ከራስ ...ለራስ... የተፃፈ ደብዳቤ!
ለተከበርከው ወድ እኔ እንዴት ከረምክ?...
ዛሬ ለውጥ የምትጀምርበት ልዩ ቀንህ ነው። መጪው ምን ይዞ እንደሚመጣ አይታወቀም፣ አንተንም ምን እንደሚጠብቀህ በእርገጠኛነት አላውቅም፣ ነገር ግን ዕቅዶች አሉህ፣ ልታሳካቸው የሚገቡ ሕልሞች እና ግቦች አሉህ።
እስከዛሬ ድረስ ለነበረህ ፅናት፣ ታጋሽነት፣ አይበገሬነት እና ለፈፀምከው አኩሪ ጀብድ ከልቤ አደናቆቴ ይድረስህ።
አምናለሁ ጥሩ ተዋጊ ነበርክ!
በትግልህ ፅና ደግሞም በብርታትህ ቀጥልበት፣ ምክንያቱም ለህልምህ እውን መሆን በምታደርገው ጥረት ሳቢያ ደስታ እና ሰላም አንተ ጋር ውለው ያድራሉ።
አየኽ! ከጠነከርክ አለም የምትሰጥህን ብቻ እየተቀበልክ ከመኖር ወጥተህ አንተ የምትፈልገውን በማግኘት ትርጉም ያለው ህይወትን መምራት ትችላለህ።
ውድ እኔ!...
አየህ እንዲህ ህይወትህን በሥርዓት መምራት ስትጀምር በሌሎች ላይ መተማመንህ ይቀርና በራስህ መቆም ትጀምራለህ።
በህይወትህ የተለያዩ ሰዎች እንደሚመጡ እና እንደሚሄዱ ተምረሃል፣ በዛው ልክ ለሌሎች ፍቅርን ለመስጠት ስታስብ በመጀመሪያ እራስህን በፍቅር መሙላት እንዳለብህ እንዳትዘነጋ።
ውዴ!...
እራስህን በበቂ ሁኔታ ካልወደድክ እንደምንስ ሌሎችን መውደድ ይቻልሃልን?
በእርግጥ አንዳንዴ፣ ለራስህ በፈጠርከው ባዶ ህልም የቀን ቅዠት ውስጥ ከመስመጥ ይልቅ ነባራዊውን የገሀዱን አለም በማስተዋል ለመገንዘብ መሻት በእጅጉ ይጠቅምሃል።
አየህ ውዴ!
ላጋጠሙህ መጥፎ ገጠመኞችህ የአንተ ድርሻ የሚናቅ ባይሆንም ግን መጭው ጊዜ ለተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ራስህን ተጠያቂ በማድረግ የምትቆዝምበት ሳይሆን ለራስህ የተሻለውን ሁሉ ለማድረግ አሀዱ ብለህ የምትጀምርበት ጊዜ ነው።
ውድ እኔ !...ተመልከት
እስካሁን ባለው ትግልህ እዚህ ደርሰሀል...ነገር ግን ጥያቄው "ላንተ የሚገባው ይሄ ብቻ ነው ወይ?" ነው።
ስለዚህ ከአሁን ጀምረህ ለራስህ እወቅበት፣ ገና ብዙ ይቀርሀል እና በጭራሽ ተስፋ እንዳትቆርጥ፣ ዛሬ አንድ እርምጃ ወደፊት የምትራመድበት ቀን ነው እናም በቁርጠኝነት እግርህን አንሳ፣... ማከናወንህንም ቀጥል።
አበጀህ!
ተላከ "ከትላንት የተሻለውን ህይወት ከምኖረው እኔ!"
ጥበብ እና ማስተዋል ለሰው ልጆች ሁሉ!
ሣሙኤል ተክለየሱስ (ዓለም አቀፍ የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
@melkam_enaseb

JACK MA
በቻይና ውስጥ እጅግ ባለጸጋ የሆነው “ጃክ ማ” ሲሆን 39 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት አለው።
ጃክ ማ እንዲህ ይላል፡- ‘’ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም!
አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል። ምክንያቱም ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ እና ህይወት የሚቀይረው ይህ እንደሆነ ስለማያውቁ ነው።
ሰዎችን ለድህነት ከሚዳርጉት ነገሮች አንዱ ከግል ስራ (ቢዝነስ) የሚመጡትን እድሎች ማየት አለመቻላቸው ነው። ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት መሆኑን ነው። ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራትን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል!
እውነት ነው የወር ደሞዝ ከድህነት ይጠብቅሃል። ነገር ግን ሀብትን እንዳታገኝ ያደርግሃል?
በህይወቴ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት የሚሰራ ተቀጣሪ ሰው ሀብታም ሆኖ አይቼ አላውቅም።’’ ይላል ጃክ ማ።
እውነት ነው እኛም አገር ያለው ነባራዊ እውነታ ይሕ ነው። ምክንያቱም ተቀጥረህ በምታገኘው የወር ደመወዝ ሀብት፣ ጥሪት፣ ቤት እና ራስህን ለውጠህ ሌላ ሰው መርዳት አትችልም። እርግጥ ነው የወር ደመወዝ ሲኖርህ የምትፈልገውን ማድረግ ባትችልም በገቢህ ልክ መኖርን ትለምደዋለህ።
ለማንኛውም በሥራ ፍለጋ ጊዜ ከማባከን በትንሹም ቢሆን የግል ስራ የምትጀምሩበትን የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።
(Getu Temesgen)

ስጦታ የአእምሮ ጤና እንክብካቤ እና የሱስ ማገገሚያ ማዕከል!
በምስሉ ላይ የምታዩት አንዲት ታካሚ ህክምናውን ከማግኘቷ በፊት እና ካገኘች በኋላ ያለውን ልዩነት የገለጸችበት ድንቅ ጥበብ ያሳያል።
ሙሉ ስሜትን ለመግለጽ ቃላቶች አቅም በማይኖራቸው ጊዜ።
#sitota
#Artherapy
አድራሻ: ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 9፣ በጦር ሀይሎችና በቶታል (3ቁጥር ማዞሪያ) መካከል።
ስልክ: +251 11 369 28 18
+251 11 369 27 74

ለአዕምሮ ጤና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
የሰው ልጅ ልቡን ሲያመው አዕምሮው ልብህን አሞሃል ሃኪም ቤት ሂድ ይለዋል። ሌሎች የሰውነት ክፍሉን በአንዳች ምክንያት ጤናው የተጓደለ ሲመስለውም ለችግሩ መላ እንዲፈልግለት አዕምሮው ይወተውተዋል።
አእምሮውን ሲታመም ግን ታመሃል ብሎ የሚነግረው አይኖርም። በዚህም ምክንያት የህክምና ድጋፍ ለማግኘት ይቸገራል።
ምክንያቱስ? ቢሉ የተጓደለውን ነገር ዐውቆ እና ተረድቶ የሚናገረለት አዕምሮው ራሱ ችግር ላይ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ችግሩን የሚያውቅለት እና የሚረዳለት ሌላ ወዳጅ የሆነ የሚገነዘብለት አካል ያስፈልገዋል ማለት ነው።
በአለም ጤና ድርጅት ትርጓሜ የአዕምሮ ጤናን "Mental health is a state of well-being in which an individual can realize his or her own abilities, interact positively with others, cope with the stressors of life and study, work productively and fruitfully, and contribute to his or her family and community.” ይለዋል። ይህን ማድረግ ሲሳነው ነው የአእምሮው ጤንነት ጥያቄ ውስጥ የሚወድቀው።
በአገራችን ቁጥሩ ቀላል የማይባል ሰው የአዕምሮ ህመም ተጠቂ እንደሆነ አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ። (Research Gate በኢትዮጵያ በአዋቂዎች ዘንድ 18 በመቶ በልጆች ደግሞ 15 በመቶ የአእምሮ ህመም ተጠቂ አለ ይላል)።
አንድ ወቅት ደግሞ የተጠና የ common mental Disorder ን 27 በመቶ በሚል ተጠቅሶ ነበር።
በአገራችን ስለ አዕምሮ ህመም እውቀት እና ግንዛቤ እምብዛም በመሆኑ ምክንያት ችግሩ በስፋት ሊታወቅ አልቻለም። ለዚህም ምክንያት አንዱ በዘርፉ የተሰማሩ የሰለጠኑ ባለሙያዎች አለመኖር ትልቁ እንደሆነ ይታመናል።
አሁን ላይ ያሉት የባለሙያዎች ቁጥር Psychiatrists 63 ,Psychiatric Nurses 525 ,Occupational Therapists 1, Psychologists engaged in clinical services 14 ,Social workers engaged in clinica services 3 መሆናቸውን ነው አንዳንድ ቦታ በመረጃ የተጠቀሱት።
ይህ ቁጥር የሙያተኞች ቁጥርን በጣም አነስተኛ መሆኑን ይጠቁማል። ከዚህ የጨመረ እንኳን ቢሆንም ብዙ የራቀ ግን አይደለም።
አብዛኛው ህሙማን የህክምና አገልግሎት ሳያገኙ እና ችግሩ ሳይታወቅላቸው የተጎዱ ራሳቸውን የሚያጠፉ ብሎም ሌላውን ስው የሚጎዱ ብዙዎች ናቸው።
ማኅበረሰቡም ታማሚውን ሰው ከማገዝ ይልቅ" ባህርይው ነው! እብድ ነው! ጨልሏል! ንክ ነው!" እያለ ችግሩን ያባብሰዋል።
እነዚህ ህሙማን ራሳቸው እርዳታ ፈላጊ ሆነው ሳለ እንደ ጤነኛ ሰው በተለያየ ሁኔታዎች ከፍተኛ የሆነ የአእምሮ ብቃትን የሚጠይቅ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው ምክንያት ምርት እና አገልግሎት ላይም የሚያደርሱት አሉታዊ ጫና ነገሩን ከባድ ያደርገዋል።
የአእምሮ ጤና ከሌለ ጤና የለም!!!
(Kefelegn Hailu ZeBihere Sew)
#PsychAddis

ፒቮታል ሪስፖንስ ትሪትመንት/ Pivotal Response Treatment (PRT)
ይህ የህክምና (የቴራፒ) አይነት ጨዋታን መሰረት ያደረገ እና በልጆች አነሳሽነት እና መሪነት የሚካሄድ ሲሆን፤ የአፕላይድ ቢሄቪየር አናላይሲስ (Applied Behavior Analysis (ABA) መርሆችን መሰረት አድርገው ከተዘጋጁት የባህሪ ህክምና አይነቶች መካከል አንዱ እና፤ በአሁኑ ጊዜ በዘርፉ በስፋት በማገልገል ላይ ያለ የባህሪ ህክምና አይነት ነው፡፡
የዚህ የባህሪ ህክምና ግቦች ናቸው ከሚባሉት ውስጥ፡-
-የተግባቦት እና የቋንቋ ክህሎትን ማሳደግ
- አዎንታዊ (positive) የሆነ ባህርይን ከፍ ማድረግ
- አላስፈላጊ የሆኑ እራስን የማነቃቂያ (self-stimulatory) ባህሪዎችን እንዲቀንሱ ማድረግ ይገኙበታል፡፡
ይህን የባህሪ ህክምና የሚሰጡ ባለሞያዎች፤ ከአንድ ልጅ ባህሪዎች መካከል አንድን ባህሪ ብቻ ነጥሎ፤ እዛ ላይ ከመስራት ይልቅ፤ ከልጆች እድገት ውስጥ “ዋና” (“pivotal”) የሆኑ ቦታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ህክምናውን ያካሂዳሉ፡፡ እነዚህ ባለሞያዎቹ በልጆች እድገት ውስጥ አስፈላጊ ናቸው በሚሏቸው ቦታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ፤ የሚሰጡት የ PRT የባህሪ ህክምናዎች፤ ማህበራዊ ክህሎት፣ ተግባቦት፣ ባህርይ እና የልጆች የመማር አቅም ላይ ጉልህ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋል፡፡
የ PRT ዋና (አስፈላጊ) የሚባሉት ቦታዎች፡- Motivation, Response to multiple cues, Initiation of social interactions, Self-management እና Empathy ናቸው፡፡
የማነሳሻ መንገዶች (Motivation) የ PRT ዘዴ ወሳኝ ክፍሎች ናቸው፡፡ ይህ ዘዴ ተፈጥሮአዊ ማበረታቻዎችን የሚጠቀም ሲሆን ለምሳሌ፡- አንድ ኦትስቲክ ልጅ የእንስሳ መጫወቻን ለመጠየቅ ሙከራ ቢያደርግ (“ስጠኝ ቢል”)፤ ለዚህ ሙከራው፤ ሽልማቱን (ማበረታቻውን) ሌላ ተያያዥ ያልሆነ፤ እንደ ከረሜላ ያለን ነገር ከመስጠት ይልቅ፤ የጠየቀውን እንስሳ እራሱ በመስጠት ማበረታታት አስፈላጊ ነው፡፡ በተጨማሪ ይህ ዘዴ፤ ልጆች ትክክል ባይሆኑም፤ ጥሩ ሙከራ ካደረጉ መሸለም (መበረታታት) አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡
PRT ያደገው በስታንፎርድ ዩኒቨርስቲዎቹ Dr. Robert L. Koegel እና Dr. Lynn Kern Koegel ሲሆን፡፡ ከዛ በፊት Natural Language Paradigm (NLP) በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ ይህ የባህርይ የህክምና ዘዴ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ግልጋሎት ላይ መዋል እንደጀመረ ይገለፃል፡፡
የስነ-ልቦና ባለሞያዎች፣ የልዩ ፍላጎት መምህራን እና የንግግር እና ቋንቋ ህክምና ባለሞያዎች፤ የPRT ህክምናን መስጠት የሚችሉ እንደሆኑ ይገለፃል፡፡
የ PRT የባህርይ ህክምና ዘዴ ምን ይመስላል?
እያንዳንዱ ፕሮግራም፤ የግለ-ሰቡን ልዩ-ፍላጎት፤ ግቦችን እና የየእለት ተእለት ክንዋኔዎችን ፍላጎት እንዲያሟሉ፤ መሰረት ተደርጎ የሚዘጋጁ ናቸው፡፡ ቋንቋ፣ ጨዋታ እና ማህበራዊ ክህሎት፤ የዚህ የባህሪ ህክምና ባለሞያዎች፤ ከልጆች ጋር በመደበኛነትም ይሁን ከመደበኛው ውጪ በሚኖራቸው ግንኙነቶች፤ ትኩረት አድርገው የሚሰሩባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡
የልጁን አዎንታዊ ለውጥ መሰረት አድርጎ፤ የእያንዳንዱ የህክምና ክፍለ ጊዜ (session) ትኩረት፤ ሊለዋወጥ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት፤ ይበልጥ ሰፋ ያሉ ግቦችን እና የልጁን ተጨማሪ ፍላጎቶች ለማስገባት ሲባል ነው፡፡ የባህሪ ህክምናው እየተሰጠው ባለ ልጅ ህይወት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ፤ ይህንን የባህሪ ህክምና፤ በልጁ ህይወት በእያንዳንዱ ክፍል በቋሚነት እንዲተገብሩት ይበረታታል፡፡
PRT ብቁ ስለመሆኑ ምንድነው ማረጋገጫው?
PRT ለኦቲዝም በደምብ የተጠና እና የተረጋገጠ የባህሪ የህክምና ዘዴ ሲሆን፡፡ ከሃያ በላይ የሚድረሱ ጥናቶች ይህ የህክምና ዘዴ ኦትስቲክ ለሆኑ ልጆች የተግባቦት ክህሎትን እንደሚያሳድግ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አብዛኞቹ እነዚህ ጥናቶች ህክምናውን አንድ-ለአንድ (ባለሞያው እና ልጁ) ሆኖ ሲሰጥ የተመለከቱ ሲሆን፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በቡድን በትምህርት ቤት መምህራን እና የሰለጠኑ ወላጆች፤ ቤታቸው ውስጥ ሲተገብሩት የተመለከቱ ናቸው ፡፡
በ2017 የጭንቅላት ምስል ውጤቶች ላይ የተሰራ ጥናት ባመላከተው መረጃ፤ የPRT የባህሪ የህክምና ዘዴ፤ ከተግባቦት እና ማህበራዊ ግንኙነት ጋር ተያይዞ፤ የጭንቅላት እንቅስቃሴን እንደሚያሻሽል አረጋግጧል፡፡
(Psychology For Children)

የዘመኑ ወጣት ፈተናዎች!
በዓለም ላይ ያሉ በርካታ ለውጦች፤ ለአዲሱ ትውልድ ጥሩ እድል ብቻ ሳይሆን ጫናም ፈጥሮባቸዋል የሚሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር እና የህፃናት እና ወጣቶች የአዕምሮ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ዮናስ ባህረ-ጥበብ ናቸው።
በተለይ የዋጋ ንረት፣ ኮቪድ ጥሎት ያለፈው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን በዋናነት የሚያነሱት ዶክተር ዮናስ ወጣቱ ሰው ከሰው ከሚያደርገው ግንኙነት ይልቅ ቴክኖሎጂ ላይ ሱሰኛ መሆን እና ግኡዝ ከሆነ ነገር ጋር ያለው ግንኙነት እንደሚያመዝን ይናገራሉ።
«ወጣቱ በዚህ በዓለም ላይ ባለው የመረጃ አቢዮት ምክንያት ሁሉም መረጃ ይደርሰዋል። ጀርመን ሀገር ካለው ወጣት ጋር ተመሳሳይ መረጃ እጁ ላይ አለ። ነገር ግን መሬት ላይ ያለው እውነተኛ ነገር ስልኩ ላይ ከሚያገኘው መረጃ ጋር በጣም የተለያየ ነው። መሬት ላይ ያለው ነገር፣ በቀን አንዴ መብላት የሚቸገር ሰው ያለበት፣ መጠለያ የሌለው፣ መንገድ ላይ ድህነት ተንሰራፍቶ ያለበት እና እውነታው በጣም የተለያየ በመሆኑ የእኛን ሀገር ወጣት ጭንቀት ይፈጥርበታል።»
ወጣቱ ወደ መጠጥ እና እፅ የሚገፋፋው አንድም በዚህ ጭንቀት ምክንያት በሌላ በኩል ደግሞ በመረጃ ፍሰቱ ምክንያት ወጣቱ እየተሳበ እንደሆነ ዶክተር ዮናስ ይናገራሉ፤ «ወጣቱ በቴክኖጂ በጣም ተስቦ የበለጠ ወደ መጠጥ እና እፆች እና ሱሶች ሊሳብ ይችላል»
ወጣቱ ወደተሻለ መንገድ እንዲጓዝ የህፃናት እና ወጣቶች የአዕምሮ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ዮናስ በዋናነት የሚያሳስቡት ወጣቱ ከአለም ላይ የሚያገኘውን እውቀት ተጠቅሞ የሀገሪቷን ሁኔታ ያገናዘበ ትውልድ እንዲፈጠር መሰራት እንዳለበት፣ አዲሱ ትውልድ የበለጠ ኃላፊነት ተሰጥቶት እንዲሰራ ቢደረግ እና በቡድን የሚሰራበት መንገድ ቢመቻች መልካም እንደሆነ ነው። (DW)

#Dailytips
“ማንም ሰው ሳያምንብህ ሊሳካልህ ይችላል፣ ነገር ግን #በራስህ ካላመንክ በፍጹም አይሳካልህም” (William J. H. Boetcker)
መልካም የስራ ሳምንት!

⬆️ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ በተያዘው የትምህርት ዘመን በሶሻል ሳይኮሎጂ እና በዴቨሎፕመንታል ሳይኮሎጂ የሦሥተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ይጀምራል።
በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ለመማር የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አመልካቾች እስከ ጥር 30/2015 ዓ.ም ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።
አመልካቾች የሚከተሉን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-
• ሁለተኛ ዲግሪ ያለው/ያላት
• ተዛማጅ የሥራ ልምድ
• ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ
• የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል
• የሁለተኛ ዲግሪ 3:00 CGPA ያለው/ያላት
• በሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ጽሁፍ ውጤት ቢያንስ 'ጥሩ' ያለው/ያላት
(የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት)

ወላጆች የልጃቸውን እድገት እንዴት መደገፍ ይችላሉ?
ወላጆች የልጆቻቸው እድገት ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። በተጨማሪም የልጆች ተግባቦትን፣ ስሜትን፣ አካላዊና የአእምሮ እድገት ላይ ትልቅ ድጋፍ ማድረግ አለባቸው።
ወላጆች ለልጆቻቸው ማድረግ ያለባቸው ነገሮች፦
- በራስ መተማመን እንዲኖራቸው መደገፍ እና በራስ መተማመናቸውን መገንባት፤
- ልጅዎችን አበረታችና ደጋፊ ይሁኑ ግን አይነቅፉዋቸው፤
- ልጅዎች ችግር እንዲፈቱ እና ውጤታማ የመቋቋም ችሎታን እንዲያዳብሩ ይርዷቸው፤
- ልጅዎች ሀላፊነቶችን እንዲወስዱ እና የፈጠራ ችሎታ እንዲኖራቸው ይፍቀዱ፤
- ከውድቀት እንዲማሩ ይርዷቸው፤
- ልጅዎች ስሜቶችን እንዲያስተካክሉ እርዷቸው፤
- ልጅዎች ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነቶች ወይም ተግባቦቶች እንዲገነቡ ያድርጓቸው፤
- የራሳቸውን ውሳኔዎች እንዲወስኑ ለልጅዎች እድል ይስጧቸው፤
- ለመማር አርአያ መሆን፤
- ልጅዎች የአስተሳሰብ ሂደታቸውን እንዲገልጹ ያበረታቷቸው፤
- ሐቀኛ ይሁኑ እና ከልጅዎ ጋር ግልጽ ንግግር ያድርጉ፤
- ልጅዎ ማለት የሚፈልገውን ወይም የሚናገረውን ያዳምጡ።
Mahlet Azene (Speech and language Therapist)

ደስታን ከየት ነው ምናገኘው?
የወደፊት ማንነታችን የተሻለ እና ደስተኛ አና ሕይወታችን ጣዕም እንዲኖረው ግዜአችንን እና ጉልበታችንን ምን ላይ ብንሰራ የተሻለ ይሆናል?
የሚሉት ከዘመን ዘመን ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ጥያቄዎች በጥናት ለመመለስ እየተሰራ ይገኛል።
ከወደ ምዕራቡ ከእውቁ ሀርቨርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተጠናው ጥናት እና ምርምር ምናልባትም በግል በሰው ሕይወት ዙሪያ ላይ ከተሰሩ ጥናቶች በአለም ደረጃ ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ ከተከወኑት ውስጥ በመሪነት የተቀመጠ ነው፡፡ ይህ ጥናት በ724 ሰዎች ላይ ከወጣትነት ማለትም ከአስራዎቹ እድሜ ክልል ጀምሮ እስከ ጎልማሳነት እና እርጅና እድሜአቸው የቀጠለ ጥናት ነው፡፡ ጥናቱም ለሰባ አምስት (75) አመታት የዘለቀ ከመሆኑም በላይ አሁንም ጥናቱ እንደቀጠለ ነው።
ታዲያ ከዚህ አንድ ምዕተ አመት ሊሞላ ጥቂት እድሜ ከቀረው ጥናት ምን ተገኘ? በተሳታፊዎቹ ሙሉ የሕይወት ሂደታቸው ውስጥ ከወጣትነት እስከ እርጅና ድረስ በሳይንሳዊ ዘዴ ከተቀዳው ምንስ ያስተምረናል?
ከዚህ ከ75 ዓመት በላይ በፈጀ ጥናት የተገኘው ቁልጭ እና ግልጥ ያለው መልስ ጤናማና ደስተኛ አርጎ የሚያቆየን ጥሩ ግንኙነት (Good relationship) ነው፡፡ ከምን ጋር አትሉም? ትልልቅ ሶስት አንኳር ነጥቦችን አስቀምጧል፡፡
1ኛው፦ ግንኙነታችን ከማህበራዊ ጋር ያለው መስተጋብር ሲሆን ከተሳታፊዎቹ ከተሰበሰበው መረጃ ውስጥ ጥሩ የሚባል ማህበራዊ ግንኙነት ሕይወት ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸው ደስተኞች ከመሆናቸውም በላይ በተጨማሪ በአካል፣ በጤንነት እና ከተመዘገበው የእድሜ ጣሪያ በመኖር የተሻለ ሆነው ተገኝተዋል፡፡
በአንጻሩ ግለኛ እና ብቸኛ ሆነው ከተመዘገቡት ተሳታፊዎች በሕይወታቸው የሚያጣጥሙት ደስታ እጅግ ያነሰ ነበር፡፡ ከዚያም በላይ ግን በተለይ ወደ ጎልማሳነት እድሜዎቹ ውስጥ በሚገቡበት ወቅት የአካላዊ ጤናቸው ላይ እና የአንጎል ስርአተ መስተጋብር ላይም አሉታዊ ተፅኖ አሳድረዋል፡፡
እንግዲህ ከሚያሳዝነው ነገር እንደ ዓለም አቀፍ ጤና ድርጅት በቅርቡ ካወጣው መረጃ ውስጥ በአለማችን ከ5 ሰው ውስጥ አንድ ብቸኛነትን ሪፓርት አድርግዋል ይላል፡፡
2ኛው፦ አንኩዋር ነጥብ ከጥናቱ የተገኘውም በብዙ ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ስላለን ወይም ታማኝ የትዳር አጋር ስላለን ሳይሆን ትልቁ ቁም ነገር ያለው በመሀከላችን ያለው የግንኙነቶችን ጥራት (relationship quality) ላይ የወደቀ ነው፡፡ ስለዚህም በአብዛኛው በግጭቶች እና ባለመግባባቶች በስራ፣ በትዳር፣ በትምህርት በሌሎችም ከተከበበ የሚታወከው ሳይኮሎጂካል ጤናችን ብቻ ሳይሆን አካላዊ ጤንነትም ላይ አሉታዊ ተፅኖ ያድርበታል ማለት ነው፡፡
ይህንን ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ከተጠቀሙት የምርምር ዘዴዎች መካከል፡-
በጥናቱ ሙሉ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል በሰማንያ እድሜ ክልል ውስጥ የደረሱትን መረጃ በመያዝ እነዚሁ ሰዎች በጎልማሳነት (ከ 45 በላይ) እድሜ በነበሩበት ሲመሳከር የወደፊት ጤንነታቸውን በተሻለ የተነብይ የነበረው በደማቸው ውስጥ ያለው ኮሌስትሮል አልነበረም፡፡ የሆነው ግን በቀጥታ ተያያዥ ሆኖ የተገኘው ግን የነበራቸው የግንኙነት ጥራት (relationship quality) ነበር፡፡
ከተመዛገቡት መረጃዎቹ ውስጥ አንዱ ደስተኛ ከተባሉት ውስጥ በሰማንያ እድሜ ክልል ውስጥ ከገቡ በኋላ አካላዊ ህመም በሚሰማቸው ወቅት ያሉበት የደስታ መጠን ሲለካ የነበረበት ላይ ወይም ለውጥ ሳያሳይ እዛው ደስታ ደረጃ ላይ ነበሩ፡፡ በተፃራሪው ደስተኛ ካልነበሩት ውስጥ በተመሳሳይ እድሜ (80ዎቹ) ውስጥ ሆነው አካላዊ ሕመም ሲያጋጥማቸው በተጋነነ መልኩ ስሜታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅኖ አድርጎ ታይቷል፡፡
3ኛው፦ ትልቁ አንኳር ነጥብ ጥራት ያለው ግንኙነት የአካላችን ጤንነት ብቻ የጠበቀ ሳይሆን የአንጎላችንንና የእምሯችን ስርዓት-ትግበራም ላይ ጭምር ነበር፡፡ ከዚህም ውስጥ ጥራት ያለው ጥሩ ግንኙነት ውስጥ ካሉት– በችግር በሚያጋጥሟቸው ወቅት ወይም ሰው እንዲደርስልን በሚያስፈልገን ወቅት በርግጠኝነት የደርሱልናል ብለው የሚያምኑት ሰዎች አሉን ያሉት በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉት የላቀ የማስታወስ ክህሎት አስመዝግበዋል፡፡ በተቃራኒው የለንም ያሉት እጅግ ያነሰ ሆኖ ተመዝግብዋል፡፡
ይህም ጤናማ የሆነ ጥሩ ግንኙነት ማለት ከጥል ወይም ከአለመግባባት የፀዳ ብቻ ማለት ሳይሆን ስንቸገር ወይም ሰው ሲያስፈልገን የደርስልኛል ብለን አመኔታ የጣልንበት ግንኙነት መመስረት መቻላችን ነው ማለት ነው እንግዲህ፡፡
ስለዚህ የዚህ ጥናት መልዕክት ጥራት ያለው ጥሩ ግንኙነት የጤናችንና የደስታችን ብሎም የሕይወታችን የጣዕም ምንጭ ነው፡፡ ይህንንም ክህሎት ማካበት የሕይወት ትልቁ ጥበብ ነው፡፡
እናንተስ ይህን የምታነቡት ምናልባት እድሜያችሁ አንበል 18 ወይ 25 ወይ 35 ወይ 50ዎቹ የግንኙነታችን ጥራት ከስራችን ወይም ትምህርት፣ ከጓደኛ ወይም ከትዳር አጋራችን፣ ከቤተሰብ፣ ከተፈጥሮ፣ ከመንፈሳዊነት፣ ከማህበረሰቡ፣ ከራሳችን በጠቅላላ በዙርያችን ካሉ ነገሮች ጋር ያለን የግንኙነት ጥራቱ ምን ይመስላል?
ያፌት ከፈለኝ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት) አብርሆት ሳይኮሎጂካል መአከል
#የጤናወግ

⬆️ Sitota Center for Mental Health Care and Rehabilitation!
Call for CPD training on Quality Improvement (QI)
For all health professionals
To register call: 0913597672
@melkam_enaseb
Call for CPD training on Quality Improvement (QI)
For all health professionals
To register call: 0913597672
@melkam_enaseb
አዲሱ የአልዛይመር መድሃኒት!
ኢሳይ እና ባዮገን በተሰኙ ሁለት የአሜሪካ የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች የተሰራውን «ለካነማብ»/lecanemab/ ወይም በገበያ ስሙ ለኬምቢ /Leqembi/ በመባል የሚጠራውን ይህንን መድሃኒት ትልቅ ስኬት ነው ይሉታል። የብሪታኒያ የዴሜንሽያ ተቋም ተመራማሪ የሆኑት ባርት ዲ ስትሮፐር።
''ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት አልዛይመር በዘር የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን፤ «አሚሎይድ ቤታ» በመባል የሚታወቀው መደበኛ የአንጎል ፕሮቲን የሰዎች ዕድሜ እየገፉ ሲሄድ ብዙውን ጊዜ አሚኖፕሮቲን ወይም አሚሎይድ ወደሚባሉ ጎጂ ቅሪቶች ይቀየር እና በአንጎል ውስጥ ይከማቻሉ። ይህ የጎጂ ህዋሳት ክምችት የነርቭ ህዋሳትን በመግደል እና የአንጎልን ስራ በማደናቀፍ የማስታወስ እና የማገናዘብ ችሎታን ያሳጣል። የአዲሱ መድሃኒት ስራም ሰውነት እነዚህን ንጣፎች እንዲያጸዳ መርዳት ነው።'' -ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት)
https://p.dw.com/p/4MNsd?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

DW
አዲሱ የአልዛይመር መድሃኒት
የህክምና ሳይንስ ተመራማሪዎች ላለፉት 50 ዓመታት ለአልዛይመር ወይም ለመርሳት በሽታ መድሃኒት ለማግኜት በርካታ ምርምሮችን አድርገዋል።በቅርቡ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በሽታውን ያክማል የተባለ መድሃኒት በምርምር መገኘቱን ይፋ አድርገዋል።
ዛሬ ቀንህን እንዴት ጀመርከው?
ዛሬ ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ደስ ብሎህ ፈጣሪህ አዲስ ቀን ስለሰጠህ አመስግነህ ዛሬ የእኔ ቀን ነው፤ እኔ ማድረግ የምፈልገውን አደርጋለው! እኔ እችላለው! እኔ ድንቅ ነኝ! እኔ ከችግሮቼ በላይ ነኝ! ብለህ ነው? ወይስ ኡፍ ደሞ ነጋ ብለህ ችግሮችህን እያሰብክ ተሰባብረህ ነው ቀንህን የጀመርከው?
ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ያለህ የስሜት ደረጃ ነው ቀንህን የሚወስነው፤ መልካም ነገሮችን አስበህ ስትነሳ መልካም ነገሮች ወደ አንተ ይመጣሉ። ስለዚህ ጠዋትህን ደስ በሚል መንፈስ ጀምረህ ቀንህን ብሩህ አድርገው። (ዳዊት ድሪምስ)
የደስታ ቀን ተመኘን!