Telegram Web Link
Forwarded from mInd SET-ETH
Life is too short to be little. You must enlarge your imagination and then act on it.

@mindset12
Forwarded from mInd SET-ETH
MINDSET - ETH
ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ይህ ቻናል እንዴት ነገሮችን በመልካም ጎናቸው መተርጎም እንደምንችል እና ህይወታችንን እንዴት አቅልለን ስኬታማ እንደምናደርግ የምንማማርበት ነው @mindset12
@mondset12



😎😎😎😎😎😎😎😎😎😎
#GMETHiopia(good morning eth)🇪🇹
___________________________

in #GMETHiopia we poat ahort news and tips.
ዜና ማየት ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል!

23 ጥቅምት 2020

የፎቶው ባለመብት,GETTY IMAGES

እኛ ራሳችን ዜና አቅራቢ ሆነን ይህን ማለታችን ወለፈንዲ ሊሆን ይችላል። ትዝብት ላይ ሊጥለንም ይችላል። ያም ሆኖ ግን ነገሩ አሳሳቢ ነው።

ቀኑን ሙሉ የዜና ቆሎ መቆርጠም ቢቀርብንስ? ሌላው
 ግን ነገሩ አሳሳቢ ነው።

ቀኑን ሙሉ የዜና ቆሎ መቆርጠም ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል።

መረጃ ትንፋሽ አሳጣን እኮ፡፡ የመረጃ ሱናሚ ጠራርጎ ወሰደን እኮ…

በኮቪድ ዘመን ደግሞ ቤት ተዘግቶ መዋል የዜና ሸመታችንን ሰማይ አድርሶታል፡፡ በብዙ ዓለም ይህ ነገር እውነት ነው፡፡

እስኪ አስቡት…

እጃችሁ ላይ የቲቪ ትዕይንት መዘርዝር መዘወርያ አለ እንበል፡፡ ሪሞት!

ሌላኛው እጃችሁ ላይ ደግሞ ስልካችሁ ይኖራል፤ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በዚህ ዘመን ከስልካችን ከራቅን ጭንቅ ነው የሚሆንብን፡፡

ምናልባትም ይህን ጽሑፍ በስልካችሁ እያነበባችሁት ይሆናል፡፡

ከንባብ የሚያናጥቡ ተከታታይ መልእክቶች እየደረሷችሁም ይሆናል፡፡ በፌስቡክ…በቴሌግራም…በዋትስአፕ…በትዊተር…

በዚያ ላይ ‹ይቺን አንብባትማ በሞቴ!› የሚለው ሰው ብዛቱ…

"ጉርሻ ይመስል!"

ለምን እንደሆነ ባይታወቅም ሁሉም ሰው የያዘውን ንባብ እንኳ ሳይጨርስ የማጋራት ሱስ አለበት፡፡

አንዳንዱ አጭሬ የቧልት ቪዲዮ ዓይቶ፣ ስቆ እንኳ ሳይጨርስ አጋርቶ ይጨርሳል፡፡ ጊዜ የለም፡፡ የመረጃ ግሽበት አለ፡፡ ስለዚህ ወደሚቀጥለው፡፡ ሳቅን ለማጣጣም ቀርቶ ፈገግታን ለመጨረስ የሚሆን ጊዜ የለም፡፡

እጃችሁ ላይ የቲቪ 'ሪሞት' አለ ብለናል፡፡
ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ ሰበር ዜና እየላኩ የአእምሮ ጫና ይፈጥራሉ፡፡

ፈነዳ፣ አፈነዳ፣ ፈነዱ….ገደለ፣ ገደሉ…ተገደለ፣ አስገደለ፣ ሞቱ፣ ቆሰሉ…አቆሰለ…ቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቅብርጥሶ…

ሪሞቱን ይዛችሁታል ብለናል….፡፡ እንዳትለቁት፡፡

ዓለምን በቲቪ መስኮት እየሾፈራችኋት ነው፡፡ በቲቪ የትእይንቶች መዘርዝር ውስጥ 300 ቻናሎች አሉ፡፡ 300 ምርጫዎች አሏችሁ ማለት ነው፡፡

የትኛውን ማየት ይሻላል? ይህ የምርጫ መብዛት ራሱ ለአእምሮ ጤና መልካም አይደለም፡፡

ከቲቪ መዘርዝሩ ጎን የራዲዮ መዘርዝር አለ፡፡ ከሱ ጎን ላፕቶፕ አለ፡፡ ላፕቶፑ ውስጥ እልፍ ፊልሞች አሉበት፡፡

በዚህ ላይ ከጎረቤት የሆነ ራዲዮ ጣቢያው ላንቃው እስኪሰነጠቅ ይጮኻል፡፡ ከወዲያ በኩል ሼልፍ ላይ ያላነበቧችኋቸው መጻሕፍት እያዛጉ ነው፡፡

ዓለም ትጨንቃለች፡፡ መረጃ ይንዠቀዠቃል፡፡ ሰቆቃ…ዜና…ሰቆቃ…መረጃ…ገደሉ፣ ተገደለ፣ ቆሰሉ አቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቁልቋል….

በዚሁ ሁሉ መሀል ሌላ መልእክት ይመጣል፡፡ ከወዳጅ፣ ከቴሌ፣ ከቴሌግራም ጉጅሌ፣ ከፌስቡክ ክበብ…
Forwarded from Fertegnochu
.........እድሌ ነው አልልም ምክንያቱም እድል የሰው ልጅ እራሱን የሚያታልልበት ትልቅ ጥበብ ናትና።

@mindset12
Amazing‼️

_mindset
💡💡💡💡💡💡💡

የሆነ ጊዜ አንድ መምህር ተማሪዎቹን የሆነ ጥያቄ ጠየቃቸው
አንድ ተለቅ ያለ container ጠጠሮች አሸዋ ተለቅ ተለቅ የሚሉ ድንጋዮች አፈር እንዲሁም ውሃ ፊታቸው በማቅረብ እነዚህን ነግሮች ሁሉንም እዚህ container ውስጥ ማስቀመጥ ወይም መጨመር ቢኖርባቹ በምን አይነት ቅደም ተከተል ታስገቡታላቹ ብሎ ጠየቃቸው
አብዛኞቹ እጃቸውን በማውጣት የተለያየ መልስ ሰጡ ....
እዚህ ጋር ቆም ብለው እርሶም ይህን ጥያቄ ራሶን ቢጠይቁ እወዳለሁ
ወደ ሀሳቤ ስመለስ መምህሩ የተማሪዎቹን መልስ ካዳመጠ በኋላ ሁሉንም በማመስገን የራሱን ወይም ትክክለኛውን ምላሽ እንዲህ በማለት ነገራቸው
በ መጀመሪያ ተለቅ ተለቅ ያሉትን ድንጋዮች እናስቀድማለን በድንጋዮቹ መሀል ክፍት ቦታዎች ስለምናገኝ ጠጠሮቹን እናስቀጥላለን አሁንም የሚቀረን ሌላ ክፍት ቦታ ስለሚኖረን አሸዋውን እንጨምራለን በጣም ጥቃቅን የሆኑ ቦታዎች ስለሚተርፉን አፈሩን እናስቀጥላለን በመጨረሻም በሚኖረን ቦታ ውሃውን እንጨምራለን።

ይህ container እንደተሰጣቹ ህይወት አርጋቹ ውሰዱት ሌሎቹን ደሞ በህይወታቹ ማድረግ ወይም ማሳካት የምትፈልጓቸው ነገሮች። ልክ container ውስጥ ሁሉንም የተሰጡንን ነገሮች ለማስገባት በተጠቀምነው ብልሀት ባዘለ ቅደም ተከተል መሰረት በህይወታችን ለምናደርጋቸው ነገሮችም ቅደም ተከተል መስጠት እና በሰጠነው ቅደም ተከተል መልኩ ነገሮችን ማስኬድ መቻል ይኖርብናል።

እስኪ ያ ሰው container ውስጥ ቅድሚያ ተለቅ ተለቅ የሚለውን ድንጋይ ማስገባቱን ትቶ ውሃውን ቢያስገባ ወይም ጠጠሮቹን ወይም አሸዋውን ውይም አፈሩን ቢያስገባ...? ሁሉንም የማካተቻ ቦታ የሚያገኝ ይመስላችኋል? በፍፁም!!!

እኛም በህይወታችን እየተቸገርን ያለነው ወይም ምንም የማድረግ ችሎታውም ሆነ ጊዜውም የለንም ብለን እያሰብን ያለነው ለነገሮች የምንሰጣቸው ቅደም ተከተል አለመጣጣም ነው ኮንቴነራችንን ቀድመን በውሃ እንሞላው እና አስፈላጊ ወይም ወሳኝ ለሆነው ትልቅ ነገር ቦታ እናጣለን ።

እናም ልብ እንበል ነገሮችን በቅደም ተከተል እናስቀምጥ ምንጊዜም ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገር ቅድሚያ እንስጥ።

ያማረ እና ውብ የሆነ ህይወትን እመኝላቹሃለው
አመሰግናልው❤️❤️❤️🙏🙏🙏

@mindset12
" እድለቢሱ ተመራቂ "


ይህ የእኛ የተለዬ ገጠመኝ ነው። የተስፋን ምንነት የምንረዳበት መጠበቅን የምንማርበት። ህልማችን በድንገት የፅሐይ ሙቀት እንደጠወለገች አበባ ሆኗል። ታሪካችን በውሃ እየጠጣች ከጠወለገች የፅጌሬዳ አበባ አይተናነስም። በቃ ማብቂያ የሌለው ታሪክ፡ ነገር ግን እየጨረስነው የሚመስለን የቅዠት አለም። ይህ ምን አይነት እድል ነው? ሰው እንዴት ለሁለተኛ አመት ጂሲ ይሆናል? 102 ቀን እየቀረን የዛሬ አመት በወረሃ መጋቢት 12 ጊቢያችንን በሚያሳዝን ሁኔታ ለቀን ወጣን። በወቅቱ ከተወሰኑ ጊዚያት በኋላ የምንመለስ ስለመሰለን ብዙም በመውጣታችን አልተገረምንም። ነገር ግን ከወጣን በኋላ በሽታው እንደ ቀትር ፅሀይ እየበረታ ሄደ። የእኛም መጠሪያ ቀን የውሃ ሽታ ሆነ። ከአሁን አሁን እንገባለን ብለን ብናስብም ነገር ግን ሁሉም ነገር እንደጠበቅነው ሳይሆን ቀረ።
ውድ አንባቢያን ይህ እንደፈልግን የማንፅፈው እንደፈለገ የሚፅፈን እንዳሻው የሚወስደን በበሽታና በጦርነት የታጀበው አለማችን ነው። ሰዎች ያሻቸውን ማለት ይችላሉ። ነገር ግን እኛ አምነን መቀበል ብቻ ነው ፀጋችን። በሁለት ቀን እየመከነ የሚሄደው የህልም ሩጫ የሚመስል አለማችንን ፀጥ ብለን ሲነግሩን እንሰማለን። ይህ ከእድሚያችን ላይ ቀንሰን የምናስቀምጠው ሌላው ውጣ ውረዳችን ነው። " ልጄ መቼ ነው የምትመረቀው? መቼ ነው መጥቼ የማስመርቅህ?" አለችኝ እናቴ ለአመታት ለእኔ ስትል ደፋ ቀና ያለ የደከመ ድምጿን ይበልጥ እያሰለለችው። ይህን ያለችኝ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲዎች ተመራቂ ተማሪዎችን የሚቀበሉበትን ቀን በማራዘማቸው ነው። እምባዬ መጣ? ተስፋ አለመቁረጧ ስሜታዊ አደረገኝ። ይህ ምርቃት ከእኔ በላይ ለእሷ ትልቅ ትርጉም እንዳለው አውቃለሁ። ቶሎ ተመርቄ ስራ ይዤ አግብቼ ወልጄ ልጆቼን እርጅና ሳይጫጫናት ማየት ትሻለች። ሌላኛው የእናቴ ህልም አስለቀሰኝ። " እማ በህመሜ ላይ ህመም አትጨምሪብኝ። ሁሉም ነገር በፈጣሪ ፈቃድ ነው የሚሆነው እንጂ እንደ እኔ ፈቃድ ቢሆንማ ይሄን ሁሉ ምን አስጠበቀኝ?" አልኳት። "እሺ ልጄ ግን በቶሎ ተመርቀህ ሞት ሳይቀድመኝ ተመርቀህ ስትደሰት ወግ ማዕረግህን ማየት ስለምፈልግ ነው። አትፍረድብኝ" አለች እምባ በተናነቀው ድምጿ " እሺ እናቴ አንቺ እንዲህ አትሁኝ። ሞትንስ ደግሞ ምን አመጣው? ገና ምን አይተሽ? ገና ብዙ አመት ትቆያለሽ። ብቻ ጠብቂ እኔ ልጅሽ በዚህ ሁሉ ፈተና አልፌ ምን እንደማሳይሽ"አልኳት ምን እንደማሳያት በውል ባላውቅም እንደው በድንገት አፌ ላይ በመጣ የወኔ ቃል" ይሁና ልጄ ብቻ አንተ ደህና ሁንልኝ እስኪ ደህና መሆንህስ አንድ ነገር አይደል" ብላ ቅር እንደተሰኘች ዝም ብላ ምላሼን ከጠበቀች በኋላ " በል ለማንኛውም የማይሆን ነገር ከሆነ ወደቤትህ ተመለስ " ብላኝ ንግግራችንን ጨረስን። ከእኔ አልፎ መመረቄን ለምትሻ እናቴ ሆዴ ተብሰከሰከ። ስንቱ ወላጅ ይሆን በልጆቹ አለመመረቅ ያዘነው።

አንዱ ወዳጄ ጋር ስናወራ " የአንዱ ልጅ ቤተሰብ እኮ ብር አንስጥም አሉት" አለኝ " ለምን?" ድንግጥ ብዬ ጠየኩት " እኔም እንዲህ እንዳንተ ድንግጥ ብዬ ነው የጠየኩት እና የመለሰልኝ መልስ የሚገርም ነበር ' ለአንተ ያዘጋጀነው በጀት ከነሱፍህ 2012 ሰኔ ላይ አልቋል' ነበር ያሉት " አለኝ ፈገግ እያለ እኔም የፈገግታውን ፅንፍ ለራሴ እያጋባሁ "ቤተሰቦቹ ግን የሌለ ከሀበሻ ሚሞች የበለጡ ቀልደኞች አይደሉ እንዴ"አልኩት " አይ አንተ ግን እውነታቸውን እኮ ነው። በእኛ እድለቢስነት ምክንያት ያልተመረቅን እንደሁ ዝንታለም ሊጠውሩን ነው እንዴ ታዲያ?" ብሎ ሀዘን በተሞላው ምናብ ጆሮውን ጣል አድርጎ የኋሊት ነጎደ። ይሄኔ እኔም በጭንቀትና በምን ይሆናል ጥያቄ መብሰልሰሌን ተያያዝኩት። ቀጣይስ ምን ይሆን የሚፈጠረው?

አወዛጋቢው የተመራቂ ተማሪ መጨረሻ በምን አይነት ድራማ ይጠናቀቅ ይሆን? ለሁለት አመት ጂሲ የሆነው ተማሪ ታሪክ የማይዘነጋው ገጠመኝ ዝንት አለም በህይወቱ ውስጥ እንደ ጥላ ከኋላ የሚከተለው ብራና ላይ የተከተበ እውነቱ ይህ ነው። በዝሆኖቹ ፀብ እየተረገጠ ያለው ውብ ጊዚያችን እየራቀ የሄደው የንጋት ወጋገናችን እየቀርብነው የሚርቀን የተስፋ ጀንበራችን ነው። ምንም ማድረግ አይቻልም። ማብቂያ የሌለው ቅዠት የሚመስል እውነት ነው። ከአድማስ ማዶ ሆና በውቂያኖስ ላይ ቀይ ቀለሟን ጣል አድርጋ በሰላም እግሮቿን ወደ ምዕራብ እንደምትተኛ ውብ የተፈጥሮ ፀሀይ በሀሴት የሚዘከር የሚደረስ ውብ ታሪክ አይደለም። በበሽታና በጦርነት የታጀበ መራራ እውነት እንጅ።" አሁን የምንማረው ጠፍቶናል። አስተማሪው ራሱ ምን እንደሚያስተምር የሚጠፋው ይመስለኛል። ወደ የት ማየት እንዳለባቸው ግራ የተጋቡ አይኖች፣ ምን መፃፍ እንዳለባቸው የተምታታባቸው ጣቶች፣ ምን ማሰብ እንዳለባቸው የተወዛገቡ አእምሮዎች፣ ወደየት መሄድ እንዳለባቸው የማያውቁ እግሮች፣ አሁንም በሌላ ትንሽየ የተስፋ ጭላንጭል ጊቢ ውስጥ የሚታዩ ተመራቂ ተማሪዎች ዝም ብለው ይመላለሳሉ። ማስክ ማድረግ ሳኒታይዘር መጠቀምም ሰልችቷቸዋል። ብቻ ልባቸው ላይ ባስቀሯት ትንሽ ተስፋ ብቻ ይወዛወዛሉ። የማህበራዊ ድረገፁ ቁርስ ምሳ ራት የሆኑት ተመራቂዎች በራሳቸው በተቀለደ ቀልድም ፈገግ እያሉ ቀልዱን በዚህ መልኩ ቢሆን እያሉ ይበልጥ እንዲቀለድባቸው እያስተካከሉ የተፃፈላቸውን ታሪክ ያነባሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ሱፋቸውን በጊዜ ለብሰው ፏ ብትን ብለው ይወጣሉ። በእርግጥ እኔም መቼም በጊዜዬ አላስመረቀኝ ብዬ ለልደትም ለሰርግም እየለበስኩት ነበር።አሁን ላይማ ሱፍ እንዴት እንደጠላሁ። የሆነ የሚያናድ ልብስ ነው። እሱን ስትለብስ ሌላ ሰው ነው የምትሆነው። አካሄድህ ሁሉ ሳይቀር ይቀየራል። ኤጭ ጭራሽ ጋወንማ ጠላቴ ሆኗል። ነገር ግን ያነን ጥቁር ጋወን በደንብ እለብሰዋለሁ። ለዛ የመከራ ጊዜ እስካሁን ላሳለፍኩበት የሀዘን ጊዜዬ ማስታዎሻ ይሆነኛል።በደንብ እለብሰዋለሁ ለዛውም ደርቤ ደራርቤ ሁለት አመት ጂሲ የሆንሁበትን ያህል ነው የምለብሰው። እስከዛ ቀን ግን በኮሶና በእሬት የተለወሰውን ቀኔን እየመረረኝም ቢሆን እየጠጣሁ እገፋዋለሁ።

የምረቃ ታሪካቸው በበሽታና በጦርነት መካከል እየተራዘመ ከተቸገሩት ተማሪዎች መካከል ነኝ! ስሜቱን አውቀዋለሁ፤ስቃዩ ይገባኛል፣ተስፋው ያባዝነኛል፣ ባዶ ነገዬ እያነሆለለኝ እንደ እብድ ብቻየን በየመንገዱ ህዳግ አወራለሁ። ትምህርት ጠፍቶብኛል። ገና እንደ አዲስ የምጀምር ነው የሚመስለኝ 17 አመት እንደተማርኩ እረስቸዋለሁ። በቃ ይህ የእኛ የማይነጥፋ የታሪክ አጋጣሚ ነው። ማንም ሊመኘው የማይፈልግ እኛም ሳንመኘው የደረስንበት የተለዬ ዕድል።

ሰርክ በሙዝና🍌 በአቡካዶ ከፈፍ የመፅፈው የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትዝታዎቼንና አንዳንድ ነገሮችን ከማስቀምጥበት መቶ ስታዎሻዬ የወሰድኩት 🍌

# አ.ም.ዩ
#አምባዬ ጌታነህ


------'-----------@mindset12
2025/07/13 18:19:38
Back to Top
HTML Embed Code: