በሽሬ ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች 1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነባቸው የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡
ሰኔ ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በማኅበረሰብ ክፍሎች፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ችግር ለማቅለል ፣ ባለፉት 7 ተከታታይ ዓመታት ሁለገብ ማኅበራዊ ድጋፎችን በመላ ሀገራችን እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህ መሠረት በሰሜን ኢትዮጵያ ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በትግራይ ሽሬ እንደ ሥላሴ ከተማና ዙሪያው በሚገኙ 18 ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ከ35,000 በላይ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
ማኅበሩም በመላ ሀገሪቱ እንደሚያደርገው ሁሉ ሰኔ 19 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመጠለያ ጣቢያዎች በመገኘት 1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት 100 ኩንታል የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፉም ከ500 የሚልቁ ወገኖች ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን በዚህ የድጋፍ ርክክብ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካን፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን ምሥራቅና ሽረ ማእከል ተወካዮች እንዲሁም የመንግሥት አካላት በመገኘት ድጋፉን ለተጎጅዎች አስረክበዋል።
በተጨማሪም በችግሩ ለተጎዱ በአካባቢው ለሚገኙ ከ10 ለሚልቁ ገዳማት ድጋፎች የተደረጉ ሲሆን በተመሳሳይ ከወራት በፊት በአክሱም ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፎች መደረጋቸው ይታወሳል።

ድጋፎቹ የተደረጉት ማኅበራዊ ቀውሶችን ለማቃለል ከፍተኛ ሚናውን እየተወጣ ከሚገኘው ከማኅበረ በዓለ ወልድ ዘሰሜን አሜሪካ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳንም በዚህ ዘመን ለወገን ደራሽነቱን በገቢር እያስመሰከረ፣ ሕያው የአገልግሎት ታሪክ እያስቀመጠ ለሚገኘው ማኅበረ በዓለወልድ ዘሰሜን አሜሪካ ልባዊ ምሥጋናውን ያቀርባል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ባለፉት 9 ወራት ብቻ በማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ ለተጎዱ የተለያዩ አካባቢዎች ከ12 በላይ ማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ አድርጓል።
መሰል የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት