ማኅበረ ቅዱሳን በዘንድሮው ዓመት ሁለት አዳዲስ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ግንባታ አጠናቅቆ ለሀገረ ስብከታቸው እንደሚያስረክብ አስታወቀ
ኅዳር ፫/፳፻፲፰ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት በ2018 ዓ.ም ሁለት አዳዲስ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ግንባታ አጠናቅቆ ለሀገረ ስብከታቸው እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የፕሮጀክት ዝግጅትና ትግበራ ምክትል ኃላፊ የሆኑት ኢ/ር ማስተዋል አበበ (ወ/ሪት) እንደገለጹት አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶችን መገንባት የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ለማስፈጸም ብቁ የሆኑ ደቀ መዛሙርትንና ከፍ ሲልም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በማፍራት ለምእመናን አስፈላጊውን የሃይማኖት አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት መንገድ እንዲወጡ የሚያደርግ በመሆኑ አስፈላጊነቱ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በፕሮጀክት ደረጃ የሚሠራቸውን ሥራዎች በሙሉ ጥናት በማድረግ የሚሠራ ተቋም ሲሆን በዚህም በአንድ ሀገረ ስብከት ቢያንስ አንድ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት እንዲኖር እየገነባና ነባር አብነት ትምህርት ቤቶችን ደግሞ የማጠናከር ሥራ ለረጅም ጊዜያት እየሠራ ይገኛል ሲሉ ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

❤34🙏3
በዘንድሮ ዓመትም በቤንሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ ሀገረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ በአሶሳ አምባ አራት ሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም እና የካፋ ሀገረ ስብከት ቦንጋ የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ በቦንጋ ከተማ እየተገነቡ የሚገኙት፣ በአዳሪነት 32ተማሪዎች የሚያስተናግዱ ሲሆን በአጠቃላይ ከ40 በላይ ደቀ መዛሙርት በአንድ ጊዜ የማስተማር አቅም ያላቸው ሁለቱ አዳዲስ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆኑ ኢ/ር ማስተዋል አበበ አክለው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በዚህ ዓመት የሚጀመሩ አዳዲስ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች እንደሚኖሩ እና አገልግሎት ላይ ለሚገኙ ደግሞ ከሀገረ ስብከታቸው ጋር በመነጋገር ልዩ ልዩ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግላቸው የገለጹት ኢ/ር ማስተዋል አበበ በመጨረሻም ከአብነት ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ደቀ መዛሙርት ለቤተ ክርስቲያን፣ ለማኅበረሰብና ለሀገር የሚጠቅሙ ዜጎች በመሆናቸው ማንኛውም አካል የአብነት ትምህርት ቤቶቻችንን ሊጠብቃቸውና ሊደግፋቸው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤41🙏13👍5
"...ምእመናን የሚገዟቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር የትኛው አካል ኃላፊነት እንደወሰደበት ማጣራት አለባቸው... "በመልእክት ዐምድ ✍️ ሐመር መጽሔት ኅዳር ፳፻፲፰ ዓ.ም
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦#ኅዳር ፳፻፲፰ ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በሚዲያ አገልግሎት ተቋም በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ #ኅዳር ፳፻፲፰ ዓ.ም መልእክት #ዘማኅበረ ቅዱሳን " #በውሸት ዕውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ ራቅ "በሚል በመልእክት ዐምዷ ታስነብባለች።
.#ዐውደ ስብከት ሥር”#በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ "በሚል ርእስ ስለጾም በስፋት ታስነብባለች።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#ፀሐይን የተጎናጸፈች ሴት አየሁ " በሚል ዐቢይ ርእስ ቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቀስ ትምህርት ይሰጣል ።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “# የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአኃት አብያተ ክርስቲያን ምን ትማር? ክፍል -፫ በሚል በዲ/ን ዶ/ር #ታደለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአኃት አብያተ ክርስቲያን ምን ትማር? የሚሉ ተያያዥ ነጥቦችን በዝርዝር ያሳያል ።ክህነትን ስለመጠበቅ፤ገዳማዊ ሕይወትን ስለመጠበቅ ፣ወጣቱን ትውልድ ከመታደግ አንጻር ፣መንፈሳዊ ሕይወትን ከዓለማዊ ሕይወት ጋር አስተባብሮ ከመያዝ አንጻር ፣ሁለንተናዊ አቅምን በማሳደግ ለመጪው ትውልድ ከማስተላለፍ አንጻር ከሌሎቹ ምን እንማ፤የኢኮኖሚ አቅምን ማጠናከር እና ተግዳሮቶችን መቋቋም የሚሉት ጉዳዮች ተዳሰዋል።

❤16🙏9🤔5👍1
• #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ኦርቶዶክሳዊ ኅብረት "በሚል ርእስ የኦርቶዶክሳዊ ኅብረት ጥቅሞች ፤የኦርቶዶክሳዊ ኅብረት መገለጫ ምን መሆን እንዳለበት ታሰተምራለች።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኘውን “የረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን " ክፍል አንድ በሚል ርእስ ስለ አመሠራረቱ ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከእኛ ምን ይጠበቃ? ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከእኛ የሚጠበቁትን መሠረታዊ ነጥቦች በመዘርዘር ታስነብባለች።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "# ሩሐማ " ክፍል አንድ በሚል ታስነብባለች ።
• #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “የአዲሱ ዘመን እንቅስቃሴ ወይም የአዲሱ ዘመን መንፈሳዊነት # ክፍል_፩ " በሚል ርእስና ተያያዥ ጉዳዮች መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ጋር የተደረገ ጥያቄና መልስ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
━━━━━༺✞༻━━━━

❤41🙏9👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዕጣው መውጫ ቀን ደረሰ! ይፍጠኑ! አሁኑኑ ትኬቱን በመግዛትና ለሌሎችም በማሠራጨት ኦርቶዶክሳዊ ግዴታዎን ይወጡ፡፡
🙏35❤23👍9
https://youtu.be/P0ONtiUqeMw?si=OkuSqZy12Uqwh61N
አርባዕቱ እንስሳ
አንቅዕተ ማኅሌት አንቅዕተ ውዳሴ
ምግባቸው ምስጋና ልብሳቸው ቅዳሴ
ዘወትር ይቀኛሉ ለቅድስት ሥላሴ /፪/
ዐይኖቻቸው ብዙ ክንፎቻቸው ስድስት የሥላሴን መንበር የሚሸከሙት
ሱራፌል ኪሩቤል መገብተ ስብሐት /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/
አዝ.....
ዘወትር አይለዩም ከመንበሩ ዙሪያ ያመሰግናሉ ብለው ሃሌ ሉያ
ይሏታል ድንግልን እኅትነ ነያ /፪/
አዝ.....
ኪሩቤል ሱራፌል ምሉዓነ ግርማ ምስጋናቸው ሲፈስ ድምፃቸው ሲሰማ
ልብን ይመስጣል የምስጋናው ዜማ /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/
አርባዕቱ እንስሳ
አንቅዕተ ማኅሌት አንቅዕተ ውዳሴ
ምግባቸው ምስጋና ልብሳቸው ቅዳሴ
ዘወትር ይቀኛሉ ለቅድስት ሥላሴ /፪/
ዐይኖቻቸው ብዙ ክንፎቻቸው ስድስት የሥላሴን መንበር የሚሸከሙት
ሱራፌል ኪሩቤል መገብተ ስብሐት /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/
አዝ.....
ዘወትር አይለዩም ከመንበሩ ዙሪያ ያመሰግናሉ ብለው ሃሌ ሉያ
ይሏታል ድንግልን እኅትነ ነያ /፪/
አዝ.....
ኪሩቤል ሱራፌል ምሉዓነ ግርማ ምስጋናቸው ሲፈስ ድምፃቸው ሲሰማ
ልብን ይመስጣል የምስጋናው ዜማ /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/
YouTube
"አርባዕቱ እንስሳ የአማርኛ መዝሙር" ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)

#MKZwT#ዜማወጥበብዘማኅበረቅዱሳን#Mahiberekidusan
Subscribe: https://www.youtube.com/channel/UC2U27bED0bj7ONXPNmBEKmA
Telegram: https://www.tg-me.com/+5e0PniMWKnsyMWFh

❤24🙏5👍4
የወላይታ ሶዶ ማእከል ለወረዳ ማእከላት እና ለግንኙነት ጣቢያ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ሥልጠና መስጠቱ ተገለጸ
ኅዳር ፰/፳፻፲፰ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የወላይታ ሶዶ ማእከል ከ11 ወረዳ ማእከላት እና ከግንኙነት ጣቢያ ለተውጣጡ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በወላይታ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ሁለ ገብ የስብሰባ አዳራሽ ሥልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወላይታ ሶዶ ማእከል ዋና ሰብሳቢ ኢንጂነር ኢያሱ እንዳሻው እንደገለጹት ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ለማየትና የዓመቱን ዕቅድ ለመከወን የማኅበሩን ዕቅዶች፣ ርእይና ተልእኮ እንዲሁም ዓላማዎች ጠንቅቆ የተረዳና በራስ ተነሳሽነት የሚያገለግል ቅን መሪ መፍጠር፣ የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ችግሮች የተረዳ ንቁ አባልና ሥራ አስፈጻሚ በየወረዳው ሊኖር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ሥልጠናው የየወረዳ ማእከላትን ሰብሳቢዎች፣ ስብከተ ወንጌልን፣ የዜማ አገልግሎትን፣ የአባላት እና ግንኙነት ጣቢያ ዋና ክፍል ኃላፊዎችን እንዲሁም የድጉማ መምህራንን ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የማኅበሩ ዕቅድና ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ዕቅዶችን ለማስፈጸም በተዘጋጁ መመሪያዎች ላይም ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡
በሥልጠናው ከ40 በላይ አባላት መገኘታቸው ተመላክቷል፡፡

❤14
ለደብረ መዊዕ ቀዳሜ አድባራት አበራ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርት የሕክምና ርዳታ እና ሥልጠና ተሰጠ
ኅዳር ፰/፳፻፲፰ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የጤና ቡድን ከጎንደር የማራኪ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ለደብረ መዊዕ ቀዳሜ አድባራት አበራ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርት የሕክምና ርዳታ እና ሥልጠና ኅዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም መስጠቱ ተገልጿል።
ከ88 በላይ ለሚሆኑ የቅኔ እና አቋቋም ደቀ መዛሙርት ሕክምና ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ስለ ግል እና አካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ፣ ስለ ተላላፊ በሽታዎች እና ስለሚደረጉ ጥንቃቄዎች ሰፊ ሥልጠና በባለሙያዎች ተሰጥቷል።
በመጨረሻም ስለ ተደረገላቸው ድጋፍና ሥልጠና ያመሰገኑት ሠልጣኞቹ ለሁሉም የጉባኤ ቤቱ ደቀ መዛሙርት የሚሆን ደረጃውን የጠበቀ ሽንት ቤት ችግር እንዳለባቸውና ኦርቶዶክሳውያን ይህንን ችግር እንድትፈቱልን ሲሉ የጉባኤ ቤቱ ደቀ መዛሙርት አደራ ብለዋል።

❤42👏2