Telegram Web Link
እባካችሁ ጥንቃቄ ይደረግ‼️

በአሁኑ ሰአት ደብረታቦር እና ባህዳር ከተማ ነዋሪ የደስታ መግለጫ በማለት ሁሉም ጥይት በመተኩስ ላይ ይገኛሉ።

ከባባድ መሳሪያም እየተተኮሰ ነውና ተባርቆ ሰው እንዳይጎዳ ሁሉም እንዲጠነቀቅ እናስተላልፋለን ።
ደስታችን ወደሀዘን እንዳይቀየር ደስታችንን በጥንቃቄ እናድርግ🙏
@monhappy
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_3

...🖊የእንጀራ አባቷ ቴድሮስ በስካር መንፈስ ሀናን ሊደፍራት
ሲታገል የውጪው በር መንኳኳቱን እንኳ አልሰማም ነበር
ሀናም የሚያንኳኳው ሰው በሩን ከፍቶ እንዲገባ በልቧ
እየፀለየች አይኗን ወደ በሩ ተክላ ቀረች ቴድሮስም
ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት እሷን መታገል አቁሞ ልብሱን
ለማውለቅ ሲነሳ ሀና ካለችበት ተነስታ አልጋው ላይ
ቆመችና ያለ የሌለ ሀይሏን ተጠቅማ ገፈተረችው እሱም
በመጠጥ ስለዛለ እዛች ጠባብ ክፍል ውስጥ በጀርባው
ወደቀ ሀናም ሮጣ ለመውጣት ካልጋው ወርዳ ጫማዋን
በማድረግ ላይ ሳለች የሀና እናት አፀደ በሩን ገፋ አድርጋ
ገባች ሀናም ልክ ሰርቆ እንደተያዘ ሰው ክው ብላ ደርቃ
ቀረች ... አፀደም በድንጋጤ ምን እንደተፈጠረ ስትጠይቅ
ሀና ግን ምን እንደምትመልስ ግራ ስለገባት ዝምታን
መረጠች ... ሰለሞንም የአፀደን መምጣት ስላየ እየሳቀ
ነገሩን አስቀየሰ ...
ቴድሮስ ከዛ ግዜ ጀምሮ ሀናን እንደ ጠላት ያያት ጀመር
ሁሌም ሀና አንድ ነገር ስትናገር ለሱ አይጥመውም
አፀደም ልጇን እጅግ ስለምትወዳት ያ ቀን ተሸፋፍኖ
ቢያልፍም ከዛ ቡሃላ ግን ማታ ማታ ብቻቸውን ትታቸው
አትሄድም ... ይህ በንዲህ እንዳለ ሀና የዘጠነኛ (9ኛ)
ክፍል ትምህርቷን ጀመረች ይሄኔ አንድ የሴት ጓደኛ ያዘችና
አብረው መሄድና መምጣት እንዲሁም እረፍት ሲሆኑም
መገናኘት ጀመሩ የሀና ጓደኛ ሶፊያ እጅግ በጣም ፀባየ
ሰናይ የምትባል ልጅ ነበረች በዚህም ነው ሀና ዱርዬ
ጓደኞቿን ትታ ሶፊያን መምረጧ...
አንድ እለተ ሀሙስ ሀና ከትምህርት ቤት ስትመለስ እናቷ
ከእንጀራ አባቷ ጋር በጣም ሲጨቃጨቁ ደረሰች ይሄን
ስታይ በጣም ተጨነቀች ደግሞ ሁሌም ቢሆንአፀደና
ቴድሮስ የሚጣሉት በሷ መሆኑን ታውቃለችስለዛም "
ደሞ ምን አረገች ብሎ ይሆን?" ብላ መጨነቋንቀጠለች
ሀና የሚያሳስባት ነገር ቢኖር እናቷ ስትበሳጭወይንም
ስትናደድ በጣም ትታመማለች ለዚም ነው ይሆዷን
በሆዷ ይዛ የምትሰቃየው ... ሀናም እቤት ገብታ
ዩኒፎርሟን እየቀየረች የጭቅጭቃቸውን መንስኤ
ለማወቅ ማዳመጥ ቀጠለች ይሄኔ ነበር የገባትትላንት
ምሽት ቤተክርስትያን አምሽታ ስትመለስ አንድየሰፈራቸው
ጎረምሳ ሀናን ሰላም ይላታል ይሄን ቴድሮስተመልክቶ
ስለነበር ነው ለአፀደ "ልጅሽን ስትንዘላዘል አየኋትለምን
አትቀጫትም...ወዘተ " እያለ ይነዘንዛት የነበረው ... ሀናም
ይሄን ስትሰማ ሽምቅቅ አለች ሀና እንኳን ከወንድጋር
ልትንዘላዘል ወንድ ጓደኛ እንኳን የላትም!
ይሄ "ልጅሽ ተንዘላዘለች..." የሚለው ወቀሳሲበዛባት
አፀደ ሀናን ለመምከር ቴድሮስና ትንሹ የሀና ወንድም
የማይኖርበትን ሰአት መረጠች ... ከዛም ለሀና
ያዳለፈቻቸውን ችግሮችና የሀና አባት ልጅ እያለች ደፍሯት
ሀና እንደተረገዘች ...በመንገር ሀና እንድትቆጠብና
ያለድሜዋ አጉል ቦታ እንዳትወድቅባት ማስጠንቀቂያ
አዘል ምክር እንባዋን እያዘነበች ሰጠቻት ሀናም
ከመቼውም በላይ ለእናቷ ያላት ፍቅርና ሀዘኔታ ጨመረ
እናትና ልጅ ተቃቅፈው አለቀሱ...
ሀናም "እማዬ እርግጠኛ ነኝ አንድ ቀን አኮራሻለው"
አለቻት እናትም በስስት እያየቻት "ሀና ልጄ ያንቺን ስኬት
አይቼ ብሞትም ቅር አይለኝም"... አለቻት
ሀና የአስረኛ ክፍል ትምህርቷን ልትጀምር ጥቂት ወራት
ሲቀራት እናቷ ኑሮን ለማሸነፍና ባሏን ለማገዝ ጠላ
መሸጥ ጀመረች ይሄኔ ሃናም እናቷን ለማገዝ ከትምህርት
መልስ ማስተናገድ ጀመረች ይሄኔ ቤታቸው የዱርዬ መአት
ይመጣ ጀመር ... በዚም ሀና ትምህርቷን በስርአት መማር
አልቻለችም በዛ ላይ ደግሞ በተደጋጋሚ የእንጀራ አባቷ
መነዝነዙን ቀጠለ...
አንድ ቀን ሀና ብቻዋን ቤት ስትጠብቅ ጠላ የሚጠጡ 7
ጎረምሶች መጡ ይሄኔ ሀና ሁሌም እንደምታደርገው ጠላ
ቀድታላቸው ተቀመጠች እነሱም ደጋግመው ሲጠጡ
ቆይተው 6ቱ በጣም ሰከሩ ሀናንም ለመድፈር
ይጠቃቀሱና ይተናኮሏት ጀመር ጀመሩ ሀናም በጣም
ፈርታ እንዲወጡ "አልቋል በቃ" አለቻቸው እነሱም
"አላለቀም ቅጂ ካለዛ አንከፍልም" አሉ በዚ መሃል
አንከፍልም ክፈሉ ሀና ያላቅሟ እያለቀሰች ስትሟገት
ከመሃላቸው አንዱ አባብሏት ብሩን በሙሉ ከፍሎ
እንዲወጡ አረጋቸው ከዛ ቡሃላ ሀናም ልጁ ላይ ቀልቧን
ጣለች እሱም እሷን ብሎ መመላለስ ጀመረ ምንም
ሳይባባሉ ባይናቸው ያወራሉ እጇን እንኳን ሳይነካት
በፍቅሯ ክንፍ አለ እሷም ለሱ የተለየ ስሜት ይሰማት ጀምሯል...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_አራትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_4

...🖊ሀና ምንም እንኳ ወንድ ልጅ ብትጠላ ባለፈው ስታለቅስ
ያዘነላትና ከጓደኞቹ ይልቅ እሷን መርጦ ከጥቃት ያዳናትን
ወንድ ከልቧ ቦታ ሰታዋለች ከትምህርት ቤት መልስ
ወደቤት ስትመለስ ጠላ ባለ ቀን ልጁን እስክታየው
ትጓጓለች ከሱ ጋር መተያየት ብቻ ደስ ይላት ነበር።
ምናልባት እንኳ ልጁ ከሴት ጋር ስልክ ካወራ ውስጧ
የቅናት መንፈስ ሲሰማት ይታወቃታል ... ልጁ ኪሩቤል
ይባላል የሀብታም ቤተሰብ ልጅ ሲሆን መልኩም እጅግ
በጣም ቆንጆ ነው ሀና እንኳ አይኗ እያየ ሴቶች ሲጣሉበት
አስተውላለች ግን ይህም ሆኖ ይህችን ተስፋ ያጣች
ምስኪን ታዳጊ ሴት ለውበቷ ቀርቶ ለነገዋ የማትጨነቅ
ሀናን ማፍቀሩ ለሃና ህልም ሆኖባታል በርግጥ ዱርዬ ነው
ትምህርቱን ትቶ ከሰፈሩ ልጆች ጋር የተለያዩ መጠጦችን
ሲጠጣ ነው የሚውለው ግን ከአባቷ አልፎም ከእንጀራ
አባቷ ያላየችውን ፍቅርና እርህራሄ እሱ አይኖች ውስጥ
ታነባለች...
አንድ ቀን ሀና የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመሆኑ
ከትምህርት ቤት በቶሎ ተመለሰች ግን ያየችውን ማመን
አቃታት እናቷ አፀደና ቴድሮስ ተጣልተው ጎረቤት
ተሰብስቧል በጣም ደንግጣ ስትገባ እናቷ ታለቅስ ነበር
ሀናም አብራት እያለቀሰች ከጎኗ ተቀምጣ የሚሆነውን
ማየት ጀመረች ቴድሮስም ለሽማግሌዎቹ "ይሄን ጠላ
መሸጥ ካላቆመች በፍፁም አብረን አንቀጥልም" ይላል
እናቷም "ታድያ ምን ልስራ ተቀምጬ ያንተን እጅ
ስጠባበቅ ልኑር?" ትላለች በርግጥ ስራው እናቷን ቀርቶ
ሀናንም ጎድቷታል ግን ደግሞ ባታቆም ደስ ይላታል
ምናልባት ከኪሩቤል ጋር መገናኘታቸው ስለሚያበቃ ሀና
የእናቷን ጠላ መሸጥ ትደግፈዋለች ... በዛ መልኩም ብዙ
ከተጨቃጨቁ ቡሃላ ሽማግሌዎቹ እሷ እንድታቆም
ወስነው አስማሟቸው....
ይህ ከሆነ ከ2 ወር ቡሃላ ሀና የ10ኛ ክፍል ማትሪክ
ውጤት ልትቀበል ወደ ትምህርት ቤት ሄደች የእንጀራ
አባቷ በርግጥም አሁን እንዳለፈው ግዜ "ካልደፈርኩሽ"
አይልም ነገር ግን እሷ ያለፈውን መርሳት ፈፅሞ
አልቻለችም በዛ ላይ አሁን ከአባትነት ወግ ያለፈ
ቁጥጥር ያደርግባታል ... ሀና ውጤት ስላልመጣላት
እጅግ በጣም ተናዳ እያለቀሰች ወደ ቤት ስትመለስ
ሶፍያን ከአንድ ቆንጆ ወጣት ጋር ቆማ አገኘቻት ሶፊም
አቅፋት እያባበለቻት መከረቻት ከሶፍያ ጋር የነበረውም
የአብስራ የሚባለው ልጅ ይሄ የሷ ብቻ እድል እንዳልሆነ
በመግለፅ ከዚ ቡሃላም ጠንካራ ሆና እንድትማር ነገራት
... ሀና የአብስራን በአይን ብታውቀውም ስለሱ ግን
ምንም የምታውቀው ነገር አልነበረም ሶፊያና ያብስራ
ሀናን ሰፈሯ ድረስ ከሸኟት ቡሃላ ሶፍያ "መጣው" ብላቸው
ወደሱቅ ጎራ አለች ያብስራም ሀናን ፈራ ተባ እያለ "ሀኒ
አላት ሀናም እንደመደንገጥ ብላ ቀና ብላ አየችው
ያብስራም ከኪሱ የተጣጠፈች ወረቀት አውጥቶ በእጁ
ይዞት የነበረው /ፍቅር እስከ መቃብር/ ልቦለድ መፅሃፍ
ውስጥ ከተተውና "ቅድሚያ ይሄን መፅሃፍ አንብቢው
ከዛም ስጨርሺ ወረቀቱን አንብቢው" አለና ሶፍያ
ወዳለችበት ሄደ ....
ሀናም ግራ በመጋባት ምን ሊሆን እንደሚችል
እያሰላሰለች ወደኋላ ዞር ስትል ቴድሮስ ከፊለፊቷ ቆሞ
ሲመለከታት አየችው በጣም ነበር የደነገጠችው እሱም
ከግር እስከራሷ ከገላመጣት ቡሃላ በፍጥነት ወደቤት
ተራመደ ሀናም ገብቶ እናቷን አንድ ነገር እንደሚላት
እርግጠኛ ሆና ተከተለችው ...ልክ ስትደርስ ልክ
እንደገመተችው እየጮኸ ነበር ሀናም አንገቷን ደፍታ በር
ላይ ቆመች ቴድሮስም መፅሃፉን ከጇ ላይ በመንጠቅ
ይሄውልሻ ደብዳቤ ከመፃፃፍም ደርሰውልሻል በዛላይ
ሰው አጥር ስር ...እነዚ ስዶች አለና ዞር ብሎ ሀናን
እንዴት ወንድም እህቱን አፈቀርኩ ይላል ከስጋሽ ጋር
እንዴት ትንዘላዘያለሽ ብሎ በጥፊ መታት ሀናም ፊቷ
በርበሬ መስሎ እንባዋ መንታ መንታ እየወረደ "ወንድም"
የምትለዋን ቃል ደገመቻት ይሄኔ የሀና ወንድም "እማዬ"
ብሎ ጮኸ ዞር ሲሉም አፀደ በድንጋጤ ወድቃለች...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_አምስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90

━━━━
አንቺ ሳትሆኚ አንቺን የወሰደው መንገድ ነው ጠላቴ😔
እንዴት ሰው በሚወደው ስው ላይ ይከፋል?…እንዴትስ በሚወደው ተስፋ ይቆርታል…ብቻ እኔጃ 🕸🦋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እውነት ነው እኔ ፍፁም አደለሁም…በስህተቶች የተሞላም ህይወት ነው ያለኝ…ግን ፈጣሪ ያለው ይሆናል ይህን አምናለው 🦋🙏🏽
:)
ከእለታት አንዱን ቀን🦋

ብቻ ግን እኔ እንዲፈረድብኝ ስለማልፈልግ አልፈርድም…ስለ እኔ የሰማሀቸው አብዛኞቹ እውነት ናቸው…

🎙 ሲፓራ ( ሊዱ )

🦋 @monhappy 🕸
🕸 @BINCJ90
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፴፪~ ( 32 )

ገባህ አይደል ቀዳማዊ? ሁሉም ነገር ጥረት እንደሚፈልግ በነፃ ምንም ነገር እንደሌለ? ነገር ግን ይሄኑ አረዳድ በሌላ እንዳትመነዝረው እኛ ለአንተ የምናደርገው አንተ በምላሹ የሆነ ነገር እንድታደርግልን አስበን ሳይሆን አንተ ያለምንም ድካም የሆነ ነገር እንዳታልምና እንዳታስብ ነው። ኢንጅነር ለመሆን ከፈለክ በነፃ ሳይሆን ማንበብ መጣር አለብህ። እኛን ለማግኘትኮ በጣም ብዙ ጥረሀል። ያለሱ ጥረት ግን በነፃ እኛን አታገኘንም ነበር ለማለት ነው። እሽ ጥረት ከእኛ ጋር አብሮ የሚቀጥል ነገር ነው። አባዛውብህ መሰለኝ " አለና አቶ ሙሉሰው ዝም አለ። ቀዳማዊ ሁሉንም በጥሞና ሲያዳምጥ ከቆየ በኋላ ለራሱ በለሆሳስ " ነፃ ግብዣ የለም! No free lunch!" አለ አቶ ሙሉሰውም ሰምቶት ስለነበር " ጎበዝ ተማሪ እኮ በአንዴ ነው የሚይዘው!" አለ " ያው መሞከር ነው እንጅ ጉብዝናውማ እንግዲህ!" አለ ቀዳማዊ እንደመሽኮርመም እያለ። " አውቃለሁ የገጠር ልጆች ጉብዝናቸውን አይናገሩም በተግባር ነው የሚያሳዩት ከነዛ መሀል እኔም እንዱ ነበርኩ። " ብሎ ሳቅ አለ

ቀዳማዊ ከትምህርት ቤት እንደተመለሰ ሁልጊዜም የተማረውን አልጋው ላይ ቁጭ ብሎ ያጠናል በደንብ ደጋግሞ ያነበዋል። ከዛ ወደ ማታ አስራሁለት ስአት አካባቢ ወጣ ይልና ጊቢ ውስጥ ይንቀሳቀሳል። ታዲያ ሔመንን ሲመለከታት ሁሌም ከትምህርት ቤት እንደመጣች ስትጫወት ያያታል። ሔመን የምትማረው አቡነጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤት ነው ። አንድ ቀን ከሔመን ጋር እኩል ከትምህርት ቤት እንደተመለሱ ሔመንን እንዲህ አላት " ሔሚ " አላት " አቤት ቀዳማዊይ " አለች " ነይ እስኪ " አላት። ሔመንም ወደ ቀዳማዊ ሔደችና " ይሄው መጣሁ " " ዛሬ ትምህርት እንዴት ነበር? ምን ተማራችሁ?" አላት " ሒሳብ፣ አካባቢ ሳይንስ ፣ እንግሊዝኛ ፣ ስነ ስዕል ፣ ግዕዝ ብዙ ነው ብቻ የተሰጠን " አለች " እና የቤት ስራ አልተሰጣችሁም?" አለ " ኧረ ተሰጥቶናል " አለችና እየሮጠች ሄዳ ቦርሳዋን አምጥታ አሳየችው " በይ አሁን እኔም የቤት ስራየን ልሰራ ስለሆነ አንቺም ስሪ ። የቤት ሴራ የማይሰራ ተማሪ መምህር ያንበረክከዋል። ስለዚህ ከትምህርት ቤት እንደተመለሽ ከመጫወትሽ በፊት ምሳሽን መቅሰስሽን ብልት አድርገሽ ትሰሪና ከዛ ሰርተሽ ስትጨርሽ ወደ ጨዋታሽ መሄድ ትችያለሽ ። ነገር ግን ከትምህርት ቤት ተመልሰሽ ወዲያው ወደ ጨዋታ ከገባሽ ይደክምሻል ከዛ የቤት ስራሽን ሳትሰሪ ታድሪያለሽ ጠዋት ላይ መምህሮቹ ያንበረክኩሻል። ሌሎች ተማሪዎችም የቤት ስራ ያልሰራችው ልጅ። እያሉ ይስቁብሻል። ስለዚህ እንደዛ ኤንደሰነፍ ተማሪ መህን ስለሌለብሽ አሁን ጀምሪ እያየሁሽ" አለ።" ግን እኮ መልሱን አላውቀውም ነገ ግን በጠዋት ሄጄ ከጓደኞቼ አይቼ እሰራለሁ" አለች። " እንዴ እንደዚህማ ማድረግ የለብሽም ይሄ እኮ የሰነፍ ተማሪ ባህሪ ነው። በይ አምጭው የቤት ስራውን አብረን እንስራ አላት ሒሳብ ነበር የቤት ስራ የተሰጣት ። ቀዳማዊይም በደንብ አድርጎ ምሳሌውን አስረድቶ የምሳሌው ውጤት እንዴት እንደመጣ አሳይቶ አንድ ተጨማሪ ከቤት ስራ ከተሰጣት ጥያቄ ሰርቶ " በይ ሌሎቹን ባሳየሁሽ መሰረት ስሪ " አላትና ሌላ ንፁህ ወረቀት ሰጣት " ትክክል ከሆንሽ አርምልሽና ከዛ ወደ ደብተርሽ ትገለብጭዋለሽ ተግባባን?" አለ " አወ ገብቶኛል እሽ እሰራለሁ" አለችና የቤት ስራዋን መስራት ጀመረች።
ቀዳማዊ ሔመን የቤት ስራዋን እስክትጨርስ የራሱን ትምህርት እያጠና ይሰራል። ሔመንም ብዙ ቆይታ ጨርሳ አሳየችው። ከአስሩ ጥያቄ ስድስቱን በትክክል መልሳዋለች። ቀዳማዊይም ሳቅ ብሎ " ፐ ጎበዝ ተማሪ አይደለሽ እንዴ! የሚገርም ነው። አሁን አራት ኤክስ ገብቶብሻል ግን ስድስቱን መልሰሻል። ጎበዝ " አለና ከተሳሳተችው አራት ጥያቄ አንዱን በምሳሌ ከሰራላት በኋላ ደግሞ ሶስቱን እንድተሰራና ስህተቷን እንድታርም ደግማ እንድትሰራ ሰጣት። ሔመንም ብዙም ሳትቆይ ባስረዳት መሰረት ሶስቱንም ሰርታ አሳየችው። ሁሉንም ልክ ነበረች። ቀዳማዊ ደስ አለው። " አሁን ደስ አላለሽም?" አላት " በጣም ነው ደስ ያለኝ ሌላም ስጠኝ አንተ እንደ የቤት ስራየ ያለ " አለች " ደስ ይለኛል እንጅ መጀመሪያ እሱን የሸራሽውን ወደ ደብተርሽ ገልብጪ ና ከዛ እኔ ደግሞ እሰጥሻለሁ" አለ ና 10 በጣም ቀላል ጥያቄ 5 መካከለኛ ጥያቄ 5 ደግሞ ትንሽ ከበድ የሚሉ ጥያቄዎችን አውጥቶ የቤት ስራዋን ሰርታ ገልብጣ ስትጨርስ ሰጣት።
ሔመን ሰርታ ጨረሰች። " ይሄው ጨርሻለሁ " አለች ደብተሯን ወደ ቀዳማዊ እያስጠጋች " ኧረ ይች ልጅ ጎበዝ ተማሪ እየሆነች ነው። " አለና ተቀብሎ አየው። ከሀያው ጥያቄ አስራሰባት መልሳለች። ቀዳማዊ በልጅቷ ቅልጥፍናና የ አረዳድ ፍጥነት ተገረመ። " በጣም ጥሩ ስራ ነው ሔሚ የሰራሽው ጎበዝ እሽ የኔ ቆንጆ በቃ ዛሬ ጎበዝ ተማሪ ሆነሽ ጀምረሻል። ከዚህ በኋላ በዚሁ ነው መቀጠል ያለብሽ እንደተነጋገርነው እሽ?" አለ በአዎንታ ራሷን ነቀነቀችና " አሁንም የምሰራው ስጠኝ!" አለች " አይ አሁን ይበቃሻል ደግሞ ተጫወች የጨዋታ ጊዜ ነው። እሽ እንዳትሰለቺ ብየ ነው።" አለ " እሽ እና አብረን አንጫወትም?" አለች " ኧረ አብረን እንጫወት? እሽ በቃ እንጫወት " አለና መፅሃፉን ከድኖ አልጋው ላይ አስቀምጦ ከሔመን ጋር ወጣ። ብዙ ሲጫወቱ ከቆዩ በኋላ ወደ ቤት ገቡ
ማታ ላይ ሁሉም ተሰባሰበ። የአቶ ሙሉሰው እህት ማህደርም አለች። ሔመንም እየሮጠች ከሻንጣዋ ሄዳ የሆነ ነገር አመጣችና " ይሄው አባየ " አለችው " ምንድን ነው ደግሞ ይሄ የኔ ልጅ " አለ " ዛሬ ቀዳማዊ ጋር ሳጠና ነበር የቆየሁት ከዛ የቤት ስራየን አሰራኝና እዛ እሱም ጥያቄ ሰጠኝና አረመልኝ። ይሄው ያገኘሁትን እይ " ብላ በሌላኛው እጇ ወረቀቱን አውጥታ አሳየችው። አቶ ሙሉሰውም ሲያየው ከሀያ አስራሰባት ይላል " ፐ ልትደፍኒውኮ ትንሽ ነው የቀረሽ የኔ ልጅ ጀግናይቱ በይ ለዚህማ ሽልማት ይኖርሻል። በቃ የሚመጣው እሁድ እንወጣና " ቤሮን ሆቴል " እንሄዳለን። ከዛ መዋኘት ትወጂየለ? ትዋኛለሽ? " አለና ሳማት " ሔመንም " አባዬ.....

@monhappy
@monhappy
ለአስተያየት
@BINCJ90
:)
ብቻ ውስጤ እንዲ ይለኛል…ክፉዋች በክፉው ይሸነፋሉ…ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ…የሚፍርዱ ይፈረድባቸዋል…ትዕቢተኞች በትዕቢታቸው ይጠፋሉ…ፍቅር ግን ያሸንፋል…ፍቅር ደሞ እግዛብሔር ነው…ፍርድም የእርሱ ናት።
የግብፅአውያን አማልክት የሚጠቀሙት "ቶ" መሳይ መስቀል እኛ አሁን የምንጠቀመውን ቶ የምንለው መስቀል ነው። ስለ ትክክለኛው ቶ መስቀል ማወቅ ከፈለጉ በዚህ 👇👇👇👇
@monhappy
@monhappy
@monhappy
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፴፫~ ( 33)
ቀዳማዊይንም ይዘኸው ትሄዳለህ አይደል?" አለች " አዎ በደንብ ነዋ ሁላችንም እንሄዳለን። " ደስ ሲል አብረን እንሄዳለን እሽ ቀዳማዊ " አለች ሔመን እየሳቀች። ቀዳማዊም " እሽ አብረን እንሄዳለን " አላት " ግን መዋኘት ትችላለህ?" አለች ቀዳማዊይም ሳብ አለና " አወ በደንብ ነዋ!" አለ " እውነት ትችላለህ? " አለ አቶ ሙሉሰው " አዎ ጋሼ ትልልቅ ባህር ላይ ነበር የምንዋኘው። ገና ህፃን እያለን ወደ ውሃው ውስጥ እያስገቡ ነው የሚያለምዱን " አለ " እና አሁን ትልልቅ የመዋኛ ገንዳ ትዋኛለህ ?" " የፈለገ ቦታ ቢሆን እኔ አልሰምጥም በቃ እየዋኘሁ እሄዳለሁ እወጣለሁ ። የትኝትም ሆነ እንደ አሳ ውስጥ ለውስጥ መሄድ እችላለሁ!" አለ " የሚገርም ነው አሁን እሁድ የምንሄድበት ሆቴል የትልልቆች መዋኛ ገንዳ አለ። እዛ ትዋኛለህ በቃ አለ። ቀዳማዊ እሽ አለና በጣም ደስ አለው። ዋና በጣም ይወዳል። ከሙሉቀን ጋር ገንዘቦቹን ወደ ጥጉ አሰማርተው ባህር ፍለጋ ነበር የሚሄዱት ወንዙ ዳር ያለ ባህር በወራጅ ውሃ የሚሞላ ባህር። እዛ ይገቡና እንደፈለጉ እየዋኙ ውለው። አሸዋው ላይ ሄደው እየተኙ ከእንደገና ደግሞ ከነ አሸዋቸው። የባህሩ አጠገብ ካለ ትልቅ ድንጋይ ይወጡና ቁልቁል ወደ ታች ወደ ባህሩ ይወረወራሉ ከዛ ለብዙ ደቂቃ ውስጥ ለውስጥ ይዋኙና ብቅ ይላሉ። ዋና የማይችል ልጅ ውሃ ውስጥ
ይወረወርና ተደፍቆ እንዲለምድ ይደረግና ያው ስለማይችል ውሃ ይጠጣል። በሌላ ጊዜ ውሃ ላለመጠጣት ሲል ይወራጫል በዛው ዋና ይለምዳል። ታላላቆችም ዝም ብለው አያዩትም ያለማምዱትና ከሰባዎቹ ከእኩዮቹ ጋር እንዲገጥም ያደርጉታል። ከዛ በግጥሚያው ላለመሸነፍ ሲል ያለ የሌለውን አቅሙን ይጠቀማል። እንዴት ማሸነፍ እንዳለበትም ሀሳብ ይነድፋል። ከዛ በግጥሚያውም ላይ አጋጣሚዎቹ " የማን አባት ገደል ገባ የማን አባት ገደል ገባ " ስለሚሉ። ያው አባታቸው ገደል እንዳይገባ በሚል ስሜት የሞት ሽረት ትግል ያደርጋሉ። በዛውም የዋና ችሎታቸው እየጨመረ ይሄዳል ማለት ነው።
" አሁን እያደረከው ያለው ነገር በጣም ትልቅ ስራ ነው። ተባረክልኝ አሁን ትልቅ መነሳሳት ላይ ነች። በጣም ብዙ ለውጦችን እያየሁ ነው። ይሄን ነበር እኔ የምፈልገው። ልጄ ጎበዝ ተማሪ እንድትሆን አክስቷ ያላደረገችላትን ነገር ነው አንተ ገና ከመጀመሪያው ያደረክላት! እና በ።ንብ ያዛት የሔመንን ነገር ለአንተ ሰጥቻለሁ። " አለና አቶሙሉሰው የቀዳማዊን ትከሻ መታ መታ አደረገው። ቀዳማዊይም ሲያጠና ከጎኑ አድርጎ ሔመንን እያስጠና እሱም እያጠና ኤሊያናን ደግሞ ሀሁን ፅፎ ሰጥቶ አስመስላ እንድትፅፍ እያደረገ ማጥንናቱን ተያያየዘው። ሔመንም ከቀን ወደቀን በትምህርቷ እየተሻሻለች ሄደች። አስተማሪዎቿም በአዲስ ጊዜ በመቀየሯ መገረማቸውን ሳይደብቁ ተናገሩ። ያቺ ቀልቃላዋ ሔመን ነፋሷ ሔመን እዚህ ታይታ ከዛ የምትታየዋ ሔመን እየተረጋጋችም ነው። ክፍል ውስጥ መረበሿንም ካቆመች ዋል አደር ብላለች። ከትምህርቷ እንደተመለሰችም ምሳዋን በልታ ትንሽ የካርቱን ፊልም ካየች በኋላ ወደ ቀዳማዊ የማንበቢያና የማደሪያ ክፍል ገብታ ታነባለች። አሁን የተወሰነ ነገር ነው እንጅ ሌላ ምንም ነገር ቀዳማዊን አትጠይቅም።በራሷ ነው የምታነበው። ወይም ደግሞ ራሱ ቀዳማዊ አነባበቧን አይቶ ከበድ ባለ አረዳድ እንድትረዳ ስለሚፈልግ ከበድ ያለውን አሰራር ያሳያታል። በዛ መሠረት የክፍል ትምህርቱ እየቀለላት መጣ። ፈተናዎቿንም እየደፈነች ነው።
በሳምንቱ መጨረሻ አቶ ሙሉሰው በገባላቸው ቃል መሠረት ወደ ቤሮን ሆቴል ይዟቸው ሄደ። የዋና ልብሳቸውን ሰጣቸው። " መጀመሪያ እዚህ የልጆቹ ላይ ዋናህን ካየሁ በኋላ ነው የትልልቆቹ ላይ የምፈቅድልህ " አለ " እሽ አለና የልጆቹ ላይ ገብቶ ቀለል ብሎ ዋኝቶ ወጣ ና " ጋሼ እዛ ልዋኝ ፍቀድልኝ" አለ " እኔኮ እንዳትሰምጥ ብየ ነው! አታያቸውም ትልልቆቹን በዋና አስተማሪ እየተለማመዱ ጥልቀት ስላለውኮ ነው" አለ ቀዳማዊም ሳቅ አለና " ብዙ ጥልቀት የለውም አታየውም የሚያስተምራቸውን ሰውየ እስከየት እንደያዘው?" አለና በእጁ አሳየው ሰውየው እስከ አኔገቱ ነው ያጠለቀው። " ግን ሰውየው ሙሉ ለሙሉ ባይቆምስ? ግዴለህም ልጄ ይቅርብህ " አለ ቀዳማዊይም " ካልክ እሽ ግን ቅርብ ነው" አለ አቶ ሙሉሰውም ለመዋኘት እንደፈቀደ እና እንደጓጓ ስላየ " እሽ በቃ ዋኝ " አለና ለሚያስዋኘው ሰውየ ልጄን እያየኸው" አለው። ሔመንም የልጆቹ ገንዳ ላይ እየዋኘች ነበር። እሷ እንደምትችል ስለሚያውቅ ትኩረቱን ወደ ቀዳማዊ አደረገ። እስካሁን አልገባም ዳር ላይ ራቅ ብሎ ቆመና " ጋሼ እይ " ብሎ ቁልቁል ወደ ገንዳው ተወረወረ። አወራወሩ ያስፈራ ነበር። ገብቶ ዝም አለ አቶ ሙሉሰውም አሁን ወጣ ወጣ እያለ ቢጠብቅም ቀዳማዊ ግን ብቅ አላለም።
የአቶ ሙሉሰው ልብ ያለቅጥ ይመታል። ሔመን ከገንዳዋ ወጣችና ዋናተኞች ራሳቸውን ከሚያደርቁበት አልጋ ተኛች። ዘወር ዘወር ብላ ስታይ ቀዳማዊ የለም ከዛ ሮጥ ብላ ወደ አባቷ " አባዬ ቀዳማዊይስ " አለች " እስካሁን አልወጣም እዚህ ልዋኝ ብሎ ገብቶ ነበር። " አለና ብድግ ብሎ ዋና የሚያለማምደውን ሰውየ እንዲፈልገው ጠየቀው። ዋናተኛውም ገንዳውን ገብቶ ከሁለት እየከፈለ እየዋኘ ይፈልገው ያዘ። የዋናው ገንዳ ረዝም ነው። ቀዳማዊ ከገባበት ጫፍ ጀምሮ እስከመጨረሻው ርዝመቱ እስከ ሀምሳ ሜትር ይሆናል። ከዚህ እስከ ዛኛው ጫፍ ለመድረስ ቢያንስ በትንሹ 20 ደቂቃ ይፈጃል። ቀዳማዊ.....

@monhappy
@monhappy

ለአስተያየት
@BINCJ90
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፴፬~ ( 34 )

ከወዲያኛው ጫፍ ብቅ አለና የትኛት ደግሞ እየዋኘ ወደ ተነሳበት ተመልሶ መጣ። ሁሉም አፋቸውን ከድነው ይመለከቱት ያዙ። ሁሉም ዋናቸውን ትተው ቀዳማዊይን እያዩ ተገረሙ። " በስመአብ እንዴት ነው የሚዋኘው? ደግሞ እኮ ገና ልጅ ነው። " አለች አንዷ በሃያዎቹ አጋማሽ ያለች ዋናተኛ። ሌላኛዋ ጓደኛዋ " በጣም መቼ ለምዶ ነው? " አለች። " እንጃ መቼም አባቱ ነው ከልጅነቱ ጀምሮ አስተምሮት ነው የሚሆነው። በለው እስኪ እየው የጀርባ ሲቀዝፍ እንዴት እንደሚያደርገው። የጀርባ ቀዘፋ ደግሞ በጣም ከባድ ነው በዛ ላይ ።ሀይልና ጉልበት ፍጥነት ይጠይቃል። እሱ ግን ቀለል አድርጎ ነው የሚቀዝፈው። ኡፍፍፍፍ ታድሎ " አለች " ጥበሽው " አለቻት ጓደኛዋ " ህህ ትልቅ ቢሆን ኖሮ አንቺ አትቀድሚኝም ነበር? ኧረ ትልቅ ቢሆንማ እንኳን ጥበሽው ልትይኝ " አለች እየሳቀች። " ይሄ ግን ኤያደገ ጭራሽ የሚገርም ዋናተኛ ነው የሚሆነው። " አለች ። ሁሉም ሰው የራሱን የጎንዮሽ አስተያየት አጠገቡ ላለ ሰው እያወራ ቃዳማዊን ይመለከታሉ። አንዱ ታዲያ " እህ እንዲህ ነው እንጅ መዝናናት መዋኘት መቼም በአለማማጅ ገብቶ ከመወራጨት እንዲህ አይነቱን ጎበዝ ዋናተኛ ልጅ አይቶ መሄድ ይሻላል። እኔ በበኩሌ ከዚህ በኋላ በዋና ልብስ ስራየ ብየ ለመዋኘት ሳይሆን ልጁን ሲዋኝ ለማየት እመጣና ሲጨርስ እኔም እመለሳለሁ። እኔ ዋኝቼ ከማገኘው ደስታ በላይ እሱ ሲዋኝ አይቼ የምደሰተው ደስታ ይበልጣል" አለ ። ሁሉም አንድ ላይ በሳቅ ወደቁ።
ቀዳማዊ የትኝት ተንጋሎ እየዋኜ እነ አቶ ሙሉሰው ያሉበት ቦታ ላይ ደረሰና መሰቃቀያዋን ወይም መሰላሏን ይዞ ቆመ። ቀዳማዊይን ሊፈልግ ወደ ውስጥ የገባው ዋናተኛ እየዋኘ ሲወጣ ቀዳማዊይን ዳር ላይ ሆኖ ተመለከተው። አቶ ሙሉሰው እጁን አፉ ላይ ጭኖ ተገረመ። ሔመንም በቀዳማዊ አወኛኝ ዋና ተገርማ " አባዬ እያየኸው ነው? እንዴት እንደሚዋኝ? " እያለችው ነበር። አሁን ዳር ላይ ቆሞ ሲያዩት ተገረሙ። አቶ ሙሉሰው ተጠጋውና " ልጄ ደህና ነህ?" አለ " አዎ ጋሼ ሰላም ነኝ ምነው አስደነገጥኳችሁ እንዴ? ይቅርታ ጋሼ ቀድሜ መናገር ነበረብኝ ተለቅ ያለ ወንዝ ባህር ምናምን ስንገባ እኮ መጀመሪያ ለብዙ ደቂቃ ያህል መስመጥ ግድ ነው። ቁጥር ይያዝልን ነበር። እኩል ገብተን ቶሎ የወጣ ተሸናፊ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ቶሎ ላለመውጣት እዛው እየዋኘን እንቆያለን። እና ለዛ ነው እኔም ትንሽ ሰምጨ የቆየሁት እሽ አለና አሁንም ደርሼ ልምጣ " አለ ቀዳማዊ አቶ ሙሉሰውም " እሽ ትችላለህ እስኪበቃህ መዋኘት ትችላለህ!" አለ ቀዳማዊይም " አመሰግናለሁ ጋሼ አለና እየቀዘፈ ተመለሰ። አሁን ግን ስላልተደፈቀ ቶሎ ደርሶ ተመለሰ። አሁንም ሰው ትኩረቱ ቀዳማዊ ላይ ነበር። ከዛ አንዷ ሴት ወደ አቶ ሙሉሰው ተጠግታ " ሰላም ነው? " አለችውና ሰላምታ ሰጠችው ሰላምታዋን ተቀብሎ ቀዳማዊን ማየቱን ቀጠለ። " በጣም ጎበዝ ልጅ አለህ? መቼ ነው እንዲህ የለመደው። አወኛኘቱ በጣም ለየት ያለ ነው። አፌን ነው ያስከፈተኝ" አለች። " አዎ ጎበዝ ነው ግን በራሱ ነው እንደዚህ የሆነው። እኔ ምንም አላደረኩለትም የዋና ፍቅርም ችሎታም አለው " አለ። ሌሎች ሰዎችም እየመጡ ለቀዳማዊ ያላቸውን ስሜትና አድናቆታቸውን ገለጡ። የዋና አለማማጁም መጥቶ " ልጁ በጣም ጎበዝ ዋናተኛ ነው! እኔ እዚህ ከተቀጠርኩ በጣም ብዙ ጎበዝ ዋናተኞች አጋጥመውኛል። ግን እንደ አንተ ልጅ አይነት ዋናተኛ አይቼም አጋጥሞኝም አያውቅም እንኳን የልብ የፊት ቀዘፋው ይቅርና የጀርባ ቀዘፋው ራሱ የሚገርም ነው። ይሄ የተፈጥሮ ስጦታ ነው። እንደ እሱ አይነት ዋናተኞች ከስንት አንድ ነው የሚገኙት። የሚገኙትም በገጠራማው የሀገራችን ክፍል ነው። እና ፈቃድህ ከሆነ የዋና ፕሮጀክት እንዲገባ ብታደርገውና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚሆንበትን መንገድ ብታመቻችለት አሪፍ ነው። " አለ " እሽ ወንድሜ አመሰግናለሁ ልጁ ገና ልጅ ነው። አሁን ትምሀርቱ ላይ ነው እንዲያተኮር የምፈልገው። ለማንኛውም በየሳምንቱ ስለምንመጣ የዛሬውን አቋሙን ካየን በኋላ እናወራለን " አለ አቶ ሙሉሰው። " ቀጣይ ሳምንት ትመጣላችሁ? " አለ የዋና አለማማጁ " አዎ ሁሌም እሁድ እዚህ እንደማመጣቸው ቃል ገብቼላቸዋለሁ። ያው ትምህርታቸውን በደንብ ካጠኑ።" አለ " እሽ አመሰግናለሁ " አለ ።
ቀዳማዊ እየተዟዟረ እንደፈለገ ሲዋኝ ቆይቶ ወጣ። "በቃህ ጨረስክ?" አለ አቶ ሙሉሰው እየሳቀ ። ቀዳማዊም ሳቅ አለና " አዎ አሁን እንኳ ጨርሻለሁ!" አለ " ሆ ጉድ እኮ ነው። እኔ መጀመሪያ ተጠራጥሬህ ነበር። ይሄን ያህል የምትችል አልመሰለኝም ነበር በእውነት። አሳ አይደለህ እንዴ ስትዋኝ ላየህ ሰውኮ ሰው ሳትሆን የአሳሁሪት የአሳ ልጅ ነውኮ የምትመስለው ። እንዳለ ሰው ሁሉ ዋናውን ትቶ አንተን ነበር ሲመለከት የነበረው። እንዳለ በአንድ ቀን አድናቂህ በዝቷል። ስትደጋግምማ በቃ ታዋቂ ትሆናለህ። " አለ አቶ ሙሉሰው " አዬ ጋሼ ከእኔ ስንት የሚበልጡ አሉ መሰለህ። የኔ ጓደኛ ሙሉቀን ራሱ ከእኔ ይበልጣል።" አለ። " ኧረ ከአንተ ይበልጣል? ከአንተ ከበለጠማ በጣም ጎበዝ ነው ማለት ነው። ግን ማን ነው እንደዚህ የሚያለማምዳችሁ ስራየ ብለው ነውስ የሚያለማምዷችሁ።" አለ " አይ አይደለም በቃ እኛ ስለምንፈልግና ደግሞ በክረምት ፍየሎቹን ስንጠብቅ እ ደግሞ ከወንዝ ወዲያ ማዶ እርሻ ካለን ማሽላ እየጠበቅን ቆይተን ወደ ቤት ስንመለስ ዝናብ ጥሎ ወንዙ ቢሞላ በዋና ለማለፍ የግድ ዋና መልመድ አስፈላጊ ነው። ካልሆነ ውሃ ይወስደናል ወይም ቤተሰቦቻችን አምነው አይልኩንም። የግድ ስራውን እንድንሰራ ከፈለጉ ደግሞ አሻግረውን ይመለሳሉ። ታዲያ ማታ ላይ እነሱ ካልመጡ ማን ያሻግረናል? ስለዚህ ያለን አማራጭ እነሱንም ላለማድከም ዋና ገና በልጅነታችን መለማመድ ነው። የውሃውን ግፊት ከላይ ሲመጣ ቆመን መቋቋም አለብን። እሱን ደግሞ ከታች ራቅ ብለው ውሃው ላይ ቆመው ያለማምዱናል። ወራጁ ወንዝ ላይ ስንቆም የቆምንበት አሸዋ እየተሸረሸረ እግራችንን .....


ከወደዳችሁት ለወደዳችሁት!
👇
@monhappy
@monhappy

በቻናሉ ላይ እንዲሁም በድርሰቶቼ ላይ አስተያየት ካላችሁ @BINCJ90 ላይ ፃፉልኝ!
Afterglow
Ed Sheeran
🎶Join @monhappy
:)
…ብቻ እንዲህ አስባለው…

ቀጥሎ ምን እንደሚፈጠር እኔጃ…እኔም እንደ እናተ አላውቅም…ግን ፈጣሪ ጥሩውን ነገር ያብዛልን…አዋ እኛ ለመኖር ብለን ብዙ ጊዜ አልኖርንም…ነገን እያልን ብዙ ዛሬዋች አልፈውናል…


🎙 ኑኑ

🖤 @monhappy 🖤
🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩🏩

ከአንድ እብድ ለዶክተሩ የተፃፈ ድብዳቤ…

በእብዶች አለም ጤነኛ የለም ይባላል። እናማ ዶክተር እንዴት ነሽልኝ?… እኔ እብድ ጓደኞቼ ይመስገኑ በጣም ደህና ነኝ… ዛሬ ይህን የፃፍኩልሽ መፃፍ ስለምችል አይደለም የፃፍኩልሽ ከመስሪያ ቤትሽ ለእኛ ደግሞ ከማገገሚያችን እንደምትወጪ ሰምቼ ነው።…ከእኛ የተሻለ እብዶች ወዳሉበት እንደምትሄጂ ሰምተን ጨንቆናል።

እኔ እብደቴን ይንሳኝ እልሻለሁ እንደ አንቺ የተማረ እብድ ማለቴ ዶክተር አይቼ አላውቅም…እኔ የተለያዩ ቦታዎች አብጃለሁ ነገር ግን እንደዚህ ደስ የሚል እብደት አጋጥሞኝ አያውቅም…በተለይ ደሞ ስትመክሪን በጣም ነው የማዳምጥሽ…አንዴ ትዝ ይልሽ ከሆነ ህይወት ለእናንተ ምንድን ነው?ስትይን እኔ እጄን አውጥቼ …ህይወት ለእኛ አዲሷ የተቀጠረችው ፅዳት ናት…ህይወት አበራ ትባላለች… እናማ ዶክተር ህይወት ፅዳታችን ናት ስልሽ የሳቅሽው ሳቅ ዛሬም ድረስ እረስቼዋለሁ።

እኛ እብዶች ስንባል ሁሉም ሰው አንደኛ ይመስለናል እኛ ሲርበን ሌላው የሚርበው… እኛ ሲከፋን ሌላው የሚከፋው ይመስለናል…

እናማ ዶክተር መሄድሽ እኛን ያሳብደናል እና እንዳትሄጂ… አይ እሄዳለሁ ካልሽ ግን ዝውውር ሞልቼም ቢሆን እመጣለሁ ያለ አንቺ ማበድ እኔ አልችልም…

ደሞ ደሞ ባለፈው ዶክተር አሸናፊ ሰብስቦ እየጠየቀን ሳለ ቢንያም ተነሳልሽ እና ዶክተርን እንዲህ አለው…
"ዶክተር እኔ ጥያቄ አለኝ …"አለው…ዶክተርም ቢንያምን ጠይቀኝ ምንድን ነው ሲለው "አይ ዶክተር ተመልሶልኛል… መጠየቅ እንደምችል ነበር መጠይቅ የፈለኩት" አለው… ሁላችንም ስንስቅ ቢንያም ተነስቶ አመሰግናለሁ ብሎን ተቀመጠ… አይ ቢኒ …ምስኪን እብድ እኮ ነው…

ይህን ደብዳቤ የፃፍንልሽ ማለቴ የፃፍኩልሽ ወረቀቱን ከቢሮ ሰርቄ ነው… ደሞ ሌባ ሆኜ አይደለም …ሰው የሌለውን እና የሚያስፈልገውን ነገር በነፃ ማግኘት ስለማይቻል ነው… ደሞም ይህን ስፅፍልሽ ህይወት አይታኝ" አንተ ወገኛ እያሳልክ ነው…" አለችኝ እኔም " ኧረ ጉንፋኑ እንኳን ተሽሎኛል ማሳሉም ትቶኛል…" ስላት አይ የእብድ ነገር ብላኝ ሄደች አይ ህይወት ታሳዝነኛለች እኮ…

ኧረ ዶክተር እረስቼው …አንዴ ምን ሆነ መሰለኝ አንቺ ያልነበርሽ ቀን… አመት በዓል እያከበርን ሁላችንም ተሰብስበን ነበረ…እና ሁላችንም የፈለግነውን እንድንነጋገር እድል ተሰጠን ከዛማ ሁሉም እየተነሳ ለፈለፈልሽ ከዛ አንተም አውራ ብለው መድረክ ላይ አወጡኝ …እኔም ከማወራ ግጥም ላንብብ አልኳቸው …ሁሉም አዎ አታንብብልን አሉኝ ከዛማ ጀመርኩልሻ…

የግጥሜ ርዕስ… "ርዕስ የለውም ነው"

ግጥም ፅፌያለሁ ግን ርዕስ የለውም:
እናንተ ንገሩኝ ሌላ የምጠይቀው የለም:
እወዳታለሁ:
እንዳልነግራት እፈራታለሁ:
ብነግራት ደሞ እብድ ነው እባለለሁ:
እናማ ለዛ ነው ግጥሜ ርዕስ የሌለው::

ብዬልሽ ልቀመጥ ስል ጓደኞቼ እንዳለ… ከዛስ ከዛስ እያሉ ቤቱን ረበሹት …እኔም ከማስታወቂያ በኋላ ይቀጥላል ብያቸው ገባሁ እልሻለሁ…ይህ ኋላ የማወራልሽ እንዳትሄጂ ነው… አንቺ ከሄድሽ የሚሰማን አይኖርም አንቺ ከሄድሽ አመት በዓል እራሱ የምናከብር አይመስለኝም…

ይህን ሁላ ብዬሽ ግን መሄድ አለብኝ ካልሽ በሀሳብሽ እኔ እስማማለሁ ጓደኞቼ ግን የሚስማሙ አይመስለኝም …ግን እኔ እየደበደብኩም ቢሆን አስረዳቸዋለሁ…

እናማ ዶክተር… ሁሉም ወደማሸለቢያ እየገቡ ነው ትተውኝ እንዳይሸለቡ ልገባ… ይህንን ደብዳቤ በርሽ ላይ አስቀምጬልሻለሁ ከዛ ትዝ ስንልሽ ብቻ አንብቢው… በመጨረሻም ዳኒ ያለሽን ልንገርሽ ተሰብስበን ቀጭ ብለን እያለ…
"ሄደን እጅዋ ላይ ወድቀን ይቅርታ እንበላት ምንአልባት እኮ በእኛ ምክንያት ይሆናል የምትሄደው" አለን ግን እውነቱን ይሆን እንዴ… እኛ እብዶች ስንባል እንደሆነ ቀልብ የለንም …ካስከፋንሽ ደግሞ እንቀጣ ለአንድ ሳምንት ከቤት አንውጣ ካላመናችሁም ደሞ ይቆለፍብን… በእኛ ምክንያት አንቺ መሄድ የለብሽም…እናማ እኛ እንቀጣ…

ሌላ ቀን እስኪብርቶ እና ወረቀት ሰርቄ እፅፍልሻለሁ እስከዛው ግን ሰላም ብለናል…

የአንቺው እብዶች!…
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_5

...🖊የሀና እናት ሆስፒታል በቶሎ ባትደርስ ምናልባትም
ህይወቷ አደጋ ላይ ይወድቅ እንደነበር ዶክተሮቹ
ተናግረው ሲያበቁ ሌላም የምስራች ይሁን መርዶ ለሀና
ያልገባትን ነገር አበሰሩ አፀደ እርጉዝ ነች ሀና ምንም
እንኳ እህት ወይ ወንድም ልታገኝ መሆኑን ብታውቅም
ከደስታ ይልቅ ጭንቀት ነበር የሚሰማት ያን ግዜ ወደኋላ
ተመልሳ አሰበችው የእንጀራ አባቷ አብሯት ሲተኛና
እስከዛሬ ከውስጧ ተፍቆ ሊወጣ ያልቻለው የህሊና
ቁስሏ ታወሳት በዛ ላይ እናቷ ስትወልድ ብዙ ትሰቃያለች
ይሄ ሁሉ ተደማምሮ ሀናን "ህልም በሆነ" ሲያስብላት
የእንጀራ አባቷ ቴድሮስ ግን በደስታ ፈነደቀ "ልጄ እህት
ሊያገኝ ነው..." አለ በምፀት ፈገግ ብሎ ሀና ይህን
ንግግሩን በሰአቱ ባታስተውለውም እያደር ግን እሷን
ማግለል ፈልጎ እንዳለ ስትረዳው ብቸኝነት ተሰምቷት
ከልቧ ታነባለች...
አፀደ ከሆስፒታል ወታለች ይሄኔ ሀና ከ3 ቀን በፊት
ስለተፈጠረው እናቷን መጠየቅ ፈልጋ "እማ" አለች
አንገቷን ወለሉ ላይ እንደሰካች "ወዬ ልጄ" አለች አፀደ
"ያአብስራ ምኔ ነው ደግሞም ቴዲ እንዳለው አይደለም
ምንም አላረግንም አላውቀውም ነበር ዛሬ ከሶፊ ጋር
መቶ..." እንባዋ እየቀደመ ንግግሯን አላስጨርስ አላት
አፀደም በልጇ የእውነቷን እየተማመነችና የልጇን እንባ
እየጠረገችላት "ልጄ ይሄ የኔና የአባትሽ ጥፋት እንጂ
ያንቺ አይደለም ያብስራ ያባትሽ ልጅ ነው ብዙ ወንድሞች
አሉሽ እናም ልጄ እኛ ካላስተዋወቅናቹ ጥፋቱ የኛ ነው!"
አለችና በሻርቧ እንባዋን ጠራረገች ሀናም የምትመልሰው
አታ የእናቷን ንግግርና ሁኔታ ብቻ ማጤን ቀጠለች
ዝምታዋ ያስፈራት እናት ልጇን ቀና አድርጋ አይኖቿን
ለማንበብ እየሞከረች "ልጄ ፍቅር ይዞሻል ?" ብላ
ጠየቀቻት ሀና እንደዚ በግልፅ አውርታ ስለማታውቅ ልቧ
ስንጥቅ አለ "መልሺልኛ" አለች እናት ሀናም ድምፅጿ
እየተቆራረጠ "እኔ ወንድ ልጅ እፈራለው ሁሉም
የሚደፍሩኝ ይመስለኛል..." አለች አፀደም ደንገጥ ብላ
ልጄ ያስገደደሽ ወይንም ሊደፍርሽ የሞከረ ሰው አለ? ብላ
ጠየቀቻት ሀናም በስሞት ከተቀመጠችበት ተነስታ አዎ
ስትል ቴድሮስ ኮቴ እንኳ ሳያሰማ ዘው ብሎ ገብቶ እናንተ
ምን እያወራቹ ነው አለ የወሬው እንቅፋት ለመሆን
እንደሆነ ዳያስነቃ አዲስ ወሬ ጀምሮ ያን ሰአት አረሳሳቸው
... ከዛም ሀናን በዘዴ ካሶጣት ቡሃላ አንድ ቃል ትንፍሽ
ብትል እናቷንም እሷንም እንደሚገላቸው አስፈራራት...
ሀና ውጤቷ ለመምህርነት በቂ ስለነበር ኮተቤ መምህራን
ኮሌጅ ለመማር ምዝገባ መከታተል ጀምራለች ሀና ብዙ
የምታስባቸው ነገሮች አሉ በእውነቱ ሀና እጅግ በጣም
ውብ ነች ነገር ግን ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች ውበቷን
ሲያደንቁ እየቀለዱባት እስኪመስላት ድረስ
አታምናቸውም ይሁን እንጂ ሀና ልቅም ያለች የቀይ ዳማ
ከለር ያላት ውብ ነች በተለይ አሁን እያደገች ስትመጣ
አይቶ የማይመኛት የለም ... ሀና የኮሌጅ ትምህርቷን
በተመዘገበች በሳምንቷ የአብስራን መንገድ ላይ
አገኘችው ያብስራ ሲያያት በጣም ደስ አለው እሮጦም
አቀፋት ሲያቅፋት ሀና በጣም ነበር የደነገጠችው ...
ያአብስራ ያፈቅራታል ግን ደግሞ ወንድሟ ነው እሱ ይህን
አያውቅም ... ሀና እንባዋ ዱብ ዱብ አለ ያብስራም ግራ
ተጋብቶ ምን እንደሆነች ሲጠይቃት ትታው እሮጠች... ያን
ቀን ስትሮጥ ድንገት ቤታቸው ጠላ ሲጠጣ
የተዋወቀችው ኪሩቤል ከጓደኞቹ ጋር በተለምዶ(ድድ
ማስጫ) የሚባለው ቦታ ተቀምጧል ሀና አላየችውም
ስለያብስራ እያሰበች እንባዋ ይዘንባል ነገሮች በሙሉ
ድብልቅልቅ ብለውባታል እድለ ቢስነቷን እያሰበች
ፈጣሪዋን እያማረረች ስታልፍ ኪሩቤል "ሀኒ" ብሎ ጠራት
ዞራ ስታየው ደነገጠች ...ኪሩቤልም እንባዋን እየጠረገ
ምን "ሆነሽ ነው" ሲል ጠየቃት ሀናም እንባዋ መውረዱ
ሳያቆም ፈገግ ለማለት እየጣረች "ምንም" አለችው
ኪሩን ስታገኘው ውስጧ የማታውቀው ስሜት ተሰምቷታል
ይህ ስሜት የሀዘን እንዳልሆነ ደግሞ እርግጠኛ ነች ...
ኪሩቤል እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አርጎ ሰፈር ድረስ
ሲሸኛት ሁለቱም አይነጋገሩም ነበር ሰፈር ደርሳም "በቃ
ተመለስ ደርሻለው" ስትለው "እሺ ሀኒ ግን ሳልነግርሽ
አልሄድም በጣም ደስ ትይኛለሽ ማለቴ..." ብሎ
ንግግሩን ሳይጨርስ የእንጀራ አባቷ ከየት መጣ ሳይባል"
አንቺ ስድ ለምን አንደኛሽን ሴተኛ አዳሪ አትሆኚም
ጭራሽ ከማንም ሰካራም ዱርዬ ጋር " ሲል ሁለቱም
ቀልባቸው ተገፈፈ... ሀናም የኪሩቤልን እጅ አስለቅቃ
ወደ ቤት እሮጠች ግን በዚ አላበቃም ነበር ቴድሮስ
ተከትሏት ገብቶ ከእናቷ ፊት ከወረደባት ቡሃላ "እዚ ቤት
ላይሽ አልፈልግም ውጪ" ብሎ አሶጣት ሀናም
ከመውጣቱ በላይ እየደረሰባት ያለው በደልና የእናቷ
ጉዳይ እያሳሰባት ቤቱን ለቃ ወጣች...
ሀና ምንም ዘመድ የላትም መሄጃዋንም አታውቅም ብቻ
የሷ መፅናኛ እንባዋ ነውና እያነባች አንድ መቃብር ስፍራ
ሄደች ይሄኔ የቴድሮስ ግፍና ስድቦች በእናቷ ላይ
የማገጠው... ሲደፍራት የኖረው እንዲሁም ዛሬ
የተናገራት "...የትም ስትንዘላዘይ ቆይተሽ መተሽ ልጄን
HIV እንዳታስይዥው አንቺስ ጉዳይሽ" ያላት አፀያፊ
ንግግር አይምሮዋ ላይ ተመላለሰባት እናም እራስዋን
ለማጥፋት ገመድ ማዘጋጀት ጀመረች...

#ይቀጥላል...

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90

━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
2025/07/10 08:28:04
Back to Top
HTML Embed Code: