የህይወት መንገድ
🔹ሰላም ቤተሰቦቻችን ዛሬ ድንቅ ትምህርት ታላቅ የህይወት ቁልፍ ስለሆነው ስለ ፍቅር ይዘንላችሁ መተናል።
✝ስለ ፍቅር
✝ማንን ማፍቀር እንዳለብን
✝ስለ ፍቅረ እግዚአብሄርና
✝ለእግዚአብሄር ያለንን ፍቅር እንዴት እንደምገልጽ
❤️✝አጠር ያለች ቪድዮ ትምህርት በyoutube ቻናላችን ለቀናል።ተመልከቱት ታተርፉበታላችሁ።❤️✝
🔵ሊንኩን በመንካት በቀላሉ ይክፈቱ
SUBSCRIBE በማድረግ ድጋፍዎን ያሳዩን
https://youtu.be/HkeRv_jcL_Y

YouTube
ታላቁ የህይወት ቁልፍ-ፍቅር Ethiopia HIWOT TUBE
suscribe በማድረግ ድጋፍዎን ያሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን
hiwot tube
@yehywetmenged
hiwot tube
@yehywetmenged
[በኮሮና ዘመን የሠኔ 14 የፀሓይ ኮሮና ልዩ ግጥምጥሞሽ]
✍️ በመ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ (ተረጋግቶ የሚነበብ ጽሑፍ)
🌞 እንደሚታወቀው ግርዶሽ ለምድራችን ዐዲስ ጉዳይ አይደለም፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ግርዶሽን በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ሲመዘግቡ ኖረዋል፡፡ ለምሳሌ ረጅም እድሜ ያስመዘገበው የጨረቃ ግርዶሽ ከ4000 ዓመት በፊት በሜሶፖታሚያ (መስጴጦምያ) የታየው ነው፡፡
🌄 በ585 (ቅ.ል.ክ) ሊድያኖችና ፐርሺያኖች ጦርነት ላይ በነበሩ ጊዜ የፀሐይ ግርዶሽ በመከሠቱ ሁለቱ ባለንጣዎችም ቁጣ ሊሆን ይችላል ብለው ጦርነቱን አቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያም በጻድቁ ዮሐንስ (አእላፍ ሰገድ) ዘመነ መንግሥት በ1661 ዓ.ም. ኅዳር 5 በ9 ሰዓት ላይ ፀሓይ በጨለመች ጊዜ በዚህ ምክንያት ንጉሡ በዕለቱ ሞት ተፈርዶባቸው የነበሩት ወንጀሎቹ እንዳይነኩ እንዳዘዙ በታሪካችን ተመዝግቧል፡፡
❤ ለእኔና መሰሎቼ የሠኔ 14 የ2012 ዓ.ም. ግርዶሽ ልዩ ሲሆን ምክንያቶቼን በዐጭሩ ለማስቀመጥ እሞክራለኊ፡፡
1ኛ) በኮሮና ዘመን የኮሮናን ግጥምጥሞሽ መታየቱ ነው፡፡
እንደ ሳይንሱ ጥናት ፀሐይ ከባቢ አየር ያላት ሲሆን የተለያዩ ሦስት ክፍሎችም አሏት፡፡ ፀሐይን ስናያት የሚታየን ብርሃናማው ውጫዊ ክፍል “ፎቶስፌር” (photosphere) ይባላል፡፡ ከርሱ ቀጥለው ያሉት ውጫዊ ከባቢ አየራት ደግሞ “ክሮሞስፌር” (chromosphere) እና የፀሐይ የመጨረሻው “አክሊል” መስሎ የሚታየው ከባቢ አየሯ ደግሞ በሳይንሱ “ኮሮና” (corona) ይባላል፡፡
❤ በመሠረታዊ ነገሩ ኮሮና ማለት በላቲን ቋንቋ “አክሊል፣ የአበባ ጒንጒን” ማለት ነው፡፡ በ2012 ዓ.ም የተከሠተው የኮሮና ቫይረስም በማይክሮስኮፕ ሲታይ የአበባ ጒንጒን ወይም አክሊል ስለሚመስል ሥያሜው ከፀሓይ ሥያሜ እንደተሰጠው ልብ እንበል፡፡ ከፎቶስፌር ከሚወጣው ብርሃን ጥንካሬ አንጻር ኮሮናንም ቀን ላይ በዐይናችን ልናይ አንችልም፡፡
❤ በሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ ጊዜ ግን በዐይናችን ማየት እንችላለን፡፡ ያሁኑ ግርዶሽም ምንም “ቀለበታዊ የፀሓይ ግርዶሽ” ቢሆንም ግን 98 ፐርሰንት ፀሓይን የሚከልል በመሆኑ ወደ ሙሉ ግርዶሽ የተጠጋ ነውና ወደ ብርሃኑና ጨለማው ወደሚገናኝበት ጠርዝ ሆነን ቀለበቱ በሚታይበት ሰዓት አካባቢ ኮሮናን ማየት እንችላለንና ግጥምጥሙ አስገርሞኛል፡፡
🌞🌞🌞🌞🌞🌞🌞
2ኛ) ይህ የ2012 ዓ.ም. ግርዶሽ ከብዙ ሺሕ ዓመታት በፊት በጥንት ሥልጡን ሕዝቦች ይህ ክስተት መጠቆሙ ለእኔ አስደንቆኛል፡፡
2.1 ይኸውም በማያ ሕዝቦች
🌄 ይኸውም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ 2000- 250 ዓ.ም. የነበሩት ሥልጡን የማያ ሕዝቦች ልዩ የዘመን መቀመሪያና ትንቢታት ነበሯቸው፡፡ ይልቁኑ የነርሱ የዘመን ቀመር ማብቂያው 2012 ዓ.ም. ላይ ነበርና በፈረንጆቹ 2012 ዓ.ም. ላይ ከፍተኛ ፍርሃት የነበረበት ናሳም ይህን ይዞ በተደጋጋሚ መግለጫ የሚሰጥበት እንደ ነበር ብዙዎቻችሁ ታውቃላችኊ፡፡ 2012 የሚል አስፈሪ ፊልም ተሠርቶ እንደነበር ትውስታችን ነው፡፡
🌞 ከብዙ ሺ ዓመት በፊት ማያዎች ከተናገሩት ውስጥ በ2012 ላይ መሬት፣ ጨረቃ፣ ፀሓይ፣ የፍኖተ ሐሊብ ማዕከል (ሚልክዌይ ሴንተር) አንድ መስመር ይሠራሉ (galactic alignment sun and milk way) ብለው ነበር፡፡ ያን መስመር ከሠሩ ዓለም ከሶላር ሲስተም ጋር የተያያዘች በመሆኗ ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ከፍተኛ ለውጥ ልታስተናግድ ትችላለች፤ የሰዎች አስተሳሰብ፣ ኢኮኖሚ ወዘተርፈ በማይገመት ፍጥነት ሊለወጥና ወደ ሌላ የዘመን ለውጥ መሄጃ ነው የሚል ነበር፡፡
🌞 ሆኖም ግን በሚገርም መልኩ በኢትዮጵያው የዘመን ቀመር ሠኔ 14/ 2012 ዓ.ም. (June 21, 2020) ያለው የፀሓይ ግርዶሽ ላይ ግን በሚገርም መልኩ ፀሓይ፣ ጨረቃ፣ መሬት አንድ መስመር በትክክል መሥራታቸው ብቻ ሳያበቃ በግንኙነት መስመራቸው ላይ ሰመር ሶልስቲስ ተጨምሮበታል፡፡
🌞 ይህ ሠኔ 14 ፀሐይ በሰማያዊው ሉል ላይ ወደ ሰሜን አቅጣጫ መጓዟን የምታቆምበት ዕለት ሲሆን “ሰመር ሶልስቲስ” (Summer Solstice) ይባላል፡፡ ይህ ዕለት በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ በጋ የሚጀምርበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በየዓመቱ ሠኔ 14 ላይ በሰመር ሶልስቲስ ወቅት ፀሐይ ከአርክቲክ ወሰን በስተሰሜን ያለው ክልል ላይ 24 ሰዓት ሙሉ የማትጠልቅ ሲሆን አንታርቲክ መስመር ጀምሮ በስተደቡብ አቅጣጫ ደግሞ 24 ሰዓት ሙሉ ጨለማ የሚሆንበት አስገራሚ ዕለት ነው፡፡ ይህ የፀሓይ፣ የጨረቃ፣ የመሬት፣ የሰመር ሶልስቲስ ግንኙነት በዚህ ሳያበቃ “ከስካይ ክሮስ” ጋር መገጣጠሙ አስደማሚ ነው ይላሉ ዘርፉ ሳይንቲስቶች፡፡
🌄 ይህንን ይዘው ሳይንቲስቶቹ፦“The June 21st , 2020 summer solstice eclipse, will be the most amazing alignment in human history. This astronomical event that will no longer take place elsewhere for tens or hundreds thousands of years ’ (የሠኔ 14/ 2012 ዓ.ም. የሰመር ሶልስቲስ ግርዶሽ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ እጅግ አስገራሚው የግንኙነት መስመር ይሆናል፤ ይህ የሥነ ፈለክ ሁኔታ ለ10 ሺም ይሁን ለ100 ሺ ዓመታትም ቢባል በየትም ቦታ ያልተከናወነ ነው) ብለዋል፡፡
🌞🌞🌞🌞🌞🌞
2.2 ከብዙ ሺ ዓመት በፊት የነበረው በእንግሊዝ የሚገኘው የሥነ ፈለክ መቀመሪያ የነበረው “ስቶንሄንጅ” በመባል የሚታወቁት ድንጋዮችና እና ውጫዊው የአውብሬይ 56 ክበባዊ መዋቅር ጂኦሜትሪ በትክክል የሠኔ 14/ 2012 ዓ.ም. ግርዶሹ የሚሠራውን መስመር ጥንቱ የመሥራቱ ነገር ለአጥኚዎች አስገራሚ ሆኗል፡፡
🌞🌞🌞🌞
2.3. የኦርዮንን ኮከብ የሚመስለው የጊዛ ታላቁ ፒራሚድ ቀመርም የሠኔ 14/ 2012 ዓ.ም. የግርዶሽ መስመር መሥራቱ ለአጥኚዎቹ አስደማሚ ነገር ከመሆኑ ባለፈ sacred geometry የመሥራቱ ነገር በአጥኚዎች ዘንድ አጀብ አስብሎታል፡፡
🌄🌄🌄🌄🌄
2.4 የጥንት ቻይናውያን ዕውቀት የነበሩት ከሒሳብ ቀመር ውስጥ የባይናሪ ማቲማቲክስ ተጠቃሽ ነው፡፡ እነዚህ ሱፐር ኪውቢትስ በቅርቡ ሲሆን የተመረመሩት በኳንተም ኮምፒውተር ተካተዋል፡፡ በቻይናውያን ጥንታዊ የባይናሪ ቀመር ላይም የሠኔ 14ቱን ግርዶሽ ጠቋሚ ነገር ማግኘታቸው ለሳይንቲስቶቹ አስገራሚ ሆኗቸው ይህንን ብለዋል፡-
✍️ This indicates that the ancient Chinese not only knew about binary mathematics but that the primary number pattern within the binary system that points directly to the astronomical event on the 21 June 2020. ይህ የሚያመለክተው ጥንታውያን ቻይናውያን ያወቁት ስለ ባይናሪ ሒሳብ ባቻ ሳይሆን በባይናሪ ዘዴ ውስጥ ያሉት ፕራይመሪ ቊጥሮች ወደ ሠኔ 14ቱ 2012 ዓ.ም. የሥነ ፈለክ ክስተትን በቀጥታ ይጠቁማሉ፡፡ በማለት እየጻፉ ነው፡፡
🌒🌒🌒🌒🌒
3ኛ) ሌላው ይኽ የሠኔ 14ቱ የፀሓይ ግርዶሽ በ4 ድብዝዝ የጨረቃ ግርዶሽ (ፕኑምብራል ሉናር ኤክሊፕስ) የተከበበ መሆኑ ለተመራማሪዎች ክስተቱ አስገራሚ ሆኗል፡፡ እነዚህም በታላላቅ ጨረቃ (super moon) የታጀቡ የጨረቃ ግርዶሾች ቀድመው ጥር 1 (January 10) ፤

ግንቦት 28 (June 5) በመቀጠል ሠኔ 28 (July 5) እና ኅዳር 21 (November 30) ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ድንቅ አድርጎታል።
🌙🌙🌙🌙🌙🌙
3ኛ) 98 ፐርሰንት ፀሓይ ጨልማ እሳታማ ቀለበት ሠርታ አስደናቂ ቅርጽዋን በምትታይበት በላሊበላ ሰማይ ላይ ንጉሥ ላሊበላ የሠራውን “ፈለገ ዮርዳኖስ” በመባል የሚታወቀውን ቦታ የግርዶሹ መስመር አቋርጦ መሄዱ አስደናቂ ሆኗል፡፡ ይህንንም የናሳ ጉጉል ማፕ ላይ ተመልከቱ፡፡
🌄🌄🌄🌄🌄
🌞🌞🌞 በተለይ ደግሞ ጠዋት ላይ ሁለቱ ፕላኔቶች ዐጣርድ (ሜርኩሪ) እና ዝሁራ (ቬነስ) በምሥራቅ ከፀሓይ ጐን ዐብረው ተሰልፈው በላሊበላ ሰማይ መታየታቸው ጥሩ አመስጣሪ ቢያገኝ መተንተን እንደሚችል ባውቅም ነገር ግን የላሊበላው ራሱን ችሎ አንድ ትልቅ ጽሑፍ ሊወጣው እንደሚችል በመገመት ጽሑፌን እዚ ላይ እቋጫለሁ፡፡
ብዙዎች ስለ መነጽሩ እየጠየቃችሁኝ በመሆኑ ሰኞ ላይ ደረጃውን የጠበቀ መነጽር የት ሊገኝ እንደሚችል ከስፔስና ቴክኖሎጂ ጋር በመነጋገር አሳውቃችኋለሁ፡፡
🌞🌙🌞 ይህን ክስተት በዘመናችን በማየታችን በማየታችን እድለኛ እንደምንሆን ይሰማኛልና ክስተቱን በፍርሃት ሳይሆን ተፈጥሮን በማድነቅና በመደሰት እናሳልፈው እላለሁ፡፡ በተረፈ ስለ መጪዎቹ ግርዶሾች አንድሮሜዳ መጽሐፋችን ላይ ስለተጠቀሱ እያነበባችሁ ዕውቀትን ቅሠሙ በጥበብም ተራቀቁ።
[መ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ]

የቤተ ክርስቲያኑን ካህን ለአንተ የተሰጠ መንፈሳዊ አባት አድርገህ ተመልከተው ምሥጢራትህንም ለእርሱ በይፋ ግለጥለት። አንድ በሽተኛ የተተሸጉ ቁስሎቹን ለሀኪሙ በመግለጥ ከበሽታው እንደሚድን ትድናለህና፡፡
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ
ምክረ አበው
ከዕለታት በአንድ ቀን አባ ፓምቦ አባ እንጦንስን “ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድነው?” ብሎ ይጠይቋል፡፡ አባ እንጦንስም እንዲህ ሲል መለሰለት “በራስህ ጽድቅ አትታመን፤ ላለፈው አትጨነቅ፤ ይልቁኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ፡፡”
አባ እንጦንስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፡- “በዚህች ምድር ላይ ስንኖር ሕይወታችንንም ሆነ ሞታችን ከባልንጀራችን ጋር ነው፡፡ ወንድማችንን ገንዘብ ካደረግነው እግዚአብሔርን ገንዘብ እናደርጓለን፤ ወንድማችንን ካስቀየምነው ግን በክርስቶስ ላይ ኃጢአትን እንሠራለን፡፡”
በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ እንጦንስን “ጸልይልኝ?” በማለት ይጠይቋል፡፡ እንጦንስም “አንተ ራስህ ጥረት የማታደርግና ወደ እግዚአብሔር የማትጸልይ ከሆነ እኔም ሆንሁ እግዚአብሔር ምሕረት ልናደርግልህ አንችልም” አለው፡፡
አባ ዮሐንስ ሐጺር አንድ ቀን እንዲህ አለ፡- “እኔ ልክ ከትልቅ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ ብዛት ያላቸው አውሬዎችና እባቦች ወደ እርሱ መጥተው ሊያጠቁት ሲሉ በፍጥነት ዛፉ ላይ ወጥቶ በማምለጥ የሚድን ሰውን እመስላለሁ፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰው ፈጥኖ ዛፉ ላይ በመውጣት እንደዳነ ሁሉ እኔም በባእቴ ውስጥ ተቀምጬ ሳለሁ ክፉ ሐሳቦች ሲዋጉኝ ፈጥኜ ወደ እግዚአብሔር በመጠጋት ከጠላቴ አመልጣለሁና፡፡”
ለመለወጥ ጥረት ስለምታደርግ ነፍስ አባ ዮሐንስ ሐጺር ለአንድ መነኰሴ ያስተማረበት ምሳሌ እንደሚከተለው ተጽፎ ይገኛል፡-“በከተማ መካከል ብዙ ወዳጆች ያሏት አንዲት ቆንጆ ሴተኛ አዳሪ ነበረች፡፡ የከተማዋ ከንቲባ ወደ እርሷ ቀርቦ፡- መልካም ሴት እንደምትሆኚ ቃል ከገባሽልኝ አሁኑኑ አገባሻለሁ ይላታል፡፡ እርሷም በሐሳቡ ተስማምታ ቃል ስለገባችለት ወደ ቤቱ ይዟት ሄደ፡፡ ወዳጆቿ ድጋሚ ሊያገኟት ስለ ፈለጉ እንዲህ እያሉ ይመካከሩ ነበር፡- የከተማው ከንቲባ ወዳጃችንን ወደ ቤቱ ወስዷታል፡፡ በግልጽ ወደ ቤቱ ከሄድን ስለሚያውቅብንና ስለሚያስፈርድብን በቤቱ ጓሮ ዞረን እናፏጭላት፡፡ የፉጨታችንን ድምጽ ለይታ ስለምታውቃቸው ከቤቷ ወርዳ ትመጣለች፡፡ ለማንኛውም ግን እርሷ ትምጣልን እንጂ እባ አንጣላም አሉ፡፡ በመጨረሻ እንደተመካከሩት በቤቱ ጓሮ ዞረው ሲያፏጩላት ጀሮዎቿ ቆሙ፡፡ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ ልትወርድ ስላልፈለገች ፈጠን ብላ ወደ እንግዳ መቀበያው አዳራሽ ገባችና በሮቹን ዘጋግታ ከውስጥ ተቀመጠች፡፡ ልክ እንደዚሁ ነፍሳችን በዚህች ሴት ስትመሰል ወዳጆቿ ደግሞ ምኞቶቻችን ይመስላሉ፡፡ ከንቲባው የሚመሰለው በምንወደው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ በቤቱ ውስጥ ያለው የእንግዳ መቀበያ አዳራሽ በዘላለማዊ ቤታችን ወይም በመንግሥተ ሰማያት ሲመሰል የሚያፋጩላት ሰዎች ደግሞ በርኩሳን መናፍስት ይመሰላሉ፡፡ በመጨረሻም ይህን ምሳሌ ነፍሳችን ሁል ጊዜ እግዚአብሔር ከተጠጋች በእርሱ ኃይል እንደምትኖር ያስረዳናል፡፡”
አባ ዳንኤል እንዲህ አለ፡- “ሥጋ የሚበረታው ነፍስ በደከመችበት መስፈርያ መጠን ሲሆን ነፍስም የምትበረታው ሥጋ በደከመበት መስፈርያ መጠን ነው፡፡”
አባ አርሳኔዎስ በበአቱ ውስጥ ተቀምጦ ሳለ ርኩሳን መናፍስት ክፉኛ ሊነዘንዙት ጀመሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ከበአቱ ውጪ በደጃፉ ላይ ቆመው የነበሩት ደቀመዛሙርቱ እንዲህ እያለ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ይሰሙታል፡- “ጌታዬ ሆይ! በፊትህ ምንም ዓይነት መልካም ሥራ ባልሠራም እንደ ቸርነትህ አቁመኸኛል! ስለዚህ ከአሁን በኋላ መልካም መሥራትን ስለምጀምር እባክህ አትተወኝ!”
(ምንጭ፡- የበረሃ አባቶች ምክሮች በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)
@mkreabew @mkreabew

✝ የጸሎት_ጠባይ
ከምንም ነገር በላይ የጸሎይ ጠባይ ማለት ምንድር ነው? ለጸሎት ድካም፥ትኩረትና ጥረት ማውጣት ተገቢ ነገር ነው?
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዲህ ብሏል፡-
" ጸሎት በሕይወት ማዕበል ውስጥ መጠጊያ ወደብ ማዕበል ለሚያንገላታቸው መልሕቅ የድሀው ሀብት የባለጸጋው ደህንነት የታማሚው መዳኛ ወይም ጤና ማግኛ ነው። ጸሎት መጥፎ ነገሮች ያስወግዳል መልካሙን ግን ይጠብቃል።"
ይኸው #እግዚአብሔር የያዘ መንፈሳዊ አባት በዚያው አስከትሎ ሲናገርም እንዲህ ብሏል፡-
" ጸሎት የነፍስን ተራ ስሜቶች ጸጥ ያደርጋል የቁጣን ዓመጽ ያበዳል ቅናትን ያጠፋል ከፉ ፍላጎቶችን ይበትናል የዓለማዊ ነገሮችን ፍቅር ያመነምናል ለነፍስም ታላቅ ሰላምና እርጋታን ያመጣል።"
የጸሎት ጠባይ ከሚሰጠው ነገር ግልጽ እየሆነ ይመጣል። ባለ መሰላሉ ቅዱስ የውሐንስ ጸሎት ሰውን #ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ መንገድ ነው ብሏል። ለእያንዳንዱ ሰው የጸሎት ጥቅም ለማስተማር ሲል ዓለሙን ኣቋርጦ ለመሄድ ይፈልግ የነበረውና በጥብቅ ምናኔ ሕይወቱ የሚታወቀው የሲናው ቅዱስ ጎርጎርዮስም እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡-
" ጸሎት ለጀማሪ ሰዎች መልካም እስት ሲሆን ቀድሞ ለጀመሩት ደግሞ በተቀጣጠለ ጊዜ መልካም መዓዛ የሚያወጣ እሳት ነው።ጸሎት ለልብ እንዲህ እያለ ይነግረዋል፡-ጸሎት የድህንነት፥ ተስፋ ፥የመንጻት ምልክት ፥የቅድስና ምሳሌ፥ #የእግዚአብሔር_እውቀት፥ #የመንፈስ_ቅዱስ አንድነት፥ #የኢየሱስ_ክርስቶስ ደስታ፥የነፍስ ተድላ፥ #የእግዚአብሔር ምሕረት፥ የእርቅ ምልክት፥ የክርስቶስ ማሕተም፥ጎልቶ የሚታይ የጸሓይ ጨረር፥ የክርስትና እምነት ማረጋገጫ የመላእክት ሕይወት ማስረጃ ነው።"
ለጸሎት ጥብቅ እንቅፋቶች እጅግ የበዛ እንቅልፍ፥ እጅግ የበዛ ምግብ፥ እጅግ የበዛ ወሬ እና እጅግ የበዛ ምቾት ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅፋቶች #እግዚአብሔርን ለማስረሳትና ሰውነት ልፍስፍስ ለማድረግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፥ ነፍስ ንቁ በመሆን መምፈሳዊ ሐሴት እንዳያደርግም ነግሮች አስቸጋሪ ያደርጋሉ። ራስን ለማጥራት አይረዱም በጸሎት ጊዜ የተረጋጉ ሰላማዊና ጸጥ ማለት ለሚገባቸው ሕሊናን ልብንና ፍትሕን ግራ ያጋባሉ።
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ቤተክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?
በግሪክኛ ቋንቋ ቤተክርስቲያን"አቅሌስያ"ተብላ ተጠርታለች።ትርጉሙም"የተጠሩ "ማለት ነው።ይህንን ትርጉም በተለያዩ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በተለይም በቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት እናገኘዋለን " በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፤"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:2)።ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያ አስራ ሁለት ቅዱሳን ሐዋርያትን ጠራ።ከእነዚህ ጋር የተጠሩ 36 ቅዱሳት አንስትን ጨምሮ 72 አርድእት ነበሩ።ኢየሱስ ክርስቶስ በእነዚህ ቤተክርስቲያንን መሠረተ።
የቤተ ክርስቲያን ዓላማ
ቤተ ክርስቲያን በምድር ያለች የእግዚአብሔር ተቋም ናት።የተመሠረተችውም ለአንድ ዓላማ ነው።የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ለመሆን ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደሰማይ ከማረጉ በፊት ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ብሎአል "" ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።"(የሐዋርያት ሥራ 1:8)። ይህ ዓላማ ቤተክርስቲያን ለምን እዚህ ምድር ላይ እንደምትኖር በሚገባ ያሳያል።የቤተክርስቲያን ሠሪዋም መሠረቷም እንዲሁም ማእዘንዋም ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"አንተ ዓለት ነህ ዓለት የተባለ ክርስቶስ የሕያው በእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ የመሰከረው መስክርነት ነው በአንተ ዓለትነት ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።"(የማቴዎስ ወንጌል 16:18)" ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:11)"በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ፤፤"(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:20)።ቤተክርስቲያን እስከ አሁን ድረስ በነቢያትና ሐዋርያት ትሠራለች፤ ሠራተኞችም ነቢያትና ሐዋርያት ናቸው። ነገር ግን እያንዳንዱ እንዴት እንደሚሠራ መጠንቀቅ ይኖርበታል።" የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:10)።ቤተክርስቲያንን ለማነጽ የሁሉም የቤተክርስቲያን አካል ደርሻ ነው። ነገር ግን በፊተ አውራሪነት የሚመግቡ መሪዎች አሉ።" እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:28)።እነዚህ ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማነጽ ሥራ ሥራቸውን መሥራት አለበቸው።" አጵሎስ እንግዲህ ምንድር ነው? ጳውሎስስ ምንድር ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደ ሰጣቸው ያገለግላሉ።"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:5) ።
ቤተክርስቲያንና ዓላማዋ
1.ሁሉንም እየስተማሩ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ማዳረግ
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።ማቴ 28፥19-20 ይህ ካልሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተክርስቲያንና ከአገለጋዮቹ ጋር አይኖርም
2. ለእግዚአብሔር ቃልና ለክርስቲያናዊ ስነምግባር ግዴለሽ አለመሆን
በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።የዮሐ ራእይ 3፥16 ይህ ደንታ ቢስነት ቤተክርስቲያንን አለማዊ ያደርጋታል .ከእግዚአብሔር መንግሥትም ያወጣታል ቤተክርስቲያን በምድር ያለሽ የእግዚአብሔር መንግሥት ናትና
3. በምድር የምታበራ መቅረዝ ናት
በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር። ራእይ 1፥13 መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። የቤተክርስቲያን መኖር በጨለማው ዓለም እንድታበራ ነው የተቃጠለ አንቦል ለምንም አይጠቅም ። ቤተክርስቲያን የክርስቶስን ብርሃን ያለማቋረጥ ማብራት ይኖርባታል
4. የዲብሎስን ሥራ ማፍርስ ይህም ዘርኘነት፤ ጥላቻ፤ ርኩሰት በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ቅዱስ ባህርይ የማይሠማሙትን ሁሉ ማስወገድ ዓላማዋና ተልኮዋ ነው
ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።1ኛ ዮሐ 3፥9
5. ፍቅርን መግለጽ
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል። 1.ዮሐ 47-12 ፍቅር የሌላት ቤትክርስቲያንና ፍቅር የሌለው ክርስቲያን እግዚአብሔር በውስጡ የለም ያለፍቅር ክርስትና የለም።

✝ "የበቃሁ ነኝ" የሚባለው መቼ ነው?
በአንድ ገዳም ውስጥ የሚኖር መነኩሴ ነበር። ከገዳሙ አበምኔት ጋርም ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው እያነሱ ሲወያዩ " አባቴ እኔ ዛሬ የዓለምን ኋጢአት ግፍና በደል አየሁ፡፡ ስለዚህ የበቃሁ ሆኛለሁ።" ብሎ አጫወታቸው፡፡ አበምኔቱም " ወንድሜ ሆይ እስቲ በርትተህ ጸልይ ፥ገና ነህ።" ብለው መለሱለት።
እንዲሁም በሌላ ግዜ ወደ አበምኔቱ ቀርቦ " አባቴ አሁንስ በቅቻለሁ ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ ሲወጡና ሲወርዱ የሕዝቡንም ኋጢአት ሲያስተርዩ አይቻለሁ።" አላቸው። " ልጄ ሆይ ገና ነህ፥ አሁንም በርታና ጸልይ።" ብለው ሸኙት፡፡ ይህም መነኩሴ ወደ ዋሻው ገብቶ ኣብዝቶ ይጾምና ይጸልይ ጀመር። ይህም መነኩሴ ወደ ዋሻው ገብቶ አብዝቶ ይጾምና ይጸልይ ጀመር። ለሶስተኛ ጊዜ ስላየውም ራእይ ለአበምኔቱ እንዲህ ሲል ገለጠላቸው፡፡ " አባቴ ሆይ ዛሬስ በዓለም ሳለሁ የሰራሁትን ኋጢአት ሁሉ አንድ በአንድ አሳየኝ።" አላቸው እርሳቸውም " ልጄ የበቃኸው አሁን ነው።" ብለው አሰናበቱት።
ክርስቲያናዊ ሕይወት ምድራዊ ፍላጎቶችንና የሰይጣን ሸንገላ በመቃወም ሰማያዊ መንግስት የሚወረስበት ምስጢር በመሆኑ ፈተናውን የዛኑ ያህል ከበድ ይላል። ብዙ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ ቃለ #እግዚአብሔር መማር ሲጀምሩ የራሳቸው ኋጢአት እያሰቡ ከማልቀስ እና ንስሓ ከመግባት ይልቅ የሌላውን በደል መቁጠር ይጀምራሉ፡፡ " እነ እገሌ እንኳን እንዲህ አደረጉ ጉድ ነው!" ማለት ያበዛሉ። ሌላውን ሲመለከቱ ሊዱኑበት የሚችሉበትን ወርቃማ የንሰሓ ጊዜ በኮንቱ ያበላሹታል። መጽሓፍ ግን "ለዚህ ዓለም ከማይመችና የአረጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ"(1ኛ ጢሞ 4 ፡ 7) ይላል። ይህ መነኩሴ የተገለጠለት ራእይ ለመዳኑ የጠቀመው የራሱን ኋጢአት ያየ ጊዜ መሆኑን ከታሪኩ መረዳት እንችላለን፡፡ እኛስ የሚታየን የማን ኋጢአት ነው? የራሳችን ወይስ የሌላው?

#ከንስሐ_ርቀን_ይቅርታን_አናገኝም
ንስሐ ለተጠመቁ ሰዎች ከጥምቀት በኋላ የተሰጠች ሀብት ናት፡፡ ይህንንም የሚያስረዳ ነገር በጥምቀት ከእግዚአብሔር ከምትገኝ ልጅነት ሁለተኛ ማዕረግ ናት፡፡ በሃይማኖት ገንዘብ ያደረግነው የመንግስተ ሰማይ መያዣ ከናት፡፡
በንስሐ ምክንያት የእግዚአብሔርን ቸርነት እናገኛለን፡፡ ንስሐ ለሚሿት ሰዎች የተከፈተች የይቅርታ በር ናት፡፡ በንስሐ በርነት ከፈጣሪ ወደሚገኝ ቸርነት እንቀርባለን፡፡ መከላከያ ከሚሆን ከንስሐ ርቀን ይቅርታን አናገኝም፡፡
አምላክ የጻፈው መጽሐፍ እንደተናገረ ሁላችን በድለናልና ያለ ዋጋ በይቅርታው ከኃጢአት እንነጻለን፡፡ ንስሐ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በሃይማኖትና በልቡና የምትገኝ ሁለተኛ ጸጋ ናት፡፡ ሀብታተ ምስጢራት ከሚገኙበት ከመንፈሳዊ ፍቅር እስክንደርስ ድረስ የሚጠብቀን መንፈሳዊ ዕውቀት ነው፡፡
(ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ)

✝እንዲህ ዓይነት ምርቃት አለ
ሁለት ካህናት ከአንድ ምእመን ጋር ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በእግራቸው ሲሄዱ ይመሽባቸውና ከሰው ቤት ለምነው ይገባሉ፡፡ ባለቤትየውም መንገደኞቹ ከጠበቁት በላይ ተንከባክቦ ያሳድራቸዋል። ጠዋት መንገዳቸውን ሊቀጥሉ ሲሉም ለቁርስ የሚሆን ቁራሽ ይቋጥርላቸዋል። በዚህም ሁሉ የተደነቁት አረጋዊ ካህን
" በሰማይ ቤት ሰይጣን ከሳሽ እርስዎ ተከሳሽ እኛን ምስክር አድርጎ ያቁመን።"
ብለው ያሳድራቸውን ሰው መረቁት።

ክፋትን_ከአንተ_አርቃት።
"ሰይጣን ክርስቶስ በልብህ ውስጥ ያለ መሆን አለመሆኑን ያውቃል፡፡ ይኸውም ስትቆጣ ወይም ስትጮህ ወይም የማይረቡ ከንቱ ነገሮችን ስትናገር ሲያይህ ጠላት በአንተ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሌለ ያውቃል ያን ጊዜ በውስጥህም በውጭህም ያለውን ሳይቀር ይገዛል ፤ መዝጊያ እንደሌለው ቤት እንደ ክፉ ሌባ ይገባና ውስጥህን ይበረብረዋል፡፡"
#ቅዱስ_ባስልዮስ

.══ ✞ ❝ የንስሐ ፍሬ❞ ✞ ══
══════ ❁✿❁ ══════
✨ንስሐ ማለት አልቅሶ ድንግል ማርያምን አብቅሎ ክርስቶስን አፍርቶ መመገብ ነው። ንስሐ ይሉኋል እንደ አባታችን አዳም ነው፥ አዳም ገነት ያጣትን ዕፀ ሕይወት በምድር በእንባው አብቅሏታልና። ይህችውም ድንግል ማርያም ናት። ፍሬውም ለዓለሙ ሁሉ በቃ! ይኸውም ፍሬ ሕይወት ክርስቶስ ነው።
©(ጸያሔ ፍኖት ከተሰኘው የአባ ገብረ ኪዳን ግርማ መጽሐፍ የተቀነጨበ /ገጽ• 370)
✞• የንሰሐ ደመወዙ ብዙ ነው •✞

✝✝✝
የኛማ ጌታ የዓለም ፈጣሪ፤
የሰላም አባት ትሑት መሐሪ፤
በደብረ ታቦር የተገለጠው፤
ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ ያየነው፤
"እንኳን ለደብረ ታቦር አደረሰን"
ዲ/ን ዳዊት
✝✝✝
የኛማ ጌታ የዓለም ፈጣሪ፤
የሰላም አባት ትሑት መሐሪ፤
በደብረ ታቦር የተገለጠው፤
ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ ያየነው፤
"እንኳን ለደብረ ታቦር አደረሰን"
ዲ/ን ዳዊት
✝✝✝
✝ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን
የአዳምና የሔዋንን የብርሃን ልብስ ሰይጣን በተንኮሉ አስገፍፎ በሐጢአት ብርድ ቢያስሸነቁጣቸው #ወልድ_አብ_ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ ቁጭ።
ዲያብሎስ በይሁዳ ልብ ገብቶ #ክርስቶስ ቢያስገድል ምን ተጠቀመ ገንዘቡን ሁሉ ተዘረፈ እንጂ። ከገነት የተዘረፈ ተመልሶ ገነት ገባ።
አይሁድ ሞኞች ናቸው #ክርስቶስ ከሰማይ ወረድሁ ቢላቸው ተመቅኝተው በመስቀል ላይ ሰቀሉት መስቀሉም ከናካቴው የሰማይ መውጫ መሰላል የቤተ ክርስቲያን ጉሉላት ሆነላቸው አረፉት። ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን ይላችኋል ይህ ነው።
ምንጭ፡- መጽሓፈ ጨዋታ

ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታዲያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደ ምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#ጌታን_በልብህ_ውደደው
ጌታ ክርስቶስን በእጁ ያቀፈው ሰው በግድ ካልሆነ በቀር ወዶ ላንዱ አይሰጠውም ነበር በክንዱ ያቀፈው ሰው ሁሌም መዓዛው ከልብሱ ተዋህዳ ትኖራለች ልብሱ ተቆራርጦ እስኪወድቅ ድረስ ፤ በፍቅር ይዞት የሚተወው አልነበረም ፡ እንዲሁ ሁሉ ጌታን ክርስቶስን በህሊናችሁ ከማፍቀር ፡ መዕዛውን ከማሽተት አትስነፉ፡፡
የህፃኑን ቃል ሰምቶ ልቡ እንደእሳት ያልተቃጠለ ማነው? እሱን ባገኘበት ቦታ ሁሉ ነገሩን ሰምቶ ደስ ያላለው አይቶትም በፍቅሩ ያልተቃጠለ ማነው? እሽኮኮ ብለህ ወደግብፅ ይዘኸው የሄድክ ዮሴፍ ሆይ ንዑድ ክቡር ነህ ፡ የሚሽከሙትን የሚሽከም ጌታን መሽከም ከባድ አይደለምና፤ ጌታ ክርስቶስን አይቶ ደስ ያላለው የልቡናውን ሐዘን ያልዘነጋ ማነው? ከእሱ ጋር መገናኘት ሐዘንን ያዘነጋል መልኩንም ማየት መከራን ያርቃል ቃሉንም መስማት ሃጢአትን ከልብ ነቃቅሎ ያጠፋል፡፡
የዮሴፍ ልጅ ያእቆብ በጌታ ፍቅር ይቃጠል ነበር በትከሻው እሽኮኮ ብሎ ካንዱ ወዳንዱ ቦታ ይወስደው ነበር መልኩን አይቶ ይጠግበው ዘንድ ዮሴፍም ወደሚጠርብበት ቦታ ይዞት ይሄድ ነበር ከእርሱ ተለይቶ መቆየት አይቻለውምና ያዩት ሰወች ሁሉ በመልኩ ደስ ይላቸው ነበር ተዓምራትን የሚያደርግ ልጅነትን የሚሰጥ ያለዘር የተፀነሰ በፍፁም ድንግልና የተወለደ ወልድን ያደንቁት ነበር፡፡ ሐዘንን አርቆ ደስ የሚያሰኝ እሱን ባየነው እያሉ ይመኙት ነበር ፡ ልደቱ ድንቅ የሚሆን ጌታን ይወዱት ነበር እንዲህም አንተ ሳታቋርጥ ጌታን በልብህ ውደደው ፤ ደስ የሚያሰኝ ሕፃን ጌታ ያዩትን ሁሉ የሚያስደንቅ ሆነ ደስ የሚያሰኝ ሕፃን ጌታን አውቀው ወደዱት ሕፃናትም ባዩት ጊዜ በፍቅሩ እሳት ይቃጠሉ ነበር ጎልማሶችም ቀርበው ባዩት ጊዜ በእርሱ ደስታ ያድርባቸው ነበር ደናግልም እሱን አይተው ንፅህናን ያገኙ ነበር (አንድም የንፅህና ፅናት ይሆናቸው ነበር) ፡ ባልቴቶችም እሱን ባዩት ጊዜ እመቤታችንን ይህን የወለደች ማሕፀን እፁብ እያሉ ያመሰግኗት ነበር ህፃናት ወጣቶች ደናግላን ጎልማሶች ሁሉ የጌታን ፊቱን አይተው ደስ ይላቸው ነበር፡፡
ወደሱ መጥተው በውጭ ለቆሙ ሁሉ እሱን ማየት ስንቅ ደስታ ይሆንላቸው ነበር እንዲሁ አንተም እሱን በማሰብ ከዚህ አለም ሃጥያት መሽሻ ስንቅን ያዝ ተዓምራትን የሚያደርግ ልጅነትን የሚሰጥ ጌታ ክርስቶስ በሰው ሁሉ ዘንድ የሚደነቅ ሆነ እሱን አይቶ ልቡ እሱን ከማየት የሰለቸ ማነው? መዓዛውን ያሽተተ እሱን ለማያዝ ቸኩሎ ደረቱን ያልደቃ ማነው? እኔስ እንኳን እሱን የዮሴፍ የቤቱን ግድግዳ አደንቃለሁ በእግሩ የረገጣትንም መሬት አደንቃለሁ፡፡
ጌታን የሚወዱት እነዚያ ግን የአምላክን ሰው መሆን ሳያውቁ ያከብሩት ነበር ሳያውቁት ሳይረዱት ልእልናውን ይናገሩ ነበር አምላክነቱን ሳያውቁ ይመኩበት ነበር ሐዘንን የሚያርቅ እሱ እንደሆነ ሳያውቁት በልባቸው ይወዱት ነበር የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ እንደሆነ ሳያውቁት በፍቅሩ እሳት ይቃጠሉ ነበር ሙታንን የሚያነሳ እሱ እንደሆነ ሳያውቁ ከእሱ ጋር በተገናኙ ጊዜ በሞቱባቸው ዘመዶቻቸው የሚያዝኑት ሐዘናቸውን ይዘነጉ ነበር ከእሱ የምትገኝ ሕይወትን የምታስገኝ መዓዛውን በአንድ ሆነው ያደንቁ ነበር ሐብት ምስጢር ከእሱ እንዲገኝ ሳያውቁ እሱን ለማየት ይሳሱ ነበር በሕፃናት ባሕርይ የተሰወረ አካላዊ ቃል እንደሆነ ሳያውቁ አንድ ሁነው መዓዛውን ያደንቁ ነበር ከሰማይ የመጣ ሙሽራ እሱ እንደሆነ ሳያውቁ በፍቅሩ ተጠልፈው በፍቅሩ ተስበው ዚህን አለም መከራውን የዚህን አለም ደስታውን ይዘነጉ ነበር አንተ ግን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር አካላዊ ቃል መድህን አለም እንደሆነ አውቀሃልና በሚበልጥ ፍቅር በተደሞ ጌታ ክርስቶስን ውደደው የዚህን አለም ደስታ የሚያስንቀውንም ጌታ ክርስቶስን እየወደድህ እያደነቅህ ይህንን አለም ግን ጥላው ናቀው፡፡
ከሄሮድስ የኮበለለ የሕፃን የክርስቶስ መልክ በግብፃውያን ዘንድ ተወደደ የግብፅ ቆነጃጅት በየጊዜው ይሰበሰቡ ነበር እሱንም በማየት ደስ ይላቸው ነበር ያለዘር የተፀነሰ በድንግልና የተወለደ ብዙ ተአምራትን የሚያደርግ ጌታን ኑ እንየው እያሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር፤ እንዲሁም አንተ ከልቦናህ ጋር ጌታህን ክርስቶስ በፀሎት በተዘክሮ ታየው ዘንድ እለት እለት ተማከር ያዩት ሁሉ ከበረከቱ ጠግበዋልና ያዩት ሁሉ የውበትን መጨረሻ አይተዋልና ያዩት ሁሉ ፍቅሩ በልባቸው ተነድፎ ቀርቶላቸዋልና ያዩት ሁሉ ከዚች ሃላፊ ብርቅርቅ አለም መለየትን አግኝተዋልና አንተም፦ ጌታን ታየው ዘንድ ወደጌታ ሂድ በእግረ ንስሃ ወደ ልብህ መቅደስ ተመለስ፡፡
(#አረጋዊ_መንፈሳዊ)

"ልቡ ጠቢብ የሆነ አስተዋይ ይባላል፥ በከንፈሩም ጣፋጭ የሆነ ትምህርትን ያበዛል። ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው። የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል። ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።"
📜(መጽሐፈ ምሳሌ፡ 16፥21-24)📜
📜(መጽሐፈ ምሳሌ፡ 16፥21-24)📜
➖ #ቃል (እውነተኛ ቃል• • •) ➖
⚡️በአንድ ወቅት አንድ ንጉሥ ብርዳማ በሆነ ምሽት ከጉብኝት ወደ ቤተ መንግሥት ሲገባ ድንገት አንድ ቀልብን የሚስብ ነገር ይመለከታል። አንድ ሰው ለራሱ በብርድ ተቆራፍዶ ነገር ግን ከጎኑ ላለው ውሻ ልብስ አልብሶት ይመለከታል። በዚህ ጊዜ ንጉሡ በጣም በመገረም ወደ ሰውየው ተጠግቶ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦
⚡️"በዚህ ቀዝቃዛ በሆነ ምሽት ከሰው በተሻለ ብርድን የመቋቋም ተፈጥሯዊ ችሎታ ላለው ለዚህ ውሻ ልብስህን አልብሰህ አንተ ግን በብርድ ትሰቃያለህ? ምንድነው እንዲህ ያደረግከው?? አለው።
⚡️#ሰውየውም፦ ጌታዬ እኔ እንደርሶ ያሉ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁኝ ከውሻው በተሻለ ስለህመሜ፣ ችግሬና ቁስሌ ባጠቃላይ ስሜቴ የመናገር ተፈጥሯዊ ችሎታ አለኝ፤ ነገር ግን ይህ ውሻ ሲያመውም ሆነ ሲበርደው አፍ አውጥቶ ስሜቱን እንኳን መግለጽ አይችልም ለዚህ ነው ያለችኝን ልብስ ያለበስኩት ብሎ መለሰ።
⚡️#ንጉሡም፦ የሰብአዊነትን ጥግ በተግባር በማየቱ በጣም እየተደነቀ ከጠባቂዎቹ አንዱን ወታደር ጠርቶ ለሰውየው ብርድ ሊቋቋም የሚችል ወፍራም ልብስ እንዲያመጣለት ትእዛዝ አስተላልፎ እየተደነቀ ወደ ቤተ መንግሥቱ ገባ።
⚡️ሰውየው በንጉሡ ንግግር በጣም ተደስቶ የሚመጣለትን ብርድ የሚከላከል ልብስ በጉጉት መጠበቅ ጀመረ። ነገር ግን ትእዛዙ የተሰጠው ወታደር የንጉሡን ትእዛዝ ረስቶት ልብሱን ሳያመጣለት ቀረ።
⚡️በነጋታው ንጉሡ ያህን ሩህሩህ ሰው ለማየት ወደ ደጃፍ ሲወጣ ያ ቅን ሰው ትናንት ትተውት ከሄዱበት ቦታ ሞቶ አገኙት። ንጉሡም ካጠገቡ አንድ ብጣሽ ወረቀት ላይ የተጻፈ መልእክት አገኘ ጽሑፉም እንዲህ ይል ነበር፦
⚡️"ንጉስ ሆይ! እኔ ለብዙ ዓመታት ብርዳማ ለሊቶችን መቋቋም እችል ነበር። ነገር ግን እርሶ በማይፈጽሙት ቃል የተነሣ የኔን ብርድ የመቋቋም ኃይሌን ነጠቀኝ፤ ስለዚህ ንጉሥ ሆይ!! እኔስ አንድ ግለሰብ ነኝ ነገር ግን እርሶ የሚመሩት ህዝብ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የገቡለትን ቃል የማትፈጽሙለት ከሆነ በእርሶ ላይ ያለውን እምነት ሊሸረሽረው ይችላልና ለማይፈጽሙት ነገር ቃል አይግቡ፤ ከገቡም ቃሎትን አይጠፉ" ሚል ጽሑፍ ነበር።
✔ይህንን ታሪክ ሳነብ ከሰሙ ባሻገር የወርቁ መልክት ጎልቶ ታየኝ ሰሙ "የማንፈጽመውን ቃል አንግባ" ሲሆን ወርቁ ደግሞ "የቃል ኃያልነት ምን ያህል እንደሆነ..." የሚገልጽ ነው።
"ልቡ ጠቢብ የሆነ አስተዋይ ይባላል፥ በከንፈሩም ጣፋጭ የሆነ ትምህርትን ያበዛል። ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው። የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል። #እውነተኛ_ቃል_የማር_ወለላ_ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።"
(መጽሐፈ ምሳሌ፡ 16፥21-24)
- ሁሉም ነገር ከቃል ይጀምራልና፥ ሰውን እንዳንጎዳ በቃላችን እንኑር።

✝የሕይወት ዘመን ምክር
#ልጅ፡ አባቴ ምን ዓይነት ሥነ ምግባር ቢኖረኝ ደስ ይልሃል?
#አባት፡ ልጄ! እንደ ውኃ ሁን፣ ባስቸገረ ጊዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈለገ ጊዜ ግን ዛፍ ማሳደጉን አይተውምና፤ እንደ ጨውም ሁን፥ ምግብን ያጣፍጣልና፣ ቢፈለግም በቀላሉ የሚገኝ ነውና።
#ልጅ፡ እሺ አባቴ እንዳልሆንስ የምትፈልገው የለም?
#አባት፡ ልጄ ሆይ! እንደ መርፌ አትሁን የሌሎችን ብዙ ቀዳዳ እየደፈነ የራሱን አንዷን መድፈን አይችልምና፤ እንደ መቋሚያም አትሁን ለሌሎች መደገፊያ እየሆነ ለራሱ ግን መቆም አይችልምና፤ አደራህ እንደ ደወልም አትሁን! ከሁሉ ቀድሞ ነቅቶ ሌሎችን ለቅዳሴ ቢቀሰቅስም እርሱ ግን ቤተመቅደስ ገብቶ አያስቀድስምና፡፡
⏱ቅዳሜ፦ ፴• ፲፪• ፳፻፲፪ ዓ•ም•
በመምህር ክብሮም ካሳ