Telegram Web Link
Forwarded from ፀዊረ መስቀል
8/12/2017
                              ማቴዎስ 7:12-26


   ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፥ ነቢያትም የሚያዝዙት ይህ ነውና ።

በጠባቢቱ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የምትወስድ ሰፊ በር፥ ሰፊ መንገድም አለችና፤ ወደ እርስዋም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው። "ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ፥ መንገድዋም ቀጭን ናትና፤ የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው።

“የበግ ለምድ ለብሰው ወደ እናንተ ከሚመጡ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፤ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ናቸው። "ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ ወይን፥ ከአሜከላም በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ ክፉ ዛፍም ክፉ ፍሬን ያፈራል። መልካምም ዛፍ ክፉ ፍሬን ማፍራት፥ ክፉ ዛፍም መልካም ፍሬን ማፍራት አይችልም። "መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። “እንግዲህ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋ ላችሁ።

“በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ ከሚያደርግ በቀር አቤቱ! አቤቱ! የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። «በዚያች ቀን ብዙዎች አቤቱ! አቤቱ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። ያንጊዜ ከቶ አላውቃችሁም፤ ዐመፅን የምታደርጉ ሁላችሁ ከእኔ ራቁ እላቸዋለሁ። ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ብልህ ሰውን ይመስላል። ዝናም ዘነመ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንም ቤት ገፉት፤ ነገር ግን አልወደቀም፤ በዐለት ላይ ተመሥርቶአልና.......


ሮሜ 9:24-ፍጻሜ
1 ጴጥሮስ 4:12-ፍጻሜ

ሐዋ.ሥራ 16:35-ፍጻሜ

           
👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ)
                
ምስባክ
                           መዝሙር 57:8-9


ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ

ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ክክሙ ሕለተ ኮነ

ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ

ትርጉም


እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም

እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ

ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል
11👍2
መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 1 ስንደሰት ወደ አለም ስናዝንና ስንከፋ ደግሞ ወደ ቤተክርስትያን የምንመጣው ነገር ማብቃት አለበት። ስናዝንም ስንደሰትም ወደ ቤተክርስትያን...❤️‍🩹
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 2


ነገ ተስተካክዬ እመጣለሁ አትበል !
ኃጢአትንም እየሠራህ ቢሆን እዛው ቤተክርስትያን ውስጥ ሆነህ ተስተካከል።
ወደ እግዚአብሔር መምጣትን የነገ ቀጠሯችን አናድርገው...🙏
👍148🥰1
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 3


ከቆረብኩ በኋላ በኃጢአት ብወድቅስ ብሎ ከቁርባን መሸሽ አያስፈልግም። ሐዋርያት እኮ ሐሙስ ምሽት ከቆረቡ በኋላ ነው አርብ ቀን ክርስቶስ ሲሰቀል ሁሉም በፍርሃት ክደውት የሄዱት።
ሰይጣን ከቁርባን እንድንርቅ የሚያመጣብንን እያንዳንዱን ሀሳብ መቃወም ያስፈልጋል !
32👍8🥰2
Forwarded from ታዚ (እንደ ልቤ)
ብዙ በጎችን የሚጠብቅ አንድ እረኛ ነበር። ታዲያ ከመንጋው ውስጥ አንድ በግ ሁልጊዜ ራቅ ብሎ፣ ተነጥሎ ይዞር ነበር። እረኛውም ይህንን በተደጋጋሚ ስለሚመለከት የበጉ እጣ ፈንታ አሳሰበው፣ በተኩላዎች እንዳይበላበት ተጨነቀ። ስለዚህ እያዘነ በራሱ እጆች የበጉን እግሮች ሰበራቸው። በመጀመሪያ ህመሙ ስለጠናበት በጉ እጅግ ተሰቃየ፣ አዘነም። ስለምን እረኛው በርሱ ላይ ይህንን እንዳደረገበት አላወቀምና።

ታዲያ እረኛው በጉን ተሸክሞት በሄደበት ሁሉ ይዞት ይዞር ነበር። በራሱ እጆች እያበላው፤ በፍቅር እየተንከባከበው  ከስሩ መዋልን አለመደው። በጉም ከእረኛው ስር መዋል ሲጀምር ፍቅርና እንክብካቤውን አስተዋለ።ከዚያ በኋላ ግን እግሩ ከዳነም በኋላ  ከእረኛው ስር መዋሉን መረጠ፣ እረኛው እንደሚወደውና እንደሚጠብቀው ስለተረዳ አመነው።

ወደራሱ ሊያቀርበን ሲፈልግና ከጎኑ እንዳያጣን ሲሻ አንዳንድ ጊዜ እግዚዓብሔር መሰበራችንን ይፈቅዳል። በፍቅሩ፣ በታማኝነቱና በቸርነቱ አብረነው እንድንኖርለት ሲፈልግ ልክ እንደ ሳምሶን ለህመምና ስቃይ አሳልፎ ሰጥቶ ወደራሱ ይመልሰናል።

በእግዚዓብሔር እጅ መውደቅ በዚች ዓለም ሀብትና ዝና ከሚገኘው ተድላ እጅግ ብዙ ይልቃል።

For comment inbox me @umbeya
በኃይሉ(ታዚ)
60🔥1🥰1
‎ ምንም ባንዛመድ በደም እና ስጋ
‎ ብንኖር ለየቅል እዚጋና እዛጋ
‎ ከተዋደደ ልብ ከተቀራረበ
‎     አንድ ሆኖ ካሰበ
‎ ወንድም እና ወንድም
‎   እህት እና እህት
‎ ወንድም እና እህት
‎             ለመሆን ከበቃ
‎ መወለድ ቋንቋ ነው
‎             እህቴ ነሽ በቃ።

🥰🥰🥰
46👍15
ቀረቤታችን በልክ ይሁን
መልካም ቀን🖐️
24👍3
የማርያም ንግስ ዕለት

(ኤፍሬም ስዩም)

የማርያም ንግስ ዕለት...
አዳፋ ነጠላ
የቀጠነ ገላ ፥ ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ...
ጥቁር ያዘን ቀሚስ ፣ ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች...
ከቤተስኪያን አጸድ ፥ ቆማ ከዋርካ ስር
አንዲት ሚስኪን ባልቴት ...ትለማመን ነበር
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም ፣ መሶቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ፣ ጀርባዬ ተራቁቷል፡፡
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ፣ ትለምናት ነበር
ከቤተስኪያን ጎሮ ፣ ቆማ ከዋርካው ስር፡፡
የደብሩ አለቃ
ካባ ላንቃ ለብሶ ፣ ምጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጩ ፣ ወደፊት ተስቦ
የንግሱን ምእመን ፣ ወደፊቱ ስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክ ብሎ ያስተምራል

የመቅደሱ ቀለም ፣ ሊታደስ ይገባል
የካህናት ደሞዝ ፣ ሊጨመር ግድ ይላል
ደጀሰላም ወንበር ፣ እጅጉን ያንሰናል
እናም...
ከዚህ ታላቅ ደብር ፣ ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን ፣ እጃችሁ የታለ? እያለ፡፡
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል፡፡
ለንግሱ የመጡ
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች...
ጥለት የለበሱ ፣ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ ...እፊት ከመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ ፣ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሰላሙ ፣ ደሞም ለወንበሩ
በሺ...የሚቆጠሩ
ብሮች ወረወሩ"
የደብሩ አለቃ ፣ ግንባር በጣም ወዛ
የሚወረወረው ፣ ብሩም በጣም በዛ፡፡
የዛች የምስኪን ነፍስ
ያች ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካው ስር
ተስፋዋ ማርያምን ፣ ትለማመን ነበር
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም ፣ መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኝም ፣ ማድጋዬ ጎድሏል
እለብሰው የለኝም ፣ ጀርባዬን በርዶታል

አንቺ ነሽ 'ተስፋዬ' ፣ የኔ 'ተስፋ 'ሞቷል
ወድቃ እየተነሳች
እንባ እያፈሰሰች፡፡
ግና -ግን ለዛሬ ፣ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ፣ ውሰጂ እንባዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ ፣ የአንገት ሀብሌን

መልካም ቀን
60👍10🔥2
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 4

እግዚአብሔር ስጠኝ ሚሉት ብዙ ልጆች አሉት የናፈቀው ልስጥህ ሚለው ነው።

እግዚአብሔር ብዙ ተገኝልኝ የሚሉት አሉ የናፈቀው ልገኝልህ የሚሉት ናቸው። 
15👍1
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 5


"ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
21👍7
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
[13/12 07:56] Sedal Sedal: አሜን አሜን አሜን
[13/12 07:57] Sedal Sedal: ምስጋናነው ስራዬ በዘመኔ በእድሜዬ
ለዋ

Downloaded by: @VKmusicTopbot
1👏1
ይኸው ነጋ ጎህ ቀደደ🙏
አዲሱ ቀን ተወለደ😊
መኖር ቻልን በእርሱ ፈቃድ
እናመስግን በትህትና ትተን ልማድ

ያለ ዋጋ እንዲው ቻለን
ሳንከፍል ዛሬን አየን
ስንቶች ሽተው ያልቻሉትን
ቸርነቱን አብዝቶልን
ዛሬን በቃን ለምስጋና
አሳደሮን በአማን ደህና

ታዲያ ሰቶን አዲሱን ቀን እንደምንስ እናበላሽ?????🤨
ስለምንስ እናሳዝን በሀጢያት ወድቀን
ለእርሱ ምላሽ?????😔
መልካም ማድረግ ምን ባንችል ደግ ደጉን ባንሰራ
ከክፉነት እንታቀብ ጨለማነትን አንዝራ

መልካም ዕለተ ሰኞ
17👍2👏1
------- ቀን --------

ቀን ቀንን አርግዞ
ቀን እየወለደ፣
አንድ ቀን ሌላን ቀን
አልፎት እየሄደ፤

በቀናት መካከል
ቀናት ተደራርቦ፣
የቀናት ክምችት
የቀናት ርብራቦ፤

ቀናቶች ስንቆጥር
ቀናት ስንመነዝር፣
ቀናት ስንዘራዝር
ቀናቶች ስንገብር፤

ቀኖች እያሰብን
ዝክር ስናዋጣ፣
ቀንን ሳንጠቀም
ምፅአት ቀን መጣ።
39
ቦግ.....እልም
.
.
ጭላንጭል ብርሃን በጽልመት ተከባ፤
ቦግ...እልም ስትል ስትወጣ ስትገባ፤
አለች እንዳይሏት በርታ ትጠፋለች፤
ከሰመችም ሲሏት ከሩቅ ትታያለች፤

ቦግ.......እልም፤
ጭልም......ጭልምልም፤
ብልጭ.....ድርግም፤

የኔም ህይወት እንዲሁ......

አይሆንላት ተሸነፈች፤
አይሳካም ተሰበረች፤

አበቃላት ወድቃ ቀረች፤
ብለዉ ሲናገሩኝ..........

የሩቋ ወጋገን ጎልታ 'ምትታየኝ፤
በተነሳሁ ቁጥር ወደኔ 'ምትቀርበኝ፤
ጠፍታ የማትጠፋዉ ያቺ ብርሃን ነኝ።
..............................
በዔደን ታደሰ
36🥰5
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን ! †



💒 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን የጠበቁ፦
•➢ የተለያዩ ትምህርቶች የሚሠጡበት፤ መዝሙሮች እና ግጥሞች የሚለቀቁበት፤
•➢ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎችን የምናገኝበት ግሩፕ ነው። እናንተም ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦችን በማስገባት ኃላፊነትዎን ይወጡ።

ለተዋሕዶ ልጆች በመላክ ኃላፊነታችንን እንወጣ!

https://www.tg-me.com/rebunimedia21
2
Forwarded from Semahegn Demeke
ሀበነ እግዚኦ አዕይንተ አእምሮ ወትረ ኪያከ ይርአያ: ወአዕዛንነሂ ቃለ ዘባሕቲትከ ይስምዓ

አቤቱ አንተን ብቻ ያዩ ዘንድ የዕውቀት ዓይኖችን
ያንተንም ብቻ የሚሰሙ ጆሮዎችን ስጠን🙏


ዛሬ ተርኅዎተ ሰማይ ነው🤗። (የሰማይ መከፈት) ውዝፍ የዓመት ጸሎትዎን ያሳርጉ🙏

እንኳን አደረሰዎ ወዳጄ💙
4
መስከረም አቅጄ ••••
                                  በሞራል ሞልቼ
ጥቅምትን አስቤ••••
                                   ለመስራት ወጥቼ
ህዳር ላይ ደርሼ••••
                                   ልሰራ አሰብኩና
ታህሳሰን መረጥኩኝ••••
                                    መንገዴን ላቀና
ጥምቀት ደርሷል ብዬ••••
                                     ጥርን ትቼ አለፍኩ
የካቲት ልዘጋጅ ••••
                                ብዬ ራሴን ሸወድኩ
መጋቢት ፀሀዩ••••
                              ከብዷል ልሻገር
ሚያዚያ ደረሰ••••
                             ፋሲካን ላክብር
ግንቦት ደብሮኛል ••••
                                 ቆይ ትንሽ ልፍታታ
ሰኔ ዘነበብኝ ••••
                          ልጠለል ለአንዳፍታ
ሐምሌ ጎርፉን ፈራው ••••
                                ተኝቼ ሰነበትኩ
በባከነ መንፈስ ••••
                               ነሀሴንም ጨረስኩ
                               •
                               •
                               •
                               •
                               •
ሆኗል የኔስ ኑሮ እንዲያው የእንጉርጉሮ
ተግባር ያጣ ህይወት የቀረ ከአዕምሮ


ብሩክ ተፈራ
89👏16👍7🥰4
አንዱ ለአገሩ ፤
አንዱ ለ'ርስቱ ፤

አንዱ ለልጁ ፤
አንዱ ለሚስቱ ፤

ጥይት ወልውሎ ፤ ጎራዴ ስሎ ፤
በዱር በገደል ይከታከታል ፤

ሲሻው ይገድላል ፤ ሲሻው ይሞታል ።

እኔ ግን ወዲህ . . .

ወይ አገር የለኝ ፤
ወይ ርስት የለኝ ፤
ወይ ልጅ አልወለድኩ ፤ ሚስት አላደለኝ ፤

ጎራዴ ሳልስል ፤ ጥይት ሳልገዛ ፤ በተኛሁበት ሀሳብ ገደለኝ ።

By Tewodros kassa
13👎3👍2
ከሞትኩኝ ቆይቷል ብዙ ዘመን ሆኗል
መቅደሱ ገላዬ
ተስፋ ገለባዬ ራሱን በትኗል፡፡
ቆይቷል ከሞትኩኝ ከሀቀኛ ሳቅ

ህይወት አይታዘዝ እንደይስሀቅ፡፡
አይለየኝም ዛሬ ከነገዬ
ያልተፈሰከ ጾም ህይወት መዲናዬ
መኖር እዳዬ
መሄድም መቆምም እኩል ነው ሚያዝለኝ ድፍረት ካልሆነብኝ ጌትዬ እዘለኝ፡፡
አንተ ትከሻ ላይ ሁሉ ቀሏል አሉ ስሰማ በዝና
መስቀልህን ስጠኝ ህይወቴን ያዝና፡፡
የመስቀልን ክብደት
ከገዛ ሕይወቴ ለክቼ ባላውቅም መኖር ግን ያዝላል ከቄሳር ፍርድ አቅም፡፡
ትንሽ... ካንተ የምለየው
የተሰቀሉኩበት እንጨት ስላላየው....
እንሽ... ካንተ የምለየው
ከድቶ የሳመኝን ወዳጅ ስላላየው...
እንጂ ከሞትኩኝ ቆይቷል...
ናፈቀኝ የምለው
ባገኘው የምለው
በል ስጠኝ የምለው
አሁን ካለሁኝ ነው፡፡
እኔ ግን የለውም...
ጌታዬ... በሚጸልይ አታስቀናኝ
እንዴት ይብለጠኝ መናኝ፡፡
የምለየው ካንተ አርገኸኝ የሰው ዘር
ቆጥሬው አያልቅም...
ስንት ግርፊያ እንደሆን መኖር ሲመነዘር !
ከሞትኩኝ ቆይቷል
ቆይቷል ከሞትኩኝ
አለ ለመባል ነው እዚህ ጋር የቆምኩኝ

✍️ኤልያስ ሽታሁን
23👍2
Forwarded from ዘ ተዋህዶ (𝕻𝖎𝖑𝖚𝕻ΔDΣR)
Old Group

2023የተከፈተ - 500 ብር
ከ 2018 እስከ 2022 የተከፈተ- 900 ብር

ያላችሁ አምጡ 👉 @pilu_pilu_p

2024 - January February March የተከፈተ ካለም አምጡ

Frist ብርር ላክ ምናምን የምትሉ አትምጡ አልገዛቹ


ልታደክሙ አትምጡ ለስራ ይምጡ 🙄

Old group መሸጥ የምትፈልጉ ተቀላልቀሉ

https://www.tg-me.com/pilu_oldgroup_trader
3
2025/10/24 10:44:18
Back to Top
HTML Embed Code: