200 ገደማ የመብት ተሟጋቾች ፍልስጤምን ደግፈው በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ሠልፍ ከወጡ ተማሪዎች ጎን ቆሙ

ዕለተ ማክሰኞ ሚያዝያ 22 - 2016 | ሸዋል 21 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ እየፈጸመች የምትገኘውን ጥቃት በመቃወም በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የሚካሄደው ሠልፍ ወደ 200 በሚጠጉ በሀገሪቱ በሚንቀሳቀሱ የመብት ተሟጋቾች ድጋፍ አገኘ፡፡ በዩኒቨርሲቲዎቹ የተካሄዱት ሠልፎች አሜሪካ ለእስራኤል የምትሰጠውን ድጋፍ ጭምር የሚቃወሙ ናቸው፡፡

ፍልስጤምን ደግፈው በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ሠልፍ የወጡ ተማሪዎች በኮሎምቢያ፣ ዬል፣ ቴክሳስ እና ሌሎችም የትምህርት ተቋማት ማሰማት የጀመሩት የተቃውሞ ድምጽ አሁንም ድረስ ቀጥሏል፡፡ ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲዎች ቅጽር ግቢ ውስጥ አነስተኛ ድንኳኖችን በመትከል እዚያው ውለው በማደር ለፍልስጤማዊያን ድጋፋቸውን ሲገልጹ ታይተዋል፡፡

ፖሊስ በዩኒቨርሲዎቹ የተካሄዱትን ሠልፎች ለመበተን ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ተማሪዎቹ ሠልፉን ቀጥለው በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ተማሪዎች መኖራቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡ ከዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዳንዶቹም በሠልፉ ላይ የተሳተፉ ተማሪዎቻቸውን ማገዳቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡

በአሜሪካ የሚገኙ የመብት ተሟጋቾች ከተማሪዎቹ ጎን የመቆማቸው ዜና የመጣው ፖሊስ እየወሰደ በሚገኘው እርምጃ ተማሪዎቹን ማሰሩ ከተሰማ በኋላ ነው፡፡ 193 የመብት ተሟጋቾቹ በጋራ ባወጡት የአቋም መግለጫ፣ ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሠልፍ እያካሄዱ የሚገኙት ‹‹የመቃወም መብታቸውን ተጠቅመው›› መሆኑን በመግለጽ ይህ መብት ሀገሪቱ በደነገገቻቸው ሕጎች የተቀመጠ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በቀጠለው ሠላማዊ ሠልፍ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ቢታሰሩም ተቃውሞው ወደ አውሮፓ ተዛምቶ በፈረንሳይ ተካሄዷል፡፡ በእነዚህ ሠልፎች ላይ በተለይ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጡ ተጠይቀዋል፡፡

እስራኤል ባለፉት ወራት በጋዛ በፍልስጤማዊያን ላይ እየፈጸመች በምትገኘው ጥቃት ቢያንስ 34 ሺሕ ንጹሐን ተገድለዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል 13 ሺሕ 800 የሚሆኑት ሕጻናት ናቸው፡፡

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
በሁለንተናዊ የእውቀት ሓሰሳ ነፍስም ኣቅላቸውም ኣላረፈም። መለኮታዊ ህልውናን ከመጠርጠር ጀምሮ በልባቸው መንገድ ተራምደው ኢኣማኒያንን በኣመክንዮ እስከመርታት በርትተዋል!

ዛሬ ምሽት ከ1፡45 ይጠብቁን!

#እነሆ_ኸበር
#የማያርፈው_ማሳኝ

ዕለተ ማክሰኞ ሚያዝያ 22 - 2016 | ሸዋል 21 – 1445
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
ሐማስ እና ፈትህ በቻይና አደራዳሪነት ውይይት ጀመሩ
ሐማስ እና ፋትህ በቻይና አደራዳሪነት ውይይት ጀመሩ

ዕለተ ማክሰኞ ሚያዝያ 22 - 2016 | ሸዋል 21 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

ያለፉትን ዓመታት በተቀናቃኝነት የቆዩት የፍልስጤሞቹ የፖለቲካ ኃሎሎች ሐማስ እና ፋታህ በቻይና አደራዳሪነት ንግግር መጀመራቸውን የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቡድኖቹ መሪዎች በአካል ተገናኝተው መወያየታቸውን ትናንት ሰኞ ገልጧል፡፡

ሐማስ እና ፋታህ በተለይ ባለፉት ዓመታት በተቀናቃኝት ቆይተው ከጥቅምት ወር አንስቶ እስራኤል በጋዛ የጀመረችው ዳግም ጥቃት ለንግግር በር ከፍቶላቸዋል፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ሊን ጂያን እንደገለጹት፣ የሁለቱ ቡድኖች መሪዎች ባካሄዱት ውይይት በመሃላቸው ያለውን ልዩነት በንግግር ለመፍታት ፍቃደኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሁለቱ ቡድኖች ተወካዮች በቻይና አደራዳሪነት ንግግር ማካሄዳቸው ቢገለጽም የት እንደተገናኙ የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

በቻይና አደራዳሪነት ንግግር መጀመራቸው የተገለጸው ሐማስ እና ፋታህ፣ በተያዘው ዓመት መጀመሪያ በተመሳሳይ የጋራ መንግሥት ስለማቋቋም በሩስያ መዲና ሞስኮ መክረው ነበር፡፡ የአሁኑን ድርድር የመራችው ቻይና በቀጣይም የቡድኖቹን ልዩነት በንግግር ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝት ገልጻለች፡፡

ከሰሞኑ የተካሄደውን ድርድር የመራችው ቻይና የፍልስጤም ችግር የሚፈታው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገርነት ዕውቅና ስታገኝ ነው የሚል አቋም በማራመድ ትተወቃለች፡፡ ሀገሪቱ እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመው ጥቃት እንዲቆም የተኩስ አቁም እንዲደረግ ስትወተውት የቆየች ነች፡፡

ሐማስ እና ፋታህ በፍልስጤም ምድር ተጽዕኗቸው የጎላ የፖለቲካ ኃይሎች ናቸው፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በእስራኤል ሀገርነት ላይ የተለያየ አቋም በማራመድ ይታወቃሉ፡፡

ከቡድኖቹ ውስጥ ሐማስ ለእስራኤል ዕውቅና የማይሰጥ ሲሆን፣ ፋታህ በበኩሉ ዕውቅና ይሰጣል፡፡ ቡድኖቹ የፍልስጤም እና እስራኤል ልዩነት በሚፈታበት የትግል ስልት ላይ እንዲሁ ልዩነት አላቸው፡፡

በድረ ገጻችን ተጨማሪ ያንብቡ ፡ https://minbertv.com/?p=7928

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
የመጅሊስን ፕሬዝዳንት ጨምሮ ዕውቅ የእስልምና መምህራን በ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ ላይ ተሳተፊ ሆኑ

ዕለተ ረቡዕ ሚያዝያ 23 - 2016 | ሸዋል 22 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ዕውቅ የእስልምና ሃይማኖት መምህራን “ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” በተሰኘ ንቅናቄ ላይ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ተሳታፊ ሆነዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ የተደረገው ይህ ንቅናቄ፣ የማኅበረሰቡን የጽዳት ባህል ክብርን የጠበቀ ለማድረግ የተወጠነ ነው። ፅዱ ኢትዮጵያ በሚል ተነሣሽነት ስር የታቀፈው ይህ ንቅናቄ መጸዳጃ ቤቶችን ዘመናዊ በሆነ መልኩ መገንባትን አካቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው እሑድ ሚያዝያ 20/2016 ላስጀመሩት ንቅናቄ ገንዘብ ማሰባሰቢያ የባንክ አካውንት ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ድጋፎቹ ቀጥለዋል።

ንቅናቄውን ከተቀላቀሉት የመጅሊስ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም በተጨማሪ ዕውቅ የእስልምና መምህራን ተሳትፈዋል። ከእነዚህ መካከል ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፣ ኡስታዝ በድሩ ሑሴን እና ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ተጠቃሽ ናቸው።

በዚህ ንቅናቄ ላይ ሚኒስትሮች፣ ከንቲባዎች፣ ርእሳነ መስተዳድሮች፣ ባለሐብቶች እንዲሁም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
ልዩ “ኸበር” - የፍልስጤማዊያንን የነጻነት ትግል የሚተርክ የልጆች የስዕል መጽሐፍ ተዘጋጀ

ደቡብ አፍሪካዊው የጥበብ ሰው ናቲ ንጉባኔ ከሰሞኑ ለልጆች ያዘጋጀው የስዕል መጽሐፍ የተለየ ትኩረት ስቧል። ናቲ ባዘጋጀው የስዕል መጽሐፍ የፍልስጤማዊያን የነጻነት ትግል ለታዳጊዎች በሚሆን መልኩ ተተርኳል። ናቲ ለመጽሐፍ ርእስ አድርጎ የመረጠው በፍልስጤም የነጻነት ትግል ውስጥ በተለይ በ1960ዎቹ ዝነኛ የነበረውን መፈክር “ፍሮም ዘ ሪቨር ቱ ዘ ሲ” ነው። ይህ መፈክር በዮርዳኖስ ወንዝ እና በሜዲትራንያን ባህር መካከል የሚገኘውን የፍልስጤም መሬት ለመግለጽ የሚውል ነው። ይህ መሬት ዛሬ በእስራኤል በወረራ የተያዘውን ግዛት ያካትታል።

በናቲ ንጉባኔ የልጆች የስዕል መጽሐፍ ውስጥ ፍልስጤማዊያን በነጻነት ትግል ውስጥ የሚያሳዩት አይበገሬነት እና የትግሉ መዳረሻ ተንፀባርቋል።

ስለ አዲሱ ሥራው የተናገረው ናቲ፣ መጽሐፉን ያዘጋጀሁት ደቡብ አፍሪካዊያንን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕፃናት ስለ ፍልስጤም ታሪክ እና ስለ ፍልስጤማዊያን ሕዝቦች ባህል እንዲያውቁ በማለም ነው ብሏል። ከመጽሐፉ ጋር አያይዞ በአሁኑ ወቅት እስራኤል በጋዛ እየፈፀመች ስለምትገኘው ጥቃት ያነሳው ናቲ፣ የስዕል መጽሐፉ በታዳጊዎች አዕምሮ ውስጥ “ከፍልስጤማዊያን ጎን የመቆም አስፈላጊነት እንዲጎለብት” ያግዛል የሚል እምነት እንዳለው መግለጹን አል ቀለም የተሰኘ የሀገሪቱ ጋዜጣ አስነብቧል።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
#የህይወት_ገጽ

በልጅነት የተጫረ ዒልም - ክፍል 2

ዑስታዝ ጠልሃ ልጅነቱን በዳእዋ ሕይወት ያሳለፈ፣ በአንዋር መስጅድ የሴቶች መድረሳ፣ ለወጣቶች ቂርአት ትልቅ አስተዋጽኦ የነበረው ወንድም ነው። በሕይወት አጋጣሚ ከኢትዮጵያ በመውጣት ኑሮውን በአውስትራሊያ አድርጓል። ከወር በፊት ኢትዮጵያ በመጣበት አጋጣሚ አግኝተን የሕይወት ጉዞውን ቃኝተናል። በዛሬው የሕይወት ገጽ ፕሮግራማችን ክፍል 2ን ይዘን እንቀርባለን።

ምሽት 3:00 ጠብቁን።
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በጽናት መቆየት - ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በጁምዓ ኹጥባ ካስተላለፉት
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፋይደን ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት እስራኤል የዘር ማጥፋት ፈጽማለች በሚል ያቀረበችውን ክስ እንደምትቀላቀል ገለጹ፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ፡-
https://minbertv.com/?p=7951

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
ዛሬ ምሽት በተወዳጁ ኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን፤ ሸይኻችን የሰው ልጅ ከአላህ መንገድ ለመራቁ እንደ ምክንያት የሚያቀርባቸውን ተጨባጭ ያልኾኑ ምክንያቶች እያነሱና ከቀደምት ነቢያት የሕይወት መንገድ ጋር እያናጸሩ የሚነግሩን አላቸው። እግረመንገድም የጨዋነትን ትርጉም እያጋሩን ያመሻሉ።
በመዲና ሰማይ ሥር ቆይታችን ወደ ሐረር ለሥራ ባቀናንበት ካገኘናቸው ተወዳጅ ሸይኽ ጋር (በተጣበበ ጊዜም ቢኾን) አድርገነው የነበረውን ምጥን ቆይታ እናቀርብላችኋለን።

ምሽት ከ2:30 ጀምሮ!

ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 24 - 2016 | ሸዋል 23 – 1445 |  ሚንበር ትቪ

#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት_ነው!
★   ★   ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ  #ሁለንተናዊ_ከፍታ#Minber_TV
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መንግስት የወረሰብንን መሬት አላህ መስጂድ ሰራበት!
- የኡስታዝ ጦልሓ ትዝታዎች

#የሕይወት_ገጽ

★   ★   ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ  #ሁለንተናዊ_ከፍታ#Minber_TV
በአዲስ አበባ ከተማ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በ“ኦንላይን” ሊሰጥ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በ“ኦንላይን” ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ባለፉት ቀናት የፈተና ቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዷል፡፡

ትምህርት ቢሮ ቅድመ ዝግጅት እያካሄደ መሆኑ የተሰማው፣ የ2016 የ12 ክፍል ተማሪዎች መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ከተደረገ በኋላ ነው፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ፡- https://minbertv.com/?p=7967

★   ★   ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ  #ሁለንተናዊ_ከፍታ#Minber_TV
ለጋሱ እጅ በሞት ተይዞ ተሰበሰበ። መዲና ላይ ከየኣለማቱ የመጡ ሙዕሚኖች ከእጃቸው በልተዋል። ከመዳፋቸው ጠጥተዋል። የመዲናው የልግስና ምልክት!
ዛሬ ምሽት ከ2:00 ጀምሮ!

#እነሆ_ኸበር
#የመዲና_ውበት

★   ★   ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ  #ሁለንተናዊ_ከፍታ#Minber_TV
ጋዛን ደግፈው አደባባይ የወጡ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የሚደግፍ ሠልፍ በኢራቅ ተካሄደ

በኢራቅ መዲና በግዳድ ከተማ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ከሰሞኑ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋዛን በመደገፍ እየተከናወነ ለሚገኘው ሠልፍ አጋርነት ለማሳየት ዛሬ ሐሙስ አደባባይ ወጡ፡፡ በዚህ ሠልፍ ላይ ከተማሪዎች በተጨማሪ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ፡- https://minbertv.com/?p=7974

★   ★   ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ  #ሁለንተናዊ_ከፍታ#Minber_TV
ሂጅራ ባንክ ከኦል ፋውንዴሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

ሂጅራ ባንክ ከኦል ፋውንዴሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የተፈራረመው ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 24/2016 ነው። ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል የሆነው ኦል ፋውንዴሽን፤ ኦፐሬሽን 1000 በሚል ሥያሜ እድሜያቸው ከ18-30 ለሆኑ ወጣቶች ለሁለት ወር የሚቆይ የሥልጠና መርሐ ግብር በማዘጋጀት ይፋ አድርጓል።

ሂጅራ ባንክ ይህን ፕሮጀክት ለመደገፍ ግንባር ቀደም ባንክ በመሆን 100 ወጣቶችን በሃገሪቱ ባሉ ቅርንጫፎቹ ለማሰልጠን ፍቃደኛ መሆኑን አረጋግጧል።

በዛሬው እለት በተካሄደው የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ሁለቱም ወገኖች ለአላማው መሳካት ያላቸውን ቅን ፍላጎት አረጋግጠዋል። በዚህም መሰረት ተሳታፊዎች/ሰልጣኞች ወርሃዊ የመጓጓዣ አበል በባንኩ የሚከፈላቸው ሲሆን፣ ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላም ብቃታቸው ታይቶ ቋሚ የስራ እድል እንደሚመቻችላቸው ተገልጿል።

ዝርዝር መረጃውን እሁድ ምሽት 02:00 በሂጅራ ቢዝነስ ዝግጅታችን ይጠብቁን።

ተጨማሪ ያንብቡ https://minbertv.com/?p=7980

★   ★   ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ  #ሁለንተናዊ_ከፍታ#Minber_TV
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሁለተኛው ጠላታችን ...
- ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በጁምዓ ኹጥባ ካስተላለፉት

#የጁምዓ_ኹጥባ

★   ★   ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ  #ሁለንተናዊ_ከፍታ#Minber_TV
ፍልስጤማዊያን ጋዜጠኞች የዓመታዊው የዩኔስኮ ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

በጋዛ በንጹሐን ላይ የሚሰነዘረውን የእስራኤል ጥቃት ሲዘግቡ የነበሩ ፍልስጤማዊያን የዓመታዊው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሣይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይፋ የተደረገው ትናንት ሐሙስ ነው።

በሽልማት መርሐ ግብሩ ላይ እንደተገለጸው፣ የሽልማቱ አሸናፊዎች በጋዛ ሲሰነዘር የቆየውን መጠነ ሠፊ ጥቃት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ተከታትለው ሲዘግቡ የቆዩ ሁሉም ፍልስጤማዊያን ጋዜጠኞች ናቸው።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ፡- https://minbertv.com/?p=7988
#የጁምዓ_ኹጥባ
ከአዲሱ የሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ
በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ

ዛሬ ጁምዓ በአዲሱ የሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የቀረበውና፤ በዋናነት እንደ አንድ ሙስሊም አኽላቃችን ምን መምሰል እንዳለበት የሚያብራሩ ነጥቦች በስፋት የተወሱበትን መልዕክት ከሥፍራው ተገኝቶ በሚንበር ቲዩብ በቀጥታ ሲያስተላልፈው የቆየው ጣቢያችን፤ ከ10:30 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ የሚያቀርብላችሁ ይሆናል።


ዕለተ አርብ ሚያዝያ 25 - 2016 | ሸዋል 24 – 1445 | ሚንበር ትቪ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
በአፋር እና ኢሳ መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ለማጽናት ያግዛል የተባለ ውይይት ተካሄደ

ዕለተ አርብ ሚያዝያ 25 - 2016 | ሸዋል 24 – 1445 | ሚንበር


በአጎራባቾቹ አፋር እና ኢሳ መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማጽናት ያግዛል የተባለ ውይይት የተካሄደው በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ ጅግጅጋ ከተማ ነው።

የሀገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ከፍተኛ አመራሮች እና የሶማሌ ክልል ያካሄዱት ውይይት “ፍሬያማ” እንደነበር ተገልጿል።

በጅግጅጋ የተካሄደው ውይይት ከሁለት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ የተደረሰውን የአፋር እና ኢሳ የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ የተከናወነ ነው። በወቅቱ በተደረሰው ስምምነት ሂደቱ በመጅሊስ መሪነት እንደሚቀጥል ተጠቁሞ ነበር።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ፡- https://minbertv.com/?p=7994

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
2024/05/04 02:53:16
Back to Top
HTML Embed Code: