ለጉባኤ ቤቶች አራተኛ ዙር የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ወልድያ ማእከል አስታወቀ
ሐምሌ ፰/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ወልድያ ማእከል በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ወልድያና አካባቢው ሥር በሚገኙ 9 ጉባኤ ቤቶች ውስጥ ለሚያስተምሩ መምህራን እና በጉባኤ ቤቶቹ ውስጥ ለሚማሩ145 ደቀ መዛሙርት ከ218,000 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
የማእከሉ ገዳማትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ዋና ክፍል ኀላፊ ዲ/ን ማርየ ንጋቴ በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከገጠር ወደ ከተማ በርካታ የአብነት ተማሪዎች እየፈለሱ በመሆኑ ለችግሩ ወቅታዊና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ድጋፉ ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል።
ድጋፍ ያደረጉትን በአሜሪካ ሎሳንጀለስ የሚገኙ በጎ አድራጊዎችን ያመሰገኑት ኃላፊው ከዚህ በፊት በሦስት ዙር በ14 ጉባኤ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ለ15 መምህራን እና ለ152 ተማሪዎች ከ456,800ሺህ ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን አስታውሰው ችግሩ ግን አሳሳቢ ስለሆነ ሌሎች በጎ አድራጊዎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
የአብነት መምህራኑና ደቀመዛሙርቱ የተደረገላቸውን ድጋፍ አመስግነው አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታና ችግር አንጻር ድጋፉ በቂ ባለመሆኑ ምእመናንና የሚመለከታቸው አካላት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

❤53🥰4👍2👏2🙏2
በርካታ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የአብነት ትምህርት እንዲማሩ ማድረጉን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ አስታወቀ
ሐምሌ ፲/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ በዘንድሮው ዓመት ካከናወናቸው ክንውኖች መካከል የአብነት መምህራንና የመማሪያ ቦታ በማመቻቸት በማእከላት 8418 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የአብነት ትምህርት እንዲማሩ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህም ትምህርቱ በተለያዩ ማእከላት የተሰጠ ሲሆን በአዲስ አበባ፣ በጅማ፣ በቦንጋ፣ በሚዛን፣ በአሶሳ፣ በሐዋሳ፣ በዲላ፣ በደብረ ብርሃን፣ በአምቦ፣ በወልዲያ፣ በደባርቅ፣ በወልቂጤ፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በፍኖተ ሰላም፣ በእንጅባራ፣ በነቀምቴ፣ በአርባ ምንጭ፣ በሻሸመኔ፣ በዱራሜ፣ በጂንካ፣ በድሬደዋ፣ በሎጊያና በደሴ ማእከላት ሥር በሚገኙ ግቢ ጉባኤያት የተማሩና ለክህነት የደረሱ 307 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ዲቁና መቀበላቸውም ተገልጿል።
ተማሪዎቹ ከዓለማዊ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የአብነት ትምህርታቸውን እንዲማሩ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡

❤107👍15🙏14🤔2
የሰቆጣ ማእከል ማኅበረ ቅዱሳን 18ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ
ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የሰቆጣ ማእከል ማኅበረ ቅዱሳን 18ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩም የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ በርናባስ በጸሎተ ቡራኬ ያስጀመሩት ሲሆን የሀገረ ስብከቱ የየክፍሉ ኃላፊዎች፣የወለህ ነቅዓ ሕይወት ጉባኤ ቤት መምህር መዝገበ ቃል ገብረ ሕይወት ፣የወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣የወረዳ ማእከላት እና የግንኙነት ጣብያ ተወካዮች፣ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች፣አጋርና የመንግስት አካላት በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤው እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤውም የዋናው ማእከል መልእክት ፣የማእከሉ የ2017 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የፋይናንስና ኦዲት ሪፖርት ፣የማእከሉ የ2018 ዓ.ም እቅድ ቀርቦ ውይይት በማድረግ ዕቅዱን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላላ ጉባኤው ከሐምሌ 12 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ተጠቁሟል።

❤54👏3🙏3
በማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል 22ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ መጀመሩ ተገለጸ
ሐምሌ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል 22ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኒቆዲሞስን ጨምሮ ሌሎች አባቶች በተገኙበት መጀመሩ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ ከዋና ማእከል የተከናወኑ ሥራዎች በዝርዝር በመምህር ዋሲሁን የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የቀረበ ሲሆን እንደ ሐረር ማእከልም በማእከሉ ሰብሳቢ በ2017 ዓ.ም የተከናወኑ ሥራዎች ቀርበው አባቶች ባሉበት ውይይት ተደርጓል።
ይህ ጉባኤ በተለያዩ ውይይቶች እስከ ነገ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል።

❤44👍8🙏3