Telegram Web Link
«..የተከበረው ወር በመሰናበቱ አትዘኑ .. ይልቁንስ መጨረሻውን ስላደረሳችሁ አሏህን አመስግኑት.. ለፆሙም ለመቆሙም ስለመራቹ ደስ ይበላችሁ .. አላህን በተክቢር አልቁትም ። ረመዳንን አትሰናበቱት ..ለቀሪው እድሜያቹና አመት አብሯቹ አድርጉት .. ረመዳን ወር ብቻ ሳይሆን የህይወት መንገድ ፣ የለውጥ ጅማሮ ነው . ስለዚህ አትሰናበቱት ..ይልቁንስ አመቱን ሙሉ አብሯቹ እንዲኖር እናንተም በሱ ህያው እንድትሆኑ እድሉን ክፍት አድርጉለት
ጾም አያልቅም ፤ ለቁርኣን ጀርባ አይሰጥም ፤ መስጊድም አይተውም ! »

https://www.tg-me.com/mededulhabib
ዒድ ሙባረክ ኩሉ ዓም ወአንቱም ቢአልፍ ኸይር ። ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሓል አዕማል።

የደስታ የአማን የፍቅር ዒድ ይሁንልን

https://www.tg-me.com/mededulhabib
ታላቁ ወልይ ሰይዲ አል ኢማም አህመድ አር-ሪፋዒ'ይ ቀደሰሏሁ ሲረሁም ሲናገሩ :

« የዒድ ፊጥር ለሊት ላይ ሰይዳችን ረሱሉላህን ﷺ በመናም አየኋቸው .. ኑራቸው ዓለሙን ሞልቶ ነበር ..

[ ሰላት ሰላም በርሶ ላይ ይሁን.. አንቱ የዓለሙ ሩሕ ..አንቱ የአላህ መላክተኛ ].. አልኳቸው

እሳቸውም ﷺ : [ አንተም ላይ ሰላም ይውረድ ] ብለው መለሱልኝ

[ የምውዶት ሆይ .. ከዕውቀት ሁሉ በላጭ የሆነው አስተምሩኝ.. ] አልኳቸው

[ ከሐቅ (ከአሏህ ) ጋር መቆም ነው ..(መሆን ነው )

{واتقوا اللهَ ويُعلمكم الله }

{ አላህን ፍሩት አላህ ያስተምራቹሀል }

ይሄ ይበቃሀል ..» አሉኝ ።

https://www.tg-me.com/mededulhabib

እንዴት ያማረ ዒድ ነበር ዒዳቸው ! በዒዱ ለሊት የዒዳችን ሲርና የደስታችን ምንጭ ከሆኑት ከሰይዳችን ﷺ ጋር ማደር ☺️

አሏህ በረሕመቱ እጣችን ያድርገው
የረመዳን ቀዳ ያለበት ከሸዋል ቀናቶች ጋር አንድ ላይ  ቀዳውንም ሱናውንም  ነይቶ ከፆመ ሁለቱንም ያገኛል። አንዱን ብቻ ከነየተ የነየተውን ብቻ ነው የሚያገኘው ። በሻፊዒያ መዝሀብ ውስጥም ሆኖ ከዚህ ሌላ እይታዎች ቢኖርም በመሻኢኾቻችን ፈትዋ የሚሰጥበት ቀውል ይሄ ነው ።

፡==================

አንድ ሰው ያለበትን ቀዷ መፆማቸው የሚወደዱና ሱና የሆኑ ቀናቶች ላይ ቢያደርገው :

1. ኢማም አር-ረምሊ'ይ በጠቀሱት እይታ ቀዳው ይገኝለታል ልክ እንደዛውም " ሱናውን ባይነይተውም እንኳን - ሙሉ ባይሆንም - አጅሩን ያገኛል " ብለዋል ። ንግግራቸው ከኪታባቸው 👇

جاء في [نهاية المحتاج 3/ 208] : "ولو صام في شوال قضاء أو نذراً أو غيرهما أو في نحو يوم عاشوراء حصل له ثواب تطوّعه، كما أفتى به الوالد رحمه الله تعالى تبعاً للبارزي والأصفوني والناشري والفقيه علي بن صالح الحضرمي وغيرهم، لكن لا يحصل له الثواب الكامل المرتب على المطلوب".

2. ሸይኽ ኢብኑ ሐጀር አል-ሀይተሚ'ይ በጠቀሱት ደግሞ .. ቀዳውን ያገኛል ። "የሱናውን አጅር ለማግኘት ግን ግዴታ መነየት አለበት ። ካልነየተ አያገኘውም.. " ብለዋል ..

" لكن صرح ابن حجر بحصول أصل الثواب لإكماله إذا نواها كغيرها من عرفة وعاشوراء"

📗 بغية المسترشدين ص 73
፡========================

ለየብቻ መፆሙ በላጭና ምርጥ መሆኑ ከመታወቁ ጋር በስድስቱ ውስጥ ማካተቱ እንደሚቻልና የሱናውንም አጅር እንደሚያስገኝ የዑለማዎቻችን የፉቀሀዎቹና የመሻይኾቹ ፈትዋ ነው ።

አሏሁል ሙስተዓን
https://www.tg-me.com/mededulhabib
«..ስለ ሰይዳችን ﷺ እንዲህም ብለዋል :

تباهى الناسُ بالعيدِ  .. وعيدي أنت يا سيدي

ሰዎች ተደሰቱ በዒዱ ድባብ ..
የኔ ዒድ አንቱ ኖት ሰይዱል አሕባብ..
(እንደማለት ነው)

ዒዳችንም ሆነ ዒዶች ውስጥ ያሉ ኸይርና ደስታ ሁሉ በሰይዳችን ሙሐመድ ﷺ የተገኘ ነው .. ምክንያቱም እሳቸው ናቸው ። እሳቸውን ባይኖሩን ኖሮ ረመዳንንም ሆነ ለይለተል ቀድርን አናውቅም ነበር ። ነገር ግን በሳቸው በረካ ነው .. እሳቸው ነው ያሳወቁን ። በዒድ ቀን ለኡመታቸው ይወጡ ነበር ይታዩዋቸውም ነበር። በእዝነት ይመለከቷቸው ነበር ፊታቸውም ላይ ፈገግታን ያሳዩ ነበር.. አሁንም እስከዚ ጊዜያችን ድረስ ይሀ ደስታ አለ ..»

💫 ሰዪዲ ሐቢብ ዑመር ቢን ሙሐመድ
https://www.tg-me.com/mededulhabib
ኢማም አሽ-ሻፊዒይ ሰይዳችንን ﷺ ሲያልቁ "አር'ሪሳላህ" ኪታባቸው ላይ ከተጠቀሟቸው አገላለፆች ውስጥ አንዱ :

«..በዲንም በዱንያም ምርጥ እድያን ያገኘንባት ግልፅም ሆነ ድብቅ ችሮታ በኛ ላይ አልዘወተረችም ልክ እንደዛውም መጥፎ የተባለ ነገር በዲንም በዱንያም ወይም በአንዳቸው ከኛ አልተመለሰም ሰይዳችን ሙሐመድ ﷺ የዛ ሰበብ ቢሆኑ እንጂ ! ወደ ኸይሯም መሪ ወደ ትክክለኛውም አመላካች ቢሆኑ እንጂ ! ከጥፋትም ሆነ ከቀናው ተቃራኒ ከሆኑ ክፉ መንገዶች ከልካይ ፤ ወደ መጥፋት ከሚያደርሱ ምክንያቶች ሁሉ አስጠንቃቂ ፤ በማስጠንቀቅና ቅኑን በማመላከት ደግሞ መካሪ ቢሆኑ እንጂ..! የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸውም በቤተሰባቸውም ላይ ይስፈን..»

«فلم تمس ﺑﻨﺎ ﻧﻌﻤﺔ ﻇﻬﺮﺕ ﻭﻻ ﺑﻄﻨﺖ، ﻧﻠﻨﺎ ﺑﻬﺎ ﺣﻈﺎ ﻓﻲ ﺩﻳﻦ ﻭﺩﻧﻴﺎ ﺃﻭ ﺩﻓﻊ ﺑﻬﺎ ﻋﻨﺎ ﻣﻜﺮﻭﻩ ﻓﻴﻬﻤﺎ، ﻭﻓﻲ ﻭاﺣﺪ ﻣﻨﻬﻤﺎ: ﺇﻻ ﻭﻣﺤﻤﺪ ﺻﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﺳﺒﺒﻬﺎ، اﻟﻘﺎﺋﺪ ﺇﻟﻰ ﺧﻴﺮﻫﺎ، ﻭاﻟﻬﺎﺩﻱ ﺇﻟﻰ ﺭﺷﺪﻫﺎ، اﻟﺬاﺋﺪ ﻋﻦ اﻟﻬﻠﻜﺔ ﻭﻣﻮاﺭﺩ اﻟﺴﻮء ﻓﻲ ﺧﻼﻑ اﻟﺮﺷﺪ، اﻟﻤﻨﺒﻪ ﻟﻷﺳﺒﺎﺏ اﻟﺘﻲ ﺗﻮﺭﺩ اﻟﻬﻠﻜﺔ، اﻟﻘﺎﺋﻢ ﺑﺎﻟﻨﺼﻴﺤﺔ ﻓﻲ اﻹﺭﺷﺎﺩ ﻭاﻹﻧﺬاﺭ ﻓﻴﻬﺎ. ﻓﺼﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻰ ﻣﺤﻤﺪ ﻭﻋﻠﻰ ﺁﻝ ﻣﺤﻤﺪ ﻛﻤﺎ ﺻﻠﻰ ﻋﻠﻰ ﺇﺑﺮاﻫﻴﻢ ﻭﺁﻝ ﺇﺑﺮاﻫﻴﻢ ﺇﻧﻪ ﺣﻤﻴﺪ ﻣﺠﻴﺪ»
📗 الرسالة : 13
https://www.tg-me.com/mededulhabib

የችሮታ የደስታችን ሁሉ ምንጫችን ናቸው .. ልባችን ውስጥ ፍቅራቸውን በማጎልበት እሳቸው ላይ ሰለዋት በማብዛት ከአላህ ለሚገኘው ስጦታ ተገቢ እንሁን☺️
#የፎሎወር_እና_የላይክ_ዘመቻ
አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ

ውድ የኢስላም ቤተሰቦች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሊንኮች ትክክለኛ እና በአል-ዒምራን የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምሕርት ተቋም የሚመሩ ገፆች ናቸው! FOLLOW, LIKE እና SUBSCRIBE በማድረግ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ በማጋራት ተደራሽነቱን በማስፋት ሁላችንም የኸይር ተቋዳሽ እንድንሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን!!
**
ትክክለኛ ማህበራዊ ገጾቻችን
አል-ዒምራን Cmc የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምሕርት ተቋም

FACEBOOK:
http://www.facebook.com/alimrancmc

TIKOTOK
https://www.tiktok.com/@alimrancmc

YOUTUBE:
www.youtube.com/@alimrancmc

TELEGRAM:
www.tg-me.com/alimrancmc

INSTAGRAM:
www.instagram.com/alimrancmc
በአላህ ፍቃድ ዛሬ ከመግሪብ ቡኃላ ተፍሲር ደርሳችንን እንጀምራለን

ቦታ : ጠሮ- ዑስማን ቢን ዐፋን መስጊድ

አህለን ወሰህለን
https://www.tg-me.com/mededulhabib
Live stream started
Live stream finished (53 minutes)
የሚወዳትን ለሕይወቱም ተስማሚ የሆነችን ሚስት መሰጠት ዱንያ ላይ አሏህ ከሚሰጠው ትላልቅ ውለታዎችና ነገ አኼራ ላይም ለባርያው ያደረገለትን ውለታ ሲነግረው ከሚጠቀሱ ችሮታዎች ውስጥ አንዱ ነው ።

ኢብኑ ሒባን በዘገቡት ሐዲስ ሰይዳችን ﷺ እንዲህ ይላሉ :

" ﻟﻴﻠﻘﻴﻦ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﺭﺑﻪ ﻳﻮﻡ اﻟﻘﻴﺎﻣﺔ ﻓﻴﻘﻮﻝ ﻟﻪ: ﺃﻟﻢ ﺃﺳﺨﺮ ﻟﻚ اﻟﺨﻴﻞ ﻭاﻹﺑﻞ ﺃﻟﻢ ﺃﺫﺭﻙ ﺗﺮﺃﺱ ﻭﺗﺮﺑﻊ؟ ﺃﻟﻢ ﺃﺯﻭﺟﻚ ﻓﻼﻧﺔ ﺧﻄﺒﻬﺎ اﻟﺨﻄﺎﺏ, ﻓﻤﻨﻌﺘﻬﻢ ﻭﺯﻭﺟﺘﻚ"
📗 صحيح ابن حبان : 7367

«.. በእርግጥ የቂያማ ቀን አንዳቹ ከጌታው ጋር ይገናኛል .. ከዛም ጌታውም ይለዋል : ግመልና ፈረስን አላመቻቸውልህም ?! የበላይ ሆነህ እንድትመራ አልተውኩህም ? እንትናን አልዳርኩህም ?! ጠያቂ ሁሉ ጠይቋት..እነሱን ከልክዬ አንተን ዳርኩህ..»

ይሄን ውለታን ጌታው የሰጠው አላህን ያመስግን ውለታውንም ይጠብቅ ። ለጥያቄውም መልስ ያዘጋጅ ።
ያልተሰጠው ደግሞ እንዲሰጠው አላህን ከችሮታው ይጠይቅ ☺️

https://www.tg-me.com/mededulhabib
ዛሬ ከመግሪብ ቡኃላ ተፍሲር ደርስ ይኖረናል ቢኢዝኒላህ

ቦታ : ጠሮ- ዑስማን ቢን ዐፋን መስጊድ

አህለን ወሰህለን
https://www.tg-me.com/mededulhabib
Live stream started
2024/05/29 05:49:01
Back to Top
HTML Embed Code: