የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 4
እግዚአብሔር ስጠኝ ሚሉት ብዙ ልጆች አሉት የናፈቀው ልስጥህ ሚለው ነው።
እግዚአብሔር ብዙ ተገኝልኝ የሚሉት አሉ የናፈቀው ልገኝልህ የሚሉት ናቸው።
እግዚአብሔር ስጠኝ ሚሉት ብዙ ልጆች አሉት የናፈቀው ልስጥህ ሚለው ነው።
እግዚአብሔር ብዙ ተገኝልኝ የሚሉት አሉ የናፈቀው ልገኝልህ የሚሉት ናቸው።
❤15👍1
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 5
"ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
❤21👍7
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
[13/12 07:56] Sedal Sedal: አሜን♥♥♥ አሜን♥♥♥ አሜን♥♥♥
[13/12 07:57] Sedal Sedal: ምስጋናነው ስራዬ በዘመኔ በእድሜዬ
ለዋ
✅ Downloaded by: @VKmusicTopbot
[13/12 07:57] Sedal Sedal: ምስጋናነው ስራዬ በዘመኔ በእድሜዬ
ለዋ
✅ Downloaded by: @VKmusicTopbot
❤1👏1
ይኸው ነጋ ጎህ ቀደደ🙏
አዲሱ ቀን ተወለደ😊
መኖር ቻልን በእርሱ ፈቃድ
እናመስግን በትህትና ትተን ልማድ
ያለ ዋጋ እንዲው ቻለን
ሳንከፍል ዛሬን አየን
ስንቶች ሽተው ያልቻሉትን
ቸርነቱን አብዝቶልን
ዛሬን በቃን ለምስጋና
አሳደሮን በአማን ደህና
ታዲያ ሰቶን አዲሱን ቀን እንደምንስ እናበላሽ?????🤨
ስለምንስ እናሳዝን በሀጢያት ወድቀን
ለእርሱ ምላሽ?????😔
መልካም ማድረግ ምን ባንችል ደግ ደጉን ባንሰራ
ከክፉነት እንታቀብ ጨለማነትን አንዝራ
መልካም ዕለተ ሰኞ
አዲሱ ቀን ተወለደ😊
መኖር ቻልን በእርሱ ፈቃድ
እናመስግን በትህትና ትተን ልማድ
ያለ ዋጋ እንዲው ቻለን
ሳንከፍል ዛሬን አየን
ስንቶች ሽተው ያልቻሉትን
ቸርነቱን አብዝቶልን
ዛሬን በቃን ለምስጋና
አሳደሮን በአማን ደህና
ታዲያ ሰቶን አዲሱን ቀን እንደምንስ እናበላሽ?????🤨
ስለምንስ እናሳዝን በሀጢያት ወድቀን
ለእርሱ ምላሽ?????😔
መልካም ማድረግ ምን ባንችል ደግ ደጉን ባንሰራ
ከክፉነት እንታቀብ ጨለማነትን አንዝራ
መልካም ዕለተ ሰኞ
❤17👍2👏1
------- ቀን --------
ቀን ቀንን አርግዞ
ቀን እየወለደ፣
አንድ ቀን ሌላን ቀን
አልፎት እየሄደ፤
በቀናት መካከል
ቀናት ተደራርቦ፣
የቀናት ክምችት
የቀናት ርብራቦ፤
ቀናቶች ስንቆጥር
ቀናት ስንመነዝር፣
ቀናት ስንዘራዝር
ቀናቶች ስንገብር፤
ቀኖች እያሰብን
ዝክር ስናዋጣ፣
ቀንን ሳንጠቀም
ምፅአት ቀን መጣ።
ቀን ቀንን አርግዞ
ቀን እየወለደ፣
አንድ ቀን ሌላን ቀን
አልፎት እየሄደ፤
በቀናት መካከል
ቀናት ተደራርቦ፣
የቀናት ክምችት
የቀናት ርብራቦ፤
ቀናቶች ስንቆጥር
ቀናት ስንመነዝር፣
ቀናት ስንዘራዝር
ቀናቶች ስንገብር፤
ቀኖች እያሰብን
ዝክር ስናዋጣ፣
ቀንን ሳንጠቀም
ምፅአት ቀን መጣ።
❤41
ቦግ.....እልም
.
.
ጭላንጭል ብርሃን በጽልመት ተከባ፤
ቦግ...እልም ስትል ስትወጣ ስትገባ፤
አለች እንዳይሏት በርታ ትጠፋለች፤
ከሰመችም ሲሏት ከሩቅ ትታያለች፤
ቦግ.......እልም፤
ጭልም......ጭልምልም፤
ብልጭ.....ድርግም፤
የኔም ህይወት እንዲሁ......
አይሆንላት ተሸነፈች፤
አይሳካም ተሰበረች፤
አበቃላት ወድቃ ቀረች፤
ብለዉ ሲናገሩኝ..........
የሩቋ ወጋገን ጎልታ 'ምትታየኝ፤
በተነሳሁ ቁጥር ወደኔ 'ምትቀርበኝ፤
ጠፍታ የማትጠፋዉ ያቺ ብርሃን ነኝ።
..............................
በዔደን ታደሰ
.
.
ጭላንጭል ብርሃን በጽልመት ተከባ፤
ቦግ...እልም ስትል ስትወጣ ስትገባ፤
አለች እንዳይሏት በርታ ትጠፋለች፤
ከሰመችም ሲሏት ከሩቅ ትታያለች፤
ቦግ.......እልም፤
ጭልም......ጭልምልም፤
ብልጭ.....ድርግም፤
የኔም ህይወት እንዲሁ......
አይሆንላት ተሸነፈች፤
አይሳካም ተሰበረች፤
አበቃላት ወድቃ ቀረች፤
ብለዉ ሲናገሩኝ..........
የሩቋ ወጋገን ጎልታ 'ምትታየኝ፤
በተነሳሁ ቁጥር ወደኔ 'ምትቀርበኝ፤
ጠፍታ የማትጠፋዉ ያቺ ብርሃን ነኝ።
..............................
በዔደን ታደሰ
❤36🥰5
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን ! †
💒 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን የጠበቁ፦
•➢ የተለያዩ ትምህርቶች የሚሠጡበት፤ መዝሙሮች እና ግጥሞች የሚለቀቁበት፤
•➢ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎችን የምናገኝበት ግሩፕ ነው። እናንተም ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦችን በማስገባት ኃላፊነትዎን ይወጡ።
ለተዋሕዶ ልጆች በመላክ ኃላፊነታችንን እንወጣ!
https://www.tg-me.com/rebunimedia21
አሜን ! †
💒 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን የጠበቁ፦
•➢ የተለያዩ ትምህርቶች የሚሠጡበት፤ መዝሙሮች እና ግጥሞች የሚለቀቁበት፤
•➢ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎችን የምናገኝበት ግሩፕ ነው። እናንተም ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦችን በማስገባት ኃላፊነትዎን ይወጡ።
ለተዋሕዶ ልጆች በመላክ ኃላፊነታችንን እንወጣ!
https://www.tg-me.com/rebunimedia21
❤2
መስከረም አቅጄ ••••
በሞራል ሞልቼ
ጥቅምትን አስቤ••••
ለመስራት ወጥቼ
ህዳር ላይ ደርሼ••••
ልሰራ አሰብኩና
ታህሳሰን መረጥኩኝ••••
መንገዴን ላቀና
ጥምቀት ደርሷል ብዬ••••
ጥርን ትቼ አለፍኩ
የካቲት ልዘጋጅ ••••
ብዬ ራሴን ሸወድኩ
መጋቢት ፀሀዩ••••
ከብዷል ልሻገር
ሚያዚያ ደረሰ••••
ፋሲካን ላክብር
ግንቦት ደብሮኛል ••••
ቆይ ትንሽ ልፍታታ
ሰኔ ዘነበብኝ ••••
ልጠለል ለአንዳፍታ
ሐምሌ ጎርፉን ፈራው ••••
ተኝቼ ሰነበትኩ
በባከነ መንፈስ ••••
ነሀሴንም ጨረስኩ
•
•
•
•
•
ሆኗል የኔስ ኑሮ እንዲያው የእንጉርጉሮ
ተግባር ያጣ ህይወት የቀረ ከአዕምሮ
✍ብሩክ ተፈራ
በሞራል ሞልቼ
ጥቅምትን አስቤ••••
ለመስራት ወጥቼ
ህዳር ላይ ደርሼ••••
ልሰራ አሰብኩና
ታህሳሰን መረጥኩኝ••••
መንገዴን ላቀና
ጥምቀት ደርሷል ብዬ••••
ጥርን ትቼ አለፍኩ
የካቲት ልዘጋጅ ••••
ብዬ ራሴን ሸወድኩ
መጋቢት ፀሀዩ••••
ከብዷል ልሻገር
ሚያዚያ ደረሰ••••
ፋሲካን ላክብር
ግንቦት ደብሮኛል ••••
ቆይ ትንሽ ልፍታታ
ሰኔ ዘነበብኝ ••••
ልጠለል ለአንዳፍታ
ሐምሌ ጎርፉን ፈራው ••••
ተኝቼ ሰነበትኩ
በባከነ መንፈስ ••••
ነሀሴንም ጨረስኩ
•
•
•
•
•
ሆኗል የኔስ ኑሮ እንዲያው የእንጉርጉሮ
ተግባር ያጣ ህይወት የቀረ ከአዕምሮ
✍ብሩክ ተፈራ
❤92👏16👍8🥰4
አንዱ ለአገሩ ፤
አንዱ ለ'ርስቱ ፤
አንዱ ለልጁ ፤
አንዱ ለሚስቱ ፤
ጥይት ወልውሎ ፤ ጎራዴ ስሎ ፤
በዱር በገደል ይከታከታል ፤
ሲሻው ይገድላል ፤ ሲሻው ይሞታል ።
እኔ ግን ወዲህ . . .
ወይ አገር የለኝ ፤
ወይ ርስት የለኝ ፤
ወይ ልጅ አልወለድኩ ፤ ሚስት አላደለኝ ፤
ጎራዴ ሳልስል ፤ ጥይት ሳልገዛ ፤ በተኛሁበት ሀሳብ ገደለኝ ።
By Tewodros kassa
አንዱ ለ'ርስቱ ፤
አንዱ ለልጁ ፤
አንዱ ለሚስቱ ፤
ጥይት ወልውሎ ፤ ጎራዴ ስሎ ፤
በዱር በገደል ይከታከታል ፤
ሲሻው ይገድላል ፤ ሲሻው ይሞታል ።
እኔ ግን ወዲህ . . .
ወይ አገር የለኝ ፤
ወይ ርስት የለኝ ፤
ወይ ልጅ አልወለድኩ ፤ ሚስት አላደለኝ ፤
ጎራዴ ሳልስል ፤ ጥይት ሳልገዛ ፤ በተኛሁበት ሀሳብ ገደለኝ ።
By Tewodros kassa
❤14👎3👍2
ከሞትኩኝ ቆይቷል ብዙ ዘመን ሆኗል
መቅደሱ ገላዬ
ተስፋ ገለባዬ ራሱን በትኗል፡፡
ቆይቷል ከሞትኩኝ ከሀቀኛ ሳቅ
ህይወት አይታዘዝ እንደይስሀቅ፡፡
አይለየኝም ዛሬ ከነገዬ
ያልተፈሰከ ጾም ህይወት መዲናዬ
መኖር እዳዬ
መሄድም መቆምም እኩል ነው ሚያዝለኝ ድፍረት ካልሆነብኝ ጌትዬ እዘለኝ፡፡
አንተ ትከሻ ላይ ሁሉ ቀሏል አሉ ስሰማ በዝና
መስቀልህን ስጠኝ ህይወቴን ያዝና፡፡
የመስቀልን ክብደት
ከገዛ ሕይወቴ ለክቼ ባላውቅም መኖር ግን ያዝላል ከቄሳር ፍርድ አቅም፡፡
ትንሽ... ካንተ የምለየው
የተሰቀሉኩበት እንጨት ስላላየው....
እንሽ... ካንተ የምለየው
ከድቶ የሳመኝን ወዳጅ ስላላየው...
እንጂ ከሞትኩኝ ቆይቷል...
ናፈቀኝ የምለው
ባገኘው የምለው
በል ስጠኝ የምለው
አሁን ካለሁኝ ነው፡፡
እኔ ግን የለውም...
ጌታዬ... በሚጸልይ አታስቀናኝ
እንዴት ይብለጠኝ መናኝ፡፡
የምለየው ካንተ አርገኸኝ የሰው ዘር
ቆጥሬው አያልቅም...
ስንት ግርፊያ እንደሆን መኖር ሲመነዘር !
ከሞትኩኝ ቆይቷል
ቆይቷል ከሞትኩኝ
አለ ለመባል ነው እዚህ ጋር የቆምኩኝ
✍️ኤልያስ ሽታሁን
መቅደሱ ገላዬ
ተስፋ ገለባዬ ራሱን በትኗል፡፡
ቆይቷል ከሞትኩኝ ከሀቀኛ ሳቅ
ህይወት አይታዘዝ እንደይስሀቅ፡፡
አይለየኝም ዛሬ ከነገዬ
ያልተፈሰከ ጾም ህይወት መዲናዬ
መኖር እዳዬ
መሄድም መቆምም እኩል ነው ሚያዝለኝ ድፍረት ካልሆነብኝ ጌትዬ እዘለኝ፡፡
አንተ ትከሻ ላይ ሁሉ ቀሏል አሉ ስሰማ በዝና
መስቀልህን ስጠኝ ህይወቴን ያዝና፡፡
የመስቀልን ክብደት
ከገዛ ሕይወቴ ለክቼ ባላውቅም መኖር ግን ያዝላል ከቄሳር ፍርድ አቅም፡፡
ትንሽ... ካንተ የምለየው
የተሰቀሉኩበት እንጨት ስላላየው....
እንሽ... ካንተ የምለየው
ከድቶ የሳመኝን ወዳጅ ስላላየው...
እንጂ ከሞትኩኝ ቆይቷል...
ናፈቀኝ የምለው
ባገኘው የምለው
በል ስጠኝ የምለው
አሁን ካለሁኝ ነው፡፡
እኔ ግን የለውም...
ጌታዬ... በሚጸልይ አታስቀናኝ
እንዴት ይብለጠኝ መናኝ፡፡
የምለየው ካንተ አርገኸኝ የሰው ዘር
ቆጥሬው አያልቅም...
ስንት ግርፊያ እንደሆን መኖር ሲመነዘር !
ከሞትኩኝ ቆይቷል
ቆይቷል ከሞትኩኝ
አለ ለመባል ነው እዚህ ጋር የቆምኩኝ
✍️ኤልያስ ሽታሁን
❤23👍2
Forwarded from ዘ ተዋህዶ (𝕻𝖎𝖑𝖚𝕻ΔDΣR)
Old Group
2023የተከፈተ - 500 ብር
ከ 2018 እስከ 2022 የተከፈተ- 900 ብር
ያላችሁ አምጡ 👉 @pilu_pilu_p
2024 - January February March የተከፈተ ካለም አምጡ
Frist ብርር ላክ ምናምን የምትሉ አትምጡ አልገዛቹ
ም
ልታደክሙ አትምጡ ለስራ ይምጡ 🙄
Old group መሸጥ የምትፈልጉ ተቀላልቀሉ
https://www.tg-me.com/pilu_oldgroup_trader
2023የተከፈተ - 500 ብር
ከ 2018 እስከ 2022 የተከፈተ- 900 ብር
ያላችሁ አምጡ 👉 @pilu_pilu_p
2024 - January February March የተከፈተ ካለም አምጡ
Frist ብርር ላክ ምናምን የምትሉ አትምጡ አልገዛቹ
ም
ልታደክሙ አትምጡ ለስራ ይምጡ 🙄
Old group መሸጥ የምትፈልጉ ተቀላልቀሉ
https://www.tg-me.com/pilu_oldgroup_trader
❤3👏1
ደገኛ ባልሆንም \ትሁት ሰው አክባሪ
ቅን ታዛዥ መልከኛ \ለሰው ተቆርቋሪ
ጨዋነት የሌለኝ \ምግባሬ የጠለሸ
ሰውን የማስቀይም\ አፌ የተበላሸ
ባልሆንም ሀቀኛ\ ለቃሌ ታማኝ
ውሸታም ሀሜታም \ውዳቂ የሆንኩኝ
ከጭካኔ ብዛት \የጠላኝ ህዝብ ሁሉ
የጎደፍኩ ያዳረስኩ \ሀጥያትን በሙሉ
ብሆንም አስታውሱ \አለኝ ግን ህሊና
አምላክ አይጠላኝም \ሰው አይደለምና
እርሱ ቢጠላኝስ ••••ለምን አላጠፋኝ???
መመለሴን ሽቶ ••••ዳግም ዕድል ሰጠኝ
ብዬ የተረዳሁ ዕለት .....
ኮቴውን ተከተልኩ ፈለኩት አምላኬን
እርሱን መፈለግ ውስጥ አገኘሁት እራሴን
✍ብሩክ ተፈራ
ቅን ታዛዥ መልከኛ \ለሰው ተቆርቋሪ
ጨዋነት የሌለኝ \ምግባሬ የጠለሸ
ሰውን የማስቀይም\ አፌ የተበላሸ
ባልሆንም ሀቀኛ\ ለቃሌ ታማኝ
ውሸታም ሀሜታም \ውዳቂ የሆንኩኝ
ከጭካኔ ብዛት \የጠላኝ ህዝብ ሁሉ
የጎደፍኩ ያዳረስኩ \ሀጥያትን በሙሉ
ብሆንም አስታውሱ \አለኝ ግን ህሊና
አምላክ አይጠላኝም \ሰው አይደለምና
እርሱ ቢጠላኝስ ••••ለምን አላጠፋኝ???
መመለሴን ሽቶ ••••ዳግም ዕድል ሰጠኝ
ብዬ የተረዳሁ ዕለት .....
ኮቴውን ተከተልኩ ፈለኩት አምላኬን
እርሱን መፈለግ ውስጥ አገኘሁት እራሴን
✍ብሩክ ተፈራ
❤33🥰10
የቅዱሳን ምልጃ
እግዚአብሔርን ፤ አስቀይመነው
ሳንፈራ ንቀነው ፤ ሳንሳቀቅ አፍረነው።
እጅግ የሚያስመካ ፤ በጣም የሚያኮራ
በፊቱ የሚያቆም ፤ ጀብዱ እንደ ሰራ።
ዓይኑን ለማየት ፤ ሳንሸማቀቅ
ብቻዬን እችላለሁ ፤ ከእርሱ ጋር መታረቅ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ።
በበደላችንስ ፤ ማፈር እንኳን ቢቀር
ከእርሱ ባልንጀራው ፤ እንደ ሚሻል ይቁጠር።
ብሎ አስተምሮን ፤ ጌታችን ትህትና
በራሳችን ትምክህት ፤ በትእቢት ልቦና።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።
እኔን በቀጥታ ፤ ቆመህ አትለምነኝ
ይቅርታ አድርጌልህ ፤ ምህረት እንድታገኝ።
ወደ አብርሃም ሄደህ ፤ ጸልይልኝ በለው
ጌታ ለአቤሜሌክ ፤ እየሰማን ሲለው።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።
እኛ የጠየቅነው ፤ ይጉዳንስ ይጥቀመን
ለይተን የማናውቅ ፤ ድኩማኖች ሆነን።
ጊዜያዊውን ሳይሆን ፤ ዘላለማዊውን
ፍቃዱን የሚያውቁ ፤ ለኛ እሚበጀውን።
ለገዛ ነብሳቸው ፤ ቅንጣትም ሳይራሩ
እኔን አጥፋኝ ብለው ፤ እኛን የሚያስምሩ
እንደ ሙሴ አይነት ፤ ደጋጎች ሲኖሩ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ በመቃብር ድንኳን
በሞት ይወሰናል ፤ ደፍረን ብንል እንኳን።
የህያዋን መላእክት ፤ ልመናና ምልጃ
መቼ ይጋረዳል ፤ በሞት መጋረጃ።
የኤልያስን ፀሎት ፤ የሚከለክለው
የሄኖክን ምልጃ ፤ የለም የሚያስቆመው ።
የሚያምንብኝ አለው ፤ የዘላለም ዋጋ
ሕያው ነው እያለን ፤ ቢሞትም በሥጋ ።
ዓይነ ህሊናችን ፤ የፃድቃኑን ጸጋ
ቢታወር ነው እንጂ ፤ እንዳያይ ቢዘጋ።
ያማልዳሉ ካልን ፤ በአለም ሲኖሩ
ዳግም በሰማያት ፤ ከጸጋ ባህሩ
ከጌታ ጋር ሆነው ፤ ይበልጡን ሲከብሩ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።
https://www.tg-me.com/menfesawigetem
https://www.tg-me.com/menfesawigetem
https://www.tg-me.com/menfesawigetem
እግዚአብሔርን ፤ አስቀይመነው
ሳንፈራ ንቀነው ፤ ሳንሳቀቅ አፍረነው።
እጅግ የሚያስመካ ፤ በጣም የሚያኮራ
በፊቱ የሚያቆም ፤ ጀብዱ እንደ ሰራ።
ዓይኑን ለማየት ፤ ሳንሸማቀቅ
ብቻዬን እችላለሁ ፤ ከእርሱ ጋር መታረቅ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ።
በበደላችንስ ፤ ማፈር እንኳን ቢቀር
ከእርሱ ባልንጀራው ፤ እንደ ሚሻል ይቁጠር።
ብሎ አስተምሮን ፤ ጌታችን ትህትና
በራሳችን ትምክህት ፤ በትእቢት ልቦና።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።
እኔን በቀጥታ ፤ ቆመህ አትለምነኝ
ይቅርታ አድርጌልህ ፤ ምህረት እንድታገኝ።
ወደ አብርሃም ሄደህ ፤ ጸልይልኝ በለው
ጌታ ለአቤሜሌክ ፤ እየሰማን ሲለው።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።
እኛ የጠየቅነው ፤ ይጉዳንስ ይጥቀመን
ለይተን የማናውቅ ፤ ድኩማኖች ሆነን።
ጊዜያዊውን ሳይሆን ፤ ዘላለማዊውን
ፍቃዱን የሚያውቁ ፤ ለኛ እሚበጀውን።
ለገዛ ነብሳቸው ፤ ቅንጣትም ሳይራሩ
እኔን አጥፋኝ ብለው ፤ እኛን የሚያስምሩ
እንደ ሙሴ አይነት ፤ ደጋጎች ሲኖሩ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ በመቃብር ድንኳን
በሞት ይወሰናል ፤ ደፍረን ብንል እንኳን።
የህያዋን መላእክት ፤ ልመናና ምልጃ
መቼ ይጋረዳል ፤ በሞት መጋረጃ።
የኤልያስን ፀሎት ፤ የሚከለክለው
የሄኖክን ምልጃ ፤ የለም የሚያስቆመው ።
የሚያምንብኝ አለው ፤ የዘላለም ዋጋ
ሕያው ነው እያለን ፤ ቢሞትም በሥጋ ።
ዓይነ ህሊናችን ፤ የፃድቃኑን ጸጋ
ቢታወር ነው እንጂ ፤ እንዳያይ ቢዘጋ።
ያማልዳሉ ካልን ፤ በአለም ሲኖሩ
ዳግም በሰማያት ፤ ከጸጋ ባህሩ
ከጌታ ጋር ሆነው ፤ ይበልጡን ሲከብሩ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።
https://www.tg-me.com/menfesawigetem
https://www.tg-me.com/menfesawigetem
https://www.tg-me.com/menfesawigetem
❤18👍6
ሚስጥረኛ ብዬ
ሚስጥሬን ብነግርሽ፣
ሚስጥሩ ነው ብለሽ
በሚስጥር ተናገርሽ፤
ያ ሚስጥር በሚስጥር
ሲዞር ሲዞር ውሎ፣
በሚስጥር ነገሩኝ
ሚስጥር ነው ተብሎ።
😂😂😂😂
ሚስጥሬን ብነግርሽ፣
ሚስጥሩ ነው ብለሽ
በሚስጥር ተናገርሽ፤
ያ ሚስጥር በሚስጥር
ሲዞር ሲዞር ውሎ፣
በሚስጥር ነገሩኝ
ሚስጥር ነው ተብሎ።
😂😂😂😂
👍14❤13🥰1
ከክፋት ለመብለጥ
ክፋት ከወደደ ፤
እራሱን ሸሽጎ
በሰው ከፈረደ ፤
ምንም አይባልም
ልቡ እስኪረታ ፤
ሰው መቼም
አይነፃ...
የማይሰራ ሀጥያት
እግዚአብሔር ይፍታ ።...😔
ክፋት ከወደደ ፤
እራሱን ሸሽጎ
በሰው ከፈረደ ፤
ምንም አይባልም
ልቡ እስኪረታ ፤
ሰው መቼም
አይነፃ...
የማይሰራ ሀጥያት
እግዚአብሔር ይፍታ ።...😔
❤7
ሀሳብ ገዳይ..፤
ፍትህ በዳይ...፤
አንደበት ማር ቢቀባበት
ምን ይገኛል ?
እንጀራ እየገዛሁ
እበላለሁ...
ግን መልሶ ይርበኛል ።🤣
ራበኝ ራበኝ ራበኝ 🫠
@dagi1u
ፍትህ በዳይ...፤
አንደበት ማር ቢቀባበት
ምን ይገኛል ?
እንጀራ እየገዛሁ
እበላለሁ...
ግን መልሶ ይርበኛል ።🤣
ራበኝ ራበኝ ራበኝ 🫠
@dagi1u
❤2🥰2
Forwarded from Esuye ከሀጥያተኞች ዋና 1ኛ ጢሞ 1:15
“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥18
የክርስቶስ ፀጋና ሰላም ይብዛላቹ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን አሜን
መስቀልን ስናከብር በጣም ብዙ የመንፈሳዊ ህይወት ጨቅላዎች መስቀሉን ሳይሆን የተሰቀለበትን አክብሩ እንጂ ይሉናል
ልጅ ለእናት ምጥ አስተማረች እንዲሉ የሀገሬው ሰው ለቤተክርስቲያን ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት አዲሷ አይደለም ሰበር ዜናዋ አይደለም ኢየሱስ ጌታ ነው ከማለት አልፋ እንዴት ጌታ እንደሆነ እና ጌትነቱን መስበክ ከጀመረች አመታት አልፈዋታል ምክንያቱም ለአንድ ክርስቲያን ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው ቃል ሳይሆን ጌትነቱን በደምብ ማብራራት ስለሆነ የሚፈልገው ምክንያቱም ክርስቲያን ሲሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነት አምኖ ተቀብሎ ስለሆነ ማለት ነው
ለምሳሌ ያክል አንድን ልጅ ትምህርት ቤት እንዲገባ ከነገርንው ብኋላ እና አስመዘገብንው ትምህርት ነው ማስተማር ያለብን ወይስ ሁሌ ትምህርት ጥሩ ነው ተማር ማለት ነው ያለብን መልሱ ግልፅ ነው ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያንም ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት ብቻ ጥቅም የለውም ቀድሞ ጌታ መሆኑን ያውቃልና ከቻሉ እንዴት ጌታ ሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው ጌትነቱ እንዴት ነው ወ.ዘ.ተ ማስተማር ቤተክርስቲያን ስንዱ እመቤት ናትና ነገር ክርስቶስ ነገር ሥጋዌ ነገር መለኮት .....እያለች ስለ ክርስቶስ በደንብ ዘርዝራ ፈትፍታ ለልጇቿ ታጎርሳለች ወንጌልን ይሄ ነው ክርስቶስን መስበክ
ታድያ ለክርስቶስ ይሄን የሀል አመለካከት ካላቹ ክርስቶስን ትታቹ ለምን እንጨቱን የሚሉ አሉ (ይቅር ይበላቸውና )እኛ እንጨት አንልም ቅዱስ መስቀል ነው የምንለው የክርስቶስ ደም ፈሶበት ቀላል ጥቅም የለሽ የሆነ ነገር አላየንምና
መስቀሉን ሲጀመር ስናከብር እኮ ክርስቶስ ተሰቅሎበታል ብለን ነው የእውቀት አለማወቅ የክፉዎች ክፉ ነው ትል ነበር አያቴ
ባጠቃላይ መስቀልን ምናከብረው
1ኛ ሀይላችን ስለሆነ ነው ጥላትን የምናስበረግግበት ድል የምንነሳበት ስለሆነ 👉👉“
2ኛ የዳንበት ሴጣን ዲያቢሎስ የተቀጠቀጠበት የዘመናት የጥል ግድግዳ የፈረሰበት ስለሆነ ነው
ነገር በሶስት ይፀናል እንዲሉ ልሥልሰው😄
3ኛ በእኛ የነበረውን መርገም በመስቀሉ ስለሆነ ያስወገደልን 👉👉
ስለዚህ በአጭሩ መስቀልን የምናከብረው ጌታ ክርስቶስ ተሰቅሎ ክቡር ደሙን ቅዱስ ስጋውን አፍስሶ ቆርሶ ስለቀደሰው ነው ለእኛም ሀይላችን ነው ለሚጠፉት ግን መኞትን ፌዝነት ነው
መልካም ቀን መልካም በዓል
✍✍ esuye (ከሀጢያተኞች ዋና
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥18
የክርስቶስ ፀጋና ሰላም ይብዛላቹ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን አሜን
መስቀልን ስናከብር በጣም ብዙ የመንፈሳዊ ህይወት ጨቅላዎች መስቀሉን ሳይሆን የተሰቀለበትን አክብሩ እንጂ ይሉናል
ልጅ ለእናት ምጥ አስተማረች እንዲሉ የሀገሬው ሰው ለቤተክርስቲያን ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት አዲሷ አይደለም ሰበር ዜናዋ አይደለም ኢየሱስ ጌታ ነው ከማለት አልፋ እንዴት ጌታ እንደሆነ እና ጌትነቱን መስበክ ከጀመረች አመታት አልፈዋታል ምክንያቱም ለአንድ ክርስቲያን ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው ቃል ሳይሆን ጌትነቱን በደምብ ማብራራት ስለሆነ የሚፈልገው ምክንያቱም ክርስቲያን ሲሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነት አምኖ ተቀብሎ ስለሆነ ማለት ነው
ለምሳሌ ያክል አንድን ልጅ ትምህርት ቤት እንዲገባ ከነገርንው ብኋላ እና አስመዘገብንው ትምህርት ነው ማስተማር ያለብን ወይስ ሁሌ ትምህርት ጥሩ ነው ተማር ማለት ነው ያለብን መልሱ ግልፅ ነው ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያንም ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት ብቻ ጥቅም የለውም ቀድሞ ጌታ መሆኑን ያውቃልና ከቻሉ እንዴት ጌታ ሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው ጌትነቱ እንዴት ነው ወ.ዘ.ተ ማስተማር ቤተክርስቲያን ስንዱ እመቤት ናትና ነገር ክርስቶስ ነገር ሥጋዌ ነገር መለኮት .....እያለች ስለ ክርስቶስ በደንብ ዘርዝራ ፈትፍታ ለልጇቿ ታጎርሳለች ወንጌልን ይሄ ነው ክርስቶስን መስበክ
ታድያ ለክርስቶስ ይሄን የሀል አመለካከት ካላቹ ክርስቶስን ትታቹ ለምን እንጨቱን የሚሉ አሉ (ይቅር ይበላቸውና )እኛ እንጨት አንልም ቅዱስ መስቀል ነው የምንለው የክርስቶስ ደም ፈሶበት ቀላል ጥቅም የለሽ የሆነ ነገር አላየንምና
መስቀሉን ሲጀመር ስናከብር እኮ ክርስቶስ ተሰቅሎበታል ብለን ነው የእውቀት አለማወቅ የክፉዎች ክፉ ነው ትል ነበር አያቴ
ባጠቃላይ መስቀልን ምናከብረው
1ኛ ሀይላችን ስለሆነ ነው ጥላትን የምናስበረግግበት ድል የምንነሳበት ስለሆነ 👉👉“
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥18
2ኛ የዳንበት ሴጣን ዲያቢሎስ የተቀጠቀጠበት የዘመናት የጥል ግድግዳ የፈረሰበት ስለሆነ ነው
👉👉“ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።”
— ኤፌሶን 2፥16
ነገር በሶስት ይፀናል እንዲሉ ልሥልሰው😄
3ኛ በእኛ የነበረውን መርገም በመስቀሉ ስለሆነ ያስወገደልን 👉👉
“በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤”
— ቆላስይስ 2፥14
ስለዚህ በአጭሩ መስቀልን የምናከብረው ጌታ ክርስቶስ ተሰቅሎ ክቡር ደሙን ቅዱስ ስጋውን አፍስሶ ቆርሶ ስለቀደሰው ነው ለእኛም ሀይላችን ነው ለሚጠፉት ግን መኞትን ፌዝነት ነው
መልካም ቀን መልካም በዓል
✍✍ esuye (ከሀጢያተኞች ዋና
❤18👍1👎1
ከሀጥያት ሳላመልጥ
ፀሎት ስገዳድፍ ፤
ስሜት ሳገለግል
ከአለም ስጨላልፍ፤
እናት ያለው እግዜር
እናት ያለው አምላክ
እሱ አልተቆጣኝም
ፍፁም ነው የታገሰኝ ፤
በቃኝ የማላውቀው
እኔ ግን ተቆጣሁ
ነውሬ እየበዛ ከሰው ሲያንሰኝ፤
እስቲ እንደው ፍረዱ
እግዜር ምን አረገ፤
እናቱን በሰጠኝ
ንስሀን ባቀና እኔን በታደገ፤ ?
አዳምን በማረ ?
እኔን ጎስቋላውን
ይዞ በትከሻው ፤
ስጋዬ ሲራገፍ
ከአፍር ስመለስ
ግራ ገብ ህይወቴ
የት ይሆን መድረሻው ፤?
ወየውልሽ ነብሴ ለምትዝበቺ ፤
ያልተፈታ ቅኔ ጮኸሽ ለምትፈቺ ፤
ግዜው አይጠብቅም
እንደጉድ ይሄዳል ፤
ሰው በምድር ሳለ
ሲኦልን ይወዳል ?
እንዴት እንዴት ነብሴ ፤
ከስጋ ልጣላ አስታርቂኝ ከራሴ፤
ቀን እየነጎደ ሲቀንስ ሲበዛ፤
ንስሀ እገባለሁ ... ንስሀ እገባለሁ
ጉራዬን ስነዛ ፤
የመዳን ቀን ዛሬ
ሲሆን እያወኩኝ ፤
ሀጥያቴን ስቆጥረው
አሁንም ሳልወጣ
ሀጥያቴ መሀል ነኝ እንደተደበኩኝ ።
@dagi1u
ፀሎት ስገዳድፍ ፤
ስሜት ሳገለግል
ከአለም ስጨላልፍ፤
እናት ያለው እግዜር
እናት ያለው አምላክ
እሱ አልተቆጣኝም
ፍፁም ነው የታገሰኝ ፤
በቃኝ የማላውቀው
እኔ ግን ተቆጣሁ
ነውሬ እየበዛ ከሰው ሲያንሰኝ፤
እስቲ እንደው ፍረዱ
እግዜር ምን አረገ፤
እናቱን በሰጠኝ
ንስሀን ባቀና እኔን በታደገ፤ ?
አዳምን በማረ ?
እኔን ጎስቋላውን
ይዞ በትከሻው ፤
ስጋዬ ሲራገፍ
ከአፍር ስመለስ
ግራ ገብ ህይወቴ
የት ይሆን መድረሻው ፤?
ወየውልሽ ነብሴ ለምትዝበቺ ፤
ያልተፈታ ቅኔ ጮኸሽ ለምትፈቺ ፤
ግዜው አይጠብቅም
እንደጉድ ይሄዳል ፤
ሰው በምድር ሳለ
ሲኦልን ይወዳል ?
እንዴት እንዴት ነብሴ ፤
ከስጋ ልጣላ አስታርቂኝ ከራሴ፤
ቀን እየነጎደ ሲቀንስ ሲበዛ፤
ንስሀ እገባለሁ ... ንስሀ እገባለሁ
ጉራዬን ስነዛ ፤
የመዳን ቀን ዛሬ
ሲሆን እያወኩኝ ፤
ሀጥያቴን ስቆጥረው
አሁንም ሳልወጣ
ሀጥያቴ መሀል ነኝ እንደተደበኩኝ ።
@dagi1u
❤22👍2
