጀምረዋል። ከሚገቡት ሰዎች ሁሉ የቫለንታይንስ ቀይ ልብስ ለብሰው የሚገቡ ሁለት ጥንዶች ቀልባቸውን ሳቡት። ልዋም ቀሰስ አድርጎ ወደ ሚሚ ሲዞር አይን ለአይን ተጋጩ። በዚህ መኃል አሌክስ:
" ታውቃለህ- ሚስት ለሌለው ክረምቱ ቀዝቃዛ ነው። ይበልጥ ደግሞ የሚቀዘቅዘው ሞቅ ያለ ትዝታ ለሌላቸው ነው።" ልዋምን መናገሩ ነው።
ማያ " ይመስለኛል ይበልጥ ሚቀዘውዘውማ ሙቅ ትዝታ ኖሮህ፣ ያ ሰው ግን ሳይኖርህ ሲቀር ይመስለኛል። " አለችው። ማያ ተቃውሞውን ተያይዛዋለች። ለልዋም የተሰነዘረው ሽንቆጣ መልሶ ራሱ ላይ ወደቀ።
"ድንቄም ተናግረክ ሞትክ" ጨመረችለት ሚሚ።
"ስለዚህ የተለያየ ብርድ ነው ያለው ነው 'ምትሉት ባለትዳሮች?" ሁለቱም ራሳቸውን ነቀነቁ።
ማያ መልሳ "ለዛ ነው አየህ ሰዎች የሆነ ያላቸው ነገር ላይ ችክ ሚሉት ደብዳቤ በለው፣ ፎቶ፣ ስዕል፣ ቦታ፣ ብቻ የሆነ ነገር። ህመማቸውን ማለፍ ስላቃታቸው አይደለም ግን አንዴ እኔም ሞቅ ያለ ፍቅር ነበረኝ ለማለት ነው። ማረጋገጫ።"
"እሱስ እውነት ብለሻል ውዷ ሚስቴ" ቡናውን ከጨለጠ በኋላ ወደ ሚሚ ንኬሉን ገፍቶ " አንዳንዴ ያ ማረጋገጫ ከዛ ሰው መሄድ በላይ ሲያምስ?"
ሃሳቦቻቸው ሳያቁት ተወሳስቦባቸው ግራ ተጋብተዋል። ከዛ መሃል ሚሚ አንዷ ናት። ቡናውን ለማፍላት ሄዳ ስትመጣ አዲስ ርዕስ ላይ ናቸው። በቀልድ አዋዝታ መልሳ ትቀላቀላለች-ከተቻለ።
ልዋም ወደ ውጪ ሲያይ ከቆየ በኋላ በጣቱ ባንኮኒውን መጠርጠር ያዘ። የአስቴር ዘፈን መሆን አለበት። "አንዳንዴ ያስቃል፣ ሰዎች ጊዜ ሁሉን ያክማል፣ ይሽራል ብለው ያስባሉ፤ነገር ግን ጊዜ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ነገሮችን ጭ...ው ማድረግ ነው። ዝም ያደርጋል ሁሉንም። ነገሮችን በጭራሽ አትረሳም። መርሳት የምትፈልገው ነገር ነው እንደውም ከምንም በላይ አብሮህ ያሚቆየው።"
ማያ ሳቅ ሳቅ አለች። ልዋም የሆነ ጊዜ እንዳለው ታውቃለች የሆነ ትዝታ በትዝታ የሚሆንበት። ወደ እሱ እና ወደ ሚሚ አቀያይራ እያየች "ፍቅር የሆነ ቅኔ አለው አይደል እ?" ጠየቀች። ማንን? "ንገሩኛ ምንድነው እንደውም ያ የሚሉ..." አሌክስ ወሬዋን ቁርጥ አድርጎ " የዛሬ አመት የሆነ ቀብር ላይ ሆኜ" በረጅሙ ተነፈሰና(ሁሉም እያዩት ነው) "ልጁን ብዙም አላውቀውም የሆነ ሁለተኛ የአጎቴ አጎት ልጅ ነገር ነው እና ሁላችንም አጅብ ብለን ስናለቅስ፣ ስናዝን የሆነ አለ አይደል? በሃዘን ውስጥ የሆነ እፎይታ ነገር፣ የሆነ ከውስጥ ሚቀል ነገር ነበረው። ምናልባትም አብረን ስላዘንን ይሁን እኔንጃ"
"ደባሪ" አለችው ሚሚ። "ምን በዚ ምሽት ቀብር ምናምን ትልብናለህ። እሱ ለራሱ ደብሮታል" ብላ ልዋምን መጥታ ጸጉሩን ነካካችው። ከመምጣታቸው በፊት ምን ያህል ከቤተሰቡ ጋር በውርስ እንደተጣላ እና ያለችው አንድ እህቱ በዘመዶቿ ክፋት ያውም የሞቱት ስጋ ሳይፈርስ ለውርስ ሲባሉ ማየት መቋቋም አቅቷት ራሷን እንዴት እንዳጠፋች ሲነግራት ነበር።
"ሚሚ ጸጉር መነካካት አብዝተሻል" ብለው ባል እና ሚስት ተሳሳቁ።
"ይልቅ እሁድ እኔ ቤት ነው ምንውለው እሺ? በጠዋት ኑ። ዶሮ ነው ምሰራላችሁ ለጾሙ መያዣ። ለልዋም ደግሞ የሚጣፍጥ ህብስት"
ይሄን ሲሰሙ እያሽሟጠጡ ተሳሳቁ። ሁሉም ሳቁን እየተከተሉ ፍርስ አሉ።
ማያ ለማውራት ተራዋን አሰፍስፋ ስትጠብቅ ቆይታ "ያው እንግዲ እንዲ ደስ ሚለውን እንደምንካፈል ሃዘናችንንም ስንካፈለው ቀላል ነው። 50 ሎሚ ምናምን ይሉ አይደለም" አለች።
"ሎሚ ሲበዛ መካካድ ይመጣል አትዪም። ክህደት ደግሞ ሰርስሮ የሚቆርጥ ቢላ ነው" አለ ልዋም ወደ ኋላ ደገፍ ብሎ። "አራት መሆናችን አሁን ጥሩ ነው። አሁን ወደ ሁለት እናሳድገዋለን ደግሞ ሂሂሂ"
"ቀልዱ እንዳለ ሆና" አለች ማያ "እውነት ነው የምልህ የሆነ ሰው ሲከዳህ፣ የሆነ ሁለቱንም እጆችህን የተቆረጥክ አይነት ስሜት ነው ያለው። ይቅር እንኳ ብትላቸው መልሰህ ማቀፍ አትችልም በቆራጣ እጅህ። በምንህ ታቅፋለህ?"
"ውይ በጌታ ስሜ ምኑን ነው ዛሬ ደግሞ ምታወሩት? መቆረጥ፣ መቀበር... " ሚሚ የሚል ድምጽ መጣ። ስለተጠራች ደስ ያላት ይመስላል፤ ቶሎ ብላ ሄደች። ስትሄድ ቀጠሉ።

ማያ ቡናዋን እያጣጣመች "እና ይቅርታ እኮ ይሄ ነው። የተሰበረ ሁሉንም ዳግም መገንባት አይጠበቅበትም ። ግን ቅድም ያላችሁትን ጭው ያለ ነገርን ለመሸከም ቀላል ያደርገዋል።
" ሚስቴ ጥያቄ ልጠይቅሽ" አሌክስ አንዳንዴ እንደ ህንድ አክተር ወይም እንደ ኢራናዊ ገጣሚ ሚስቱን በቅኔ ማውራት ይወዳል። ግጥም የሚገጥምላት ነው የሚመስለው። " እና ይቅርታ እንደዛ ከሆነ ለምንድነው ነገሮች ወደነበረበት ሳይመለሱ ሲቀሩ ሰዎች የሚደነቁት?"
ልዋም ቀበል አድርጎ "እሱማ ብዙ ሰዎች የህወት ኗሪ ሳይሆን ዝም ብሎ ታዳሚ ስለሆኑ ነዋ። የሆነ መስኮት ላይ ሆነው መንገዱን እያዩ ጉዞውን እንደሚያውቁ ሚያስቡ ስለሆነ ነው።"
ማያ ቅንድቧን አገለማምጣ "ታዲያ የሆነ እንደሆነስ?"
"ታዲያማ ጉዞው ምን አይነት ስሜት እንዳለው ቅንጣት ታህል የሚይውቁት ነገር የላቸውም። በነገርሽ ላይ ሃሳባችን ተመሳሳይ ነው ለምን ትዋወሚኛለሽ ? ሂሂሂ"
ትንሽ ዝም አሉ። ማያ የቀረችዋን ቡናዋን ጨለጠች። ልዋም ስልኩት አውጥቶ የሆነ ነገር ጎርጉሮ መልሶ ዘጋው። ከወደውጪ አንድ ትልቅ ሰውዬ ትንሽዬ ልጁን ሲጮህበት ሁሉም ዞረው ትክ ብለው አዩት። ዱላ ቀረው እንጂ ይሄ ትንሽ ልጅ እያለቀሰ እምባውን እየጠረገ ከፊት ከፊት ቀድሞ በህፍረት እየሮጠ ከባሩ ወጣ። አባትየው ተከተለው።
አሌክስ እንደዞሩ እንዲህ አለ " አስበህ ታውቃለህ ብዙ ቤተሰቦች የራሳቸውን ህልም ልጆቻቸው ውሥጥ እንዴት እንደሚወሽቁ? ምጽ። የራሳቸውን ነገር እንደመከተል፣ ሸክማቸድን ለአንድ ፍሬ ህጻናት ያሸክማሉ። በ40 እና 50 አመት ያልቻሉትን፣ በ50 አመት ሙሉ ያላመጡትን ሃብት ካላመጣችሁ ብለው ልጆቻቸውን ማንነት ያሳጣሉ።"
ማያም "እነዚህ ልጆች ያንን ሸክም አይችሉትም። ካልቻሉት ደግሞ ይሰብራቸዋል፣ይጨፈልቃቸዋል። "
ልዋም የራሱን ቤተሰብ እያሰበ "ከዚህ የባሰው ደግሞ፣ አንድ ቀን ይሄ አባት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ፣ የሱን ህይወት ሌላ ሰው እንዲኖርለት ሲጠብቅ ኖሮ በከንቱ እንዳለፈ ይረዳል። ከንቱ"
ለጥቂት ሰከንዶች ሁሉም ሃሳብ የያዘው ይመስላል። ካፌው ከምሽቱ ድባብ ጋር አሁን ዝም ነገር ብሏል። አሌክስ ከተንጠራራ በኋላ በሚስቱ ጎን ሄዶ ተቀምጦ እቅፍ ካደረጋት በኋላ "ብቻ እኔ በበኩሌ በህይወቴ ብዙ ጀብዱ የለኝ ይሆናል። ግን በእርግጠኝነት የምነግርህ: ጥሩ ጥሩ ሽንፈቶች አሉኝ" ብሎ ሚስቱን ነከሳት። ሽርደዳው ገብቷት በቀልድ ትከሻውን ጣ አደረገችው። ልዋም ቀልዳቸው ሙላ ኒስረዲንን ትዝ አስባለው። ያ ጎበዝ፣ ሁሌ ሚስቱን እንዳሾፈሻት እና እንዳጫወታት የኖረው የሱፊ ጀግና። " በርታ ጃል። ከዚህ በላይ ምን ሽንፈት አለ። ማለቴ ምን ድል አለ ሂሂሂ። እኔም ልሸነፍ መሰል"
ሚሚ ያለ ስራ ልብሷ ተመልሳ መጥታ ሁሉንም አየቻቸው።
" ምን ተፈጠረ" አሏት በደቦ።
"ሆዴን አመመኝ ትንሽ አልኳቸው። መሽቷል በቃ ሂጂ ተባልኩ። ሆዴን አሞኛል ትንሽ አትሸኘኝም ልዋሜ?"
"ኧረ እሸኝሻለሁ። በኋላ መንገድ ላይ ቢያምሽ የማን አለ ልል ነው ? በይ ነይ። ሂሳቡን ክፈሉ እንግዲህ" ብሏቸው ሲነሳ ሚሚ ዞራ እነ ማያን ጠቀሰቻቸው። እጇን ክንዱ ውስጥ ወሸቅ አድርጋ ወደ በሩ ሲራመዱ ማያ እና አሌክስ በአንድ ድምጽ
" መልካም ሽንፈት ጃል" አሉት።
እየሄዱ ሹክሹክታ በሚመስል ድምጽ እንዲህ ሲሉ ይሰማ ነበር
"የምን ሽንፈት ነው ደግሞ ምታወሩት?"
" ተያቸው ባክሽ ስለ ጦርነት እያወሩ። ማያወሩት የለ እንደው"
በሩን አልፈው በመብራት የደመቀውን መንገድ ተቀላቀሉ።
@mahtot

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንዲህ እንደምትሉት ቀላል ያ'ርግላችሁ...
መልካም የሴቶችም ቀን😎👳♀🧕👩🍳👩🌾💪
መልካም የሴቶችም ቀን😎👳♀🧕👩🍳👩🌾💪
ካርል ቮን ክላውስዊትዝ Hit them where it hurts ይላል። እና እንዴት ክፉ መሆን እንደምንችል ሲያወራ " በደንብ አድርገህ ሃይላቸው፣ ልባቸው ተጠራቅሞ የሚኖርበትን ፈልግ፣ እና ምናልባት አንድ ወይ ሁለት ነገር ይሆናል። ከቀናክ ደግሞ አንድ ብቻ ሆኖ ታገፕዋለህ። እሱን ስታገኘው፤ በማያዳግም መንገድ ስበረው" ይላል።
ይሄ center of gravity ከተመታ ሰው ምን ህይወት አለው? በቃ ያ ሰው ባዶ ነው የሚሆነው። ሰው አብዝቶ የሚወደው ነገር ካለ፤ ልቡ እዛ ውስጥ ይሆናል ይባል አይደለ? እና ያ ነገር ከተመታ ያበቃል። እና ይሄ ክፉ ሰውዬ እንዳለው ከሆነ፣ ምናልባት ያለን center of gravity አንድ ሆኖ ከተገኘ- ተመቸ ማለት አይደለ ታዲያ? ያ ሲመታ it hurts.

....for feminists in my channel
And regarding those sexual stereotypes: the other night I was in a situation with David [Sontag’s son David Rieff] when we went out to Vincennes University, where I was invited to attend a seminar, and then after the seminar, four people plus David and myself went out to have coffee. And it so happened that the four people from the seminar were all women. We sat down at the table, and one of the women said, in French, to David, “Oh, you poor guy, having to sit with five women!” And everybody laughed. And then I said to these women, who were all teachers at Vincennes, “Do you realize what you’re saying and what a low opinion you have of yourselves?” I mean, can you imagine a situation in which a woman would sit down with five men and a man would say, “Oh, you poor thing, you have to sit with five men and we don’t have another woman for you.” She’d be honored.
I wonder what David thought of that remark.
I’m sure that if he had been asked about it, he probably would have just said, What else is new? [laughing] But in fact I know that he was overwhelmed by those women’s lack of self-esteem, by the misogyny of women. And don’t forget that these were professional women who probably would have called themselves feminists, and yet what they were expressing was quite involuntary.
The one and only #susan sontag

❁❁❁❁❁ የቱ ይሻለናል ?
ሰሞኑን ስለተጋጋለው የሃይማኖት ጉዳይ ስናወራ ነበር። ሁላችንም በየቤታችን፣ በግልጽም በድብቅ፣ በየ ስራ ቦታችን አውርተናል። እኔም ከሰማህል(እዚው ቻናላችን ላይ ምናውቃት) ጋር ሳወራ ነበር። ያወራነውን ባልጽፈው ራስን መዋሸት ይሆንብኛል። ያው እንደምታውቁት ማስበውን፣ የምሰማውን፣ ጥሩ የምለውን አጋራችሁ አይደለ .. እንደዛ እዩት።
መጀመርያ ወሬው የተነሳው፣ ስራ ጨርሳ ከሆስፒታል(ለህይወቷ ስለሚያሰጋ የት እንደሆነ አልጠቅሰውም )አጠገብ ያለው ካፌ ቁጭ ብለን ነው። ፕሮፋይሏን 'እኔም ከእፎይ ጋር ነኝ' የሚል የእፎይን ፎቶ አድርጋ ሳይ "እንደው ከአንድ ዶክተር ይሄ ይጠበቃል፣ ዲሲፕሊን ነው?" ብዬ ቀልጄ ነው።
"እናሳ፣ አንተስ አይደለህም? እ?" ሳቅ ነገር ብላ። ይሄን ብላኝ ቀድሞ የጀመርነው ወሬ ውስጥ ገባችና እሱን አውርታ፣ ስራ ቦታ ያጋጠማትን አንድ ችኮ(እሷ እንዳለችው) አምታ ጨርሳ ተመለሰችና:
"አንተስ ሊብራል፣ ሰኪውላር ነኝ እያልክ ነው? ዳር ቆም ቆም ልትል?" ተደላድላ ተቀመጠች ለወሬው።
"ኧረ ምን በወጣኝ። አልሰማሽም ከሁለቱም አይደለሁም የሚል በሁለት ጥይት እንደሚሞት?"
ከት ብላ ሳቀችብኝና አየችኝ። "ወደህ አይደለማ ከእፎይ ጎን የሆንከው?"
"ምን ልዩነት አለው? ምን ጊዜም ቢሆን ከቤተክርስቲያን ጎን ነኝ።"
"እንዴ እንዴ ምን ማለት ነው? በል ለያያቸው። ይሄ ልጅ የቤተክርስትያን ልጅ እንጂ ቤተክርስትያን አይደለም።"
"አሁን እኮ ችግሩ አንቺ 'ከእፎይ ጎን ነኝ' ስትዪ እና እኔ 'ከእፎይ ጎን ነኝ' ስል ይለያያል። እኔ ምንም ከእፎይ ጎን ብሆን እፎይን ሰደብሽው ብዬ አልቀጠቅጥሽም"
"ሂድዛ...እኔስ እወግርሃለው?"
"ያለ ጥያቄ!" ተቀላልደን ሳቅንና ለጥቂት ሰከንድ በዝምታ ተቀመጥን። የሆነ ነገር እንዳስታወሰ ሰው ስልኳን አወጣችና ከፍ ዝቅ አድርጋ የሆኑ ቪድዮዎች አሳየችኝ። አንዳንዱ ስድብ፣ ዛቻ፣ የዛሬ አስር አመት የተወራ ወሬ፣ ህጻናት በአንድ ላይ ሆነው መፈክር ሲያሰሙ፣ ታዋቂ ሰዎች መልዕክት ሲያስተላልፉ ምናምን አሳየችኝ።
"አሁን እኮ ችግሩ ምን መሰለህ፣ ይሄ ሁሉ ነገር ከሁለቱም 'side' ካለ አማኝ ከተሰነዘረ የቱ የቱን ይካሳል? እኔ እፎይን እወደዋለሁ። ማንም ሰው እንዲነካው አልፈልግም። ልክ እንደሱ ሲሳደቡ የነበሩ የሉም?"
"አሁን ሰዉ ምን ቢደረግ ነው ደስ ሚለው? ደሞስ እፎይን እወደዋለው ስትዪ፣ ከመቼ ጀምሮ ነው ሃይማኖት ላይ 'interested' የሆንሽው ?"
"ብዙ ማታውቀው 'side' አለኝ እኮ" ምላሷን አውጥቷ መጎረሯን ካሳወቀችኝ በኋላ " ያው በህግ ተይዞ ቢታሰር ቢቀጣ የሚረግብ ይመስለኛል"
"ግን እኮ ስታስቢው ሰሚ፣ ለምሳሌ ህጉ የሚፈልጉትን ላይሰጣቸው ይችላል። ለምሳሌ አስቢው ይሄ ልጅ በህግ ታይቶ 'ነጻ ነው ምንም አላደረገም' ቢባልስ? ምን እንደሚሉ ታውቂያለሽ? ህጉ ራሱ ችግር አለበት ወይ ዳኛው በመላ ተጭበርብሯል ነው የሚባለው። እኛ እንፍረድ ነው የሚሉት።"
"ሊሆን ይችላል። ግን ደግሞ ማንም አያስረውም። ምንም አላጠፋም። ለምን ያስሩታል?"
"አሃ አንቺን ማን ፈራጅ አደረገሽ?"
"ቆይ አሁን እኛ ሃገር የጥላቻ ንግግር ህጉ ምን ያህል ይተገበራል? እና መስመሩስ 'well defined[የተብራራ]' ነው? እና ደግሞ በዚህ አይነት ይሄ ልጅ ታስሮ -ሌላው ቢቀር ህጉን 'fair[የማያዳላ]' ያደርገዋል? ወይስ እሱ አሁን ስለተናገር እነ እገሌ የዛሬ አመት ስለተናገሩ የሱ መቀጣት ልክ ይሆናል?"
"እኔንጄ እኔ ምንም ማውቀው ነገር የለም። ሲጀመር የ'hate speech' ህግ አለን እንዴ?"
"ንገረኝ እንጂ ወሬውን አንስተኸው አይደለ?"
"እኔንጃ እውነት። አሁን ለምሳሌ crusade (የመስቀል ጦርነት በሙስሊሞች እና በክርስትያኖች መሃል ተደርጎ ቢያንስ 300 አመት ዘልቋል) አብቅቷል አይደለ? ማለትም የዛሬ 700 አመት ነበር አይደለ የተደረገው?"
"አዎ ወደ 400 ምናምን?"
"አታቋርጪኝ 'ሪቶሪክ' እኮ ነው🙄"
"ራስህ አይደለህ፤ እሺ ቀጥል።"
"ብቻ አሁን ላይ ስለ crusader ስናነብ ብዙ ሌላ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የዘር አጀንዳ እንዳለው እናውቃለን። ሌላውን ተይው ባለፈው የሰጠሺኝ ያ መጽሃፍ (Bullies and Saints: an honest look at the..crusade. by John Dickson.)ላይ እንዴት ሲስተማቲካሊ financial system እንደዘረጉ፣ ሰዎች ይገደሉ እና ይደፈሩ እንደነበር ምናምን አንብበናል መቼስ። እና ዛሬ ላይ ምንም ሊመስል ይችላል ግን ነገ ሲታይ ግን ብዙ ድብቅ አጀንዳ እንደነበረ ትረጃለሽ።"
"አ...ዎ" አለች በረጅሙ። አገኘሁክ በሚመስል መንገድ "እሱን ነው ምልክ አሁን ይሄ ነገር ድብቅ ሌላ ሴራ ቢኖረውስ?"
"ሊኖረው ይችላል እኮ። የሚያሳዝንሽ እኮ አብላጫው ምእመን ምንም አያውቅም። ያንቺ አከራይ አሁን ሙስሊም ናት አይደል?"
"አዎ"
"ስለ እፎይ ታውቃለች አሁን?"
"አዋ! ድብን አድርጋ። ባነሳባት ይቀጥቀጥ ነው የምትለው።"
"ወሬ አታቆርፍጂ። ያንቺ አከራይ ቲክታክ ስለምትጠቀም ነው። እሺ ግን እኛ ጊቢ ለምሳሌ 3 የሙስሊም ቤተሰብ አለ። ምንም ስለዚህ ነገር የሚያውቁት ነገር የለም። እህቴ እፎይ ምናምን ስትል ይሄ እፎይ ምንድነው ስትል ነበር። ታዲያ አሁን እኔ እፎይ ተነካ ብዬ እዚ ምንም የማያውቀው ሙስሊምን ልጥላ? ልጣላ?"
"ማን ተጣላ። ከእፎይ ጎን ቁም ነው የተባልከው።"
"እንዴት ነው መቆም ቆይ? ምን ማድረግ ነው ያለብኝ? ልጠይሽ እስኪ 'let's say' አንቺ አሁን አንድ ሙስሊም ሆኖ እፎይን የሚጠላ ታካሚ ቢመጣ አታክሚውም? "
"አክመዋለው እንጂ። ምን አገናኘው?"
" (ኤግዛክትሊ) እሱን ነው የምልሽ። ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ሁሉም ጸብና ጡዘት ያለው አየር ላይ ነው። የቲክቶክ አለም ላይ። እኔ ማንንም ምመክረው 'ቲክቶክ ላይ ለተነሳ ጸብ፣ ሲያምህ ሾርባህ የሚያመጣልህን ምስኪን ጎረቤትህን አታስቀይም' የሚል ነው።"
"ቲ በናትህ ምንም ማይገናኝ ነገር ነው የምታወራው። ሲቀጥል በዚህ አይነት አንተ ምኑን ክርስትያን ነህ ለእፎይ ካልቆምክ?"
"እኮ ምን ላድርግ ነው የምልሽ እኮ? አንቺ ሙስሊሙን ካከምሽ፣እፎይን ለሚጠላ መድሃኒት ከጻፍሽለት እኔ ስራዬ ቦታ ሚመጣውን በድንጋይ እንዳባርር ነው ሃሳብሽ?"
"አይ በህግ እንዲቀጡ ቢያንስ መጣር አለብህ።" አለችኝና የሆነ ሽንፈቷን በምላሷ ምትቀምስ ይመስል ምላሷን ደጋግማ ላንቃዋ ላይ አዞረች።
"በነገርህ ላይ crusade ያልከው እና ይሄ ፈጽሞ የተለያየ ነው።"
(እንዴት)
"አሁን ላይ ማንም ማንንም የመናገር ሞራል የለውም። ሁሉም ለራሱ የማይዋሽ ቢሆን ኖሮ የየራሱን ልጅ ወስዶ መክሮ፣ ገስጾ ለወደፊት እንዳይደገም ማስገንዘብ ነው የነበረበት። አንድ የምስማማልክ ነገር ቢኖር፣ ጸቡ ያለው እውነትም ክላውዱ(ሶሻል ሚዲያው) ላይ ነው። ኮሜንቱ ላይ እኮ የሚወራው ጩቤ እና ቆንጭራ ይዤ እንዲ ነው ማደርግህ ነው። እዛ የሚወራው ልጆቹ ከተናገሩት የባሰ ለጆሮ የሚዘገንን ነው። የማመሰግነው መሬት ላይ ሁሉም እስካሁን ተከባብሮ መቀመጡን ነው። ሆነም ቀረ እፎይን ማንም አይነካውም።"
ይሄን እያወራች የጠጣነውን የለውዝ ቂቤ ሂሳብ ከፍላ ወጣንና ወደታች ወደ ኢትዮ ኩባ ፓርክ መውረድ ያዝን።
"አንተ ግን መንፈሳዊ መጻህፍት ላይ እንዴት ነህ? እኔ በቃ ይሄ አናቶሚ፣ ኦፕታልሞሎጂ፣ ናርኮሌፕሲ እያነበብኩ ድንዝዝ ብያለው።"

"እንደዚህ እንደምታዪኝ አይምሰልሽ። ሃ..ሃ"
"የማታውቂው ሳይድ አለኝ እያልክ ነው?"
"ምን ጥያቄ። ላንቺ ብቻ ማን ሰጠሽ።"
"ቁም ነገር ግን እንዴት ነው? 'I know you're interested in Christianity' ምናምን። የሌላውን ማንበብም ግድ ይላል። መመርመር ምናምን" አዲሱ ፓርካችን ዳር ቁጭ እንዳልን፤ሁሌ ሳንቡሳ የምታመጣልን ሴትዪ 2 ሳንቡሳ ይዛልን ከች አለች።
"ባይዘዌ ዱላ ካልተመዘዘብኝ በደንብ አድርጌ ስለ ሃይማኖቴ መልስ መስጠት እችላለው። ማን ያውቃል፣ ያውቃሉ ከሚባሉት ራሱ የበለጠ ጂኒየስ እንሆን ይሆናል።" ሁለታችንም ድክም ብለን ሳቅን።ሳንቡሳ ያመጣችልን ሴትዪም አብራን ሳቀች።
"የኔ ጂኒየስ ምን ይሳንሻል። ቀጥቅጠውሽ ስትመጪ ብዙ ደም እንዳይፈስሽ እዚው አከባቢ ተዘዋወሪ። ያ ማይወድህ ፖስተር ነው አንተንማ የሚቀጠቅጥህ።"
"ግን ሰሚ- አሁን ለምሳሌ ካንቺ ጋር ያለኝን ልዩነት ለማሳየት ግዴት በሰው ፊት የሚወራውንም፣ የማይወራውን እያወጣሁ ማውራት አለብኝ ብለሽ ታስቢያለሽ?"
" No ለምን"
"እኔንጃ ለምሳሌ ሙስሊምን እና ክርስትያንን የሚለያየው እኮ ቅድስቲቷ ከተማ የት ናት ሳይሆን ሌላ መሰረታዊ 'ዶግማቲክ' ኢሹ አለ። ለምሳሌ 'ኢየሱስ ተሰቅሏል አልተሰቀለም?' ይሄን ብቻ መመለስ እኮ በቃ የሰውን እምነት መወሰን ይችላል። ግዴታ መነዋወር ላይኖርብሽ ይችላል። አይ አይበቃም ካልሽ ምናልባትም ሰው ማያጋጭ ነገር ነገር ግን ዶግማቲክ የሆነ ጥያቄ አይጠፋም፣ ለምሳሌ...እምምም ብቻ የሆኑ ነገሮች አይጠፉም። "
"የማውራት ነጻነትስ እ? የፈለግነውን ማውራት ማነው ሚከለክለን? የፈለግኩትን አንስቼ ማውራር እችላለው እኮ!"
ኮስተር ስልባት መልሳ ተኮሳተረች "nooo አትችዪም! እንዲ የሚባል ነገር ከየት ነው ያመጣሽው? ሲጀምር ይቅርታ አድርጊልኝና በክርስትናም ራሱ ጥያቄ ስትመልሱ በትህትና እባ በፍርሃት ይሁን (1ጴጥ 3-15)ነው የተባለው። የሚያከብረውን ነገር እየሰደብሽለት የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅር እይ ብትይው ውሸት ነው። ፍቅር አይሳደብማ። of course የፈለግሽውን ቲክቶክ ላይ ሆነሽ ልትናገሪ ትችያለሽ ግን ምን ጥቅም አለው? አልያዝም ብለሽ። ፈጣሪም አይወደው፣ ሰውም ይጋደላል። ልጅ እያለው የእነ ዶክተር ዛኪርን ክርክር አይቼ 'ምን አለ እኛም ሃገር እንዲ ቢኖር' እል ነበር። አየሽ እሱ አለመኖሩ ነው የጎዳን። ሲጀመር በአካል ሆኖ ቢሆን ሰው ለሚናገረው ነገር ይጠነቀቅ ነበር ክርስትያኑም ሙስሊሙም። anyways ይመስለኛል።"
"በለው" ብላ የለበጣ አጨበጨበች። "አምጣ ስልክህን አሁን፣ ፕሮፋይልክን ልቀይርልህ።"
"አዲሱ ቢዝነስሽን ልታስተዋውቂ ነው"😂😂
ተነሳንና እንደ ባለፈው ወደ ታች ወረድን።
ይሄን ይመስል ነበር ከእሷ ጋር ያወራነው። እና ምናልባት ይሄ ቻናል ኮሜንት ሴክሽን ቢኖረው አንዳንዱ ያደንቅ አንዳንዱ ይሳደብ ነበር። እንኳንም አልኖረው። ሁሌ ሪያክት ከማድረግ አንብቦ ወይ አይቶ ወደ ውስጥ reflect ማድረግ። ነገሩን ለሰኮንዶች ማሰላሰል ጥሩ ነው። ሰማህል " ለምን ግን ደሃ ሃገር ላይ እንዲህ የሃማኖት ጸብ በዛ?" ብዬ ስጠይቃት፣ እንዲህ ብላ ነበር "ምንአልባትም ያለን ብቸኛ ሃብት እሱ ይሆናላ።" እውነቷን ነው። ግን ታዲያ ጸቡ እርስ በእርስ ነው ወይስ ይሄ ያለንን ነገር ሊቀማን ከመጣ አካል ጋር? ከዘመናዊነት፣ ከሰይጣናዊነት፣ ከፖለቲካ ጋር፣ ሃይማኖታችንን በስልጣኔ መልክ ከሚቀሙን ጋር እንጂ እርስ በእርስ ተባልተን ምን ልንጠቀም?
ስስ ብልታችን ይሄ እንደሆነ ስለሚያውቁ ይሄ ጸብ ሲከሰት ያልነበሩ ተቆርቋሪዎች ካሉበት ይከሰቱና አምታተው የእለት ጉርሳችንን፣ መቀመጫችንን፣ ዕሴታችንን ይቀሙናል። ወገኔ ባቴ በል። በጦርነት እና ፍቅር ውስጥ ሁሉም ልክ ነው። ጸብ ከተጫረ በጥቅስ አይምሰልህ ምትተማመነው፣ በቀስት እና ጦር እንጂ። ጥቅሱ እና ተግሳጹ ይሻለናል።
#ሀሉም_ይከበር
እኔ እና ሰማህል ነበርን

--በሳምንት አንዲት ሴት ለማናውቀው አምላክ?!---
(አሌክስ አብርሃም)
እንደቀልድ ዓይናችን እያያ ከሦስትና አራት ሺ ዓመታት በፊት ወደነበረው የማያ ስልጣኔ ዘመን "ክፉ አምልኮ" ተመልሰናል። በዚያ ዘመን አንዲት ሴት ትመረጥና ራሷን መከላከል በማትችልበት ሁኔታ እጇ ተጠፍሮ መሰዊያው ላይ ትቀመጣለች። ትፈራለች፣ አድኑኝ ትላለች፣ ትንቀጠቀጣለች፣ ወላጆቿን፣ ዘመዶቿን፣ ያደገችበትን ህዝቧን፣ እነዛን አገርና ህዝብ ይጠብቃሉ ብላ የዘፈነችላቸውን ፈርጣማ ወታደሮች ትማፀናለች። ግን ማንም አያድናትም። "ዝም በይ አምላክ ይቆጣል እየሳቅሽ ሙች" ፣ ትባላለች። "የአምልኮ ስርዓቱን አትረብሽ" ትባላለች።
በለመደ አጋፋሪ ደም ስሯን በሹል ብረት ትወጋና ደሟ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ መሰውያው ላይ ይፈሳል። በስቃይ ስትወራጭ ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ ያለቅሳል፣ ሰበዓዊነት የተሰማው ሲቃ ይይዘዋል፣ በተቃራኒው አንዳንዱ ለተሰዋለት አምላክ ጥብቅና ይቆምና ሁሉም ዝም እንዲል ያዛል። ሌሎች እልልታና ውዳሴ ያቀርባሉ። ሲቆይ እንባውም እልልታውም አምልኮውም ያልቅና ድል ያለ ድግስ ተበልቶ ህዝቡ ይበተናል። ቀጣይ መስዋዕት ማናት? የእልል ባዮ፣ ወይም የአልቃሹ ወይም የሚሰዋለት አምላክ አገልጋይ ሴት ልጅ ልትሆን ትችላለች። ግን የመሰዊያው ቀን እስኪቃረብ ሁሉም ረስቶት ሲስቅ፣ ሲጫወት፣ ሲሰራ፣ ሲዘፍን ይከርማል። መስዋዕቱ የሚቀርብበት ምክንያት ብዙ ነው፣ ዝናብ ከጠፋ አንዲት ሴት ትሰዋለች፣ ጦርነት ከመጣ አምላካቸው ድል እንዲሰጣቸው ሌላ ሴት፣ ንጉሱ ወይም የንጉሱ ወንድ ልጅ ከታመመ እንዲድን ሌላ ሴት ትገደላለች...
ይሄው በዚህ ዓመት እኛም እንደአገር በአማካኝ በሳምንት አንድ ሴት "ለማናውቀው አምላክ" "በማይታወቁ አካላት" አጋፋሪነት ገብረናል። ተመልሳችሁ ቁጠሩ። በሳምንት አንዲት ሴት፣ ተደብድባለች፣ ተጠልፋለች፣ ተደፍራለች ፣ አልያም ተገድላለች። ጩኸትና የሶሻል ሚዲያ ሙሿችንም የአምልኮው አካል ከሆነ ቆየ። አናውቅም ነገ የማንኛችን ልጅ፣ እህት፣ እናት መሰዊያው ላይ እንደምትቀመጥ፣ መስዋዕቱ ወንድም ሊሆን ይችላል ደም ፆታ የለውም። በደል ጠንካራ መከታ የሚሆን መሀበረሰብ እስካልተፈጠረ ድረስ ደካሞች ላይ ሰይፏን እየመዘዘች ትቀጥላለች። ከድርጊት የተለየ ለቅሶም ይሁን ከንፈር መምጠጥ አምልኮውን ከማድመቅ ያለፈ ሚና አይኖረውም። የገነባነው የአስተሳሰብ መሠዊያው ካልፈረሰ ቀስ በቀስ ሰብዓዊነት ይፈርሳል።
✍alex_Abraham

✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
የ'ኔ ህይወት እና object permanence
So, ህጻን እያለን እናቶቻችን ይሄ 'አየሁሽ፣ ህምም አየሁሽ' እያሉ ያጫውቱን አልነበር? ይሄ ፊታቸውን ደብቀው-ከዛ ብቅ ሲሉ ምንስቀው ነገር የለም? እሱ ነገር ለምን እንደሚያስቀን ማወቅ ፈለጉና ሳይንቲስቶች አጠኑት።
ለካ ሕጻናት አእምሮአቸው ስለ ኦብጀክት ፐርማነንስ ምንም ሚያውቀው ነገር የለውም። ማለትም በነሱ ጥንጥዬ አእምሮ እንግዲ የሆነ እቃ ከተሸፈነ ወይ ከእይታ ከተሰወረ-የለም ማለት ነው። እና እናታችን ፊቷን ስትከልለው ፊቷ በቃ ከሕልውና የጠፋ ይመስለናል፣ ከዛ ግልጥ ስታደርገው የተመለሰ ወይ የተፈጠረ ይመስለናል እና በጣም ያስቀናል።
እና አሁን ላይ ስረዳ፣ አሁን ላይ ሲገባኝ- object permanenceን የሚረዳው የአእምሮዬ ክፍል ሙሉ ለሙሉ አልበሰለም። አሁንም ነገሮች ከፊቴ ከረሰወሩ፣ ህልውናቸውን መጠራጠር እጀምራለሁ። አእምሮዬ ገና አልተረዳም፣ ገና ነገሮች ቢሰወሩም-ለአይኔ ባይታዩም በነበራቸው ባህሪይ ህልውናቸው እንደሚቀጥል አያውቅም።
ለዛም ነው ሳላይሽ ከቀረሁ፣ በቃ ውስጤ ብክንክን 'ሚልው እና ላብድ የምደርሰው። ቢያንስ ልጅ እያለሁ ያስቀኝ ነበር፤ አሁን ግን አዝናለሁ። ስትመጪ ደስ የሚለኝን ያህል ነው ስትሄጂ የሚከፋኝ። ባላይሽም እንዳለሽ ማን ይንገረኝ🤷♂ ልክ አና እንዳለችው ነው(አና ካረኒና): አጠገቤ ስትሆኚ ምንም ችግር የለብኝም፣ ስትርቂ እና ከእይታዬ ስትሰወሪ ግን በቃ አላውቅበትም።
እና ወገኖቼ እንዲህ እንደ'ኔ የሚያደርጋችሁ ከሆነ- ሌላ አይደለም። እንዲሁ object permanence የሚባለውን በደንብ ስላላዳበርን ነው። የኛ ጥፋት አይደለም!

ዛሬ አሰብኩት! ምን ያህል አስቀያሚ የትምህርት ህይወት እንዳሳለፍን። ልጅ እያለሁ ስንተኛ ክፍል እንደሆነ ባላውቅም፤ ሁሉንም subject የሚያስተምረን አንድ ሰው ብቻ ነበር።
ምናልባት ችግሮች ሁሉ አእምሮአችን ውስጥ ብቻ እንጂ በእውነታው ሁሉም ሰላም የሚል ትውልድ የዳበረው ከዚህ አይነት የትምህርት style ይሆናል። እንዴት?
እንዴት ማለት ጥሩ። አሁን እነዚህን ሰብጀክቶች(የትምህርት አይነቶች ስንማር፣ በአንዴ 3 ክፍለ ጊዜ፣ ከዛ ሌላ 2፣ ከዛም በመጨሻ ሁለት እንማራለን። እስኪ የመጀመሪያዎቹን 3 ክፍለ ጊዜ አስቡት። ይሄ መምህር በተከታታይ 132 ደቂቃ( ድምር ከተሳሳትኩ በመምህሩ ምክንያት እንደሆነ ይታወቅ) ያለማቋረጥ ያስተምረናል። የትምህርት ክፍለጊዜው በአቦሰጥ(randomly) ስለሚደረደር አንዳንዴ የሰማይ እና የምድር ያህል የሚራራቁ ትምህርቶች በቅደም ተከተል ይመጣል። ለምሳሌ ግብረገብ-ከዛ ፊዚክስ- ከዛ ባይሎጂ ሊከታተሉ ይችላሉ። አሁን አንዱን እንኳን ከአንዱ አጣጥማለሁ ብንል እንኳን ማጣጣም ማንችላቸው ይሆናሉ።
ለምሳሌ አማርኛ ከዛ ኢንግሊሽ ከዛ ታሪክ ቢመጣ ከአማርኛ ተርጉመን ታሪክ መማር ብለን ለማጣጣም እንሞክራለን። ግን በቃ ሁሌ የሚጣጣም ሰብጀት አብሮ አይመጣም።
እና ይሄን አከታትለን ስንማር በሶስቱም መሃል ያለው እፎይታ ቦርድ ጠፍቶ ደብተር እንክናወጣ ነው። እሱም ደግሞ 'አሁን ቦርድ እናጥባ- በጋራ' ፣ አሁን ደፕተር እናውጣ' አንባልም በሆነ ቅጽበት ግብረገብ እየተማርክ ከዛ የሆነ ሰአት ራስህን velocity, mass, momentum ውስጥ ታገኘዋለህ። አስተማሪው አይለወጥም እረፍት የለም። እና ከአንተ ወይ ከተማሪው ምን ይጠበቃል? በቃ ነገሮችን በአእምሮው እንዲለዋውጥ። የሆነ ሰአት ፊዚክስ እያሰበ ያለ አእምሮ ከዛ በፍጥነት ስለ ባይሎጂ እንዲያስብ ይገደዳል።
አይምሮክ ውስጥ ምትሃት ነው የምትፈጥረው። የተለያዩ situation ለመፍጠር ትሞክራለህ። ለምሳሌ እንበልና አንድ ሰው ላርጎ የተበጠበጠ ገንዳ ውስጥ ቆይቶ ከዛ በፍጥነት በሴራሚክ የተወለወለ ረጅም ኮሪደር ላይ ሶምሶማ ግባ ቢባል ይሆናል? አይሆንም። ቢሆንም ብዙ ጥርስ መልቀም እና ብዙ መሰባበር ነው። እና በዚህ አይነት የአእምሮ ድሪሊንግ ወይም ማደንዘዝ ነው የተማርኩት በግሌ። እና አንድን ሃሳብ ጨርሼ ሳላሰላስል ወድያው ሌላ የሃሳብ ምህዋር ውስጥ እንድገባ ተደርጌ አድግኩ። ዛሬ ሃሳቤን በየደቂቃው ብቀይር። የሆነን ሃሳብ እስከ ጫፍ ማሰብ ባልችል የኔ ጥፋት ነው? የውሸት የአእምሮ ውስጥ scenario ወይም ጉዳየ ጉዳዮች ያለምክንያት ብፈጥር ይገርማል? አይገርምም!