ሰኔ ፳፪ /22/
በዚችም ዕለት ለመነኰሳት መጀመሪያቸው ለሆነ ለከበረ እንጦንስ ረድእ የነበረው የዋህ ጳውሎስ አረፈ። ይህም ጳውሎስ በረኸኛና እጅግ የዋህ ነበረ ደም ግባቷ ውብ ሥራዋ ግን ክፉ የሆነ ሚስት አገባ ከእርሱም ልጆችን ወለደች።
በአንዲትም ቀን ከእርሻው በተመለሰ ጊዜ ከሎሌው ጋራ ስታመነዝር አገኛት በአያቸውም ጊዜ ሣቀ ያንን ሎሌውንም ከልጆቿ ከቤቷና ከንብረቷ ጋራ ውሰዳት እኔ ምንም አላዝንም እግዚአብሔርም ወደ ፈቀደልኝ እሔዳለሁ አለው። ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አባ እንጦንስ ሒዶ የምንኵስና ልብስ ለበሰ የአባ እንጦንስንም ሥራ ተከተለ ። በደዌያትና በሰይጣናት ላይ ጸጋና ኃይል እስከተሰጠው ድረስ በጾምና በጸሎት ተጋደለ።
በአንዲት ዕለትም ጋኔን የያዘውን ሰው ያድነው ዘንድ ወደ አባ እንጦንስ አመጡ። አባ እንጦንስም ይፈውሰው ዘንድ ረድኡ ጳውሊን አዘዘው ጳውሊም ጋኔናሙን ሰው ወስዶ አባቴ እንጦንስ ውጣ ይልሃል አለው ሰይጣኑ ግን መውጣትን እምቢ አለ ። እርሱንም እንጦንስንም ተሳደበ። ጳውሊም ካልወጣህስ ለእንጦንስ እነግረዋለሁ እንደሚቀጣህም ታያለህ አለ።
ይህንንም ብሎ በቀትር ጊዜ ወጥቶ ፀሐይ በአጋለው ደንጊያ ላይ ቁሞ ይህ ጋኔን ያደረበት ሰው እስኪድን ድረስ ከዚህ አለት እንዳልወርድ እንዳልበላና እንዳልጠጣ ሕያው እግዚአብሔርን አለ በዚያንም ጊዜ ጋኔኑ ጮኸ በታላቅ ዘንዶ አምሳልም ከሰውዬው ላይ ወጥቶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ገባ። ይህም የዋህ ጳውሊ የሰዎችን ሥራ ሁሉ እያየ ስለ ኃጥአን ያለቅስ ነበር ስለ እነርሱም ይማልድ ነበር። በመልካም እርጅናም በሰላም አረፈ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር

ፈተና ነው
በአፍ ያመኑትን ሃይማኖት በሥራ መካድ ፣ የመሰከሩለትን እውነት መልሶ መጣል ፈተና ነው ። ውጤትን እያሰቡ ማገልገል ፣ ምድራዊ ዋጋን እየሻቱ በፈጣሪ ቤት መመላለስ ፈተና ነው ።
እየበሉ መራብ ፣ እየጠጡ መጠማት ፣ ተቀብሎ እንዳልተቀበለ ማጉረምረም ፣ ያለውን ከጎደለው አለማወቅ ፈተና ነው ።
ለእውነት አንቀላፍቶ ለስሜት ታማኝ መሆን ፈተና ነው ። መልካሙን ሰው አጠልሽቶ ማየት ፣ ንጹሑን ወገን መጠራጠር ፣ በጎ ንግግርን በክፉ መተርጎም ፈተና ነው ። ሰውን በጉልበት መልካም አደርጋለሁ ብሎ መነሣት ፣ ትላንት ባደረጉት መልካም ነገር መጸጸት ፈተና ነው ።
ስለማናውቃቸውና በመለኮት ፊት ስለማንከሰስባቸው ሰዎች አስተያየት ሲሰጡ መዋል ፣ ስለ ማንም በጎ መናገር አለመቻል ፈተና ነው ። በየደረሱበት መስገድ ፣ አምልኮን እየወደዱ የሚመለከውን አምላክ አለማወቅ ፈተና ነው ። እንዴት እኔ ይህን አደርጋለሁ ብሎ መመጻደቅ ፣ ለቁጭት እንጂ ለንስሐ አለመብቃት ፈተና ነው ።
ፈጣሪን የከደነለትን የወንድምን ገመና ማውጣት ፣ በሌሎች ምሥጢር መሳለቅ ፣ በፍቅር ቀን ለጠብ ቀን ብሎ መረጃ መያዝ ፈተና ነው ። ባማረ ፊት የተቀበሉንን ፣ ክፉውን ቀን ያሻገሩንን ረዳቶች መርሳት ፣ መመሪያን ትቶ መሪን መከተል ፣ ማምለክን ፈልጎ ፈጣሪንን ለማወቅ አለመፈለግ ፈተና ነው ።
ይሙትም ይዳንም ሲባል ማጨብጨብ ፣ ለሕሊና ትቶ ለሆድ ማደር ፈተና ነው ። ሰውዬው የኮራበትን ክፋት አለማመን ፣ ዝንጀሮን አቆነጃለሁ ብሎ ቀለም መጨረስ ፈተና ነው ።
ጊዜ ተሰጥቶት ጊዜ መጠበቅ ፣ የቀበሩትን ቂም ቆፍሮ ማውጣት ፣ ለአምላክ የሚሰጠውን ፍቅር ለሰው መስጠት ፈተና ነው ። ራሱን የሰጠንን አምላክ እያመለክን ፣ ገንዘባችንን ለአሥራትና ለመባ መሰሰት ፈተና ነው ። ባልጋበዙን በሰው ጉዳይ መግባት ፣ የታገሡን ላይ ሌላ ጭነት መጨመር ፣ የተኰነነውን ኃጢአት ጽድቅ ለማድረግ መታገል ፈተና ነው ። የራስን ችግር አጉልቶ የሌላውን ረሀብ አሳንሶ ማየት ፣ በመጣው ነገር መማርን ጥሎ ማማረር ፈተና ነው ።
ራስን መምራት ከሥልጣን በላይ መሆኑን ዘንግቶ ሥልጣን መሻት ፣ ክፉ ሳይመጣብን ወደ ክፉ መሄድ ፣ እግዚአብሔር ያድነኛል ብሎ በበሽታ መጫወት ፈተና ነው ።
በገነት መሰቃየት ፣ በምቾት መጨነቅ ፣ ከመልካም ሰውና ከመልካሙ ነገር እንከን መፈለግ ፣ ባሌ የማይመታኝ ስለማይወደኝ ነው ፣ ሚስቴ የማትሰድበኝ ስለማትቀናብኝ ነው ብሎ ፣ ጦር አውርድ ጸሎት መያዝ ፈተና ነው ።
ጭር ሲል አልወድም ብሎ ነገር ማለኳኮስ ፣ በሚዋደዱ መካከል ጠብ መዝራት ፈተና ነው ። ሲሄድ የሚኖረውን ሰው አትሂድብኝ ብሎ ማልቀስ ፣ የወደደንን አምላክ ትቶ በጠሉን መደነቅ ፈተና ነው ። ያለፉትን ሰዎች ላሉት ሰዎች ማማት ፣ በማይመጣው ትላንት ላይ ማቀድ ፈተና ነው ።
አቤቱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ! በምን እየተፈተንን እንደሆነ እንኳ አናውቅምና ከፈተና አድነን !!!

ባስልዮስ ሆይ! ንገረኝ...
በዚህ ዓለም የሥራ መስክ ገበሬ መርከብ ለመንዳት የማይነሣው፣ ወይም ወታደሩ የግብርናን ሥራ የማይሠራው፣ ወይም ሙያው መርከብ ነጂ የኾነ ሰው ጦር እንዲመራ እልፍ ጊዜ ቢጎተትም እንኳ እሺ የማይለው ለምንድን ነው? እያንዳንዱ ያለችሎታው ቢሰማራ የሚከተለውን አደጋ አስቀድሞ ስለሚያይ አይደለምን? ታዲያ ጥፋቱ ቁሳቁስና ንብረት በሚኾንበት ኹኔታ አስቀድመን ብዙ የምናስብና ግፊትና ግዴታን የማንቀበል ኾነን ሳለ፥ ክህነትን እንዴት እንደሚይዙትና እንደሚያገለግሉበት ለማያውቁ ቅጣቱ ዘለዓለማዊ በኾነበት ኹኔታ ግን ያለብዙ ማሰብና ማሰላሰል እንዲሁ በዘፈቀደ ወደዚህ ዓይነት ታላቅ አደጋ ውስጥ ዘለን እንገባለንን? የሌሎች ሰዎች ግፊትስ ምክንያት ሊኾነን ይችላልን? አንድ ቀን ፈታሒ በጽድቅ ኰናኒ በርትዕ የኾነው እግዚአብሔር ይጠይቀናል፡፡ ይህ ሰበብም አያድነንም፡፡ ከምድራዊ ነገሮች ይልቅ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ይበልጥ ጠንቃቆች ልንኾን ይገባናልና፡፡ በትንንሽ ነገሮች ላይ ጠንቃቆች ስንኾን እንታያለንና፡፡ እስኪ ንገረኝ! አንድ ሰው የቤት ሥራ ሙያ ሳይኖረው ብትሠራልን ስንለው እሺ ብሎ ቢመጣና ከዚያ በኋላ ግን ዕንጨቱንና ድንጋዩን ቢያበላሽና የሠራው ነገር ወዲያውኑ ተበታትኖ ቢወድቅ በራሱ ፈልጎ አለመምጣቱና በሌሎች ግፊት ሥራውን መጀመሩ በቂ ምክንያት ሊኾነው ይችላልን? በጭራሽ! የሌሎችን ግፊትና ጥሪ አልቀበልም ማለት ነበረበትና በርግጥም ተጠያቂ ነው፡፡
ታዲያ እንዲህ ዕንጨትና ድንጋይ ለሚያበላሽ ሰው በጥፋቱ ከመጠየቅና ከመቀጣት ለመዳን ምንም ምክንያት ከሌለው፥ ነፍሳትን የሚያጠፋ፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በግድየለሽነት የሚያንጽ ሰው’ማ እንዴት? የሌሎች ግፊትና ማስገደድ በቂ ምክንያት ይኾነኛል ብሎ ሊያስብ ይችላልን? እንዲህ ብሎ ማሰብስ ሞኝነት አይደለምን?
ፈቃደኛ ያልኾነን ሰው ማንም ሊያስገድደው እንደማይችል ለማሳየት ብዬ ሐተታ መስጠት አያስፈልገኝም፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት እንደ ተናገርኩት ይህ ፈቃደኛ ያልኾነ ሰው እጅግ ተጭነዉትና ግድ ብለዉት ሌሎች ብዙ መንገዶችንም ተጠቅመው ወደዚህ ኃላፊነት አመጡት እንበል፡፡ ታዲያ ይህ ከቅጣት ሊታደገው ይችላልን? እማልድሃለሁ፤ በፍጹም ራሳችንን አናታልል! ሕፃናት ሳይቀሩ በቀላሉ በሚያውቁት ነገር ላይ እንደማናውቅ ኾነን አናስመስል፡፡ እንደማናውቅ ማስመሰላችን በዚያች ዕለት ላይ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም አይጠቅመንምና፡፡
(በእንተ ክህነት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ 4፥2
በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመው)