Telegram Web Link
የነሐሴ ወር ሐመር #መጽሔት #በውስጧ ምን ይዛለች ?

የነሐሴ ወር ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን "#ሁሉም ወገን ለቤተክርስቲያን ተገቢውን ክብር ይስጥ ! . ›› በሚል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ሉዓላዊነት እንዲሁም ልማትና ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራት ሲባል ለኦርቶዶክሳውያን ብቻ የሚጠቅም ማለት አይደለም፤ መላውን የሀገር ዜጋ በአንድም በሌላም መንገድ የሚጠቅም እንጂ በማለት  በመልእክቱ ዐምድ ይዛለች።
       .#ዐውደ ስብከት ሥር” ጾምና ፈተናዎቹ" የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በልዩ መንፈሳዊ ዝግጅትና ሙቀተ መንፈስ ቅዱስ ባልተለየው መንፈሳዊነት እንዲፈጽሟቸው ከተሠሩት የመንፈሳዊ ተጋድሎ መንገዶች መካከል አንዱ ጾም እንደሆነ በስፋት በመጋቤ ምሥጢር ቀሲስ ስንታየሁ አባተ  የቅዱሳት መጻሕፍትና የሊቃውንቱን አስተምህሮ  መሠረት በማደረግ ትምህርት ይዛለች፡፡
  አጠቃላይ ጾም ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ የምናስገዛበት፣ ጠላት ዲያብሎስን ድል የምናደርግበት፣ ከእግዚአብሔር በረከትን የምንቀበልበት መንፈሳዊ ተጋድሎ ጾም እንደሆነ ሐመር መጽሔት ታስነብባለች፡፡

#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር” ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር "በሚል ርእስ ይህንን ቅዱስ ቃል ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የራቀውን አቅርቦለት የቀረበውንም አጉልቶለት በትንቢት መነጸር ከሩቅ ሆኖ አይቶ የተናገረው ልዑል እግዚአብሔር እንደ ልቤ ያለው ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት  የተናገረውን  ግሩም ጹሑፍ በትምህርተ ሃይማኖት ይዛለች።
25🙏10👍5🥰4
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዋፅኦ ለሀገር ግንባታ  " በሚል ርእስ   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ታሪክ ሥልጣኔና ዕድገት፣ የሞራልና የሥነ ምግባር ግንባታ ውስጥ ታላቅ ድርሻ ያላት መንፈሳዊት መንግሥት ፣ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በረጅም ጊዜ ታሪኳ ውስጥ ከመንፈሳዊ አገልግሎቷ ባሻገር ሞልቶ በተረፈ አስተዋፅኦዋ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ዘርፈ ብዙ ሚና ተጫውታለች የሚል ዐቢይ ትምህርት  ይዟል።
"#ክርስትና በማኀበራዊ ኑሮ፦ ኦርቶዶክሳዊነትን በማኅበረሰቡ ውስጥ በማጽናት ቦታችን የት ነው? ክ ፍል አራት  ? በማለት በመጨረሻው በክፍል አራት ደግሞ ለነፍስ ተስፋዋ የሆነችውን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን በእሳቤ፣ በእይታ፣ እና በተግባር በማኅበረሰባችን ውስጥ ከመትከል፣ ከማለምለም፣ ከማስፋትና ከማጽናት አንጻር ቦታችንን  ያሳያል ።

#በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#፲፪ ዓመታትን በባሕር ውስጥ የጸለየች እናት  "በሚል ርእስ የተጋድሎ ሕይወቷ  ፣ትውልድና ልደት ፣ የምናኔ ሕይወት፣ የአማላጅነት ጸጋ፣የተሰጣት ቃል ኪዳን፣ ዕረፍቷ ላይ  ሰፊ ትምህርት ይሰጣል ።
#በነገዋ ቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነት "በሚል የወጣትነትና መገለጫዎቹ፣ የወጣትነት ፈተናና መፍትሔው ፣ አጠቃላይ ወጣትነት እግዚአብሔርን የምናስብበት ዕድሜ፣ ለሽምግልና ዘመን ለጭንቅ ወራት ድጋፍ የሚሆነንን የጽድቅ ዛፍ አስቀድመን የምንተክልበት ዘመን መሆኑን   ሐመር  መጽሔት  ታስነብባለች።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ #ሲሳይ -ክፍል ሁለት "ውድ አንባቢያን ከወርኃ ሐምሌ ዕትም ‹‹ሲሳይ›› በሚል ክፍል አንድ አስነብበናል ክፍል ሁለት ታስነብባለች ።
#የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ "#ዘመነ ክረምት " ውድ አንባብያን ዘመነ ክረምትን መሠረት አድርገው የሚነሡ ጥያቄዎችን በሐምሌ ወር ክፍል አንድን ማስነበባችን ይታወቃል። ክፍል ሁለትንና የመጨረሻውን    ላይ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን፣ክረምት የምን ምሳሌ ነው?፣ ዘመነ ክረምትን ከሥነ ፍጥረትና ከነገረ ድኅነት ጋር በማያያዝ   ምላሽ  ይዛለች  ።
ሐመር መጽሔት #፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፰ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
Magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
🙏3129👍6👏6
የ2017 ዓ.ም የማእከላት ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ሀኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ

ነሐሴ ፱/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን ወደ 50 የሚሆኑ ማእከላት የ2017 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤያቸውን ማካሄዳቸው ተገልጿል።

በጠቅላላ ጉባኤያቸው ሊቃነ ዻዻሳት፣የየሀገረ ስብከታቸው የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የየማእከላቱ አባላት፣ባለድርሻ አካላት፣የየወረዳ ማእከላት ተወካዮችና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶችና የግቢ ጉባኤያት ተወካዮች ተገኝተዋል።

በማኅበረ ቅዱሳን ማእከላት አገልግሎት ማስተባበሪያ የሀገር ውስጥ ማእከላት ማስተባበሪያ ዋና ክፍል ኃላፊ ዲ/ን መንግሥት ሰጠው ጠቅላላ ጉባኤ ማኅበረ ቅዱሳን በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት መንፈሳዊ አገልግሎቱን በአግባቡ ለማከናወን እንዲያስችለው በተለያየ ጊዜ በተለያየ ቦታ ከዋናው ማእከል ጀምሮ እስከ ግቢ ጉባኤያት ድረስ የሚደረግ ጉባኤ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በዚህም ወደ 50 የሚጠጉ የሀገር ውስጥና የውጪ ማእከላት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ማከናወናቸውን ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም በመርሐ ግብራቱ የየማእከላቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፣ በዋናው ማእከል የተሠሩ ዋና ዋና ተግባራትና አጠቃላይ መልእክት፣ የየማእከላቱ የ2017 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ፣ የፋይናንስ ፣ የኦዲት አገልግሎት ሪፖርቶች፣ የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ቀርበውና ሐሳብ ተሰጥቶባቸው የማጽደቅና የተለያዩ የመወያያ አጀንዳዎች መነሳታቸውን ገልጸዋል።
38🙏2
የዘንድሮው ዓመት የማእከላት ጠቅላላ ጉባኤ ከባለፈው ዓመት ሲነጻጸር ከአሁናዊ ከሀገሪቱና ከቤተ ክርስቲያን ነባራዊ ሁኔታ አኳያ በተለይ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ አገልግሎት ለመፈጸም አስቸጋሪ ቢሆንም ማእከላቱ ይህ ሁኔታ ሳይገድባቸው ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዋጋ እየከፈሉ አፈጻጸማቸውን ከዕቅዳቸው አንጻር ያሻሻሉበትና ማኅበሩ ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤያቸውን በተቀመጠላቸው ጊዜ ማከናወናቸው መልካም ነው ያሉት ዲ/ን መንግሥቱ ከአፈጻጸም ረገድም ለውጥ ታይቶባቸዋል ሲሉ አመላክተዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
45🥰4🙏3
በውጭ ማእከላት የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያንን ቤተሰባዊ አቅም ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

ነሐሴ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም

የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በሥልታዊ ዕቅዱ ትኩረት አድርጎ ከሚሠራባቸው አገልግሎቶች መካከል መንፈሳዊ የምክክር አገልግሎት በመስጠት ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን የሚያጠናክሩ ካህናትና ባለሙያዎችን አሠልጥኖ ማሰማራት አንዱ ነው።

በሀገር ውስጥ በልዩ ልዩ አህጉረ ስብከቶች ሥልጠና ሲሰጥ የቆየው አገልግሎት ክፍሉ በውጭ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያንንም የዕድሉ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ የሚገኝ ሲሆን በዚህም መሠረት በቅርብ ርቀት ከሚገኘው የኬኒያ ማእከል ጋር በመተባበር ለተመረጡ ካህናትና ባለሙያዎች በበይነ መረብ /ቨርችዋል/ የታገዘ የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

በሥልጠናው የምክክር አገልግሎትን በማጠናከር አርአያ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ለመፍጠር የሚረዱ ክብረ ክህነትና አበ ነፍስ፣ መንፈሳዊ የምክክር አገልግሎት አሰጣጥ፣ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻና የልጆች አስተዳደግ፣ ሱስና አሁናዊ ተግዳሮቶች እንዲሁም ምጣኔ ሀብትና ማኅበራዊ ዕድገት ጉዳዮች ተዳሰውበታል፡፡

በመርሐ ግብሩ ከሃያ ስድስት በላይ ሠልጣኞች የተሳተፉ ሲሆን ሥልጠናው መንፈሳዊውን አስተምህሮ ከሳይንሳዊው ጋር በማስተሳሰር ዘመኑን በዋጀ መልኩ መሰጠቱ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል፡፡

ሠልጣኞች አክለውም በሥልጠናው ጥሩ ግንዛቤና ልምድ እንዳገኙበት ገልጸው በተለይ ኬኒያና አካባቢው በስደት ኑሯቸውን የሚመሩ ኢትዮጵያውያን መቆያ እንደመሆኑ በሁለንተናዊ አቅማቸው ጎልብተው ለሀገራቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሚናቸውን ለመወጣት እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡
45🙏4
ማኅበረ ቅዱሳን ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን ለማጠናከር የአመካካሪዎች ሥልጠና እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ዓመታትም ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ለዚህም የቤተ ክርስቲያን አካላት በዕውቀት፣ በገንዘብና ቁሳቁስ በመደገፍ በቅንጅት አብረው እንዲሠሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ይህን የሥልጠና መርሐ ግብር በገንዘብ መደገፍ ለምትፈልጉም፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
54🙏14🤔1
2025/09/15 12:17:51
Back to Top
HTML Embed Code: