ብርጭቆው ከባድ ነው ወይስ ቀላል?
አንድ አሰልጣኝ እንዲህ ሲል ለሰልጣኞቹ በመጠየቅ አንዲትን ቀላል የምትመስል፣ ነገር ግን እጅግ ወሳኝ ቁምነገር አስተላለፈ፡- “አንድ ብርጭቆ ውሃ በእጃችሁ ብትይዙት ከባድ ነው ወይስ ቀላል?”
ሁላችንም እንደምንጠብቀው ሰልጣኞቹ በአብዛኛው ቀላል እንደሆነ በመስማማት ገለጹ፡፡ አሰልጣኙም በመመለስ፣ “መልሳችሁ ትክክልም፣ ስህተትም ነው” በማለት ሲያብራራ፣ “ይህንን ውኃ የተሞላ ብርጭቆ ለአንድ ደቂቃ ከያዛችሁት ቀላል ነው፡፡ ለአንድ ሰዓት ከያዛችሁት ደግሞ እየከበዳችሁ ይሄድና እጃችሁን የሕመም ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ሙሉ ከያዛችሁት እጃችሁ ይደነዝዛል፣ ይዝላል፣ እንዲያውም ብርጭቆውን ልትለቁት እስከምትደርሱ ድረስ ልትደክሙና ሊከብዳችሁ ሁሉ ትችላላችሁ”፡፡
የዚህ ብርጭቆ ክብደት ልክ በመጀመሪያ እንደነበረ፣ ከአንድ ደቂቃ በኋላ፣ ከአንድ ሰዓት በኋላና፣ ከአንድ ቀን በኋላ ያው ነው፡፡ እዚህ ጋር ልዩነት ያመጣው ብርጭቆውን በእጃችን የያዝንበት የጊዜ ርዝመት ነው፡፡
መልእክቱ ይሄ ነው፡- የስሜትም ጉዳይ እንዲሁ ነው! ማንኛውም እንደ ጭንቀት፣ መረበሽና ፍርሃት የመሳሰለ ቀላል የተባለ የስሜት ሁኔታ ለጊዜው ምንም ችግር ላይኖረው ይችላል፣ ሆኖም ስሜቱን ለረጅም ጊዜ ስንይዘው ግን መዛላችን፣ መድከማችን፣ መታመማችንና ሕይወት ከአቅማችን በላይ እየሆነ መምጣቱ አይቀርም፡፡
ምናልባት የመኖር ጣእም ያጣችሁ፣ ድብርት የሚጫጫናችሁና የውስጥ (የስሜት) ህመም የሚሰማችሁ አንዳንድ ስሜቶችን ለረጅም ጊዜ እየያዛችሁ ሊሆን ይችላልና አላስፈላጊ ስሜቶችን ገና በትንሽነታቸው ቶሎ ቶሎ ለማራገፍ ሞክሩ!
(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)
@melkam_enaseb

Yetena Weg Clubhouse Discussion!
ከ ዶ/ር እንቁ ደረስ ጋር ለእምሮ ህክምና የሚውሉ መድሃኒቶች ላይ የምናደርገውን ውይይት ይቀላቀሉ።
🗓ሰኔ 18 (በዚህ እሁድ )
⏰ ከ12 ሰአት እስከ ምሽቱ 2 ሰአት
ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ ⬇️
https://www.clubhouse.com/invite/UrVKlxDn

ባህሪያችንና የቀለም ምርጫችን!
ማንኛውንም ነገር የምንመርጠው ከእኛ ባህሪ ጋር የተገናኘ ነገር ስላለው ነው፡፡ ከባህሪያችን ጋር ግንኙነት የሌለውን ነገር ልንመርጥ አንችልም፡፡ ሌሎች ሰዎች ካልመረጡልን በስተቀር፡፡
የቀለም ምርጫችንም እንደዚሁ ከባህሪያችንን ጋር ግንኙነት አለው፡፡ እንደባህሪያችን የምንመርጠው ቀለም ይለያያል፡፡ ጥቂቶቹን እንደምሳሌ እንዘርዝር፡፡
ጥቁር፦ የብዙዎች ምርጫ ነው፡፡ በብዛት ይህንን ቀለም የሚመርጡ ሰዎች የሃላፊነት ሰዎች የሆኑና ቁርጠኛ የሆኑ ሰዎች ሲሆኑ በተጨማሪም በጣም ውድ ነገሮችን የሚወዱ፣ መሳሳት የማይፈልጉና ስልጣን መያዝ ወይም የበላይ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው፡፡
ቀይ፦ ይህን ቀለም የሚመርጡ ሰዎች ሁሌም ማሸነፍ የሚፈልጉ፣ በጣም ቁጡ የሆኑ ሰዎች ሲሆኑ በተጨማሪም ፍቅርን፣ ህይወትን፣ ወሲብን፣ አደጋን፣ ፍጥነትን የሚያመላክት ቀለም ነው፡፡ ከሌሎች ቀለሞች ሁሉ ትልቅ ተጽዕኖ በሰውነታችን ላይ በመፍጠር የመጀመሪያው ነው፡፡
ብርቱካናማ፦ ዘና ማለትን፣ ደስታን፣ ፈጠራን፣ ተነሳሽነትን፣ ስኬትን የሚያመላክት ትርጉም ያለው ቀለም ነው፡፡ እነዚህ ባህሪ ባላቸው ሰዎች ተመራጭ ነው፡፡
ቢጫ፦ ደስታን፣ ተማኝነትን፣ ጎልቶ መታየት መፈለግን፣ እውቀትንና የፀሃይን ትርጉም የያዘ ነው፡፡
አረንጓዴ፦ ተፈጥሮን፣ ውህደትን፣ መታደስን፣ ጥንካሬን፣ ጤናን፣ እድገትን፣ ገንዘብ፣ መረጋጋትንና ደህንነትን የሚያመላክት ቀለም ነው፡፡
ሰማያዊ፦ መታመንን፣ መረጋጋትን፣ እውቀትን፣ ጥልቀትን፣ እውነትን፣ በራስ መተማመንን የሚያመለክት ቀለም ነው፡፡
ነጭ፦ ንጽህናን፣ ፍፁማዊነትን፣ ደህንነትንና የፈጠራን ትርጉም የያዘ ነው፡፡
የቀለማት ትርጉም እንደምንኖርበት አካባቢ ባህልና ወግ የሚለያይ ነገር ሊኖረው ይችላል፡፡
ተመስገን አብይ (የስነ-ልቦና በላሙያ)

የህይወት ግቦች (goals) ማስቀመጥ የሚሰጠው ጥቅም!
በሕይወታችን የት መድረስ እንደምንፈልግ ማወቁ አስፈላጊ ሲሆን፣ ለምን መድረስ እንደፈለግን በውል ማወቅ የበለጠ አስፈላጊ ነው። አንዳንዶቹ ይህን መድረስ ከምንፈልግበት በስተጀርባ ያለውን ምክንያት እውነተኛው ግብ እያሉ ይጠሩታል። የሕይወት አጭር ወይም ረጅም ግብ (goal) ማዘጋጀት ለምን እንደሚጠቅም ባለሙያዎች እንደሚከተለው ያብራራሉ።
1. ፍላጎታችን እና ምኞታችን ይሟላል፦
በሕይወታችን አንድ ነገር ላይ መድረስ ለምን እንደምንፈልግ አስቀምጠን ስንቃኝ፣ ያስቀመጥነው ግብ በእውነትም ያንን ውጤት ሊያመጣልን እንደሚችልና እንደማይችል መመርመር እንችላለን። ስለሆነም በስሜታችን፣ በደስታችን እና በማንነታችን ላይ ለውጥ የሚያመጡ ነገሮች ላይ ብቻ አተኩረን እንድንሰራ ይረዳናል።
2. በሕይወታችን ምን እንደሚያነሳሱን ብሎም እራሳችንን የበለጠ እንድናውቅ ይረዳናል፦
ግቡን አስቀምጠን የሚያመጣልንን ደስታ እና ትርፍ ስናመዛዝን በዚያ ሂደት ከሕይወታችን ምን ማግኘት እንደምንፈልግ ብሎም ደስታችን በምን ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የበለጠ እናውቃለን። ይህም ለበለጠ የእራስ ማስተዋል እና ግምገማ ጥሩ ዕድል ይፈጥርልናል። ወደ ጥሩ የሕይወት አላማም ለመጉዋዝ ማስተካካያወች እንድናደርግ ይረዳናል።
3. ለአእምሯችን ጤንነት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል፦
የሕይወት ግቦችን ማስቀመጥ እና እንደምንደርስባቸው ለራስ መንገር ለአምሯችን ሰላም መሰማት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። አእምሮአችን፣ ወደ ግባችን ለመድረስ ስንሰራ ደስታን ያገኛል፣ በዚህም የተነሳ ስለወደፊት ሕይወታችን ያለን አመለካከት ከፍ እያለ ይመጣል። በዚህም ትልቅ የአእምሮ ሰላም እናገኛለን። (ሰዋስው)

ሜንታል ሄልዝ አዲስ ቀጣዩን ወርሃዊውን ዝግጅቱን ይዞላችሁ መጣ።
ቅዳሜ ሀምሌ 29/2015 ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በአዶር አዲስ ሆቴል “የስብዕና መዛባት ምንድን ነው? እንዴስ ይታከማል?” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲናገሩ ዶ/ር ቢንያም ወርቁን ጋብዟል፡፡
መግቢያ ክፍያ:- ነፃ!!!
ለመታደም በዚህ መስፈንጠሪያ ይመዝገቡ=> https://forms.gle/FJA7iLaXYWXVR1DB8
Mental Health Addis is holding its monthly event on Saturday Aug 5/2023 (Hamle 29, 2015) at Adore Addis Hotel near Atlas at 4:00PM (10:00 local time) on the topic of "What is personality disorder and how does it get treated?
FREE OF CHARGE.
This month’s speaker is Dr Benyam Worku. Please fill out and submit this form using this link https://forms.gle/FJA7iLaXYWXVR1DB8

የድባቴ መንስኤ፣ ምልክቶችና መከላከያ መንገዶች!
አንድ ሰው ከገባበት ሀዘን ወይም ጥሩ ያልሆነ ስሜት በቶሎ መላቀቅ ካልቻለ የድባቴ ስሜት አጋጥሞታል ማለት ይቻላል፡፡
የድባቴ ስሜት በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት ችላ ከተባለ ግን የአዕምሮ ጤናን የሚያውክ ደረጃ የሚደርስ ነው።
የድባቴ ምልክቶች በሁሉም ሰው ላይ አንድ አይነት ላይሆኑ ይችላሉ፤ ደረጃ፣ ቆይታና አስከፊነት እንደየግለሰቡ የድባቴ ሁኔታ ይለያያል፡፡
ሆኖም ተከታታይ የሆነ የሃዘን፣ የንዴት፣ የብስጭት፣ የቁጣና የባዶነት ስሜት፣ የተስፋ ማጣትና ጨለምተኝነት አመለካከት፣ ራስን መውቀስ፣ ዋጋቢስና ረዳት የለሽ የመሆን ስሜት፣ በትንሽ በትልቁ መበሳጨትና ቅብጥብጥነት፣ ለወትሮው በፍቅር ለምናከናውናቸው ተግባራት ፍላጎት ማጣት፣ ድካምና ተነሳሽነት ማጣት የድባቴ ምልክቶች ናቸው፡፡
እንዲሁም አትኩሮት ማጣት፣ ዝንጉነትና ውሳኔ ለመስጠት መቸገር፣ መጫጫን፣ የእንቅልፍ መዛባት ወይም ለረዥም ጊዜ መተኛት፣ ከመጠን ያለፈ መመገብ ወይም የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ራስን ማጥፋት መፈለግና መሞከር፣ በህክምና መታገስ ያልቻለ ራስ ምታት፣ ቁርጠት፣ ቁርጥማትና የምግብ አለመፈጨት ችግር ካጋጠመ ድባቴ መኖሩን ይጠቁማል፡፡
አዕምሮን የሚረብሽ ከባድ የህይወት አጋጣሚ፣ የሚወዱት ሰው በሞት መለየት፣ ከሰዎች ጋር ያለ ሠላማዊ ግንኙነት መናጋት፣ አዕምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ የሆነ ሀሳብና ሁኔታ ሲገጥም፣ ጭንቀት፣ መገለልና የሞራል ውድቀት ለድባቴ ከሌላው ሰው ይልቅ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ያመላክታል።
ድባቴን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት መከተል፣ ከአልኮል፣ ከትምባሆ እና ከአደንዛዥ እፆች መቆጠብ፣ አሉታዊ ሀሳቦችን ከአዕምሮ አስወግዶ አዎንታዊ ጎኖችን ማሰብ መለማመድ፣ በህይወት ውስጥ ለችግሮች ፍፁም የሆነ መፍትሄ እንደሌለ ማስታወስ ናቸው፡፡
እንዲሁም የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለማለፍ በትዕግስት ጠንክሮ መስራት፣ ለሳቅ ለጨዋታ በአጠቃላይ ለመዝናኛ ጊዜ ማበጀት፣ ለሰዎች በጎ ነገር በማድረግ መልካም ወዳጅነትን ማፍራት፣ ጭንቀትና ስጋትን ለቅርብ ሰው ማካፈልን መልመድ ይጠቀሳሉ።
ፍ/ማርያም ተስፋዬ (ሳይኮሎጂስት)

ናርስሲዝማዊ የስብዕና ችግር/ አፍቅሮተ ራስ
ጤናማ የሆነ ራስን መውደድ በራስ መተማመንና ጤናማ የሆነ የውድድር መንፈስን ስለሚያላብሰን ጥሩ ነው::
ራስን መውደድ እንደችግር የሚቆጠረው መቼ ይሆን?
ይህ የስብዕና ችግር ስያሜውን ያገኘው በግሪክ አፈታሪክ ከምትታወቀው ናርሲሰስ ነው::
Diagnostic and statistical Manual አምስተኛው እትም ምልክቶቹን እንዲህ ይገልጻቸዋል፦
1. ከልክ ባለፈ ሁኔታ ራስን የተለዩ፣ የተመረጡ እና ያየሉ አድርጎ ማቅረብ
- ስለራሳቸው በጎነት አብዝተው ያወራሉ ወይንም ያስወራሉ እንዲወራ ይፈልጋሉ:: ራሳቸውን ሲክቡ ሌሎቹን በማጣጣል ጭምር ነው::
2. በእውን ያልሆኑትን በምናባቸው ስኬታማ፣ ተወዳጅ፣ ዝነኛ እንደሆኑ ያስባሉ::
3. የተለየን ነን ብለው እንደማሰባቸው እነሱን ሊረዱ የሚችሉቱ በነሱ ደረጃ ያሉ ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ያስባሉ:: አለመቻላቸውን አምኖ ከመቀበል ይልቅ ሰዎች የነሱን ችሎታ ለመረዳት እቅም እንዳነሳቸው አድርገው ያቀርባሉ::
4. አድናቆትና ውዳሴን አብዝቶ መሻት
- የባዶነት ስሜታቸው እረፍት ስለሚነሳቸው የሌሎችን አድናቆት፣ የልቦናቸውን ባዶነት ለመሙላት አጥብቀው ይሻሉ::
5. የተለየ ክብካቤና አክብሮት እንደሚገባቸው ማሰብ
- ሰልፍ ላይ በተለየ ሁኔታ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ይሻሉ አልያም ሰልፍ ጥሰው ሲገቡ ይታያሉ:: እኮ ለምን ከተባሉ መበሳጨትና ለምን ተነካሁ አካኪ ዘራፍ ማለት ይቀናቸዋል:: እነዚህ ሰዎች ውጭ ውጫቸውን አስደናቂ ባህርይ (superficial charm) ያላቸው መስለው ይታያሉ::
6. ሌሎችን ለራስ ጥቅም መበዝበዝ
- ስራ ወዳድና ታታሪ ቢመስሉም ስለሌሎች ድካምና መዛል ደንታ ስለሌላቸው ሰራተኞቻቸውን ሊበዘብዙ ይችላሉ:: ፍቅረኛቸውን እና ወዳጆቻቸውን ለግል ጥቅም ማስፈጸምያ ሲጠቀሙባቸው ይስተዋላል:: ሰው ምን ይሰማዋል ብሎ ነገር የለም::
7. የሰውን ስሜት ለመረዳት ይቸገራሉ
- ለፍቅረኛቸው ስሜት አልባና ቀዝቃዛዎች ናቸው::
- በታመመ ሰው ፊት ስለጤናቸው መጠበቅ ሊታበዩ ይችላሉ::
- ምናልባትም በልጅነታቸው ያጋጠሟቸው ስነልቦናዊ ቀውሶች የሰዎችን ስሜት እንዳይረዱ (impaired mentalization) አድርጓቸው ሊሆን ይችላል::
8. ቀናተኞች ናቸው /ሌሎች ይቀኑብኛል ብለውም ያስባሉ
- ሌሎች ሰዎች ሲደነቁ ማየት ይከነክናቸዋል::
- እንከን ፈላጊናዎች ናቸው::
- የተሳካላቸውን ሰዎች ያጣጥላሉ::
- በተቃራኒው የሚክቧቸው ሰዎች ይኖሯቸዋል:: እነዚህ የሚክቧቸው ሰዎች ሲነኩባቸው እነሱ የተነኩ ያህል እረፍት ይነሳቸዋል::
9. እብሪተኝነት
- የባዶነት ስሜታቸውን እና ፊት ለፊት ላለማሳየት ይጥራሉ:: ወቀሳን ለሚሰነዝርባቸው ሰው ቂምን ቋጥረው ለበቀል ሊነሳሱና ለማጥቃት ሊሸርቡ ይችላሉ::
መንስኤው ምን ይሆን?
እንደ self psychology አስተምህሮ ሰዎች ሲያድጉ self object ያስፈልጋቸዋል::
- ይህ self object በአግባቡ የሚያየን፣ የሚረዳን፣ ያየብንን አቅም በግብረመልስ መልሶ የሚያንጸባርቅልን እና ሞዴል የምናደርገው ነው::
- ይህን ፍላጎታችንን የሚያሟሉልን ወላጅ/አሳዳጊዎቻችን ናቸው::
- ይህ 'self object' በአግባቡ ኖሯቸው ያላደጉ ልጆች: ያልተቀናጀና(lack cohesiveness) እና መሰረት ያልያዘ ስብዕና ስለሚኖራቸው የማይጨበጥ አይነት ሰዎች ይሆናሉ::
- ባንድ በኩል ያጡትን ትኩረትና ስነልቦናዊ ምልአት ለመቀዳጀት በውጫዊ እሴቶች ማለትም በሃብት በቁንጅና እና በጉልበት የሚታበዩ እና እብሪተኛኞች
- በሌላ በኩል ውስጠታቸው በባዶነት ስሜት የሚናጥ እና በወቀሳዎች ተሰባሪ ሰዎች ሆነው ይገኛሉ::
ናርሲስዝማዊ ስብእና ባላቸው ወላጆች የሚያድጉ ልጆች ወላጆቻቸው የነሱ ተቀጽላ እንደሆኑ በማሰብ የልጆቻቸውን ድክመት እንደራሳቸው አድርገው ስለሚያስቡ በከባዱ ይቀጧቸዋል::
- ልጆቹም ከወላጅ/አሳዳጊያቸው ግምት ላለመውረድ ይኳትናሉ::
- አድገውም በስራና በሌሎች የህይወት መስኮቻቸው ስህተቶቻቸውን አምነው የማይቀበሉ፣ ድብቅ ባህርይ ያላቸው (ስስ ጎናቸው እንዳይታይ) እና ግብረመልስ የማይሹ ጥፋታቸውን የሚሸፋፍኑ ይሆናሉ::
ህክምናው:-
- እነዚህ ሰዎች: ባህርያቸው ለነሱ ልክና አግባብ (egosyntonic) ሰልሆነ ወደ ህክምና እምብዛም ላይሄዱ ይችላሉ:: ከሄዱም ምናልባት ለተጎዳኝ የአእምሮ ህመሞች (ድብርት፣ ደስታን ማጣት፣ ራስን የማጥፋት ስሜት አስቸግሯቸው) ቢሆን ነው::
- ባህርይን በአንድ ጀምበር መቀየር ቢያዳግትም የተወሰኑ የስነልቦና ህክምናዎች ሊያግዙ ይችላሉ::
- በዋነኝነት የስነልቦና ህክምና (ሳይኮአናሊሲስ፣ ሃሳብና ድርጊትን መሰረት ያደረገ ህክምና/cognitive behavioral therapy፤ Mentalization based therapy..እና የመሳሰሉት ናቸው።
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአእምሮ ህክምና ሬዚደንት ሃኪም)

የንዴት መነሻ ምክንያቶች እና መፍትሄው!
ብዙ ሰዎች ተናዳጅና ብስጩ ቢሆኑም የንዴታቸውን መንስኤ ግን በእርግጠኝነት እንደማያውቁት ይነገራል።
ብስጭት እየጨመረ ሲመጣና ሰዎች ስሜታቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው ወደ ንዴት ያመራል። የንዴት መነሻ ምክንያቶች ውስጣዊ እና ውጫዊ በማለት የዘርፉ ባለሞያዎች በሁለት መልኩ ከፍለው ይመለከቱታል።
በእርግዝና ወቅት፣ በድህረ ወሊድ ጊዜ የሚከሰት ውጥረት፣ ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት ውስጣዊ የብስጭት ምክንያቶች ሲሆኑ፤ እውነታዎችን መቀበል አለመቻል፣ ቅናት፣ ወቀሳና አላግባብ የሚሰነዘሩ ትችቶች ውጫዊ ምክንያቶች መሆናቸውን ባለሞያዎች ያነሳሉ፡፡
ከጤና እክሎች በተጨማሪም እንደ ድብርት፣ ጭንቀት እና የአይምሮ እድገት ውስንነት መሰል ስነልቦናዊ ጉዳቶች መንስኤም ሊያጋጠጥም እንደሚችልም ይናገራሉ።
ተናዳጅ እና ብስጩ የሚሆኑ ሰዎች ለእንቅልፍ እጦት፣ ለአይምሮ ህመም እና ለሌሎች የጤና እክሎች አጋላጭ ሲሆን ይስተዋላል ተብሏል፡፡
በመልህቅ የትዳር አማካሪ እና አሰልጣኝ አቶ ጸጋዬ አሰፋ ብስጭት ተፈጥሯዊ መሆኑን በማንሳት ተደራርበው የሚመጡ ችግሮች ሰዎችን ለንዴት እንደሚዳርግ ይናገራሉ። ስሜትን መቋቋም አለመቻል ዋነኛው ችግር መሆኑን በማንሳት፡፡
ምልክቶች፡
በማንኛውም ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ሃሳቦችን መስጠት፣ ችኩል መሆን፣ በንግግር መሃል የድምጽ መጠን መጨመር፣ መናገር አለመቻል፣ የአካል መንቀጥቀጥ፣ የትንፋሽ መቆራረጥ፣ የምራቅ መድረቅ እንዲሁም የሌሎችን ሃሳብ አለመቀበል ምልክቶች መሆናቸውን ባለሞያው ተናግረዋል፡፡
አሉታዊ ጎኖች፡
"መርዝ ከተድፋበት ቦታ ይልቅ የሚቀመጥበትን ቦታ የመመርዝ አቅም አለው" የሚሉት አቶ ጸጋዬ ተናዳጅ አልያም ብስጩ ሰው በመጀመሪያ እራሱን የሚጎዳ ሲሆን ለሌሎችም የጤና እክሎች ተጋላጭነቱ ይጨምራል ብለዋል።
ብስጩ እና ተናዳጅ መሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ጥላቻን፣ ተፈላጊነት እንዳይኖራቸው እንዲሁም ሃሳቸውን ለመናገር ፍላጎት እንዳይኖራቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡ ወላጆች ይህ አይነቱ ባህሪ ካላቸው ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን መልካም ግንኙነት ሊረብሸው እንደሚችል ገልጸው በልጆች ላይ ፍራቻን ይፈጥራል ብለዋል።
መፍትሄዎች፡
- ያለፉ ችግሮች መለወጥ ባይቻልም እንኳን ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጉዳዮችን ማስተካከል፡፡
- የንዴት ወይም የብስጭትን መነሻ ምክንያቶችን ለይቶ ማወቅ፣ ችግሩን በሰአቱ ለመፍታት መሞከር፣ ቂም በቀልን በመተው ይቅርታ ለማድረግ መሞከር ችግሩን ይቀርፋል ተብሏል፡፡
(በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የተጠናቀረ)

አንድ ሰው በአልኮል፣ አደንዛዥ እና አነቃቂ ዕፆች ወይም በሌሎች የባህሪ ሱሶች መጠቃቱን ለማወቅ በአጭሩ የሚከተሉትን 4 ነጥቦች መጠቀም ይችላል፤
1. ለመቋቋም የሚከብድ በልምምዱ ውስጥ የመቆየት ከፍተኛ ጫና/ውስጣዊ ግፊት፤
2. ቁጥጥር ማጣት፤ ለማቆም እየፈለጉ ያለመቻል፤
3. ልዩ ልዩ ጉዳቶች (የጤና፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ወዘተ...) እየተከሰቱም መጠቀምን መቀጠል፤
4. መቋቋም የሚያስቸግር ከፍተኛ አምሮት፤ እንዲሁም በማይጠቀሙ ጊዜ በድብርት፣ ብስጭትና የማይመች ስሜት መጠቃት።
እነዚህ ችግሮች ከተከሰቱ ባለሙያ ማማከር እና መፍትሄ ማግኘት ያስፈልጋል።
ሱስን በህክምና እገዛ መላቀቅ ይቻላል።
ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት፤ የሬናሰንት የአዕምሮ ጤና እና የሱስ ተሃድሶ ማዕከል መስራች)

መልካም ዜና!
ስጦታ የአእምሮ ህክምና እና የሱስ ማገገሚያ ማዕከል በሰውነት ውስጥ ሱስ አምጪ ንጥረ ነገሮች እና አደንዛዥ እጾችን መመርመሪያ በማስገባት የሱስ ምርመራ መጀመሩን በደስታ ሊያበስርዎት ይወዳል!
አድራሻ: ቶታል (3 ቁጥር ማዞሪያ)፤ ኦሜጋ ት/ቤት አጠገብ
ስልክ: +251113692818
+251113692774

ስሜት!
''የስሜቶቻችን ጥራት የሕይወታችን ጥራት ነው'' ይለናል ታዋቂው ቶኒ ሮቢንስ
በርግጥ ስሜት ላንተ/ላንቺ ምንድነው?
ለምንድነው የምትፈራው? ምን ላለማጣት ብለህ ነው ከመንገድህ የቆምከው? ማድረግ የምትፈልገውን ነገር ላለማድረግ ምን ገደበህ?
በሕይወት መንገድ ላይ የስሜቶቻችን ድርሻ ጉልህና ቀላል የሚባል አይደለም፣ በአውንታዊም ሆነ በአሉታዊ ጎኑ።
አለም ላይ የተሰጠህ እድሜ በሙሉ ያንተ ውድ ስጦታ ነው፦ እያንዳንዷን ግዜህን በፈለግከው መንገድ ልትጠቀምባት ተፈቅዶልሃል፣ የምታደርገውን ማወቅ ያንተ ድርሻ ነው።
ይህን ዉድ ስጦታ የሆነ ግዜአችንን በፈለግነው መንገድ እንድንጠቀምበት ስለ ስሜቶቻችን ያለን ምልከታና ግንዛቤ ወሳኝ ነው።
ዳንኤል አያሌው (Certified NLP Practitioner)

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ነሃሴ 27/2015 ቀን አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል፤
የዚህ ወር ርዕስም፡ “ስለሱስ እና ሱሰኝነት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን የስነልቦና አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ ናርዶስ ማሞ ናቸው፡፡
ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡ ⬇️
https://forms.gle/EpY5jjAUmMpXTLjV7

ካናቢስ እና የአዕምሮ ጤና!
አንድ ሰው ካናቢስ የመጠቀም ችግር አለበት ከሚያስብሉ ባህርያት (ምንጭ DSM-5 TR) :-
- አጠቃቀማቸውን ለመመጠን መቸገር (ለረጅም ሰአት መጠቀም፣ ካሰቡት ልክ በላይ መጠቀም፤ መጠኑን ለመቀነስ ወይንም ለማቆም እየፈለጉ አለመቻል፤ አምጡ የሚል ውስዋስ።
- በማህበራዊ ህይወት፣ በስራ፣ በቤተሰብ ጉዳዮችን ላይ ችግር ካስከተለ።
- በአደገኛ ሁኔታዎች እና ወቅቶችም መጠቀምን መቀጠል (ጡዞ ማሽከርከር፤ የጤና እክል አስከትሎም መጠቀሙ ከቀጠለ)።
- ለማቆም ሲሞክሩ የስሜትና አካላዊ ጤንነት መዛባት/Withdrawal (መነጫነጭ፣ መጨናነቅና መቅበጥበጥ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ድብርት) እና በጊዜ ሂደት የሚፈልጉትን ስሜት ለማግኘት የሱሱን መጠን መጨመር ካስፈለገ።
ካናቢስና ተጓዳኝ የአእምሮ ህመሞች፦
- ካናቢስ ከሳይኮሲስ (ከእውነታው ማፈንገጥ/ ጥርጣሬ፣ እንግዳ የሆነ ድምጽ መስማት፣ ለሌሎች የማይታዩ ነገሮችን ማየትና የመሳሰሉ)፣ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባት ጋር ይያያዛል::
ካናቢስ ለ ስኪዞፍሬንያ (ከባድ የሳይኮሲስ ህመም) ያጋልጣል?
🔹በዴንማርክ በተሰራ ጥናት መሰረት: በተለይም ወጣት ወንዶች የካናቢስ ተጠቃሚዎች፣ በተለይም ከ16-25 አመት ያሉት ላይ የስኪዞፍሬኒያ ተጋላጭነታቸው ጨምሮ ታይቷል:: በጥናቱ እንደተመላከተው የካናቢስ ተጠቃሚነትን መቀነስ ቢቻል 1/5ኛ ያህል ስኪዞፍሬኒያን ማስቀረት ይቻል ነበር:: (Hjorthøj C, Compton W, Starzer M, et al.)
🔹በስዊድን ለ15 አመታት ካናቢስ የሚጠቀሙ ሰዎችን በመከታተል በተሰራ ጥናት ከ50 ጊዜ በላይ የተጠቀሙ ሰዎች በ6 እጥፍ ተጋላጭነታቸው ጨምሯል:: (https://www.sciencedirect.com/science/article/pii/S0140673687926201)
🔹በተለይም ከአፍላ እድሜያቸው ጀምረው ረዘም ላለ ጊዜ የተጠቀሙ ሰዎች ለስኪዞፍሬኒያ ተጋላጭነታቸው ይጨምራል:: በዚህ እድሜ የአእምሮ ህዋሳት የሚጎመሩበት እድሜ ነውና ሱሱ በዚህ ሂደት ላይ ተጽዕኖ ስለማያሳድር ነው::
እንደምክንያት የሚነሱ ነጥቦች:-
- የዶፓሚን ንጥረነገር መዛባትና የአእምሮን ስራ ማወክ
- ከሌሎች ስነህይወታዊ እና ዘረመሌዛዊ ጉዳዮች ጋር በጋራ አጋላጭነት መጨመር (Stress- vulnerability model)
ሱስ ለማቆም የሚረዱ ነጥቦች፦
- እስካሁን እንዳታቆሙ ሰበብ የሆኑባችሁን ነገሮች ከዚህ መረጃ ጋር አመዛዝኗቸውና ራሳችሁን ጠይቁ::
- የማቆም ሂደቱን የምትጠቀሙትን መጠን በመቀነስ መጀመር ይቻላል::
- ዶፓሚናችሁ በሌሎች ነገሮች እንዲመነጭ በማድረግ (በስፖርት፣ በንባብ፣ ፊልም በማየት፣ ከከተማ ወጣ ብሎ በመዝናናትና ወዘተ) የካናቢሱን አስፈላጊነት ቀስ በቀስ መግታት ይቻላል::
- በጊዜ ሂደት ካናቢሱን በመሞከር ተጀምሮ ከተለያዩ ነገሮች ጋር በማስተሳሰር መጠቀሙን እንደገፋችሁበት፣ በጊዜ ሂደት ማቆም የመጠቀም ዑደቱን ያስቀጠሉ (ደስታን መሻት/reinforcement፣ ወይንም ሲያቆሙ ጊዜ የሚፈጠሩ ደባሪ ስሜቶችን/Withdrawal symptoms ላለማስተናገድ) በመግታት ባህርይውን ማረቅ ይቻላል:: በlearning theory መሰረት ማለት ነው!
- ከባለሙያ ጋር መመካከር ደሞ እንዴት ጥሩ መሰለችሁ!
Reference: DSM-5 TR
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ሬዚደንት ሃኪም)

አዲስ ዓመት አዲስ ጅማሮ!
አዲስ ዓመት የአዳዲስ ነገሮች ጅምሬ መነሻ ነው! አዲስ አመት ዳግም እንደ አዲስ እነደ መወለድ ነው። አዲሱ ዓመት ሲጀምር፣ በሕይወታችን ውስጥ ከአጉል ልምዶቻችን ለመላቀቅ፣ ለችግሮቻችን መፍተሔ ለማበጀት እና ስኬታማ ስለመሆን እናስባለን።
ብዙውን ጊዜ አዲስ ዕቅዶችን እናቅዳለን እንዲሁም አዳዲስ ውሳኔዎችን መወሰን እንጀምራለን። በአዲስ አመት የደስታ፣ የተመስጦ እና የተስፋ ስሜት ሊሰማን ይችላል፣ በዛው ልክ አንዳንድ ጊዜም ፍርሃት ያድርብናል።
በሕይወታችን ውስጥ እውነተኛ ለውጦችን ማድረግ ከፈለግን ላሰብነው አላማ እስከመጨረሻው በፅናት መታገል የግድ ነው። ትልቅ ማለም ትልቅነት ነው! ሆኖም ግን ህልማችን እውን እንዲሆን በየቀኑ ማለም ብቻ ሳይሆን መተግበር ተገቢ ነው።
አዲሱ ዓመት ባዶ ገጾች እንዳሉት መጽሐፍ ነው። እነዚህን ገጾችን እንዴት መሙላት እንፈልጋለን? ነው ጥያቄው አዲስ ዓመት አዳዲስ ጅማሬዎችን እንድንጀምር እና በሕይወታችን ውስጥ ለውጦችን እንድናደርግ ያነሳሳናል፣ ግን ይህ መነሳሳት ዓመቱን ሙሉ መቀጠል አለበት።
በስሜታዊነት ላይ ሳይሆን በጥበብ ላይ በመመርኮዝ በራስ ተነሳሽነት ውሳኔዎችን መወሰን ያስፈልገናል። ችግሮች እና መሰናክሎች ቢኖሩም ውሳኔዎቻችን የውስጥ ጥንካሬን እና በፈተና የመፅናት ችሎታን ያጎናፅፉናል።
በመጪው አመት መጨረሻ ውሳኔዎቻችን በመፈፀም እና ያሰብነውን በማሳካት ዓመቱ በህይወታችን ጎልቶ እንዲታይ ማድረግ እንችላለን።
አዲሱ ዓመት በህይወት መፅሀፋችን ውስጥ የምንፅፈው አዲስ ምዕራፍ ነው። የጠራ እና ግልፅ ግብ በማውጣት እና በመተግበር ይሄንን ምዕራፍ የስኬት ምዕራፍ ልናደርገው ይገባል።
ሣሙኤል ተክለየሱስ
(ዓለም አቀፍ የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

በአዲሱ አመት በ2016 ከሱስ ለመላቀቅ (New Year Resolution) ለምታስቡ!
1. ውሳኔያችሁ ግልፅና የሚተገበር ይሁን፤ በፅሁፍም አስፍሩት፤
2. ለለውጥ አጋዥና አደናቃፊ ነገሮችን በዝርዝር ፃፉ፤ ለምሳሌ፣ በሱስ ከተጠቃ ጓደኛ መራቅ፤
3. የሌሎች ሰዎች እንዲሁም የባለሙያ ድጋፍ ያስፈልጋችሁ እንደሆነ አስቡ፤
4. ከዚህ በፊት ሞክራችሁ ውጤት ያላገኛችሁበት መንገድ አትድገሙ፤
5. ስኬታችሁን እየተከታተላችሁ መዝግቡ፤ ብትደነቃቀፉም መጓዝን አታቋርጡ፤ ተስፋ አትቁረጡ።
መልካም የስኬት አመት ይሁንላችሁ!
ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት)

ይህ አመት!
የአዕምሮ ደስታ፣ ሰላም፣ እረፍት የምታገኙበት፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት አመት ይሁንላችሁ፡፡
🌼መልካም አዲስ አመት!🌼