+ ከብዙ ባለጸግነት ይልቅ ጥቂት መታመን ይሻላል +
እነሆ ከ6 ወር በፊት በአሜሪካ የኾነ እውነተኛ ታሪክ።
በአሜሪካ ካንሳስ ሲቲ ነዋሪ የኾነችው ሳራ ዳርሊንግ በአንድ ወቅት ከሥራ ወጥታ ወደ መኖሪያ ቤቷ በማቅናት ላይ ሳለች ፣ አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ከመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ሲለምን ትመለከተዋለች።
ሳራ ወደ አዛውንቱ በመጠጋት ቦርሳዋን ከፍታ የተወሰኑ ዶላሮችን ሰውዬው ከጎኑ ባስቀመጠው የፕላስቲክ የገንዘብ ኮረጆ ውስጥ አኑራ ጉዞዋን ትቀጥላለች።
♦♦♦♦♦♦♦
ታዲያ በዚያ ቀን ማታ ቦርሳዋና በከፈተች ጊዜእንደሰጠችው ቀለበቱ በቦታው አልነበረም። ለየኔ ቢጤው ከገንዘቡ ጋር አብራ ያስተዋለቺው ሳራ በአስቸኳይ የኔ ቢጤው ወደ ነበረበት ብትመለሰም ከቦታው አላገኘችውም። በሚቀጥለው ቀን ለእጮኛዋ የኾነውን ነግራው አብረው መጡ። አኹንም ሰውዬው በቦታው አልነበረም። ለሦስተኛ ጊዜ በቀጣዩ ቀን ተመልሰው መጡ። በዚኽ ጊዜ ግን ሰዎዬው በቦታው ነበረ። ሳራ በደስታ ተመልታ ዳግመኛም ፣ "ይክደኝ ይኾን?" በሚል ፍራቻ ተውጣ ፣ የኾነውን ለአዛውንቱ አስረዳችው። አዛውንቱም መለሱ ፣ " አንድ ሱም እንደምትመለሺ ዐውቅ ነበር። ኦሪጅናል ወይም ኮፒ እንደኾነ ዐውቅ ዘንድ ወደ ጌጣጌጥ ሱቅ ወሰድኹት። እነርሱም $4000 እንደሚያወጣ ነገሩኝ። እኔ ግን ልትረዳኝ ፈቃደኛ የኾነችን ሴት ንብረት ልወስድ አልወደድኹም " ብሎ ቀለበቱን ያስረክባታል። በተአማኒነቱ የተደነቁት እሊኽ ጥንዶች በስሙ ድኅረ - ገጽ ከፍተው ዳግመኛም በማኅበራዊ ድኅረ ገጽ ገጠመኙን ነዙት። ወሬው ከጥግ እስከ ጥግ ተሰማ። ከ $190,000 በላይ መዋጮም ተሰበሰበለት!!!
♦♦♦♦♦♦♦♦
ቢል በአኹን ሰዓት የራሱ ቤት አግኝቷል። የራሱም መኪናም አለው። ባደረገው የሚኾን በቂ ገንዘብ እንዲኹ አግኝቷል። ይኽ ብቻ አይደለም። ስለኾነው ነገር ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረገው ቃለ መጠየቅ ፣ ከ16 ዓመት በላይ የተለያቸውን ቤተሰቦቹን ሞቷል ብለው ተስፋ ቆርጠው የተቀመጡትን ቤተሰቦቹን ለመገናኘት በቅቷል።
♦♦♦♥♥♦♥♦♦
ታማኝነት መልሶ ይከፍላል ማለት እንግዲኽ እንዲኽ ነው!
@menfesawimeker

#ካህኑ_ለምን_በእጁ_ያሳልመናል ?
................................................................
የካህኑን እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል ይላሉ።
ነገርግን ሚስጢሩ ይሄ ነው የካህኑ እጅ እኮ እሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት
የማይቻላቸውን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው።
በቅዳሴ ላይ ቅዱስ ሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ ነው ፤
ሁለተኛው ካህን እንኳን መንካት አይችልም። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን
የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ ያሳልመናል እኛም የተቀደሰውን የጌታ ስጋና ደም
የተዳሰሰበት እጅ እየተሳለምን የቅዳሴው በረከትና የአምላካችን ምህረት በእኛ ላይ
እንዲሆን አሜን አሜን እንላለን።
ድንቅ መለኮታዊ ሚስጢር ማለት
እንዲህ ነው...
አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦
ዲያቆኑ ይህን በሚልበት ጊዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ ላይ ያነሳል ፤ ይህም
የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ የማንከባለሉ ምሳሌ ነው። ከዚህ በኋላ ጌታችን
በምሴተ ሐሙስ ሕብስቱን እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን ከፍ አድርጎ
ይይዘዋል ፤ ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ ነው።
እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦
በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ይህም የዕርገቱ
ምሳሌ ነው። ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤ ይህም
አርባው እግዚኦታ አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ እንገርፋለን ብለው እያዛቡ ብዙ ግዜ
የመግረፋቸው ምሳሌ ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን የሚላት እግዚኦታ ደግሞ
የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ ስንል
ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን ስንል ነው።“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ”
የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!እንዲሁም 12ግዜ
በእንተእግዚትነ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ ስነንል ደግሞ ስለእናትህ ብለን ማረን
ማለታችን ሲሆን*ቅድስት ድንግል ማርያም*የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር
12 ይሆናልና ነው
ወንጌል፦
የመጀመሪያው መልዕክት ሲነበብ ዲያቆኑ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ ያነባል;
ሁለተኛው ዲያቆን ፊቱን ወደ ሰሜን አዙሮ ያነባል; ንፍቅ ካህን ወደ ደቡብ ዙሮ
የሐዋርያት ሥራን ሲያነብ ዋናው ካህን ደግሞ ወደ ምሥራቅ ዙሮ ወንጌልን ያነባል
፤ ይህም ግሩም የሆነ ምሳሌ አለው፦ አንድም ወንጌል በአራቱም አቅጣጫ
መሰበኩን ለመግለጽ ነው; አንድም ገነትን የሚያጠጡ 4 ወንዞች አሉ; ኤፍራጠስ
ጤግሮስ ጊዮን [ዓባይ] እና ፊሶን ናቸው። ገነትን አጠጥተው ለምለም
እንደሚያደርጓት ጌታችን የተጠማ ቢኖር የህይወትን ውሃ በነፃ ይጠጣና ይርካ
እንዳለው ወንጌሉም እንዲሁ ያለመልማል ሲሉ ነው።
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ
ቤተክርስቲያን እየተናገረች ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለች!!
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አያናውጧትም
ቤተክርስቲያን አ..ት..ታ..ደ..ስ..ም!
ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት
በኅበ እግዚአብሔር!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
እንማልዳለን!
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨

በተመሳሳይ ኃጢአት እየወደቅኩ ተቸገርኩኝ፡፡ ምን ላድርግ?
ጥያቄ፦ አንድ ኃጢአት በተደጋጋሚ እሠራለሁ፡፡ ንስሐ አባቴ ጋር በተደጋጋሚ ብሔድም ኃጢአቴን መተው አልቻልኩም፡፡ ምን ላድርግ? እባካችሁ ጉልበት የሚኾነኝ ምክር ስጡኝ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡”
አንድ ሰው “ምን ላድርግ?” ብሎ ሲጠይቅ መንፈሳዊ ሕይወትን መፈለጉ ማሳያ ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን “ምን ማድረግ ይገባኛል?” የሚል ጥያቄ ካነሣ ለማደግ መፈለጉን፣ መንፈሳዊ መፍትሔ መሻቱን፣ እግዚአብሔር እንደሚረዳው በማያጠያይቅ መንገድ ማመኑን ያመለክታል፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሚያስተምርበት ጊዜ ሕዝቡ፣ ቀራጮች እንዲኹም ጭፍሮች እየመጡ፡ “ምን እናድርግ?” ይሉት ነበር ሉቃ.3፡10-14 ፡፡ ስለጠየቁም “ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ” ብሏቸዋል /ማቴ.3፡8/፡፡ ሐዋርያት ሲያስተምሩ፡- “ወንድሞች ሆይ! ምን እናድርግ?” ያሉት የገባቸው ናቸው /ሐዋ.2፡37/፡፡ ስለዚኽ ምንም ደካሞች ብንኾንም ድካማችንን ከእኛ የሚያርቀው አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር “በርሱ ቃል እታነፃለኁ፤ እመከራለኁ” ብሎ “ምን ላድርግ?” ብሎ መጠየቅ ታላቅነት፣ አንድም ትሕትና፣ አንድም የመንፈሳዊ ሕይወት ፍላጎትን የሚያሳይ ነውና ኹል ጊዜ ጠያቂዎች ለካህናት፣ ለቤተ ክርስቲያን መምህራን “ምን ማድረግ ይገባኛል?” ብለው ሲጠይቁ ሊበረታቱ ይገባቸዋል፡፡ በመኾኑም ውድ ጠያቂያችን ምሥጢራቸውን በማካፈል የኃጢአት ልምምድ ድል መንሻ ጥበባትን እንድንማማር ምክንያት ስለኾኑን በልዑል እግዚአብሔር ስም ላመሰግናቸው እወዳለኁ፡፡ ጥያቄው የብዙ ሰዎች ጥያቄ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ፡- “ሰው ኾኖ የማይበድል እንጨት ኾኖ የማይጤስ” እንዲሉ እንደየኑሮአችን ደረጃ፣ እንደየሥራችን ዓይነት ይለያይ እንደኾነ እንጂ ክርስትና ሕይወታችን ስንመላለስ አንድ ከሚያደርጉን ነገሮች ውስጥ ኃጢአት የሚስማማን መኾኑ ነው፡፡ ጥያቄአችንም ጠያቄአችን እንዳነሡት “ምን እናድርግ?” ነው፡፡ በርግጥም “ምን እናድርግ?”፦ የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ማወቅ፡- አንድ ሰው የሚወድቅበት ሌላኛው የማይወድቅበትና ትኩረት የማይሰጠው ሊኾን ይችላል፡፡ ከዚኽ አንጻር ጠያቂው “በተመሳሳይ ኃጢአት ደጋግሜ እወድቃለኁ” ያሉት ኃጢአት ምንድነው? እየተደጋገመ ያስቸገራቸው ምንድነው? ከምንም በፊት የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ያጢኑት፡፡ መፍትሔው የሚዠምረው ከዚኽ ነው፤ የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ከማወቅ፡፡ የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ከለዩ በኋላ ለዚያ ከሚዳርጉን ቦታዎች፣ ወይም ጓደኞች፣ ወይም ኹኔታዎች መሸሽ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ወደምንወድቅበት ኃጢአት የሚገፋፉ ኹኔታዎችን፣ ቦታዎችን ወይም ጓደኛን በአጠቃላይ እንደየኃጢአቱ መነሻነት መራቅ ያስፈልጋል፡፡ “ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ኾነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ኾነህ ትገኛለህ” ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት /መዝ.18፡ 26/፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም፡- “አትሳቱ፤ ክፉ ባለንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል” ይላል /1ኛ ቆሮ.15፡33/፡፡ በዚኽ መሠረት ጠያቂያችን ብቻ ሳይኾኑ ኹላችንም ኃጢአትን ደጋግመን የምንሠራው በኹኔታዎች ተጽዕኖ ነው? ወይስ በጓደኞች ግፊት? ወይስ በምንሰማው፣ በምናየው፣ በምንዳስሰው ተጽዕኖ? ይኽን በአግባቡ ከለየን በኋላ ከምንጩ ለማድረቅ ለዚያ ከሚዳርጉ ኹኔታዎች መሸሽ ነው፡፡ ይኽን ስናደርግም ከምንም በፊት ኅሊናን ማሳመን ይጠይቃል፡፡ በመቀጠልም አካላዊ ውሳኔ መስጠትን ነው፡፡ ለኃጢአት በሚዳርግ ቦታ ተቀምጠን “በፍጹም አይነካኝም፤ አይደርስብኝም” ማለት መመጻደቅ ነው፡፡ ሰይጣንም እኛን ለመጣል አያርፍምና የምንወድቅበትንም መንገድ ያዘጋጃልና በኅሊናም በአካልም ከዚያ መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ የጴጢፋራ ሚስት ዮሴፍን ለክፉ ሥራ ስትከጅለው ቆሞ አልተሟገተም፤ ጥሏት ሸሸ እንጂ /ዘፍ.39/፡፡ ስለዚኽ ለተደጋጋሚ ኃጢአት ከሚዳርጉንና ከሚገፋፉን ነገሮች “እችለዋለኁ፤ እቋቋሟዋለኁ” ብሎ መመጻደቅ ሳይኾን መሸሽ ካለብን መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ እንደየኹኔታው በይበልጥም ከክፉ ቦታዎች፣ እንደየኃጢአቱ መነሻነት መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ ኃጢአቱ በሥጋም በነፍስም ጎጂ እንደኾነ ማስተዋል፡፡ ይኽ በተመሳሳይ እየወደቅንበት ያለው ኃጢአት በሥጋም ጭምር የሚጎዳን ይኾናል፡፡ ከክርስትና ሕይወት ባሻገር ስብእናን የሚያጎድፍ፣ ጤናን የሚያውክ ሊኾን ይችላል፡፡ ከዚኽ አንጻር የዚኽ ጉዳት በጥልቀት ማስተዋል ያስፈልጋል፤ ጉዳት ማሰብ ለመጠንቀቅ ይረዳልና፡፡ ከመምህረ ንስሐ፣ ከመምህራን እንዲኹም ከመጻሕፍት ትምህርት ማግኘት፡፡ እድገት በደረጃ ነው፡፡ በአንድ ጀምበርም ለውጥ ላይመጣ ይችላል፡፡ በመኾኑም በሒደት ያንን የመተው መስመር ውስጥ እንድንጠነክር ከዚኽ ኹኔታም ፈጽመን ለመራቅ በራሳችን ጉልበት ብቻ አንችልም፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብሎናልና /ዮሐ.15፡5/፡፡ በዚኽም መሠረት ከመምህራን የምንሰማው የእግዚአብሔር ቃል፣ ከመጻሕፍት የምናገኘው፣ ከመምህረ ንስሐም በጸሎትና በምክር የምናገኘው ሐሳብ ያ እያጠቃንና እየጣለን ያለውን እንዲኹም የምንደጋግመውን ኃጢአት ለማስወገድ ኃይል ይኾነናል፡፡
መንፈሳዊ ተግባራትን ማዘውተር፡፡ እንግዲኽ እንደየ ክስተቱ ለየትኛውም የኃጢአት ተግባር መንፈሳዊ ሕይወት፣ መንፈሳዊ ተግባር ድል መንሻው ነው፡፡ ይኽም “እንዲኽ ያለውን ክፉ መንፈስ ያለ ጾም ያለ ጸሎት ከእናንተ አይወጣም” እንዳለ /ማር.9፡29/ ጾምን፣ ጸሎትን፣ ንስሐን የሕይወታችን መሠረት ማድረግ ነው፡፡ መተውን መለማመድ፡፡ ይኽም ማለት ጠቢቡ “ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር” እንዳለ /ምሳ.23፡17/ “እስኪ ዛሬ ተቆጥቤ ልዋል” ብሎ መወሰን ማለት ነው፡፡ ከዚያ ከምንጠላው ግን ደግሞ እየወደቅንበት ካለው ስሕተት ተቆጥበን ከዋልን ማታ ላይ ተመስገን ብሎ ጸልዮ ማደር ነው፡፡ ነገም ሲነጋ “ዛሬም እንዲኹ እንደ ትናንትናው መንፈሳዊ መንገድና ሒደት ልዋል፡፡ ዛሬም እንዲኽ ካለው ተግባር ፍጹም ተቆጥቤ መዋል አለብኝ፡፡ ደግሞም እችላለኁ፡፡ እግዚአብሔር ያስችለኛል፡፡ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ኹሉን እችላለኁ፡፡ እግዚአብሔር ያበራታኛል” ስንልና ዕለት ዕለት ኹኔታውን እየኰነንነው፣ እያወገዝነው፣ “በዚያ መንፈስ ዛሬ አልውልም፡፡ ይልቁንም በመንፈሳዊ መንገድና በጥንካሬ እውላለኁ” ብለን ስንወስን ያን ውሳኔአችንን እያደነቅን ስለተደረገልን ጥንካሬም ተመስገን እያልን ልምምድ ማድረግ ይቻላል፡፡ ደጋግመን የምንሠራው ኃጢአት እጅግ ብዙ ዘመናት ከእኛ ጋር የቆየ ሊኾን ይችላል፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ኃይል በላይ የኾነ ኃጢአት የለም፡፡ ዋናው የእኛ ውሳኔ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የምንታለለው እዚኽ ጋር ነው፡፡ ለመተው እንፈልጋለን፤ ለመተው ግን በተግባር አንወስንም፡፡ ንስሐ መግባት የማይፈልግ ሰው የለም፤ በተግባር ወስኖ የሚገባ ግን ጥቂት ነው፡፡ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ መኖር የማይፈልግ ክርስቲያን አይኖርም፡፡ ብዙዎች መቁረብ ይፈልጋሉ፤ ወስነው የሚቆርቡት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙ ሰዎች ከዝሙት ኃጢአት መራቅ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ዝሙትን የሚያበረታቱ ማስታወቂያዎችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ምስሎችን እንዲኹም የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ዘፈኖችን እንዲኹም ጽሑፎችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ንግግሮችን ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ እነዚኽን ሰዎች ስናያቸው በውስጣቸው ከዚያ ኃጢአት የመራቅ ፍላጎት አለ፤ ተግባሩ ላይ ግን ከዚያ የሚያሸሻቸው አይደለም፡፡ ለዚኽም ነው ጌታ፡- “ብዙዎች ይፈልጋሉ፤ አይችሉምም” ያለው:: @menfesawimeker

🦋 ክርስቲያን ሴት ሊገጥማት ከሚችሉ ፈተናዎች መካከል፦
1.በሌሎች አቻዎች መገለል ማለትም በአለባበስ በአነጋገር አመጋገብ እንዲሁም በሌሎች ነገሮች ፍጹም የተቆጠበችና ሥርዓት የምትጠብቅ በመሆኗ በአለማውያን ዘንድ ተቀባይነት አያገኝም ስለዚህ ትገለላለች።
2. ከመገለል በተጨማሪ የአቻ ግፊትም ይደርስባታል ይህ ማለት፤ ዓለማውያኑን ወደእነርሱ አነዋወር እንድትሄድ ከክርስትና ሩጫ ለማስወጣት ዲያቢሎስ ይጠቀምባቸዋል
3.ፈተናውን ውጫዊና ውስጣዊ
ብለን ልንከፍለው እንችላለን፡፡
1) ውስጣዊ ፦ ፍትወት [ የትውዝፍት ፤ የዝሙት ፤ የሀብት ፤ የመሳሰሉት....]
2) ውጫዊው ፦ የውስጣዊው መገለጫዎች ናቸው፡፡
[ አለባበስ( የምንዝር ጌጥ ) ፤ ዝሙት( በገቢር ) ፤ Sensuality , apathy , loss of control etc..
ይህ በሁሉም ወጣት ሊደርስ የሚችል ሲሆን ክርስቲያኖች ላይ ግን ይጸናል።

፨በጭንቀት ጊዜ የሚያፅናኑ ቃላት፨
።> እነሆም እኔ እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴ28፥20
∞∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞
።> በአንቺ ላይ የተሰራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም። ኢሳ 53፥17
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >እኔ ነኝ አትፍሩ አላቸው።
ዮሐ 6፥20
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ፤ ሰዎች በእኛ ላይ በተነሱ ጊዜ ቁጣቸዉ በላያችን በነደደ ጊዜ ፤ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤ ....ለጥርሳቸዉ ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ ። ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን ። ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ነዉ። መዝ 123፥2፤3፤6-8
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> ፃድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ ፤ የኃጥአን በትር በፃድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም። መዝ 124፥3
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስልሃለሁ ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።
ዘፍ 28፥15
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> ከአንተ ጋር ይዋጋሉ ፤ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሱህም ፤ ይላል እግዚአብሔር ኤር 1፥19
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> እኔ ከአንተ ጋር ነኛ ፤ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሳብህ የለምና አትፍራ፤
ሐዋ18፥9-10
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ፤ነገር ግን አይዟችሁ ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ።
ዮሐ 16፥33
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም። ኃጢአተኞች በጀርባዬ ላይ መቱኝ ፤ኃጢአታቸዉንም አስረዘሟት ። እግዚአብሔር ፃድቅ ነው ፤ የኃጢአተኞችን አንገታቸውን ቆረጠ ።
መዝ 128፥2-4
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።>ገፉኝ ለመዉደቅም ተንገዳገድሁ ፤ እግዚአብሔር ግን አገዘኝ ። መዝ 117፥13
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ ፤አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም።
መዝ 22፥4
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አስር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደአንተ ግን አይቀርብም ። በአይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ ፤ የኃጥአንን ብድራት ታያለህ። መዝ 90፥7-8
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል ፤ ነፍስህንም ይጠብቃታል ። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለአለም እግዚአብሔር መዉጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል። መዝ 120፥7-8
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> እግዚአብሔር ብርሃኔና
መድሀኒቴ ነው ፤ የሚያስፈራኝ ማንነው ? እግዚአብሔር የህይወቴ መታመኛዋ ነው ፤የሚያስደነግጠኝ ማነው ? ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም ፤ ሰልፍም ቢነሳብኝ በዚህ እተማመናለሁ
መዝ 26፥1-3
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን ይላክልን ቸሩ አምላካችን!
📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌
@Menfesawimeker
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ)
#
#የንስሐ_መሰናክሎች (እንቅፋቶች)
ሰይጣን ከሚዋጋቸው የድኀነት መንገዶች ውስጥ ንስሐን የሚያክል የለም። ምክንያቱም ንስሐ ጠላት ዲያቢሎስ የክርስቲያኖች ሕይወት ለማጥፋት የገነባውን የኃጢአት ሕንፃ ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት እንዳልነበር በማድረግ ስለሚያፈርስበት ነው ። ከዚህ የተነሳ የሰው ልጅ ንስሐ እንዳይገባ ፣ ቢገባም ቶሎ እንዳይሆን የተቻለውን ከማድረግ ፈጽሞ አያርፍም ። ከሚጠቀማቸው መሰናክሎች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ ።
#ሀ እንቅፋት መፍጠር ፦ እነዚህ ድንገተኛ ፈተናዎች ወይም አጋጣሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ ። እነዚህ አጋጣሚዎች ወይም ፈተናዎች ተነሳሒው በድፍረት ወደ ንስሐ እንዳይመጣና ከኃጢአቱ እንደረይመለስ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ናቸው ።
#ለ ኃጢአተኛው ራሱን ከእርሱ የቀለጠ ኃጢአት ሠሩ ከሚላቸው ጋር በማነፃፀር የተሻለ እንደሆነ እንዲገምትና ንስሐም እንደማያስፈልገው ራሱን ማሳመን ፤ #ቅድስና ግን ከኃጢአተኛ ሕይወት ሕይወት ጋር ሊነፃፀር አይገባም ። ኖኀ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቅዱስ እንደነበር ዮሴፍ፣ ሎጥና ሙሴም በኃጢአተኞች መካከል ቅዱሳን እንደነበሩ እኛም መቀደስ አለብን እንጂ እራሳችንን ማነፃፀር የለብንም ።
#ሐ ከሥጋ ድካም የተነሳ በአካባቢ ተፅእኖ መመራት ፦ ተነሳሒው ሰው በዓለም የማይታለል ጽኑ አቋም እንዲኖረው ያስፈልጋል ። ቅዱስ ጳውሎስ "ይህን ዓለም አትምሰሉ " እንዳለ ። (ሮሜ 12:2) #ዓሣ ትንሽ ሲሆን ማዕበል በሚያናውጠው ባሕር ውስጥ ይዋኛል ። ክርስቲያንም እንዲህ ሊሆን ይገባዋል ። ደካማ ስጋን ቢለብስም ፈተናውን ተቋቁሞ ለንስሐ መብቃትና በመንፈሳዊ ሕይወት መኖር ይገባዋል ።
#መ መዘግየት ፦ ዲያቢሎስ ንስሐ እንዳንገባ የሚወረጋን በቀጥታ አይደለም ። ነገር ግን የተለያዩ ስውር ፈተናዎችን እየደቀነ እንዳንገባ ያዘገየናል። #መዘግየት ከሚያስከትለው አደጋ አንዱ ለንስሐ የተዘጋጀውን ልቡና መለወጥና ለንስሐ ያለውን ዕድል ማጥፋት ነው ።
#ሠ ተስፋ መቁረጥ ፦ ይህ ንስሐ የማይቻልና ሊደረግ የማይሞከር እንደሆነ አድርጎ ማሰብ ነው። ሰይጣን በኃጢአት ከመውደቃችን በፊት የእግዚአብሔርን ቸርነትና ይቅርታ በማሰብ እንድንራ ያደርገናል ፤ ከሰራነው ቡሃላ ደሞ የእግዚአብሔርን ፍርድና ጨካኝ እንደሆነ ያሳስበናል ። ንስሐ እንዳንገባም ተስፋ ያስቆርጠናል ።

✟
#ይህን_የመሰለ_ጠባቂ_ከቶ_አታገኝም።
#የኢየሱስ_ክርስቶስ_ስቅለት_ሁሌም_በፊታቸው_ይስሉ_ዘንድ_ለልጆችህ_በጥንቃቄ_አስተምራቸው።
✟
ልጄ ሆይ ማናቸውንም ነገር በምትፈፅምበት ጊዜ ሥራህን በፀሎት ጀምር። የምትሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በትምህርተ መስቀል ባርካቸው።
በምትበላም፣ በምትጠጣም ጊዜ፣ በምትተኛም፣ በምትነቃም ጊዜ፣ በቤት ውስጥም ሳለህ ይሁን በጎዳና፣ ማማተብን አትዘንጋ። የጌታህን ስቅለት አስታውሶ ከክፋት የሚጠብቅህ ይህን የመሰለ ጠባቂ ከቶ አታገኝም።
እርሱ ለምታደርጋቸው ድርጊቶችህ ሁሉ እንደ ግንብ ነው (ማስተዋልን ይሰጥኻል)። ማማተብን በስርዓት ይፈፅሙት ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሁሌም በፊታቸው ይስሉ ዘንድ ለልጆችህ በጥንቃቄ አስተምራቸው።
✍...
#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ
✤
የሕይወት እናቱ ሆይ፤ ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው በአንድ ልጅሽና በእኛ መካከል አስታርቂን።

ጸሎት መጸለይ ለምን እንደሚከብድህ ታውቃለህ?
ወንድሞች በአንድ ወቅት አባ አጋቶንን ጠየቁት፤ “ከመልካም ሥራ ሁሉ የትኛው በጎ ሥራ ከሁሉ የበለጠ ጥረት (ድካም) ይጠይቃል?”። እርሱም መለሰ “ይቅርታ አድርጉልኝ፣ እኔ ወደ እግዚአብሔር ከመጸለይ የበለጠ ከባድ ሥራ ያለ አይመስለኝም። አንድ ሰው ለመጸለይ በፈለገ ጊዜ ሁሉ፣ ጠላቶቹ አጋንንት እንዳይጸልይ ሊከለክሉት ይሻሉ፤ ከመንገዱ ሊያደናቅፉት የሚችሉት ከጸሎት እንዲርቅ ሲያደርጉት ብቻ መሆኑን ያውቃሉና። ሰው ማንኛውንም ዓይነት በጎ ሥራ ቢሠራ፣ በሥራውም ቢጸና እረፍትን ያገኛል። ጸሎት ግን እስከ መጨረሻ ህቅታ ድረስ [እረፍት የሌለበት] ውጊያ ነው።
ስለዚህ ወዳጄ ውጊያ ከሰው ሳይሆን ከአጋንንት ነው እና ሁላችሁንም የሱን ጦር ሚያርቁልንን ጾም ጸሎት በማድረግ ሚከላከሉልንን መላእክት ማቅረብ አለብን ።

✝ ውዳሴ ኮንቱ የመሻት መዘዝ
ውዳሴ ኮንቱ መሻት የገሃነም እሳት እናት ናት። ውዳሴ ኮንቱን መሻት እስቱ የማይጠፋው ትሉ የማያንቀላፋው ዓለም መግቢያዋ ናት። ሌሎች ክፉ ምግባራት በሞት ይገታሉ። ውዳሴ ኮንቱን ግን አንድ ሰው ከሞተ በኋላ እንኳን ሊያደርገው የሚችል የከፋ ምግባር ነው ። በመኾኑም ውዳሴ ኮንቱ የገሃነመ እሳት እናት ናት እላለሁ። ሌሎች ክፉ ምግባራት ሰው ሲሞት ይቆማሉ ውዳሴ ኮንቱ ግን ከሞቱ በኋላ እንኳም የሚቀጥል ነው። ታድያ ከዚ የባሰ ምን አለ ልንል እንችላለን ? ምን ማለቴ እንደሆነ እነግራችህ ዘንድ ትሻላችሁን እስኪ ወደ መካነ መቃብር ሂዱ ብያንስ አሁን በአካል ባትሄዱ በአይነ ህሊናችህ ሂዱ ብዙ የበዙ ሐወልቶች አታገኙምን ? አዎ ከዚህ ሰዎች ከመሞታቸው በፊት የሚናዘዙት ሀብታቸው ለድኾች እንዲስጥ አይደለም። ሀብታቸው ብል እንዲበላው ሀወልት እንዲቆምላቸው እንጂ በቀብር ስነ ስርአት ላይ ለየት ያለ ትርዒት እንዲፈጸምላቸው ነው የሚናዘዙት። እነዚህ ሰዎች በዘመናቸው ድኾች ሲሳደቡ የነበሩ ናቸው። አንድ ቁራሽ ዳቦ ለድኻ መመፅወት ሲያሳፍራቸው የነበሩ ናቸው። የምድር ትላትል ይበሉት ዘንድ መቃብራቸው እንዲያምር ሲናገሩ ግን እጅግ ይጨነቃሉ። ወዮ! በአርአያ #ቅድስት_ስላሴ የተፈጠረውን ሰው ረስቶ ለትላትል ከመጨነቅ በላይ ምን ኮንትነት አለ ? ከዚህ የባሰ ምን ክፉ ደዌ ምን አለ።
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

እየጾሙ አለመጾም
ተወዳጆች ሆይ! እየጾሙ የጾምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦
✔ ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣
✔ ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
✔ ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ፣
✔ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትዕይንቶችን ከማየት ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ እየጾሙ እንዲህ አለመጾም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አምላከ ቅዱሳን እየጾሙ ካለመጾም ይሰውረን!

አላፍርም
✨✨✨✨✨
የብርሃን ጅረት ከእጆችሽ ይፈልቃል
ጨረቃ ከእግርሽ ከጫማሽ ሥር ወድቋል
ከዋክብት በዙሪያሽ ይመላለሳሉ
የጌታችን እናት አንቺ ነሽ እያሉ
ፈጣን ደመና ነሽ ገስግሰሽ ስትደርሺ
ስምሽን በሚጠራው በህዝብሽ ንገሺ
ንገሽ እመቤቴ ግነኚ በዓለም
ከፍጡራን መሐል የሚመስልሽ የለም
ማነው ልበ ንፁህ የሃሳብ ድንግልና
አጣምሮ የያዘ ከሥጋ ንፅህና
እናትም ድንግልም ለመሆን የቻለ
ቅድስት ሆይ አንቺ እንጂ ሌላ ወዴት አለ?
ብርሃን አፍልቃ ወልዳ ፀሐየ ጽድቅ
ማናት የተሰኘች አማናዊት ምሥራቅ?
እመቤቴ አንቺ ነሽ ድንቅ ምልክቷ
በኪዳናት መሐል ምሥክር ሐውልቷ
ጽዮን ቅድስቲቷ ማርያም ንግስቲቷ
ርኅርይተ ኅሊና ድንግል አዛኝቷ
አምሳለ ኪሩብ ነሽ መንበረ መንግስት
የእሳት መቅረዝ ይዘሽ ወለድሽ መለኮት
ለማይነገረው ለክብርሽ ብዛት
እጅ እነሳለሁኝ የጌታዬ እናት
የባለፀጋ እናት ፀጋሽ በእኔ በዝቶ
ባዶ ማድጋዬ በረከት ተሞልቶ
ሃፍረቴ ይከደን ይቅር ነውር እርሜ
ቀና ብዬ ልሂድ ተጠግኖ ቅስሜ
በልጅሽ ፀጋ ውስጥ በክብርሽ ተውጬ
የመንግሥቱ ዜጋ ልሆን ተለውጬ
ፊትሽ በሚፈሰው ብርሃን ተጥለቅልቄ
ቃላት በማይገልጠው ግርማሽ ተደንቄ
ለመኖር እሻለሁ ናፍቄያለሁ በጣም
ዕድል ፈንታዬ ነሽ እመቤቴ ማርያም
ምልጃ ቃልኪዳንሽን አንቺን ተመርኩዤ
የልጅሽን መስቀል ቸርነቱን ይዤ
አምናለሁ እናቴ አልጠራጠርም
ተሥፋዬ ጽኑ ነው እኔ በአንቺ አላፍርም!
_
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
✨✨✨✨✨
የብርሃን ጅረት ከእጆችሽ ይፈልቃል
ጨረቃ ከእግርሽ ከጫማሽ ሥር ወድቋል
ከዋክብት በዙሪያሽ ይመላለሳሉ
የጌታችን እናት አንቺ ነሽ እያሉ
ፈጣን ደመና ነሽ ገስግሰሽ ስትደርሺ
ስምሽን በሚጠራው በህዝብሽ ንገሺ
ንገሽ እመቤቴ ግነኚ በዓለም
ከፍጡራን መሐል የሚመስልሽ የለም
ማነው ልበ ንፁህ የሃሳብ ድንግልና
አጣምሮ የያዘ ከሥጋ ንፅህና
እናትም ድንግልም ለመሆን የቻለ
ቅድስት ሆይ አንቺ እንጂ ሌላ ወዴት አለ?
ብርሃን አፍልቃ ወልዳ ፀሐየ ጽድቅ
ማናት የተሰኘች አማናዊት ምሥራቅ?
እመቤቴ አንቺ ነሽ ድንቅ ምልክቷ
በኪዳናት መሐል ምሥክር ሐውልቷ
ጽዮን ቅድስቲቷ ማርያም ንግስቲቷ
ርኅርይተ ኅሊና ድንግል አዛኝቷ
አምሳለ ኪሩብ ነሽ መንበረ መንግስት
የእሳት መቅረዝ ይዘሽ ወለድሽ መለኮት
ለማይነገረው ለክብርሽ ብዛት
እጅ እነሳለሁኝ የጌታዬ እናት
የባለፀጋ እናት ፀጋሽ በእኔ በዝቶ
ባዶ ማድጋዬ በረከት ተሞልቶ
ሃፍረቴ ይከደን ይቅር ነውር እርሜ
ቀና ብዬ ልሂድ ተጠግኖ ቅስሜ
በልጅሽ ፀጋ ውስጥ በክብርሽ ተውጬ
የመንግሥቱ ዜጋ ልሆን ተለውጬ
ፊትሽ በሚፈሰው ብርሃን ተጥለቅልቄ
ቃላት በማይገልጠው ግርማሽ ተደንቄ
ለመኖር እሻለሁ ናፍቄያለሁ በጣም
ዕድል ፈንታዬ ነሽ እመቤቴ ማርያም
ምልጃ ቃልኪዳንሽን አንቺን ተመርኩዤ
የልጅሽን መስቀል ቸርነቱን ይዤ
አምናለሁ እናቴ አልጠራጠርም
ተሥፋዬ ጽኑ ነው እኔ በአንቺ አላፍርም!
_
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🍟🎂ተጠቃሚ ያጡ መድኃኒቶች🍛🍧🍟
🍡🍢1/ ቃለ እግዚአብሔር
🌕🌒ጠዋት አንድ
🌒🌙ማታ አንድ
🍢🍡2/ ንስሐ
🌺በየሳምንቱ አንድ አንድ
🍢🍡3/ ስጋወ ደሙ
🌹🌺🌼 ቢያንስ በ40 ቀን አንዴ
🍢🍡4/ ጸበል
⛈⛈ ከምግብ በፊት በየቀኑ አንዴ
🍢🍡5/ እምነት
❤️ዘወትር በየሰከንዱ ያለማቋረጥ
🍢🍡6/ ፍቅር
💔ዘወትር ያለማቋረጥ ለሁሉም
🍢🍡7/ ሰላም
🍁ለተከታታይ ሰዓታት እስከ ዘላለም
🍢🍡8/ጸሎት
📕📗🙏 በቀን ሰባት ግዜ ያለማቋረጥ
🍢🍡9/ ፆም
😒☺️ ከምግብ በፊት
🍬🍢10/ ምፅዋት
💰💷 በየቀኑ ከምታገኘው ጥቂቱን
🍢🍡11/ ስግደት
🙇🙇♀ ጠዋት 41
🙇♀🙇 ማታ 41
☞☞ማሳሰቢያ፡- ሁሉም መድኃኒቶች ተስፋ በተባለ ውሃ ማወራረጃነት መዋጥ ይኖርባቸዋል።
⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅

በሕይወት ሳለን በዚህ ዓለም የሚዋሰን ከአልፈለግን በሰማይ የሚዋሰን አናገኝም ይህ ማለት በዚህ ዓለም እንደሚቻለን ርኅራኄ ከአላደረግን ድኆችን ጦም አዳሪዎችን ከረሳን በሰማይ የሚዋሰን የሚቀበለን የለም ማለት ነው ፡፡
እግዚአብሔር በቅዱሳኖቹ ስም ድኆችንና ጦም አዳሪዎችን ብናስብ በሱ ብናምን ወዳጆቹን መላእክትን ብናከብር ስማቸውን ብንጠራ በጸሎታቸው ብንማፅን እሱም ይቅር ይለናል እነሱም ይቀበሉናል ።
እነሱም በሰማይ ባለው ቤት ይቀበሏችሁ ዘንድ በዐመፃው ገንዘብ ወዳጅ ግዙበት ብሎ ጌታችን እንደተናገረ ያላቸው ድኆች ናቸው ።
እግዚአብሔርን ባናምን መላእክቱን ወዳጆቹን ባናከብር ትእዛዙን ቸል ብንል ግን በፍርድ ቀን የሚያድነን የለም ።
በዚህ ዓለም ንሥሓ ከአልገባን ቸርነት ከአላደረግን በሰማይ ምሕረትን አናገኝም ።

ራስህን ኃጥእ አድርግ!
‹‹በብዙ ሲጋደሉ እንደኖሩ የቅዱሳንን ታሪካቸውን ሰምተናል፡፡ ነቢይ ዕዝራ የዱር ዛፍ ፍሬ እየተመገበ ውሃም እየጠጣ በምድረ በዳ እየጾመ ኖረ፡፡ ነቢይ ኢሳይያስም የሜዳ ጎመን እየቆረጠ ከእርሱም እየተመገበ ውሃም እየጠጣ በተራራ እየጾመ ኖረ፡፡ እግዚአብሔር ስሙን ‹የበረሃ ኮከብ› ብሎ የጠራው የመነኰሳት በኩር የሆነ አባ እንጦንስና አባ መቃርስም በደረቅ ኅብስትና በውሃ ብቻ ሲጋደሉ ኖሩ፡፡ እኚህ ምድራዊያን ሲሆኑ ሰማያውያን ሆኑ፡፡ ነቢይ ኤልያስም በኅብስትና በውሃ ብቻ በምድረ በዳ ሲጋደል ኖረ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ግን ሰባት ዓመት ሙሉ ውሃ ሳይቀምስ ኖረ፡፡ ከመነነ በኋላ እስከሞተበት ዕለት ድረስ እህል የሚባል አልቀመሰም፡፡ እርሱ ግን ራሱን በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ ያደርግና በትሕትናም ሆኖ ስለ ኃጢአቱ ሁልጊዜ ያለቅስ ነበር፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ይህን ሁሉ የተጋደለ በራሱ ኃይል አይደለም፤ በእግዚአብሔር ኃይል ነው እንጂ፡፡ አንተም ወንድሜ ሆይ! ራስህን ዕወቅ፡፡ ምንም ተጋድሎን ብታደርግ ጾምኩ፣ ተራብኩ፣ ስለ እግዚአብሔርም ብዬ ራሴን አደከምኩ፣ እግዚአብሔርንም ስላገለገልኩ በሥራዬም እድናለሁ አትበል-መጨረሻህን አታውቅምና፡፡ አንተ ግን ስለ እግዚአብሔር ብለህ ራስህን ኃጥእ አድርግ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ያጸድቅሃልና፡፡ ›› ገድለ አባ በግዑ፡፡
አምላከ ቅዱሳን ይደምረነ ምስለ ኩሎሙ ቅዱሳኒሁ 👉 @menfesawimeker
👆👆👆📖👆👆👆
ለ አስተያየት ወይም መንፈሳዊ ጥያቄ ካሎት
@menfesawimekerbot

✍ መንፈሳዊ፡ህይወት፡ማለት
መንፈሳዊ መሆን ማለት የራሰን ፊቃድ ለእግዚአብሔር ማስገዛት ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራል
ራሱ ግን በማንም አይመረመርም፡፡ (1ኛ ቆሮ2÷15) ሥርዓተ ሃይማኖትን ትውፊተ አበውን ገንዘብ አድርጎ መኖር መንፈሳዊነት ነው፡፡
አንድን ሰው መንፊሳዊ ነው ለማለት ሊፈጽማቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡እነርሱም፡
1.ተዓምኖ፤(መታመን) ፤እምነትን በተግባራዊ መልስ ማሳየት ማለት ነው፡፡ስለንስሓ የሚሰብከ ንስሓ የገባ መሆን አለበት፡፡ካልሆነ ችግር ነው፡፡ጣዕሙን አያውቀውም፡፡የዘመናችን ሰባክያነ ወንጌል መሠረታዊ ችግር ይህ ነው፡፡የሚጮህ አልጠፋም በተግባር የሚሰብከ
ግን ማግኘት ከባድ እየሆነ ነው፡፡
አንድ አባት አንዱን ሰባኪ ወንጌል ሰው ዕኮ ቤተ ክርስቲያንን አይደለም የጠላው አሉት ! ታዳያ ማንን ነው ሲላቸው ሰባኪው እናንተን ነው የጠላው ያላችሁትን ስለማታደርጉ አሉት ፡፡
አንድ ፓስተርም ጸልዩ አልቅሱ እያለ እሱ ግን አይጸልይም
አያለቅስም ይባስ ብሎ ስልክ ያወራል፡፡ፓሰተር ለምን አንተ አታለቅሰም ? ሲሉት አይ ጌታዬ የእኔ ሥራ ማስለቀስ ነው አለ፡፡
2.ምግባራተ ሠናያት አንድ ሰው እምነትን ተስፋን ገንዘብ ካደረገ በኋላ የሚቀረው ምግባረ ሠናይ ነው፡፡
መንፈሳዊ ሕይወት በማኀበራዊ ሕይወት ከተዋጠ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የነበረው አንድነትይላላል፡፡ሰዎችም ሐሳባቸው ሁሉ ምድራዊ ( ሥጋዊ) ወደ
መሆን ያዘነብላል፡፡ የበዓል ቀናትን ወደ ዕድር ዕቁብ ስብሰባ ይሆንና የመንፈሳዊ ሕይወት መስመር መላቅጡ ይጠፋል፡፡ መንፈሳዊነት በማኀበራዊነት ሲዋጥ በግለሰቡም በማኀበረሰቡም የሚታዩ ምልከቶች አሉ፡፡
1.ምክንያተኝነት፤ሰው ከመንፈሳዊ ሕይወት እየራቀ በሄደ ቁጥር አውቆም ሳያውቀውም ለፈጻማቸው ስሕተቶች ይቅርታን ከመጠየቅ ይልቅ ምክንያትን በመደርደር መታለፍን ይፈልጋል፡፡ በአዳምና በሔዋን የታየው የመንፈስ መራቆት የተገለጠው በምክንያተኝነት ነው፡”ወይቤ አዳም
ብእሲትየ እንተ ወሀብከኒ ምስሌየ ትንበር ይእቲ ወሀበተኒ ወበላዕኩ ”(ዘፍ3÷12)
መ. ምሳ18÷1” ምክንያተ የኀሥሥ በእሲ ዘይፈቅድ
ይትፈለጥ እም አዕርክቲሁ፤ከባልጀሮቹ ይለይ ዘንድ የሚፈልግ ሰው ምክንያት ይፈልጋል፡፡እንደ ሁለቱ አኀው በአንድ ቦታ የሚኖሩ ናቸው፡፡አንዱ የተማረ የበቃ ነው፡፡
አንዱ ያልተማረ ያልበቃ ነው፡፡ያልተማረው ያልበቃው መለየት ፍቃዱ ነውና ጓደኛውን ፀሐይ በየት ትወጣለች ብሎ ጠየቀው በምሥራቅ ብሎ ቢመልስለት ከዚህ ደንቆሮ
ጋር አልኖርም ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡መከራም አገኘው፡፡( ማር ይስሐቅ) ዛሬም አሉ የማይጠቅም ምክንያት በመደርደር ከአገልግሎት የሚርቁ ፡፡
2.መጎምጀት፤መንፈሰዊ ሕይወት የማደጉ ምልከት የሚታወቀው እንደ ሰራፕታዋ መበለት ያለውን አካፍሎ በመመገብ ነው፡፡የተገኘውን ለራስ ብቻ አውሎ ያለተገኘውንም በመጎምጀት መኖር ኃጢአት ሥር ይሰዳል፡፡
3.መመኘት፤ምቀኝነት መንፈሳዊ ሕይወት በሌለበት ምድር
የሚበቅል የልቡና አረም ነው፡፡ምቀኝነት በዘመናችን ምቀኝነት ከቤተ ክህነት እስከ ቤተ መንግስት ሰፊ የምሪት
ቦታ አለው፡፡ይህንን ሁሉ መከራ የምናስተናግደው ግን
መንፈሳዊ ሕይወት ጠፍቶና ሥጋዊነት ና ማኀበራዊ ሕይወት ብቻ በነገሠበት ምድር ላይ ነው፡፡
4.መተቸት፤መተቸት አብዛኛውን ጊዜ
“ሊቅነት”ከሚሰማቸው ለነገር ግን የፊደላት እጅና እግር
ከማያውቁ ሰዎች አካባቢ አይጠፋም ፡፡አይሠሩም
የሚሰራውን ይተቻሉ፡፡አያስተምሩም የሚያስተምረውን ዕዳ
ፍዳውን ያሳዩታል፡፡ ታዲያ ምን ይደረግ ተብለው ሲጠየቁ መልስ የላቸውም፡፡ ዕውቀታቸው መንፈሳዊነትን የተላበሰ
ሳይሆን መስፈርቱ ዕውቀት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡የዚህ ችገር ምኝጭ ማኀበራዊንቱ ብቻ በሰፈነባት ምድር ላይ በመሆኑ
አያሰደንቅም፡፡
5.የአኗኗር ለውጥ
ማኀበራዊነት ብቻ በዋጣት ምድር የሚኖሩ ሁሉ አንዱ ያደረገውን ሌላው ካላደረገ ራስን እንደኋላ ቀርነት
መቁጠር የተለመደ ነው ፡፡በዘመናችን ራስን ሁኖ ለመኖር የሚያስችል መንፈሳዊነት ተሟጦ ጠፍቷል፡፡የፊልሙ ጋጋታ የዓለም ገጽታ መለዋወጥ መንፈሳዊ ሕይወታችን ን በድርቅ እየመታው ነው፡፡
ገላትያ 5÷25” በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ
እንመላለስ”

መልካሙን ስለ መርሳት
💎💎💎💎💎💎💎
መልካም አድርግና እርሳው...
ስላደርግኸው ስለዚህ ነገር ማንኛውንም ዓይነት ውዳሴም ሆነ ሙገሳ አትሻ።
መልካም ያደረግህለት ሰው አንተ እንዳደረግህለት ለአንተ መልካም የሆነውን አጸፋ እንዲመልስልህ ወይም አንተ አንደተንከባከብከው እርሱም እንዲንከባከብህ አትጠብቅ።
መልካም ስታደርግ በምላሹ መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን! መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን።
መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን። መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገር ይሁን።
እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል።
መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ።
ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ