Telegram Web Link
EBS MUSIKA
🎤 🎶 EBS MUSIKA1 ⓚⓑ

➊ ከ ሰኞ ➽ እሁድ አማርኛ ሙዚቃዋች ብቻ በKb ተዘጋጅተው የሚለቀቁበት ቻናል ከፈለጉ ትክክለኛ ቻናል ነው ያላቹት 😊 👍
➋ ቻናላችን ላይ በአነስተኛ ብር(package)ዘፈንያገኛሉ cross @adoniking53
https://www.tg-me.com/ghost_note
Mindset_ETH
----------------
@MINDSET12
@MINDSET12
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ዛሬ በጣም ጠቃሚ የሆኑ 12 ቦቶች አቅርበንላቹሃል። ይጠቀሙባቸው👇👇

♐️ @ChatIncognitoBot -ይሄን ቦት ተጠቅማቹ Randomly ቻት ማድረግ ትችላላቹ። አዲስ ጓደኛ ታገኙበታላቹ😜

♐️ @UnitConversionBot - ይህን ቦት ተጠቅማቹ ማንኛውንም የልኬት አሀድ መቀየር ትችላላቹ

♐️ @iFlipTextBot - የፈለጋቹትን text ስትልኩለት ከታች ወደ ላይ ይገለብጠዋል።

♐️ @liverobot - premier leauge እና laliga የጨዋታ መርሃ ግብር ለማየት ይጠቅማቹሃል።

♐️ @GeezNumberBot - ማንኛውንም ቁጥር ወደ ግዕዝ ቁጥር ለመቀየር ከፈለጉ።

♐️ @FBvidzBot - ከፌስቡክ ላይ ቪድዮ ማውርድ ከፈለጋቹ ይህን ቦት ተጠቀሙ።ከናንተ ሚጠበቀው የቪዲዮውን ሊንክ ለቦቱ መላክ ብቻ ነው።

♐️ @MyAndroidNewsBot - ስለ አንድሮይድ ስልክዎ አዳዲስ እና ትኩስ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ይህን ቦት ምርጫዎ ያድርጉ።

♐️ @MyGenderBot - ይሄ ቦት ስምን በመጠቀም ጾታን ለመለየት ያገለግላል።

♐️ @joinhider_bot - ሰው ወደ ግሩፓቹ ሲገባ የጆይን ሚሴጅ እንዳይገባ ከፈለጉ ይህን ቦት ይጠቀሙ።

♐️ @RemoveHiBot - ግሩፓቹ ላይ Hi/Hello የመሳሰሉ ሚሴጆችን እንዳይላኩ ከፈለጋቹ ለዚህ ቦት አድሚን ስጡት👍

♐️ @Anonymous_telegram_bot - ማንነታቹ ሳይታወቅ ግሩፕ ላይ ማውራት/መሳደብ😡 እንዲሁም ፎቶ መላክ ትችላላቹ።


@mindset12
የቻይና ቁጥር አንድ ባለሀብትና 231 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተው አሊባባ ግሩፕ መስራች jack ma አለም ላይ ካሉ ጥቂት ገራሚ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ከመሬት ተነስቶ ሰማይ ጠቀስ የቴክኖሎጂ ድርጅት መስርቷል፡፡የjack ma ታሪክ አነቃቂ ነው፡፡ያስገረሙኝ #25 ጥቅሶቹን ተጋበዙልኝ፡፡
+

1. “ዛሬ ከባድ ነው፡፡ነገ እንዲሁም ይከፋል፡፡ተነገ ወዲያ ግን ፀሐይ ትወጣለች፡፡መቼም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ”– Jack Ma

+

2. “ፍላጎቴ መወደድ ሳይሆን መከበር ነው፡፡ ”– Jack Ma

+

3. “ሊኖሩን ከሚገቡ እጅግ ጠቃሚ ነገሮች መካከል ትዕግስት ዋነኛው ነው፡፡”– Jack Ma

+

4. “ከተፎካካሪህ መማር እንጂ መኮረጅ የለብህም፡፡ኮርጅ.... በኋላ ግን ትሞታለህ፡፡ ”– Jack Ma

+

5. “ገንዘብ አላጣንም፡፡ያጣነው ህልመኛ ሰዎችን ነው፡፡ብርቅ የሆኑት ለህልማቸው የሚሞቱ ሰዎች ናቸው፡፡”– Jack Ma

+

6. “በህይወት የሆነ ነገር ስትሞክር፣ የሆነ ነገር ላይ ጠንክረህ ስትሰራና የሆነ ነገር ስትለወጥ መጥፎ ነገር መከሰት ያቆማል፡፡”– Jack Ma

+

7. “መሬቱ ላይ ዘጠኝ ጥንቸሎች ካሉ ፤ ያንተ ፍላጎት አንዷን ጥንቸል መያዝ ከሆነ እሷ ላይ ብቻ አተኩር፡፡ ”– Jack Ma

+

8. “መሪ ባለራዕይ መሆን አለበት፡፡ተከታዮቹ ከሚያዩት በላይ አሻግሮ ማየት አለበት፡፡ ”– Jack Ma

+

9. “ተፎካካሪዎችን እርሳ፡፡ዝም ብለህ ደንበኞችህ ላይ አተኩር፡፡”– Jack Ma

+

10. “ተስፋ ካልቆረጥክ አሁንም እድል አለህ፡፡ ”– Jack Ma

11. “ካልደረከው ምንም ነገር አይቻልም፡፡ ”– Jack Ma

+

12. “ሰዎች ስለአንተ በጣም አካብደው ሲያስቡ የመረጋጋት እና ራስህን የመሆን ሀላፊነት ሊኖርህ ይገባል፡፡ ”– Jack Ma

+

13. “ጥሩ ቡድን ሆነን ምን ማድረግ እንደምንፈልግ በትክክል ካወቅን አንዳችን አስራቸውን ማሸነፍ እንችላለን፡፡”– Jack Ma

+

14 “ምርጥ ሰዎችን ሳይሆን ትክክለኛ ሰዎችን ፈልግ፡፡ ”– Jack Ma

+

15. “በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለማሸነፍ ከፈለክ ሰዎች ከአንተ የተሻሉ እንደሆኑ በመንገር ልታበረታቸው ያስፍለጋል፡፡ይህን ካደረክ ስኬታማ መሆንህ አይቀርም፡፡”– Jack Ma

+

16. “እውነተኛ የቢዝነስ ሰው እና የስራ ፈጣሪ ጠላት የለውም፡፡ይሄን ከተረዳ ምንም ነገር አይገድበውም፡፡”– Jack Ma

+

17. “ሁሉም ሰው ጠላቴ ነው ብለህ ስታስብ በዙርያ ያለው ሰው ሁሉ ጠላትህ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ”– Jack Ma

+

18 “የተለየ mindset ካለህ የተለየ ውጤት ታመጣለህ፡፡ ”– Jack Ma

+

19. “መስፈርቱን የሚያሟሉትን አትቅጠር፡፡እብድ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ቅጠር፡፡ ”– Jack Ma

+

20. “ሰው ምንም ያድርግ ምንም፣ ተሳካለት አልተሳካለት ከስራው የሚያገኘው ልምድ በራሱ ትልቅ ስኬት ነው፡፡”– Jack Ma

+

21 “አፋቸውን ብቻ የሚጠቀሙት ሞኞች ናቸው፡፡ብልህ ሰው አእምሮውን ጠቢብ ደግሞ ልቡን ይጠቀማል፡፡ ”– Jack Ma

+

22. “በፍጹም በፍጹም በዋጋ አትፎካከር፡፡በአገልግሎት ጥራት እና በአዲስ ግኝት ተፎካከር፡፡”– Jack Ma

+

23 .“ቅድሚያ ለደንበኛ ነው፡፡በመቀጠል ሰራተኛ ኢንቨስተር? ሶስተኛ፡፡”– Jack Ma

+
24. “የቱንም ያህል ጎበዝ ብትሆንም እንዴት ከሰው ጋር መስራት እንዳለብህ ካላወክ ተሸናፊ ነህ፡፡”– Jack Ma

+
25. “የተናከርከውን ቃል አለም ላያስታውሰው ይችላል፡፡ያደረከው ነገር ግን በፍጹም አይረሳውም፡፡”– Jack Ma

+

26.“ደንበኛ ሲወድህ መንግስትም ይወድሃል፡፡”– Jack Ma

የትኛው Jack Ma ጥቅስ ተመቻችሁ?
Inbox
የህይወት ልጓም


አንድ የሥነ-ሕይወት (Biology) መምህር ለተማሪዎቹ ፤ 'አባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ የሚለወጥበትን ዑደት' እያስተማራቸው ነው ። ለጥቆም ፤ "በሚቀጥሉት ሰዓታት ከአባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ የተቀየረው አካል ከዕጭ-ሽፋኑ (cocoon) ውስጥ ለመውጣት ትግል የሚያደርግበት ጊዜ ነው ፤ ሂደቱን ከመመልከት ውጪ ታዲያ ማንም ቢራቢሮውን ለመርዳት እንዳይሞክር!" ብሎ በማስጠንቀቅ ተማሪዎቹን ጥሎ ከቤተ-ሙከራው ይወጣል ።

ተማሪዎቹም የሚሆነውን ለማየት በጉጉት ይጠባበቁ ጀመር ፤ ልክ መምህሩ እንዳላቸውም ቢራቢሮው ከእጭ-ሽፋኑ (cocoon) ውስጥ ለመውጣት ይታገል ጀመር ። ይሁንና ከተማሪዎቹ አንደኛው ልጅ የቢራቢሮውን ትግል ዐይቶ ያዝንና ከመምህሩ ትእዛዝ በተቃራኒ- ብራቢሮውን ከእጭ-ሽፋኑ ሊያወጣው ይወስናል ። 'ትግሉን ባቀልለት' ሲልም የእጭ-ሽፋኑን ይሰብረዋል ፤ ይሁንና እንደጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ከደቂቃዎች በኋላ ቢራቢሮው ይሞታል ።

መምህሩም የተማሪዎቹን ሁኔታ ሊያይ ሲመለስ የተፈጠረውን ነገር ይነግሩታል ። ይህን ጊዜ መምህሩ የእጭ- ሽፋኑን ለሰበረው ተማሪ ሁኔታውን ያስረዳው ጀመር ፤ "ቢራቢሮውን የገደልከው እርሱን ለመርዳት በማሰብህ ነው ፤ ምክንያቱም ከእጭ-ሽፋኑ ለመውጣት ትግል ማድረጉ አንተ እንዳሰብከው ቢራቢሮውን የሚጎዳ ሳይሆን ለክንፉ ጥንካሬና እድገት የሚረዳው ነበር ። ይህ የተፈጥሮ ህግ ነውና ። አንተ ግን ትግሉን በማቋረጥህ ወይንም በመከልከልህ ምክንያት ቢራቢሮው ሊሞት ችሏል ።"

* * *
🔥ይህ ህግ በህይወታችንም ይሠራል ። ከትግል ውጪ ወደ ህይወታችን የሚመጣ (ምንም ዐይነት) ስኬት የለም ። አንዳንዴ ወላጆቻችን ከሃዘኔታ ስሜት ተነስተው የትግል ህይወትን ከኛ በማራቃቸው ጎድተውናል ። እንዳንጠነክርና እንዳናድግም አድርገውናል ። ብዙውን ጊዜ ትግል ምቹ ሜዳን ስለማይፈጥርልን አንወደውም ። የምንፈልገው ስኬት ሁሉ ያለ ትግል ሰተት ብሎ እንዲመጣ ነው ። ስኬቱን እንፈልጋለን ትግሉን ግን አንፈልገውም ።

💧አንድ ቢራቢሮ ቢራቢሮ ለመሆን-- ከእንቁላል ወደ እጭ (larva) ፤ ከእጭ ወደ ሙሽሬ (pupa) ፤ ከሙሽሬ ወደ አባጨጓሬ ፤ ከአባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ ፤ ከቢራቢሮነት መብረር እስከቻለባት ደቂቃና ሰአት ድረስ ያለውን *ትግል* ማለፍ የግድ ብሎታል ። ልክ እንዲሁ ፤ በህይወት ለማደግ/ለመለወጥ (ምንጊዜም) በትግል ውስጥ ማለፍን ይጠይቃል ። ስኬት መፈለግህ ጤነኛና ብሩህ አእምሮ የመያዝህ ምልክት ነው ። ይሁንና ስኬታማ ለመሆን ጥንካሬና እድገት የግድ ይሉሃል ፤ እነርሱ የሚገኙት ደግሞ በትግል ውስጥ ነው ።

🔥ይኸውልህ ፤ የህይወት ትልቁ ልጓም ምንድነው ካልን- ትግል ነው ። ነጻነት ያለው ሰው ለመሆን እንጂ ነጻ ለመሆን መፈለግ የለብንም ። ፈጣሪም ቅርፅ የሚሰጠን በትግል ውስጥ እያቀለጠ ነው ። ምናልባት ልጓም- እርምጃን የሚገታ ፣ እረፍት የሚያሳጣ ፣ ምቾት የሚነሳ ፣ ገደብ የሚጥል ፣ ከመንገድ የሚያስቀር ፣ ሊመስል ይችላል ። ይሁን እንጂ ፤ ልጓሙ- ከግብ የሚያደርስ ፣ የተገራ ማንነትን የሚያላብስ ፤ ብቁና ስልጡን የሚያደርግ ፣ ወደ ዓላማ-መርና መርኽ-ገዝ ህይወት (Self actualization/realization) የሚያሳድግ፣ ጥንካሬን የሚሰጥ ፣ ከሁሉ በላይ ከራስ አልፎ ለሌላው የሚቆረስ ስብእና ባለቤት የሚያደርግ--ነው ። ስለዚህ ትግል ማለት የስኬት ተቃራኒ ሳይሆን የስኬት አካል ነውና- ትልቁን የህይወት ልጓም- ትግልን አንጥላው!
በአለማችን በስኬታማነታቸው የሚታወቁ የቢዝነስ ሰዎች ቀን በቀን የሚያደርጓቸው ተመሳሳይ ልምምዶች አሉ፡፡ እነዚህ ልምምዶች የቢዝነስ ስራቸውን በቅልጥፍና እንዲሰሩ፤ አእምሯቸው በፍጥነት እንዲያስብ እና ስራቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚረዷቸው እንደሆኑ ይታመናል፡፡

እነዚህ ልምዶች እኛም ህይወታችንን ለመቀየር በምናደርገው ትግል ውስጥ ሊረዱን ስለሚችሉ እነሆ ብለናችኋል፡፡

1. ማንበብ፡- በአለማችን አሉ የተባሉ የቢዝነስ ሰዎች ወይንም ቢሊየነሮች በአብዛኛው በሳምንት አንድ መፅሃፍ ያነባሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ይሄ ማለት በአመት 52 መፅሃፍት ማንበብ ማለት ነው፡፡ እንደውም አብዛኛዎቹ የቢዝነስ ሰዎች ስኬታቸው እየጨመረ ሲመጣ የበለጠ ያነባሉ፡፡በተለይ ኢ-ልብወለድ የሆኑ መፅሃፍትን ለምሳሌ የታሪክ፤ የፖሎቲካ፤ የእምነት፤ የቢዝነስ፤ የባዮግራፊ እና የስነልቦና መፅሃፍትን በብዛት ያነባሉ፡፡
በአለም በሃብት ደረጃው በሶስተኛ ላይ የሚገኘው ዋረን በፌት በቀን ከአምስት እሰከ ስድስት ሰአት የሚያሳልፈው በማንበብ ነው፡፡ የሚያነበውም መፅሃፍትን፤ በቀን 5 ጋዜጦችን እና የተለያዩ ሪፖርቶችን ነው፡፡ ከኦሞሃ ሄራልድ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ “በቀን 500 ገፅ አንብቡ ብየ ሰዎችን እመክራለሁ፡፡ እውቀት እንደዚህ ነው የሚጠራቀመው፡፡ ግን ብዙ ሰዎች እሺ አይሉኝም” ብሏል፡፡

2. የገንዘብ አጠቃቀም እና አስተዳደር፡- የግል ቢዝነስን ለማስተዳደር ከፈለግን የገንዘብ አጠቃቀም ላይ በጣም ጠንቃቃ መሆን አለብን፡፡ ብዙዎቹ ታዋቂ የቢዝነስ ሰዎች ገንዘባቸውን ምን ላይ ማውጣት እንዳለባቸው እና ምን ላይ ማውጣት እንደሌለባቸው ሲወስኑ በጥንቃቄ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ኮመን ቦንድ የተሰኘ የፋይናንስ ተቋምን የመሰረተው ዴቪድ ክላይን ድርጅቱ የተደላደለ ቦታ እስኪደርስ ድረስ የቤት ኪራይ ወጪ ላለማውጣት ለአመታት የሚኖረው እዛው ቢሮው ውስጥ ነበር፡፡ በ2019 ግን የዴቪድ ክላይን ድርጅት ከኢንቨስተሮች ወደ 4 ቢሊየን ብር ማግኘት ችሏል፡፡
የገንዘብ አጠቃቀምን ማወቅ ማለት እራስን መጨቆን ማለት አይደለም፡፡ ገንዘብን ዝም ብሎ እየበተኑም አለኝ አለኝ ማለትም አይደለም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዷን ብር ህልማችንን ለማሳካት መጠቀም ማለት ነው፡፡

3. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡- ብዙዎቹ ስኬታማ የስራ/ቢዝነስ ፈጣሪዎች የሆነ አይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ይሄ ለምን ይመስልሃል? ጠንካራ ሰውነት ጠንካራ አእምሮን ስለሚፈጥር ነው፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል፤ የፈጠራ ችሎታን ይጨምራል፤ አትኩሮት እንዲኖረን ይረዳናል እንዲሁም ጭንቀትን ወይም ውጥረትን ይቀንሳል፡፡

የፌስቡክ ፈጣሪ የሆነው ማርክ ዙከርበርግ “በሳምንት በትንሹ ሶስት ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አደርጋለሁ፡፡ ማንኛውንም ስራ በብቃት ለመስራት ሃይል ያስፈልጋል፡፡ ድካም ድካም እንዳይለኝ እና ሃይል እንዲኖረኝ ስፖርት መስራት ግዴታ ነው” ይላል፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉት በስጋ ብቻ ሳይሆን በአእምሮም በመንፈስም ጠንክሮ እና ብቁ ሆኖ ለመገኘት ነው፡፡ የራስን ቢዝነስ ለመምራት ደግሞ ግዴታ የአእምሮ ጥንካሬ ያስፈልጋል፡፡

4. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ስኬታማ የቢዝነስ ሰዎች አእምሯቸው መቼ ንቁ እንደሚሆን፤ መቼ መቼ ስራቸውን በአግባቡ እና በቅልጥፍና መስራት እንደሚችሉ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ በነዚህ ሰአታት ሙሉ ጊዜያቸውን እና አትኩሮታቸውን ለስራ ብቻ ያደርጋሉ ፡፡ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኛ ጋር ጊዜ የሚያሳልፉት ወይም መዝናናት የሚጀምሩት ከእነዚህ ውጤታማ የስራ ጊዜያት በኋላ ነው ፡፡ ይሄ ማለት ቅድሚያ ለስራቸውና ለአላማቸው ይሰጣሉ ማለት ነው ፡፡

5. በጠዋት መነሳት ፡- ማልዶ የተነሳ ቢለምን አያጣ የሚባል የተለመደ አባባል በኛ ሀገር አለ ፡፡ በአብዛኛው ስኬታማ የሆኑ የቢዝነስ ሰዎችም በጊዜ ተኝተው በጠዋት የሚነሱ ናቸው ፡፡ ሁላችንም ግዴታ በሌሊት መነሳት ባይኖርብንም ጠቃሚ ልምድ ግን ሊሆን ይችላል ፡፡ ለምሳሌ የትዊተር መስራች የሆነው ጃክ ዶርሲ (በቅርቡ ኢትዮጲያ መጥቶ ነበር) ጠዋት የሚነሳው 11፡30 ላይ ሲሆን ሜዲቴት በማድረግ እና አስር ሺ ሜትር በመሮጥ ነው ቀኑን የሚጀምረው ፡፡

ማልዶ መነሳት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚሆን ሰአት እንዲኖረን ያደርጋል ፤ የሚረብሽ ነገር ብዙም ስለማይኖር ስራችን ላይ አትኩሮት አድርገን እንድንሰራ ይረዳናል ፡፡ አእምሯችንን ለመሰብሰብ እና ከፊታችን ያለውን ቀን ለማቀድም ይረዳናል ፡፡

6. ባለራእይ ናቸው ፡- ብዘዎቹ ስኬታማ የቢዝነስ ሰዎች በልባቸውና በአእምሯቸው ያሰቡትና ያዩት ህልም ያላቸው ሰዎች ናቸው ፡፡ በገሃዱ አለም ከሚያዩት ነገር ለየት ያለ ህልም ለራሳቸው ወይም ለድርጅታቸው ማለም ይችላሉ ፡፡
“አንድ የቻይና የቀርከሃ ዝርያ አለ … የቀርከሃውን ዘር ከተከልክ በኋላ ለ5 ዓመታት ያህል ምንም አይነት እድገት አታይም - ከትንሽዬ እብጠት መሰል ነገር በቀር !! በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ የቀርከሃው እድገት መሬት ውስጥ ነው፡፡ ቀርከሃው እጅግ ውስብስብ የሆነ ሥሩን ይዘረጋል፡፡ ልክ አምስተኛ አመቱ እንዳበቃ ግን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ 25 ሜትር ይመነደጋል !!! ሁሌም እንደሚሆነው ያየው ሁሉ አጀብ ይላል፡፡ በሕይወታችን፣ በሙያችን እና በሌላ ሌላውም የሚያጋጥሙን አብዛኞቹ ነገሮችም ልክ እንደዚህ የቻይና ቀርከሃ ናቸው፡፡ ጊዜና ጉልበትህን አፍስሰህ፣ ሰርተህ፣ ለፍተህ … ባጠቃላይ ለእድገትህ አስፈላጊ ነው ያልከውን ሁሉ ነገር አድርገህ ለሳምንታት፣ ለወራት ምናልባትም ለአመታት ምንም አይነት ውጤት ላታይ ትችላለህ፡፡

ግና ታግሰህ ከቀጠልክ … ለእድገትህ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ማድረግህን ከቀጠልክ ድንገት ያንተ 5ኛ አመት መምጣቱ አይቀርም - ያኔ ታዲያ አልመኸውም እንኳ የማታውቀው ለውጥ ድንገት ይጎበኝህና ወደ ሰማይ ትተኮሳለህ… ልብ አድርግ … በአይን የሚታይ እድገት አላየሁበትም ብለህ ቀርከሃውን ውሃ ካላጠጣኸው፣ ካልተንከባከብከው 5ኛ ዓመት ሲሞላ ምንም አይነት ተዐምራዊ እድገት አይኖርም፡፡
አንተም እንደቀርከሃው ነህ - የሚታይ ለውጥ ባይኖርም እድገቱ በአይን የማይታይ ነውና ያንተ 5ኛ ዓመት ደርሶ ድንገት በእድገት ወደ ሰማይ እስክትተኮስ ሳትሰለች ጥረትህን ቀጥል…አስታውስ … አንድ ሰው ወደ ታላቅ ከፍታ ይወጣ ዘንድ ጀግንነት እና ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል … በዚያ ላይ ደግሞ መሬቱን ቆንጥጦ የያዘ ሥርም ያሻዋል…”

📖📖📖
ደራሲ ፦ ፓውሎ ክዌሎ
በአለም ላይ በብዙ ሚሊዮን ኮፒ የታተሙ ና በብዙ ቋንቋዎች የተተረጎሙ ተወዳጅ 10 የሳይኮሎጂ (የስነልቦና) መፅሐፎችን እነሆ በነፃ ጋብዣለሁ ።

1.The power of Now - Eckhart Tolle🌟

2.The secret- Rhonda Byrne

3.ትርጉም -ለአሸናፊነት መገዛት - ቪቩ ኬራ

4.How to Win friends and influence people- Dale Carnage🌟

5.ትርጉም -ታላቁ ሀይል- Rhonda Byrne🌟

6.Critical Thinking Skills Success in 20 minute -

7.The power of your subconscious mind -Joseph Murphy🌟

8.Pushing your limit - unknown

9.The art of Public Speaking- Dale Carnagey

10.The 7 Habits of Highly Effective people- Steven R.🌟

🙏መልካም ንባብ🙏
Mindset ETH

₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩₩

10Q FOR BEING WITH US
ሰላም እንዴት ዋላችሁ .
⭕️ ንዴትን_ማብረድ⭕️

ለብዙ ሰው መድኃኒት የሆነ ሞክሩት

አንዳንድ ሰዎች ምንም የሚያበሳጭና የሚያስቆጣ ነገር ሳይኖር በትንሹ ይናደዳሉ ወይም ይቆጣሉ፡፡ ንዴት በመጠኑ ሲሆን የጤናማ ባህርይ መገለጫ ነው ነገር ግን መጠኑን ሲያልፍ ግንኙነትን ከማበላሸት ባሻገር ጤናንና አእምሮአዊ ሰላምን ይነሳል፡፡ ንዴትን በፍጹም ማስወገድ ባይቻልም ማስታገስና ማብረድ ይቻላል፡፡ ታዲያ ንዴትን እንዴት ማብረድ ይቻላል? እነሆ!

1.ከመናገር በፊት ማሰብ፡-በቶሎ የሚናደዱ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ አንድ ነገር ከመናገራቸው በፊት ጥንቃቄ አያደርጉም፡፡ በሚናገሩት ነገር ሰዎችን ያስቀይሙና “ምነው አፌን በቆረጠው!” ብለው ይጸጸታሉ፡፡

2.ስሜትን አረጋግቶ እራስን መግለጽ፡- ሳያስቡ መናገር ጸጸትን እንደሚያመጣ ሁሉ የተናደዱበትን ምክንያት ስሜትን አብርዶ አለማስረዳትና አለመናገር በእራሱ ሌላ ንዴት ስለሚፈጥር እራስን መግለጽ ያስፈልጋል፡፡

3.መተንፈስ፡- በቀላሉ የሚናደዱ ሰዎች የንዴት ስሜት በሚሰማቸው ሰዓት አንድ እጃቸውን ደረታቸው ላይ አድርገው ቢያንስ ሶስቴ ዓየር በረጅሙ በአፍንጫቸው መሳብና በአፋቸው ማስወጣት ስሜታቸውን ለማረጋጋት ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡

4.ንዴትን ከሚቀሰቅሱ አካባቢዎች መራቅ፡- ንዴትን በቀላሉ መቆጣጠር አስቸጋሪ ከሆነ የንዴት ስሜት በሚፈጠርበት ወቅት አካባቢውን ለቆ መሄድ፡፡ ከቻልክ አካባቢህን ቀይር አካባቢህን መቀየር ካልቻልክ እራስህን ቀይር እንደሚባለው፡፡

5.መፍትሄ መፈለግ፡-የሚያበሳጨኝና የሚያናድደኝ ነገር ምንድን ነው ብሎ ከማሰብ ይልቅ ንዴቴን እንዴት መቆጣጠርና ማብረድ እችላለሁ ብሎ በራስ መፍትሄ ማፈላለግ፡፡

6.ለራስ እውቅና መስጠት፡- ንዴትን በውስጥ አምቆ ያልተናደዱ ከመምሰል ለአእምሮ ሰላምና እርፍት ለመስጠት እንዲያስችል “አዎ እኔ ተናዳጅ ሰው ነኝ ቢሆንም እራሴን መቀየር እችላለሁ“ ብሎ ለራስ ዕውቅና መስጠት፡፡

7.ቂም አለመያዝ፡- ሰዎች የፈለጉትን የሚያናድድ ነገር በእኛ ላይ ቢያደርጉ ይቅር የሚል አእምሮ ካለንና ቂም የማንይዝ ከሆነ ንዴታችን በቀላሉ መቆጣጠር እንችላለን፡፡

8.እውነታውን ለማወቅ መጣር፡- ስሜትን በንዴት ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅረጋ ብሎ ስለሁኔታው ማጤንና የሰከነ ውይይት ለማድረግ መሞከር፡፡

9.ትዕግስትን መለማመድ፡-የመጨረሻዋን የንዴት ጣሪያ ላለመንካት ትዕግስተኛ መሆን፡፡ ይህንን ለማድረግ ዘውትር ትዕግስተኝነትን መለማመድ፡፡

10.የሌሎች ዕርዳታን መሻት፡- አንዳንድ ጊዜ ለዘመናት አብሮ የቆየን ንዴት በእራስ መንገድ ብቻ ለማብረድ መሞከር አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ሌሎች ሊያግዙን የሚችሉ ሰዎችን ዕርዳታ መጠየቅ ትልቅ ብልሃት ነው፡፡
2025/07/08 19:24:37
Back to Top
HTML Embed Code: