Telegram Web Link
Channel name was changed to «መንፈሳዊ ግጥም እና መነባንብ»
የመጋቤ ምሥጢር መሠረት ተሰማ የንባብና ዜማ ትምህርት ሕይወት ፤ በራሳቸው አንደበት ሲተዘት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አርታኢ ወአስተጋባኢ፦ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

መንደርደሪያ

ታኅሣሥ ፳፪ ቀን 2013 ዓ.ም
ከኮሮና አመጣሽ የዘጠኝ ወር አሰልቺ እረፍት መልስ የተጀመረው ትምህርት እየተጧጧፈ ያለበት ጊዜ በመሆኑ እኔም ሆነ ወንድሜ አብነት የተወጣጠረ ጊዜ ላይ እንደነበርን አስታውሳለሁ።
ይህ አስቸጋሪ ወቅት ሊቁ መምህራችን እንደልብ ለመጠየቅ አላስቻለንም። እንዲህ ባለው ጊዜ ነው እንግዲህ “ባስቸኳይ እፈልጋችኋለሁ” የሚል መልእክት በልጅ ልጃቸው ዲያቆን ናታን በኩል የተላለፈልን።

እንዲህ ያለ አስቸኳይ ጥሪ ስላልተለመደ ወዲያው ወደ ቤታቸው ሄድን። ከሳሎኑ ስንገባ ከሳሎኑ ስንገባ በተለመደ ሞቅ ያለ ሰላምታ ተቀበሉን። እንደሌሎቹ ጊዜያት ግን ትንሽ ትልቅ በማይመርጥ ትኅትና ቆመው ለማስተናገድ ቤት ያዋላቸው መጠነኛ የእግር ሕመም አላስቻላቸውም።
ከዚህ በኋላ ያሉን ነገር ቃል በቃል አይረሳኝም።

“እንግዲህ ነገ የሚፈጠረው ነገር አይታወቅም። እናንተ የመጨረሻ ልጆቼ ናችሁ። ይኼን ሁሉ ጊዜ ደክማችሁ አንድ ነገር ብሆን ልፋታችሁ ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር የተማራችሁትን ዘርዝራችሁ ጽፋችሁ እንድታመጡልኝና የምስክሩን ወረቀት እንድሰጣችሁ ነው የጠራኋችሁ። እሱን ከያዛችሁ እንግዲህ አቅም እስከፈቀደና ነፍስ እስክትወጣ ድረስ ትቀጥላላችሁ።” ነበር ያሉን።

በጊዜው ንግግሩ ከማስደንገጥ ይልቅ አስገርሞን ነበር። ”ትንሽ እግራቸውን ያዛቸው እንጂ አሳሳቢ የሆነ የጤና እክል አልገጠማቸውም። ለምን እንዲህ አሉ?” ብለን ግራ እንደ መግባት አለን። ወዲያው ግን መምህር ደረጀ ከ4 ወይም ከ5 ወር በፊት የጉባኤ ቤታቸውን(በኋላ መካነ መቃብራቸውን) ሁኔታ እንዲመለከትና ጥገናም ያስፈልገው እንደሆነ እንዲያየው ያደረጉትን ነግሮኝ “እኚህ አባት ምን ታይቷቸው ነው?” ያለኝን አሰብኩና “ምናልባትም ለበቁ አበው ቀድሞ የሚሰጥ ነገር አለ።” በሚል እምነት የታዘዝነውን ግዴታ ፈጽመን ከ2 ቀን በኋላ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን የምስክር ወረቀቱን ይዘን ሄድን። ጽሕፈቱን በሚገባ ተመልክተው ሁሉም ሳይጓደል መካተቱን ካረጋገጡ በኋላ “የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ማኅተም በቅድሚያ ማረፍ አለበት። ሂዱና አስመቱ” ብለውን ያንን አስደርገን ከሁለት ቀን በኋላ ተመልሰን በመምጣት የራሳቸውን ማኅተምና ፊርማና ማኅተም አኑረውልን ሁለቱን ኮፒ ለእኛ ቀሪውን ሁለት ኮፒ ለራሳቸው ካስቀሩ በኋላ እንዲህ አሉ።

“እንኳን ደስ አላችሁ። ይኼን በብዙ ድካም የጨረሳችሁት መንፈስ ቅዱስ ስላበረታችሁ ነው። እኔም ደግሞ በተጋድሎ ሳይሆን ሥራዬ ግዴታዬ ስለሆነ ጤንነት ሰጥቶኝ እኚህን ዓመታት (5 ዓመታት) ማንም የማያገኝውን ዕድል መንፈስ ቅዱስ ሰጥቷችሁ ተማራችሁ። ወንጌልን ብቻ ለመማር አምስት ዓመትም የማይጨርሱ አሉ። እናንተ ግን ሐዲሳትን ሙሉ ትርጓሜያቸውን ከብሉይ የዳዊትን ትርጓሜ አጠናቃችሁ እንዲያውም ቅዳሴንና ሃይማኖተ አበውን ጨምራችሁ እዚህ ደርሳችኋል። ታዲያ እናንተ እዳ አለባችሁ። ‘በከንቱ የተቀበላችሁትን በከንቱ ስጡ’ ይላልና ቃሉ።”
ይኼን ካሉ በኋላ ለእኛ በከንቱ የሰጡትን ዕውቀት በከንቱ የሰጧቸውን መምህራን ሊዘረዝሩ ፣ የአብነት ትምህርት ሊተርኩ ገቡ። እኔም ይኼንን እንደወረደ ምንም ማሻሻያና ጭማሪ ሳላደርግ አቅርቤዋለሁ።
ልክ መንግሥቱ ለማ ለ48 ሰዓት ከሊቁ አባታቸው ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ምንም ሳይጨምሩ ቃል በቃል “መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ ወልደ ታሪክ” ብለው እንዳሳተሙት በተለይ የመጋቢን አንደበተ ርቱዕነትና የቋንቋ አጠቃቀም ፣ የጊዜውንም መንፈስ በሚገባ ያሳያልና ይልቁንም በEOTC TV ላይ ከተላለፈላቸው በራሳቸው አንደበት ከተገለጠው የሕይወት ታሪክ አንጻርም ዘርዘር ያለ ገለጻ ያለው በመሆኑ ሰፊ ግንዛቤ ያስጨብጣል ብዩ አምናለሁ። ከዚህ ቀጥሎ ያለው ሙሉ በሙሉ የእሳቸው ቃል ነው።

ተቀምጦ ማስተማር

እኔ ለአባቴ ለአስተማሪዬ ትንሽ ልጅ ሆኜ እንደ በኵር እንደ በኵረ ተማሪ እቆጠር ነበር። የመጽሐፍ መምህሬን። እጃቸውን ይዤ አብሬያቸው ተቀምጬ ነበር ምውል። ያ ነው አሁን እኮ ተቀምጦ ተማሪዎችን ለማስተማር የረዳኝ የልጅነቴ ጊዜ ሁኔታ ነው።
ያኔ መቀመጥ ያልተማረ ልቅሶ መሄድ ሠርግ መሄድ ሚያበዛ ዛሬ መቀመጥ አይችልም። እኔ ልቅሶ አልሄድም። ሠርግ አልሄድም።የታመመ አልጠይቅም። የታሠረ አልጠይቅም። አስተማሪ ነኝ አስተምራለሁ።

ንባብ ዜማና ቅኔ

ስንት መምህራን ዘንድ ተምሬያለሁ? ንባብ ከተማርኩባቸው መምህራን የመጀመርያው የተከበሩ አባት መምሬ ዳምጤ ገብረ ጊዮርጊስ ናቸው። ከፊደል ጀምሮ ዳዊት ያስደገሙኝ። በጥቂት ጊዜ ውስጥ። “እንደገና ዳዊት ደግሞ መከለስ አለብኝ እነ አርጋኖን እነ ሌሎችም ንባብ ማስፋፋት አለብኝ” ብዬ ያስተማሩኝ ክቡራን አባቶቼ መምሬ ሣህሌ አባ ፋንታዬ አባ ገብረወልድ ጠቅላላ ከእኚህ አራት አባቶች ዘንድ ንባብ ከጨረስኩ በኋላ እዚያው የተወለድኩበት ሃገር አንጎለላ መጣሁ። እንደ እድሌ ሆኖ ከንባብ በኋላ በዜማ ቤት በመጽሐፍ ቤት ያስተማሩኝ መምህራን ዓይነስውራን ናቸው። ሦስቱ።
ከዚያ አሁን ዜማ ፤የቤተልሔም ዜማ ይባላል፤ የኔታ ምትኬ ዘንድ። አባቴ እንድማርለት ይወዳል። እዚያችው ቤተክርስቲያን አጠገብ አክስት አሉኝ ፤ ወይዘሮ አስካለ ገብረሕይወት የሚባሉ ፤ እንደ በግ እየጠበቁኝ ሲያገኙኝ እዚያው ሲያገኙኝ
“አለ?”
”አዎ”
“ይማራል?” እያሉ እየተቆጣጠሩኝ የኔታ ምትኬ ጋር ቀጸልኩ።
ዓይነ ሥውር ናቸው የኔታ ምትኬ። ከየኔታ ምትኬ ዘንድ ደግሞ ጾመ ድጓ ጀመርኩና የቃል ትምህርት የሚባል አለ። መስተጋብዕ። ከሰኞ እስከ ዓርብ ድረስ። ጾመ ድጓ ጀምሬ ልጆች እንሂድ ሲሉ ጅሩ ዳዋ የሚባል ሃገር አለ ሃገራችን። ዳዋ ኢየሱስ ይባላል። አለቃ ወልደ አብርሃም ዘንድ። አለቃ ወልደ አብርሃምም ዓይነ ስውር ናቸው። እሳቸውም ደግሞ ዘንድ ጾመ ድጓ ስናጋምስ እንሂድ ተባለና በጌምድር ። ጎንደር ማለት ነው። ሰሜን ጎንደር። ገና ዓባይን ሻገር ስንል ምክሬ ማርያም የምትባል አለች። እሷ ጋር የኔታ ይኄይስ የሚባሉ አሉ። በጣም በጣም በጣም ግሩም የሆኑ መምህር ናቸው። መንደር ሰጥተውን እንደ ወንድሜ የሆነ ጓደኛዬ አለ። የማንለያይ። አብረን ስንሄድ ለእርሱም ስም ለእኔም ስም አውጥተው እሱን ዜናዊ እኔን ጸዳለብርሃን ብለው ሰይመው እኔን በተለይ ባለቤታቸውም ሆኑ እሳቸው በጣም ይወዱኝና ያቀርቡኝ ነበር።መምህር ናቸው። ጸሐፊ ናቸው። እማራለሁ እላቸዋለሁ።ለምሳ ሲገቡ “ና እንጀራ ብላ” ይሉኛል “አልበላም የኛ እንጀራ ምን ሁኖ ነው” እላቸኋለሁ። ያመጣላ ዜናዊም። በግድ ያስገቡኛል። እና እዚያ ሳልለይ ከማዕዳቸው ተምረን ጾመ ድጓ ዘለቅን። የቃል ትምህርት ክሥተት አርያም የሚባል አለ መወድስ ያንን ሁሉ ተማርንና እንደገና አሁን ደጋ ወጣሁ ጋይንት። ይኼ ቆላ ነው። አንዳቤት ይባላል። ሰሜን ጎንደር ነው ይኼም። ከዚያ ከአንዳቤት ምክሬ ሐናን ለቀቅሁና የጥጆ ማርያም የምትባል ዙርአምባ የሚባል የአቡነ አረጋዊ ገዳም አለ። ከዚያ በአፋዛዥ ናት። የገዳሙን ተራራ እንደዚህ እንደ ጭላሎ ተራራ ነው ምናየው። የሁለት ሰዓት መንገድ አይሆንም በእኛ አካሄድ። ሂጀ አልሳምኩም እዚያ። ጓደኛዬ ሄዶ “ዙርአማባ የተባለውን ዞረን አይተን መጣን።” ይለኛል። ግድ የለኝም እኔ። እንደ አጋጣሚ ሲሆን ብዙ ገዳሞችን ረግጫለሁ። “ይኼ ገዳም ማነው?” “እገሌ ይባላል” “ፍቀዱልን
👍76
እስቲ ገድሉን እዚያ ያለውን እናንብ” እላቸዋለሁ። “ጥሩ!” ይላሉ ገዳማውያኑ እያበሉ ዐሥራ አምስት ቀን ወይ ሳምንት ተቀምጬ ነው እንጂ የገባሁበት ገዳም ዝም ብዬ አልሄድም። በበዓል አይደለም የምሄደው። ከተጓዦች ጋር አይደለም የምሄደው። ከዚያ ሳሊ ገበያ አጠገብ ወፍ ዋሻ የምትባል አለች። የዝማሬ መዋሥዕት መማርያ ናት። እዚያ የተማረ ዙር አምባ ሄዶ ይመረቃል። ዝማሬ መዋሥዕት አልሞከርንም።
እዚያ ጋይንት የኔታ እጅጉ የሚባሉ ዘንድ ዜማ በጥቅሉ ከአራት መምህራን ዘንድ ዜማ ተማርንና እኔም ጓደኛዬም አንለያይም። ሰባክያን ሲሰብኩ ምን ሲሉ ደስ አለን። መንፈስ ቅዱስ መራን። ትርጓሜ ለመማር ደሞ የት እንሂድ ብለን አየን። እዚያም መካነ ኢየሱስ ነበሩ አንድ ታላቅ አባት። አባትህ እዚያ ተምረዋል መልአከ ምሕረት። የትግሬ ሰው ናቸው። የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ ነው ሚባሉ። የቅኔና የመጽሐፍ መምህር ናቸው። አዪ! ወንበር አይደርስም። በዚህ ላይ ሰውየው ጸሎተኛ ስለሆኑ ወደ ቅኔ ማስነገሩ እንጂ ወደ መጽሐፉ አይደሉም። ስንጠይቅ “መጽሐፍ ድሮውንም እዚህ አይደለም ሂዱ ጎጃም ዲማ” ተባለ።

ቅኔስ።

መርጡለማርያም ጥሩ የሆኑ አባት ነበሩ። አለቃ ኢሳይያስ ይባላሉ። ዋድሌ ናቸው። መምህር የሆኑ ፤ አባት የሆኑ በእውነት! ትንቢተ ኢሳይያስ ናት ልጃቸው። ቅኔ ትቀኛለች። አታሲዝም። ትንቢተ ኢሳይያስ ነው ስሟ። እዚያ ገባን። እዚያም ደግሞ አሁን ግብረ በላ ነኝ እኔ። አይለቁኝም በእድሜ ስላነስኩኝ። ሌላ የለም እኮ አዪ እኔ ደሞ ወደ ትምህርት ስል ዛሬ ቅፈፋ ሲሉ አዪ እላለሁ። ጓደኛዬ ይሄዳል ያኔውኑ። የእኔንም ለእርሱ ስጡ ብዬ ለመንደሮቹ ስላሳወቅኩ ይሰጡታል የሁለታችንንም እንጀራ። የሚሰጡት ምንድነው ለእኔ ሲባል ቅርብ ቦታ መደቡኝ። ለእኔ አምስት ቤት ለእርሱ አምስት ቤት ዐሥር ቤት። ከዐሥር ቤት አንዳንድ እንጀራ እየታጠፈ ነው ሚሰጠው። ጨው ስጡኝ ካለ አንዳንድ ጭልፋ ጨው ይሰጣሉ። ጨው ማለት እዚያ ድልህ ነው። ያንን ይዞ ይመጣል። “አዪ እንጀራ በጨው አይደለም ና ና አንተ” ይሉኛል። ልክ እንደ የኔታ ይኄይስ አሁንም እዚህ ግብረ በላ ነበርኩ። የኔታ እጅጉ ቤት ግብረ በላ አይደለሁም። ወንድሜ ያመጣል እንጀራ። እንዲያው አንዱ የገብስ እንጀራ እንኳን ለሁሉ ይበቃል። መንደራቸው የራቀ ልጆች ይሳተፋሉ ከእኛ ጋር። እንግዳ ሲመጣ እናሳትፋለን። እግር አጥበን ራት ሰጥተን እናበላለን። የኔታ እጅጉ ቤት አልበላሁም። የኔታ ምትኬና ሸዋ ላይ የጠቀስኳቸው መምህራን ንባብ ያስተማሩኝ ጋርም አልበላሁም። ወላጆቼ አካባቢ ስለሆነ አንጎለላ መምሬ ዳምጤም አያቴ ቤት አጠገብ ስለሆኑ ቤቴም ቅርብ ስለሆነ እንጀራ ከቤቴ ነው ምበላው። አንጎለላም ደጀ ሰላም ሁሉ አለ አልሄድም። ልምድ የለኝም የደጀ ሰላም። ከዚያ እንግዲህ በየዓመቱ ደብረ ሊባኖስ አንቀርም እኔም ወንድሜም።

እንግዲህ ቅኔ የኔታ ኢሳይያስ ዘንድ ግሩም በሚያሰኝ ሁኔታ ተቀኘሁ። እዚያ ብሉይ መጻሕፍትን ተማርኩ። “እማራለሁ እይዛለሁ አይ የኔታ ይጠይቁኝ እንጂ እኔ ይኼንን ሁሉ በቃል ሳጠና አልገኝም። በቃል ለምን አጠናለሁ እኔ መጽሐፍ አለ አይደለም ወይ? ያስረዱኝ ይጠይቁኝ” እላቸዋለሁ። ደስ ይላቸዋል በቃ። ከዚያ ጀምሮ ነው እንግዲህ በቃል ትምህርት ላይ ያለኝ አቋም እንዲያ የሆነው።
በዚህ ሁኔታ አራቱን ብሔረ ነገሥት ስምንቱን ብሔረ ኦሪት የኔታ ኢሳይያስ ዘንድ ከቅኔ ጋር እኔና ወንድሜ ተምረን እዚያ እንግዲህ ዜማ ተውን። ዜማ ለምን ተዋችሁ ብለኸኝ ታውቃለህ? የተውኩበትን ምክንያት ነግሬአችኋለሁ? አልነገርኳችሁም።
አሁን ከአንጎለላ ጀምሮ በደቡብ ጎንደር የተማርኩት የቤተልሔም ዜማ ነው። ቁሙ ማለት ነው። አቋቋም አልተማርኩም። አቋቋም መማር ከቅኔ በኋላ ስለተባለ ወደ ጎጃም መጣሁ ማለት ነው። የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ ዘንድ ብንሄድ ወንበራቸው ፈጣን አይደለም። ዋልን አደርንና እንዲህ ነው ሚማሩት አዎ አይ እንሂድ አልን መርጡለማርያም መጣን ኢሳይያስን አገኘን። ባለቤታቸው እንዴት ያሉ ናቸው። እንዴት መጣችሁ ወንድሞች አሉ። የት ናችሁ ሸዬዎች ናችሁ አሉ። ያውቁናል በመልካችን ባነጋገርም።
“እንዴት መጣችሁ?”
“ኧረ እንዲያውም ጋይንት ድረስ እንዲህ ሄደን ነበረ።” ብለን ስንላቸው ገረማቸው።
“አንተም እዚያ ሄድክ?”
“አዎ”
“አዪ ቅኔ ለመማር ነው?”
“አዎ”

ጭናቸውን መታ መታ አድርገው ቅኔ ሲጀምሩ ቀድመን እንገኛለን። የቅኔው ተማሪ ሲሄድ መጽሐፍ ያስተምራሉ። ቁጭ!
“ምነው?”
“እኛም እንማራለን!”
እንዳጋጣሚ ኦሪት የጀመሩ ነበሩ። ከነእርሱ ጋር ሄድን። ዳዊትን ከጨረስን በኋላ መጽሐፈ ነገሥት ከተማርን በኋላ ሐዲሳት ልንማር ብለን ቅባቶች ናቸው እዚያ ያሉት።
ዜማ የተውንበት ምክንያት ይኽ የጎጃም ዜማ አጫብር ፣ ወጨሬ ሦስተኛም አለ ስሙ ጠፋኝ እንዲህ ያለ ነው። ርዝመቱ አንጀት ይበጥሳል። ዜማው ጥሩ ነው። ግን ማይዘለቅ ነው ርዝመቱ። ልብ ያፈርሳል። ወረብም ስንገባ ለመወረብ የጎንደሮች አጭር አጭር ናት።
የነሱ እንደዚያ ሲሆንብን ዜማ ተውን ተውን ተውን!

ከዚህ የቀጠለውንና የተረፈውን በEOTC TV ከተላለፈው የአንደበታቸው ምስክርነት ያድምጡ።

@menfesawi_getem_ena_menebanb
👍4
፥፥፥፥ ድንግል አርጋለች፥፥
@menfesawi_getem_ena_menebanb
.

.
መጥቁል በተንኮል - ከማይደርስበት
ሄሮድስ ሰይፍ ይዞ - ከማይሄድበት
ልቧ በሀዘን - ከማይጎዳ
ከድካም ዓለም - ከምድር ጓዳ
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች።
.
.

ሰዶም፣ ገሞራ - ከሱባማ
ሱባዮንና - አድያማ
ከእሳት ገብተው - ከነደዱበት
በኃጥአት ምክንያት - ሞትን ካዩበት
የኖህን ዘመን ሰው - በእርጥብ እሳት
ከለበለበው - የግፍ ትኩሳት
ከዚሁ ምድር - ከቅጣት ሰፈር
እንዳይገባት - ለእሷ መደመር
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች።
.
.
በሰማይ ሆነው - ስለሚጣሯት
ሊያይዋት ጓግተው - ተነሽ እያሏት
በህብረ ምሳሌ - በአፈ ነቢያት
ሁሉም ሠራዊት - ሁሉም መላእክት
ድንቅ አቀባበል - እያደረጉ
እሷኑ ሆኖ - የሰማይ ጥጉ
ለአምላክ ማደሪያ - የሚሆን ማደሪያ
ማረፊያ ክፍሏ - ስሙ መጠሪያ
አንክሮ ሆኖ - ለቅዱሳኑ
ለዚህም ደስታ - እንዲፋጠኑ
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች
.
.
የምድሩን ልትስብ - ወደ ከፍታ
ልትጎትተው - ወደ እርፍት ቦታ
ለድል ትንሳዔ - አብነት ሆና
ቶማስ እንዳያት - ከፍላ ደመና
የኛስ መመኪያ - በቀኝ ቆማለች
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች።

(አክሊሉ ደበላ ነሐሴ 16/2009ዓ.ም)
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
1👍1
ግሸን ማርያም !
።።።
ኤልያስና ኤልሳ በእድሜ ገርጅፈው
ልጄ 'ማይሉትን...
ደፍረው 'ማይቀርቡትን...
አቅፋ ስማዋለች በ አስራምስት ዓመቷ
ድንግል ወላዲቷ
.
ሰዎች ውሸት አሉ ማረጓ ተናቀ
ግና...
አዲስ ሰማይ አይቶ ሰማይ ተደነቀ
.
በማህፀን እሳት ... መለኮትን ማጀብ
አጀብ!
.
የዓለም ትልቁን በማህፀን ይዛ
ማማለድ አትችልም አለኝ ያ ፈዛዛ
አሁን ምን ይሉታል ለትልቁ ታጭቶ ትንሹን መከልከል
እንደዚህም አይደል !
.
አለቀብን ወይን ሳሳብን ማጀቱ
እሱ ግን ባረከው ስትነግረው እናቱ
ቅጠል ለቅሞላታል ያኔ ህፃን ሳለ
ወላጅህን አክብር
ይሉት የኦሪት ህግ እንዲሁ ቀጠለ...
.
ተከትዬህ ከጫፍ መስቀልህ ስር ቆሜ
በመለየት ፍርሀት በፅኑ ታምሜ
ሳለቅስ ሲከፋኝ ስደበት ሳነባ
ድንግልን ሰጠኸኝ የሞገሴን ካባ !
Michael Aschenaki
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
👍31
ግጥም በእንተ
#መጻጉዕ
@menfesawi_getem_ena_menebanb

የቱ ፍቅሬ ስቦህ እንደምን ፈታኸኝ
እኔ እኮ ብኩን ነኝ...
አንተ ስትሰቀል ከአይሁድ ጋር የምገኝ
እኔ እኮ ምንም ነኝ ተራ የህመም ሰው
ጌታዬ እንድትምረኝ ምክንያትህ ምንድነው

በከሀሊነትህ ቢቆምም የኔ አሳር
ከደግነት ደጅህ የቆረጥኩኝ ምሳር
ብትወደኝ ብትምረኝ እኔ ምንተዳዬ
ከሰቀሉህ ጋራ ልስቀልህ ጌታዬ
እንዲ ነኝ መጻጉዕ ውለታ የምረሳ
ስወድህ እንድኖር ህመሜን አትፈውስ ቀንበሬን አታንሳ
ስንኩል ነው የኔ እግሬ ለሐሰት ያጋደለ
ጠማማ ነው ልቤ ፍቅርህን የጣለ
ቀጤማ ነው እጄ ክፋት ያቃጠለው
ያዙት ያን ክርስቶስ ብሎ የሚጠቁመው
እውር ነው ብሌኔ እያየ የሚከዳ
ከደግነት ኩሬ መአት የሚቀዳ
እዳ ነኝ ለራሴ እዳ ነኝ ለዓለም
ሲጀመር ነው የካድኩህ ሲፈጸም አይደለም
ከወንዙ ጥግ ሆኜ በአልጋዬ ላይ ሳለሁ
አምንብህ ነበረ ስትፈውስ እያየሁ
አልጋህን ተሸከም ስትለኝ ምን አልባት
ልቤን አናተበው የመራመድ ክፋት
አትማረኝ መድኅኑ በአልጋዬ ላይ ልክረም
አልጋዬን መሸከም ለኔ መጥፋት እንጂ መፈወስ አይደለም
እባክህ ክርስቶስ እባክህ ጌታዬ
አንተን ከምከዳ አልጋዬን አዝዬ
የዳዊት ልጅ ተወኝ አትፈውሰኝ ይቅር
መች እክድህ ነበር ልክ እንዲህ ከነበር ::

ዳዊት አየነው
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
3👍1😢1
እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሠረት ተሰማን ቢያንስ በወር አንደዜ “ለምን መጽሐፍ አይጽፉም?” የሚል የልጅነት ቅንዓት ፣ ጉጉትና ምኞት የወለደው ሃሳብ በጉባኤ መሃል ወርወር ባደረግላቸው ቁጥር እንዲህ ብለው ይመልሱ ነበር።
“መጽሐፍ ልጻፍ ብል ቤት መቀመጥ ፣ መጻሕፍት ማገላበጥ ግድ ይሆናል። ይህ ደግሞ የእናንተን የትምህርት ጊዜ ይሻማል። ስለዚህ እኔ እናንተው ላይ መጻፉን መርጫለሁ። እናንተ ደግሞ መጽሐፉን ትጽፉታላችሁ።”
ይህ አነጋገራቸው “ሰዎች ሁሉ በሚያውቁትና በሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደሆናችሁ የተገለጠ ነው።” የሚለው የቅዱስ ጳውሎስን ኃይለ ቃል ይመስላል።
እንዳሉትም እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነትን ሦስትነትን ማመንን የሚያጸና ትምህርት እየጻፉ አረፉ። “መጽሐፉን እናንተ ትጽፉታላችሁ” የሚለው ትንቢትም ከዐሥር ዓመታት በፊት በበኩር የመንፈስ ልጃቸው በዲ/ን ዶ/ር አቤል ኃይሉ “የማእዘን ራስ” መጽሐፍ ተፈጽሟል። እነሆ አሁን ደግሞ የገዛ ብዕራቸው ውጤት “መጽሐፈ መሠረት” በሚል ርእስ ለኅትመት ብርሃን በቃ።

ይኼን መጽሐፍ የማዘጋጀት እድሌን አደንቃለሁ። ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር ይኼ ኃላፊነት ወደ እኔ እንዲመጣና እኔም በልዩ ትኩረት እንድፈጽመው ያደረጉኝ ክስተቶች ግን አሉ። በሕይወተ ሥጋ ሳይለዩን የአብነት ትምህርት የምስክር ወረቀት ከሰጧቸው የመጨረሻ ልጆቻቸው ማካከል አንዱ መሆኔ ፣ የመጨረሻ የጉባኤ ስብከታቸውን ያደግሁበትና በሰ/ት/ቤት አመራርነት ያገለገልኩበት ደብሬ ባዘጋጀው የኅዳር ሚካኤል ጉባኤ ላይ ጋብዣቸው ያስተማሩ መሆኑ ፣ በመጨረሻ በግል ሄጄ የተቀበልኩት የ”ዕዳ አለብህ” ቃላቸው ፣ የጊዜ ዕረፍታቸው የዓይን እማኝነት ዕጣ ከመንፈስ ልጆቻቸው መካከል እኔ ጋር የወደቀ መሆኑ በአጋጣሚ የሆነ አይመስለኝም።

ይልቁንም ዜና ሕይወታቸውንና ሥራዎቻቸውን ይዞ የወጣው የዳረጎት ልዩ ዕትም ዋና አዘጋጅ መሆኔ እኔ በግሌ ካሰባሰብኳቸው ሰነዶች በብዙ እጥፍ የሚበልጡ የልዩ ልዩ ዘመን አበርክቶአቸው እጄ እንዲገባ ምክንያት ሲሆን አንድ ላይ ሰብስቦ መጽሐፍ የማድረግ ሐሳብ ተፀነሰ። በፈቃደ እግዚአብሔርም እዚህ ደረሰ።

መጽሐፉ ሦስት አበይት ምእራፎች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው ምእራፍ ለኮርስ ስልጠና የተዘጋጁ ወጥ ሥራዎች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምእራፍ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በጽሑፍ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በጽሑፍ የሰጡትን ምላሽ ይዟል። የመጨረሻው ምእራፍ የሕይወት ታሪክ አምድ ሆኖ የግላቸውን የጉባኤ ቤት ቆይታ በወፍ በረር ፣ ለስንክሣርና ግብረ ሕማማት መተርጉም ወዳጃቸው ለሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ የጻፉትን በቅኔ የተዋዛ ጽሑፍ ፣ እንዲሁም ዜና ሕይወታ ለማርያም ድንግልን አካቷል።
በቅጽ አንድ የተካተቱት ሥራዎቻቸው ለኅትመት በሚበቃ ምሉዕነት ስለተገኙ ብቻ እንጂ በቀጣይ ተሟልተው የሚዘጋጁ ብዛት ያላቸው ርእሰ ጉዳዮች እንደሚኖሩ ይታወቅልኝ።
በተረፈ ስለ ብዕራቸው የሥነ ጽሑፍ ውበት ፣ የምሥጢር ጉልበትና የሐሳብ ፍሰት እየተነተኑ ሊቁን ለእናንተ ማስተዋወቁ አስፈላጊ አልመሰለኝም። “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” ይላልና ቃሉ ከፍሬያቸው ዕወቋቸው። የቻልኩትን ያህል ለቅሜ በያዛችሁት ቅርጫት አኑሬላችኋለሁ። የተባረከ ማዕድ ይሁላችሁ።
https://www.instagram.com/p/CqYPYpXIA4T/?igshid=MDJmNzVkMjY=
3👍2
ፊርማ ለወዳጅ

ለመላው አብሮ አደጎች ፣ አብሮ አገልጋዮች ፣ ክላስ ሜቶች ፣ ወዳጆችና የመንፈስ ልጆች በሙሉ።

አንዳንዶቻችሁ በቅርብ ለገበያ የቀረበውን መጽሐፌን " አዘጋጁ ካልፈረመበት አንገዛም ሙተን እንገኛለን" ማለታችሁን ሰምቻለሁ። ሌሎቻችሁ ደግሞ "ለበዓል መጥተን ሰኞ ፣ ማክሰኞ ሂያጅ ነን። መጽሐፉን አስቀምጥልን" እያላችሁ በውስጥ መስመር እየወተወታችሁኝ ነው። እኔ የሺህ ወዳጅ ወንድማችሁ ወገቤ እስቲንቀጠቀጥ ጥፌ ማዘጋጀቴ አንሶ እናንተን እግር በእግር እየተከተልኩ መጣፍ ማቀብልበት ጊዜውም ጉልበቱም የለኝምና የግቢ ጉባኤ ፣ የዓለም ት/ቤት ፣ የፕሪፕ ፣ የሚካኤልና የሌላም ሌላም የሰፈር ወዳጅ ፣ ጓደኛ ፣ ደቀ መዝሙርና ደቂቀ መዝሙር ሁሉ በትንሣኤ ዋዜማ በቀዳም ሥዑር ዕለት በደብረ መድኃኒት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ከትተህ ላግኝህ። ማኅተምና ፊርማዬን ከስምህ ጋር ከትቤ እንዳስፈላጊነቱም በሥዕል አስውቤ ዘላለማዊ የወዳጅነት ማስታወሻ ይሆን ዘንድ መጽሐፈ መሠረትን አበረክትልሃለሁ። መርኃ ግብር አይደለም ደግሞ መጥቶ መሄድ ነው። አንድ የጋራ መገናኛ ለመፍጠር ያመች ዘንድ ነው። ማን ያውቃል በስንት እግዚኦታ ፣ ሠርግና ምርቃት መገናኘት ያልሆነለትን ጀማ ማገናኛ ሰበብ ይሆናል። ዘር ፣ ቀለም ፣ ጾታ ፣ እድሜ ፣ ባች ፣ ጸባይ ፣ የአመራርነትና የሥራ እርከን አይለይም። "ከሣችን አውቀዋለሁ" የሚል ሁሉ ጎራ ይበል።
https://www.instagram.com/p/Cq8b-10oXh8/?igshid=MDJmNzVkMjY=
1👍1
#ጎጆ_ቀለስኩልህ
@menfesawi_getem_ena_menebanb
(በሰመረ ፍስሃ)

በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ
ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ
የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ
እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡
...................ወዲህ ሲመልሰኝ

ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ
...................ጉድፌን አፅድቶ
ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል
ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡

ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ
በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡

ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ
የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ
አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል
አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡

የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም
አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም
ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ
የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡

ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ...
የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ
ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ
አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ
ሁሌ 'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡
ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል
ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡

እናም ሚካኤል ሆይ....
ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ
በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡
_
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
4👍4😁1🤔1
መንፈሳዊ ግጥም እና መነባንብ pinned «የመጋቤ ምሥጢር መሠረት ተሰማ የንባብና ዜማ ትምህርት ሕይወት ፤ በራሳቸው አንደበት ሲተዘት ፨፨፨፨፨፨፨፨፨ አርታኢ ወአስተጋባኢ፦ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ መንደርደሪያ ታኅሣሥ ፳፪ ቀን 2013 ዓ.ም ከኮሮና አመጣሽ የዘጠኝ ወር አሰልቺ እረፍት መልስ የተጀመረው ትምህርት እየተጧጧፈ ያለበት ጊዜ በመሆኑ…»
አበው ስለ እመቤታችን

"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው "  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት" ቅዱስ አውግስጢኖስ


"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"  ቅዱስ ኤፍሬም

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
4👍4
፥፥፥፥ ድንግል አርጋለች፥፥
@menfesawi_getem_ena_menebanb
.

.
መጥቁል በተንኮል - ከማይደርስበት
ሄሮድስ ሰይፍ ይዞ - ከማይሄድበት
ልቧ በሀዘን - ከማይጎዳ
ከድካም ዓለም - ከምድር ጓዳ
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች።
.
.

ሰዶም፣ ገሞራ - ከሱባማ
ሱባዮንና - አድያማ
ከእሳት ገብተው - ከነደዱበት
በኃጥአት ምክንያት - ሞትን ካዩበት
የኖህን ዘመን ሰው - በእርጥብ እሳት
ከለበለበው - የግፍ ትኩሳት
ከዚሁ ምድር - ከቅጣት ሰፈር
እንዳይገባት - ለእሷ መደመር
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች።
.
.
በሰማይ ሆነው - ስለሚጣሯት
ሊያይዋት ጓግተው - ተነሽ እያሏት
በህብረ ምሳሌ - በአፈ ነቢያት
ሁሉም ሠራዊት - ሁሉም መላእክት
ድንቅ አቀባበል - እያደረጉ
እሷኑ ሆኖ - የሰማይ ጥጉ
ለአምላክ ማደሪያ - የሚሆን ማደሪያ
ማረፊያ ክፍሏ - ስሙ መጠሪያ
አንክሮ ሆኖ - ለቅዱሳኑ
ለዚህም ደስታ - እንዲፋጠኑ
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች
.
.
የምድሩን ልትስብ - ወደ ከፍታ
ልትጎትተው - ወደ እርፍት ቦታ
ለድል ትንሳዔ - አብነት ሆና
ቶማስ እንዳያት - ከፍላ ደመና
የኛስ መመኪያ - በቀኝ ቆማለች
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች።

(አክሊሉ ደበላ ነሐሴ 16/2009ዓ.ም)
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
👍2👏1
2025/10/28 06:06:18
Back to Top
HTML Embed Code: