ከጃሂሊያ ምልክቶች መካከል :-

1- መሃይምነት የተጠናወታቸው አካሎች በሐሳብ የተቃረናቸውን አካል በሙሉ በመረጃ ፣በማስረጃና በጠንካራ ሐሳብ መርታት ሲከብዳቸው የሚወስዱት እርምጃዎች እነኚህን ይመስላሉ :-


1- ከቻሉ ማሰር፣ማሳሰር
2- ይህን ካልቻሉ መግደል
3-ይህን ካልቻሉ የነሱን አቋም እንድታራምድ ጫና ማሳደር ወይም አቋምኽን በነፃነት ከማንፀባረቅና ከማራመድ በመከልከል፣ስም በማጥፋት ከሀገር ማባረር ነው !


አይገርምኽም ውዱ ነብይ ይህን ሁሉ ፈተናና ችግር አልፈው ነው እስልምናን ያደረሱን !

የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው፣የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው፣ከሀገርም ተባረሩ ፤ አላሁ አክበር

አላህ እንዲህ ይላል :-

وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ ۚ وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ اللَّهُ ۖ وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ

እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም (ከመካ) ሊያወጡህ ባንተ ላይ ባሴሩብኽ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ያሴራሉም አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል፡፡ አላህም ከሴረኞች ሁሉ በላይ ነው፡፡


አላህ ካንተ ጋር ከሆነ ምን ትሆናለኽ !

https://www.tg-me.com/mewedachannel
ሰዎች አራተኛ የላላቸው ሶስት አይነት ናቸው :-

የመጀመሪያዎቹ :-

አላህ ወደርሱ ባማረ መልኩ ያለምንም ፈተናና ችግር የሚመልሳቸው ናቸው ፣አምልኮን የሚወዱ፣ወንልጀል ሲሰሩ የሚደነግጡ ፣ ደግሞም ቶሎ ብለው ከወንጀላቸው የሚመለሱ፣ልባቸው ንፁህ ፣የሚራሩ፣ከምቀኝነት የጠሩ ፣ለሰው መልካም አሳቢዎች ፣አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩ ፣በእርሱ ላይ ቅንጣት ይኽል አንድንም የማያጋሩ ናቸው። ለአላህም የቀረቡ ምርጦቹ እነኚህ ናቸው ።

አላህ ከእነርሱ ያድርገን

ሁለተኞቹ :-

አላህ ወደርሱ የሚመልሳቸው ናቸው ፤ነገር መቼ ነው ? ከፈተና በኃላ ነው ። ወይ በበሽታ፣ወይ በችግር ወይም ደግሞ ህይወታቸው እንዲበለሻሽ በማድረግ ይፈትናቸዋል ።

ልክ አላህ በቁርአኑ እንደነገረን :-

ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ)፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡

ሶስተኛው አይነቶቹ ደግሞ

አላህ እርሱን ማምለካቸውን የጠላባቸው ናቸው ፣ልቦናቸውን የዘጋባቸው ናቸው፣ ለሰላት ያልተገራ ኾኖ ታገኘዋለኽ፤ሰላቱን የተወ፣ምላሱ ባለጌ፣የሰውን ሐቅ የሚያግበሰብስ ፣በአላህ ላይ የሚያጋራ ሙሽሪክ ሆኖ ታገኘዋለኽ ።

ይኽ አይነቱን ነው አላህ እንዲህ ያለው :-

ۚ وَمَن يُرِدِ اللَّهُ فِتْنَتَهُ فَلَن تَمْلِكَ لَهُ مِنَ اللَّهِ شَيْئًا ۚ

አላህም መፈተኑን የሚሻበትን ሰው ለእርሱ ከአላህ (ለመከላከል) ምንንም አትችልም ፡፡

ወንድም እህቶቼ ቆም ብለን ልናስተውል ይገባናል እኛ ከየትኞቹ ነን ? ከመጀመሪያዎቹ ከኾንን አላህን እናመስግን፣ በዛው ላይም እንፅና፤ከሁለተኞቹ ከኾንን ደግሞ ወደ አላህ ለመቅረብ እንሞክር፤ከሶስተኞቹ ከኾንን ግን ጊዜው እንዳያመልጠን እንጠንቀቅ !!!

https://www.tg-me.com/mewedachannel
አንድ ሰው ወደ አላህ ከሚሰራው ወንጀል ተውበት አድርጎ በንሰሓ ሲመለስ ፤ ሶስት ትልልቅ ፀጋዎችን ያገኛል ።

1) አላህ ከነበረበት ወንጀል ተውበት እንዲያደርግ ጊዜ መስጠቱና ይህን እድል ለርሱ ማመቻቸቱ በራሱ አንድ ፀጋ ነው።
አስበኸዋል ወንጀል እየሰራ በዚህ ሁኔታኽ ሞተ ቢሆን ኖሮ ምን ሊከሰት እንደሚችል ፤ አላህ ይጠብቀን ።

ሁለተኛው ፀጋ
2) አላህ ይህ ሰው የሰራውን ወንጀል በሙሉ ሰብስቦለት ሁሉንም ወደ መልካም ስራነት ይቀይርለታል ፤አላሁ አክበር ፣ወንጀሉ መማሩ ብቻ ትልቅ ፀጋ ነበር ፤ የሚገርመው ግን፣ ቀድሞ የሰራውን ሁሉንም ወንጀል ወደ መልካም ስራነት መቀየሩ ነው ። ምንኛ ቸር ነኽ ጌታዬ !

አላህ እንዲህ ይላል ;-

إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

እስኪ አስተውል ስንት ወንጀል ሰርተኻል ፣ያ ሁላ ወንጀል ነው እንግዲህ ወደ መልካም ስራነት የሚቀየረው ።

ትልቁ ፀጋ ደግሞ፣እየሰማከኝ ነው አይደል ትልቁ ፀጋ ደግሞ ሶስተኛው ነው :-

3) አላህ ባሮቹ ከወንጀላቸው ተፀፅተው ወደርሱ በንሰሓ በመመለሳቸው ምክንያት ይደሰታል ፤ይደሰታልኮ ነው የምልኽ፣በኛ መስተካከል አላህ ይደሰታል፣ሲገርም ፣እኛ ተስተካከልን አላህን የምንጠቅመው ነገር የለም፣ወደጥፋት ብናመራም ምንም አንጎዳውም፣ እርሱ የተብቃቃና ሀብታም ነውና ። ነገር ግን በኛ መስተካከል ፣ወደርሱ በንሰሓ መመለሳችን ያስደስተዋል ። ቸር ነው አላልኩኽም ጌታዬ ለዛኮ ነው !!!


አላህ ሆይ ማረን !


https://www.tg-me.com/mewedachannel
ይህች ዓለም አንድ ቀን ከደስታዋም ከሃዘኗም ጋር ያበቃላታል!

እድሜያችንም ረዘመም አጠረም አንድ ቀን ይቆማል !

ሁሉም ሰው ጌታውን ይገናኛል !

فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡


وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ

የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

በቻልከው አቅም ጥሩ ሰው ኹን ፣ጥሩ ሰው መሆን ካልቻልክ ቢያንስ መጥፎ ሰው አትሁን ፣ በቻልከው አቅም ጥሩ ተናገር ፣ጥሩ ተናጋሪ መሆን ባትችል ፣ቢያንስ መጥፎ አትናገር ።

እወቅ ....ነገ ገንዘብኽ፣ንብረትኽ፣የምትመካባቸው ዘመድ አዝማዶችኸ አይጠቅሙኽም ፤የሚጠቅምኽ ምን እንደሆነ ታውቃለኽ ? ይኸውልህ ከአላህ እዝነት በኃላ ከሽርክ፣ከኒፈቅ፣ከፀያፍና ከመጥፎ ነገሮች ርቀኽ አላህን በብቸኝነት ማምለክኽ ፤ ተውሒድኽን አስተካክለኽ ወደ አላህ በንጹህ ልብ መምጣትኽ ብቻ ነው !

﴿يَومَ لا يَنفَعُ مالٌ وَلا بَنونَ﴾﴿إِلّا مَن أَتَى اللَّهَ بِقَلبٍ سَليمٍ﴾

ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡
ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»

አሁን ካለኽበት ችግር እንድትወጣ ትልቅ መፍትሔ ልጠቁምኽ ':-
አላህ አንዲህ ይላል :-

سَابِقُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا كَعَرْضِ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ أُعِدَّتْ لِلَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ ۚ ذَٰلِكَ فَضْلُ اللَّهِ يُؤْتِيهِ مَن يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ

ከጌታችሁ ወደ ኾነች ምሕረት፣ ወርዷ እንደ ሰማይና ምድር ወርድ ወደ ሆነችም ገነት ተሽቀዳደሙ፡፡ ለእነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ ላመኑት ተዘጋጅታለች፡፡ ይህ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡

https://www.tg-me.com/mewedachannel
📚 4 ባህሪያቶች ያሟሉ ሰዎች ከአላህ
የሆነ ብስራት አላቸውና አበስራቸው !

አላህ እርሱን በማምለክና ትዕዛዙን በመፈፀም ላይ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራንና፤ እነዚህን አራት ባህሪያቶች ያሟሉ ሰዎች የታደሉና ከአላህ የሆነ ብስራት የተሰጣቸው ናቸው፤በተቃራኒው እነዚህን አራት ባህሪያቶች ያላሟሉ ሰዎች እድለ ቢስና ክስረት ውስጥ ናቸው ።

1ኛ - አላህ ሲወሳ በአላህ ፍራቻና ትልቅነት የተነሳ ልባቸው የሚርድ፣የሚሸበር፣ትዕዛዙን የሚፈፅሙ ፣የከለከላቸውን በሙሉ የሚከለከሉ ናቸው ።

2ኛ- ፈተና ሲደርስባቸው የእርሱን ፊት ፈልገው፣የሚያገኙትን አጅር ሒሳብ ሰርተው ፣ትዕግስት የሚያደርጉ ፤በትንሽ በትልቁ ተስፋ የማይቆርጥ ናቸው ።

3ኛ- ሰላትን መስፈርቶቹን በሙሉ አሟልተው ፣ አርካኑን፣ ዋጂባቱን ጠብቀው ፣በተለምዶ ሳይሆን በሸሪዓዊ ስርዓት ወቅቱን ጠብቀው የሚሰግዱ ናቸው ።

4ኛ- አላህ ከሰጣቸው ፀጋ የሚመፀውቱ፤ ግዴታ የሆነባቸውን እንደ ዘካ፣ከፋራ፣በስሮቻቸው የሚተዳደሩ ለሆኑ ቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው የሚለግሱና ፤ ግዴታ ያልሆነ ተወዳጅ የሆኑ ማንኛውንም አይነት ሰደቃዎችን የሚለግሱ ናቸው ።

አላህ እንዲህ ይላል :-
وَبَشِّرِ المُخبِتينَ

« ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡»


الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَالصَّابِرِينَ عَلَىٰ مَا أَصَابَهُمْ وَالْمُقِيمِي الصَّلَاةِ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

«እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን፣ በደረሰባቸውም (መከራ) ላይ ታጋሾችን፣ ሶላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱትን (አብስር)፡፡»

💎 አላህ ሁላችንንም ለሚወደው ንግግርና ተግባር ይምራን !


https://www.tg-me.com/mewedachannel
Audio
🎙 ኡስታዝ ማህሙድ ሀሰን

" نعمتان مغبون فيهما كثير من الناس"

1-መጀመሪያ እራስህን አድን

2- ከአላህ ጋር ታረቅ ከዛ ...

https://www.tg-me.com/mewedachannel
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📜 እሷን መውደድኽ ጀነት አስገባህ

https://www.tg-me.com/mewedachannel
Audio
በኡስታዝ ማሙድ ሀሰን

  
🟦 የሴቶች አደባባይ መውጣት

ከእኛ አብሮ የተፈጠረ ስሜት

     🎤የሸህዋ ጣጣ
"

https://www.tg-me.com/mewedachannel
ስድስቱ የተውበት መስፈርቶች
~
በህይወታችን ብዙ ጊዜ ወንጀሎችን እንፈፅማለን። አላህ ያደለው በወንጀሉ አላህ ፊት እንዳይጠየቅ ተውበት ማድረግን ያስባል። ግን ስንቱ ነው ተውበቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ እንዲሆን የሚጨነቀው? እራሳችንን በሚገባ ጠይቀን እናውቃለን?! ለመሆኑ መስፈርቶቹን ምን ያህሎቻችን በሚገባ እንለያቸዋለን? ለማያውቁ ጥቆማ፣ ለሚያውቁ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እጠቅሳለሁ። የተውበት መስፈርቶች ስድስት ናቸው።

እነሱም:–

① ኢኽላስ: – አላህን ብቻ በማሰብ መፈፀም ማለት ነው። አንድ ሰው ወንጀልን የሚተወው ዱንያዊ ጥቅሞችን አስቦ ከሆነ የመጀመሪያውን የተውበት መስፈርት ዘንግቷል።

② ወንጀሉን ማቆም:– አንድ ሰው የሚፈፅመውን ወንጀል ባላቋረጠበት ሁኔታ "ቶብቻለሁ" ቢል ቀልድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ተውበት ያሰበ ሰው ጥፋቱን በቀጠሮ ሳይሆን ቀጥታ ሊያቆም ይገባል።

③ ወደ ጥፋቱ ዳግም ላይመለሱ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ። አንድ ሰው ከወር ቡ በኋላ እንደሚመለስ እያሰበ ረመዳን ሊገባ ሲል አንድን ወንጀል ቢተው መስፈርት ስላላሟላ ተውበት አድርጓል ማለት አይቻልም።

④ በወንጀሉ መፀፀት፦ ሰውየው ሲፈፅመው በቆየው ወንጀል ላይ ደንታ ቢስ ከሆነ ተውበቱ የሐቂቃ አይደለም። ፀፀቱ "ሰው ምን ይለኛል" ወይም "ክብሬ ጎደፈ" በሚል ሳይሆን የጌታውን ህግ በመጣሱ ሊሆን ይገባል። ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዝሙት ፈፅመው ጌታቸው ዘንድ ካለው ሂሳብ ይልቅ ዱንያ ላይ ያለው የሰው ወሬ ሲያስጨንቃቸው ይፀፀታሉ። እንዲህ አይነት ፀፀት የተውበትን መስፈርት አያሟላም። ይልቅ ከዛሬው የበዛ ህዝብ ፊት ነገ በአኺራ መዋረድ ከመምጣቱ በፊት ትክክለኛውን ፀፀት እዚሁ ልናስገኝ ይገባል።

⑤ ተውበቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆን። ይህም ሞት አፋፍ ላይ ከመድረሱ በፊት እና ፀሀይ በመጥለቂያዋ ከመውጣቷ በፊት መሆኑ ነው።
⑥ ወንጀሉ የሰው ሐቅ መግፋት ከሆነ ሐቁን ሊመልስ ወይም ይቅርታውን ሊያገኝ ይገባል። ያን ማድረግ ካልቻለ ዱዓእ ሊያደርግለት እንዲሁም ኢስቲግፋርና ኸይር ስራ ሊያበዛ ይገባል።
=

Ibnu .Munewor
Audio
ተቅዋን እንዴት እናሳካ

በኡስታዝ ማሕሙድ ሐሰን

   ሰው የሚከብደው :-

1,ግቡን ማስቀመጥ
  2,ግቡን ለማሳካት የሚለፋው ነገር
 

https://www.tg-me.com/mewedachannel
Forwarded from መወዳ ቻናል(MEWEDA CHANNEL) (Abu Shewkani)
1⃣ አስሩ የረመዳን የመጨረሻ ቀናቶች

🔶 በነዚህ አስር ቀናቶች
اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عنا" የሚለውን ዱዓ ማብዛት ይገባናል ።

🔶 ለይለቱል ቀድር ለ84 አመታት ከሚሰራ መልካም ስራ የበለጠ ደረጃ አለው። አስቡት አንዲት ሌሊት ከ84 አመታት በላይ
!

T.me/MewedaChannel
ـ💡💡
ـ💡
📌 ለይለተል-ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ?

እናታችን ዓኢሻ -ረዲየ አላሁ ዓንሀ- እንዲህ ብለዋል:–

☀️ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለይለተል-ቀድርን ባገኝ (ያቺ ለሊት ለይለተል-ቀድር መሆኖን ባውቅ) ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? ብዬ ጠየቅኳቸው።


እሳቸውም:– اللهم إنك عفو تحب العفو فعفوا عنا.
« አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሂቡ አል-ዓፍው ፈዕፉ ዓኒ »

👉( አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ) በይ አሉኝ።

(ቲርሚዚይ፣ኢብኑ ማጃህ፣ ኢማሙ አህመድ እና ሃኪም ዘግበውታል)

#Learnmore
የቴሌግራም አድራሻችን👇
Http://www.tg-me.com/Abdhik

💡
💡💡
እንኳን ለ1445 አ.ሂ ዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒዱኩም ሙባረክ ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሃል አዕማል!!

عيدكم مبارك.
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال.


https://www.tg-me.com/Tarefi1443
💎የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል

"አላህ ይህን ሙስሊም ማህበረሰብ የሚረዳው በደካሞች ዱዓ እና በቅንነታቸው ነው።"

👉አልባኒ ሰሒህ ብለውታል

📚አነሳኢይ በቁጥር (3178) ዘግበውታል

https://www.tg-me.com/mewedachannel
روائع_الفجر_ما_تيسر_من_الفرقان_عبد_الرشيد_صوفي_Sh_Abd_Al_rashid.mp4
79.8 MB
☀️ ጣፋጭ ቂራኣ

📌 ቃሪእ :—አብዱረሺድ ዓሊ ሱፊ

💎 ሱረቱል ፋርቃን

📖✏️📜
.
•┈┈• ❀ 🍃🌸🍃 ❀ •┈┈•

መወዳ

http://www.tg-me.com/AbdHik
🔶 ማንኛዉም ህዝብ በመሰረታዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ካልተስማሙ በቅርንጫፋዊ ጉዳዮቻቸው ላይ አይስማሙም ። ህዝበ ሙስሊሙ በተዉሒድ ላይ ካልተሰባሰ በኢስላማዊ ማንነት ስም የሚደረጉ ቲርኪሚርኪ መፈክሮች አንድ አያደርጋቸዉም።

فوائد الطريفي

Http://www.tg-me.com/mewedachannel
🗞 የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

"ፀሀይ ከወጣችበት እለት ሁሉ
በላጩ የጁምዓ ቀን ነው።"

📚 ሙስሊም ሰሒሕ ብለውታል

Http://www.tg-me.com/mewedachannel
Forwarded from خالد الراشد
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/06/13 08:02:31
Back to Top
HTML Embed Code: