Telegram Web Link
የዓሹራ ጾም ትሩፋት | በኡስታዝ ቶፊቅ ባህሩ
የዓሹራ_ጾም_ትሩፋት_በኡስታዝ_ቶፊቅ_ባህሩ_Minber_TV.pdf
1.9 MB
ዐሹራ የሙሐረም ወር ዐስረኛው ቀን ነው። የዐሹራን ቀን መጾም ተወዳጅ ነው። በርካታ ትሩፋቶች እንዳሉት በሐዲሶች ተዘግቧል። ነገር ግን በተጨማሪነት ዘጠነኛውን ቀን ወይም/እና ዐስራ አንደኛውን ቀን ጨምሮ መጾምም ተወዳጅ ነው።

ይህንን በተመለከተ በሶሒሕ ሐዲሶች የተገኙትን ተከታዮቹ ዘገባዎች እንመልከት። በመልካም ኒያ እንጹም። ቤተሰቦቻችንንም እንቀስቅስ!

ከዐብዱላህ ኢብኑ አቢ የዚድ እንደተዘገበው፡-
"ኢብኑ ዐባስ ስለ ዐሹራ ጾም ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ ሰምተዋቸዋል፡- "እንደዚህ ቀን የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከሌሎች ቀናት አስበልጠው፣ ትሩፋቱን ከጅለው ሲጾሙት የማውቀው ቀን የለም። ከዚህ ወር (ከረመዳን) በላይ ከወራት መካከል አስበልጠውት የጾሙት ቀንም አላውቅም።"
በሌላ ዘገባ ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡-
"የዓሹራ ጾም ያለፈውን ዓመት ኃጢኣት ያሰርዛል ብዬ ከአላህ እከጅላለሁ።"
ሙስሊም ዘግበውታል።

ከዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው፡-
"የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መዲና ሲገቡ አይሁዶች የዓሹራን ቀን ሲጾሙ ተመለከቱና "ለምንድን ነው የምትጾሙት?" በማለት ጠየቁ። "ይህ መልካም ቀን ነው። አላህ ሙሳን (ዐ.ሰ) እና የእስራኤል ልጆችን ከጠላቶቻቸው ያዳነበት ቀን ነው። ሙሳ (ዐ.ሰ) ጾመውታል።" አሉ። የአላህ መልእክተኛ ዓሹራን ጾሙ። ሌሎች ሰዎች እንዲጾሙም አዘዙ።"
ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
"እስከመጪው ዓመት ከቆየሁ ዘጠነኛውን ቀንም እጾማለሁ።" በሌላ ዘገባ፡-
"የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የዓሹራን ቀን ሲጾሙ እና እንዲጾም ሲያዙ ሰዎች መመሳሰል አይሆንብንም?" አሏቸው። እርሳቸውም፡- "አላህ ከሻ በመጪው ዓመት ዘጠነኛውን ቀንም እንጾማለን።" አሉ። ነገርግን መጪው ዓመት ሳይደርሱ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አረፉ።"
ሙስሊም ዘግበውታል።

9️⃣ ኛው - ዕለተ አርብ - ሰኔ 27 - 2017
🔟 ኛው - ዕለተ ቅዳሜ - ሰኔ 28 - 2017


ከዓመት አመት ያድርሰን!

ይህን ጽሑፍ ለማንበብ እና ለማተም በሚመች መልኩ የቀረበ ሲሆን በቴሌግራም ገጻችን አሊያም በድረገጻችን የመጣጥፍ ክፍል ያገኙታል።

ድረገጽ ፡ 🔗 https://minbertv.com/?p=8390 🔗

መልካም ንባብ! መልካም ዒባዳ!

#ዓሹራ #የሱና_ጾም #Ashura #ሙሐረም

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
አዋሽ ባንክ በዓመቱ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ በእጥፍ ማደጉን አስታወቀ

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://www.tg-me.com/minberkheber/1334
ሕይወት በፈተናዎች የተሞላች ብትሆንም፤ እያንዳንዳችን በውስጣችን የማይታጠፍ የአሸናፊነት መንፈስ አለ። አሹራ ይህን ውስጣዊ ጥንካሬ የምናስታውስበት፣ ከጨለማ በኋላ ብርሃን፣ ከመከራ በኋላ ደግሞ እውነተኛ ድል እንደሚመጣ የምንዘክርበት ዕለት ነው። ይህ ቀን መልካምነት ክፋትን እንደሚያሸንፍ፣ እውነት በሃሰት ላይ እንደሚነግሥና፤ በደል የቱንም ያህል ቢገዝፍ በፍትሕ ድል እንደሚነሳ የምናረጋግጥበትም ታላቅ ዕለት ነው።
ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን፤ ከፈተና በላይ የመሆንን ትርጉም በተጨባጭ ስለሚያስተምረን አሹራ ያሰናዳነው ልዩ ዝግጅት ዛሬ ምሽት ከ02:00 ሰዓት ጀምሮ ይቀርብላችኋል።

#አሹራ
ከትግል እስከ ድል...

ዕለተ ረቡዕ ሰኔ 25 -2017 | ሙሃረም 7 -1447

★ ★ ★
Minber TV | Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ተጨማሪ መረጃ፡ በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95 በመቶ ገደማ የተቀመጠውን የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸው ተገልጿል። የመዲናዋ ትምህርት ቢሮ ያስቀመጠው ዝቅተኛ ማለፊያ 50 በመቶ ነው።

ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጡ አማራጮችን በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል። (ሚንበር ቲቪ)

LINK፡ https://aa6.ministry.et/#/result
Telegram bot፡ @emacs_ministry_result_qmt_bot

★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ፕላስቲክ ሳይ ሰብስብ ሰብስብ ይለኛል!”

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/ToonMcef2iU 🔗

#ቲጃራ_ፖድካስት #ንግድ #business
#ፕላስቲክ #plastic #repurpose

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
#ፓርላማ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 26/2017 በፓርላማ ቀርበው ከአባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://www.tg-me.com/minberkheber/1336
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሂጅራ አቆጣጠር እንዴት ተጀመረ?

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/lSp6QLsgTwU 🔗

#ጥያቄ_አለኝ #አዲሱ_የሂጅራ_ዘመን #1447ኛው_ዓመተ_ሂጅራ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
#ሚንበር_ቲቪ_ከሥፍራው፡- የዘካ እና አውቃፍ ኮሚሽን ምሥረታ ኮንፍረንስ

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://www.tg-me.com/minberkheber/1338
ሐማስ በአሜሪካ ለተዘጋጀው የጋዛ ተኩስ አቁም ምክረ ሐሳብ በነገው እለት ምላሽ ሊያቀርብ ነው

ዝርዝሩን ያንብቡ፡- https://www.tg-me.com/minberkheber/1340
ዕውቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ሑሴን ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 26/2017 ወደ አኺራ መሻገራቸው ተሰምቷል።

ኢንና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!

ሚንበር ቲቪ ሸይኽ ሙሐመድ ሑሴን ኅልፈት የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ፣ እርሳቸውን አላህ (ሱ.ወ) ማረፊያቸውን ጀነት እንዲያደርግ፣ ለቤተሰብ እና ወዳጆች እንዲሁም ለመላው ሙስሊም ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል።

የፎቶ ምንጭ፡ አሕመድ ነጋ
★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
በሕዳሴ ግድብ ምርቃት እንዲሳተፉ ለግብፅ እና ሱዳን ግብዣ ቀረበ

ዝርዝሩን ያንብቡ፡- https://www.tg-me.com/minberkheber/1345
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኸሚስ_ምሽት በዚህ ሳምንት...
ዘወትር ሐሙስ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ!

★ ★ ★
Minber TV | Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
የተለያየ ዕውቀት የምንገበይባቸውን ኪታቦች መሠረት በማድረግ፤ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በየዕለቱ በሚቀርበው "ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራማችን፤ በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እየቀረበ የሚገኘውን "ረሒቀል መኽቱም" የሲራ ኪታብ ትንታኔና ትምህርት ዛሬ ምሽት ከ12:30 ጀምሮ እናቀርብላችኋለን።

#ሚንበሩል_ዒልም
#ረሒቀል_መኽቱም_ሲራ
#ክፍል_25
#ኡስታዝ_ካሚል_ሸምሱ

ዕለተ ሐሙስ ሰኔ 26 -2017 | ሙሃረም 8 -1446

★ ★ ★
Minber TV | Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
2025/07/06 18:36:14
Back to Top
HTML Embed Code: