Telegram Web Link
ናና አማኑኤል
Orthodox Mezmur Channel
ናና አማኑኤል | ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ  (የአእላፋት ዝማሬ)

ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
ናና አማኑኤል ና መድኀኒቴ
ፍቅርህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
አዝ
የምሕረት አባት     አማኑኤል
የቸርነት ጌታ           ''
ፊትህ የተመላ         ''
ሁሌ በይቅርታ         ''
ካለው ፍቅር በላይ    ''
አባት ለአንድ ልጁ     ''
አምላክ ይወደናል       ''
አይጥለንም ከእጁ      ''
አዝ
መድኃኒቴ ልበል        አማኑኤል
ድኛለው በሞትህ         ''
ቁስሌ ተፈውሷል         ''
በቁስልህ በሞትህ        ''
ስሸጥህ አቀፍከኝ         ''
ስወጋህ አይኔ በራ         ''
በፍቅርህ አወጣኽኝ       ''
ከዚያ ከመከራ               ''
አዝ
አንተ ከኔ ጋር ነህ          አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ                    ''
ድል አርገህልኛል             ''
የጭንቄን ተራራ               ''
በጉባኤ መሀል                ''
አፌ አንተን አወጀ             ''
የከበረ ደምህ                 ''
ነፍሴን ስለዋጀ                ''
አዝ
የድንግሏ ፍሬ                አማኑኤል
የበላቴናዋ                       ''
የቤቴ ምሰሶ                     ''
የነፍሴ ቤዛዋ                    ''
መሠረቴ አንተ ነህ              ''
ያሳደገኝ እጅህ                  ''
አተወኝም አንተ                  ''
ስለሆንኩኝ ልጅህ               ''
ገብርኄር
.
የክርስቲያን ወጉ ፤
የክርስቲያን ህጉ፤

ነፍስን በዘራበት በአምላኩ አምኖ፤
መክሊቱን አትርፎ በጥቂቱ ታምኖ፤

ሞገስን አግኝቶ በብዙ መሾም ነው፤
ከሀጢአት ርቆ በፅድቅ መኖር ነው።

ይህ ነው ክርስትና
በአፍ እያወራ ድኛለው አይልም
ተግባር የሌለው ቃል ከቶ ፅድቅ አይሆንም
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!

#ኤልዳን
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
=======================

"የምላስ ወለምታ በቅቤ አይታይሽም"ይላል የድሮ ሰው፤
ከአፍህ የወጣውን ቃል ዳግም ላትመልስ ደግመኸም ላትጎርሰው።
አስብ አስር ጊዜ አስብ መቶ ጊዜ አንዴ ሳትናገር፤
በወንጭፍ ምላስህ የወረወርከው ቃል የሰው ልብ ሳይሰብር።

=======================

ጦቢያ
🔴 አዲስ ዝማሬ "ማርያም ማርያም" ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ.mp3
ማርያም ማርያም

ማርያም ማርያም ልበል
እረፍቴ ሆይ በስምሽ ልጠለል
የቃል እናት ያድናል ቃልሽ
ታምር ይሰራል ስምሽ


አዝ
ማር ልበል በምድር ያም ልበል በሰማይ
የማይጠግቡት መና የማይጨርሱት ሲሳይ
መንፈስ ቅዱስ ቃኝቶ ሰርቶ በሚስጥሩ
አፌ ላይ ጣፈጠኝ ስምሽ አጠራሩ (2)

አዝ
መዳኒት ታቅፈሽ  የአለሙን ጌታ
ከቤተልሄም ደጅ እስከ ጎለጎታ
የዓለሙን ህምም የዓለሙን በሽታ
ታክሚው ነበረ ድንግል በዝምታ (2)

አዝ
በምን እንመስልሽ የለሽም ምሳሌ
አንጠግብም ብንጠራሽ ብንዘምርልሽ ሁሌ
ምስክር አያሻም ያንቺ ልእልና
የአለሙን ንጉሥ ወልደሺዋልና (2)

አዝ
የወርቅ ማእጠንት እሳት የታቀፍሽ
የአዲስ ኪዳን ኪሩብ ማርያም አንቺ ነሽ
የአርያም እጣን ነሽ መአዛሽ ያማረ
ዘላለም አይወድቅም አንቺን ያከበረ (2)
ኃያል ነው እግዚአብሔር
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
ኃያል ነው እግዚአብሔር

ኃያል ነው እግዚአብሔር
ኃያል ነው ቅዱሱ /2/
አይቻለሁ በዓይኔ ሲቆም ማዕበሉ
አይቻለሁ በዓይኔ ሲታዘዝ ነፋሱ
አዝ
ሰረገላውን በእሳት ሠርቶታል
በደመና ላይ ይረማመዳል
በብርሃን ድንኳን በሰማይ ያለው
እርሱ ነው ጌታ የምናመልከው  /2/
አዝ
እውነት በፊቱ ፍትሕ በእጁ
ሲኦልም ገነት አሉ በደጁ
ሥልጣን የእርሱ ነው አለቅነት
ማን እንደ ጌታ ከአማልክት /2/
አዝ
ታቦር ተራራ ተንቀጠቀጠ
ግርማው ሲገለጥ ሁሉ ቀለጠ
ድንቅን አድራጊ ተአምረኛ
ከማዳኑ ጋር ይምጣ ወደ እኛ /2/
አዝ
ምድር ጠፈሩ ታዟል ለእርሱ
እሳት ተፈትሎ ሆኗል ቀሚሱ
የክብርህ ብርሃን ይብራ በልቤ
አንተ ነህ ለእኔ ውድ ገንዘቤ /2/

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

እርሱ ነው ጌታ የምናመልከው
Guys ለዛሬ ይሄን መዝሙር ተጋበዙልኝ😘😘😘
፨አህያዋ፨

ከእንስሳት ተለይታ
ልትቆም በሰው ተርታ
ሊቀመጥባት ጌታዋ
ሊታወቅላት ዋጋዋ
ላይጠፋባት አደራዋ
ሰው የማገልገል ስራዋ
ሲመጣላት ፈጣሪዋ
ደስ አላት አህያዋ
ሲቀመጥባት በጀርባዋ።
ውርንጭላነቷ ቀርቶ
የታሰረችበት ገመድ ተፈቶ
መናቅ መሰደቧ ጠፍቶ
የዋሁ የጺዮን ልጅ ትህትናን ተመልቶ
አስገባት ከተማ በህዝቡ ፊት መርቶ።
አፋቸው ተለጉሞ
ሃሳባቸው ከፍቶ ጠሞ
አዋቂ ነን ባዮቹ
የአይሁድ ካህናት ግብዞቹ
ዝም ቢሉ ለምስጋና
ለመራቸው በደመና
ለመገባቸው ከሰማይ መና
መመስገኑ መቼ ቀረና
እየተባለ ሆሳእና።
በሴቶች በወንዶቹ
በአዛውንት በልጆቹ
በህጻናት ጡት ጠቢዎቹ።
የዘኪዮስ ምኞት
መቼ ተረሳ በእጥረቱ
ዛፍ ላይ ብቻ በመታየቱ
አለቀረም ፍላጎቱ
ለመዘመር መጓጓቱ
ገብቶለታል ወደ ቤቱ
የጺዮን ልጅ ያትሁቱ
ሊበላ አብሮት ከፍትፍቱ።
መቅደስ ገብቶ ዞሮ ሲቃኝ
ሲመለከት ጊዜ አባካኝ
ጽሎት ትቶ ሲቸረችር
ከሌባ ጋር ሲደራደር
አልቻለም ስለ ቤቱ
ሲያቃጥለው ቅንአቱ
ጅራፍ ሰራ ለትምህርቱ
ቤቱን ሊያጠራ ከጠላቱ።
ሆሳዕና
.
.
ዘንባባን አንጥፈዉ አንተን ያከበሩ፤
ሆሳዕና ብለዉ ትናንት የዘመሩ፤

ቀን ቢጨልምብህ.......

በጲላጦስ ጊቢ አቁመዉ ከሰሱህ፤
ቀራንዮ ወስደዉ ጌታዬ ሰቀሉህ
.......................................።..

በዔደን ታደሰ
Forwarded from Ab
🙏ወጣቱ ዘማሪ ብሩክ እንዳለማው
ያወጣው አዲስ መዝሙር
🙏

👏የ ጸሎቴ ጉልበት 👍

የተሰኘው መዝሙር ተለቀቀ
ሁላቺንም ገብታችሁ ስሙት

ለመስማት
🔽🔽🔽
➡️https://youtu.be/heboIXmJlok
➡️https://youtu.be/heboIXmJlok
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ንሴብሆ ለእግዚአብሔር
❤️ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ❤️
✞ ንሴብሆ ✞

ንሴብሆ /2/ለእግዚአብሔር /2/ 
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4 
እናመስግነው/2/ እግዚአብሔርን/2/ 
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/ 
       አዝ-----
ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ሕይወት የሚሰጥ መና ነው ምግባችን
       አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራ ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
       አዝ-----
ከአለት ላይ ውሃ ፈልን ጠጣን
ይህን ታላቅ ጌታ ኑ እናመስግን
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
       አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተና ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
7 የመስቀሉ ቃላት
👉 በግጥም 👈
➊ኛ ➪ ኤሎሄ ኤሎሄ
ዘጠኝ ሰአትም ሲሆን
ክርስቶስ በመስቀል ላይ ጮሀ
ኤሎሄ ኤሎሄ ለማ ሰበቅታኒ
ብሎ በከፍታ ድምፅ ጮሀ
አምላኬ አምላኬ
አባቴ የኔማ መጮሄ
ለጠላቴ መዳን
ሆንኩላቸው አዲስ ኪዳን
ኤሎሄ ኤሎሄ እላለው
ስለ ምንስ ተውከኝ
ስለ ሁሉ ስላም ሁሉ መዳን
በመስቀል ተሰቀልኩኝ
ብሎ አሰምቶ ጮሀ
ከመስቀል ስር ያሉት
ክርስቶስ ያለውን ሰሙት
ይሄስ ኤልያስን ይጠራል አሉት
ሌሎቹን ያድናል ይፈዉሳል
እስኪ እራሱን ያድን
ከመስቀል ላይ ይውረድ
ያን ግዜ አይተን እናምንበታለን
ብለው ተዘባበቱበት
እየነቀነቁ አንገታቸውን

❷ኛ ➪ አባት ሆይ የሚደርጉትን አያቁምና ይቅር በላቸው
አባት ሆይ ሚያደርጉትን
አያቁም እና ይቅር በላቸው
እንደ እነርሱ አይተ
ፍርድን አትፍረድባቸው
እንደ ቸርነት ይሁን
አይሁን እንደ በደላቸው
እንደ ፍቃዳቸው እንደ እነርሱ
አትመልከት እንደ ስራቸው
እኔ ልጅህ ልሙት
እኔ ቤዛ ልሁን ስለ ሂወታቸው
ጨርቅ ልብሴን ተካፈሉት
እርስ በእርስ ዕጣ ተጣጥለው

❸ኛ ➬ዛሬ ከኔ ጋር በገነት ትሆናል
ተዘከረነ እግዚኦ
በውሰተ መንግስትከ
እየሱስ ሆይ በመንግስት
ስትመጣ አስበኝ አለው
በቀኙ የተሰቀለው ወንበዴው
እውነት እውነት እልሃለው
ዘጠና ዘጠኙን የተውኩት
ስለ ጠፋው ስለ አንዱ ነው
እውነት እውነት እልሃለው
እኔ የተሰቀልኩት ስለ ሃጣን ነው
እውነት አንተስ ታድለሃል
በመንግስት አስበኝ ያልከው
ዛሬ ከኔ ጋር በገነት ትሆናለ
አዳምንም ትቀድማለ አለው

❹ኛ ➪አባት ሆይ ነብሴን በእጅ አደራ እሰጣለው
አባት ሆይ አባት ሆይ
ነብሴን በእጅ አደራ እሰጣለው
ስለ ሃጢያተኞት ስለ ሃጣን ስራ
ቤዛ ሆንኩኝ ተቀበልኩኝ መከራ
አባት ሆይ ነብሴን ተቀበላት
ስለ ሚገድሉኝ በደለኞች
እኔ ሄያው ልጅ ልሙት

❺ኛ ➪አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ
አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ
ዮሃንስ ወዳቼ እነኋት እናትክ
ለአንተ ሰጠው አደረ እናቴን
ይዘሃት ሂድ ወደ ቤትክ
አታልቅሺ ዝም በይ እናቴ
ዮሃንስ ወዳጄ ይሆንሻል ምትክ
እናቴ ዙፋኔ በጅግር ያሳደክሽኝ
ወደ ዮሃንስ ቤት ግቢ
እኔስ ለአለም ቤዛ ሆንኩኝ
እናንተ የተዋህዶ ልጆች
እነዋት እናቴ እናታቹ
አደረ ሰጠዋቹ እናቴን
ይሄው ውሰዷት ወደየቤታቹ

❻ኛ ➬ ተጠማሁ
ተጠማሁ ተጠማሁ አለ
እየሱስ በመስቀል ተሰቅሎ ሳለ
ሆምጣጤ መራራ ሰጡት
የባህርን ጌታ ውሃን ነፈጉት
መራራውን ሆምጣጤ ተቀብሎ
እርሱ አልቻልም ለነጠጣት
በጣም መራራ ነው
ክፉ ጉሮሮን የሚልጥ

❼ ኛ ➪ተፈፀመ
ተፈፀመ አዎ ሁሉም ተፈፀመ
በናዝሬቱ እየሱስ
ሁሉም እንደ ታለም
ነብያት እንደ ተናገሩለት
ሁሉም በእርሱ ተፈፀመ
እስከ መስቀሉ ሞት
እስከ መስቀሉ ሞት
እስከ መስቀሉ ሞት፡፡

👉ተፃፈ ሃብታሙ አበራ
√ በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ ዐማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

ኪርያላይሶን፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬኤሌይሶን» ነው፡፡
«ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡
«ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይሄውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በዐማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
ናይናን፡- የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ ፣ማረን» ማለት ነው፡፡
እብኖዲ፡- የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡
«እብኖዲናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው፡፡
ታኦስ፡- የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ ፣አምላክ» ማለትነው፡፡
«ታኦስናይናን» ማለትም  «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
ማስያስ፡- የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
ትስቡጣ፡- «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው፡፡

አምንስቲቲ = አስበን፤ 
ሙኪርያ = አቤቱ ጌታ ሆይ፤ 
አንቲ ፋሲልያሱ = በመንግሥትህ፤
ሙአግያ = ቅዱስ፤ 
ሙዳሱጣ = ቸር ጌታ ማለት ነው፡፡

አምነስቲ ቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-ki-riey enti vasilia so፡- የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ - አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡

አምንስቲ ቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-a-geh-e enti vasilia so፡- የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው።

አምንስቲ ቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-zess-pota enti vasilia so፡- የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

√ ሥርዓተ ሕማማት
በሐዋርያት ቀኖና እንዲህ ይላል «ይልቁንም በእነዚህ በስድስቱ ቀኖች መጾም የሚችል ቢኖር ሁለት ሁለት ቀን ይጹም፡፡ የማይችል ግን አንድ አንድ ቀን ይጹም፡፡ ሌሎችን ቀኖች እስከ ዘጠኝ ሰዓት ይጹሙ፤ እችላለሁ የሚል ግን ፀሐይ እስኪገባ ይጹም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰብስባችሁ መጻሕፍተ ኦሪትን እና መጻሕፍተ ነቢያትን፣ የዳዊትንም መዝሙር እያነበባችሁ በምስጋና በጸሎት ዶሮ እስከሚጮህ ድረስ የሌሊቱን ሰዓት ጠብቁ፡፡

አንድ ምእመን የታመመ ቢሆን ወይም ክርስቲያን በሌለበት አገር ሆኖ ሳያውቅ የሕማማት ሰሞን ቢያልፍበት ወይንም በደዌ ውስጥ ሆኖ ቢቀርበት ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ሰውነቱን በማድከምም ደስታን ያድርግ፡፡ ባለመፍራት እንዳይጠፋ ውስጣዊ ሰውነቱን ይመርምር፡፡ ጾምን ከመፍታታቸው በፊት ገላቸውን ይታጠቡ፤ ሁሉም መብራት የሚያበሩ ይሁኑ፡፡ የቻለ ዓርብ እና ቅዳሜ ኹለት ቀን ይጹም፤ ሁለት ቀን መጾም የማይችል በሽተኛ ቢሆን ግን ቀዳም ሥዑርን ይጹም፡፡ የኀዘን ቀን ስለሆነች፡፡ እንጀራ እና ጨውም አይቅመስ፡፡»

√ የሰሙነ ሕማማት ሥርዓት በፍትሐ ነገሥት

• ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 
ቊጥር 578:- በነዚህ በስድስቱ ቀኖች (በሰሙነ ሕማማት) ከቂጣ ከጨው ከውኃ ብቻ በቀር አይብሉባቸው፡፡ በነዚህ ቀኖች ከወይን ከሥጋ ተለዩ የኀዘን ቀኖች ናቸውና የደስታ ቀኖች አይደሉም፡፡ ዓርብንና ቅዳሜን ግን ኹለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፡፡ የሚችል እስከ ሌሊቱ ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው ሰውየውም ኹለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻለው ግን የቅዳሜን ጾም ይጹም፡፡
ቊጥር 590:- ካህን ሰሙነ ሕማማትን ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል አስቀድሞ ቢያውል ይሻር፡፡ ከሕማማት ቀጥላ ከምትሆን ከቅዳሜ ስዑር በቀር እሑድንና ቅዳሜን የጾመ ካህን ቢኖር ይሻር፡፡
ቊጥር፡ 593:- ከካህናት ወገን ማንም ቢሆን በአርባ ጾም በዓርብና በረቡዕም ጾም ወይን መጠጣት አይገባውም ወደ መዋት (ውሽባ ቤት) አይግባ፡፡ በዐቢይ ጾም ወራት ሰው ከሚስቱ ጋር አይተኛ፡፡
ቊጥር 597 :- ሴቶችም ጌጣቸውን ይተው፡፡ ሁሉም ለእያንዳንዱ በአርባ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል ድኅነታችንና የኃጢአታችን ሥርየት በእነርሱ ነውና፡፡ ይኸውም ሥራ አንዱስ እንኳ በአርባ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ ሕግ የወጣ ነው፡፡ ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን ኃጢአት የሚሠራት ሰው ወዮለት፡፡ በአርባ ጾም በተድላ በደስታ ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን ወዴት አለ?
ቊጥር 599:- በተባሕትዎ በትሕትና አርባ ቀን ጾምን ይጹሙ፡፡ ከጥሉላት መከልከል ይገባል፡፡ አያግቡም፡፡
ቊጥር 600:- በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሣት ክህነት መስጠት ለሞቱ ሰዎች መጸለ ይአይገባም፡፡ በእነዚህም ቀኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጅ፡፡ በሰሙነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሐዋርያት ሥራ ወንጌላት የሙታን ፍትሐት በሆሣዕና በዓል ቀን ይነበብ እንጅ፡፡
ቊጥር 601:- በጸሎተ ኀሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት አይባልም (አይጸለይም)፡፡ ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል ፍትሐት ይፈታል፡፡ ከመሳለም በቀር ጸሎተ ዕጣንም ይጸለያል፡፡ በዕለተ እሑድ ግን ዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም፡፡ ዳግመኛም በውስጧ በአርባ ጾም ከተድላ ከደስታ ወገን ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ መጋባት ክህነት መስጠት ክርስትና ማንሣት ከሹመትም ወገን ስለሚሞቱት ከመጸለይ በቀር ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና ይደረግለታል፡፡

የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ኅብረት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ያለ ጥርጥር በፍጹም ልባችን ከምናምን ምእመናን ጋር ይኹን! [፪ኛቆሮ.፲፫፥፲፬]፡፡
#ታነባ_ነበር

በእርግዝናዋ
ስንት ያየችበት፣
የወለደችው
በከብቶች በረት፣
እየተላካት
እየታዘዘ፣
ዉሀ እየቀዳ
ሸክም እያገዘ፣

ያሳደገችው
በምድረ በዳ፣
የምትሳሳለት
የልጇ ቆዳ፣
ከግርፊያ ብዛት
ተነጫጭቶ አልቆ፣
ስጋውን አልፎ
አጥንቱ ዘልቆ፣
ርቆት ደምግባት
ተገፎ ልብሱ፣
መስቀል ላይ ሲጮህ
ስቶጣ ነብሱ፣
እያየች ማርያም
ሁሉንም ነገር፣
በታላቅ ስቃይ
ታነባ ነበር።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
( የወጉት )
=============

ያኔ ....
አይሁድ በጭካኔ
ክንድህን ወጥረው
ለፍቅርህ ብድራት ለውለታህ ዋጋ
አምስት ችንካር ቆጥረው
ያለ ርህራሄ
በመስቀሉ አግድም
እጅህን ሲዘረጉት
አላወቁት እንጂ ...
ባንተ መዳፍ በኩል
እልፍ ልቦችን ነው በምስማር የወጉት !!
አሻግሬ አየሁት
.
.
በግርግር መሐል ጨርቄን ጥዬ ስበር፣
አሻግሬ አየሁት ከቀራንዮ ጫፍ ከጎለጎታ ስር።

መንገዱን በማያዉቅ እልፍ መንገደኛ መንደሩ ታዉኮ፣
አንዱ ካንዱ ሲጋጭ ከሌላኛዉ ተጓዥ ሳይተያይ ታክኮ፣

አላፊ አግዳሚውን ወጪና ወራጁን ቆሜ ስመለከት፣
ደምግባቱን ያጣ የተራቆተ ሰው አየሁኝ በድንገት፣

በደም ረስርሶ በወዝ የረጠበ ቀይ ከለሜዳ፣
በሀሰት ተከሶ ፍርዱን የሚጠብቅ ከጲላጦስ ዘንዳ፣

ይታየኛል አንድ ሰው........

በአይሁድ ሊቀ ካህናት ግራና ቀኙን ተከቦ፣
በህዝብ መካከል የቆመ በእነ ቀያፋ ተዋክቦ፣

ሲንጠበብ ወዙ ሲነሳ ሲወድቅ፣
በጥፊ ሲመቱት እጅጉን ሲሳቀቅ፣

ይታየኛል ንፁህ ሰው......

በቁርጥራጭ ብረት፣
በተሰበረ አጥንት፣

እረፍት በሌለው በወንበዴ ጅራፍ ጀርባውን ተገርፎ፣
አልባስ ተለይቶት እርቃኑን የዋለ ቀሚሱን ተገፎ፣

ስጋዉ ሲቦጫጨቅ፣
ፅሂሙም ሲነጫጭ፣

ቁጥር በማይቆጥረዉ በአይሁድ ግርፋት ቆዳዉ ተገሽልጦ፣
እዡን እያነባ ህማም አይሎበት ፊቱ ተላልጦ፣

በድካም ሲያጣጥር፣
ይታወቀኝ ጀመር፣

ከአይኔ ተንከባሎ ጉንጩን እያራሰ እንባዬ ሲወርድ፣
ላብ እያጠመቀኝ እግሬ ተብረክርኮ ሰዉነቴ ሲርድ፣

አሻግሬ አየሁት.........

በተሳለ ቅንዋት ለአዳም ሲቸነከር፣
በደሙ ቤዛነት ብድራትን ሲቸር፣

በመስቀሉ ካሳ አርአያ ሊሆነን እንባችንን ሊያብስ፣
ለዘላለም ፍቅሩ ለታመነ ቃሉ እስከመሞት ሲደርስ።

በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
አንዳድ ጊዜ ብቻችሁን ሁኑ!

በመጀመሪያ ለብቻ በመሆንና በብቸኝነት መካከል ልዩነቱን እንወቅ፡፡ 

ለብቻ መሆን ማለት አንድ ተግባርና ልምምድ ነው፡፡ በራስ ፈቃድና ሆን ተብሎ ከሰዎች ገለል ያለ ቦታና ጊዜ መርጦ ከራስ ጋር ማሳለፍ ማለት ነው፡፡ ለብቻ ለመሆን የግድ በአካልም ሆነ በማሕበራዊ ሚዲያ ከሰዎች ለየት ማለትን ይጠይቃል፡፡

ብቸኛ መሆን ማለት ተግባር ሳይሆን ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት የሚመጣው በእኛ ፈቃድ ሳይሆን በውስጣችን ካለው የምልከታና የስነ-ልቦና ቀውስ ነው፡፡ ብቸኝነት ስሜት እንዲሰማን የግድ ከሰው በመለየት ብቻችንን መሆን የለብንም፡፡ በሰዎች መካከል እየኖርን እንኳን ይህ ስሜት ሊያጠቃን ይችላል፡፡

•  ከእለት እለት ከሰዎች ጋር የምታሳልፉ ከሆነና አንድም ቀን ለብቻችሁ የምታሳልፉበት ጊዜ ከሌላችሁ . . .

•  ሁል ጊዜ ከሰው ጋር ካልሆናችሁ የሚጨንቃችሁ ከሆነ . . .

•  በአካል ከሰዎች ጋር ካልሆናችሁ የግድ ሶሻል ሚዲያ ላይ የምታሳልፉ ከሆነ . . .

•  ብቻችሁን ስትሆኑ የብቸኝነት ስሜት የሚያጠቃችሁ ከሆነ፡፡

ከላይ የተጠቀሱትና መሰል ስሜቶች እንዳለባችሁ የምታስቡ ከሆነ ብቻችሁን የመሆን ልምምድ እንደሌላችሁና የለብቸኝነት ስሜት ተጋላጭ እንደሆናችሁ አሳባቂ ሁኔታ ነው፡፡

ለብቻችሁ ከራሳችሁ ጋር ጊዜን ማሳለፍ ለብዙ ነገር ይጠቅማችኋል፡፡

•  ከሰዎች አመለካከት አጉል ተጽእኖ ነጻ በሆነ መልኩ ውስጠ-ህሊናችሁን እንድታደምጡ፣

•  ተረጋግቶ ስለወደፊት ለማቀድ፣

•  ከሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማመዛዘን፣

•  ምቾት የማይሰጡ ስሜቶች የፈጠሩባችሁን ሁኔታዎች ለይቶ በማወቅ ለማስተካከል

እና ለመሳሰሉት ስኬታማ ልምምዶች ይጠቅማችኋል፡፡  

ለመጨረሻ ጊዜ ለብቻችሁ ያሳለፋችሁት መቼ ነው?

በየስንት ጊዜው ለብቻችሁ የመሆን ልምምድ አላችሁ?

ይህንን ልምምድ ዛሬውኑ ለመጀመር ብትወስኑ ምን ይመስላችኋል ?

እስኪ ኮመንት ላይ መልሳቹን ጻፉ😅
  
  
  
Find your happiness in your own world.
2025/06/27 09:44:21
Back to Top
HTML Embed Code: