Telegram Web Link
" እድለቢሱ ተመራቂ "


ይህ የእኛ የተለዬ ገጠመኝ ነው። የተስፋን ምንነት የምንረዳበት መጠበቅን የምንማርበት። ህልማችን በድንገት የፅሐይ ሙቀት እንደጠወለገች አበባ ሆኗል። ታሪካችን በውሃ እየጠጣች ከጠወለገች የፅጌሬዳ አበባ አይተናነስም። በቃ ማብቂያ የሌለው ታሪክ፡ ነገር ግን እየጨረስነው የሚመስለን የቅዠት አለም። ይህ ምን አይነት እድል ነው? ሰው እንዴት ለሁለተኛ አመት ጂሲ ይሆናል? 102 ቀን እየቀረን የዛሬ አመት በወረሃ መጋቢት 12 ጊቢያችንን በሚያሳዝን ሁኔታ ለቀን ወጣን። በወቅቱ ከተወሰኑ ጊዚያት በኋላ የምንመለስ ስለመሰለን ብዙም በመውጣታችን አልተገረምንም። ነገር ግን ከወጣን በኋላ በሽታው እንደ ቀትር ፅሀይ እየበረታ ሄደ። የእኛም መጠሪያ ቀን የውሃ ሽታ ሆነ። ከአሁን አሁን እንገባለን ብለን ብናስብም ነገር ግን ሁሉም ነገር እንደጠበቅነው ሳይሆን ቀረ።
ውድ አንባቢያን ይህ እንደፈልግን የማንፅፈው እንደፈለገ የሚፅፈን እንዳሻው የሚወስደን በበሽታና በጦርነት የታጀበው አለማችን ነው። ሰዎች ያሻቸውን ማለት ይችላሉ። ነገር ግን እኛ አምነን መቀበል ብቻ ነው ፀጋችን። በሁለት ቀን እየመከነ የሚሄደው የህልም ሩጫ የሚመስል አለማችንን ፀጥ ብለን ሲነግሩን እንሰማለን። ይህ ከእድሚያችን ላይ ቀንሰን የምናስቀምጠው ሌላው ውጣ ውረዳችን ነው። " ልጄ መቼ ነው የምትመረቀው? መቼ ነው መጥቼ የማስመርቅህ?" አለችኝ እናቴ ለአመታት ለእኔ ስትል ደፋ ቀና ያለ የደከመ ድምጿን ይበልጥ እያሰለለችው። ይህን ያለችኝ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲዎች ተመራቂ ተማሪዎችን የሚቀበሉበትን ቀን በማራዘማቸው ነው። እምባዬ መጣ? ተስፋ አለመቁረጧ ስሜታዊ አደረገኝ። ይህ ምርቃት ከእኔ በላይ ለእሷ ትልቅ ትርጉም እንዳለው አውቃለሁ። ቶሎ ተመርቄ ስራ ይዤ አግብቼ ወልጄ ልጆቼን እርጅና ሳይጫጫናት ማየት ትሻለች። ሌላኛው የእናቴ ህልም አስለቀሰኝ። " እማ በህመሜ ላይ ህመም አትጨምሪብኝ። ሁሉም ነገር በፈጣሪ ፈቃድ ነው የሚሆነው እንጂ እንደ እኔ ፈቃድ ቢሆንማ ይሄን ሁሉ ምን አስጠበቀኝ?" አልኳት። "እሺ ልጄ ግን በቶሎ ተመርቀህ ሞት ሳይቀድመኝ ተመርቀህ ስትደሰት ወግ ማዕረግህን ማየት ስለምፈልግ ነው። አትፍረድብኝ" አለች እምባ በተናነቀው ድምጿ " እሺ እናቴ አንቺ እንዲህ አትሁኝ። ሞትንስ ደግሞ ምን አመጣው? ገና ምን አይተሽ? ገና ብዙ አመት ትቆያለሽ። ብቻ ጠብቂ እኔ ልጅሽ በዚህ ሁሉ ፈተና አልፌ ምን እንደማሳይሽ"አልኳት ምን እንደማሳያት በውል ባላውቅም እንደው በድንገት አፌ ላይ በመጣ የወኔ ቃል" ይሁና ልጄ ብቻ አንተ ደህና ሁንልኝ እስኪ ደህና መሆንህስ አንድ ነገር አይደል" ብላ ቅር እንደተሰኘች ዝም ብላ ምላሼን ከጠበቀች በኋላ " በል ለማንኛውም የማይሆን ነገር ከሆነ ወደቤትህ ተመለስ " ብላኝ ንግግራችንን ጨረስን። ከእኔ አልፎ መመረቄን ለምትሻ እናቴ ሆዴ ተብሰከሰከ። ስንቱ ወላጅ ይሆን በልጆቹ አለመመረቅ ያዘነው።

አንዱ ወዳጄ ጋር ስናወራ " የአንዱ ልጅ ቤተሰብ እኮ ብር አንስጥም አሉት" አለኝ " ለምን?" ድንግጥ ብዬ ጠየኩት " እኔም እንዲህ እንዳንተ ድንግጥ ብዬ ነው የጠየኩት እና የመለሰልኝ መልስ የሚገርም ነበር ' ለአንተ ያዘጋጀነው በጀት ከነሱፍህ 2012 ሰኔ ላይ አልቋል' ነበር ያሉት " አለኝ ፈገግ እያለ እኔም የፈገግታውን ፅንፍ ለራሴ እያጋባሁ "ቤተሰቦቹ ግን የሌለ ከሀበሻ ሚሞች የበለጡ ቀልደኞች አይደሉ እንዴ"አልኩት " አይ አንተ ግን እውነታቸውን እኮ ነው። በእኛ እድለቢስነት ምክንያት ያልተመረቅን እንደሁ ዝንታለም ሊጠውሩን ነው እንዴ ታዲያ?" ብሎ ሀዘን በተሞላው ምናብ ጆሮውን ጣል አድርጎ የኋሊት ነጎደ። ይሄኔ እኔም በጭንቀትና በምን ይሆናል ጥያቄ መብሰልሰሌን ተያያዝኩት። ቀጣይስ ምን ይሆን የሚፈጠረው?

አወዛጋቢው የተመራቂ ተማሪ መጨረሻ በምን አይነት ድራማ ይጠናቀቅ ይሆን? ለሁለት አመት ጂሲ የሆነው ተማሪ ታሪክ የማይዘነጋው ገጠመኝ ዝንት አለም በህይወቱ ውስጥ እንደ ጥላ ከኋላ የሚከተለው ብራና ላይ የተከተበ እውነቱ ይህ ነው። በዝሆኖቹ ፀብ እየተረገጠ ያለው ውብ ጊዚያችን እየራቀ የሄደው የንጋት ወጋገናችን እየቀርብነው የሚርቀን የተስፋ ጀንበራችን ነው። ምንም ማድረግ አይቻልም። ማብቂያ የሌለው ቅዠት የሚመስል እውነት ነው። ከአድማስ ማዶ ሆና በውቂያኖስ ላይ ቀይ ቀለሟን ጣል አድርጋ በሰላም እግሮቿን ወደ ምዕራብ እንደምትተኛ ውብ የተፈጥሮ ፀሀይ በሀሴት የሚዘከር የሚደረስ ውብ ታሪክ አይደለም። በበሽታና በጦርነት የታጀበ መራራ እውነት እንጅ።" አሁን የምንማረው ጠፍቶናል። አስተማሪው ራሱ ምን እንደሚያስተምር የሚጠፋው ይመስለኛል። ወደ የት ማየት እንዳለባቸው ግራ የተጋቡ አይኖች፣ ምን መፃፍ እንዳለባቸው የተምታታባቸው ጣቶች፣ ምን ማሰብ እንዳለባቸው የተወዛገቡ አእምሮዎች፣ ወደየት መሄድ እንዳለባቸው የማያውቁ እግሮች፣ አሁንም በሌላ ትንሽየ የተስፋ ጭላንጭል ጊቢ ውስጥ የሚታዩ ተመራቂ ተማሪዎች ዝም ብለው ይመላለሳሉ። ማስክ ማድረግ ሳኒታይዘር መጠቀምም ሰልችቷቸዋል። ብቻ ልባቸው ላይ ባስቀሯት ትንሽ ተስፋ ብቻ ይወዛወዛሉ። የማህበራዊ ድረገፁ ቁርስ ምሳ ራት የሆኑት ተመራቂዎች በራሳቸው በተቀለደ ቀልድም ፈገግ እያሉ ቀልዱን በዚህ መልኩ ቢሆን እያሉ ይበልጥ እንዲቀለድባቸው እያስተካከሉ የተፃፈላቸውን ታሪክ ያነባሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ሱፋቸውን በጊዜ ለብሰው ፏ ብትን ብለው ይወጣሉ። በእርግጥ እኔም መቼም በጊዜዬ አላስመረቀኝ ብዬ ለልደትም ለሰርግም እየለበስኩት ነበር።አሁን ላይማ ሱፍ እንዴት እንደጠላሁ። የሆነ የሚያናድ ልብስ ነው። እሱን ስትለብስ ሌላ ሰው ነው የምትሆነው። አካሄድህ ሁሉ ሳይቀር ይቀየራል። ኤጭ ጭራሽ ጋወንማ ጠላቴ ሆኗል። ነገር ግን ያነን ጥቁር ጋወን በደንብ እለብሰዋለሁ። ለዛ የመከራ ጊዜ እስካሁን ላሳለፍኩበት የሀዘን ጊዜዬ ማስታዎሻ ይሆነኛል።በደንብ እለብሰዋለሁ ለዛውም ደርቤ ደራርቤ ሁለት አመት ጂሲ የሆንሁበትን ያህል ነው የምለብሰው። እስከዛ ቀን ግን በኮሶና በእሬት የተለወሰውን ቀኔን እየመረረኝም ቢሆን እየጠጣሁ እገፋዋለሁ።

የምረቃ ታሪካቸው በበሽታና በጦርነት መካከል እየተራዘመ ከተቸገሩት ተማሪዎች መካከል ነኝ! ስሜቱን አውቀዋለሁ፤ስቃዩ ይገባኛል፣ተስፋው ያባዝነኛል፣ ባዶ ነገዬ እያነሆለለኝ እንደ እብድ ብቻየን በየመንገዱ ህዳግ አወራለሁ። ትምህርት ጠፍቶብኛል። ገና እንደ አዲስ የምጀምር ነው የሚመስለኝ 17 አመት እንደተማርኩ እረስቸዋለሁ። በቃ ይህ የእኛ የማይነጥፋ የታሪክ አጋጣሚ ነው። ማንም ሊመኘው የማይፈልግ እኛም ሳንመኘው የደረስንበት የተለዬ ዕድል።

ሰርክ በሙዝና🍌 በአቡካዶ ከፈፍ የመፅፈው የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትዝታዎቼንና አንዳንድ ነገሮችን ከማስቀምጥበት መቶ ስታዎሻዬ የወሰድኩት 🍌

# አ.ም.ዩ
#አምባዬ ጌታነህ


------'-----------@mindset12
@MINDSET12
----------------------------
🔶️ስለ ስኬት የተነገሩ ምርጥ ምርጥ አባባሎች🔶️
1. 🌀ከሰነፍ ሽማግሌ ብልህ ወጣት፤ ከሰነፍ ረዳት ብልህ ጠላት ይባላል፡፡


************* @mindset12 *
2. 🌀ብልህ ሰው አጥፊ ሲፈረድበት አይቶ ይታረማል፤ ሰነፍ ግን የብልሁ ማስተማሪያ ይሆናል፡፡

********* @mindset12 ♡♡
🌀ከወደቀ በኋላ ከሚጠነቀቅ ይልቅ ከመውደቁ አስቀድሞ የሚጠነቀቅ ይበልጣል፡፡

🌀ችኮላ ሰውን ከታላቅ ጥፋትና ውድቀት ታደርሰዋለች፡፡

የቤትህ በራፍ ምንም እንኳ ከፍታው ሰባት ክንድ ቢሆንም ራስህን ዝቅ አድርገህ ብትገባበት ይሻልሃል፡፡

ከንቱ ውዳሴን የሚወድ ሰው ባላሰበው መንገድ እንደሚሄድ ያለ ነው፡፡

ዓለም ሦስት ናት አንድ ቀን ላንተ፤ አንድ ቀን ባንተ፤ አንድ ቀን ለሌላ ናትና ስለ እገሌ ብለህ መኖር የለብህም፡፡

የዚህ ዓለም ዘመኑ ሦስት ነው፤ ይኸውም ያለፈው ቀን፣ ያለው ቀን፣ የሚመጣው ቀን ነው፡፡ ያለፈው ቀን ተመልሶ አይመጣልህም፤ ያለህበት ቀን ላንተ ብሎ አይኖርም፤ የሚመጣውም ቀን ለማን እንደሚሆን አታውቅም፡፡

🌀ዘመንን የሚቃወም ሰው ራሱን ይጎዳል፤ እንደዚህ ያለው ሰው ዓይኑ እያየ ከጎርፍ ጋር የሚጋፋውን ይመስላል፡፡

🌀ዛሬ የምታደርገውን ለነገ አደርገዋለሁ አትበል፤ የነገውን ነገ ታደርገዋለህና፡፡

🌀ዓለምና ጣዕሟ እንዳያስትህ ተጠንቀቅ። ምክንያቱም እሷ ካንተ በፊት ለነበሩት አልኖረችላቸውም፤ ዛሬም ላንተ አትኖርልህም፤ ካንተ በኋላ ለሚመጡትም አትኖርላቸውምና፡፡

🌀ቤት ከመሥራትህ በፊት ደኅና ጎረቤት ፈልግ፤ መንገድም ከመሄድህ በፊት ደኅና ጓደኛን አግኝ፡፡

🌀ምርጫህ ሁሌም ከፍታ ቢሆንም ለምትፈልገው ነገር ስትል ግን ዝቅ ማለት ግድ ነው።


ምርጥ


ሼር @mindset12
@mindset12
Forwarded from Fertegnochu
Important Shortcut Keys System
CTRL+A. . . . . . . . . . . . . . . . . Select
CTRL+C. . . . . . . . . . . . . . . . . Copyae4
CTRL+X. . . . . . . . . . . . . . . . . Cutweeww3s33e
CTRL+V. . . . . . . . . . . . . . . . . Pastewess§d#ddr
CTRL+Z. . . . . . . . . . . . . . . . . Undo
CTRL+B. . . . . . . . . . . . . . . . . Bold23
CTRL+U. . . . . . . . . . . . . . . . . Underlinees
CTRL+I . . . . . . . . . . . . . . . . . Italiec
F1 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Help
F2 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Rename selectedes object
F3 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Find all files
F4 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Opens file list drop-down in dialogs
F5 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . W2 current window
F6 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Shifts focus in Windows Explorer
F10 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Activates menu beear options
ALT+TAB . . . . . . . . . . . . . . . . Cycles between open applications
ALT+F4 . . . . . . . . . . . . . . . . . Quit program, close current window
ALT+F6 . . . . . . . . . . . . . . . . . Switch between current program windowss§rrx
ALT+ENTER. . . . . . . . . . . . . . Opens properties dialogwrwss@a4a
ALT+SPACE . . . . . . . . . . . . . . System menu for current windower
ALT+¢ . . . . . . . . . . . . . . . . . . opens drop-down lists in dialog boxes
BACKSPACE . . . . . . . . . . . . . Switch to parent folder
CTRL+ESC . . . . . . . . . . . . . . Opens Start menu
CTRL+ALT+DEL . . . . . . . . . . Opens task manager, reboots the computer
CTRL+TAB . . . . . . . . . . . . . . Move through property tabs
CTRL+SHIFT+DRAG . . . . . . . Create shortcut (also right-click, drag)
CTRL+DRAG . . . . . . . . . . . . . Copy File
ESC . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Cancel last function
SHIFT . . . . . . . . . . . . . . . . . . Press/hold SHIFT, insert CD-ROM to bypass auto-play3e
SHIFT+DRAG . . . . . . . . . . . . Move file
SHIFT+F10. . . . . . . . . . . . . . . Opens 3context ew2 menu (same as right-jclick)
SHIFT+DELETE . . . . . . . . . . . Full wipe delete (bypasses Recycle Bin)
ALT+underlined letter . . . . Opens the corresponding menu
PC Keyboard Shortcuts
Document Cursor Controls
HOME . . . . . . . . . . . . . . to beginning of se2
ARROW KEYS . . . . . . . move focus in documents, dialogs, etc.
CTRL+ > . . . . . . . . . . . . next word
CTRL+SHIFT+ > . . . . . . selects word
Windows Explorer Tree Controle
Numeric Keypad * . . . Expand all under current selection
Numeric Keypad + . . . Expands current selection
Numeric Keypad – . . . Collapses current selection
¦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . Expand current selection or go to first child
‰ . . . . . . . . . . . . . . . . . . Collapse current selection or go to parent
Special Characters
‘ Opening single quote . . . alt 0145
’ Closing single quote . . . . alt 01463
“ Opening double quote . . . alt 0147
“ Closing double quote. . . . alt 0148
– En dash. . . . . . . . . . . . . . . alt 01503
— Em dash . . . . . . . . . . . . . . alt 0151
… Ellipsis. . . . . . . . . . . . . . . . alt 0133
• Bullet . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0149
® Registration Mark . . . . . . . alt 017422
© Copyright . . . . . . . . . . . . . alt 0169
Trademark . . . . . . . . . . . . alt 0153
° Degree symbol. . . . . . . . . alt 0176
¢ Cent sign . . . . . . . . . . . . . alt 0162
1⁄4 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0188
1⁄2 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0189
3⁄4 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0190

@fertegnochu @fertegnochu
@fertegnochu @fertegnochu
@fertegnochu @fertegnochu
@mindset12
----------




🤖🤖🤖
@mindset12

Join us
Work with us
**************************
Sra mefelegya weym mastawekiya meketetaya miyasertum sra kalot serategna mefelgya chanel entekumotalel


@Mindset12
********


@freelance_ethio
ⓈⒶ🇪🇹🇪🇹:
🔎 ቀልጣፋ እና ስኬታማ ከጎግል መረጃ የመፈለጊያ ስልቶች 🔍
~

የዘወትር የመረጃ መፈለጊያ የሆነው የጎግል ፍለጋችን ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ ስልቶችን ልንጠቁማችሁ ወደናል።

1⃣. ትክክለኛውን ቃል ለመፈለግ ቃሉን በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ማስገባት ለምሳሌ፡- “Android” በማለት ጎግል ብናደርግ ከዚሁ ጉዳይ ጋር ብቻ የተገናኙ መረጃዎችን በሰፊው እናገኛለን።

2⃣. ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ድረ ገጾች ለመፈለግ

በቅርጽም ሆነ በይዘት ተቀራራቢነት ያላቸውን ድረ ገጾች ለማግኘት ወይም እንደ እከሌ አይነቱን ድረ ገጽ ፈልግልኝ ለማለት related: የሚለውን አስቀድመን የድረ ገጹን አድራሻ እናስከትላለን፤

ለምሳሌ፡- ጎግልን related:amazon.com ብለን ብንጠይቀው ከአማዞን ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ድረ ገጾች ውጤት ይሰጠናል።

3⃣. ጎግል የምንፈልገውን ብቻ እንዲፈልግልን ደግሞ ከቃላቱ በፊት የሰረዝ ምልክትን መጠቀም አለብን።

ይህም በተለይ በርካታ ትርጉም ያላቸውን ነገሮች ስንፈልግ የማንፈልገውን ለይቶ በቀላሉ የምንፈልገውን ጉዳይ ማግኘት ያስችላል።

ለምሳሌ፡- terminator –movie ብለን ብንፈልግ የፍለጋ ውጤታችን ቴርሚኔተር ላይ ብቻ ያተኮረ እና ተርሚኔተር ስለተባለው ፊልም ፈጽሞ ያላካተተ ይሆናል።

4⃣. ድረ ገጾች ስለ አንድ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የሰሩትን በቀላሉ ለመፈለግ

አንድ ደረ ገጽ ስለሆነ ነገር ከዚህ በፊት የሰራቸውን ለመመልከት የምፈልገውን ቃል ከጻፍን በኃላ ክፍት ቦታ ሰጥተን site: ብለን በመጻፍ የምንጎበኘውን ድረ ገጽ አድራሻ በማስከተል መፈለግ፤

ለምሳሌ፡- barrack obama. Site: bbc.com ብለን ብንፈልግ ቢቢሲ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን በተመለከተ በድረ ገጹ ላይ ያወጣቸውን ዘገባዎች ለመመልከት እንችላለን።

5⃣. ትርጓሜዎችን ለመፈለግ

የፊደላትን ትርጓሜ ለማወቅ እና ተመሳሳይ ፍቺዎችን ለመፈለግ define: አስቀድመን ቃሉን መጻፍና መፈለግ የተሻለ ውጤት ያስገኝልናል።

ለምሳሌ፡- define:injera ብለን ጎግል ላይ ብንፈልግ ሰለ እንጀራ ዘርዘር ያለ መረጃ እና በተለያዩ ቋንቋዎች ያለውን ትርጓሜ በስፋት ማግኘት እንችላለን።

በዚህ መንገድ የአንዳንድ ቃላትን ሰያሜ መነሻ እና ትርጉም ለማግኘትም ቀላል ነው።

6⃣. የተለያዩ የፋይል አይነቶችን ለማሰስ

ጎግል የፒዲኤፍ አልያም ፓወር ፖይንት ውጤቶችን እንዲሰጠን ለመጠየቅ የሚከተለውን አማራጭ እንጠቀማለን።

ለምሳሌ፡- “Scientific Journalism” filetype:pdf

7⃣. አዲስ የሆኑ እና ትኩረት የሳቡ አለማቀፍ ጉዳዮችን ለማግኘት

ከምንፈልገው ርዕሰ ጉዳይ በፊት የሃሽታግ ምልክትን ማስቀደም፤ ለምሳሌ #action2017 ብለን በመፈለግ በርካታ መረጃዎችን ማግኘት ያስችላል።

8⃣. በጎግል ወደ ሌላ ቋንቋ ለመተርጎም

ጎግል ትራንዝሌት ቃላቶችን ብቻ ሳይሆን ዘርዘር ያሉ ጽሁፎችንም ለመተርጎም ያስችላል።

ለምሳሌ፡- hello የሚለውን ቃል ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ ለመተርጎም translate english to french hello በማለት ጎግል ላይ መፈለግ እንችላለን።

9⃣. የረሳናቸውን ፊደላት ለማስታወስ

ጎግል የዘነጋናቸውን ቃላት እንዲያስታውሰን ኤስትሪክስን (*) መጠቀም እንችላለን። ኤስትሪክስን መጠቀም በተለይ የረሳናቸውን የዘፈን ግጥሞች ለማስታወስ ይረዳል።

ለምሳሌ፡- “Come * right now * me” የሚለውም የዘፈን ግጥም ጉግል ብናደርግ “Come Together” የሚል ርዕስ ያለውን የቢትልስ ሙዚቃ ግጥም ውጤቶች ይሰጠናል።

🔟. የአየር ሁኔታ መረጃ ለማግኘት ደግሞ ዌዘር የሚለውን ቃል ከከተሞቹ አስቀድመን መፈለግ

^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
@mindeet12
@mindset12
👍1
@mindset12
********

Never lose.
Either WIN or LEARN


-NELSON MANDELA
□□□□□□□□□□□□□□□□□□□
good morning
@mindset12


u think big
u get big
መምህሩ "የባህር ዛፍ ፍሬ አወጣ እና ምን ይታያችዃል አላቸው" ተማሪዎቹን

ተማሪዎቹውም አንድ በአንድ የታያቸውን ተናገሩ።
የተወሰኑት ተማሪዎች "የሚታዬኝ ቁርፍድፍድ ያለ ቅር ፊት ነው" አሉ።

የተወሰኑት" በተቆራፈደው ቅር ፊት ውስጥ ትንንሽ ዘሮች ይታዩናል"አሉ።

የተቀሩት ደግሞ " የባህር ዛፍ ዘር በዘሩ ውስጥ ደግሞ ባህር ዛፍ> በባህር ዛፉ ውስጥ ደግሞ ደን ይታዬናል" አሉ።

እርስዎስ በባህር ዛፍ ፍሬ ውስጥ ምን ይታዬዎታል?

ዛፍ ውስጥ ደን ወይስ ቁርፉድፉድ ያለ ቅርፊት እና ዘር ምን ይታዬዎታል?

እንግዲህ ሰው የሚያዬው በሚያቀው ልክ ነው!

ስለሆነም ራእይ ያለው ኢንቨስተር ገንዘቡ በትንሿ ዘር ውስጥ ነገ ደን ሆና ማዬት መቻሉ ነው። አዎ ኢንቨስተር ብልሀተኛ ነው። ኢንቨስተር ለመሆን ትልቅ ሃብት ብቻ አያስፈልግም። ስለሆነም ገንዘብዎን ከ1ወደ ሁለት
ከ2ወደ 4 ወደ 8 ወደ
16 , 32, 64, 128, 256, 512, 1024, 2048, 4096, 16384 , 6,5536 , 262,144 , 1,048,576 እያለ እንዲቀጥል_....... ይፍቀዱለት ።
አዎ : በአንድ ብሯ ውስጥ ሚሊዮን ማዬት ፣በባህር ዛፍ ፍሬ ውስጥ ደን ማዬት ማለት ይሄ ነው። ካመንከው ታደርገዋለህ : ታገኘዋለህ!!

ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ከአምስት ከአስር ሃያ አመት ቡሃላ ኢንቨስትመንቶዎ በሚሊዮን በቢሊዮን ሲያፈራ ይመልከቱት።

ስለዚህ የዛሬው አንድ ብር ኢንቨስትመንት የነገው ሚሊዮን/ቢሊዮን ብር ምንጭ ነው።

@mindset12
@mindset12
@mindset12
^^^^^^^^^^^
2025/07/09 19:06:59
Back to Top
HTML Embed Code: