✨✨✨✨ ህያብ ✨✨✨✨
ክፍል 28
ፀሃፊ ረምሃይ
ሃበን ቢበሳጭም ህያብ ሙሉ ሃሳባ አሃዱ ጋር ስለነበር ምንም አላስተዋለችም በደመነብስ ወደ አሃዱን መከተል ስትጀምር ሃበን ከኃላ እጇን ያዛት። ያምሻል እንዴ እኔ እዚ ቆሞ ሌላ ወንድ ላይ ማፍጠጥሽ ሳያንስ ልትከተይው አማረሽ አላት ህያብ እየተበሳጨች ኡፍፍፍፍ አሁንስ የሰለቸኝ ያንተ ድራማ ነው ተወይ በቃ አቦ ብላ እጇን አስለቅቃው ጥላው ወደዶርሟ ሄደች።
ህያብ በጣም ደክሟት ስለነበር ዶርም እንደገባች አልጋዋ ላይ ዝርር ብላ ተኛች አሃዱን የት እንደምታውቀው ትልቅ እንቆቅልሽ ሆኖባታል ሆኖም ግን ምንም ሊመጣላት አልቻለም። ድካሙ በእንቅልፍ ሸለብ እያደረጋት እያለ በሩ ብርግድ ተደርጎ ተከፈተ ህያብ በድንጋጤ ብንን አለች። ፀጥ ያለ ሰላም ሰፍኖበት የነበረው ዶርም በአንዴ የቀለጠው መንደር ሆነ ሶስቱ ጓደኞቿ እየተሳሳቁ ወደውስጥ ገቡ። ረቂቅ ህያብ ቀድማቸው መግባቷን ስታይ አንቺ ማታ የት ጥለሽን ተሸበለልሽ ባክሽ አለቻት። ህያብ እንደማኩረፍ እያለች እናንተ ናችሁ እንጂ ጥላችሁይ የሄዳቹት አለቻቸው ምን ጥለንሽ እንሄዳለ ያ ባልሽ ነዋ ከነጋ ነች ብሎ ሲጎፈጥጥ ያስደበረን አለቻት ፌቨንም የሆነ ነገር ትዝ እንዳላት ወይ...ኔ ህያብ እኮ ውርደትሽ ትናንት ከሃበን ጋር ክለብ ውስጥ ስትሳሳሚ ማን ቢያይሽ ጥሩ ነው ሚኪ ራስታው ያ... ቢዝነስ ካምፓስ ያለው ባልሽ... የሌለ ቦግ ብሎ ነው የነቀለው አለቻት ህያብ እንደማፈር እያለች ወይኔ...ጉዴ እያለች ከት ብላ ሳቀች ረቂቅና ፌቨንም አብረዋት ሳቁ። ተይው ባክሽ ድሮንም ደብሮኛል እሱ አለቻት። ሶስቱም የህያብ አልጋ ላይ ተደርድረው ስለአዳራቸው እያወሩ እያለ የተቀሩት የዶርማቸው ልጆች ነጠላቸውን እንዳጣፉ ከቤተክርስቲያን አስቀድሰው ሲመለሱ ተገጣጠሙ ሲሳሳቁ የነበሩት በአንዴ ዝም አሉ። ግዴታ ሆኖባቸው እንጂ ከነሱ ጋር አንድ ላይ ባይሆኑ ምንኛ ደስ ባላቸው። አለባበሳቸው፤ አኳኃናቸው፤ አነጋገራቸው፤ ሙዳቸው ምንም አይገጥምም ቢሆንም ግን አንድ ዶርም ውስጥ ናቸው። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ሆኖ አንዷ መንፈሳዊ ቦታ ስትሆን ሌላኛዋ ስትጨፍር ስትሳከር ትገኛለች። እነሱ ባሉበት ምንም ነገር ማውራት ስላልፈለጉ ሁሉም ወደየአልጋቸው ሄደው ተኙ የለሊቱ አዳር አድክሟቸው ነበር። ዶርሙ ዳግም ወደነበረበት ፀጥታ ተመለሰ።
.........................................
ርሻን ዶርሟ እንደገባች ማልቀስ ጀመረች የምታለቅሰው ግን ለራሷ ሳይሆን ለጓደኛዋ ነበር። ከልጅነቷ ጀምሮ የምታውቃት አብሮአደግ ጓደኛዋ ህያብ አሁንም ፊት ትነሳታለች ድሮ የነበራትን ቀና አመለካከትና የዋህነቷን በደምብ ታውቃለች አሁን ግን መስመሯን ስታ በሌላ የህይወት.መንገድ ላይ እንደሆነችም ታውቃለች በዚህ ከቀጠለች መጨረሻው እንደማያምርም ታውቃለች። አንድ አፈር ፈጭተው አንድ ጭቃ አቡክተው ተጫውተው ስንት ነገር አሳልፈው እንዳላደጉ አሁን ላይ አይንሽም ለአፈር ተባባሉ። ርሻን የማንም ጥፋት ቢሆን ይህ ፀብ ከዚ በላይ መቀጠል እንደሌለበት እናም ልትታረቃት ወሰነች የድሮ ጓደኛዋ ናፍቃታለች። ስልኳን አወጣችና ደወለች ከሌላኛው በኩል ስልኩ ተነሳ ሜሮን ነበረች። ርሻንና ሜሮን ባይጣሉም ህያብ ጋር ከተጣሉ በኃላ እንደበፊቱ አልነበሩም ተራርቀዋል ሲገኑ ግን ያወራሉ። ሰላም ነው ርሹ እንዴት ነሽ ጠፋሽ እኮ በጣም አለቻት አለው ያው ክላስ ቢዚም አይደለን አለቻት ሜሮን እየሳቀች ገና ክላስ መች ተጀመረና ዛሬ አደል እንዴ መግቢያው ብላ ለማስተባብያ የሰጠቻትን መልስ እየሳቀች ውድቅ አደረገችባት። ርሻንም እየሳቀች ይልቁንስ እሱን ተይውና መቀሌ አልመጣሽም እንዴ አለቻት። አልመጣሁም ባክሽ ገና ምዝገባ ሲጀመት ነው ምመጣው ምነው ሁሉ ሰላም? አለቻት። አው ሁሉ ሰላም ነው ሜሪዬ በቃ ስትመጪ እማወራሽ ነገር አለኝ ደውይልኝ መቀሌ ስትመጪ አለቻትና ተሰነባብተው ስልኩ ተዘጋ።

✨✨✨✨ ህያብ✨✨✨✨
ክፍል 29
ፀሃፊ ረምሃይ
ዳግም ተመልሻለው ፀሃፊው ነኝ ረምሃይ... በክረምቱ ብርድ ተቀዛቅዞ የነበረው አሪድ ካምፓስ ተማሪዎቹ ከያሉበት ብቅ ብቅ ሲሉ ዳግም ሞቅታው ማንስራራት ጀመረ። መቀሌ ከመጣው ሳምንት ቢሞላኝም ግቢ የመጣው ቀን ብቻ ነበር የሄድኩት። ከተማ ቡቲክ እየከፈትኩ ስለነበር ትንሽ ተጨናንቄ ነው የከረምኩት ከጓደኞቼ መሃል ማንንም ያገኘሁት አልነበረም ከኖሊ በስተቀር(በሌላኛው ታሪክ የምታውቋት)።
በአንደኛው ቀን ሱቄን ቀኑን ሙሉ ሳስተካክል ውዬ ድካም ተጫጭኖኝ ወደማታ ላይ ሱቁን ዘጋግቼ ልወጣ ስዘጋጅ አራት ሴቶች ተንጋግተ ገብተው የእራት ቀሚሶች ማየት ጀመሩ። ደክሞኝ ስለነበር ብዙም ልብ ብዬ አላየኃቸውም። ከአራቱ አንዷ እንዴ ረምሃይ አለችኝ ስሜን ወደጠራችው ልጅ ሳይ አውቃታለው! ሰላም ነው ህያብ? አልኳት ደና ነኝ እዚ ምን ትሰራለህ አለችኝ ግራ በመጋባት ስሜት። አዲስ የከፈትኩት ሱቅ ነው አልኳት ዳግም አገኛታለው ብዬ ስላላሰብኩ አስገረመኝ። ኦ...ውውው አሪፍ ነዋ discount በደምብ ነዋ ሚደረግልን ብላ ፈገግ አለች ከጓደኛቿ ጋር እየተያየች እኔም ፈገግ እያልኩ ያው ፀባያቹ ታይቶ ነዋ አልኳቸው። ውይ ተዋወቃቸው ጓደኞቼ ናቸው አለችኝ ሶስቱም በየተራ ስማቸውን እየነገሩኝ ተዋወቅን ፌቨን ረቂቅ ህይወት አሉኝ። ምነው ታዲያ ከመሸ ልወጣ ስል መጣችው አልኳት ኦው ልትወጣ ነበር እንዴ አለችኝ። አይ ችግር የለውም እምታዩትን እዩና ስትጨርሱ ወጣለው ያው ደምበኛ ንጉስ አይደል አልኳት። እነሱም እንደደከመኝ ገባቸው መሰለኝ ትንሽ ልብሶቹን ካዩ በኃላ በድጋሚ እንደሚመጡ ነግረውኝ ሄዱ ህያብንም ተሰናበትኳት። ከወጡ ትንሽ ቆይታ በኃላ እኔም ቆላልፌ ከፎቁ ስወርድ እታች አስፓልቱ ዳር ቆመው አገኘኃቸው። ከህያብ ጋር አይን ለአይን ተገጣጠምን ምነው? አልኳት ባክህ ኦቨር ልንወጣ ብለን ወዴት እንደምንሄድ እያሰብን ነው አለችኝ። ምንም እነሱ ላይ መፍረድ ስላልፈለኩኝ አይ ጥሩ ነው ብያቸው ልሄድ ስል ለምን ከኛ ጋር አቶቭርም አለችኝ። አይ ይቅርብኝ ሌላ ግዜ አልኳት። እየሳቀች አረ አይታካብድ አለችኝ እኔም እየሳቅኩ እውነት ህያብ ዛሬ ደክሞኛል ሌላ ግዜ ይደረግልኝ ይልቁንም ራሳችሁን ጠብቁ አልኳቸውና ድጋሚ ቻው ብያቸው ወደ ግቢ ሄድኩ።
ግቢ እንደደረስኩ ምን እንዳነሳሳኝ ባላውቅም ቢመሽም የናፈቀኝን እንዳኢየሱስ ቤተክርስቲያን ልሳለም ሄድኩ። የአሪድ ግቢ ሁሉ ነገሩ ይናፈቃል። ቤተክርስቲያን እንደገባሁ ፀሎት አድርጌ ከአንድ ጥግ ላይ ቁጭ ብዬ መመሰጥ ጀመርኩ ከኔ በቅርብ ርቀት ላይ ጨለማ ውስጥ ያለ አንድ ሰው ዳዊት ሲደግም ይሰማኛል።
በግምት ሰላሳ ደቂቃ ያክል ከተቀመጥኩ በኃላ ተነሳውና ተሳልሜ ልሄድ ስል ረምሃይ? የሚል ጥያቄ መሰል ድምፅ ከኃላዬ መጣ የጠራኝን ሰው ለማየት ዞርኩ። ሰላም ነው ረሙ የድሮ ጓድ እንዴት ነህ ባክህ አለኝ ልጁን አላወቅኩትም ግራ ተጋባው። አላወቅከኝም? አሃዱ ነኝ እኮ የልጅነት ጓደኛህ ያኔ ናዝሬት እያለን ወደ ባህርዳር ሳልሄድ በፊት አለኝ። ወዲያው የልጅነት ምስሉ ከፊቴ ብልጭ አለ እንዴ... ሰላም ነው አሃድ እንዴት ነህ ባክህ እዚ ግቢ መሆንክን አላወቅኩም ነበር የሚገርም አጋጣሚ ደና ነሃ? በጣም ተጠፋፋን የሌለ ተለውጠሃል አልኩት። እኔ አሃዱን እማውቀው ልጅ እያለን ለሁለት አመታት ብቻ ነው የባህርዳር ልጅ ነው አባቱ በስራ ምክንያት ከባህርዳር ወደ ናዝሬት ሲዘዋወር ከቤተሰቡ ጋር መጣ ከዛም ከሁለት አመት ቆይታ በኃላ ተመልሰው ወደባህርዳር ሄዱ ታዲያ በዚያች ሁለት አመታት ውስጥ ጥሩ ጓደኛሞች ነበርን።
እዛው እንዳእየሱስ ቤተክርስቲያን ቁጭ ብለን ቢጨልምም የልጅነት ትዝታችንን እያወራን ብዙ ቆየን። አሃዱ ድንገት የእጁን ሰአት አየና 05፡00 ሰአት ሆኗል ረምሃይ አንድ ነገር ላስቸግርህ ለከተማው አዲስ ነኝ አንዴ ከተና ደርሰን መምጣት እንችላለን አለኝ። በዚ በእኩለሊሊት? ጥያቆው ያልተለመደና እንግዳ ነገር ሆነብኝ። ምነው በሰላም መሽቷል እኮ ነገ እሚደርስ ነገር አይደለም አልኩት። አይ አይደለም እባክህ እንሂድ አለኝ ተነስ እንዳይረፍድ አለኝ ግራ እየተጋባው ምኑ ነው ሚረፍደው አልኩት ይበልጥ ግራ እየገባኝ መልስ አልሰጠኝም ተነስቶ ተሳለመና በፍጥነት መገስገስ ጀመረ ባህሪው እንግዳ ስለሆነብኝ ዝም ብዬ ተከተልኩት ። ከቤተክርስቲያን ወጥተን በከነአን በአፍሪካ ዶርሞች አድርገን ወደ ግቢው በር በፍጥነት ተጓዝን።
ልክ የግቢው በር ጋር እንደደረስን ኮንትራት ባጃጅ አጊንተን ወደከተማ መጓዝ ጀመርን አሃዱ በተደጋጋሚ ሰአቱን እያየ ባለባጃጁን በፍጥነት እንዲነዳ ይነግረዋል። ምን ሆነህ ነው ብለውም ምንም መልስ ሊሰጠኝ ፈቃደኛ አልሆነም ነገሩ ይበልጥ ግራ እያጋባኝ መጣ። ልክ ባጃጁ ታክሲዎች የሚያቆምበት ቦታ ላይ ሲደርስ መቶ ብር ሰጥቶት መልስ እንኳን ሳይቀበለው በፍጥነት ወጥቶ ወደ 16 ቀበሌ የጭፈራ ቤቶች አቅጣጫ መሮጥ ጀመረ እኔም ወርጄ እየሮጥኩ ተከተልኩት። 16 ውስጥ ለውስ አንዴ በቀኝ አንዴ በግራ እየታጠፈ ፍጥነቱን ጨምሮ ሮጠ እየጮህኩ ብጠራውም አልሰማኝም። በስተመጨረሻ አንድ ከአይን ሰወር ያለ ጨለማ አከባቢ ሰብሰብ ብለው የቆሙ ወንዶች ጋር ደርሶ አንደኛውን ገፍትሮ ስጥለው አየው ደንግጬ ከቦታው ስደርስ እነኛ የተሰበሰቡት ወንዶች የሆነችን ልጅ ሊደፍሯት እየቷገሏት እንደሆነ ገባኝ አንደኛ አ ፏን እና እጇን ግጥም አድርጎ ይዟት ቀሚሷን ሊያወል እየታገለ ነው። በጣም ተናደድኩ ማንም ሴት ብትሆን እንዲህ ልትደረግ አይገባም ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ልክስክስ ውሻ ብቻ ነው። አሃዱ ከሌሎቹ ወንዶች ጋር ሰጣገባ ጀምሯል ዘልዬ ሄጄ ልጅቷን ጥፍንግ አድርጎ የያዛትን ወንድ አሽቀንጥሬ ገፈተርኩትና ልጅቷን አስለቀቅኩት መልኳን ሳያት ማመን አልቻልኩም ደነገጥኩ ቅድም ራስሽን ጠብቂ ብያት የሄድኳት ህያብ ነበረች። የገፈተርኩት ልጅ ድጋሚ ከወደቀበት ተነሳ!
ውድ ቤተሰቦቻችን እንደተለመደው አብሮነታችው አይለየን ቻናላችንን ለጓደኞቻችው ሼር በማድረግ እንዲቀላቁሉ አድርጉልን ህያብ ክፍል 30 ይቀጥላል እስከዛው share & like
@monhappy
@BINCJ90

ክፍል 30
ፀሃፊ ረምሃይ
...አሃዱ ከሌሎቹ ወንዶች ጋር ሰጣገባ ጀምሯል ዘልዬ ሄጄ ልጅቷን ጥፍንግ አድርጎ የያዛትን ወንድ አሽቀንጥሬ ገፈተርኩትና ልጅቷን አስለቀቅኩት መልኳን ሳያት ማመን አልቻልኩም ደነገጥኩ ቅድም ራስሽን ጠብቂ ብያት የሄድኳት ህያብ ነበረች። የገፈተርኩት ልጅ ድጋሚ ከወደቀበት ተነሳ!
ህያብን ወደኃላዬ አደረግኃትና ልጁን ለመደባደብ ከፊቷ ቆምኩ እጁን ሲሰነዝር በክንዴ መለስኩትና ጉሮሮውን በኃይል መታሁት ልጁ መተንፈስ አቅቶት አንገቱን እንደያዘ እያቃሰተ መሬት ላይ ወደቀ።
በጣም ተናድጃለው እንደ እንስሳ የሚያስብን ሰው እንደ ሰው በውይይት ችግሩን ልትፈታ አትችልም በሚገባው ቋንቋ ታናግረዋለህ እንጂ። ወደ አሃዱ ስዞር አሁንም እየተደባደበ ነው እሱን ለማገዝ መንደርደር ስጀምር ማነህ አንተ እዛጋ አሉ የሆኑ ሰዎች ስዞር የለሊት ሮንድ ፖሊሶች መሆናቸውን አየው። እርዱን ሌቦች ናቸው ብዬ ጮህኩ ፖሊሶቹ በፍጥነት ሲመጡ ልጆቹ ከአከባቢው ሮጠው አመለጡ ፖሊሶቹም ተከትለዋቸው ሮጡ። ውጥረቱ ትንሽ ረገብ ሲል ወደ ህያብ ዞርኩ ጥግ ላይ ከዛፍ ስር ሆና በሰቀቀን እያለቀሰች ነው። ወደሷ ጠጋ አልኩና ክንዷን ያዝ አድርጌ ላረጋጋት ስል በፍርሃት ወደኃላ ሸሸችኝ። አይዞሽ ህያብ ረምሃይ ነኝ እምጎዳሽ ሰው አይደለሁም አልኳት ማልቀሷን ልታቆም አልቻለችም። አይዞሽ ህያብ ያው አንዳንድ ግዜ እንደዚህ አይነት.ነገር ያጋጥማል ጠንከር በይና ራስሽን ለማረጋጋት ሞክሪ ያልፋል አልኳት። ትንሽ ግዜ ዝም ካለች በኃላ ራሷን ማረጋጋት ጀመረች። ወደኃላ ዞሬ አሃዱን ልጠራው ስል የለም! ወዴት እንደሄደ ግራ ገባኝና ዞር ዞር እያልክ ማየት ጀመርኩ የለም! ወዴት ጥሎኝ እንደሄደ ግራ ገባኝ። ወደመታጠፊያው ጋር ሄጄ ላየው ስል ህያብ እባክህን ጥለኀኝ እንዳትሄድ አለችኝ። እንዳትፈራ ብዬ ወደሷ ተመለስኩ። ጓደኞችሽስ ብዬ ጠየቅኳት። አላውቅም ብቻ አንድ ላይ እየጠጣን ነበር ክለብ ውስጥ የሆነ ሰአት ላይ ወደራሴ ስመለስ የማላውቃቸው ወንዶች ከክለብ ይዘውኝ ወጥተው መንገድ ላይ ሊደፍሩኝ እየታገሉ ኝ ነበር አለችኝ። በግዜ ባንደርስላት ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቤ ሰቀጠጠኝ። ቆይ እናንተ ስትጠጡ እንኳን በልክ አድርጉት እንጂ ሲቀጥል ለምን እርስበርሳቹ አትጠባበቁም ጓደኛሞች አይደላችሁም አልኳት። ተወው ባክህ ስንወጣ ነው እንጂ ስንመለስ አንድ ላይ አይደለንም ጠዋት ዶርም ነው ምንገናኘው አለችኝ። በሰው ህይወት መፍረድ ስላልፈለኩ ምንም ሳልላት ወደግቢ እንሂድ አሁን አልኳት እሺ አለችኝና ከጨለማው አከባቢ ወጣን። ኮንትራት ባጃጅ ይዘን ወደ ግቢ ተመለስን። ቀስ እያልን ወደ ዶርም ወክ እያደረግን ነው ድንጋጤና ፍርኃቷ የለቀቃት ትመስላለች። አሁንም አሃዱ በዛ ጨለማ ወዴት እንደጠፋ እና እንዴት እሷ እዛ ቦታ ችግር ላይ እንደነበረች ማወቁ እንቆቅልሽ ሆኖብኝ ለመፍታት እየታገልኩ ብዙ ደቂቃዎች ዝም ብያት ነበር። ረሙ ቆይ አንተ ግን በዛ ሰአት እዛ አከባቢ ምን እየሰራህ ነበር ማለት ራሳችሁን ጠብቁ ብለኀን ወደ ዶርም ሄደክ አልነበር አለችኝ ከየት እንደደረስኩላት ጥያቄ ሆኖባት። አው ወደ ግቢ መጥቼ ነበር ቤተክርስቲያን ስሄድ ቅድም አብሮ ሲደባደብ የነበረውን ልጅ አገኘሁት አይተሽዋላ አልኳት ራሷን በአሉታ ነቀነቀች እሺ ካላየሽው ለማንኛው አሃዱ ይባላል እሱ ነው እንዴት እንዳወቀ አላውቅም ከግቢ እያሯሯጠ ይዞኝ አንቺ ወዳለሽበት ቦታ ያመጣኝ አልኳት። ግራ እየገባት ማለት እንዴት አወቀ! አለችኝ እሱ የኔም ጥያቄ ነው አልኳት። እንዲ እያወራን በግተራ ጋር ደረስን። ለማንኛውም ራስሽን በደምብ ጠብቂ ሁሉን በማስተዋል አድርጊ ጓደኞችሽንም ለዪ አልኳትና ተሰናብቻት ልሄድ ስል አመሰግናለው ረሙ አሃዱን ስታገኘው ንገረኝ ልተዋወቀው ፈልጋለው ታላቅ ባለውለታዬ ነው አለችኝ እሺ ቻው ብዬት ሄድኩ። ሰአቴን አየሁት 07፡45 ይላል በጣም ደክሞኛል በዚህ ሰአት የሚታየኝ ዶርም ገብቼ ጥቅልል ብዬ መተኛት ነው። ፈጠን ፈጠን እያልኩ እየተራመድኩ ወደ ዶርሜ አቀናው ልክ ብሎኩ ጋር ስደርስ አንድ ሰው በሩ ጋር ቆሟል ምንም ግድ ሳይሰጠኝ ወደ ውስጥ ልገባ ስል ረምሃይ ህያብ በሰላም ገባች አለኝ። ከድምፁ አሃዱ መሆኑን ለማወቅ ግዜ አልፈጀብኝም። ዞርኩና ወዴት ሄደህ ነው አንተ! ፖሊሶቹ ልጆቹን ካባረሯቸው በኃላ ወዴት እንደጠፋህ አላየሁም ስፈልግህ የለህም ስልክህን እንዳልደውልም ስልክህ የለኝም አልኩት። አው ወደ ግቢ መጣው አለኝ። እየተበሳጨው እንዴት በዛ ሰአት አብረን መጥተን ጥለኀኝ ትሄዳለህ አልኩት። ይቅርታ! ህያብ እንድታየኝ ስላልፈለግኩ ነው አለኝ። ለምን! አልኩት ሌላ ቀን ነግርሃለው አለኝ። እና ደሞ እንዴት ነው እሷ እዛ ቦታ ችግር ላይ እንዳለች ያወቅከው አልኩት። እሱንም ሌላ ቀን ነግርሃለው አሁን ደክሞሃል ግባና ተኛ ስለትብብርህ አመሰግናለው አለኝ። በማያገባኝ ጉዳይ ብዙ ልጨቃጨቀው ስላልፈለግኩ በቃ ስላም እደር አልኩትና ወደ ዶርሜ ገብቼ ተኛው።
ውድ ቤተሰቦቻችን እንደተለመደው አብሮነታችው አይለየን ቻናላችን ለጓደኞቻችው ሼር በማድረግ እንዲቀላቁሉ አድርጉልን ህያብ ክፍል 31 ይቀጥላል እስከዛው Share Like
ሀሳብ አስተያየት @BINCJ90 ላይ ይፃፉልን ህያብ ድርሰትን የምናዘገይበት ምክንያት ተፅፉ ስላላለቀ መሆኑን ለማሳሳብ እንወዳለን

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ህያብ
ክፍል 31
ፀሃፊ ረምሃይ
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
የተወሰኑ ቀናት አለፉ....
የአሪድ ጊቢ መደበኛው የትምህርት ጊዜ ተጀመረ። ለረጅም ጊዜ ያልተገናኙት ርሻን እና ሜሮን በተደዋወሉት መሰረት ተገናኙ። ርሻን የህያብ ነገር ያሳሰባት ትመስላለች ሜሮንም አፍ አውጥታ ባትናገር እንኳን ተመሳሳይ ስሜት ነበራት ምንም እንኳም አሁን ላይ ተጣልተው ባይነጋገሩም ዘውትር ህያብን ስታያት ያለችበት ሁኔታ ያሳስባታል ድሮ የነበሯትን መልካምነትና የዋህነቷን እርግፍ አድርጋ ትታ ፍፁም ሌላ ማንነትን ተላብሳለች
ከአመታት በፊት የምታውቃት ህያብ ላትመለስ ዳግም የሄደች መሰላት። ሜሮን እና ርሻን እንደድሮዋቸው ዲያና ላውንች ቁጭ ብለው ፓስታ በእንጀራ እየበሉ ለረጅም ጊዜያት የተጠፋፉባቸውን አዳዲስ ነገሮች ያወራሉ... በመጨረሻም ርሻን የድሮ ጓደኝነታቸው አብሮነታቸው እንደናፈቃት ህያብ እንደናፈቀቻት ግን አሁን ያለችበት መንገድ ጥሩ እንዳልሆነ እያሳሰባት እንደሆነና አሁን ያሉት ጓደኞቿም ጥሩ እንዳልሆኑ የሆነ መጥፎ ነገር ሳይደርስባት በፊት ሊያድኗት እንደሚገባ አውራቻት ። ሜሮን ይህንን ከርሻን ስትሰማ በጣም ደስ አላት የውስጥ ስሜቷን አውጥታ መናገር ስለማትወድ እንጂ እሷም ጋር ያለ ተመሳሳይ ስሜት ነበር። እንደው ምን ላርግሽ ርሹ አፌ ቁርጥ ይበልልሽ ሁሌም እማስበውን ነገር ነው የነገርሽኝ ርሹ... እኔም በጣም ናፍቃቹኛል ያ ድሮ አንድ ዶርም ሆነን እያወራን የምናመሽባቸው ለሊት አይኔ ላይ ው..ልልል ይላሉ። ህዩ ስትፍለቀለቅ በአይነህሊናዬ ትመጣለች በጣም ናፍቃኛለች ግን.... ግ...ን ምን ማድረግ እንችላለን ርሹ ህያብ አደለም ልታናግረን ልታየን እንኳን ፍቃደኛ ምትሆን አይመስለኝም መንገድ ላይ እየሄድን ከሩቅ ስታየን እንኳን ፊቷን አኮሳትራ ነው ምታልፈው እንዳት አግባብተናት እንደምናውራት አላውቅም አለቻት2 ለደቂቃ የነበረው አሪፍ ትዝታዋ አሁን ባለው መጥፎ ሁኔታ መተካቱን እያስተዋለች። ችግር የለውም ሜሪ አንቺ እሺ በይኝ እንጂ እንደምንም እንመልሳታለን እንደድሮዋችን መሆን እንችላለን አለቻት። ሜሪ ደስ ብሏት ርሻንን አቀፈቻት። በይ ተነሽ እና ወደ ክላስ እንሂድ ተባብለው ተነሱ።
...............................................
ህያብ ከሰሞኑን በደረሰባት ድንገተኛ ነገር ቀዝቀዝ ብላለች ምን እንደተፈጠረ ለማንም ምንም ነገር አልተናገረችም። ከብዙ ግዜ በኃላ ህይወቷ ወዴ እያመራ እንደሆነ ቆም ብላ እያሰበች ነው። እንደወትሮው ከጓደኞቿ ጋር ከመሆን ይልቅ ብቻዋን ሆና ምሳ እየበላች ስላሳለፈችው ህይወት እና ስለጓደኞቿ ታስባለች። የእውነት ጓደኞቿ ሳይሆን ጓደኝነታቸው ከአንገት በላይ እንደሆነ የገባት ይመስላል ግራ በሚያጋባ በመንታ መንገድ ላይ የቆመች መስሎ ታያት። ለረጅም ግዜ ትክዝ ብላ እንደቆየች የሆኑ ሴቶች እየተንጫጩ ሲመጡ አየች ከሰላሟ የበጠበጧት መሰላት ጓደኞቼ የምትላቸው ፌቨን ረቂቅ ናቸው። ልክ እሷ ጋር እንደደረሱ አንቺ ምን ሆነሽ ነው ብቻሽን ምሳ ምትበይው ጥለሽን አለቻት ረቂቅ። አይ ምንም እንዲው ብቻዬን መሆን ስለፈለኩይ ነው አለቻት። ረቂቅ እየሳቀች ሰሞኑን ግን የሆነ ነገር ሆነሻል የዛን ቀን ኦቨር ከወጣን በኃላ ምንም ልክ አይደለሽም አለቻት። ህያብ አጭሯ ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠቻቸውን ወረቀቶችና ደብተር እያነሳች ዳህና ነይ ረቂቅ ምንም አልሆንኩም አሁን ክልስ ስለረፈደብይ ልሂድ ብላ በፍጥ ነት ተነስታ ቻው ብላቸው ሄደች።
ህያብ ክላስ ስትደርስ አስተማሪው ገብቶ እያስተማረ ጠበቃት። ስላረፈደች ቀስ እያለች ገብታ በአይኗ ባዶ ቦታ ሄዳ ተቀመጠች። ደብተሯን አስተካክላ ወደጎን ዞር ስትል ከአጠገቧ ያሉት ርሻን እና ሜሮን ነበሩ ሁለቱም እሷን እያዩ ፈገግ ሲሉ ህየብ ግን ገልመጥ አድርጋቸው እየተመናቀረች ወደ ደብተራ አቀረቀረች።
አስተማሪው ትምህርቱን አስተምሮ ጨርሶ ሲወጣ ህያብ በፍጥነት ደብተሯን እና ወረቀቶቿን አንድ ላይ አድርጋ ልትወጣ ስትል ርሻን ህየብ! ብላ ጠራቻት። ህያብ ዞር ብላ አየቻትና ኮስተር ብላ አይታት ምንም ሳትናገር ተነስታ ወጣች። ከዋይት ሃውስ መማሪያ ክላሶች ፀጥ ባለው የኮንልስቶን መንገድ ወደ ዶርማ በፍጥነት እየሄደች ህሊናዋ ዳግም ይወቅሳት ጀመር! የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማት ጀመር ርሻንን አስቀየምኳት እንጂ አላስቀየመችኝም ለምንድነው እንዲህ ምሆንባት ብላ ማሰብ ጀመረች ርሻን ከልጅነቷ ጀምሮ የምታውቃት አብሮ አደግ ጓደኛዋ ብትሆንም አሁን ባሉት በነ ረቂቅ ተክታታለች አእምሮዋ ይበልጥ ይወቅሳት ቀጠለ። ለምንድነው እንዲህ ምሆነው? ለምን መልካምነቴን አጣው? ለምን ከማይጠቅሙኝ ጓደኞች ጋር ግዜዬን አባክናለው? ጥያቄዎች ነጎዱ... ለራሷ እንኳን መመለስ የማትችላቸው ጥያቄዎች ነበሩ... አልቻለችም መንገድ ላይ እየሄደች እንባዋ ቀደማት እንደዥረት ታወርደው ጀመር እንባዋን መቆጣጠር አቃታት። በእጆቿ ከአይና የሚፈሰውን እንባ እየጠረገች ለማስቆም እየሞከረች ከዋናው መንገድ ወጥታ ከቨተርነሪ ቤተመፅሃት ጀርባ ቦሉት ቦታዎች ላይ ተቀምጣ ጉልበቷን ተደግፋት ማልቀሷን ቀጠለች።

ምን ሆነሽ ነው ምታለቅሽው? የሚል ጎርነን ያለ ድምፅ ከኃላዋ መጣ ደንገጥ እያለች ሳታየው እንባዋን እየጠራረገች ለመደበቅ ሞከረች። በጣም ከፍቷት ሄዳ ስትቀመጥ ከሌላ ሰው ፊት እንደተቀመጠች ገባት። ፊቷ እና አይኗ ቀላልቶ ሰው እንዲያያት ስላልፈለገች እሚያወራትን ወንድ ሳታየው ጀርባዋን እንደሰጠችው ምንም አልሆንኩም ትንሽ ስለከፋኝ ነው አለችው። አይዞሽ እናት ሁሉም ያልፋል እሺ ሊነጋ ሲል እንደሚጨልመው ለጠራ ሲል እንደሚደፈርሰው አንቺም ደስታሽ ከመምጣተ በፊት ሊከፋሽ ግድ ነው አላት። ለምን ልከፋ ሁሌ መደሰት ካለብኝ አለችው። ሁሌ ምትደሰች ከሆነማ የደስታን ጥቅም አታውቂውም ለዛ ነው አላት። ልጁ ያለው ነገር ስላልገባት ማለት ብላ ጠየቀችው አሁንም ጀርባዋን እንደሰጠችው ነው ልታየው አልፈቀደችም። ማለትማ ሁሌ የምትደሰች ከሆነ የደስታ ትርጉም ምን እንደሆነ አታውቂም አንዳንዴ የደስታን ትርጉም እንድታውቂ ሲባል መከፋት ግድ ይላል ሁለት የሚቃረኑ ነገሮች አንደኛው የሌላኛውን ህልውና ያጎላዋል ጨለማ ስላለ አይደል የብርሃንን ምንነት የምናውቀው። ስንታመም አይደል ጤነኛ በመሆናችን ማመስገን እንዳለብን የምናውቀው ለዛ ነው አንዳንዴ የምናዝነው መደሰት ምን እንደሆነ እንድናውቅ ስለሚፈለግ ነው አላት። በመልሱ ተገረመች ያልጠበቀችውና ለየት ያለ አመለካከት ነበር ልታየው ፈለገች ግን የፊቷን መበላሸት እንዳያይ ስለፈለገች አልዞረችም። ልጁ ቀጠለ አይዞሽ እሺ ህይወት እንደዚህ ናት ልክ እንደሰንሰለት ቀለበቶች... አንደኛው ቀለበት የማዘን ሌላኛው የመደሰት ሌላኛው የመናደድ ሌላም ሌላም ሁሉም አንድ ላይ ተያይዘው የህይወትን ሰንሰለት ይሰራሉ የግድ አንደኛው ጋር ለመድረስ ሌላኛውን ማለፍ አለብሽ። አንዳንዴ ህይወት ረግጣ ረግጣ እታች ልታደርግሽ ትችላለች አይክፋሽ! ምክንያቱም ከዛ በኃላ የምትጓዥው ወደ አንድ አቅጣጫ ነው እሱም ወደላይ መነሳት ብቻ ነው!። አላት ህየብ የዚህ ሰው ንግግር ውስጧ ዘልቆ ገባ በጣም ተገረመች ማንነቱን ልታውቅ ልታየው በጣም ፈለገች! ብዙ ካንገራገረች በኃላ ልታየው ወሰነች ወደኃላ ዞራ አየችው! ልጁ ቡኒ ኮፍያና ጥቁር መነፅር አድርጓል ማንነቱን ልትለየው ስላልቻለች ተናደደች። ማነህ ግን አለችው። አሃዱ እባላለው አላትና ከመቀመጫው ተነሳ ባሁኑ ሰአት ይህ ቦታ ከኔ የበለጠ ላንቺ ያስፈልግሻልና አልበጥበጥሽ ብሏ አልፏት መራመድ ጀመረ ህያብ ጥሏት እንዲሄድ አልፈለገችም! ግን ዝም አለች። ትንሽ ራመድ እንዳለ ቆመና መነፅሩን አውልቆ ሰላምሽ ይብዛ ደህና ሁኚ ህያብ ብሏት ሲሄድ ህያብ ደነገጠች። ስሜን እንዴት አወቀው ልጁን ከዚ በፊት ከርሻን ጋር ከቤተክርስቲያን ሲመለሱ አፍጥጣ ያየችው እንደሆነ አስታወሰች። አሃዱ ሲሄድ ተነስታ ልትከተለው ፈለገች ግን አልቻለችም። ድንገት የሆነ ነገር ጭንቅላቷ ውስጥ አቃጨለ "ካላየሽው ለማንኛውም አሃዱ ይባላል እሱ ነው እንዴት እንዳወቀ አላውቅም ከግቢ እያሯሯጠ ይዞኝ አንቺ ወዳለሽበት ቦታ ያመጣኝ" ረምሃይ ያላት አሃዱ እሱ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነች ለሷ ብቻ የተላከላት ጠባቂ መልአክ መሰላት። አ....ሃ...ዱ!!! ብላ እየጮኀች በፍጥነት ተነስታ ወደሱ ሮጠች።
ይቀጥላል ከተመቻችው ነበብ ነበብ አርጉና 👍
ሀሳብ አስተያየት @BINCJ90 ላይ ያድርሱን
@monhappy
ይቀጥላል ከተመቻችው ነበብ ነበብ አርጉና 👍
ሀሳብ አስተያየት @BINCJ90 ላይ ያድርሱን
@monhappy
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ህያብ
ክፍል 32
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፀሃፊ ረምሃይ
አ....ሃ....ዱ!!! ብላ እየጮኀች በፍጥነት ተነስታ ወደሱ ሮጠች። የኮብልስቶኑን መንገድ አቋርጣ ወደ አስፓልቱ ስትታጠፍ አሃዱ ከሁለት ሴቶች ጋር ቆሞ ሲያወራ አየችው። ሁሉቱም የምታውቃቸው ሴቶች ናቸው ርሻንና ሜሮን! ሩጫዋን ገትታ ባለችበት ቆመች። ልታወራው በጣም ፈልጋለች ግን የቀድሞ ጓደኞቿ መሰናክል ሆኑባት የቀድሞ ጥፋቶቿ እንዳትቀርበው አደረጋት ወደኃላ ማፈግፈግ ጀመረች.... ተደበቀች።
................................................
አሃዱ ህያብን አውርቷት ከሄደ በኃላ በዋናው የአስፓልት መንገድ ላይ ታጥፎ ሲሄድ ከርሻን ጋር ተገጣጠሙ ሰላም ተሻብለው ከሜሮን ጋር ካስተዋወቀችው በኃላ እያወሩ ወደ ዶርም መንገዳቸውን ቀጠሉ። አሃዱ ሰለሁሉም ቢያውቅም እንዳላወቀ ሆኖ ሁሉን እንደ አዲስ ማድረግ የዘውትር ልማዱ ነው። የተሰጠውን ስጦታ ለሰው ለማሳየት አይጥርም እውነቱን እሱና የላይኛው ብቻ ያውቁታልና። ርሻን ሜሮን እና አሃዱ የተወሰነ መንገድ አንድ ላይ እንደተጓዙ ሜሮን ወደ ርሻን ጆሮ ጠጋ እያለች ርሹ ሰውዬሽ ቆንጅዬ ነገር ነው ለምንድነው እስካሁን ያልጠበሽው አለቻት የለበጣ ሳቅ እየሳቀች። ርሻን ኮስተር እያለች ሆ.... አለች እየተሽኮረመመች በይ ስነስርአት አለቻት እያንሾካሾከች እጇን ጥብቅ አድርጋ ይዛት ሜሮን ርሻንን ስላሳፈረቻት ከት ብላ መሳቅ ጀመረች ርሻንን በደምብ ታውቃታለች ከወንድ ጋር ያላት ቀረቤታ በልኩ ነው ብዙም ሰው አታቀርብም። አሃዱ ፈገግ አለ ሜሮን ያወሩትን የሰማ መስሏት ደንገት አለች። መንገዳቸውን በኮሞሮስ ሱቆች በኩል አድርገው ወደ ባለመስታወቱ ዝነኛ ካፌ ህዳሴ አከባቢ ሲደርሱ ርሻን ሹክሹክታውን ለማስቀየር በማሰብ... ግቢውን እንዴት ነው ለመድከው መቀሌንስ እንዴት አገኘሃት አለችው። አሃዱ ፈገግ እያለ አሪፍ ነው ሁሉም እንደጠበቅኩት ነው መቀሌ ደስ የምትል ሃገር ናት አላት። ርሻን ቀጣይ ምን እንደምታወራ ግራ ገባት ዝም አለች.... መንገዳቸውን ወደ በግተራ ቀጠሉ
............................................
ህያብ ወደሃላ ከተመለሰች በጋላ እነ አሃዱን በቅርብ ርቀት እየተከተለቻቸው ነበር። ከሳዋ መንደር ጀምሮ በኮሞሮስ ታጥፈው በህዳሴ ካፌ ጋር አድርገው ሲሄዱ እሷም በተመሳሳይ መንገድ ትንሽ ራቅ ብላ ከኃላቸው ቀስ ትከተላቸዋለች... ሜሮን ከት ብላ ስትስ ውስጧ ተቃጠለ አሃዱን የምትቀማት መሰላት... ምን ያስገለፍጣታ እዋይ! ትላለች። ሶስቱም በግተራ ጋር ሲደርሱ ቆሙ! እሷም ባለች ቆማ ፊቷን ወደጎን አዙራ በጎሪጥ ታያቸዋለች። አሃዱ ርሻንና ሜሮንን ቻቅ ብሏቸው ሲሄድ ሜሮን አትጣፋ እሺ አሃዱ ቻ....ው! ስትለው አየች። እነ ርሻን ተያይዘው ወደ ዶርም ፊታቸውን አዙረው መሄድ ሲጀምሩ ህያብ ፈጠን ፈጠን እያለች አሃዱ ወደሚሄድበት አቅጣጫ አመራች።
...............................................
አሃዱ ከነ ርሻን ጋር ከተለያየ በኃላ የግራ እጁን ከፍ አድርጎ ያደረገውን ቡኑ ሌዘር ሰአት አየት አደረገና ፈጠን ፈጠም እያለ ከበግ ተራው ፊት ለፊት በምትገኝ ቀጭን ሰው የማይበዛባት መንገድ መሄድ ጀመረ ውጥ ለውስጥ እየተጓዘ የቴክኖ ላይብረሪ አከባቢ ሲደርስ የሆነሰው ከኃላ እጁን ያዝ! አደረገው ደንገጥ ብሎ ዞር ሲል ህያብ ናት።
ሰላም ነው? አላት። ህያብ አፏ ረሳሰረ ምን እንደምትለው ግራ ገባት.... እእእእ ሰ..ሰ..ላም ነው አ...አሃዱ ከ..ከቅድም ጀምሮ እየተከተልኩህ ነበር ይቅሬይታ አድርግልይ አንድ ቦታ ተቀምጠንስ ማውራት ንችላለን አለችው። አሃዱ ሰአቱን አየት አደረገና ይቅርታ ህየብ አሁን ማልቀርበት ጉዳይ አለኝ ወደዛ ልሄድ ነው ሌላ ግዜ እናውራ አላት። ህያብ ቅር ቢላትም አማራጭ ስለሌላት እሽይ ስልክህን ስጠይ አለችው። ይቅርታ ህያብ ቸኩያለው ስልኬን ከረምሃይ ውሰጅ በኃላ ታገኚዋለሽ አላትና ፈጠን ብሎ ሄደ ህያብ ተንተባተበች ልታስቆመው አልቻለችም... ቆ...ይ እ.ንጂይ ም.. ም..ን... አልጨረሰችውም እሱ ሄዷል። ወደዶርም መመለስ ጀመረች ቆይ ማነይ ነው ሚል እሱ ወለች እየተነጫነጨች ሄደች።
ይቀጥላል
ሀሳብ አስተያየት @BINCJ90
ላይ አድርሱን
ከወደዳችሁት Like እና Share አድርጉት መልካም ንባብ

ክፍል 33
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፀሃፊ ረምሃይ
ሰላም ዳግም ተመልሻለው ፀሃፊው ነኝ! ረምሃይ። አመሻሽ ላይ የመቀሌን ብርድ የምቋቋምበት ጃኬት አድርጌ ወደ በፕሮግራሜ መሰረት ቤተክርስተያን ልሄድ ተፍ ተፍ ስል ስልኬ ጠራ አንስቼ አየሁት የማውቀው ስልክ አልነበረም ። አረንጓዴውን ተጫንኩና ሄሎ አልኩ። ሰላም ነው ረሙ ህያብ ነይ አለች። ህያብ ትንሽ ያዝ በሚያረጋት አማርኛ አነጋገር ሁሌም አስታውሳታለው እሷ እንደሆነች ለማወቅ አልተቸገርኩም። ሰላም ነው ህያብ እንዴት ነሽ ስልኬን ደሞ ከማን አገኘሽው ብዬ ጠየቅኳት። አለሁ ረምሃይ ከመይ? ጠፊዕኻ እኮ አለችኝ አለው አለው አልኳት። ረሙ አንዲ ግዜ ላገይህ ፈልጌ ነበር ይመችሃል አለችኝ። አሁን ወደ እንዳየሱስ ልሄድ ነው ስመለስ ላግኝሽ አልኳት። ልምጣ አለችኝ ቶሎ የምትደርሺ ከሆነ ነይ ከነአን አከባቢ ጠብቅሻለው አልኳት። መጣው ብላኝ ስልኩ ተዘጋ። ልብሴን አስተካክዬ ስጨርስ ከዶርም ወጥቼ በሉሲ መንደር ቀስ እያልኩ ወክ እያደረግኩ አፍሪካን አልፌ ከነአን ላውንች አከባቢ ስደርስ መንገዴን ገትቼ ወደኃላ ዞሬ አየው። ምንም ነጠላ የለበሰች ሴት አትታየኝም። በእግሬ መሬቱን እየጠበጠብኩ አስሬ ሰአቴን እያየው ህያብን መጠበቅ ጀመርኩ። አሁንም አሁንም አላፊ አግዳሚውን እየታዘብኩ መጠበቄን ቀጠልኩ። ከቆይታ በኃላ ህያብ ደረሰች አጠር ያለ ጥቁር ቀሚስ ብቻ ለብሳለች ሳያት ክለብ ልትወጣ እንጂ ቤተክርስቲያን ልትሄድ አልመሰለኝም። ሰላም ስትለኝ የኔ እናት ቤተክርስቲያን ነው እሄዳለው ያልኩሽ አውቀሻላ! ምናልባት ጆሮሽ.... አው ሰምቼሃለው ባክህ አታካብድ አለችኝ። ተናደድኩ በይ በይ እንደዚ ሆነሽ ሄደሽ እንዳታስቀስፊኝ ነጠላ እንኳን ይዤልሽ ልምጣ አልኳትና ፈተን ብዬ ዶርም ሄጄ የጓደኛዬን ነጠላ ይዤላት መጣውና ለብሳ ወደ እንዳ እየሱስ መሄድ ጀመርን። እንግዲ እስከዛሬ ድረስ ህያብን ለሶስተኛና ለመጭረሻ ግዜ ያገኘኃት የዚህን ቀን ነበር። የእንዳ እየሱስን አለታማ ዳገት እየወጣን ባለፈው ስላጋጠማት ሁኔታና አሁን ስላለችበት ጠየቅኳት ደህና መሆኗን ነገረችኝ። ትዝ ሲለኝ... ለምንድነው ፈለግሽኝ ግን? አልኳት ምን ሊሆን እንደሚችል እያሰብኩ። ህያብ የአቀበቱ መንገድ አድክሟት ቁና ቁና እየተነፈሰች አይ እንዲው ንቀላል ገዳይ ነው አለችኝ እንቀመጥና ነግርሃለው አለችኝ። እኔም ዳገቱ አድክሞኝ እያለከለኩ ደረስኩ። ልክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስንገባ ፀሎት አድርን ስንጨርስ ከቤተክርስቲያኑ ጀርባ እንዳገኛት ተነጋገርንና ተለያይተን በየመንገዳዥን ሄደን። በቤተክርስቲያኑ በላይኛው በኩል ሄጄ ፀሎት አድርጌ ስጨርስ እንድንገናኝ ወደነገርኳት ቦታ ሄድኩ ቀድማኝ ሄዳ ቁጭ ብላ ጠበቀችኝ። እኔም ሄጄ አጠገቧ ከተቀመጥኩ በኃላ እሺ... ብዬ ወደ ገደለው እንድትገባ አደረኩ። እንትን ነይሩ ረሚዬ የ አሃዱን ስልክ እንድትሰጠይ ፈልጌ ነበር እናም ስለሱ አንዳንድ ነገሮች እንድትነግረይ ነበር አለችኝ። ከት ብዬ እየሳቅኩ ደሞ ከየት አገኘሽው እሱን ለዚ ነው እንዲ ላግኝህ ቅብርጥሴ ያልሽው እዛው ሳመጪ አያልቅም ነበር አልኳት። እሂ.... ነገርያ ቅድም እኮ አግኝቶይ ነው አሃዱ ማለት ባለፈው ያልከይ ቀይ ረዘም ያለ ፂማም ፀጉሩ ሉጫ ልጅ አይደል አለችኝ አው እሱ ነው አልኳት። ታዲያ ንገተኛ አለችኝ። በመጀመሪያ ስልኩ የለኝም ሲቀጥ.... አላስጨረሰችኝም እንዴ.... ለምን እሱ ራሱ እኮ ነው ካንተ ውሰጅ ያለይ ምንድነው አለችኝ። አይ ስልኩ የለኝም እንደሌለኝም እሱም ያውቃል እንደዛ ያለሽ ለሌላ ምክንያት ይሆናል። ለምን?። አላውቅም አልኳት።
የሆነ ነገር ትዝ ያለኝ መሰል.... አሃዱ ስልኩ እንደሌለኝ ያውቃል ለምን እኔ ጋር ላካት ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን?ራሴን ጠየቅኩ?። ህያብ ትንሽ የምትሄድበት መንገድ ልክ እንዳልሆነ ይገባኛል ግን... ግን ታሪኳን አላውቅም ምን እንዳሳለፈች አላውቅም ልፈርድባት አልፈልግም ግን ልመክራት ፈለኩ...
ህያብ ብዬ ጠራኃት ወዬ ረሚ አለችኝ። አሁን በምትሄጅበት የህይወት መስመር ከአምስት አመት በኃላ ራስሽን ምን አይነት ቦታ የምታገኚው ይመስልሻል አልኳት። አላውቅም አለችኝ። ታውቂያለሽ ህያብ ድሮ ልጅ እያለው በጣም ምስኪን እና መልካም ነበርኩ ነገር ፍን እዚ ግቢ ስገባ ብዙ እወዳቸው የነበሩ ስብእናዎቼን እያሳጣኝ መጣ ከዚ ግቢ የምጠላው ትልቁ ነገር ቢኖር ድሮ የነበረኝን ማንነት ገፍፎ አዲስ የማልፈልገውን ስብእናና ክፋት አስተምሮኛል ለዛም ያስጠላኛል አንዳንዴ ወደድሮ እኔነቴ ብመለስ እላለው.... ይህንን ሁሉ ሳወራላት ህያብ አጎንብሳ እየሰማችኝ ነበር በተቀመጠችበት ጉልበቷ ላይ ተደፍታ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች። አሃዱ ለምን ወደኔ እንደላካት ገባኝ!
ይቀጥላል
ውድ አንባቤዎቻችን ህያብ እንዲህ እንዲህ እያለ እዚህ ደርሷል የብዙሆቻችሁን ሀሳብ አንብቤዋለሁ ግን ለሁላችሁም መመለስ ስለማልችል በዚህ ልመልስላችሁ ህያብ ተፅፎ አላለቀም ለዛም ነው የምናዘገየሁ የፅሁፍን ነገር እንደምታውቁት ግዜ የሚፈልግ ነገር ነው ስለዚህ ለናንተ በተቻለን አቅም እናደርሳለን
መልካም ንባብ
ሀሳብ አስተያየት @BINCJ90 ላይ ይላኩልን ይደርሰናል

ክፍል 34
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፀሃፊ ረምሃይ
ህያብ ስታለቅስ ላባብላት አልሞከርኩም አንዳንዴ ተናግረናቸው የማይወጡልን ነገሮች በእንባችን ታጥበው እንደሚወጡ አምናለው። ህየብ ለተወሰነ ደቂቃ ስታለቅስ ከቆየች በኃላ እንባዋን በለበሰችው ነጠላ ጠራርጋ ዝም አለች። ጥያቄዬን ጀመርኩ። ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው አልኳት በጣም ከፋይ አለችኝ። ለምን ከፋሽ? ብዙ ያስቀየምኳቸው የበደልኳቸው ሰዎች አሉይ የድሮ እኔነቴ ናፈቀይ አለችኝ። ወደድሮ ማንነትሽ እንዳትመለሽ ምን ያዘሽ? አሁን ያለው ማንነቴና ጓደዮቼ... ኢሄ ጊቢ ሳልፈልግ ኩፉ አደረገይ ድሮ የነበረይን መልካም ስብእና አጠፋው አለችኝ።
ህያብ አውቃለው እኔና አንቺ ብዙም አንተዋወቅም ምናልባት እኔን በድሮው ማንነቴ ታውቂኝ ይሆናል የቀደመ ታሪኬንም ተውቂ ይሆናል በህይወት እስካለን ከመስመራችን እሚያስወጡን አንዳንድ አጋጣሚዎች ይኖራሉ እኔም መስመሬን ስቼ የነበረበት ረጅም ግዜ ነበር እስከቅርብ ግዜ እኔ ሌላ ሰው ነበርኩ ግን በህይወት አጋጣሚዎች የምትተዋወቂያቸው ጓደኞች ከአላማሽ የሚያስቱሽ ከመልካምነትሽ የሚያርቁሽ ቢሆኑም በዛው ልክ ደግሞ ወደ ቀደመ ማንነትሽ የሚመልሱሽም ጓደኞች ይኖራሉ እኔም እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ በእንዳንቺ አይነት መስመር ላይ ነበርኩ አንዲት ሴት እስከምተዋወቅ ድረስ... እሷ ለኔ መንገድ እንደሆነችልኝ ዛሬ ናይ እኔ ደግሞ ላንቺ መንገድሽ መሆን እፈልጋለው። ህያብ ስትባል ምን አይነት ልጅ እንደምትመጣልኝ ታውቂያለሽ... የድሮ እኔነቴን የምታስታውሰኝ ልጅ በአእምሮዬ ትሳላለች ባላውቅሽም ከምታወሪያቸው ነገሮች በመነሳት መልካም ስብእና ያላት ለሁሉም የምታዝን አይነት ሴት እንደነበርሽ መገመት አይከብደኝም ምክንያቱም እኔም ልክ እንዳንቺ ነበርኩ ግቢ ስገባ ምንም የማያውቅ ገራገር ልጅ ነበርኩ ነገር ግን በግዜ ሂደት ሰዎች ሲጎዱኝ መቀየር ጀመርኩ ክፋትን ተማርኩ ብልጥነት የበላይነት ይመስለኝ ጀመር የድሮ ማንነቴን ጥዬ አዲስ ስብእና ተላበስኩ ልክ እንዳንቺ... ታሪካችን ይመሳሰላል ለነገሮች ግድ አይሰጠኝም ነበር ግን የሆነ ሰአት ናይ ስነቃ እምኖረው ህይወት የውሸት እንደሆነ በአስመሳይ ሰዎች እንደተከበብኩ ገባኝ የዛኔ በውስጤ ግጭት ጀመረ የድሮ መልካምነቴ እና አሁን ያለው ማንነቴ ይጣረሱ ጀመር።
የአስመሳይነት ህይወት አቅለሸለሸኝ የዛኔ ወደቀደመ ማንነቴ መመለስ ጀመርኩ ግን ቀላል አልነበረም ወደኃላ ልትመለሽ ስትይ የሚይዙሽ ብዙ እክሎች አሉ ዋናው ደግሞ በአሁን ያለሽበት ጓደኞች ናቸው እንደድሮሽ ለመሆን ስትሞክሪ ይይዙሻል ይስቁብሻል ይፈትኑሻል ፋራ ትባያለሽ ሌላም ሌላም... እኔ ግን ልንገርሽ በአስመሳይነት አራዳ ከምባል ትክክለኛው እኔነቴን ይዤ ዘላለም አለም ፋራ ብባል እመርጣለው። ግን ያም ሆኖ ይህ ግዜው ይሄዳል ይረሳል ግዜ የሁሉም ነገር መድሃኒት ነው። አንቺም ጋር አሁን ያለው ጉዳይ ይህ ይመስለኛል የድሮ ማንነትሽ ይወቅስሻል አሁን ያለው ማንነትሽ ደግሞ ሁሉም ነገር አሪፍ እንደሆነ ይነግርሻል። የድሮ ጔደኞችሽን ስታዪ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማሻል አሁን ያሉትን ስታዩ ደግሞ አሪፍ እንደሆነ ይሰማሻል ግን ውስጥሽ ውሸት እንደሆነ ይነግርሻል... ህያብ አላስጨረሰችኝም እያለቀሰች ነበር። አው አው ልክ ነህ በጣም! ሰላሜን እያጣው ነው ምንም እረፍት የለኝም አለችኝ በአፅንኦት ። ከራስ ጋር ትጣልቶ ሰላም ከወዴት ይገኛል እረፍትስ ኬት የምታገኚ ይመስልሻል ከራስሽ ጋር ታረቂ የዛኔ ሰላምሽ ይመለሳል... ህያብ እኔ ይሄንን ስልሽ እኔ ጠንካራ ወይም ካንቺ የተሻልኩ ሰው ሆኜ አይደልም ገና ብዙ የሚጠብቀኝ ፈተና እንዳለ አውቃለው ግን አልፈራም የውስጥ ሰላምን እስካላጣው ድረስ ምንም ቢመጣ እንደማልፈው አውቃለው አንቺም ብዙ የሚጠብቅሽ ፈተና ይኖራል በመጀመሪያ የውስጥ ሰላምሽን ጠብቂ ከዛ የምታቀርቢያቸውን ሰዎች አስተካክይ ስትደክሚ የሚየበረቱሽን እንጂ አብረውሽ የሚወድቀትን አታድርጊ በተረፈ ሌላ ምን እልሻለው.... ብቻ ወደፊት በመልካሙ ጎዳና ላይ እንደማገኝሽ ተስፋ አደርጋለው አልኳት። አመሰግናለው ረሙዬ ብላ አቀፈችኝ። በቃ እንነሳና እንሂድ አልኳት እሺ ቆይ አንዴ ፀሎት ላድርግና እንሄዳለን አለችኝና ተነስታ ወደ ቤተክርስቲያኑ አፀድ ሄደች።
ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኃላ ፀሎታን ስትጨርስ ተሳልማ ከእንዳኢየሱስ ቤተክርስቲያን ወጣን። ቅድም እያለከለግን የወጣነውን ዳገት አሁን ፈጠን ፈጠን እያልነው ወረድን። ሳይታወቀኝ ብዙ ስል ነው መሰለኝ ረሙ ብላ ጠራችኝ አቤት አልኳት። ቅድም መንገዴ ነበረች ያልከይ ልጅ ግን ማናት አለችኝ። እእእእ.... ኖላዊት ትባላለች ኤሌክትሪካል 4ተኛ ተማሪ ናት አልኳት። ና..ላ...ዊ..ት? አለችኝ እንደማሰብ እያለች ቀይ ልጅ ናት ፀጉሯ ረጅም ቆንጅዬ? አለችኝ አው እሷ ናት ታውቂያታለሽ አልኳት። እውውውይ አው አውቃታለው እኛ ፍሎር ላይ ናት ዶርም ብአይኒ አውቃታለሁ ኢንጂ አንግባባም አለችኝ። በጣም አስተዋይ ልጅ ናት ተዋወቂያት አልኳት። ኢሺ እተዋወቃታለሁ አለችኝ። መንገዳችንን ቀጠልን በግተራ ጋር አድርሻት ቻው ብያት ሄድኩ።
ይቀጥላል
ሀሳብ አስተያየት @BINCJ90 ላይ ያድርሱን
ከወደዳችሁት Like እና Share አድርጉት

ክፍል 35
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፀሃፊ ረምሃይ
ህያብ ዶርም ስትገባ ፈተናዋ ጀመረ ጓደኜቿ ገና እንደገባች ከት ብለው መሳቅ ጀመሩ ረቂቅ እማ...ሆይ ከየት ነው ከቅዳሴ ብላ በነገር ጠቅ አደረገቻት። ህያብ ግድ አልሰጣትም እኪ ተውይ ብላ አልጋዋ ውስጥ ገብታ ጥቅልል ብላ ተኛች።
ብዙም ሳይቆይ ስልኳጠራ። ብርድልብሷን ገለጥ አድርጋ አየችው አዲስ ቁጥር ነው አነሳችውና ሄሌ አለች። ሄሎ ህያብ ሰላም አመሸሽ አሃዱ ነኝ ይላታል አ..ሃ..ዱ! አለችና በደስታ ከአልጋዋ ተስፈንጥራ ተነሳች። የጓደኞቿ አይኖች እንዳለ ወደ እደሷ አማተሩ። ሰላም ነው አሃዱ እንዴት ነሂሳ አለችው ስሜቷን ለመቆጣጠር እየሞከረች። ደህና ነኝ ክብሩ ይስፋ አላት። ህያብ ደስ እያላት ጥሩ ጥሩ ንፋስ አለ የት ሁነህ ነው አለችው። ከተማ ነበርኩ አሁን ወደ ግቢ እየገባው ነው በር ላይ ነኝ አላት ኢሂ... ጥሩ ነው እና ለምን ሳትገባ በእኛጋ አልፈህ ሰላም ብለኀኝ አታልፍም አለችው። አሃዱ ትንሽ እንደማሰብ አለና እእእ እሺ ስደውልልሽ ውጪ አላት ህያብ የስስስ... ብላ በደስታ ዘለለች። የዶርሟ ልጆች ለማንም ወንድ እንደዚ ስትሆን አይተዋት አያውቁም ለሃበንም ቢሆን ገርሟቸው ያያት ጀመር።
ህያብ በፍጥነት ወደሎከሯ ሄዳ ልብስ መቀየር ጀመረች። ረቂቅ ገርሟት ቆይ ማነው እንዲ ልብሽን ያሸፈተው አለቻት እየሳቀች። ህያብ እየተቻኮለች ነው ስመለስ ነግርሻለው ብላት ልብሷት ትለባብስ ጀመር። አንዱ ቀይ የእራት ልብስ ከነማንጠልጠየው አንስታ ሰውነቷ ላይ እየለጠፈች እንዴት ነው ይሄንን ልልበስ ያምርብያል ትላታለች ረቂቅ በሳቅ ፈረሰች። ህዩ የት ነው እንዴ የተቀጣጠራቹት አለቻት የትም እዚው ነው ሰላም ብሎኝ ሊያልፍ ነው ትላታለች ሁሉም ከት ብለው ሳቁ አንቺ ልጅ የሌለ ነው የገባልሽ ይሄ ልጅ! በዚ በብርድ ያውም እዚ ግቢ ውስጥ የተገላለጠ የእራት ልብስ መልበስ አማረሽ ቆይ ማነው እናውቀዋለን አለቻት። እውውውይ አታውቁትም አሁን እሱን ተዉትና ንገሩይ የትኛውን ልልበስ አለቻት። እንዲ እየተከራከሩ ስልኳ ድጋሚ ጠራ... አየችው የአሃዱ ቁጥር ነው። ህየብ እየዘለለች ደውለ ደወለ ደወለለለ... አረ የትያውን ልልበስ አለች። ሁሉም በሳቅ ሞቱ ረቂቅ አሁን የለበሽው እኮ አሪፍ ነው ነጠላውን ብቻ አውልቂውና ሂጂ አለቻት። እሺ ብላ ነጠላውን አውልቃ ቅድም እንደነበረችው አጭር ጥቁር ቀሚስብበፍጥነት ወጣች። ደረጃውን በፍጥነት ወርዳ ከብሎካቸው ወጥታ ወደ በግተራ ሄደች። ስትደርስ አሃዱ ከበግተራው ፈንጠር ብሎ ወደ ዲያና ላውንች መሄጃ ጋር ቆሞ እየጠበቃት ነው ስታየው ደስታዋ እጥፍ ጨመረ ።አጠገቡ ስትደርስ እንዴት መሆን እንዳለባት ጠፋት ልታቅፈው ፈለገች ግን የሱን አታውቅም። ሰላም ነው አሃዱዬ አለችው ደና ነኝ አላትና መላ ሰውነቷን ገርመም አድርጎ እያያት አይበርድሽም ግን በዚ ምሽት እንደዚ የተገላለጠ አጭር ቀሚስ ማድረግ አላት። ምን ችግር አለው አንተ ታቅፈኛለሃ አለችው አሃዱ ፈገግ እያለ እእእ አለና የለበሰው ቡኒ ጃኬት አውልቆ ከላይ አለበሳት። ህያብ ፈገግ እያለች ላለማቀፍ ነዌዋዋ! አለችው አሃዱ ፈገግ ብሎ አያትና ዝም አለ። በቃ ካለበስከኝ አይቀር ወክ እናድርግ አለችው አሃዱ እሺ አላትና ቀስ እያሉ መራመድ ጀመሩ።
አሃድዬ ባለፈው ስካደረክልይ ነገር በጣም አመሰግናለው እሺ አንተ ባታገኘይም ረሙ ነግሮያል... እስኪ ስለራስህ ንገረይ ስላንተ ማወቅ እፈልጋለው አለችው። አሃዱ ፈገግ እያለ ምን ማወቅ ትፈልጊያለሽ አላት። ሁ..ሉ..ን..ም! አህልዱ ከት ብሎ እየሳቀ እንደዛማ ከሆነ 25 አመት ያስፈልግሻላ አላት። እሺ በቃ ደስ ያለህን ንገረይ አለችው። አሃዱ እንደማስብ እያለ እእእ እሺ ያው አሃዱ እባላለው የተወለድኩት ያደግኩትም በባህርዳር ከተማ ነው ዩኒቨርስቲም እዛው ባህርዳር ነበርኩ አምና። በዚህ አመት ነው ወደ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ያስቀየርኩት ሲላት አ ቋረጠችውና ለምን ወደ መቀሌ ማስቀየር ፈለግህ አለችው። አሃዱ እየሳቀ አንቺን ለማግኘት አላት ህያብ ከት ብላ ሳቀች አንተ ትቀልዳለህ አይደል አለችው። አሃዱ እውነቱን እንደቀልድ እያዋዛ ቢነግራትም እሷ እንደቀልድ አይታው አለፈች። ውክ እያደረጉ ከከነአን ወደ እንዳ እየሱስ ቤተክርስቲያን የሚውስደውንን መንገድ እየሄዱ ነው በአከባቢው የሰው ዘር የለም። ህያብ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅማ አሃዱን የራሷ ልታደርገው አሰበች ፈጠን ብላ ወደፊት ሄደችና ከፊቱ ቆመች አሃድዬ እያለች ፊቱን በለግላጋ ጣቶቿ በስሱ የደባበሰችው በጣም ተመችተኀኛል ብላ ከንፈሩን ልትስመው ስትል አሃዱ ፊቱን አዞረባት። ህያብ ተበሳጨች ምን ሆነሃል አለችው? ምንም ግን እኔ እዚ ግቢ ውስጥ እንደምትቀያይሪያቸው አይነት ወንዶች አይደለሁም በጣም ለነገሮች ትፈጥኛለሽ መረጋጋት ጀምሪ ሰከን ብለሽ አስቢ አላት። ህያብ ክብሯ የተነካ መሰላት በጣም አጉል የኮራባት የተንቀባረረባት መሰላት። ቆይ ማነኝ ነው ምትለው አለች። አሃዱ ቆጣ እያለ ህያብ! መጀመሪያ ከያዝሽው ጓደኛ በስነስረአት ተለያዩ እኔ ጓደኛ ካላት ሴት ጋር የምዘል አይደለሁም እኔ ላይም እንዲደረግ አልፈልግም አላት። ህየብ ገንፍሎ የነበረው ገሞራ በአንዴ ስክን አለ ልክ ልኳን ነግሮ ወደቦታዋ የመለሳት መሰላት። እሺ ይቅርታ አለችው። አሃዱ ምንም ሳይናገር ወደጎን አድርጓት ወደፊት ቀስ እያለ መራመድ ጀመረ። ህያብ ሁኔታው ቢያናዳትም ለሱ ያላትን ስሜት መቆጣጠር አልቻለችም ማንም.ወንድ እንዲ ተናግሯት አያውቅም ጥላው ልትሄድ ብትፏግም አልቻለችም ቀስ እያለች ከኃላው ጠጋ ብላ ተከተለችው።
ቀስ ብላ ቀኝ እጁን እቅፍ እያደረገችው ይቅሬይታ! ልስልስ ባለ አንደበት። እሺ አላትና በቃ ወደዶርዎርም እንመለስ አላት። እንደደበረው ስለገባት ብዙም ስሜቱን ልትጋፋው አልፈለገችም እሺ በቃ እንሂድ ተባብላው በዝምታ ወደ ዶርም መጓዝ ቀጠሉ እሰም ዝም! እሷም ዝም!... ብቻ እሷ ጥምጥም ብላ አቅፋዋለች። የከነአንን አስፓልት ጨርሰው በአፍሪካ መንደር አድርገው ወደተመራቂዎቹ ሰፈር ሉሲ አከባቢ ሲደርሱ ከአንዱ ዶርም በረንዳ ላይ ህ...ያ...ብ!? የሚል ጎርናና አሥደንጋጭ ድምፅ ጮኀ ደንግጣ ስማ ወደተጠራበት ቀና ስትል ሃበን ነው! ህያብ የምትገባበት ጠፋት ጨነቃት! ልብ ምቷ ሲፈጥን ታወቃት። ሃበን የዶርሙ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ ስልክ እያወራ ነበር ያያቸው። ወዲያውኑ ስልኩን ዘግቶ ወደውስጥ ገባና ደረጃውን ሲበር ወርዶ ወደ ህያብ መጣ ህያብ አሃዱን እንዳቀፈችው አይን ለአይን ተፋጠጡ!
ይቀጥላል
ከወደዳችሁት Like እና Share

ክፍል 36
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፀሃፊ ረምሃይ
ህያብና ሃበን ተፋጠጡ ሃበን በንዴት ቁና ቁና እየተነፈሰ ያያታል። ህያብ መሬት ተከፍታ ብትውጣት ምንኛ ደስ ባላት። ጭራሽ በቁሜ ሌላ ወንድ ይዘሽ መሄድ ጀመርሽ!? ብሎ አንቧረቀባት። አይደለም እኮ ሀበንዬ አንድ ግዜ ተረጋጋና ላስረዳህ አለችው። ሃበን ህያብን ትቶ ወደ አሃዱ ተመለከተ ሲያየው የሚያውቀው ፊት መሰለው የሆነ ቦታ እንደሚያውቀው እርግጠኛ ነው የት እንደሆነ ባያስታውስም.... አንተ! እኔ የሷ ፍቅረኛ መሆኔን ሳታውቅ ነው እምትደረበው አለና ሊመታው እጁን አነሳ። ህያብ ቆይ አይሆንም ብላ ልታገላግላቸው መሃል ስትገባ ሃብን ህያብን ወደሃላ ገፈተራት ህያብ ከጀርባዋ የነበረ ድንጋይ ላይ ወደቀች።
አሃዱና ሃበን ሲደባደቡ ህያብ ራሷን ስታለች ከራሷ ደም እየፈሰሰ ነው ። ሁለቱም እልክ ተጋብተው ሲጣሉ ህያብን ያያት አልነበረም። በአከባቢው የነበሩ ሌሎች ሰዎች ድብድቡን አይተው ሲመጡ ህያብ እንደወደቀች አዩ ተሯሩጠው ወደሷ ሄዱ። አሃዱ እንደድንገት ዞር ሲል ህያብ መሬት ላይ ተዘርራ ሰው ከቧት አየ በጣም ደነገጠ ድብድቡን ጥሎ ወደሷ ሮጠ። ሃበንም አሃዱን ሲከተል ህያብ እንደወደቀች አየ እሱም በፍጥነት ወደሷ ሄደ... ሁለቱም በግራና በቀኝ ሆነው ህያብ! እያኑ ይጠሯት ጀመር። በኃላም ሃበን በፍጥነት አንስቷት ወደ ጊቢው ክሊኒክ ይዟት ይሄድ ጀመር በአከባቢው የነበሩ ሃበንንና ህያብን የሚያውቋቸው ተማሪዎች ተከትለውት ሄደ። አሃዱ ግን ባደረገው ነገር በጣም ተፀፀተ ለደቂቃዎች እንኳን ቢሆን ንዴቱ ገንፍሎ ሲወጣ ህያብ ላይ ያስከተለውን ጉዳት ተገነዘበ። ወደኃላ ቀረ ከኃላ ቀስ እያለ ተከትሏቸውሄደ። ሃበን ልቡ እየተንሰፈሰፈ በእቅፉ እንዳለች ህያብ ንቂ! ይላታል ፍጥነቱን ጨምሮ ወደ ክሊኒኩ ደርሶ ይዟት ገባ። አሃዱ ከክሊኒኩ ፊትለፊት ያለው ሞሞና ፓርክ ውስጥ ተቀመጠ።
ሰአታት አለፉ... ለሊቱ ተጋመሰ...
ሃበን ለደቂቃዎች እንኳን ከአጠገቧ አልተለየም! አብረዋቸው የመጡት ሌሎች ጓደኞቻቸው ለሊቱ እየገፋ ሲሄድ አንድ በአንድ ሁሉም ሄዱ ከተወሰኑት በቀር። አሃዱ በዛ ብርዳማ ለሊት ሞሞና ፓርክ ውስጥ ተቀምጧል። የሆነ ሰአት ላይ አንዲት ሴት አጠገቡ መጥታ ከድንጋዩ ወንበር ላይ ተቀመጠች። አያት! ርሻን ነበረች። ምንድነው የተፈጠረው አሃዱ ሁሉም ሰው አንተ ህየብን እንደገፈተርካትና እንደወደቀች እያወሩ ነበር እና ደግሞ ከህየብ ጋር እንዴት ነው ምትተዋወቁት አለችው። እሱን እኔ አላደረኩም የሃበን ወሬ ነው... ግን.... አንድ እውነት ብነግርሽ ታምኚኛለሽ!? ብሎ ጠየቃት። ርሻን ግራ ስለገባት የምን እውነት ብላ ጠየቀችው። መጀመሪያ ታሪኩን እስከምጨርስልሽ ድረስ ጥለሽኝ እንደማትሄጅ ቃል ግቢልኝ አላት። ርሻን ምን ሊነግራት እንደሆነ ግራ እየገባት እሺ አለችው። እንደ እብድ ትችያለሽ ወይም ሌላ ነገር.... ትዝ ይልሻል እኔና አንቺ መጀመሪያ የተዋወቅን ለት አላት። አው አንተ ከባህርዳር ስትመጣ እኔ ደግሞ ከቤት ስመጣ ሻንጣችንን እየጎተትን የግቢያችን በር ላይ በአጋጣሚ ተገናኘን አለች።
አው አንቺ እምታውቂው በአጋጣሚ እንደሆነ ነው ለእኔ ደግሞ በአጋጣሚ አልነበረም በስነስረአት የተነደፈ እቅድ ነበር አላት። ርሻን አሃዱ ሌላ ተልእኮ ያለው መስሏት ደነገጠችና እንዴት አለችው። ትዝ ይልሻል የዛን ቀን የለበሽው ጥቁር ሱሪ እና ነጭ ሸርት ነበር። ከቤት ከመውጣትሽ በፊት ከታላቅ እህትሽ ጋር እየተከራከራችው ነበር የእህትሽን ትልቁን ቡኒ ሻንጣ ለመውሰድ ፈልገሽ እሷ አልሰጥም ብላሽ እየተከራከራችው ነበር በመጨረሻም እናትሽ መጥታ አስታርቃችው ሌላ ትልቅ ጥቁሩን ሻንጣ ይዘሽ መጣሽ እህትሽ ስላናደደችሽ የምትወደውን ሽቶ ሰርቀሻት ነበር የመጣሽው አላት። ርሻን በጣም ደነገጠች... እየተከታተልከኝ ነው እንዴ ብላ ተቆጥታ ልትሄድ ስትል አሃዱ እጇን ያዝ አደረጋት... ርሻን እባክሽ አትሂጂ ገና ምንም አልነገርኩሽም እኮ ቃል የገባሽልኝን አትጠፊ አላት። እና እንዴት አወቅክ ይሄንን ሁሉ ይህንን ነገር ከኔ ውጪ ማንም አያውቅም አለችው። ርሻን እኔ መጥፎ ሰው ሆኜ አይደለም አንቺን ሆነ ማንንም ሰው የመጉዳት አላማ የለኝም አላት። እና... አለችው።
አየሽ ርሻን ላታምኚኝ ትችያለሽ ግን እኔ ከሌላው ሰው በተለየ የተሰጠኝ ስጦታ አለ ህልም አያለው! በአሁን ሰአት እየሆኑ ያሉና በቅርብ የሚሆኑ ነገሮችን በህልሜ አያለው። ይህንን ነገር ካንቺ እና ከአንድ ሰው ውጪ ለማንም ተናግሬ አላውቅም። ላታምኚኝ ትችያለሽ ግንብዙ ግዜ የማየው የማውቃቸውን ሰዎች ነው እነሱንም አልፎ አልፎ ነው። ከአራት አመት ወዲህ ግን የተለየ ሆነብኝ የሆነች የማላውቃትን ሴት በተደጋጋሚ አያለው እሷ እና ሶስት ጓደኞቿ እና የሷ የነበረ በጣም የምትወደው የወንድ ጓደኛዋ። እቺ ሴት ህያብ ነበረች ጓደኞቿም እናንተ... ሃበን....
ይቀጥላል
አብሮነታችሁ አይለየን እስቲ ህያብን ስንት ሰው ያነበዋል 🤚
ማንኛውም ሀሳብ አስተያየት @BINCJ90 ላይ ያድርሱን

የኮሮና ቫይረስ በዓለም ከ23 ነጥብ 1 ሚሊየን የሚበልጡ ሰዎች አጥቅቷል። ከ800ሺ በላይ ሰዎችን ከመቃብር በታች አውሏል።
ይህ ቫይረስ በሀገራችንም አጠቃላይ ከ37 ሺህ በላይ ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን ከ637 የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ለህልፈት ተዳርገዋል።
#ጥቁርን - ከነጭ ፣#ሀብታም - ከደሀ፣ #ከአዛውንት እስከ #ጨቅላ ሳይቀር ለህመም ብሎም ለህልፈት እየዳረገ ያለው ይህ የኮሮና ቫይረስ በርግጥ በዚህ ጊዜ ይጠፋል ለማለት ቢያዳግትም እራሳችንን መጠበቅና ማድረግ የሚገቡንን ጥንቃቄዎችን በመከወን ቫይረሱ መከላከል ነገን በተስፋና በጽናት ብሎም በመደጋገፍ መጠበቁ ምርጫ የሌለው ጉዳይ ነውና እራሳችንን እንጠብቅ።
ሰላምና ጤና የተሞላበት ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ!

ክፍል 37
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፀሃፊ ረምሃይ
ለማመን እንደሚከብድሽ አውቃለው ግን እውነታው ይሄ ነው። ይህች በልሜ የማያት ልጅ ቀልቤን ገዛችው በጣም የሚያምር ስብእና ነበራት አስተሳሰቧ መልካምና የዋህ ነበረች። ይህ ማንነታ ሳላውቃት እንዳፈቅራት አደረገኝ አንድ ቀን የልቤን መሻት አይቶ ይህሽን ሴት ሳገባት በህልሜ አየው!።
እናንተ የምታደርጉትን ነገር በሙሉ እኔ ባህርዳር ሆኜ አውቅ ነበር! እንዴት አራታችው ጥሩ ጓደኛሞች እንደነበራችው ህያብ እሷና ሜሮን እና ሜላት። እንዴት እሷና በህያብ አማርኛ ሜላትና ሜሮን እንዴት ሙድ ይይዙባቸው እንደነበር ሁሌ ዲያና ሄደው እራት ሲበሉ... በኃላም ሜላት ከሃበን ጋር ስትሳሳም አይታ እንደተቀያየሙ በኃላም ህያብ ባህሪዋ እየተቀየረ መጥቶ የመልካምነት ካባዋን አውልቃ ከነሱም ጋር ተጣልታ አሁን ያለችበት ስብእና ላይ እንደደረሰች... አሃዱ በሰፊው እያንዳንዷን ነገር ለርሻን ለሰአታት አስራዳት። ርሻን ከአእምሮዋ በላይ ሆነባት! ምን እንደምትለው ግራ ገባት። እኔ ምን ማላት እንዳለብኝ አላውቅም የነገርከኝ ነገር እሚዬምን ቢሆንም ለማመን ይከብደኛል ግን... ህያብ ያንተ እንደምትሆን ካወቅክ ለምን ይሄንን ሁሉ ግዜ መጠበቅ ፈለግክ ለምን በጊዜ አልመጣህም አለችው። አሃዱ ራሱን እያሻሸ... ትክክለኛውን ግዜ እየጠበቅኩ ነበር። ወደፊት የኔ ሚስት የምትሆን ሴት ከሌላ ውፕንድ ጋር ሆና እንደማየት የሚከብድ ነገር የለም ቢሆንም ግን የነ እንደምትሆን አወኩኝ እንጂ ግና የኔ አልነበረችም ግዜው እስኪደርስ በትእግስት ማጠበቅ ነበረብኝ። ትክክለኛ የሆነ ነገር እንኳን ቢሆን በትክክለኛው ግዜ እስካልመጣ ድረስ ትክክል አይሆንም ለዛ ነው ግዜው እስኪደርስ መጠበቅ የነበረብኝ። እግጥ ነው ወደመቀሌ ከዚህ በፊት አንዴ መጥቼ ነበር ግን ትክክለኛው ሰአት ስላልነበር ተመለስኩ አሁን ግዜ ሲደርስ ዳግም መጣው አላት።
ርሻን ነገሩ ለማመን ቢከብዳትም እጅግ ግራ የሚያጋባ ነገር ቢሆንም አመነችው አሃዱን በምታውቀው መጠን መልካም ሰው እንደሆነ ታምናለች። ህያብ የምትወዳት ጓደኛዋ ነበረች አሁን ላይ ባይነጋገሩም ለክፉ ግዜ አብራት ልትሆን መጥታለች ደግሞም ከሃበን በላይ አሃዱ ለህያብ እንደሚሆናት ገብቷታል። ድንገት ስልኳ ጠራ ደነገጠች! አላሰበችውም ነበር። አየችው ሜሮን ናት! ወዬ ሜሪ አለቻት... አንቺ የት ነው የጠፋሽው በዚ ለሊት ህያብ እየነቃች ነው ቶሎ ነይ አለቻት። ወዲያው ስልኩን ዘጋችና ተነሳች አሃዱ በቃ ወደ ውስጥ ልግባ ህያብ እየነቃች ነው ከቻልክ ና ካልፈለግክ ደሞ ተመልሼ መጥቼ ያለችበትን ሁኔታ አሳውቅሃለው ብላው መልሱን ሳትጠብቅ እየረጠች ወደ ክሊኒኩ ገባች።
በስተመጨረሻ ህያብ ቀስ ነቃች! ያለችበትን ቦታ ማስተዋል ጀመረች... የድሮ ጓደኞቿ ሜሮን እና ርሻን ጎን ለጎን ቆመው በጭንቀት ያያታል በቃ ሌላ ማንም የለም። ስራክማት የነበረችውን ነርስ ስንት ሰአት አለቻት ወዲያው ስልኳን አውጥታ አየችና ሩብ ጉዳይ ለአስር አለቻት። ከቀኑ ነው ከለሊቱ አለቻት ያለችበትን ፍፁም አታውቅም። አይ ከለሊቱ ነው የኔ ቆንጆ አለቻት። ጓደኞቼ የምትላቸው ዶርማቸው ተኝተው ክፍል አስራስድት ህልም ላይ ደርሰዋል። ህያብ አሁን ጓደኞቿን በደምብ ለየች! ርሻንና ሜሮን ያስቀየመቻቸው የድሮ ጓደኞቿ ቂም ሳይዙባት በተቸገረች ግዜ በዚ በብርዳማ ለሊት እየጠበቋት ነበር በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ ይዛቸው የነበሩ ጓደኞቿ በችግሯ ግዜ አልተገኙ ግማሿ ተኝታለች ግማሿ ጭፈራ ላይ ነች። ህያብ በጣም ተሰማት እንዲ እያስቀየመቻቸው መጥተው ከጎኗ አሉ። ህያብ አለቀሰች! ርሻን ልቧ እየሳሳ ምነው ህዩ አይዞሽ አታልቅሽ ደህና ነሽ እኮ ብዙም አተጎዳሽም ይሻልሻል አለቻት። ህያብ ከተኛችበት እያለቀሰች ስትነሳ ነርሷ ወዴት ነው አለቻት ደህናንነኝ ችግር የለውም ልቀቂኝ አለቻት ለቀቀቻት ተነስታ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ከርሻን እግር ስር ወደቀች። ይቅርታ አድርጊልይ ርሻን ሃፍተይ በጣእሚ አስቀይሜሻለሁ ይቅር በይይ ብላ እግሯ ላይ ተደፍታ አለቀሰች። ርሻን ሁኔታው በፍጥነት ቅፅበታዊ ስለሆነ ደንግጣ አረህዩ በይዛኪ ተላኣሊ አልተቀየምኩሽም ህዩ ተነሽ በላ ደግፋ አነሳቻት። ህያብ ግን አላቆመችም ወደ ሜሮን ሄዳ ገና ልታጎነብስ ስትል ሜሮን በፍፁም ህያብ! አይደረግም እኔ ምንም አልተቀየምኩሽም በላ ደግፋት ወደ አልጋው ወሰደቻት። ህያብ ትንሽ ህሊናዋ ተረጋጋ የምትፈልገውን ሁሌ ውስጧን ሲበላት የነበረውን የጓደኞቿን ይቅርታ አገኘች።
ይህ ሁሉ ሲሆን ሃበን ጥግ ላይ ተቀምጦ ከማየት ውጪ ምንም ቃል አላወጣም በሱ ጥፋት እንደተጎዳች ያውቃል። ሜሮን ሃበን ወደተቀመጠበት ቦታ ሄዳ ካየችህ እንዳትናደድ እና ይበልጥ እንዳትጎዳ ውጪ ሁን ከፈለገችህ እኔ ጠራሃለው አለችው እንዴ እኔኮ ምንም አላደረኬትም ያ ልጅ ነው ገፍትሮ የጣላት አላት። ቢሆንም ያው ስኪረጋጋ አለችውና አግባብታው በፀባይ እንዲወጣ አደረገችው። ሃበን ሲወጣ የክሊኒኩ ጠባብ አራት መአዘን ግቢ ውስጥ ከአሃዱ ጋር አይን ለአይን ተፋጠጡ ሃበን ሲያየው ተናደደ እንደምንም ስሜቱን ተቆጣጥሮ ከሱ ፊትለፊት በተቃራኒ ወንበር ላይ ሄዶ ተቀመጠ። ህያብ ትንሽ ወደራሷ ስትመለስ ለመጨረሻ ግዜ ራሷን ከመሳቷ በፊት የነበረውን ሁኔታ አስታወሰች። ሃበንና አሃዱስ አለቻቸው ርሻን ወደ በሩ ጋር ወጣ ብላ እያየች ሁለቱም አሉ ውጪ ቁጭ ብለዋል የምትፈልጊውን ልጥራልሽ አለቻት። አው ሃበንዬን ጥሪልኝ አለቻት ርሻን ስላቆላመጠችው ግራ ገባትና ወደ ውጪ ወጣ ብላ ህያብ ትፈልግህልለች ና አለችው ሃበን ደስ አለው አሃዱን ገልመጥ አድርጎት እየተራመደ መጥቶ ወደክፍሉ ገባ!።

ክፍል 38
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፀሃፊ ረምሃይ
ሃበን ቀስ ብሎ ወደ ህያብ ተጠጋና ጎንበስ ብሎ እጇን ሳም አደረጋት። ህያብ እጇን ወደራሷ ሰበሰበች። እንደተናደደችበት ስለገባው ይቅርታ ህያብ እኔ ልጎዳሽ ፈልጌ አልነበረም ወደኃላ የገፋሁሽ ልታገላግይን ስትገቢ እንዳይመታሽ ብዬ ነው ይቅርታ! አንቺን ከማንም ወንድ ጋር ላይሽ ስለማልፈልግ ነው ታውቂያለሽ ትንሽ ስናደድ እማረገውን አላውቅም አላት። ህያብ ከተናገረው ሁሉ ነጥላ አው አንተ ስትናደድ እምታደርገውን አታውቅም! ብላ ደገመችለትና ከወገቧ ቀና ብላ ተደግፋ ተቀመጠች። በትንሽ በትልቁ ዝም ብለህ ትገነፍላለህ ማን ይሁን ምን ይሁን ምንም ሳታውቅ አለቅጥ ትበሳጭብኛለህ ። ሰለቸይ ሃበን በጣ...ም! ሰለቸይ ካብ ሃይስኩል ጀምሮ ታገስኩህ ጠበቅኩህ ግን አንተ እምትስተካከል አይነት አይደለህም.... ብላ ልትቀጥል ስትል ሃበን አቋረጠትና አይደለም እኮ ህያ.... አላስጨረሰችው አታቋርጠጠጠይ! ብላ ጮኀችበት ሲጀመር አንተ ማንን ትሰማለህ ራስህን ብቻ ኢኔን ለመስማት እንኳን አይትፈልግም! መጀመሪያ አሃዱ ማን እንደሆነ ጠይቀሀያል! ዘመዴ ቢሆንስ ኖሮ! ያየኀውን ወንድ ሁሉ ልትደበድብ ነው? ዝም ብለህ ከወንድ ጋር ስላየኀይ ብቻ ትገነፍላለህ በጣም ሲበዛ ቅናተያ ነህ! ቅናትና ፍቅሪ ድሞ በሃደ አይኸይድን! በቃ! ከዚህ በላይ ኢኔ መቀጠል አልችልም ይበቃያል አለችው ህያብ ይህንን ስትል ከአይኗ የእንባ ዘለላ እየወረደ ነበር።
ሃበን ይህንንም ብትለውም ዳግም ሊያቋርጣት አልደፈረም ውስጡ ቢቃጠልም ድጋሚ ተናዶ ልክ እንደሆነች ሊያረጋፍጥላት አልፈለገም። ዝም ስትል ግዜ... ነው? አላት። መልስ አልሰጠችውም ተመልሳ ጋደም ብላ ተኛች። ሃበን በንዴት የድንገተኛ ህክምና ክፍሉን ጥሎ ወጣ!። ልክ የበሩ ጫፍ ላይ ሲደርስ አሃዱን አየው በፍጥነት ወ ደሱ ሄደ!። ኮስተር ብሎ አንተ ለህያብ ምና ነህ? አለው ኮስተር ብሎ። አሃዱ በተረጋጋ መንፈስ ሆኖ ከእኔ ይልቅ ህያብን ብትይቃት አይሻልም ነበር? አለው። ዝምብለህ የተጠየቅከውን መልስ አለው። አሃዱ ፈገግ አለ... ጉልበት እና ቁጣ ለለምንም ነገር መልስ አይሆንም ተረጋጋ ወንድሜ አለው።
ሃበን ህያብ ያለችው ነገር ትዝ አለው ዘመዷ ቢሆንስ ብሎ አሰበና ከዚህ በላይ መናደዱ ፋይዳ ያለው ስላልመሰለው ቀዝቀዝ ማለት ጀመረ። እሺ ጠይቃታለው ይቅርታ ብሎት በፍጥነት ሄደ። ርሻን የሃበንን እግር ተከትላ ወደ አሃዱ ሄደችና። ሃይ አሃዱ ለሊቱ እንዴት ይዞሃል ብርድ ነው አይደል? አለችው። አይ ባህራርም ነፋሻማ ስለሆነ ብዙም አልከበደኝም አለ በእጆቹ ክንዱን እያሻሸ። ጥሩ እሺ ህየብ እየጠራችህ ነው ና እስኪ ግባና አናግራት አለችው። እሺ አላትና ተያይዘው ወደክፍሉ ገቡ።
አሃዱ ህያብ ከተኛችበት አልጋ በእግርጌው በኩል ሄዶ ለህያብ ጀርባውን ሰጥቷት ዝም ብሎ ተቀመጠ። ህያብ ከአሁን አሁን ያወራል ብላ ብትጠብቅም ምንም አላለም ዝም አለ! አታወራይም እንዴ ብላ ጠየቀችው። አይ እኔ ከማውራቴ በፊት አንቺ የምትይኝ.ነገር ይኖራል ብዬ ነው አላት። ህያብ እርጋታው ይበልጥ አስገረማት በእንደዚ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንኳን ማእበል እንደማያናውፀው ሃይቅ ልቡ የተረጋጋ እንደሆነ አየች። በሃበን እና በአሃዱ መካከል ያለው ትልቅ ልዩነት ምን እንደሆነ ገባት ልዩነታቸው የሰማይና የምድር ነበር። ሁለቱም ፍቅርን መስጠት ይችሉ ይሆናል ግን ፍቅር አይቸኩልም የተረጋጋ መንፈስ ነገሮችን ማየት ይፈልጋል ለዚህ ደሞ ከማንም በላይ አሃዱ ይበልጣል።
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዝምታ ሰፈነ...። አሃዱዬ በትግርኛ "ኀደ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃለህ አለችው። ራሱን በአሉታ ነቀነቀ። ብትግርኛ "ኀደ" ማለት ከግእዙ "አሃደ" ከሚል ቃል የመጣ ነው አንድ ወይም አንደኛ ማለት ነው። ሳላውቅህ ነው የወደድኩህ እርጋታህ አስተሳሰብህ ደስ ይላል የድሮ እኔነቴን መልካምነቴን ታስታውሰያለህ አንተ ለኔ አንደያዬ ነህ አሃዱ! አለችው። አሃዱ ፈገግ አለ... "ህያብ" ማለት በትግርኛ ምንም ማለት እንደሆነ አይጠፋሽም አይደል? አንቺ ደግሞ ለኔ ስጦታዬ ህያቤ ነሽ ሳላውቅሽ የተሰጠሽኝ ስጦታ ሳላገኝሽ የወደድኩሽ ሳላውቅሽ ያየሁሽ አላት። ህያብ ይህንን ስትሰማ ልቧ በሃሴት ተሞላ።
ይቀጥላል
Like እና Share ማድረግ እንዳይረሳ

ክፍል 39
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፀሃፊ ረምሃይ
የተወሰኑ ቀናት አለፉ... ህያብ ከጉዳቷ ለማገገም ወደቤቷ ሄዳለች። ጊቢ ውስጥ ያለው ሁኔታ ያስጠላት ይመስላል ጓደኞቿ፣ ሃበን፣ አስመሳይነቱ፣ ወሬው... ቢሆንም ግን ከአሃዱ ጋር ያላት ግንኙነት ከቀን ወደቀን እየጨመረ ሄዷል። በየቀኑ በስልክ ሳያወሩ አያድሩም። ህያብ ለሊቱን ሙሉ በምታወራበት ቅፅበት ለሱ ያላት ስሜት ይበልጥ እየጨመረ ሲሄድ ይታወቃታል ሁሌም ቤት መጥቶ እንዲጠይቃት በትለምነውም ለመምጣት ፈቃደኛ አልነበረም። የአሃዱም ስሜት በተመሳሳይ መልኩ ቢጨምርም ግን ቁጥብነቱ አሁንም እንዳለ ነው።
ህያብ ቤት በነበረችበት ግዜ ሜሮን እየደወለች ትጠይቃታለች ሲመቻት ደግሞ ከርሻን ጋር እየመጡ ይጠይቋታል። አንድ ቀን አመሻሽ ላይ ወደህያብ ጋር ሲሄዱ አሃዱን በስንት ጭቅጭቅ አስማምተውት ይዘውት ሄዱ... የነህያብ ቤት በር ተንኳኳ እህቷ ከፈተችላቸው። ሜሮንና ርሻን ወደውስጥ ገቡ አሃዱ ውጪ ቀረ። ወደ ሳሎኑ ሲዘልቁ ህያብ ጋቢ ለብሳ ሶፋ ላይ ተቀምጣ ቴሌቪዥን እያየች አገኟት። መጣችው ብላ ተነስታ ሰላም አለቻቸው እነሱም አቅፈው ሰላም ካሏት በኃላ በእጃቸው የያዙትን ፌስታል አሃዱ ነው የላከልሽ ብለው ሰጧት። ህያብ ፌስታሉን እያየች ራኒ ማንጎ ከሚያመጣልኝ ራሱ ቢመጣ አይሻልም ነበር አለቻቸው። ሜሮን ወደህያብ እያየች ለምን ወክ አናረግም ላንቺም አሪፍ ነው ወጣ ብለሽ ዞር ዞር ማለቱ ሲቀጥልም ሰአቱ ወክ ለማድረግ ምርጥ ነው አለቻት።
ህያብ በሃሳባቸው ተስማምታ ጋቢዋክ እንደለበሰች የቲቪውን ሪሞት ሶፋው ላይ ጣል አድርጋ እንደነገሩ ካልሲ እና ሸበጥ አድርጋ ወጡ። አሃዱ ከቤታቸው ቀጥሎ ያለውንብግንብ ተደግፎ ቆሟል ሰፈር ውስጥ የሚያውደለድሉ ጎረምሶች አንዱ መስሏት ብዙም ልብ ብላ ሳታየው አለፈችውና ሄደች። ርሻንና ሜሮን ፈገግ እያሉ ዝም ብለው ይከተሏታል ቀጣይ ምን እንደሚፈጠር ለማወቅ ይጓጉ ይመስላሉ። ርሻን ወደ አሃዱ እየዞረች ጠቀሰችው። አሃዱ ቀና አለና ህየብ ብሎ ጮክ ብሎ ጠራት። ህየብ ደንገጥ እያለች ወደኃላ ስትዞር አሃዱ ነው። ስንት ቀን ሰፈራቸው እንዲመጣ ጨቅጭቃው እምቢ ብሏት ዛሬ ስታየው... አሃዱዬ... ብላ ሮጣ ሄዳ ተጠመጠነችበት ደስስስ... አላት በጣም ናፍቋት ነበር ዝም ብላ አይን አይኑን ታየዋለች። ርሻን እና ሜሮን ሁኔታቸውን ሲያየ ቀኑባቸው። ሜሮን በፍቅር አይን እያየቻቸው እውውውውይ ደስ ስትሉ አለቻቸው።
ፀሃይዋ የፅልመት ካባዋን እየተከናነበ መተኛት ጀምራለች። ህያብና አሃዱ ከፊት ርሻንና ሜሮን ደግሞ ከኃላ እያጀቧቸው ወክ ያደርጉ ጀመር።
አሃዱ ወሬውን ለማስጀመር ያክል... እንዴት ነው ተሻለሽ አላት። አው በጣም ዳህና ነይ አለችው። ታዲያ መች ወደ ጊቢ ትመለሻለሽ አላት። እኔ እንጃ ከዚህ በኃላ ግቢ መመለስ አልፈልግም እዚው ከቤት እየተመላለስኩ ብማር ይሻለያል። ጊቢው አስጠልቶያል የሰዉ አይን እና ወሬ ይሰለቻል አለችው። እሺ አንቺ ደስ ያለሽን አድርጊ ግን ይህንን እወቂ ችግር ሲያጋጥምሽ መጋፈጥ ነው ያለብሽ እንጂ ፈርተሽ ወደኃላ መሸሽ የለብሽም ጠንካራ ሴት መሆን የምትሺ ከሄነ ችግሮችሽን ተጋፈጫቸው አላት። ህያብ ፈገግ እያለች ምንም ቃል ሳታወጣ ራሷን በእሺታ ነቀነቀች።
ትንሽ ዝም ከተባባሉ በኃላ... ርሻን ወይ ሜሪ ጋር ዶርም ካገኘሁ እመጣለው እንጂ ወደበፊት ዶርሜ ወደበፊት ጓደኞቼ መመለስ አልፈልግም አለችው። አሃዱ ለምን እንደዛ እንዳለች ቢያውቅም ለምን ብሎ ጠየቃት። የዛኔ ረምሃይና አንተ ከመከራቹይ በኃላ ራሴን መለስ ብዬ እያየው ነው ባለፉት አመታት ብዙ ደስ የማይሉ ነገሮችን ሳደርግ ነበር እናም ሲፀፅቱይ ነው ያለሁት ድጋሚ እንደበፊቴ መሆን እፈለጋለው። አንተና ረሙ በደምብ ብትመክሩይ ደስ ይለያል አለችው። ረምሃ...ይ አሁን የሚችልበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው አላት። ውይ ምን ሆነ ሰላም አይደለም ብላ ጠየቀችው። ሰላም ነው ግን በራሱ የህይወት ኡደት ላይ እየተፈተ ይገኛል እሱም እንዳንቺ የማንነት ጥያቄና መልስ ላይ ነው ጥሩ ግዜ ላይ አይደለም አሁን ኡደቱን ሲጨርስ ታገኚው ይሆናል አላት። ወይ ምንድነው የሆነው ልደውልለት ብላ ስልኳን ስታወጣ ስልኩ አይሰራም ስልክ መጠቀም አቁሟል አላት። እንዴ ምንድነው የሆነው ቆይ አለችው። አሃዱ ፈገግ እያለ... ተረጋጊ ህያብ ምንም አልሆነም አላት።
ይቀጥላል
አብሮነታችሁ አይለየን ታሪኮን ከወደዳችሁት Like & Share