በደቡባዊው አፍሪካ የካህናትና የምእመናን ሥልጠና በእንግሊዘኛ ቋንቋ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገለጸ
ሰኔ ፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ ማእከል የሚገኘው በኤስድሮስ ሴሚናሪየም አዘጋጅነት በደቡባዊው አፍሪካ የካህናትና የምእመናን ሥልጠና በእንግሊዘኛ ቋንቋ እየተሰጠ እንደሚገኝ ማኅበረ ቅዱሳን ደቡብ አፍሪካ ማእከል ገልጿል።
ዶ/ር ሰለሞን ድሪብሳ የደቡባዊ አፍሪካ ማእከል የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ እንደገለጹት ሥልጠናው ሁለት ዓላማዎችን መሠረት ያደረገ ሲሆን ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ቦትስዋና፣ ናምቢያ፣ ሌሴቶና በሌሎችም ደቡባዊ አፍሪካ ባሉ አገራት ሐዋርያዊ ተልእኮን ማስፈጸም እንዲቻል በእግሊዘኛ ቋንቋ ማስተማር የሚችሉና አዳዲስ አማንያንን አስተምሮ ማስጠመቅ እና ማጽናት የሚችሉ መምህራንን ለማፍራት ሥልጠናው እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ኃላፊው አክለውም በማእከሉ ስር በሚገኙ አገራት ተወልደው ለሚያድጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ለደቡባዊ አፍሪካዊ ሕጻናት ልጆች እንዲሁም ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርቱን ተደራሽ ለማድረግ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በሥልጠናው የመጀመሪው ዙር በ2016 ዓ.ም ሁለት ደቡባዊ አፍሪካ ካህናት በዲፕሎማ መርሐ ግብር የተመረቁ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ አራት ሠልጣኞች ማለትም አንድ በደቡባዊ ካህንና ሦስት ምእመናን እየሠለጠኑ እንደሚገኙ ተመላክቷል።
በዚህም ሥልጠናው ሁለት ዓመት ተኩል የሚፈጅ የዲፕሎማ መርሐ ግብር ሲሆን በተለያየ መንገድ ማለትም በኦላይን በሳምንት ሁለት ቀን ለሁለት ሰዓትና ለተማሪዎች በተዘጋጀ Student Learning Managnment platform አማካኝነት እየተሰጠ እንደሚገኝ ዶ/ር ሰሎሞን ገልጸዋል።

የማእከሉ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊው እንዳሉት ሠልጣኞች ከሥልጠናው ባገኙት መንፈሳዊ ዕውቀት፣ ክህሎትና ጥበብ በመጠቀም አዳዲስ ምእመናን አስተምሮ ማስጠመቅና በሃይማኖት እንዲጸኑ ለማድረግ ማስተማር፣ ለአገልግሎት መሰማራት፣ ልጆችን፣ ወጣቶችን እንዲሁም ግቢ ጉባኤ ትምህርት ላይ የሚገኙትንም መንፈሳዊ ትምህርት እንዲያስተምሩ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በመጨረሻም ኃላፊው ሙሉ የትምህርት ወጪን በመሸፈንና ስኮላርሺፕ በመስጠት በማእከላቱ ለሚገኙ ካህናትና ምእመናን ሥልጠናው እንዲሰጥ በማድረግ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ያበረከቱትን ለማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን አሜሪካን ማእከል እና ኤስድሮስ ሴሚናሪየምን አመስግነዋል።

“ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ” በሚል መሪ ቃል የአባላት ቃል ኪዳን ማደስ መርሐ ግብር ተካሄደ ፡፡
በአሜሪካ ማእከል የአባላትና ማእከላት ማስተባበርያ ዋና ክፍል አዘጋጅነት አርብ ምሽት ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ለሶስት ሰዓታት የዘለቀ ልዩ መርሐ ግብር ተከናወነ ። በመርሐ ግብሩ ከ450 በላይ አባላት የተገኙ ሲሆን በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ “እግዚአብሔርን ማሳየት” በሚል ርእስ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን መምህሩ እንደ ዮሴፍ በባእድ ሀገር እግዚአብሔር የሚታይበትና የሚከብርበት እኛም በረከት የምናገኝበት አገልግሎት ለመስጠት አባላት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከዮሴፍ ታሪክ በመነሳት አስረድተዋል። በመቀጠልም የማኀበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ ደግሞ ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ ስንል ምን ማለት እንደሆነና አባላትን የበለጠ ለአገልግሎት ለማሳተፍ የሚያስችሉ የአገልግሎት መስኮችን ከተቋማዊ ለውጡ ጋር አያይዘው አቅርበዋል። ለውጥና አስፈላጊነቱን በተመለከተም ከኢትዮጵያ አቶ ሰይፋ ዓለማየሁ ከእለት ተእለት ክርስቲያናዊ ሕይዎታችንና አገልግሎት ጋር አያይዘው ለታዳሚው አቅርበዋል። በመጨረሻም ከአባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን አባላት ቤተ ክርስቲያንን በማኀበራቸው በኩል ለማገልገል የገቡትን ቃል አስበውና አድሰው በሚችሉት ሁሉ እንዲያገልግሉ መልእክት ተላልፎ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል፡፡ ዘገባው የአሜሪካ ማእከል ሚዲያ ዋና ክፍል ነው።

ለ12ኛ ክፍል የአገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
ዛሬ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በሚሰጠው የፈተና ሥነ ልቡና ዝግጅት ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል። ሥልጠናው ከሥር በተቀመጠው የቴሌግራም ቻናል ላይ የሚሰጥ ይሆናል።
👇
https://www.tg-me.com/Mkfor12th

የአጋርፋ የግብርና፣ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ 142 የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን ማስመረቁ ተገለጸ
ሰኔ ፱/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ስር ከሚገኙ ሰባት ግቢ ጉባኤያት ውስጥ አንዱ የሆነው የአጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ 142 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በአጋርፋ ኮሌጅ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ማስመረቁ ተገልጿል።
በምርቃ መርሐ ግብሩ ቀሲስ ዋለ በቃ የአጋርፋ ኮሌጅ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ዲያቆን እንደሻው አድማሱ የማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ተጠሪ፣የማኅበረ ቅዱሳን አጋርፋ ወረዳ ማእከል ሰብሳቢ መ/ር ዝናቡ ኢያሱ፣ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ተካሄዷል።
ዲያቆን እንደሻው አድማሱ የማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ተጠሪ ተመራቂ ተማሪዎች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅሯን ጠብቀው እንዲያገለግሉ ፣ በኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ አገልግሎት ንቁ ተሳታፊ ሆነው ያስተማራቸውን ማኅበረሰብ በእኩልነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉ መልእክት አስተላልፈዋል።
በዕለቱም ትምህርተ ወንጌል ፣መዝሙር በግቢ ጉባኤያት ተመራቂ ተማሪዎች እና በወረዳ ማእከሉ መዘምራን የቀረበ ሲሆን የአደራ መስቀል በቀሲስ ዋለ በቃ የአጋርፋ ኮሌጅ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ለተማራቂ ተማሪዎች ተበርክቷል።

በአሜሪካ ማእከል የቦስተን ንዑስ ማእከል እሁድ ሰኔ ፰ ቀን ፳፩፯ የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አካሄደ።
በሰሜን አሜሪካ በከነክትኬት ግዛት በሚገኘው በደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዞ የተደረገ ሲሆን በጉዞው ላይ ካህናት፣ ምእመናንና ሕጻናት ታድመዋል። መነሻቸውን ቦስተን፣ ኬምብሪጅና ውስተር ያደረጉ አራት ትልቅ አውቶቢሶች በጠዋት ተነስተው ወደ ሁለት ሰአት ገደማ ተጉዘው ቤተክርስቲያኑ ወደሚገኝበት ሀምደን ከተማ አምረተዋል። አዋቂዎች ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰባዊነት በሚል ርእስ የተወያዩ ሲሆን በመጋቤ ሀዲስ እሸቱ ሰፋ ያለ የማጠቃለያ ትምህርት እና በውይይቱ ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል። ልጆች በእድሜ ተከፍለው የቃለ እግዚአብሔር እና የውይይት መርሐ ግብር በሀገሩ ቋንቋ አካሂደዋል። በመርሐ ግብሩ የተሳተፋ አዋቂዎችና ታዳጊዎች ደስተኛና ለመንፈሳዊ ሕይዎታቸው የሚሆን ስንቅ እንዳገኙበት በመግለጽ ቢያንስ በተደጋጋሚ ሊዘጋጅ እንደሚገባ አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል፡፡