እጅህን አንስተህ የምትፈልገውን ጠይቀህ ምላሽ ካልሰጠህ፤ አልሰጠኝም ብለህ ከመበሳጨት ይልቅ, አላህ ሊሰጥህ የፈለገውን ለመቀበል መዘጋጀት ጀምር። ምክንያቱም አንተ ፈልገህ የጠየከውን ካልሰጠህ እሱ የፈለገው ይበልጣልና ..!
ISLAMINDSET.
ISLAMINDSET.
👍2
አሁን አሁን ላይ ሲታሰብ ምክንያታችን አፈንግጦ የወጣ ይመስላል። ወረርሽኝ ሲነሳ በዚህ ምክንያት ነው ብለን ትንታኔ ለመስጠት እንጂ ወደ አላህ ለመመለስ ስንጣደፍ አንታይም። ጦርነት መጣ ሲባል እንደለመደብን ለትንታኔ እንሯሯጣለን። የጎርፍ አደጋ ተነሳ ሲባል እንደለመደብን የለመደብንን እንጂ አላህ እያስጠነቀቀን እንደሆነ አናስተነትንም። ከዚህም ባስ ብሎ የእሳተ ጎመራ እና የመሬት መንቀጥቀጥን አብሮ አምጥቶብናል። እንደለመዱት ምክንያት ከሚተነትኑ ሳይሆኑ ካሉበት የወንጀል ጫካ ለመውጣት ለተውበት ከሚሯሯጡ ያድርገን🤲
ISLAMINDSET.
ISLAMINDSET.
👍5❤2👌2
አላህ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሊያረጋጋህ ሲፈልግ በዱንያ ላይ ችግሮችን በችግር ላይ ደራርቦ ይሰጥህና ምን እንደምታደርግ ይመለከተሃል። ያኔ አስተንታኝ ከሆንክ በትግዕስት ወደሱ መሸሽን ትመርጣለህ!..የዚህም ምሳሌው ወርቅ ወርቅነቱ ጥርት እንዲል ዘንድ በእሳት እንደሚቀልጠው እና ለብቻው ዋጋ እንዳለው እንደሚለየው ማለት ነው!
ISLAMINDSET.
ISLAMINDSET.
❤4
አላህን ሳንጠይቀው ብዙ ነገር ሰጥቶናል። እንዲሁም በህይወት ስንኖር ጥቂት ነገሮችን እንድንፈፅም ግዴታ አድርጎብናል። ግዴታዎቻችንን በአላህ ፍቃድ ከተወጣናቸው ቀን በቀን እናመስግን። አሁን ካለንበት ደረጃ በላይ እንዲሰጠን ከፈለግን, ግዴታ ካደረገብን ነገሮች በተጨማሪ ወደን እና ፈቅደን ኢባዳ እናድርግ። ..ነገር ግን ግዴታ ያደረገብንን አላህ በፈለገው መልኩ ሳንወጣ ትርፍ የምንጠይቅው ከሆነ ከውስጣችን ጋር ተጋጭተናል እና ራሳችንን እንመልከት፤ ግዴታ ያደረገብንን ሳንወጣ ተጨማሪ አልያም ትርፍ የሆነን ነገር አላህ እየሰጠን ከሆነ ትልቅ የሆነ ፈተና ውስጥ ሰለሆን ሳናባክን ለሚገባው የሚገባውን ነገር ብቻ እናድርግ። ወደ አላህም እንቃረብ🙏
ISLAMINDSET.
ISLAMINDSET.
👍5❤1
ሶሀቦች በጁሙዓ ቀን ሰለዋትን ማብዛት ይወዱ ነበር። ሰዎችንም እንዲያበዙ ያበረታቱ ነበር።እንዳውም
አብዱላህ ኢብን መስዑዱ (ረ.ዐ) እንደሚለውም :-
"አንተ ዘይድ ኢብን ወህብ ሆይ! የጁሙዓ ቀን ላይ አንድ ሺ ሶላት አለነቢ ማለትን አትዘንጋ!" ብሎ ጓደኛውን ያበረታታ ነበር።
✍️ ኢብነል ቀይም ረሂመሁላህ.
📕 ጀላኡል አፍሃም
ISLAMINDSET.
አብዱላህ ኢብን መስዑዱ (ረ.ዐ) እንደሚለውም :-
"አንተ ዘይድ ኢብን ወህብ ሆይ! የጁሙዓ ቀን ላይ አንድ ሺ ሶላት አለነቢ ማለትን አትዘንጋ!" ብሎ ጓደኛውን ያበረታታ ነበር።
✍️ ኢብነል ቀይም ረሂመሁላህ.
📕 ጀላኡል አፍሃም
ISLAMINDSET.
❤4👍1
ጤነኛ እና በአላህ ቀጥተኛው መንገድ ላይ ሆነህ ጁሙዓ ቀን ከደረስክ አላህ ከዚህ በላይ ጀነት እንድትገባ ምን አይነት እድል ይስጥህ!.. "እንዴት?" ካልክ, ሙሉ ኢባዳ እንዳይሰሩ በህመም ላይ ያሉ ብዙ ሰዎች አሉ, ላንተ ጤና ሰጠህ፤ ጤነኛ ሆነው ግን ደግሞ ኢባዳ መስራት ያልቻሉ ብዙ ሰዎች አሉ ቅኑን መንገድ ስላልተመሩ...አስተንትን! አላህ አዕምሮ የሰጠህ የሱን ፀጋ እንድታስተነትን ነው።
✍️عقلية الإسلام | .ISLAMINDSET
✍️عقلية الإسلام | .ISLAMINDSET
❤7👍1
በልዩ አቀራረብ ወደናንተ ቀርቧል።ከታሪኩ ተጠቃሚዎች ከሚሆኑት ያድርገን። ቪዲዮውን ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ።
https://youtu.be/5NAJf3pbfC8
https://youtu.be/5NAJf3pbfC8