የቦንጋ ማእከል በርካታ አዳዲስ አማንያንን ማስጠመቅ መቻሉን አስታወቀ።
ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን የቦንጋ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን በዚህም ከ3 ሺህ 1 መቶ በላይ አዳዲስ አማንያንን ማስጠመቅ መቻሉን አስታውቋል።
ማእከሉ የወረዳ ማእከላትና የቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች እንዲሁም የከፋ ሀገረ ስብከት ልዑካን በተገኙበት በዓመቱ ያከናወናቸውን ዕቅድ ሪፖርት አቅርቧል።
የማእከሉ ጠቅላላ ጉባኤ በጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን የዕለቱን ትምህርት ከምዕራብ ማስተባበሪያ ዲያቆን ሙሉጌታ ረጋሳ ሰጥተዋል።
በዋና ማእከል በተሰጠው ዕቅድ መሠረት በርካታ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኘው ማእከሉ 3 ሺህ 1 መቶ 75 አዳዲስ አማንያንን በየወረዳውና በማእከላት መምህራን በመመደብ ማስጠመቅ መቻሉን በሪፖርቱ ቀርቧል።
እንዲሁም ወረዳዎች አባላትን በሙያ ማኅበራት በማደራጀት ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዲተጉ እየተደረገ መሆኑም በጉባኤ ተገልጿል።
ጠቅላላ ጉባኤው በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን የ2018 ዓ.ም እቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

❤26🙏6
ባሕር ዳር ማእከል ፴፩ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ
ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ፴፪ኛ ዓመት ፴፩ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ መልአከ ብርሃን ፍስሐ ጥላሁንን ጨምሮ የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት የመምሪያ ኀላፊዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ተወካይ ዲ/ን ብርሃኑ ታደሰ፣ የሰሜን ምዕራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተወካይ፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የማእከሉ አባላት በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል።
ጠቅላላ ጉባኤው በጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ሰብሳቢ ዶ/ር ትልቅ ጤና የእንኳን አደረሳችሁና እንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመልእክታቸውም ማእከሉ ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ወቅታዊና አካባቢያዊ ችግሮች ምክንያት ሲፈተን የቆየ ማእከል መሆኑን ገልጸው ይሁን እንጅ በችግርም ውስጥ ብንሆን የቻልነውንና እግዚአብሔር የፈቀደልንን አገልግሎት እያገለገልን እንገኛለን ብለዋል።
በጉባኤው የጠዋቱ መርሐ ግብር የማእከሉን ፳፻፲፯ ዓ.ም ስልታዊ እቅድ አፈጻጸም፣ የኦዲት አገልግሎት ዋና ክፍልና የውጭ ኦዲተር ሪፖርት እንደሚቀርብ ከተያዘው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ሚዲያ ዘግቧል።

❤26🙏4👍2
ደብረ ማርቆስ ማእከል ፴ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ እንደሆነ ገለጸ
ሐምሌ ፲፪/ ፳፻፲፯ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ማርቆስ ማእከል ፴ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም መጀመሩን ገልጿል።
እየተካሄደ በሚገኘው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ኤልያስ ታደሰ፣ የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊ መልአከ ምህረት ይትባረክ ክንዴና የልዩ ልዩ መምሪያ ኃላፊዎች፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ኃይለማርያም ታገለና ሌሎች የቤተ ክህነቱ ኃላፊዎች፣የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የማእከሉ ሰብሳቢ ድረስ እንዳላማው እንኳን ለ፴ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዚህ ወቅት ከባቢያዊ ችግርን ተቋቁመው ጉባኤው ለመሳተፍ የመጡትን የወረዳ ማእከላት አባላትን በማመስገን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ኤልያስ ታደሰ
እስከሞት ድረስ የታመንክ ሁን እንደተባለው በዚህ ሰዓት የቤተ ክርስቲያን ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች የበዙበት ወቅት እንደመሆኑ እስከመጨረሻው ጸንተን ቤተ ክርስቲያንን ማገልገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመርሐ ግብሩ የማእከሉ በ2017 ዓ.ም 5ኛ ዙር 2ኛ ዓመት ስልታዊ ዕቅድ አፈጻጸም እና የኦዲት አገልግሎት ሪፖርት ቀርቦና ውይይት ተደርጎ መጽደቁን ተጠቁሟል።
ጠቅላላ ጉባኤው ነገ የሚቀጥል ሲሆን የማእከሉን የ2018 ዓ.ም 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት ስልታዊ እቅድ ዙሪያና በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

❤31🙏3