Telegram Web Link
19ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በዘንድሮው ዓመት ማካሄዱን ወልቂጤ ማእከል አስታወቀ

ሐምሌ ፲፬/፳፻፲፯ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን ወልቂጤ ማእከል የ2017 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤውን ከሐምሌ 11 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በመንበረ ጵጵስና ወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ አዳራሽ መካሄዱን አስታውቋል።

በመርሐ ግብሩ የዋናው ማእከል ልዑካን፣የደብራት አስተዳዳሪዎች፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች፣ አጋር አካላት እና የወልቂጤ ወረዳ ማእከል አባላት ተገኝተዋል።

በጉባኤው የመጀመሪያ ምሽት የወረዳ ማእከላቱን ልዑክ አቀባበል በማድረግ በማእከሉ አባላት፣ ካህናት አባቶች በጸሎት ተከፍቶ ከየወረዳ ማእከሉ በዋና ዋና አገልግሎት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መደረጉ ተገልጿል።

ባለፉት ለሁለት ቀናት በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የእንኳን ደኅና መጣችሁና የዋናው ማእከል መልእክት የተላለፈ ሲሆን የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም በማእከሉ ሰብሳቢ ዲ/ን ዶ/ር ከበደ ውድማ እና የፋይናንስና የኦዲት ሪፖርቶች በዋና ክፍሉ ተጠሪዎች መቅረቡን ተጠቁሟል።

በመጨረሻም የ2018 ዓ.ም የማእከሉ ዕቅድ፣የኦዲትና የበጀት ዕቅዶች ላይ አስተያየትና ጥያቄ ቀርቦ ምላሽና ማብራሪያ በዋና ክፍላት የተሰጠ ሲሆን የዋናው ማእከል ልዑካን በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በመስጠት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቅቋል።
22👏10🙏3👍2
‎"በዚህ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ከሚያስፈልጓት ማኅበራት ቀዳሚው ማኅበረ ቅዱሳን ነው።" ብፁዕ አቡነ በርናባስ

ሐምሌ ፲፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የሰቆጣ ማእከል 18ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለተከታታይ ሁለት ቀናት አካሂዷል።

‎በጉባኤው የተገኙት የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ በርናባስ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን የተዘጉ አቢያተ ክርስቲያናትን በመክፈት፣አዳዲስ አማንያንን ወንጌል በማስተማርና በማስጠመቅ ፣ጉባኤ ቤቶችን በመደገፍ በኩል የሠሩት ሥራ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

‎ብፁዕነታቸው አክለውም ዘመኑ ክርስትያኖች የሚፈተኑበት፣ቤተ ክርስቲያን የውጭና የውስጥ ጠላቶች በበዙባት በዚህ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ከሚያስፈልጓት ማኅበራት ቀዳሚው ማኅበረ ቅዱሳን ነው ብለዋል።

‎በጠቅላላ ጉባኤው ተገኝተው የዋናውን ማእከል መልእክት ያስተላለፉት ዲ/ን መንግሥት በበኩላቸው ማኅበሩ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፣የገጠሪቷን አብያተ ክርስትያናት በመደገፍ፣የጉባኤ ቤቶችን በማጠናከር እና ማኅበሩን ዓለም ዓቀፋዊ ለማድረግ የተሠሩ ሥራዎች የሚበረታቱ እንደሆነ ገልጸቷል።

‎በመጨረሻም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 18ኛው ጠቅላላ ጉባኤ በ2018 ዓ.ም የሚከወኑ የሥራ ዕቅዶችን ተወያይቶ በማጽደቅና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ጠቅላላ ጉባኤው ተጠናቋል።
85🙏9👏4
የሰብአዊ ድጋፍ ጥሪ!
+++
ማኅበረ ቅዱሳን በሀገራችን ኢትዮጵያ በማኅበራዊ ቀውሶች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እያሰባሰበ በማድረስ ላይ ይገኛል።
እርስዎም ድጋፍ በማድረግ ኃላፊነትዎችን እንዲወጡ ተጋብዘዋል።
ድጋፍ ለማድረግም፡-
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
(Mahiber kidusan social support and rehabilitation accounts )
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 
መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
44👍5🙏5
በሰሜን ምዕራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የደረጃ ሁለት ተተኪ መምህራን ሥልጠና መጠናቀቁን ደብረ ማርቆስ ማእከል አስታወቀ

ሐምሌ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ማርቆስ ማእከል ግቢ ጉባኤ ማስተባበሪያ አዘጋጅነት ከተለያዩ የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲ ለተዉጣጡ ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ለሃያ ስድስት ተከታታይ ቀናት እየተሰጠ የቆየው የደረጃ ሁለት ተተኪ መምህራን ሥልጠና የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ኤሊያስ ታደሰ በተገኙበት አስመርቋል።

ተመራቂ ሠልጣኞች ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፣ከቡሬ ካምፓስ፣ከጤና ካምፓስ እና ከተለያዩ የከተማ ግቢ ጉባኤ የተወጣጡ ቁጥራቸው 36 መሆናቸው ተገልጿል።

ሠልጣኞቹ በቆይታቸው ነገረ ቤተክርስቲያን ፣የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት፣የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣የስብከት ዘዴ፣ሕይወትና ክህሎት፣ ምሥጢራትና ሥርዓት፣ ነገረ-ማርያም እና ሌሎች ሥልጠናዎች እንደተሰጠም ተመላክቷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ቆሞስ አባ ኤሊያስ እንደገለጹት የተካሄደው ሥልጠና እጅግ ጠቃሚ የሆነና ሊበረታታ የሚገባው መሆኑን ጠቅሰው የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው በማለት ሠልጣኞች በተሰጠው ሥልጠና እግዚአብሔርን በመፍራት፣ ሕይወታቸውን በመምራት፣ መክሊታቸውን በማትረፍ በሚሄዱበት ሁሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን፣ ግቢ ጉባኤዎቻቸውን፣ ወላጆቻቸውንና አገራቸውን እንዲያገለግሉ የአደራ መልእክትና አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።
76👍8🙏7
2025/09/16 10:17:13
Back to Top
HTML Embed Code: