⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️
👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ መዝሙራት
📖▓⇨→Audio ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
https://www.tg-me.com/+lVXHSARuil5kZDU0
https://www.tg-me.com/+lVXHSARuil5kZDU0
https://www.tg-me.com/+lVXHSARuil5kZDU0
👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺👆🏽
👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ መዝሙራት
📖▓⇨→Audio ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
https://www.tg-me.com/+lVXHSARuil5kZDU0
https://www.tg-me.com/+lVXHSARuil5kZDU0
https://www.tg-me.com/+lVXHSARuil5kZDU0
👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺👆🏽
ኅዳር ፳፩
ጽዮን ማርያም
ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓሏ መታሰቢያ ነው።
“ታቦተ ጽዮን” የሚለውንም ስያሜ ያገኘችው ጽዮን ተብላ በምትጠራው የእስራኤል ከተማ ስም ነው፡፡ ጽዮን ማለት ተፀወነ፡ ተጠጋ፣ ተማጠነ ማለት ነው፡፡ ክቡረ ዳዊትም ጽዮንን አምባ፣ መጠጊያ አድርጎ ብዙ ጠላቶቹን ተዋግቶ አሸንፎ ድልን ተጎናጽፏል።
ጽዮን የተባለችው የታላቁ የዳዊት ከተማ የተገፉና የተበደሉ ሕዝቦች ሁሉ እውነተኛ ፍርድ ለማግኘት፣ ተሰብስበው የሚሰነብቱባት ከተማ ስለነበረች፣ ጽላተ ሙሴም በዚያ ስለነበረች በርሷ ተማጽነውም ችግራቸው ሰለሚቃለል ታቦቷ “ታቦተ ጽዮን” ተብላለች፡፡
ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።
"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19)
የአምላክ ማደሪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በቃል ኪዳን ታቦት ትመሰላለች ይኽቺም ፦
✿ የእግዚአብሔር የጌትነቱ መግለጫ የኾነችው፤
✿ በፍልስጥኤም ይመለክ የነበረ ጣዖትን ቀጥቅጣ ያጠፋች፤
✿ በድፍረት ሊነካት የሞከረ ኦዛን የቀሰፈች፤
✿ በታላቅ ክብር ወደ ሀገሯ ስትመለስ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ በፊቷ የዘመረላት ፤
✿ ልጁ ሰሎሞንም ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርቶ በክብር ያኖራት ናት፡፡
ጌታ የታቦቷን አሠራር ሲነግረው "ሽምሽር ስጢን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት ቀርጸኽ አብጅ ከታች እንደ ዙፋን አራት እግር አውጣለት ሞላልነቱን ኹለት ክንድ ከስንዝር ቁመቱ ክንድ ከስንዝር ወርዱን ክንድ ከስንዝር ኹለት ክንድ ከስንዝር ምስሃል ለዚኽ ቁመት የለውም አራት ቀለበት ኹለት ሙሎጊያ አበጅለት አፍአውን ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለብጠው በምስማኩና በምስማኩ ኹለቱን ኪሩቤል እንደሚናተፉ አውራ ዶሮዎች አንገታቸውን ደፋ አድርገኽ በላይ ሣልበት ዙሪያውን ፈለግ አውጣለት ብጽብጽ ወርቅ አፍስበት ጽላቶቹን በውስጡ አኑር" ብሎታል፡፡
ይኸውም ምሳሌ
✅ታቦት ፡- የእመቤታችን
✅ወርቅ፡- የንጽሕናዋ የቅድስናዋ
✅ታቹ መቀመጫው ፡- የንጽሓት እንስት
✅ላዩ መግጠሚያው ፡- የንጹሓን አበው
✅ግራ ቀኙ ፡- የሐና የኢያቄም
✅ወደ ውስጥ የገባችው:-የድንግል ማርያም ያቺ በመኻከላቸወም እንደኾነች እመቤታችንም ከሐና ከኤያቂም ለመገኘቷ ምሳሌ ነው።
✅ኹለት ክንድ ከስንዝር:- ከአዳም እስከ ኖኅ ባለው ዘመን 2260 ዘመን ይመስላል ይኸውም በኖኅ ዘመን አርአያ ድንግል ታቦተ ኖኅ ለመገኘቷ ምሳሌ፡፡
✅አንድ ክንድ ከስንዝር ቁመቱ :- ከኖኅ እስከ ሙሴ ባለው ዘመን ይመስላል ይኸውም 1600 ዘመን ነው። በዚህ ዘመን አርአያ ድንግል ጽላተ ሙሴ ለመገኘቷ ምሳሌ ነው፡፡
✅አንድ ክንድ ከስንዝር ወርዱ:- ከሙሴ እስከ እመቤታችን ባለው ዘመን ይመስላል ይኽውም 1640 ዘመን ይኾናል ይኽ በኾነ አርአያ ድንግል ታቦተ ኖኅ አርአያ ድንግል ጽላተ ሙሴ ምሳሌዎቿ የሚሆኑ አማናዊት ድንግል ማርያም ለመገኘቷ ምሳሌ ነው፡፡
✅አራቱ ቀለበት:- የአራት ወገን ንጽሕናዋ ምሳሌ ይኸውም ክርእይ /ኃጢአትን ከማየት/፤ ከሰሚዕ/ኃጢአትን ከመስማት/ ፤ ከገሲስ/በእጅ ዳሰሶ ኃጢአትን ከመሥራት እና ከአጼንዎ /የኃጢአት መዐዛን ከማሽተት/ እመቤታችን ከነዚኽ ኹሉ ተጠብቃለችና
✅ኹለቱ ቀለበት:- የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌ
✅ኹለቱ ሥዕለ ኪሩቤል:- የጠባቂ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልና የአብሳሪ መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ምሳሌ ናቸው ይኽውም የብሉይ ሊቀ ካህናት በዓመት አንድ ቀን ገብቶ ከኹለቱ ኪሩቤል መካከል ቃል ሰምቶ ይወጣ ነበር ቅድስት ድንግል ማርያም በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ተጠብቃ ከቅዱስ ገብርኤል ቃል ሰምታ አካላዊ ቃልን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ያለ ዘር ያለ ሩካቤ ፀንሳ ተገኝታለችና።
ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ይኽንን መንፈሳዊ ምስጢር በጥልቅት በመመርመር ድንግል ማርያምን ፡-
👉በምስጢር የተመላች ታቦት
👉 እሳትን የተመላች ታቦት
👉የቅዱስ ቃል ታቦት
👉የቃል ኪዳን ታቦት በማለት ገልጿታል፡፡
ኅዳር 21 ቀን የሚከበረውም የእመቤታችን ምሳሌዎች የተገለጡበት እና የተለያዩ ሥራዎች የተሰሩበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ እነዚህም፡-
1. ነቢዩ ዘካርያስ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ፣ የዘይት ማሰሮ በራሱ ላይ የነበረበትንና ሰባት መብራቶች ያሉትን መቅረዝ ሲያበራ ያየበት ዕለት ነው፡፡ ዘካ. 4፤1-2። ዘካርያስ ያየው ብርሃን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ዮሐ. 8፤12፡፡ ይህ ብርሃን የታየባትና የተገለጠባት መቅረዝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ ብርሃን መቅረዝ እንዲያዝና እንዲገለጥ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ተገልጦልናል፡፡ ጨለማ ዓለምን አብርቷል፡፡ ብርሃን ክርስቶስን ወልዳለችና እርሷም እመ ብርሃን / የብርሃን እናት/ ትባላለች፡፡
2. ታቦተ ጽዮን ዳጎንን ገልብጣ በመጣል ኃይሏን የገለጠችበት ዕለት ነው፡፡ በፍልስጥኤማውያን ተማርካ ቤተ ጣዖት ወስደው ከጣዖታቸው ከዳጎን በታች አስቀምጠዋት ነበር፡፡ ታቦተ ጽዮን ግን በላይዋ ያለውን ዳጎንን ገልብጣ ጥላ እርሷ ከላይ ተቀመጠች፡፡ በታቦት የሚገለጠው የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡ ምክንያቱም በታቦቱ ላይ ያለው ሕገ እግዚአብሔርና ስመ እግዚአብሔር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስም የጸና ክንድ ነውና ሁሉን ያሸንፋል። ስለዚህ ምንም እንኳ ለጊዜው ስትማረክ ደካማ ብትመስልም መማረኳ ግን ኃይሏን ለመግለጥ፣ ለአሕዛብ የጣዖትን ከንቱነት የታቦትን ክቡርነት ለመግለጥ ነበር፡፡
3. ቀዳማዊ ምኒልክ ታቦቱን ይዞ አክሱም የገባበት፣ ንግሥት ሳባ ታላቅ በዓል አድርጋ የተቀበለችበት፣
4. አብረሃ ወአጽብሐ በአክሱም ከተማ 12 ቤተ መቅደስ ያለው ቤተ ክርስቲያን በአስደናቂ ሁኔታ ሠርተው ከጨረሱ በኋላ ቅዳሴ ቤቱን ያከበሩበት፣ እንዲሁም
5. በ9ኛው መ/ክ/ዘመን ዮዲት ክርስትና ለማጥፋት በተነሳች ጊዜ በእርሷ ምክንያት ታቦተ ጽዮን ወደ ዝዋይ ሐይቅ የተሰደደችበት፡፡ በኋላም የሰላሙ ዘመን ሲመጣ ተመልሳ አክሱም የገባችበት በዚሁ በኅዳር 21 ስለሆነ በእነዚህ በተደራራቢ ታሪኮች ምክንያት በየዓመቱ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል “ኅዳር ጽዮን በአክሱም ጽዮን” የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡
የእመቤታችን ልመናዋ ክብሯ አማላጅነቷም ከእኛ ከህዝበ ክርስቲያን ጋር ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር! አሜን!

"ከሁለቱ የጽድቅ እንቅፋቶች እናስተውል"!
፩.ጸድቄአለሁና
፪. አልጸድቅም
ጸላኤ ሠናያት ሰውን የሚጎዳበት ሁለት ወጥመዶች አሉት። አንዱ ጸድቂያለሁ ማሰኘት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አልጸድቅም ማሰኘት ነው። በሁለቱም ምክንያቶች ጽድቅ መሥራት አይቻልም። ጸድቄያለሁ የሚያሰኛቸው መናፍቃንን ነው። ለምን ሲባሉ ጌታን እወደዋለሁና ይላሉ። አምናለሁና ይላሉ።
ጌታን ስለምወደው ጸድቄያለሁና ጽድቅ አልሠራም የምትል ከሆነ የምትድን አይምሰልህ። ለምን ትለኝ እንደሆነ ጌታ ራሱ በመውደድ ብቻ አላዳነንምና። እወዳችሁአለሁና ዳኑ ብሎ በዙፋኑ ተቀምጦ ትእዛዝ ሰጥቶ አልቀረም።
ወዶ ምን አደረገ ትለኝ እንደሆነ፦
ምሉዕ ስፉሕ ጌታ በጠባብ ደረት በአጭር ተወሰነ። ሰማይን በደመና የሚሸፍነው በጨርቅ ተጠቀለለ።
ከነደ እሳትነቱ የተነሳ ኪሩቤል የሚንቀጠቀጡለት በብላቴናዋ በድንግል ማኅፀን ተወሰነ። ምድርና ሰማይን የሚያቀልጣቸው የክብር መብረቅ በክንደቿ ታቀፈችው። በፊቱ የእሳት ጎርፍ የሚንቆረቆርለትን በከንፈሮቿ ሳመችው። አገልጋዮቹን የእሳት ነበልባል የሚያደርገውን እንዳይበርደው እንስሶች አሟሟቁት። አዳራሹን በመብረቅ የሠራው በበረት ተኛ። ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን የተሠወረው ቅጠል ለበሰ። የስደተኞች ተስፋ ተሰደደ። የሰማይና የምድር አባት በየጥቂቱ አደገ። ምድርን በደሙ የሚያነጻት ማይን ያነጻት ዘንድ ተጠመቀ። የዓለማት ዓለም ማደሪያ አጥቶ ቀን በምኩራብ ሌሊት በተራራ ተንከራተተ። የመምህራን አምላክ ለማይሰማ ሕዝብ በሰው ቃል ዝቅ ብሎ አስተማረ። ለመምህራን በሞገስ መከበርን የሰጠ እየተሰደበ አስተማረ። መላእክት እያመሠገኑ ለማመስገን የሚሳሡለት የአይሁድን ጽርፈት ሰማ። ለተበደሉት የሚፈርድላቸው በፍርድ አደባባይ ቆመ። ከፍርድ የሚያድነው ተፈረደበት። እስረኞችን የሚፈታ ታሰረ። ሰውን ወደ ሰማይ በልዕልና ስቦ የሚያሳርገውን ጎተቱት። መንሥኤ
ሙታኑን ጣሉት። ቁስለኞችን የሚፈውሰውን ቸንክረው አቆሰሉት። ራሱን ሊያለብስ የመጣውን አራቆቱት። ርኩሳኑን በደሙ ያጠበውን ርኩስ ምራቅ ተፉበት።የኃጢአትን እሾህ የሚነቅለውን የእሾህ አክሊል ደፉበት። የሕይወትን ውኃ መራራ አጡጡት። ዲያብሎስን በመስቀሉ የቸነከረውንበጦር ወጉት። ሕይዎት እርሱን ሰቅለው ገደሉት። የምድር መሠረት የሰማይን ጽንዓት በምድር ውስጥ ተቀበረ። ትንሣኤና ሕይወት ነውና ሞትን በሞቱ ደምስሶ ተነሣ!
ወደጄ ሆይ ጌታን ስለምወደው ስለማምነው ጸድቄያለሁ የምትል ከሆነ እንዲህ ብሎ ሲጠይቅህ ምን ትመልስለታለህ? ልጄ ሆይ እኔ አንተን ወድጄ ተሰቀልኩልህ።አንተ እኔን ወደህ ምን ሆንህልኝ?በዚህ ጊዜ ስለምወድህ ትጋት ትቼ ሰነፍሁልህ ልትለው ነው? ሁሉን የሚችል አምላክ በቃሉ ብቻ ማዳን እየቻለ ነገር ግን ፍቅሩን በመከራ ገልጦ ካዳነ ሰው ለአምላኩ ቃል ብቻ እንዴት ይበቃዋል?
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወረቅ እንዲህ ሲለን እንስማ!
"ኢትበል እፈቅድ ባሕቲቱ=ወዳጄ እወዳለሁ ብቻ አትበል"ዋናተኛ ዋና እወዳለሁ በማለት ወንዝ ይሻገራልን?ሐናጺ መሆን የሚሻ ቤት መስራት በመፈለግ ብቻ ሙያውን ሳይለምድ ቤት መስራት ይችላልን? መርከበኛ መሆን የሚሻ መርከብ መቅዘፍን ሳይለምድ ሊቀ ሐመር መሆን ይችላልን?ጸሐፊስ መጻፍ በመፈለግ ብቻ ፊደል ሳያውቅ መጻፍ ይችላልን? መንጻት የሚፈልግስ ሳይታጠብ በመፈለግ ብቻ ይነጻልን? የተራበስ ስለ ምግብ በማሰብ ብቻ ይጠግባልን? ጽድቅንስ በመሥራት እንጅ በመውደድ ብቻ መዳን ይቻላልን?
ሁለተኛው ደግሞ አልጸድቅም ማለት ነው።
እንደዚህ የሚያሰኛቸው ደግሞ ምእመናንን ነው። መጀመሪያ ጥቂት ጥቂት እያለ ከጽድቅ ስራ ያወጣቸዋል። ከዚያ እግዚአብሔር መሐሪ ነው እያሰኘ ኃጢአት እንዲጨምሩ ያደርጋቸዋል። ከዚያ ወዲያ ፍጹም ኃጢአተኛ ሲሆኑ በኋላ እንዳይመለሱ መቼም አልጸድቅ ያስብላቸዋል።
የእመቤ ታችን ልጆች ንቁበት። ላልጸድቅ ሲያሰኛችሁ ክርስቶስ የውበት ባሕር ነው ብላችሁ መልሱለት። በአንዲት ውኃ ብዙ ሰዎች ቢታጠቡ ትደፈርሳለች። ክርስቶስ ግን የጎሰቆሉ ሁሉ ወደ እርሱ ገብትው ሲነጹ የእነርሱ ጉስቁልና እርሱን የማይለውጠው የምሕረት ባሕር ነውና እየገባን እንንጻ! በጭቃ የተለወሰውን ወርቅ ወልውለው አጥርተው ለአክሊልነት ያበቁታል። በእግር ከሚረገጥ ጭቃ በታች የነበረውን አጥርተው ከራስ በላይ ያውሉታል። ከምእመንነት በታች ወርዶ ጌታውን የካደውን ቅዱስ ጴጥሮስን በንስሐ ጠርቶ ርእሰ ሐዋርያት እንዳደረገው አትዘንጋ! እግዚአብሔር ቸር ነው ብሎ ኃጢአት መስራት ነው እንጅ ክፉ
እግዚአብሔር ቸር ነው እያሉ መመለስ ያድናል።
አሁንም ተስፋ ቆርጠን አንዘግይ! ለመመለስ ያብቃን!ደግሞ ማንንም የማትጸየፍ እናት አለችን። ምን ብንገዳገድ እርሷን እየተመረኮዝን እንነሳ!( በትረ ሃይማኖት ድንግል ማርያም)
ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን

🏆አስደሳች ዜና ለቻናል 🏵wner🏆.
🎗🎗🎗🎗🎗
የቻናሎ ሜምበር አላድግ ፣ አልጨምር ብሎቦታል። እንግዲያውስ የምሥራጅ አለን❤
በአጭር ጊዜ ውስጥ የቻናሎን ሜምበር የሚያሳድግ ምርጥ ዌቨር " ማኅቶት ፕሮሞሽን " ይዘንሎ መጣን።
ከ5ሺ ሜምበር በታች ያለው ቻናል ለጊዜው እደግመዋለሁ ለጊዜው አንቀበልም።
በተጨማሪ መንፈሳዊ ቻናል ብቻ‼️‼️‼️
ለመመዝገብ ከስር ያለውን ይጫኑ🤲
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ ✞ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ✞ █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

Telegram
Zian
Be happy ❤️
ታህሳስ 3
እመቤታችንን 3 አመት ካሳደጓት በኋላ ቅድስት ሐና ለባሏ ለቅ.ኢያቄም ልጃችንን ለቤተ እግዚአብሔር እንስጥ ቤተ እግዚአብሔርን ልታገለግል እንጂ በዚህ አለም እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን አስብ አለች
ቅ.ኢያቄምም ደስ ብሎት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ወሰዷት ካህናትም ወጥተው ተቀበሏቸው በአንብሮተ እድም ባረኳቸው
ዳግመኛ መልአኩ ቅ.ፋኑኤል እመቤታችንን የመገበበትና
አቡነ ዜና ማርቆስ ያረፉበት አመታዊ ክብረ በዓል ነው
ከእመቤታችንና ከሁሉ ቅዱሳን በረከት ረድኤት ያካፍለን ።

😥ገዳም እንሂድ...ይለኛል ወንድሜ።ዘማነቴን አያውቀውም። ሴሰኝነቴ አይገባውም።እኔ በምናብ ከፈጠርኳት ሴት ጋ ቀን ከሌት በራሴ አለም ስዳራ የኖርኩ መሆኔን ቢያቅብኝ እንኳን ገዳም አብሮኝም ቆሞ ለመታየት ያፍርብኝ ነበር አንተ ያሬድ ተነስ ሰአቱ እረፈደ ነው። ውጣ እንጂ...አለ።(ዛሬ የቁርጥ ቀን ነው።ገዳም ከመሄዱ በላይ የሚፈታተነኝን ግለ ወሲብ የት ጥዬው እንደምሔድ ጨንቆኝ ስገላበጥ ነው ያደርኩት እ....እሺ ይኸው ወጣሁ(ቦርሳዬን ሸክፌ ተከተልኩት።ለአመታት ልወጣበት ካልቻልኩት ድብቁ ሱስ የሚገላግለኝ ሀይል እንደሌለ አምኛለሁ። ተውኩት ስል እየመጣ፤ የሀጥያት ሀፍረት ሲያከናንበኝ ለአመታት ቆይቶብኛል።አንዳንዴ ግልግል ማለትም ያምረኛል.... ሰውዬ ውረድ እንጂ ምነው ዛሬ ፈዘካል....ከረጅም የፒስታ መንገድ በኋላ በጫካ የተከበበች መሀሪት ማርያም ቤተክርስትያን ደረስን።ጫማ ማድረግ የለም።ምግብ የለም። ስልክ አይገባም።ንሰሐ ሳይገቡ መውጣት...(ገና ከበሩ የግቢው ዘብ ህጉን ሲዘረዝረው ልቤ እንደ ሰም ቀለጠች።ስልኬ ላይ በድፍረት የተሸከምኳቸው የነውር ምስሎሽ በአይኔ እየዞሩ ስልኬን አስረክቤ ወንድሜን ተከትዬ ገባሁ...... "አረ አለም በምን ጣዕሟ" እያልኩ እያማረርኩ ነበር የመሸልኝ።ከተማ ጥዬው የመጣሁት ዝሙት ገዳም ስገባ ጭራሽ ያቅበዘብዘኝ ይዟል።ከፀሎቱ ይልቅ ዝሙት አእምሮዬን ወጥሮት የአንድ ሰአቱን ፀሎት እንደጨረስን ስሮጥ ወደ ጫካው ወረድኩ።ሱሴን ላስታግስ...በዝሙት ልወድቅ....እንደገና ደጁ ልበድል...... ሱሪህን ፍታው....!! አረ ተው ፈጣሪን ፍራ!! እዚህ ጨለማ ማን እንዳያይህ ነው!? ከውስጤ ጋ ትግል እየገጠምኩ ከተራራው ቅጠል እያንኮሻኮሸ የሚወርድ የአውሬ ድምፅ ስሰማ ሱሪዬን እየጎተትኩ ወደ ማደሪያው አመለጥኩ...... ጎረምሳው ና እስቲ እቺን ውሀ አድርስልኝ...(ከኪዳን ስንመለስ ጎልመስ ያሉ መለኩሴ ከሰው መሀል ጠሩኝ እሺ አባቴ ችግር የለም..... ባዶ እግሬን ሸንከል እያልኩ ለመለኩሴው ውሀውን በሩ ላይ አድርሼላቸው እንደዞርኩ ሳትገባማ አትሄድም።ና ግድ የለም ጦም ቢሆንም ትንሽ እረፍት አድርግ..... ኦና የሆነ።ጨለማ የወረሰው ቤት ተከትያቸው ገባሁ።እጣን እጣን ይሸታል።በቆርቆሮው ቀዳዳ የሚገባው ጨረር ቀይ ረጅም መጋረጃቸው ላይ ስላረፈ የሚታየው እሱ ብቻ ነው።የተደገፍኩበት ግድግዳ በምርጊት የቀረ የጭቃ ቤት መሆኑ ያስታውቃል።መሬቱም አባጣ ጎርባጣ አቧራማ መሆኑ እግሬ በዳበሳ ሰልሎታል.... ልጅ ያሬድ ተጫወት (አሉ ከጨለማ ውስጥ ለስለስ ያለ ድምፅ አውጥተው በስመአብ ወወልድ።አማተብኩ።ፈራሁ።ስሜን ማን ነገራቸው...??? አይዞህ እንግዲህ የመለኩሴ ቤት።እስቲ እቺን ገመድ ያዛት ልጄ አሉ ጨረሩ እጃቸው ላይ ሲያርፍ አረንጓዴ ገመድ አይቼ ተቀበልኳቸው ምን ላድርገው አባ??? አንገትህ ውስጥ አጥልቀው አልገባኝም።ለምን??ልላቸው ብዬ ገዳም መሆኑ ትዝ ብሎኝ እጄ እየተንቀጠቀጠ አንገቴ ውስጥ ከተትኩት።የሆነ ነገር ነብሴን እየጨነቃት ገመዱ እየተሳበ እየጠበቀ ሲመጣ ይታወቀኛል..... አ....አባ ም...ምንድነው??አልኳቸው የሞት ሞቴን ትንፋሽ እያጠረኝ ።እሳቸው ጋ ግን ከማጥበቅ ውጪ መልስ የለም አባ እያነቁኝ ነው።ገመዱን አስለቅቁኝ አባቴ.....(መልስ የለም አባ ልሞት ነው...(ትንፋሼ እየተቆራረጠ በግድ አወራሁ።ገመዱ እየገዘገዘኝ ደምስሬ እየተወጠረ የጣሬን ገመዱን ይዤ በመጨረሻ አቅሜ... አ....አባ (ስል ገመዱ ድንገት ሲረግብ እኩል ሆነና ትንፋሼን እየለቀቅኩ ተነስቼ ለማምለጥ ቃጣኝ ቁጭበል!! እንዴ ምንድነው ከኔ ሚፈልጉት?? ምን አድርግ ነው ሚሉኝ ቆይ.... ምንም አላልኩህም።ሞት እንዴት እንደሆን በትንሹ ላሳይህ ብዬ ነው።ልጅ ያሬድ ከመጣህ ቀን ጀምሮ አውቅሀለሁ ወንድምህ አንተን እዚህ ሲያመጣህ ተማክረን ነው።አየህ በመጀመርያ ቀን ንሰሐ ግባ ሲልህ አሻፈረኝ ብለካል ነገሩ በግድ ስለማይሆን ተውንክ።አንተ ግን ሌላ በደል.... ሌላ በደል!??? አዎ እንግዲህ እዚ ድረስ መጥተህ ከምትጠፋ ብነግርህ ይቀላል።ያንተን ችግር እኔም ወንድምክም እናቀዋለን።ባለፈው በለሊት ጫካ ውስጥ ከራስህ ስትታገል እንደ አውሬ ጩኼ ያባረርኩህ እኔ ነኝ።አስተውል ያሬድ ቅድም ገመዱን ስሰጥህ ቀለል አርጌ ነበር ሸምቀቆው እየጠበበ ሲመጣ ግን መተንፈስ አቃተህ።ግለ ወሲብም እንዲህ ነው።በተዘዋዋሪ በቀላሉ ትገባበትና እየጠበቀ ሲመጣ ግለ ሞት እራስን በፈቃደኝነት በነብስም በስጋም ማጥፋት ይሆናል።እራስህን ብቸኛው ሀጥያተኛ አድርገህ አታስብ ከመድሀኒቱ ቀድመህ ስለበሽታው ካላወቅክ አትድንም።መተፋፈሩ ይበቃል ከዚህ በላይ ሰይጣን እንዲያዋርድህ አትፍቀድ።ለመንፃት ሳትሰለች ተጠመቅ ንሰሐ ግባ ሰይጣን የደበቅክለትን ነውሩን በእግዜር ፊት ስትገልጥበት እግዚአብሔር ደሞ ከሰይጣን የዘማዊነት አሰራር ይከልልካል።አሁንስ ልጅ ያሬድ ምን ትለኛለህ አባ ለንሰሐ መች ልምጣ...እንዲ መሞት አልፈልግም።(ሲሰንፍ የነበረው ልቤ ያዋረደኝን ሰይጣን ለመጣል ሲነሳሳ ለእግዜር ደሞ ሲብረከረክ ተሰማኝ የመዳን ቀን ዛሬ ነው ልጄ ከመጣህ አሁኑኑ ሀጥያትህን ተናዘህ ሂድ...
ለብዙ ሰው ይጠቅማል #ሼር
https://www.tg-me.com/meazasenay
ለብዙ ሰው ይጠቅማል #ሼር
https://www.tg-me.com/meazasenay
Telegram
መዓዛ ሠናይ
☞ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችን እንወቅ
☞እንረዳ
☞እንማማር
♥♥♥♥♥♥
ለበለጠ መረጃ @Tadi16 ላይ ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት እንቀበላለን፡፡

“ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ አላት።” /ማር 5÷34/
"እምነት" በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ እግዚአብሔር ከፅንሰቱ እስከ እርገቱ ድረስ በምድር ላይ ሰው ሆኖ በፈቃዱቨ ያደረገውን ሁሉ ማመን መቀበል ሳያጎድሉ በምልዐት መቀበል ነው (ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ መድልተ ጽድቅ ቅጽ 1) የሰው ልጅ ውድቀቱ መነሳቱ በእምነት ማጣት እና ማግኘት ነው።
አስቀድሞ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ሲፈጥረው እንደራሱ አድሮጎ በተፈጠረለት ማንነቱ በንፅሕናው ተፈጥሮ መልካምና ክፍውን ይለይ ዘንድ ነፃ ፍቃድ ሰጥቶ ፈጠው ከእርሱ በፈት የተፈጠሩት ፍጥረታት ሁሉ አዳም የእግዚአብሔር ስራ አይቶ በመድነቅ ከእግዚአብሔር ጋር በእምነት በታማኝነት አንድላይ ይኖሩ ዘንድ ፍጥረታት ተፈጠሩለት እግዚአብሔር ከዚህ ከተፈጠረለት ማንነት እንዳይወጣ አሰቀድሞ " ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካም እና ክፍውን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ በማለት አዞት " ግን ከእግዚአብሔር ይልቅ የሴጣንን ምክር ሰምቶ አምኖ ሞትን በራሱ ላይ አመጣ የቀደመችው ሔዋን ሴጣንን አምና ሞትን በእራሷና ከአብራኩ ካስገኛት አዳም ሞትን አመጣች።
ዳግማዊቷ ሔዋን ድንግል ማርያም ግን መጀመርያ ሞት በመጣበት መንገድ የእምነት ማጣት ትሞላ ዘንድ ቀድማ የሴጣንን ምክር በተቀበለችው ሔዋን ፍንታ የመላኩን ቃል በእምነት በመቀበል ለፈጣሪ ያለንን እምነት መለሰችልን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእምነት በመኖራቸው የእምነታቸውን ፍሬ ያፈሩ እና በሕይወታቸው ሁሉን የእግዚአብሔር ቻይነት የመሰከሩ እሩስም ታማኝነታቸውን በበረከት የመሰከረላቸው አሉ ከእንዚህም ውስጥ የመጥምቁ እናት ቅድስት ኤልሳቤጥ ናት እስከ እርጅናዋ ዘመን ድረስ እግዚአብሔር ስታገለግል የኖረች የካህኑ ዘካርያስ ሚስት ኤልሳቤት ታሪኳ በሉቃ 1÷5 ተፅፎ እናገኛለች ኤልሳቤጥ በዘመኗ ሁሉ እግዚአብሔር ባይሰጣትም ልጅ እንደሚሰጣት አንድ ቀን አምና የእግዚአብሔር ሁሉ ቻይነት እመሰከረች ኖረች።
እግዚአብሔር የኤልሳቤጥን እሱን አምና ለዘመናት ሳታማርር መኖሯን አይቶ ጌታን የሚያጠምቀውን መጥምቁ ዮሐንስን ሰጥቷት እምነቷን መሰከረላት ይህ ሁሉ የሆነው በኤልሳቤጥ በእምነት መኖር ነው። ሰማዕታት የእግዚአብሔርን ክብር እየመሰከሩ በርሃብ እርሱን ምግብ አርገው ሁሉን እንደማያሳጣቸው እየመሰከሩ ኖሩ እግዚአብሔር በገባላቸው ቃልኪዳን ዘወትር ፍጥረታትን በስማቸው እየመገበ እምነታቸውን መሰከረላቸው።
(ማቴ 20÷22) ተፅፎ የምናገኘው አንድ ታሪክ አለ ከአስራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም ይፈሳት የነበረች ሴት ብዙ ባለመዳኒቶች ጋር ገንዘቧን የጨረሰች ግን የገንዘቧ ማለቅ ደሟ መፍሰሱን ያላስለቀቀላት" ያልቆመላት ሴት። ይች ሴት ክርስቶስን ልብሱን የነካው እንደሆነ እፈወሳለሁ ብላ በእምነት አምና ቀረበች ዳሰሰችውም ዳነች። ክርስቶስ ልጄ ሆይ አይዞሽ እምነትሽ አድኖሻል ብሎ መሰከረላት። ይህች ሴት የክርስቶስን በስጋ ውስጥ ሳይታይ ያለውን ሁሉን ቻይነት አምና ሊፈውሳት እንደሚችል አምላክነቱን በእምነት መሰከረች። ክርስቶስ በማይታየው እምነቷ የሚታየውን በሽታዋን በመፈወስ እምነቷን መሰከረላት።
ወዳጆቼ ብዙ የሚታይ በሽታ ይዞን ይሆናል እንደ ዘመኑ ሰው የመግደል በሽታ አልቅሶ እስካለየነው ደስታ የማይሰማን የመሆን በሽታ ፍቅርን በመግፍት አንጂ በተጠላን ልክ የማይገኝ ሲመሰለን በትውልድ ውስጥ ጥላቻ እየጫሩ የመኖር ይህ ሁሉ የሚታይ የግፍ ውጤት ሊቆም ያልቻለው የማይታየው እምነት ስለሌለን ፈጣሪ ሳይሆን ሴጣን እየመሰከረልን እየኖርን እንገኛል። ስለዚህ ፈጣሪ እንዲመሰክርልን ወደ እርሱ እንመለስ።

#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል (#ታኅሣሥ_19)
ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅ ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡
ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡
በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡
የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡
መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
( ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ)

"ልጆቼ! የሚያሳፍር ነገር፣ የስንፍና ንግግር ወይም ዋዛ ፈዛዛ የማይገቡ ናቸውና በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ ከቶ አይሰሙ፡፡ እስኪ ንገሩኝ! የዋዛ ፈዛዛ ንግግር ጥቅሙ ምንድን ነው? እስኪ ንገሩኝ፤ አንድ ጫማ ሰፊ፣ ጫማ እየሰፋ በአንድ ጊዜ ሌላ ሥራ መሥራት ይችላልን? አይችልም፡፡ ከዋዛ ፈዛዛ የሚያሳፍር ንግግር ይወለዳል፡፡ የአሁኑ ጊዜ ደግሞ ለእኛ ለክርስቲያኖች ዋዛ ፈዛዛ የምንናገርበት ሳይኾን የንስሐችን ጊዜ ነው፡፡ እስኪ አሁንም ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! አንድ ቦክስ የሚጫወት ሰው ውድድሩን ችላ ብሎ ዋዛ ፈዛዛን ይናገራልን? እንዲህ የሚያደርግ ከኾነስ በተጋጣሚው በቀላሉ የሚሸነፍ አይደለምን? ታዲያ ባለጋራችን ዲያብሎስ‘ኮ የሚውጠውን ፈልጐ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙርያችን ቁሟል፡፡ ጥርሱን እያንቀጫቀጨብን ነው፡፡ እኛን የሚጥልበት ወጥመድ በማዘጋጀት ላይ ነው፡፡ የደኅንነታችን መንገድ ላይ እሳት እየተነፈሰ ነው፡፡ ታዲያ ዲያብሎስ እንዲህ እኛን ለመጣል ሲተጋ እኛ ዋዛ ፈዛዛን፣ የሚያሳፍር ነገርን፣ የስንፍናንም ንግግር ስንናገር ቁጭ ልንል ይገባናልን?
የምወዳችሁ ልጆቼ! ጊዜው የምንተኛበት ጊዜ አይደለም፡፡ የተጋድሎ ጊዜ ነው እንጂ፡፡ ቅዱሳን ጊዜያቸውን እንደ ምን እንደሚያሳልፉት ማወቅ ትፈልጋላችሁን? እስኪ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስን አብረን እንስማው፤ እንዲህ ያለውን፡- “ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ”፤ … “በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችኋለሁ…”፡፡ … “የሚደክም ማን ነው፤ እኔ አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፤ እኔም አልናደድምን?”፤ “… በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን”፡፡ ታዲያ እነ ቅዱስ ጳውሎስ ጊዜያቸውን እንዲህ ካሳለፉ፣ ኃጥአን የምንኾን እኛ ጊዜያችንን በሳቅና ስላቅ ልናጠፋ ይገባናልን? በክርስቶስ ፍቅር የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በንግግሬ አትማረሩ፡፡
ጊዜው የተጋድሎ ጊዜ ነው፤ ታዲያ ስለ ምንድን ነው የዘፋኞችን መሣርያ አንሥተን ከዓለም ጋር የምንዘፍነው? በጦር ግንባር ያለ ወታደር ከጠላት ሊመጣ የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል ከመዘጋጀት ይልቅ ጊዜውን በዋዛ ፈዛዛ ያጠፋልን? አያጠፋም፡፡ ታዲያ እኛም‘ኮ የክርስቶስ በጎ ወታደሮች ነን፡፡ ..."
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

የከተራና የጥምቀት መዝሙሮችን ለማጥናት 👇👇
🎶 እግዚኡ መርሐ ♡
🎶 ከድንግል ተወልዶ ✞
🎶 በዮርዳኖስ የተጠመቀው ✧
🎶 ዘወይን ዘወይን ✞
🎶 ጥምቀተ ባሕር ♡
🎶 እርሱ ፍጹም ሊልቅ ✞
🎶 ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠመቀ
🎶 ዮሐንስ አጥመቆ ♡
🎶 ዮሐንስኒ_ያጠመቀ ♡
🎶 እንዘስውር ✧
እነዚህን ለማጥናት ከስር Join አድርጉ
join join join
Join join join
🎶 እግዚኡ መርሐ ♡
🎶 ከድንግል ተወልዶ ✞
🎶 በዮርዳኖስ የተጠመቀው ✧
🎶 ዘወይን ዘወይን ✞
🎶 ጥምቀተ ባሕር ♡
🎶 እርሱ ፍጹም ሊልቅ ✞
🎶 ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠመቀ
🎶 ዮሐንስ አጥመቆ ♡
🎶 ዮሐንስኒ_ያጠመቀ ♡
🎶 እንዘስውር ✧
እነዚህን ለማጥናት ከስር Join አድርጉ
join join join
Join join join
ጌታችን ስለተወለደባት ምሽት ቅዱስ ኤፍሬም አንዲህ አለ....
.
‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት! ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት! የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡ ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››
እንኳን ለአምላካችን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡
ሰብአ ሰገል ይዘው የመጡት ወርቅ ዕጣንና
ከርቤ ከየት መጣ?
በቅድምያ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ! በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሁንልን።
ጌታችን በተወለደ ጊዜ ሰብአ ሰገል የገበሩተለት ወርቅ ፣ ዕጣንና ከርቤ መገኛቸው ከገነት እንደሆነ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን? ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ ጥንት አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን በገነት ውስጥ በሰላምና በተድላ ይኖሩ ነበር። ታዲያ ዲያቢሎስ አትብሉ የተባሉትን እንዲበሉ ሐሳብ አቅርቦ ካሳታቸው በኋላ ያን አትብሉ የተባሉትን በመብላታቸው ትዕዛዝ በመተላለፋቸው ሰባት ዓመት ከ47 ቀን በተድላ ከኖሩበት ገነት ተባረሩ። ከገነት ከወጡ በሁላ አዳምና ሔዋን በዚህ ምድር ላይ ኑሮአቸውን ሀ ብለው ጀመሩ።
አንድ ቀን አዳም እናታችን ሔዋንን በባል ልማድ ሊጨዋወታት (ሊገናኛት) ወዶ በመንገድ ጠብቆ አስደነገጣት ታዲያ ይህን ጊዜ ሥላሴ ተገልጠው "ምነው ማጫውን ሳትሰጠን ልጃችን ትነካለህን?" ቢሉት አዳምም "ጌታዩ የአንተ ያልሆነ የኔ የሆነ ምን አለኝና እሰጥሀለው!" ቢሊ "አይ ለኋልኛው ዘመን ሥርዓት ነውና ይህን ለእርሷ ስጣት እንኳ" ብለው ቅዱስ ሚካኤል ወርቁን ፣ ቅዱስ ገብርኤል ዕጣኑን ፣ ቅዱስ ሩፋኤል ደግሞ ከርቤውን ለአዳም ሰጥተውታል። አዳምም ተቀብሎ ለሔዋን ሰጣት ፣ ሔዋን ለሴት ሰጠችው ፤ ከሴት ሲወርድ ሰዋረድ ከኖህ ደረሰ፡ ኖህ በጥፋት ውኅ ዘመን ወደ መርከብ ሲገባ የአዳምን አጥንትና ወርቅ ፣ ዕጣን ፣ ከርቤውን በአንድነት ይዞ ገባ።
ኋላ የጥፋት ውኀው ጎደለና ከመርከብ ይዞትጰወጣ በሁላ ለሴም ሰጠው ፤ ሴምም መልከጼዴቅን ተገናኘውና የአዳምን አጥንት በጎለጎታ ቀበሩት። ለዚህም ነው የጌታችን የሥነ ስቅለቱ ስዕል ሲሳል ከሥር የራስ ቅል አጥንት የሚደረገው ያም የአዳም አጥንት ምሳሌ ነው። ከዚያም ሴም ለመልከጼዴቅ ወርቅ ፣ ዕጣን ፣ ከርቤውን በአደራ አስጠበቀው፡ መልከጼዴቅ ለአብርሃም ሰጠው።
ከአብርሃም ሲወርድ ሲወረድ በዳዊት በሰለሞን አድርጎ ከአካዝ ደረሰ፡ በአካዝ ዘመን ቴልጌልፌልሶር ማርኮ ወስዶ ከቤተ መዛግብት አኑሮታል፡ አባታቸው ዥረደሸት ፈላስፋ ነበር፡ አንድ ቀን በቀትር ከውኃ ዳር ሆኖ ሲፈላሰፍ በሰሌዳ ኮከብ ድንግል ሕፃን ታቅፋ አየ ያየውን በሰሌዳ ቀርጾ አሰቀመጠው ከመሞቱ በፊትም እንዲህ ያለ ኮከብ ሲወጣ ባያችሁ ግዜ ሰማያዊ ንጉስ ይወለዳልና ወስዳቹ ይህን ወርቅ ፣ ዕጣን ፣ ከርቤ ስጡት ብሎ ለልጆቹ ተናዞ ሞተ። በዚህ መልኩ ከእነዚህ ነገሥታት እጅ ደርሷል። በእርግጥ ታሪኩን ለመተረክ አንድ መጽሐፍ የሚበቃውም አይደለም ከረጅም በአጭሩ ግን ይህን ይመስላል።
ታዲያ ኮከቡም በታየ ግዜ የታዘዙትን ለመፈፀም 12
ነገስታት ፍርሻኩር የተባለ ንጉሥ እየመራቸው ከሀገራቸው ተነሱ እያንዳንዱ ነገሰታት 10 ሺህ የሚሆን ሠራዊት ይዘው በጉዞ ላይ እያሉ ኤፍራጥስ ወንዝ ሲደርሱ ፍርሻኩር የተባለው መሪያቸው ዘጠኙን ነገስታት ከነሰራዊታቸው ይዟቸው ተመለሰ ከተመለሱበት ምክንያት ውስጥ ግማሹ ስንቅ አልቆባቸው ሌሎቹ ደግሞ በሀገራቸው ጠላት ተነስቶባችዋል የሚል ወሬ ሰምተው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ኢየሩሳሌም ለሰላሳ ሺ ሠራዊት አትበቃም ጠባብ ናት ብለው የተመለሱም አሉ። ምስጢሩ ግን ከበረከተ ልደቱ እንዲሳተፋ የተመረጡት ሦስቱ ብቻ መሆናቸውን የጠይቃል የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ጥቂቶች ናቸው እንደተባለ።

ማኅቶት ፕሮሞሽን💓
You’ve been invited to add the folder “ማኅቶት ፕሮሞሽን💓”, which includes 99 chats.