በሃሎ መምህር ፕላትፎርም ከ300 በላይ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠታቸው ተገለጸ

ጥቅምት ፲፱/፳፻፲፰ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ለሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ምላሽ ማግኘት በሚቻልበት በሃሎ መምህር ፕላትፎርም ከምእመናን ለተነሡ ከ300 በላይ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠታቸው ተገልጿል።

በሃሎ መምህር ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ጠይቀው ምላሽ እንዲያገኙ ምእመናን በሚመቻቸው ጊዜና ቦታ ሁሉ አገልግሎቱን ማግኘት የሚያስችል የቴክኖሎጂ መንገድ በመሆኑ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም ተጠቁሟል።

በማኅበረ ቅዱሳን የዋናው ማእከል መደበኛ መምህር ሊቀ ልሳናት ቀሲስ ክፍያለው ጥላሁን እንደገለጹት ከሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች በርካታ የስልክ ጥሪዎች የሚመጡ ሲሆን እንደየ አካባቢያቸው ጥያቄያቸውም የተለያየ መሆኑን ተናግረዋል።

ለሚነሡት ጥያቄዎችም ምላሽ እንደሚሰጥ የገለጹት ሊቀ ልሳናት ቀሲስ ክፍያለው ጥላሁን አክለውም ምእመኑ ከመጻሕፍት፣ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ከማኅበራት፣ ከመምህራን ተገናኝተው የበለጠ መማር፣ ማወቅ እንዲችሉ መንገድ የምናሳይበትም ነው ብለዋል።

በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት የስብከተ ወንጌልና ዕቅበተ እምነት ዋና ክፍል ምክትል ኃላፊ ዲያቆን ዐቢይ ጌታሁን በበኩላቸው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት የጠፉትን በመመለስ፣ ያላመኑትን በማሳመንንና ያመኑትን በማጽናት የስብከተ ወንጌል ተልእኮን ከግብ ለማድረስ አንደኛው መሣሪያ የሃሎ መምህር ፕላትፎርም ነው በማለት ገልጸዋል።

የስልክ አገልግሎቶቱ ከተጀመረ ስምንት ወር እንደሆነው አያይዘው የገለጹት ዲያቆን ዐቢይ ጌታሁን አክለውም ፕላትፎርሙን በመጠቀም ለተነሡ በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱንም አብራርተዋል።
50👍12👏5🙏3
በመጨረሻም ምክትል ኃላፊው የእምነቱ ተከታይ የሆነውም ያልሆነውም ሁሉም ምእመን በተዘጋጀላቸው የስልክ ፕላትፎርም ሃማኖታዊ ጥያቄዎችን ዘወትር ከሰኞ እስከ ዐርብ ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ደውለው በመጠየቅ ምላሽ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ገልጸዋል።
👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
👍2313👏10🙏4
ለመመዝገብ እና የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ👉👉https://forms.gle/jkjeZnNBunzKHvp69                                                 ማሳሰቢያ መጠይቆችን ሞልተው ሲጨርሱ Submit የሚለዉን መጫንዎን እንዳይረሱ
🙏188🤔1
የገቢ ማሰባሰቢያ የትኬት ሥርጭት ከማኅበረ ቅዱሳን!
ማኅበረ ቅዱሳን “ዘመኑን የዋጀ ብቁ ትውልድ ለቤተ ክርስቲያን” የተሰኘ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የዕጣ ትኬት በማሠራጨት ላይ ይገኛል፡፡
እርስዎ ትኬቱን ገዝተዋል? ለሌሎችስ አዳርሰዋል? ይፍጠኑ፡፡
የዕጣው የሚወጣበት ቀን ኅዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም
58👍14🙏7
˝ዘመኑን የዋጀ ንቁ ትውልድ ለቤተ ክርስቲያን̏ በሚል ርእስ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የዕጣ ትኬት እየተሠራጨ እንደሚገኝ ተገለጸ

ጥቅምት ፳፪/፳፻፲፰ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ˝ዘመኑን የዋጀ ንቁ ትውልድ ለቤተ ክርስቲያን̏ በሚል ርእስ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የዕጣ ትኬት እየተሠራጨ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከሐምሌ ወር ጀምሮ እየተሠራጨ የሚገኘው የዕጣ ትኬቱ ገቢ በግቢ ጉባኤ (በዩንቨርስቲና በ ኮሌጅ) ለሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በሃይማኖትና በሥነ ምግባር ለማነጽ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የሚውል በመሆኑ በሁሉም ምእመን እጅ ሊኖር እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን ኅዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም የዕጣ ትኬቱ እንደሚወጣም ተመላክቷል።

የዕጣው ዝርዝርም፦
1ኛ ዕጣ ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ጉዞ ለ7ቀናት፣
2ኛ ዕጣ ወደ ግብጽ ገዳማት ጉዞ ለ7 ቀናት፣
3ኛ ዕጣ ከአንድ ቤተሰብ ጋር ከኢትዮጵያ ገዳማት ወደ አንዱ በአውሮፕላን መንፈሳዊ ጉብኝት ለ5 ቀናት፣
4ኛ ዕጣ ከሁለት ቤተሰብ ጋር ከኢትዮጵያ ገዳማት ወደ አንዱ በየብስ ትራንስፖርትመንፈሳዊ ጉብኝት ለ7 ቀናት፣
5ኛ ዕጣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር COREI i7 10THG፣
6ኛ ዕጣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር COREI i5 8THG፣
7ኛ ዕጣ ሳምሰንግ ታብሌት (SAMSUNG GALAXY TABLET A8 10.5) ናቸው።

የትኬቱ ዋጋ 100 ብር ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን ሱቆች፣ በግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች፣ በማኅበሩ አባላት እጅና በማኅበሩ የዕለት ገቢ መሰብሰቢያ መስኮቶች ትኬቱ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።
35🙏1
ዕጣውን ሲገዙ ከታች በተዘረዘሩት አካውንቶች፦
በንግድ ባንክ 1000003774957፣
በዳሽን ባንክ 00888872166011፣
በአሐዱ ባንክ 0003488720301፣
በአቢሲንያ ባንክ 15203196፣
በአዋሽ ባንክ 013040800017700 እና
በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ማኅበር ባንክ 1033100028297 ገቢ በማድረግና ሪሲት በመላክ ትኬቶቹን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ለጠቅላላ መረጃ በስልክ ቁጥር በ+251966636363፣ +251904155477፣ በ+251962171717 ይደውሉ።
43🙏4
የአሜሪካ ማእከል ሚዲያ ዋና ክፍል ልዩ ጉባኤ ማዘጋጀቱን ገለጸ።

"ሚዲያ ዘመኑን ለዋጀ አገልግሎት"  በሚል መሪ ቃል የሚዘጋጀው ይህ ጉባኤ  በመላው ዓለም የሚገኙ የማኅበሩ አባላትና የአገልግሎቱ ደጋፊ ምእመናን የሚሳተፉበት ነው ።

በእለቱ መልአከ ኤዶም ኤፍሬም እሸቴ  ለዘመናችን የቤተክርስቲያን  አገልግሎት የሚዲያን አስፈላጊነት  አስመልክቶ ገለጻ የሚያደርጉ ሲሆን ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ደግሞ የእለቱ መምህር እንዲሁም ምልከታቸውን የሚያካፍሉ ይሆናል። በእህታችን መስከረም ጌታቸው ደግሞ  የማኅበረ ቅዱሳን የብሮድካስት አገልግሎት ያለበት ሁኔታና ተግዳሮቶች  ማብራሪያ ይቅርባል። በጉባኤው የማኀበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ተወካዮችም ተገኝተው መልክት የሚያስተላልፉ ይሆናል።

ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጉባኤ የማኅበሩን የሚዲያ አገልግሎትና አስፈላጊነት እንዲሁም ማኅበሩ በሚዲያው በኩል እየሰጠው ያለውን አገልግሎት ለመረዳት ፍላጎት ላላቸው ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ ክፍት መሆኑን የአሜሪካ ሚዲያ ክፍል አሳውቋል።

መርሐ ግብሩ እሁድ ጥቅምት  23 ቀን 2018 ዓ/ም  (Sunday Nov. 02 ,  2025 @ 8pm EST) የሚካሄድ ይሆናል።
59🙏7👍4🥰3
Time: Nov 2, 2025 08:00 PM EST
Zoom Link
https://us06web.zoom.us/j/82845275204?pwd=E0iQG8Sq7oS8NLvF7nk4AnVasGv916.1

Meeting ID: 828 4527 5204
Passcode: 480870


ስላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች Zoom Meeting የሚጀምረው በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ሌሊት 10:00 ሰዓት ነው።
35🙏4
''ከፈተና ማለፍ መጨረሻው በረከትን ማምጣት ነው!’’:- ብፁዕ አቡነ ገሪማ

ጥቅምት ፳፭/፳፻፲፯ ዓ.ም

የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈትነው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ ዩንቨርስቲ ለገቡ የተፈጥሮ ሳይንና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሽልማት መርሐ ግብር አከናውኗል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ አቶ ንጉሤ መብራቱ የማኀበረ ቅዱሳን ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ፣ ዶ/ር በሪሁን ተፈራ የማኀበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ፣ የክፍሉ ኃላፊዎችና አባላት ተገኝተዋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ከፈተና ማለፍ መጨረሻው በረከትን ማምጣት ነው ያሉ ሲሆን አንድ ተማሪ ለስኬት ሲበቃ የብዙዎች ማለትም የራሱ፣የቤተሰብ እና የመንፈሳዊ ወንድሞችና እኅቶች ጥረቶች ውጤት ነው ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ አክለውም ቅድመ ግቢ ጉባኤ ትልቅ ነገር ያለው እና ለተማሪዎች ውጤታማነት ጉልህ ድርሻ የሚወጣ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጹ ሲሆን በተለይም ሽኝት የተደረገላችሁ ተማሪዎች ˝ትምህርታችሁን አጥኑ፣ቤተሰቦቻችሁን ስሙ፣ ዘመኑ ክፉ እንደ መሆኑ መጠን በግቢ ጉባኤ መሳተፍ እንዲሁም ጊዜአችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት̏ ሲሉ አባታዊ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ለተማሪዎቹ የላፕቶፕ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
53🙏13
እርስዎ ትኬቱን ገዝተዋል? ቀኑ እየደረሰ ነው፤ ትኬቱን በእጅዎ አስገብተዋል? ይፍጠኑ! ለሌሎችም ያድርሱ፡፡
5👍5
2025/11/05 08:26:33
Back to Top
HTML Embed Code: