Telegram Web Link
ድጋፎቹ የተደረጉት ማኅበራዊ ቀውሶችን ለማቃለል ከፍተኛ ሚናውን እየተወጣ ከሚገኘው ከማኅበረ በዓለ ወልድ ዘሰሜን አሜሪካ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን  ማኅበረ ቅዱሳንም በዚህ ዘመን ለወገን ደራሽነቱን በገቢር እያስመሰከረ፣ ሕያው የአገልግሎት ታሪክ እያስቀመጠ ለሚገኘው ማኅበረ በዓለወልድ ዘሰሜን አሜሪካ ልባዊ ምሥጋናውን ያቀርባል።

የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ባለፉት 9 ወራት ብቻ በማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ ለተጎዱ የተለያዩ አካባቢዎች ከ12 በላይ ማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ አድርጓል።

መሰል የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት
የአዲስ አበባ ማእከል 650 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በትናንትናው ዕለት ማስመረቁ ተገለጸ

ሰኔ ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማእከሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአራት ፣ የአምስት እና የስድስት ኪሎ ግቢ ጉባኤያት ፣ የሲፒዩ ኮሌጅ ፣የሂልኮ ኮሌጅ ፣ ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ ፣ ኪዊንስ የማታ እና የካ ኢንዱስቱሪያል ኮሌጅ ግቢ ሲያስተምራቸው የነበሩ ስድስት መቶ ሃምሳ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ በትናንትናው ዕለት ማስመረቁ ተገልጿል፡፡

በዕለቱ ወረብ በተመራቂ ተማሪዎች ፣ የበገና ዝማሬ ፣ የክብር እንግዳ መልእክት የቀረበ ሲሆን በከፍተኛ ማዕረግ ለተመረቁ ተማሪዎች እውቅናና ለተመራቂዎቹ የአደራ መስቀል ተበርክቷል።

ተመራቂ ተማሪዎች በበኩላቸው በግቢ ጉባኤ ሕይወት ውስጥ ማለፋችን ከዓለማዊ ፈተናዎች ተጠብቀን ከመጣንበት ሳንወጣ እንድንኖር አስችሎናል በማለት በቀጣይም በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ሁሉ ቅድስት ቤተክርስቲያንን በማገልገል ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
2025/06/30 15:52:13
Back to Top
HTML Embed Code: