Telegram Web Link
††† መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላት †††

@MEHERENI_DNGL

††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን †††

††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ #አውሴ ይባላል:: ዘመኑ #እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና #ሊቀ_ነቢያት_ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ: ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::

ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን ኢያሱ ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው::

ኢያሱ ማለት " #መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:-
1.ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል: ምድረ ርስትን አውርሷል::
2.ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው::

ቅዱስ ኢያሱ በበርሃው ለዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዞታል (አገልግሎታል): እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ #ደብረ_ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን: ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::

††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ:
¤ሕዝቡን አሻግሮ:
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ:
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ:
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ:
¤ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::

የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዛን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል: በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚሕች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ::

ሰባት #አሕጉራተ_ምስካይ(የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ:- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::

ይህችውም የቅድስት #ድንግል_ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው #አባ_ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት::

ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::

††† ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ †††

††† አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው::

ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው::

ጌታችንን እስከ እግረ #መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል:: ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው።

ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል::

ሶስት መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል::

††† እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
¤ወንጌላዊ
¤ሐዋርያ
¤ሰማዕት ዘእንበለ ደም
¤አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
¤ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
¤ወልደ ነጐድጉዋድ
¤ደቀ መለኮት ወምሥጢር
¤ፍቁረ እግዚእ
¤ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
¤ቁጹረ ገጽ
¤ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
¤ንስር ሠራሪ
¤ልዑለ ስብከት
¤ምድራዊው መልዐክ
¤ዓምደ ብርሃን
¤ሐዋርያ ትንቢት
¤ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
¤ኮከበ ከዋክብት

††† በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ #ማርያም_ባውፍልያ: ከአባቱ #ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች::

††† አባ ሙሴ ዻዻስ †††

እሥራኤላዊ ሲሆኑ ከአቡነ #ሰላማ ቀጥለው የመጡ የሃገራችን ዻዻስ ናቸው:: ፍጹም ገዳማዊና ትጉህ: ባለ ረዥም ዕድሜ ጻድቅም ናቸው::

ገዳማቸው #ወሎ ውስጥ ቢገኝም አስታዋሽ ያጣ ይመስላል:: መናንያኑ ለዕለት እንኩዋ የሚቀምሱት አጥተው ሲቸገሩ መመልከቱ እጅግ ያማል::

††† በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር:: ቸሩ ጌታ ስም አጠራራቸው ካማረና ከከበረ ወዳጆቹ በረከትን ያሳትፈን::

††† መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኢያሱ ወልደ ነዌ (ነቢይና መስፍን)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ልደቱ)
3.ቅዱሳን ዘብዴዎስና ማርያም ባውፍልያ
4.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት
5.አባ ሙሴ ዻዻስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

††† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" †††
(ኢያሱ. 24:14)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

በየዕለቱ ገድለ ቅዱሳን ፣ ምስባክ ፣ ምክረ አበው እና የተለያዩ ኦርቶዶክስ ነክ ነገሮች ለማግኘት ከታች ያለው Link ይንኩት ከዛን join በሉት እግዚአብሔር ሀገራችን ከከፉ ነገሮች ይጠብቅልን !

#መሐርኒ ድንግል
👇👇👇👇
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
በነገው ዕለት የሚነበበውን ምስባክ እና ገድለ ቅዱሳን እናቀርባለን ይጠብቁ !
‹‹‹‹ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤››››

መስከረም 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

@MEHERENI_DNGL

+" ቅድስት ሐጊያ ሶፍያ "+

+ዘመነ ሰማዕታት በሚል በሚታወቀው 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ብዙ ቅዱሳት እናቶቻችን ስለ ፍቅረ ክርስቶስ አንገታቸውን ሰጥተዋል:: አንዳንዶቹ ደግሞ ሕይወታቸው እጅግ የሚያምር ነበር:: ከእነዚህ ቅዱሳት እናቶቻችን አንዷ ዛሬ የምናከብራት ሐጊያ ሶፊያ ናት::

+በዚህ ስም ከሚጠሩት አንዷ ስትሆን በቀደመ ሕይወቷ ክርስቶስን አታውቅም ነበር:: ጣዖትን የሚያመልኩ ወላጆቿ አሳድገው አጋቧት:: ከትዳሯም 2 ቡሩካት ሴቶች ልጆች ወልዳለች:: ስማቸውም አክሶስናና በርናባ ይባላል:: ልጆቿ ልብ እያገኙ በሔዱ ጊዜ ቅድስት ሶፍያ ስለ እውነተኛው አምላክ ትመራመር ገባች::

+በወቅቱ የነበሩ ብዙ ሃይማኖቶችን መዘነች:: ከክርስትና በቀር ግን ሌሎቹ ሚዛን እንደማይመቱም አስተዋለች:: "እውነኘተኛው አምላክ ሆይ! ምራኝ: እርዳኝም" ስትል ጸለየች:: መድኃኔ ዓለም ለጠሩት አያሳፍርምና ፈጥኖ በጐውን ጐዳና አሳያት::

+ድኅነት ለልጆቿም ይሆን ዘንድ ሁለቱንም ጠርታ ስለ ክርስትና አማከረቻቸው:: ደስ ብሏቸው ተቀበሏት:: እርሷም ጊዜ ሳታጠፋ ወደ ዻዻስ ሒዳ ማሕተመ ክርስትና: ሃብተ ውልድናን ትቀበል ዘንድ ከልጆቿ ጋር ተጠመቀች:: በቅድስናና ደስ በሚያሰኝ አኗኗርም እስከ መከራ ቀን ቆየች::

+የመከራ ጊዜ ሲደርስም ልጆቿን ጠርታ "ስለ ክርስቶስ ፍቅር እንሙት" አለቻቸው:: ቡሩካቱ አክሶስናና በርናባም ደስ እያላቸው "እሺ" አሏት:: ወዲያውም በመኮንኑ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ከመካድና ከስቃይ ሞት የትኛውን እንደሚመርጡ ቢጠየቁ እነርሱ መሞትን መረጡ:: ወደ እሥር ቤትም ከተቷቸው::

+ቅድስት ሶፍያ 2 ልጆቿ ይጸኑላት ዘንድ አዘውትራ ገድለ ሰማዕታትን እና ክብራቸውን ትተርክላቸው ነበር:: በተለይ የታላቁዋን አንጌቤናይት (እመቤት) ሶፍያንና የ3 ልጆቿን (ዺስጢስ: አላዺስና አጋዺስ) ተጋድሎ እየነገረች ታጸናቸው ነበር::

+ከእሥር በኋላ ግርፋት ታዞባቸው እናት ራቁቷን ስትገረፍ መልአክ ወርዶ ሲጋርዳት ልጆች በማየታቸው ደስ አላቸው:: ቅድስት ሐጊያ ሶፍያና 2 ልጆቿ እጅግ የበዛ ስቃይን ስለ ቀናች እምነት ተቀበሉ:: ምላስ እስከ መቆረጥም ደረሱ:: በመጨረሻ ግን በዚህች ቀን ተገድለው አክሊለ ሰማዕታትን ገንዘብ አደረጉ::

+የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የሁሉን ቅዱሳን ቤት ሠርቶ የእርሷን በመዘንጋቱ ለራሱ ባሰራው ቤተ መንግስት ላይ ተአምር ታይቷል:: ለ3 ያህል ጊዜ ስሙን ሲያስቀርጽ መልአክ እየወረደ ይፍቀው: የሶፍያንም ስም ይጽፈው ነበር::

+በመጨረሻም ንጉሡ ልጁን እስከ መገበር ደርሶ ቤተ መንግስቱ የቅድስት ሶፍያና የ2 ልጆቿ ቤተ ክርስቲያን ለመሆን በቅቷል:: ምንም ለ3 ጊዜያት ያህል ሙሉ እድሳት ቢደረግለትም ዛሬ አሕዛብ የያዙትን ይህንን ቅርስ ንጉሡ የሠራው ከ1700 ዓመታት በፊት ነው::

+" ቅዱስ ማማስ ሰማዕት "+

+የሰማዕቱ ወላጆች ቴዎዶስዮስና ታውፍና ሲባሉ ማማስ የሚለው የስሙ ትርጉም 'ዕጉዋለ ማውታ - እናት አባቱ የሞቱበት' ማለት ነው:: ለምን እንደዚህ ተባለ ቢሉ:- በዘመነ ሰማዕታት ስደት በሆነ ጊዜ ወላጆቹ ይዘውት ተሰደው ነበር:: ማምለጥ ባይችሉ ይዘው አሠሯቸው::

+በእሥር ቤትም ከስቃዩ ብዛት 2ቱም ልጃቸውን ማማስን እንዳቀፉት ሕይወታቸው አለፈች:: ሕጻኑ ሲያለቅስ የተመለከተች አንዲት ሴትም ራርታ እነርሱን አስቀብራ: እርሱን አሳድጋዋለች:: ስሙንም 'ማማስ' ብላዋለች::

+ቅዱሱ ባደገ ጊዜ የወላጆቹን ጐዳና በመከተሉ ተይዞ ለፍርድ ቀረበ:: ክርስቶስን አልክድም በማለቱም ብዙ ስቃይን አሳልፎ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆኗል:: ቅዱስ ማማስ ከዐበይት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በአንበሳ ጀርባ ላይም ይቀመጥ ነበር::

+" አቡነ አሮን መንክራዊ "+

@MEHERENI_DNGL
+ኢትዮዽያውያን ጻድቅ አቡነ አሮን በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ኢትዮዽያዊ ሲሆኑ በገዳማዊ ሕይወታቸው: በሐዋርያዊ አገልግሎታቸውና ነገሥታቱን ሳይፈሩ በመገሰጻቸው ይታወቃሉ:: በተለይም ሕይወታቸው በተአምር የተሞላ ስለነበር 'አሮን መንክራዊ' (ድንቅ አባት) ተብለው ይጠራሉ::

+አንዳንድ ጊዜም 'አሮን ዘመቄት /ዘደብረ ዳሬት/' በሚልም ይጠራሉ:: የአቡነ አሮን ወላጆች ገብረ መስቀልና ዓመተ ማርያም የሚባሉ ሲሆን ከልጅነታቸው ጀምረው በቅዱስ ቃሉ የታነጹ ነበሩ:: ምናኔን በደብረ ጐል: ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጀምረው ብዙ ገዳማትን መሥርተዋል:: በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል::

+ለወንጌል አገልግሎት በወጡበት ጸሐይን አቁመው: ሕዝቡን ድንቅ አሰኝተዋል:: እንኳን ሰዉ ይቅርና አጋንንትም ያደንቁዋቸው ነበር:: ነገሥታቱንም ስለ ኃጢአታቸው በገሰጹ ጊዜ ራቁትነት: እሥራት: ግርፋትና ስደት ደርሶባቸዋል::

+ጻድቁ ከብዙ ተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን ወሎ መቄት ውስጥ በሚገኘው ገዳማቸው ዐርፈው ተቀብረዋል:: ገዳሙ እስካሁን ያለ ሲሆን ድንቅ ጥበበ እግዚአብሔር የሚታይበት ነው:: ጣራው ክፍት ሲሆን ዝናብ አያስገባም::

+" አፄ ልብነ ድንግል "+

+እኒህ ንጉሥ ኢትዮዽያን ለዓመታት (ከ1500 እስከ 1532 ዓ/ም) ቢያስተዳድሩም 15ቱ ዓመት ያለቀው በስደት ነው:: ከደጋጉ አፄ ናዖድና ንግሥት ወለተ ማርያም ተወልደው: በሥርዓቱ አድገው ቢነግሡም: በክፉ መካሪዎች ጠንቅዋይ ወደ ቤታቸው ገብቶ ሃገሪቱን ለመከራ ዳርጉዋታል::

+ዛሬም ድረስ ጠባሳው ያለቀቀው የግራኝ ወረራ ለ15 ዓመታት ሃገሪቱን ያለ ካህንና ቤተ ክርስቲያን አስቀርቷት ነበር:: ብዙ ክርስቲያኖችም ሰልመው ቀርተዋል:: አፄ ልብነ ድንግል ግን ደብረ ዳሞ ገዳም ውስጥ ገብተው ንስሃ ጀመሩ: አለቀሱ: ተማለሉ::

+እመቤታችን ተገልጣም "ይቅርታን በነፍስህ እንጂ በሥጋህ አታገኝም" አለቻቸው:: እርሳቸውም ሱባኤውን ቀጥለው: 'ስብሐተ ፍቁርን': 'መልክአ ኤዶምን' የመሰሉ መጻሕፍትን ደርሰው በዚህች ቀን በ ዓ/ም ዐርፈዋል:: እኛ ክርስቲያኖችም እናከብራቸዋለን::

+የቅዱሳኑ አምላክ የወዳጆቹን ፈተና አስቦ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቡንም ከስደት ይሰውርልን:: ከበረከታቸውም አይለየን::

+መስከረም 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
2.ቅዱሳት አክሶስናና በርናባ
3.ቅዱስ ማማስ ሰማዕት
4.ቅዱሳን ቴዎዶስዮስና ታውፍና
5.አቡነ አሮን መንክራዊ
6.አፄ ልብነ ድንግል

++"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን:: +"+ (ሮሜ. 6:5)

‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl

Follow
👇👇👇
http://tiktok.com/@mehereni_dngl
በነገው ዕለት ​መስከረም 05/01/2013 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፴፱፥፭(39፥5)
ብዙኅ ገበርከ እግዚኦ አምላኪየ መንክረከ
ወአልቦ ዘይመስሎ ለሕሊናከ
አይዳዕኩ ወነገርኩ ወበዝኀ እምኁልቍ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፩፥፲፭-፳፭(1፥15-25)
ዮሐንስ ሰማዕቱ በእንቲአ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ጢሞቴዎስ ፩ ም ፭፥፩-፯(5፥1-7)
ሊቃናተ ኢታመጕጽ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፫፥፭-፲(3፥5-10)
ወከማሁ ትካትኒ ቅዱሳት አንስት…



👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፮፥፰-፲፮(16፥8-16)
ወሐሊፎሙ እምነ ሚስያ…


📜ምስባክ ዘቅዳሴ

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ
ወትቀወወም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት


👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፭ ቊ. ፱

፱ የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።


📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፫ ቊ. ፴፩ - ፵፬

፴፩ ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ። መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤

፴፪ እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፥ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።

፴፫ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ። መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።

፴፬-፴፭ ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም። በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።

፴፮ በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው። የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።

፴፯ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው። መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤

፴፰ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤

፴፱ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።

፵ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።

፵፩ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥

፵፪ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

፵፫ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

፵፬ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።


📜ቅዳሴ


👉ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl

follow
👇👇👇
http://tiktok.com/@mehereni_dngl
05 meskerem awalide nigest.wma
898.5 KB
በነገው ዕለት መስከረም 05/01/2013 ዓ.ም

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፴፱፥፭(39፥5)
ብዙኅ ገበርከ እግዚኦ አምላኪየ መንክረከ
ወአልቦ ዘይመስሎ ለሕሊናከ
አይዳዕኩ ወነገርኩ ወበዝኀ እምኁልቍ

📜ምስባክ ዘቅዳሴ

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ
ወትቀወወም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት

📜ቅዳሴ


👉ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl

Follow
👇👇👇
http://tiktok.com/@mehereni_dngl
Forwarded from 𝓟𝓪𝓫𝓵𝓸 via @SuperQualitybot
ነይ ነይ እምዬ ማርያም 🥰

❤️ ለኦርቶዶክሳውያን ምርጥ ቻናል ነዉ
join በማለት ቤተሰብ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።መዝሙሮቹ በkb size ስለሆኑ ምንም ካርድ አያሳስብም።መዝሙር, መዝሙሮች በፅሁፍ ,የመዝሙር ጥናቶች መፅሀፍ ቅዱስ በትረካ ሁሉም አለን ተቀላቀሉ👇
                                                        @ney_ney_emye_maryam
✞ እሰይ እልል በሉ ✞
የመዝሙር ግጥሞች
​​እሳይ እልል በሉ

እሰይ እልል በሉ
ተገኘ መስቀሉ (፪)

የጥል ግድግዳ - አበባ -የፈረሰበት -አበባ
ሰው ከእግዚአብሔር ጋር -አበባ -የታረቀበት -አበባ
የእግዚአብሔር ልጅ - አበባ -የነገሰበት -አበባ
የሞት አበጋዝ - አበባ -የወደቀበት- አበባ
አዝ=====
አይሁድ በቅናት -አበባ -መስቀሉን ቀብረው - አበባ
ቢከድኑት እንኳን - አበባ -በቆሻሻቸው - አበባ
ጌታን መቃወም - ስለማይችሉ - አበባ
ይኸው ተገኘ - አበባ -ወጣ መስቀሉ አበባ
አዝ=====
ደጉ ኪራኮስ - አበባ -ሽማግሌው -አበባ
እሌኒን መራ - አበባ - በደመራው - አበባ
ጌታ በሱ ላይ - አበባ - በመሰቀሉ - አበባ
ጢሱ ሰገደ - አበባ - ወደ መስቀሉ - አበባ
አዝ=====
የእምነት ምልክት - አበባ - መስቀል ነውና - አበባ
ተራራው ሜዳ - አበባ - ሆነ እንደገና - አበባ
እንደ ተነሳው - አበባ -ጌታ እንደቃሉ - አበባ
ከጉድጓድ ወጣ - አበባ - እፀ መስቀሉ - አበባ
አዝ=====
እኛም በመስቀል - አበባ -እንመካለን - አበባ
በእግዚአብሔር ጥበብ - አበባ -መች እናፍራለን - አበባ
ሞኝነት እንኳን - አበባ -ቢሆን ለዓለም - አበባ
ኃይል እፀ ወይን ነው - አበባ - ለዘላለም - አበባ
አዝ=====
ግድግዳው ፈርሷል -- አበባ - የልዩነቱ - አበባ
ምድርና ሰማይ - አበባ - ሆኑ እንደ ጥንቱ - አበባ
ነፍስና ስጋ - አበባ - በሱ ታርቀዋል - አበባ
ሕዝብና አሕዛብ -አበባ - ወንድም ሆነዋል - አበባ

መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አበበ ታዬ

ከ የመዝሙር ግጥሞች ቻናል የተወሰደ

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
🌼እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ !🌼

መሐርኒ ድንግል

በሰላም እና በጤና ለሚመጣ ዓመት ያድርሰን !
እግዚአብሔር ሀገራችንን ሰላሟን ይስጣት !

አዲስ bot ላስተዋውቃችሁ ስሙም Nice creative ይባላል እና ለግሩፕ ወይም ለቻናል የሚሆኑ መንፈሳዊ እና አለማዊ logo በነፃ የሚሰራ ነው እና ሊንኩ 👉 @nice_creative_bot


🌼መልካም በዓል 🌼


@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ " ጸሎተኛው ፣ ደጉ፣ ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል " ብሏል።

ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ከዚህ ዓለም ድካም እንዳረፉ ተገልጿል።

የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ተወስኖ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
@mehereni_dngl
Forwarded from ስልክ መግቫና መሸጫ (𝓟𝓪𝓫𝓵𝓸)
ከ5k በላይ የሆነ የኦርቶዶክስ የቻናል ባለቤቶች wave መግባት የምትፈልጉ @kingo8 አናግሩኝ

@kingo8
2024/06/16 08:33:36
Back to Top
HTML Embed Code: