Telegram Web Link
ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ዙር የትምህርት ቤቶች ዓመታዊ የምክክር ጉባኤ እያካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ

ሐምሌ ፲፱/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዓመታዊ የምክክር ጉባኤ በዛሬው ዕለት በማከናወን ላይ ይገኛል።

በጉባኤው ከ24 ከተሞች የተወጣጡ የአቡነ ጎርጎርዮስ፥ የአቡነ ጴጥሮስ እና የመቅረዝ ትምህርት ቤቶች የቦርድ ሰብሳቢዎች፣ የትምህርት ቤቶች ሥራ አስኪያጆችና ርእሳነ መምህራን እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በማኅበረ ቅዱሳን የኢንቨስትመንትና የሀብት ልማት ሥራ አመራር ውስጥ የትምህርት ፕሮግራሞች ሱፐር ቪዥን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደመላሽ አሰፋ እንደገለጹት ጉባኤው ዓመታዊ የትምህርት ቤቶች ዕቅድ አፈጻጸም የሚገመገምበት መርሐ ግብር መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የትምህርት ቤቶችን እንቅስቃሴ የሚያጠናክሩ፣ የትምህርቱን ጥራት የሚያስጠብቁ አሠራሮችን በዘመናዊ መንገድ ሊያስኬዱ የሚችሉ ሥልጠናዎችም እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

ማኅበሩ በአገር ውስጥ በ24 ከተሞች ትምህርት ቤቶችን  በማቋቋም ትውልድን በተሻለ ጥራት ለማፍራት እያደረገ ያለው ጥረት አመርቂ ውጤት ያመጣል ብለን እናምናለን ያሉት አቶ ደምመላሽ አሰፋ ለዚህ ክንውን ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ መልእክት አስተላልፈዋል።
60🙏10
በሜሪላንድና ቨርጅንያ በሚገኙ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች መካከል የተደረገውን የጥያቄና መልስ ውድ ድር-  ክፍል አንድ

https://www.youtube.com/watch?v=ln_m_dIYrCg&t=285s
48👍3👏3
እንጅባራ ማእከል 19ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ገለጸ

ሐምሌ ፳፩/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን በእንጅባራ ማእከል 19ኛ ዓመት 19ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ከሐምሌ 18 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሦስት ቀናት ማካሄዱን ገልጿል።

በጉባኤው የኮሶበር መንበረ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ አማረ ወንዴ ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን ምዕራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተወካዮች ፣ የወረዳ ማእከላት ተወካዮች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የሰ/ት/ቤት አንድነት ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የማእከሉ አባላት ተግኝተዋል።

የኮሶበር መንበረ ሥላሴ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ አማረ ወንዴ እንደተናሩት ማኀበረ ቅዱሳን የትህትና እና የሥርዓት ባለቤት ነው ስለሆነም ከሰ/ት/ቤቶች ከልዩ ልዩ በጎ ማኅበራት ከገዳማት እና ከጉባኤ ቤቶች እና ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመግባባት እና በመደማመጥ ለአንዲት ቅድስት ሐዋርያዊት እና ኩላዊት ቤተክርስቲያን ተግታችሁ እንድታገለግሉ ሲሉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም የማእከሉ ነባር አባላት አቶ ተስፋየ ማኅበረ ቅዱሳን እኔን ለአለሁበት ያደረሰኝ መገለጫዬ ነዉ በማለት በማኅበረ ቅዱሳን እንጅባራ ማእከል ስም ለኮሶበር ፈለገ ሕይወት ጉባኤ ቤት በተለያዩ ሊቃዉንት የተፃፉ 27 መፅሐፎችን በስጦታ አበርክተዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን እንጅባራ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ይበልጣል አበጀ ለጠቅላላ ጉባኤው መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን ያመሰገኑ ሲሆን ልዪ አስተዋፅኦ ለአደረጉ አካላት የሰርተፍኬት እና ስጦታዎችን አበርክተዋል።ጠቅላላ ጉባኤው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በመወያየትና ውሳኔዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

በተመሳሳይ ደባርቅ ማእከል 2ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን አስታውቋል።
52👏1🙏1
ባሌ ሮቤ ማእከልየመጀመሪያ ዙር የርቀት ትምህርት ተማሪዎች እና አንደኛ ደረጃ ተተኪ መምህራንን አስመረቀ።

ሐምሌ ፳፩/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ስብከተ ወንጌል አገልግሎት ዋና ክፍል ለአንድ ዓመት መሠረታዊ የርቀት ትምህርት በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ ቋንቋ በሞጁል በመጀመሪያ ዙር 35 ተማሪዎችን እና ለሁለት ወራት ሲያሠለጠናቸው የቆዩ 25 አንደኛ ደረጃ ተተኪ መምህራንን በሮቤ ፈለገ ብርሃን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በአባቶች ቡራኬ አስመርቋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የሮቤ ከተማ እና አካባቢዋ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርኤል እና የወረዳ ቤተ ክህነቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ መምህር ለታ ግርማ፣ የሮቤ ፈለገ ብርሃን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መምህር አብረሐም ግርማ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ሥራ አስ ፈጻሚ ፣ተማራቂዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ስብከተ ወንጌል አገልግሎት ዋና ክፍል ተጠሪ መምህር ተስፋዬ ኮማ ማእከሉ በ5 ወረዳ ማእከላት አስተባባሪነት 35 ተማሪዎችን በመሠረታዊ የርቀት ትምህርት በሞጁል አሰተምሮ ያስመረቀ ሲሆን ከ148 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት በሚያስተላልፉበት ወቅት ገልጸዋል።

ከተማራቂዎች ከ1ኛ -3ኛ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሠልጣኞች የሽልማት መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመጨረሻም ለመርሐ ግብሩ መሳካት አስተዋጾ ላደረጉ አካላት የምስጋና እና ለተመራቂዎች የምስክር ወረቀት በሊቀ አዕላፋት ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርኤል ተበርክቶላቸዋል።
36👏4👍2🙏1
2025/09/16 00:58:32
Back to Top
HTML Embed Code: