ሙሉ ጤንነት!
ብዙ ሰዎች ለአካላዊ ጤናቸው ትልቅ ትኩረት ሰጥተው በአመት ሁለት ጊዜ የህክምና ክትትል (ቼክ አፕ) ያደርጋሉ፤ እንዲህ አይነት ልምድ እጅግ መልካም ነው። ነገር ግን የሳንባ፣ ኩላሊት፣ ጉበት፣ ጨጓራ፣ ጥርስና የመሳሰሉ አካላት ደህንነት ብቻ የጤናማነት ምልክት ሊሆን አይችልም።
የአለም ጤና ድርጅት ጤና ለሚለው ቃል ትርጉም ሲሰጥ ጤንነት ማለት "ሙሉ አካላዊ፣ አዕምሮአዊና ማሕበራዊ ደህንነት ነው እንጂ አለመታመም ብቻ አይደለም" ይላልና።
WHO defines health as well-being, “a state of complete physical, mental and social well- being and not merely the absence of disease or infirmity”.
ለመሆኑ የአዕምሮ ጤና ምንድን ነው?
አንድ ሰው የአዕምሮ ጤንነት አለው የምንለው ግለሰቡ ያልተዛነፈ አስተሳሰብ፣ ባሕርይና ስሜት ሲኖረው እንዲሁም ከማሕበረሰቡ ጋር ተቀላቅሎና በጥሩ ሁኔታ ሰርቶ መኖር ሲችል ነው።
እስቲ በዝርዝር እንመልከታቸው፦
ሀ) የአስተሳሰብ ጤንነት (cognitive health)
ጥሩ የማሰብ፣ የማስታወስ (memory)፣ የማሰላሰል፣ ፍሰት ያለው ሀሳብ የማፍለቅ፣ የትኩረት፣ የማቀድ፣ ችግሮችን የመፍታትና ውሳኔ የመስጠት ችሎታዎች የአስተሳሰብ ጤንነትን ያመላክታሉ።
ለ) የስሜት ደህንነት (emotional well-being)
አንድ ሰው የስሜት ጤንነት አለው ለማለት በብዛት በቀን ውስጥ የሚያስተናግዳቸውን ስሜቶች ማወቅ አስፈላጊ ነው። በብዛት ከአሉታዊ ስሜቶች (ለምሳሌ ንዴት፣ ጥላቻ፣ ፍርሃት፣ ቂም...ወዘተ) ይልቅ አዎንታዊ ስሜቶችን (ለምሳሌ ፍቅር፣ መገረም፣ ተስፋና ደስታ) የሚያስተናግድ መሆን አለበት።
ሐ) ጤናማ የህይወት ዘይቤ (Healthy life style)
አንድ ግለሰብ ሰናይ ባሕርያት አሉት የምንለው የሚያደርጋቸውን ነገሮች (አመጋገብ፣ አለባበስ፣ አነጋገር...ወዘተ) ተመልክተን ነው። ለምሳሌ በብዛት አትክልትና ፍራፍሬ ይመገባል፣ የአካል እንቅስቃሴ ያደርጋል፣ ሰው ይረዳል፣ አይሳደብም፣ አልኮል አይጠጣም፣ አይቅምም፣ አያጨስም፣ ነውጠኛ አይደለም...ወዘተ።
መ) ማሕበራዊ ደህንነት (social well-being)
ጥሩ አስተሳሰብ፣ አካላዊ ጤንነት፣ አዎንታዊ ስሜትና የሕይወት ዘይቤ አንድን ሰው ጤናማ ነው ለማለት መሉ መስፈርት አይሆኑም። ያ ሰው ከሰዎች ጋር ተስማምቶ መኖር፣ ሀሳቡን ማስረዳት፣ የሌሎችንም ሀሳብ መረዳት በጠቅላላው ከሌሎች ጋር በጥሩ ሁኔታ አብሮ መኖር አስፈላጊ ነው።
መደምደሚያ: ጤንነት አካላዊ ደህንነት እንዲሁም አለመታመም ብቻ አለመሆኑን ተረድተን ጤናማ የባሕርይ እና የአዕምሮ ጤንነታችንን መጠበቅ አለብን።
(ሳይኮሎጂ 101)
@melkam_enaseb

ለስልጠና ፈላጊዎች!
ስልጠናው የሚፈጀው ጊዜ 3 ወር።
የስልጠናው ትኩረቶች በጥቂቱ
- ልዩ-ፍላጎትን ማካተት
- የባህሪ ቴራፒ
- የንግግርና ቋንቋ ቴራፒ
- የክዋኔ ቴራፒ
- መሰረታዊ ምዘና
- ሌሎች ተያያዥጉዳዮች
ፕሮግራም
- በቀን፣ በማታ እና ቅዳሜና እሁድ
ስልጠናው በዘርፉ ብቁ በሆኑ ባለሙያዎች የሚሰጥ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ፦
0924616769
0930101202
@melkam_enaseb
ስልጠናው የሚፈጀው ጊዜ 3 ወር።
የስልጠናው ትኩረቶች በጥቂቱ
- ልዩ-ፍላጎትን ማካተት
- የባህሪ ቴራፒ
- የንግግርና ቋንቋ ቴራፒ
- የክዋኔ ቴራፒ
- መሰረታዊ ምዘና
- ሌሎች ተያያዥጉዳዮች
ፕሮግራም
- በቀን፣ በማታ እና ቅዳሜና እሁድ
ስልጠናው በዘርፉ ብቁ በሆኑ ባለሙያዎች የሚሰጥ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ፦
0924616769
0930101202
@melkam_enaseb
ስሜቶቻችን (Emotions)
ስሜቶቻችን (Emotions) የህይወት ቀለማት ናቸው። ህይወት ውበት እንዲኖራት ያደርጋሉ። ደግሞም ለመኖራችን ምክንያት ናቸው (they have survival value).
ስሜት (Emotions) አንጎላችን ለክስተቶች የሚሰጣቸው ግብረመልሶች ሲሆኑ ለሆነ ክስተት ተገቢውን ምላሽ እንድንሰጥ ያስችሉናል።
ይህም ማለት:-
- አስፈሪ ክስተት ሲያጋጥመን የፍርሃት ስሜት በመፍጠር ወይ እንድንጋፈጥ ወይ ሩጠን እንድናመልጥ ያደርገናል።
- በሚያስደስተው እንድንደሰት እና ሰውነታችን ዘና እንዲል፣ በሚያሳዝነው እንድናዝን፣ በሚያስጠይፈው እንድንጠየፍ እና ራሳችንን ከመጥፎ ነገር እንድናርቅ ያደርገናል፣ በሚያናድደው እንድንናደድ እና ችግሩን እንድንቀርፍ ያስችለናል። ይህ ህይወት እንድትቀጥል ወሳኝ ሚና አለው።
Aristotle, The Nichomachean Ethics በተሰኘ መጽሃፉ እንዲህ ይለናል:-
''Anyone can be angry- that is easy. But to be angry with the right person, to the right degree, at the right time, for the right purpose, and in the right way; that is not easy.''
ይህን አባባል ዳንኤል ጎልማን 'Emotional intelligence' በተባለ መጽሃፉ እንደ መግቢያ ተጠቅሞበታል።
እኔም ይህን አባባል እመራዋለሁ። ችግሩ መናደዳችን ሳይሆን ንዴታችን አውዱን ያልጠበቀ መሆኑ ላይ ነው፤ ንዴታችንን አውድ እና ጠርዝ እንዲኖረው ማድረግ መቻል አለመቻላችን እንደ አንድ የስነልቦናዊ ብስለት እና ራስን የመግዛት ችሎታ ነው።
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)

በተለየ አንድ ነገር የመፍራት መታወክ (specific phobia)
ብዙውን ጊዜ ከትክክለኛው አደጋ ጋር የማይመጣጠን የአንድን ነገር ወይም ሁኔታ በጠንካራ፣ በቋሚ እና ምክንያታዊነት የጎደለው ፍርሃት የሚታወቅ የጭንቀት መታወክ ነው።
ይህ ፍርሃት ከፍተኛ ጭንቀትን ያስነሳል እና ነገሮችን ማራቅ ባህሪያት በማምጣት በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ጣልቃ እየገባ ችግር ይፈጥራል።
ዋና ዋና ባህሪያት እና ምልክቶች፦
- ከባድ ፍርሃት፦ ፍርሃቱ ያልተመጣጠነ ጠንካራ እና ዘላቂ ነው ቢያንስ ለ 6 ወራት ይቆያል።
- ኢ-ምክንያታዊነት እውቅና፦ ግለሰቦች ፍርሃቱ ምክንያታዊ እንዳልሆነ ሊገነዘቡ ቢችሉም አሁንም ሊቆጣጠሩት አይችሉም።
- መራቅ፦ ፎቢያ ያለባቸው ሰዎች የሚፈራውን ነገር ወይም ሁኔታ ለማስወገድ ብዙ ጊዜ ከነገሩ ይርቃሉ።
- የአካል ምልክቶች፦ ለተፈራው ነገር ወይም ሁኔታ በመጋለጥ ሂደት ዉስጥ፣ ወይም ነገሩን ይፈጠራል በሚል ግምት ዉስጥ እንኳን እንደ ድንጋጤ፣ ላብ፣ ፈጣን የልብ ምት እና ማዞር የመሳሰሉ አካላዊ ምልክቶችን ያስነሳል።
- በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ጣልቃ ገብነት፦ ህመሙ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፣ ይህም ወደ ጭንቀት ወይም በትምህርት ቤት፣ በሥራ ወይም በማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ችግር ያስከትላል።
የተለመዱ የተለየ የፍርሃት ዓይነቶች፡-
- የእንስሳት ፎቢያ፡- እንደ ሸረሪቶች፣ እባቦች፣ ውሾች ወይም አይጦች ያሉ የተወሰኑ እንስሳትን መፍራት።
- የተፈጥሮ አካባቢ ፎቢያ፦ እንደ ከፍታ፣ ውሃ፣ ማዕበል፣ ወይም ጨለማ ያሉ የተፈጥሮ ክስተቶችን መፍራት።
- የመቁሰል ፍርሃት፡- መርፌን፣ ደምን ወይም ጉዳቶችን መፍራት።
- ሁኔታዊ ፍርሃቶች፦ እንደ በረራ፣ የታፈኑ ቦታዎች ወይም የህዝብ ማመላለሻ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን መፍራት።
መንስኤዎች እና የአደጋ ምክንያቶች፡
- የዚህ የጭንቀት መታወክ የቤተሰብ ታሪክ አደጋን ሊጨምር ይችላል።
- አስደንጋጭ ገጠመኞች፡- ልዩ የሆነ አስፈሪ እንደ ዉሃ ዉስጥ መስጠም ያሉ አሰቃቂ ክስተቶች ካጋጠሙ በኋላ ሊዳብሩ ይችላሉ።
- ከሰው በመማር የምንወስደው ባህሪያት ልጆች የወላጆቻቸውን የተጋነነ ፍርሃት ሊኮርጁ ይችላሉ።
- ቁጣ፡- አንዳንድ ግለሰቦች በተፈጥሮ ዓይናፋርነታቸው ወይም በባህሪያቸው ምክንያት ለነዚህ ፍርሃቶች በጣም የተጋለጡ ሊሆኑ ይችላሉ።
ምርመራ እና ሕክምና፡
ምርመራ፦ ምርመራው የሚካሄደው ከመጠን በላይ ፍርሃትን፣ ነገሮችን የመራቅ ባህሪያትን እና ከፍተኛ ጭንቀትን ወይም እክልን ጨምሮ ልዩ ምልክቶች በመኖራቸው ላይ ነው።
ሕክምና፡-
- የተጋላጭነት ሕክምና፡- ቀስ በቀስ ግለሰቦችን ለተፈራው ነገር ወይም ሁኔታ ደህንነቱ በተጠበቀ እና በተቆጣጠረ መንገድ ማጋለጥ።
- የግንዛቤ ባህሪ ሕክምና (CBT)፡- ግለሰቦች ስለተፈራው ነገር ወይም ሁኔታ አሉታዊ አስተሳሰቦችን እና እምነቶችን ለይተው እንዲያውቁ መርዳት።
መድሃኒት፣ በአንዳንድ ሁኔታዎች የጭንቀት ምልክቶችን ለመቆጣጠር የሚረዳ መድሃኒት ሊታዘዝ ይችላል።
ጠቃሚ ማሳሰቢያ፡ የተወሰኑ ፎቢያዎች ሊያዳክሙ ቢችሉም፣ ብዙ ጊዜ በተገቢው መንገድ ሊታከሙ ይችላሉ። የባለሙያ እርዳታ መፈለግ የግለሰቡን ሁኔታ ያሻሽላል።
ለማማከር ይደውሉልን: 0995011035
አጭር ቁጥር: 8187
(Sitota Mental Health Care & Rehabilitation Center)

የግንቦት ወር በአለም አቀፍ ደረጃ የአዕምሮ ጤና የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ተብሎ ይታሰባል።
- የአዕምሮ ህመም ስንል በስሩ ከ 300 በላይ ህመሞችን ያቀፈ ነው።
- እንደ ጥናቶች ከሆነ ከ 4 ሰዎች መሃል በአንዱ ላይ ሊከሰት ይችላል።
- ምልክቶቹም ከሰው ሰው የተለያዩ ናቸው። በአጠቃላይ በስሜት፣ አስተሳሰብና ባህርይ መዛባት ሊገለጥ ይችላል።
- ልክ እንደ ሌሎች ህመሞች ሁሉ ውጤታማ የሆነ ህክምና ያለው ነው።
የአዕምሮ ጤና ይመለከተናል!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb
- የአዕምሮ ህመም ስንል በስሩ ከ 300 በላይ ህመሞችን ያቀፈ ነው።
- እንደ ጥናቶች ከሆነ ከ 4 ሰዎች መሃል በአንዱ ላይ ሊከሰት ይችላል።
- ምልክቶቹም ከሰው ሰው የተለያዩ ናቸው። በአጠቃላይ በስሜት፣ አስተሳሰብና ባህርይ መዛባት ሊገለጥ ይችላል።
- ልክ እንደ ሌሎች ህመሞች ሁሉ ውጤታማ የሆነ ህክምና ያለው ነው።
የአዕምሮ ጤና ይመለከተናል!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb
ለአዕምሮ ህክምና ወሳኙ ከህክምናው በተጨማሪ ሁሌም ያልተቋረጠ ግንዛቤ መፍጠር ነው።
- የአዕምሮ ህመም የስርጭት መጠኑ በጣም እየጨመረ መምጣቱ ለሁላችንም ግልፅ ነው።
- ህክምናውም ውስብስብ መሆኑ ግልፅ ነው።
- ህክምናው ረዘም ያለ ጊዜ መውሰድን ይፈልጋል።
- የህክምና ሂደቱ ግን ውጣ ውረድ የበዛበት ነው።
- በሚፈለገው ደረጃ ለውጥ ማምጣቱ በቂ እንዳይሆን ካደረጉት ዋነኛው ምክንያቶች ውስጥ፤ ውሳኔ ሰጪ የሆነው የአንጎላችን የአዕምሮ ክፍል በመታመሙ ስለሆነ፣ የአዕምሮ ህመም እና ህክምናው ሁሌም አስቸጋሪ ይሆናሉ።
- ስለሆነም ሁልጊዜም ማስተማር ማስተማር ማስተማር፣ ማስረዳት ማስረዳት ማስረዳት፣ ግንዛቤ መፍጠር...
ዶ/ር ሔኖክ ይትባረክ (የአዕምሮ ሀኪም)

ከስሜት ቀውስ ጋር የሚታገሉ ሰዎች . . .
- እርዳታ እየፈለጉ እንኳን እርዳታ መጠየቅ ስለሚያስቸግራቸው ሁል ጊዜ ሁኔታቸው በራሳቸው ለመፍታት ይታገላሉ፡፡
- ፈታ የማለት (relax የማድረግ) ስሜት ስለሌላቸው ሁል ጊዜ የሆነ ነገር እንደጎደለ አይነት ስሜት ይዘው በተጠንቀቅ ነው የሚኖሩት፡፡
- ላጠፉትም ላላጠፉትም ነገር ይቅርታ የመጠየቅ ዝንባሌ አላቸው፡፡
- ከሰዎች ጋር ካሳለፉ ወይም ከተነጋገሩ በኋላ ሁኔታውን በሃሳባቸው በማውጣትና በማውረድ “ምነው እንዲህ ባልኩኝ” እና “ምነው እንዲህ ባላልኩኝ” የሚሉት ነገር ብዙ ነው፡፡
- እነሱ በውል ምክንያቱን አያውቁትም እንጂ ገና ለገና ሰዎች ይገፉኛል በማለት ቀድሞኑ ሲቀርቧቸው ራሳቸውን ክፍት ማድረግ ያታግላቸዋል፡፡
- ሁል ጊዜ ከሰዎች መደነቅንና ጎሽ መባልን (approval and validation) ይፈልጋሉ፡፡
- በምንም ሁኔታ ውስጥ ሰዎችን ቅር ማሰኘት ስለማይፈልጉ ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እነሱ ሃላፊነትን የመውሰድ ዝንባሌ አላቸው፡፡
(ዶ/ር እዮብ ማሞ)

ዛሬ እስኪ ስለ Gaslighting በጥቂቱ...
"Gaslighting" (ጋዝላይቲንግ) ማለት የስነ ልቦና ጥቃት ወይም የማታለል አይነት ነው።
ዋና ትርጉሙም፦
አንድ ሰው ሌላውን ሰው የራሱን/የራሷን እውነታ፣ ትውስታ፣ ወይም የአዕምሮ ጤንነት እንዲጠራጠር ሆን ብሎ የሚያደርግበት ስልት ነው። ይህንን የሚያደርጉት ሰውዬው በተጎጂው ላይ ስልጣን እና ቁጥጥር ለማግኘት ነው።
ጋዝላይቲንግ የሚያደርግ ሰው የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦
• መካድ፦ የተናገሩትን ወይም ያደረጉትን ነገር እንዳልተናገሩ ወይም እንዳላደረጉ አድርጎ መካድ። ("እንዲህ አላልኩም"፣ "ይሄ በፍፁም አልተፈጠረም")
• ማጣመም፦ የተፈጠረውን ነገር ትርጉም በማዛባት ተጎጂው የራሱን ትውስታ እንዲጠራጠር ማድረግ።
• ዋጋ ማሳጣት፦ የተጎጂውን ስሜት ወይም ስጋት በማቃለል "በጣም ስሜታዊ ነህ/ነሽ" ወይም "ነገሮችን ታካብዳለህ/ታካብጃለሽ" በማለት ራሱን እንዲጠራጠር ማድረግ።
• ውሸት መናገር፦ ግልጽ የሆኑ ውሸቶችን በመናገር እና እውነታውን በመካድ ተጎጂውን ማደናገር።
• ተጠያቂነትን ማሸሽ፦ ጥፋትን ወደ ተጎጂው በማዞር የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማው/እንዲሰማት ማድረግ።
• ማግለል፦ ተጎጂውን ከጓደኞች ወይም ከቤተሰብ በመለየት የጋዝላይት የሚያደርገው ሰው ብቸኛ የመረጃ ምንጭ እንዲሆን ማድረግ።
ስያሜው የመጣው "Gas Light" (ጋዝ ላይት) ከተባለ የ1938 ተውኔት እና በኋላም ፊልም ነው። በዚህ ታሪክ ውስጥ ባል ሚስቱ እያበደች እንደሆነ እንድታስብ ለማድረግ በቤታቸው ውስጥ ያሉትን የጋዝ መብራቶች በማደብዘዝ እና ስትጠይቀውም ምንም እንዳልተለወጠ በመንገር ያታልላታል።
በአጭሩ ጋዝላይቲንግ ማለት አንድ ሰው ሌላውን ሰው "እኔ እንደማስበው ነው ወይስ አእምሮዬ እየተዛባ ነው?" ብሎ ራሱን እንዲጠይቅ የሚያደርግ ከባድ የስነ ልቦና ጥቃት ነው።
(Ephrim Fekade)

መርጦ ዝም ማለት/ Selective Mutism (SM)
በዋነኛነት ህጻናትን የሚያጠቃ ውስብስብ የጭንቀት መታወክ ነው፣ ህክምና ካልተደረገለት እስከ ጉርምስና እና አዋቂነት ሊቆይ ይችላል። ይህ ችግር ያላቸው ግለሰቦች የንግግር ቋንቋን የመናገር እና የመረዳት ችሎታ አላቸው፣ ነገር ግን የመናገር ተስፋ ባለባቸው (ለምሳሌ፣ ትምህርት ቤት) በተወሰኑ ማህበራዊ ሁኔታዎች ውስጥ ያለማቋረጥ መናገር ይሳናቸዋል፣ ምንም እንኳን በሌሎች (ለምሳሌ፣ ቤት ውስጥ ከቤተሰብ ጋር) ቢናገሩም።
መስፈርቶች፡-
- በሌሎች መቼቶች ውስጥ ቢናገርም በተወሰኑ ማህበራዊ ሁኔታዎች ውስጥ ያለማቋረጥ አለመናገር።
- ችግሩ በትምህርት ወይም በሙያ ስኬት ወይም በማህበራዊ ግንኙነት ላይ ጣልቃ ይገባል።
- የረብሻው ቆይታ ቢያንስ አንድ ወር ነው።
- አለመናገር በእውቀት ማነስ ወይም በንግግር ቋንቋ ምቾት ማጣት ምክንያት አይደለም።
መንስኤዎች እና የአደጋ ምክንያቶች፦
1. የጭንቀት መታወክ፦ የማህበራዊ ጭንቀት መታወክ በጣም የተለመደ የጋራ በሽታ ነው. ይህ ችግር በብዙ ጉዳዮች ላይ እንደ ከፍተኛ የማህበራዊ ፍርሃት አይነት ይቆጠራል።
2. ቁጣ፦ የሚሸማቀቁ ወይም የተገለሉ ልጆች ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው።
3. የቤተሰብ እና የጄኔቲክ ምክንያቶች፡- የጭንቀት ወይም የባህሪ መከልከል የቤተሰብ ታሪክ።
4. የአካባቢ ሁኔታዎች፡- የንግግር እና የቋንቋ ጉዳዮች እና አሰቃቂ ገጠመኞች ናቸው።
ስርጭት፦
በግምት ከ 0.03% እስከ 1% ከሚሆነው ህዝብ ውስጥ ይከሰታል።
ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው ከ 5 ዓመት በፊት ነው፡ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ትምህርት ቤት እስኪገባ ድረስ አይታወቅም።
በሴቶች ላይ ከወንዶች ይልቅ ትንሽ የተለመደ ነው።
ምልክቶች እና ባህሪያት፦
- ምቹ በሆኑ አካባቢዎች (ቤት) ውስጥ በመደበኛነት መናገር ይችላል።
- በማህበራዊ ወይም በግምገማ መቼቶች (ትምህርት ቤት) ውስጥ ሙሉ በሙሉ ጸጥ የማለት ባህርይ።
- ቃል ሳያወጡ በሰዉነት አካላቶች የሆነ ግንኙነት (መጠቆም)።
- እንዲናገር ግፊት ሲደረግ ያለመናገር ፍላጎት፣ የዓይን ንክኪን ማስወገድ ወይም የጭንቀት ምልክቶች።
- ግትር አቋም ወይም ማህበራዊ መራቅን ያሳያል።
የሕክምና ዘዴዎች፦
1. የባህሪ ህክምና (በጣም ውጤታማ)
ቀስ በቀስ መጋለጥ (Desensitization): በንግግር ሁኔታዎች ውስጥ ምቾትን ቀስ በቀስ ይጨምሩ።
መቅረጽ፡- ማንኛውንም የቃል ግንኙነት ሙከራዎችን ማጠናከር።
ቀስ በቀስ ከሚታወቁ ግለሰቦች ጋር መናገርን ከዚያም በሰፊ መቼቶች ማስተዋወቅ።
2. የግንዛቤ ባህሪ ሕክምና (CBT)
በተለይም በትልልቅ ልጆች እና ጎረምሶች ውስጥ ውጤታማ።
3. የቤተሰብ ተሳትፎ፦ የወላጅ ስልጠና እና የትምህርት ቤት ቅንጅት ወሳኝ ናቸው።
ለመናገር ግፊትን ወይም ለዝምታ ቅጣትን ያስወግዱ።
4. መድሃኒት፦ SSRIs (ለምሳሌ fluoxetine፣ sertraline) አንዳንድ ጊዜ በትልልቅ ልጆች ወይም በከባድ ጉዳዮች ላይ ጥቅም ላይ ይውላሉ።
🔷 እነዚህ ምልክቶች ሲሰሙን የስነ-አእምሮ ባለሞያን ማማከር ብልህነት ነው፡፡

Cognitive Behavioral Therapy!
CBT ከስነ ልቦና ህክምናዎች አንዱ ነው። በዚህ የህክምና አይነት መሰረት አስተሳሰባችን (Cognition) ሚዛናዊ መሆን አለመሆኑ ውስጣዊ ስሜታችን/feeling እና አካላዊ ጤንነታችን ላይ ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ይታመናል።
በዚህም መሰረት ሃሳቦቻችንን ሚዛናዊ ማድረግ ላይ አጽንኦት ሰጥቶ ይሰራል። በተጨማሪም ድርጊት/ባህርያቶቻችን (Behavior) ምክንያታዊ እና ችግር ፈቺ እንጂ ችግር ፈጣሪ እንዳይሆኑብን ይሰራል።
ይህ የስነልቦና ህክምና አይነት፦
- ለ ድብርት እና ጭንቀት ህመሞች፣
- ለድህረ አደጋ ሰቀቀን- Trauma focused CBT
- ለ ሳይኮሲስ ህመሞች- CBT for psychosis
- ለOCD (በተለይም Exposure and response prevention የሚባለው አይነት ህክምና...በምሳሌ ለማስረዳት ያህል...obsession ልክ እንደ እከክ ስሜት ናቸው...የእከክ ስሜቱን ለማብረድ ወድያው ማከኩ Compulsion ይሆናል...ትንሽ ታግሰን ለእከክ ስሜቱ መልስ ካልሰጠን (Compulsion ካልፈጸምን) ያ የሚያሳክከን ቁስል እየደረቀ ይሄድና ይድናል የእከክ ስሜቱም ይቀንስና ይጠፋል...በየጊዜው ካከክነው (Compulsion ከፈጸምን) ግን ቁስሉን ቢያሰፋብን እና ጊዜያዊ እረፍት ቢሰጠን ነው እንጂ መፍትሄ አይሆነንም..የሚሻለው የእከክ ስሜቱን መታገሱ ነው ማለት ነው...Exposure and response preventionም ሃሳቡ ቢመጣም ወድያው ለሃሳቡ ምላሽ ባለመስጠት በጊዜ ሂደት ሃሳቡ እንዲመናመን ማድረግ ነው።)
እና ለመሳሰሉት መሰጠት የሚችል አይነተኛ የስነልቦና ህክምና አይነት ነው።

ሁለንተናዊ የልጆች እድገት /Holstic Child Development!
የልጆች የእድገት ዘርፎች የምንላቸው:-
አካላዊ እድገት፣ የስሜት እድገት፣ የአእምሮ እድገት፣ የማህበራዊ ግንኙነት እድገት፣ የቋንቋ/ ተግባቦት እና የመንፈሳዊ እድገት ናቸው። እነዚህን የእድገት ዘርፎች ለማጎልበት የወላጆች፣ የቤተሰብ እና የመምህራን ብሎም የማህበረሰቡ ድርሻ ትልቅ ነው።
ስኬታማ፣ ሁለንተናዊ እድገት እንዲኖሩ:-
- ልጆች ሊያደርጉ ስለሚገባቸው ነገሮች ከመንገር ይልቅ አርአያ በመሆን ማሳየት።
- ልጆች የሚያደርጓቸውን ጥረቶች ማበረታታት እና መደገፍ።
- በራስ መተማመን በጣም አስፈላጊ ክህሎት መሆኑን ማሳወቅ እና ክህሎቱን እንዲያጎለብቱ ማገዝ።
- በእለት-ተእለት የሚገጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መፍታት እንዳለባቸው እና ካጋጠማቸው ችግር ምን ሊማሩ እንደሚችሉ ማሳየት።
- ችግር የመቋቋም ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት።
- የልጆች ሀላፊነት፣ መብት እና ግዴታ ምንድነው የሚለውን ማሳወቅ።
- ያዪ እና የሰሙትን እንዲያደርጉ ብቻ ሳይሆን የራሳቸው የፈጠራ ክህሎት እንዲኖራቸው ማበረታታት።
- ስለሚሰማቸው ስሜት መግለፅ እና ምን አይነት ስሜት እየተሰማቸው እንደሆነ እንዲገልፁ ማበረታታት።
- ከስህተት እና ከውድቀት መማር እንደሚቻል ማሳወቅ።
- ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ማድረግ እና መደጋገፍ አስፈላጊነቱን ማስተማር።
- ውሳኔ የመወሰን ክህሎት እንዲያዳብሩ እድል መስጠት።
- ከልጅዎ ጋር እድሜው/ እድሜዋ በሚፈቅደው ጉዳዬች ላይ በግልፅ መወያየት እና ለልጆች ክብር እና ጊዜ መስጠት።
- ጥፋት ሲያጠፉ መቅጣት ብቻ ሳይሆን መልካም ሲያደርጉ ማበረታታት።
- ልጆች በቀለም ትምህርት ጥሩ እንዲሆኑ እንደምንለፋው ሁሉ ጠንካራ መንፈሳዊ መሰረት እንዲኖራቸው ትኩረት እንስጥ። እውቀት ያለሞራል ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።
- ከምንም በላይ ልጆች የሚያዳምጣቸው፣ የሚረዳቸው እና ባግባቡ የሚመራቸው ሰው ይፈልጋሉ ወላጆች ይህንን አስቀድሙ።
- ውብ እና ድንቅ ሆነው በፈጣሪ አምሳል እንደተፈጠሩ መንገር።
- አቅም በፈቀደ ሁሉ የተመጣጠነ እና እቤት ውስጥ የተዘጋጀ ምግብ እንዲመገቡ እና ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ።
- ለአካላዊ፣ ስነልቦናዊ እና አእምሯዊ ጉዳት እና አደጋ ተጋላጭ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መጠበቅ እና መከላከል።
በመአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

ከአስደንጋጭ ገጠመኝ በኃላ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት (Post-Traumatic stress Disorder)
የህይወት ገጠመኝ የሌለው ሰው ይኖር ይሆን? ይብዛም ይነስም ሁላችንም ዛሬ እስካለንበት ድረስ ለመልካም ነገር ወይም ደግሞ ለመጥፎ ነገር ተጋልጠናል። ብዙ ሰዎች እጅግ አስደንጋጭ ነገር በራሳቸው አልያም በቤተሰቦቻቸው ላይ ገጥሟቸው ተጨንቀው፣ ተረብሸው ኑሮን በመከራ ይኖራሉ።
በአደጋ፣ በተሽከርካሪ፣ በወንጀል፣ በድብደባ፣ በስለት መወጋት፣ በጦርነት፣ በጾታዊ ትንኮሳ፣ በተፈጥሯዊ አደጋ፣ ወዘተ በኃላ የሚፈጠር የአዕምሮ ህመም ድህረ ሰቀቀን ጭንቀት (PTSD) በመባል ይታወቃል።
ስርጭት፦
ሴቶች ላይ ይበዛል። 10 በመቶ በሴቶች/ ጾታዊ ጥቃት ስለሚበዛ፣ 4 በመቶ በወንዶች/ ከግጭት ጋር በተያያዘ፣ በወታደሮች ላይ 30 በመቶ እንደሚጠጋ ጥናቶች ያሳያሉ። ወጣቶች ላይ ስርጭቱ ከፍተኛ ነው።
አጋላጮች፦
ማንም ሰው ከዚህ ችግር የተጠበቀ አይደለም። ነገር ግን ማህበራዊ ተሳትፏቸው አነስተኛ የሆኑ ሰዎች የበለጠ ሊጠቁ ይችላሉ፤ እንደ ምሳሌ ብቸኛ ሰዎች፣ ትዳር የሌላቸው/ በሞት አልያም በፍቺ ሊሆን ይችላል፣ ከፍተኛ ድህነት ውስጥ ያሉ፣ የወንጀል ስለባ የሆኑ፣ አብዝቶ የሱስ ተጠቃሚዎች፣ አንዳንድ የስብእና ችግር አይነቶች፣ ተያያዥ ጭንቀቶች እንዲሁም ድባቴ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው።
ምልክቶቹ፦
1. ለአሰቃቂ ነገር ተጋላጭ ከሆኑ በኋላ የሚፈጠር፦
በራሳቸው ላይ የተፈጠረ ገጠመኝ ሲሆን፣ ሌሎች ሰዎች ላይ ሲደርስ መታዘብ፣ በቤተሰብ አባል ላይ መድረሱን ሲያውቁ፣ እና ተደጋጋሚ አጋላጮች ሲኖሩ/ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች።
2. ተመላላሽ፣ ጣልቃ ገብ የሆነ የሚረብሽ ትውስታ፣ ቅዠት፣ ሰመመን ውስጥ መግባት፦
አደጋው እንደ አዲስ በእውን የሚፈጠር ይመስላቸዋል፣ ሁኔታውን እንደነበረው ይተገብሩታል፣ ፍንጭ የሚሰጡ ነገሮች ሲሰሙ፣ ሲያዩ ይረብሻቸዋል።
3. የጸና ሽሽት ውስጥ ይገባሉ፦
ስለሁኔታው ትውስታ የሚሰጣቸውን ላለመስማት፣ ላለማየት፣ ሰዎችንም ላለማግኘት በጽናት ይሸሻሉ። ትውስታውንም ለመርሳት ሱስ ይጠቀማሉ።
4. አሉታዊ አስተሳሰብ እና ስሜት ይኖራቸዋል፦
''እኔ መጥፎ ነኝ፣ ማንም ሰው አይታመንም፣ አለም ክፉ ናት'' የሚሉ አስተሳሰቦች በግለሰቡ ላይ ይነግሳሉ። እራስን መውቀስ፣ እራስን ለማጥፋት መገፋፋት፣ ሌሎችን መውቀስ እንዲሁም ለከፋ የአዕምሮ ጤና መታወክ፣ ሱሰኝነት ብሎም ክፋት ይዳርጋሉ። ፍርሃት፣ ቁጭት፣ ቁጣ መግለጫቸው ይሆናል። እነዚህ ስሜቶች ቁጥጥር ከሌላቸው ሌሎች ሰዎችን ሳያውቁት ሊጎዱ ይችላሉ።
5. ድንጉጥ እና ደንታ ቢስ ሊሆኑ ይችላሉ፦
ቶሎ ይቆጣሉ፣ ሁሉንም ነገር በነቂስ ይከታተላሉ፣ ይበረግጋሉ፣ ይወራጫሉም። እንቅልፍ ላይ ይሰቃያሉ፣ በህይወታቸውም ደንታ ቢስ ይሆናሉ።
ህክምናው፦
የስነልቦና እንዲሁም የመድኃኒት ናቸው። ጊዜ የሚፈልግ እና ቀስ በቀስ በሂደት የሚስተካከል የህመም አይነት ስለሆነ በጊዜ ህክምና ከተገኝ ውጤታማና አመርቂ ይሆናል።
#PTSDawareness June 27
ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ (MD, Psychiatrist)