Telegram Web Link
ግዜያቶች ባለፉ ቁጥር አላህ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ያሳያሃል። ጥሩነትን እና መጥፎነትን፤ መራቅን እና መቅረብን፤ ህይወትን እና ሞትን ፤ ጥሬ መሆንን እና መብሰልን ፤ ብርድንን እና ሙቀትን ፤ ብቸኝነትን እና በሰዎች መከበብን ፤ ማግኘትን እና ማጣትን ፤ መጥገብንን እና መራብን እንዲሁም መደሰትን እና መጨነቅን... እነዚህ ሁሉ በዱንያ ህይወት ተሰጥቶት የኖረ ሰው ሁሉ የሚያልፍባቸው አላህ ባሮቹን በሱ ያመኑትን ሆነ ያላመኑትን የሚፈትንበት ሚዛኖቹ ናቸው። ዳሩ ግን ሁሉም ባሮቹ አንድ አለመሆናቸውን በነዚህ ፈተናዎች ወደው ሳይሆን በግዳቸው ማንነታተውን ይገልፁበታል። ያ ነው ያንተ ማንነት...ሙዕሚን ማለት ግን አላህ ባሮቹን ለመፈተን ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ቢፈጥርም አንተ ማንነት የሚረጋገጠው " አንድ ማንነት ብቻ ስትይዝ ነው!" ያኔ ብቻ ነው አላህ ዘንድ ሙዕሚን የሚባል ስም የሚኖርህ...ይህንን ማንነት ነብዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ሲገልፁልህ "ይገርማል በአላህ የሚያምን አማኝ, ነገረ-አለሙ ሁሉ ለዚህ አማኝ መልካም ነው!, ጥሩ ነገር ሲያገኝ አላህን ያመሰግናል ፣ በማመስገኑ ከአላህ መልካም ነገር ያገኛል፤ ነፍሱ ደስ የማያሰኘው ነገር ሲያገኘው ይታገሳል፣ በመታገሱ ከአላህ መልካም ያገኛል ይህ ግን ትክክለኛ በአላህ ላመነ ብቻ ነው!" ያሉት..
...ባህሪያቸው አንድ ከሆኑት ውስጥ ነህ ወይስ በነገሮች ሁሉ ባህሪያታቸው ከሚለዋወጥ...?

#islamindset #follow #like
🥰2👍1
2025/10/22 17:00:14
Back to Top
HTML Embed Code: