Telegram Web Link
የተወደዳችሁ፣ በድጋሚ እንኳን ለዒድ አል አድሓ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። 🥳🎉

ሚንበር ቲቪ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚከናወነውን የዒድ ሰላት እንዲሁም ሙሉ የበዓል መርሐ ግብሩን በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች አማራጮች (ዩትዩብ፣ ፌስቡክ እና ቴሌግራም) በቀጥታ ለማስተላለፍ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ይገልጻል። በዓሉን በጋራ እናሳልፍ።🤗 🎊

ሚንበር ቲቪ - ሁለንተናዊ ከፍታ
😍145👍5
🔵🌙 ዒድ አል አድሓ ብሔራዊ በዓል ሆኖ ሲከበር ሐምሳ (50) ዓመት ደፈነ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዛሬ በመላው ሀገሪቱ በአደባባይ የሚያከብሩት ዒድ አል አድሓ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በታኅሣሥ 1967 ነበር።

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://www.tg-me.com/minberkheber/1163
12👍2
Live stream started
በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚከናወነው የዒድ ሰላት ላይ ለመሣተፍ ምዕመናን ከተለያዩ የከተማው ክፍሎች እየተጓዙ በሥፍራው ደርሰዋል።

ሚንበር ቲቪ በስታዲየም የሚከናወነውን የዒድ ሰላት እንዲሁም ሙሉ የበዓል መርሐ ግብሩን በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች አማራጮች (ዩትዩብ፣ ፌስቡክ እና ቴሌግራም) በቀጥታ እያስተላለፈ ይገኛል። ይቀላቀሉን። በዓሉን በጋራ እናሳልፍ።🤗 🎊
15👍4😢4
በአሁኑ ሰዓት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀ በኋላ በአንዋር መስጅድ ኢማም ሸይኽ ጠሃ ሐሩን አማካይነት ኹጥባ ተደርጎ በይፋ ተጠናቋል።
👍41😍1
የፎቶ ዘገባ፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም በአዲስ አበባ ስታዲየም
15
Live stream finished (2 hours)
2025/07/13 18:18:24
Back to Top
HTML Embed Code: