Telegram Web Link
በአሜሪካ ማእከል የቦስተን ንዑስ ማእከል እሁድ ሰኔ ፰ ቀን ፳፩፯ የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አካሄደ። 
 

በሰሜን አሜሪካ በከነክትኬት ግዛት በሚገኘው በደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዞ የተደረገ ሲሆን በጉዞው ላይ ካህናት፣ ምእመናንና ሕጻናት ታድመዋል። መነሻቸውን ቦስተን፣ ኬምብሪጅና ውስተር ያደረጉ አራት ትልቅ አውቶቢሶች በጠዋት ተነስተው ወደ ሁለት ሰአት ገደማ ተጉዘው ቤተክርስቲያኑ ወደሚገኝበት ሀምደን ከተማ አምረተዋል። አዋቂዎች ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰባዊነት በሚል ርእስ የተወያዩ ሲሆን በመጋቤ ሀዲስ እሸቱ ሰፋ ያለ የማጠቃለያ ትምህርት እና በውይይቱ ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች  ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል። ልጆች በእድሜ ተከፍለው የቃለ እግዚአብሔር እና የውይይት መርሐ ግብር በሀገሩ ቋንቋ አካሂደዋል። በመርሐ ግብሩ የተሳተፋ አዋቂዎችና ታዳጊዎች ደስተኛና ለመንፈሳዊ ሕይዎታቸው የሚሆን ስንቅ እንዳገኙበት በመግለጽ ቢያንስ በተደጋጋሚ ሊዘጋጅ እንደሚገባ አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል፡፡
2025/07/01 05:25:43
Back to Top
HTML Embed Code: