“ዑቁ እንከ ዘከመ ተሓውሩ ከመ ጠቢባን በንጽሕ ወአኮ ከመ ዓብዳን፤ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት በንጽሕና እንደምትመላለሱ ዕወቁ” (ኤፌ. 5*15)፤ ሁሉንም መስጠትና መንሣት የሚችለው እግዚአብሔር አምላክ ጥበብን ለሰው ልጆች ሰጥቶአል፤ የሚሰጠው የጥበቡ ደረጃ የተለያየ ቢሆንም እግዚአብሔር ከጥበብ ባዶ አድርጎ የፈጠረው ግን የለም፤ የእግዚአብሔር ስጦታዎች ለፍጡራን ሲሰጡ ሊጠቀሙባቸው እንጂ እንዲሁ በከንቱ ሊያባክኑዋቸው አይደለም፡፡
ቅዱስ መጽሐፍ ስለ ጥበብ አስፈላጊነት በብዙ ቦታ ያስተምራል፤ በተለይም ጠቢቡ ሰሎሞን “ጥበብ ትኄይስ እምኲሉ መዛግብት ወኲሉ ክብር ኢመጠና ላቲ፤ ከሀብት ሁሉ ጥበብ ትበልጣለች፤ ክብርም ሁሉ አይመጣጠናትም፤” በማለት የጥበብ ብልጫ ተወዳዳሪ የሌላት እንደሆነች ያስገነዝበናል፤ እግዚአብሔርም ሥራውን ሁሉ በጥበብ እንደሚሠራ “ወኲሎ በጥበብ ገበርከ፤ ሁሉንም በጥበብ አደረግህ” በሚል ተጽፎ ይገኛል፤ እግዚአብሔር ሥራውን በጥበብ እንደሚሠራ፣ እኛንም በጥበብ መሥራት እንዳለብን ሲያስተምረን፣ ‹‹ኩኑ ጠቢባነ ከመ አርዌ ምድር እንደ እባብ ብልሆች ሁኑ›› ብሎናል፡፡
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት!
ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች!
ዘመንና ቦታ ሳይገድበን ምንጊዜም ሥራችንን በጥበብ መሥራት እንዳለብን ቢታወቅም ዛሬ ላይ ከምን ጊዜውም በበለጠ በጥበብ መመላለስ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፤ የዛሬዎቹ ችግሮች በአንድ አካባቢ ብቻ ያሉ ሳይሆኑ ዓለም ዓለፍ ቅርጽ ያላቸው እንደሆኑ ታላላቅ መሪዎች ሳይቀሩ በዓለም መድረክ ላይ ስሞታ ሲያቀርቡ በዓይናችን አይተናል፤ በጆሮአችንም ሰምተናል፤ በሁኔታውም የክርስትና ሃይማኖት በአጠቃላይ በተለይም ደግሞ የኦርቶዶክሱ ወገን የችግሩ ገፈት ቀማሽ እንደሆነ እየተስተዋለ ነው ፡፡
እኛም የዚሁ ወገን አካል በመሆናችን የችግሩ ቀማሽ መሆናችን አልቀረም፤ በየቀኑ ካህናትና ምእመናን ይገደሉብናል፤ አብያ ክርስቲያናት ይቃጠሉብናል፤ የእምነትና የኅሊና ነጻነት በእጅጉ የሳሳ ሆኖብናል፤ አላስፈላጊ ጫናዎችም በዝተውብናል፤ ከውጭና ከውስጥ በተቀነባበረ ስሌት የቤተክርስቲያናችንን ስም ማጥፋት የዕለት ተግባራቸው ያደረጉ አካላት ተበራክተዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ከነባሩና ረጅም ዘመን ካስቈጠረው ሰፊ ማእዷ እያበላቻቸው ያለች መሆኗን ዘንግተው እንብላሽ፣ እንዋጥሽ የሚሉዋት ወገኖች በዝተዋል፣ በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች አባቶች እንደልብ ተንቀሳቅሰው መሥራት የማይችሉባቸው አጋጣሚዎች እየተፈጠሩ ነው፤ የወለጋው ችግር ለዚህ በዋናነት ተጠቃሽ ነው፡፡
ታድያ እነዚህን ፈተናዎች ለማለፍ ጥበብ ያስፈልጋል፤ ነገር ግን ጥበብ መከተል ማለት ዝም ብሎ ማለፍ ወይም አይተው እንዳላዩ ሆኖ መኖር ማለት አይደለም፤ በጥበብ መመላለስ ማለት ከሁሉ በፊት ችግሮችንና የችግሮችን መንሥኤዎች በአግባቡ መረዳትና መለየት መቻል ነው፤ ከዚያም ራስን ለከፋ አደጋ በማያጋልጥ መልኩ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም መሸጋገር መቻል ነው፤ በዚህ ዘመን እንዲህ ያለ ጥበብ መጠቀም የግድ ያስፈልጋል፡፡
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት!
ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች! ቤተ ክርስቲያናችን እየተፈተነች ያለችው ከውጭ ብቻ ሳይሆን ከውስጥም ጭምር እንደሆነ መካድ የለብንም፤ ንጽሕትና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥር የሰደደ የቅድስና ሕይወትና በፈሪሀ እግዚአብሔር የተቃኘ ሥነ ምግባር ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፤
በአሁኑ ጊዜ ግን እነዚህ ሁሉ ቦታቸውን እየለቀቁ ያሉ መስለዋል፤ ቤተ ክርስቲያን በረጅሙ ታሪኳ ሲያስተምሩም ሆነ ሲማሩ፣ ሲመንኑም ሆነ ሲመነኲሱ፣ ሲቀድሱም ሆነ ሲያስቀድሱ ያለምንም ደመወዝ በራሳቸው ዓቅም በግብርና እየተዳደሩ ቤተ ክርስቲያንን በጥሩ ሰብእና በንጽሕና እና በቅድስና ጠብቀው ያስረከቡ እልፍ አእላፍ አበው እንዳልነበሯት ዛሬ የተሻለ ኑሮና ደመወዝ እያገኘን እግዚአብሔርን እንደቀኖናው በጥንቃቄ ማገልገል አቅቶናል፤ ምእመናንም በዚህ ምክንያት እየተሰናከሉ እንደሆነ እየተስተዋለ ነው፡፡ ሚድያውም ስሕተቶችን ወደ ውጭ በማውጣት ሰድቦ ለሰዳቢ እየዳረገን ነው፤ ይህ ሊሆን የቻለው የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት በአግባቡ በመያዝ ለታለመለት ዓላማ ማዋል አለመቻላችን ነው፤ ይህ ችግር ባለበት ከቀጠለ ሌላ ጦስ ይዞብን እንዳይመጣ ሁነኛ ለከት ማኖር የግድ ይሆናል፡፡
የሰበካ ጉባኤ አደረጃጀት የቤተ ክርስቲያናችንን ሀብተ ጸጋ በማሳደግ ረገድ አስተማማኝ ስልት እንደሆነ በተግባር የተረጋገጠ ነው፤ ሆኖም ሲጀመር ሳለ የነበረ መነቃቃት በአሁኑ ጊዜ የቀነሰ መስሎ ይታያል፤ አሁን በቤተ ክርስቲያን ሰፊ ሽፋን ይዞ የሚገኘው የሙዳየ ምጽዋት ገቢ እንጂ የሰበካ ጉባኤ አስተዋፅኦ እንደአይደለ ሁላችንም እናውቃለን፤ በተለይም በከተሞች ውስጥ ነገሩ ጎልቶ ይታያል፡፡
ይህ የሆነበት ምክንያት ምናልባትም በየደረጃው በኃላፊነት ያለን ሰዎች ሻል ያለ ደመወዝ ስለምናገኝ የሰበካ ጉባኤው ተልእኮ ከሚፈለገው ደረጃ ላይ የደረሰ መስሎን ይሆናል፤ ነገር ግን ከ85% ያላነሰ የገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ መምህርና ካህን አሁንም ያለ ደመወዝ የሚኖር ነው፤ ሕዝበ ክርስቲያኑም ከቤተ ክርስቲያኑ ሊያገኘው የሚገባ የበጎ አድራጎት የጤና የትምህርትና የማኅበራዊ ዋስትና አገልግሎት በሚጠበቀው ደረጃ ሊያገኝ አልቻለም፤ የገዳማትና የአብነት ት/ቤቶች ችግሮችም በነበሩበት የልመና ኑሮ እየቀጠሉ ነው፤ በውጤቱም በችግር የሚኖሩ ገዳማት የተዘጉ የአብነት ት/ቤቶችና አብያተ ክርስቲያናት ከተበራከቱ ሰነባብቶአል፡፡
ታድያ ይህንን ሁሉ መልክ ማስያዝና ቤተ ክርስቲያንን ለቀጣዩ ትውልድ ማሸጋገር የሚቻለው በጥበብና በጥበብ ብቻ መሥራት ሲቻል ነው፤ ይህንን ችግር መፍታት የሚያስችል ጥበብ ደግሞ በዘመናችን አለ፤ የጠፋው ቅንነቱና ፈቃደኝነቱ ነው፡፡
በየዓመቱ የምናካሄደው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እንደነዚህ ያሉትን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችል ካልሆነ ተሰብስበናል ማለቱ ብቻ ትርጉም ሊኖረው አይችልም፤ ስለሆነም ከዚህ በላይ የተጠቃቀሱና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያናችን ተግዳሮቶች ካሉ በዚህ ጉባኤ በማንሣት በማየትና በመገምገም ለቤተ ክርስቲያን አሻጋሪና ጥበባዊ ውሳኔ እንዲያሳልፍ አባታዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም
ዓመታዊው ዓለም ዓቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎተ ወንጌል የተከፈተ መሆኑን በእግዚአብሔር ስም እናበስራለን፡፡
መልካም ጉባኤ ያድርግልን
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ !!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!!
አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲8 ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

❤31👍10🥰7🤔1🙏1
"መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ልዕልና የሚለካው በተሰጠን የማእረግ ስም ሳይሆን በምንሠራው ሥራ ነው!" ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
ጥቅምት ፬/፳፻፲፰ ዓ.ም
ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት በሚካሄደው 44ኛው የመንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የምስካየ ኃዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኀላፊ ዘመኑ ሳይቀድመን በአገልግሎት በርትተን ጉድለታችንን ማረም ይኖርብናል ብለዋል፡፡
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት በሚገባን ልክ እና መጠን ተዘጋጅተን ለሃይማኖት መስፋፋት፣ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ክብር እና አንድነት እንዲሁም ለምእመናን ደኅንነት የተሰጠንን ኃላፊነት መወጣት ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ብፁዕነታቸው አክለውም መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ልዕልና የሚለካው በምንለብሰው ልብስ፣በተሰጠን የማእረግ ስም ሳይሆን በተግባር በምንሠራው እውነተኛ ሥራ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡
በአንድ ቢሮ ሆነን የምንሰጠው አገልግሎት ወደ ኋላ እንዳይል መሥራት ይጠበቅብናል ያሉት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በባለፈው በጀት ዓመት ያከናወነውን የሥራ ትሩፋት በበለጠ ኃላፊነት ማጠናከር ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

❤37🤔16🙏13🥰1
ከ30 ማእከላት ለተውጣጡ የክፍል ተወካዮች እና ከማስተባበሪያ ኀላፊዎች ጋር ምክከር ማካሄዱን ሙያ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ገለጸ
ጥቅምት፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ባለፈው ዓመት ባከናወናቸው ተግባራት ላይ እና በዚህ ዓመት ከማእከላት ጋር በመናነበብ ሊያከናውናቸው በያዛቸው ዕቅዶች ዙርያ ከ30 ማእከላት ለተውጣጡ የክፍል ተወካዮች እና ከማስተባበሪያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ በመርሐ ግብሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ከምሥረታው ጀምሮ ዋና ዓላማው አድረጎ ከያዛቸው ነገሮች መካከል ቤተ ክርስቲያንን በሙያ ማገልገል እንደሆነ ገልጸዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሰዓት በሁሉም ዘርፍ የእኛን ሙያ የምትፈልግበት ሰዓት ነው ሁላችሁም ቤተ ክርስቲያን በምትፈልጋችሁ ፣ባላችሁ ሙያ ሁሉ በማገልገል የተሰጣችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ ሲሉ አሳስበዋል።
በጉባኤው ላይ ተገኝተው ትምህርትና አባታዊ መልእክት ያስተላለፉት የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ ኣባል ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ሥዩም የማኅበሩ ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን በሙያ፣ በእውቀት እና በጊዜው ማገልግል ነውና በሙያ ማልገልን ትኩረት እንድትሰጡት ሲሉ አሳስበዋል።
ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ሥዩም አክለውም አሁን ላይ በሀገራችን ሰፊ ማኅበራዊ አገልግሎት የሚፈልጉ ጉዳዮች ስላሉ ማኅበራዊ አገልግሎት በትኩረትና በትጋት ሊሠራበት ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

❤14
የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ አባልና በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሥነ አእምሮ ሐኪምና ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር እንግዳ ግርማ የአሰቃቂ ክስተቶች ቁስል በማኅበረሰብ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ እና መፍትሔው በሚል ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በአጠቃላይ ጉባኤው ያለፈው ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በዘንድሮው ዕቅድ እና የአገልግሎት አቅጣጫዎች ላይ ውይይትና ምክረ ሐሳብ ተሰጥቶ ተጠናቋል።👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤13