Telegram Web Link
🇪🇹 እንኳን ደስ አለን ኢትዮጵያ የካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ አለፈች 🇪🇹
፡ ከህይወት ማህደር…ከእስዋ ጋር👫

ሌላው የሌላ ነው…እኔም የሌሎች አደለሁም ሌሎችም የእኔ አደለሁም…ዳሩ ግን እኔ ፀሐፊ ነኝ…ፍቅር ግን ለእኔ ውለታ አደለም…




🍂 @monhappy 💙
♥️ @BINCJ90 🦋
የቅዳሜ ቀደዳ-19(፲፱)
እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ?
ቅዳሜ ነውና እንደተለመደው ፈካ፣ ዘና፣ ፀዳ ልናደርጋት ተከስተናል!
እስቲ ዝም ብለህ አንዴ አስበው!
እንግሊዝ፣ እስራኤል እና ፈረንሳይ አንድ ላይ ሆነው ጦርነት ቢከፍቱብህ ምን ትሆናለህ? ምን ይውጥሃል? የት ትገባለህ?
ምን መሰለህ አባዬ?
ሰሞኑን "Suez Canal"ን ስለዘጋችሁ መርከብ እና ስለተፈጠረው ውጥንቅጥ ስሰማ ግብፅ እና ጀግናው መሪያቸው "Gamal Abdel Nasser" ትዝ አለኝ!
እንፈታታው፣ እናውርደው፣ አቅልለን እናውራው!
በቀላሉ "Suez Canal" አርቴፊሻል በሆነ መንገድ የተሰራ ቦይ(ማሳለጫ) ሲሆን "ቀይ ባህር" እና "ሜድትራኒያን ባህር" በቀላሉ የሚገናኙበት መስመር ነው። ይህ ማሳለጫ ከመገንባቱ በፊት የንግድ መርከቦች ያላቸው ብቸኛ አማራጭ በአትላንቲክ ውቅያኖስ አድርገው አፍሪካን በታች በኩል ዞረው የህንድ ውቅያኖስን ማቋረጣቸው ግድ ነበር። አድካሚ ነው፣ ነዳጅ ይበላል፣ ጉልበት ይበላል፣ ለደህንነት አደጋ ነው፣ ረጅምምምም ቀናቶችን ያኝካል። አፍሪካን ከመዞር እና ረጅም መንገድ ከመሄድ በቀላሉ ኤስያ እና አውሮፓን በውሃ ማገናኘት የሚቻልበትን መንገድ አጠኑ። ለዚህ ደግሞ ምቹ ቦታ ላይ የተቀመጠችው ግብፅ ነበረች። እ.ኤ.አ 1859 ላይ አንድ የፈረንሳይ ዲፕሎማት በወቅቱ የግብፅ መሪ የነበሩትን "Ismail Pasha"ን አነጋግሮ በግብፅ በኩል ቀይ ባህር እና ሜድትራኒያን እንዲገናኙ በማሰብ አርቴፊሻል ቦይ(canal) እንዲቆፈር ተስማሙ። ቁፋሮው እና አጠቃላይ ግንባታው ላይ 1.5 ሚልዮን ግብፃዊያን ተሳተፉ! የሲና በረሃ ሙቀት እና የተለያዩ በሽታዎች ታክለውበት ከ 125 ሺህ በላይ ግብፃዊያን በቁፋሮው ወቅት ህይወታቸው አለፈ! በመጨረሻም 10 ዓመት ፈጅቶ የዛሬ 151 ዓመት ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። ግዜውን ለማዛመድ አፄ ቴዎድሮስ ያረፉት "Suez Canal" ከመከፈቱ አንድ አመት ቀደም ብለው እ.ኤ.አ 1868 ላይ ነበር!
ከዛስ?
በግብፃውያን ደም እና አጥንት የተገነባው "Suez Canal" በኢምፔሪያሊስቷ እና ቀኝ ገዢዋ እንግሊዝ ቁጥጥር ስር ወደቀ። እንግሊዝ እንደፈለገች ከፈረንሳይ ጋር በ "Monopoly" ይዛው ማሳለጫውን ትነግድበት፣ ታተርፍበት እና ትንፈላሰስበት ተያያዘችው። ግብፅ እ.ኤ.አ 1922 ላይ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ ብትወጣም "Suez canal"ን ግን አሳልፋ አልሰጠችም!
ታሪክ ሲቀየር!
ኮሎኔል "Gamal Abdel Nasser" እ.ኤ.አ 1956 ላይ መፈንቅለ መንግስት አድርጎ የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆነ። ሃገር ወዳድ፣ ቆራጥ እና ግርማ ሞገሳሙ "Gamal Abdel Nasser" የ "Suez canal" ከፈረንሳይ እና መሰሪዋ እንግሊዝ ቁጥጥር ስር እንዲወጣ እና ሙሉ በሙሉ በግብፅ ባለቤትነት እንዲተዳደር ወሰነ። ውሳኔው ግን አደገኛ ነበር! የዓለማችን ሃያላን ሃገራት ከአዲሱ የግብፅ ፕሬዝዳንት ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር መባጠስ ጨመሩ። አሜሪካ እና እንግሊዝ የአስዋን ግድብን ግንባታ በገንዘብ ለመርዳት ሳይቀር ቃል ገቡ። ሰውየው ግን ኮሚዩኒስቶቹን መወዳጀት መረጠ። ሃገሩ ከእስራኤል ጋር የገባችው ሰጣ ገባ ስላሳሰበው ብዙ የጦር መሳርያዎችን "ከቼኮዝሎቫኪያ" ሸመተ። ቀጠል አድርጎ ከቻይና ጋር ተሻረከ። በዚህ ንዴት እንግሊዝ እና አሜሪካ የአስዋን ግድብን ግንባታ በገንዘብ ለመደገፍ የገቡትን ቃል አጠፉ!
"....ከዛሬዋ ምሽት በኃላ የግብፅ የግል ሃብት የሆነው የስዊዝ ካናል በግብፃዊያን ባለቤትነት ስር ይተዳደራል!ግብፃዊያን ይህንን ማሳለጫ የቆፈሩት በአጥንታቸው እና በደማቸው ነው። የአስዋን ግድብን ግንባታ እውን ለማድረግ በገንዘብ አሜሪካ እና እንግሊዝ ባይረዱንም ከማሳለጫው በምናገኘው ገንዘብ እንገነባዋለን! ወደኃላ መመለስ የለም!...."ብሎ "Gamal Abdel Nasser" ተናገረ። እንዳለውም እ.ኤ.አ ሃምሌ 26,1956 ላይ "Suez Canal" ከዛሬ ጀምሮ የግብፅ ሃብት እንደሆነ በይፋ አወጀ! የግብፅ ህዝብ በደስታ ጮቤ ረገጠ!
በዛኛው ጎራ!
እንግሊዝ የአረቡ ዓለም አምባገነን ብላ የምትጠራው "Gamal Abdel Nasser"ን ማስወገድ እንዳለባት አሰበች። ፈረንሳይም በዚህ ተስማማች። አሜሪካ ግን "...ይቅርባችሁ! ጦርነቱን መክፈት የአረቡን ዓለም ማመስ እና ለራሽያ ተጨማሪ ወዳጆችን መፍጠር ነው!..." ብላ ተማፀነች!
ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ግን ለጦርነት ቋምጠዋልና እስራኤልን በድብቅ ወደ ፓሪስ ጋብዘው ለሶስት ቀመሩ!
ቀመሩ በአጭሩ!
"...እስራኤል ግብፅን እንድትወር እና በዚህ መሃል ፈረንሳይ እና እንግሊዝ አስታራቂ መስለው እንዲገቡ፤ ከዛም ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ወክለው ጦርነት ውስጥ ያሉት ሁለቱ ሃገራት(ግብፅ እና እስራኤል) ከ "Suez Canal" አካባቢ ጦራቸውን እንዲያነሱ ግፊት እንዲያደርጉ፤ ይህንን ውሳኔ እስራኤል እንደምትቀበል ነገር ግን ግብፅ አሻፈረኝ ስለምትል ያኔ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በቀጥታ ከግብፅ ጋር ወደ ጦርነት እንዲገቡ!.." ነበር!
ወደ ስራ!
እንደተቀመረው እስራኤል ግብፅ ላይ ጦርነት ከፈተች! እንግሊዝ እና ፈረንሳይ አስጠነቀቁ! እንደተፈራው ግብፅ የ "Suez Canal" አካባቢን አለቅም አለች!
ከዛማ ጌታዬ!
ለሶስት ተባብረው ግብፅ ላይ እሳት አዘነቡ! የጦር ካምፖቿ አመድ ሆኑ! መሰረተ ልማት ወደመ፣ ህይወት ጠፋ፣ መሰረታዊ የሚባሉ የግብፅ ቦታዎችን በሶስቱ ሃገራት ወታደሮች ቁጥጥር ስር ወደቁ! ወደ 600 የሚሆኑ የግብፅ ወታደሮች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ተገደሉ! ከሶስቱ ሃገራት ግን ከ 30 በላይ እንኳን ወታደር አልሞተም። "Nasser" ያለው ብቸኛ አማራጭ የ "Suez canal" አገልግሎት እንዳይሰጥ ወደ 40 የሚሆኑ ግዙፍ መርከቦችን በማስመጥ መዝጋት ነበር!
እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና እስራኤል ለሶስት ተባብረው ክፉኛ የወጓት ግብፅ ወዳጅ አጣች! ነገር ግን በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ አሜሪካ እና ራሽያ ግብፅ ላይ የተፈፀመውን በደል በጋራ አወገዙ። በወቅቱ የራሽያ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት "Nikita Khrushchev" በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ፈረንሳይ እና እንግሊዝ የሚያደርጉትን ካላቆሙ "ፓሪስን" እና "ለንደንን" በሚሳይል እንደሚደበድቡ አስፈራሩ። በመጨረሻም እስራኤል፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በደረሰባቸው ጫና ምክንያት ተኩስ አቁም ላይ ደረሱ! የእስራኤል ጦር የሲና በረሃን በአሜሪካ በኩል ጫና ደርሶበት እንዲለቅ ተደረገ! የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሃይልም ጣልቃ ገባ! ቆራጡ እና ሃገር ወዳዱ የግብፅ ፕሬዝደንት "Gamal Abdel Nasser" የሃገሩ ህዝቦች እንዳለው በደም እና በአጥንት የገነቡትን ሃብት እንካችሁ አላቸው!
ሃቅ!
"War" ወይም "ጦርነቱን" ሶስቱ ሃገራት አሸነፉ። "Battle" ወይም "አውደ ውጊያውን" ግን ግብፅ አሸነፈች። የዲፕሎማሲ ብቃቷን ተጠቅማ ሶስቱ ሃገራት በተግባራቸው እንዲያፍሩ አደረገች! የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ተሸማቀው ስልጣን ለቀቁ! "Nasser" የግብፅ ብቻ ሳይሆን የአረቡም ዓለም ጀግና ሆነ። የአውሮፓ ኢምፔሪያሊስቶችን አንገት ማስደፋትም ቻለ። ራሽያ፣ አሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም(UN) ከግብፅ ጎን እንዲቆሙ ማድረግ ቻለ!
አንዳንድ ገራሚ ነገሮች!
"Suez canal" 193 ኪሎ ሜትር ይረዝማል፣ ጥልቀቱ ደግሞ 24 ሜትር ነው! በፊት ይደረገ የነበረውን ጉዞ ከ 5000 ኪሎሜትር በላይ ቀንሶታል!
የዓለማችን እረፍት አልባው እና ረጅሙ ማሳላጫ የሚባለው "Suez Canal" የእስያ እና አውሮፓ ሃገራት በቀላሉ እንዲገናኙ፣ እንዲነግዱ እና እንዲተሳሰሩ አድርጓል። 12% የሚሆነው የዓለማችን ንግድ የሚተላለፈው በዚህ ቦይ(canal) በኩል ነው። 20% የሚሆነው ነዳጅ ከአረብ ሃገራት ወደ አውሮፓ የሚሻገረው በዚህ በኩል ነው። ግብፅ ከዚህ ማሳለጫ በቀን 15 ሚልዮን ዶላር ታገኛለች! በየአመቱ እስከ 6 ቢልዮን ዶላር ድረስ ገቢ የምታገኝበት ትልቅ ሃብቷ ነው። ወደ 10 ቢልዮን ዶላር የሚሆን የካርጎ እቃ በየቀኑ የሚያልፈው በዚህ በኩል ነው። በ "2018" ብቻ ከ "18 ሺህ" በላይ ግዙፍ መርከቦች 1.1 ቢልዮን ቶን የሚሆን ካርጎ ይዘው በዚህ ማሳለጫ በኩል አልፈዋል። ጌታዬ በቀን ከ 50 በላይ መርከብ ያልፍበታል!
ይህ ማሳለጫ ለግብፃዊያን የኢኮኖሚ ዋልታ፣ የንግድ መተላለፊያ እና ዶላር መሰብሰቢያ ብቻ ሳይሆን የሃገር ሉዓላዊነት መገለጫም ጭምር ነው።
እንደምታውቀው ባለፈው ሳምንት አንድ ካርጎ የጫነ መርከብ በማይታወቅ ምክንያት ማሳለጫው ውስጥ ተቀርቅሮ ዓለም የምትገባበት ጠፍቷት ነበር! የነዳጅ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የምግብ ዋጋ ሳይቀር ጨምሯል! አውሮፓ እና ኤስያ መግቢያ እና መውጫ ጠፍቷቸው ሰንብተዋል። ግብፅም ብትሆን በዚህ ምክንያት በቀን እስከ 12 ሚልዮን ዶላር አጥታለች! ማሳለጫው አሁን ላይ ድጋሚ ተከፍቶ ወደ ስራ ገብቷል!
ማጠቃለያ!
ግብፅ ሆይ! በዚህ ጋር "Suez canal"ን ይዘሽ፤ በዚህ ጋር ደግሞ አባይን አትንኩብኝ ብለሽ ትዘልቂዋለሽ ወይ? ግድ የለም እንተሳሰብ! በዓመት ከማሳለጫው የምታገኚው ዶላር ብቻ እኮ የኛን አጠቃላይ አመታዊ በጀት ይገዳደራል!
መልካም ምሽት ይሁንላችሁ!

(የዘገየ ቢሆንም ከመቅረት ይሻላል)

@monhappy
@BINCJ90
የቅዳሜ ቀደዳ 20-(፳)
እንዴት ነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? እንደተለመደው ቅዳሜን ልናፈካት ተከስተናል! ዛሬ 20ኛ ሳምንታችን ላይ ደርሰናል!
እኔ የምልህ?
እነሱ ጋር "Generation (ትውልድን)" አብጠርጥረው ማጥናት ጀምረዋል። ትውልዶች የሚጋሩትን፣ አንድ የሚያደርጋቸውን እና መገለጫ የሆኑ ባህሪያቸውን በስፋት እየነገሩን ነው።
ለማንኛውም!
እ.ኤ.አ ከ "1981 እስከ 1996" ባሉት አመታት ከተወለድክ ወይ ከተወለድሽ "Millennial Generation" ወይም "ሚሊኒያል ትውልድ" ይሉሻል/ ይሉሃል።
የ "Millennial" ትውልድ መገለጫዎች ብዙ ናቸው። ብዙ ጥናቶችም ተደርጎባቸዋል። አብዛኛዎቹ በዚህ ትውልድ ተወልደው ያደጉ ሰዎች ዓለም በቴክኖሎጂ በተሳሰረችበት እና "digital" በሆነችበት ወቅት ነው። አብዛኛዎቹ "Millennial" ትውልዶች "Global Citizen" ወይም "ዓለም-አቀፋዊ ዜጎች" ናቸው። እራሳቸውን ወደ ብሄራቸው ወይም ወደ ሃገራቸው ከመውሰድ ይልቅ "ዓለም አቅፋዊነት" ላይ ያመዝናሉ። ብሄሩ ወይም ሃገሩ ላይ እየተፈጠረ ስላለ ችግር ስታወራው "ምን አገባኝ!" ሊልህ ጭምር ይችላል። የተሻለች ዓለምን ማየት ላይ ያተኩራሉ! ብዙዎች ይህ ባህሪያቸው "ሃገር ወዳድ(patriotic)" እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል ሲሉ ሌሎች ደግሞ ከብሄራቸው ወይም ከሃገራቸው ወጥተው "ዓለም አቀፋዊነት" ላይ እንዲያተኩሩ ስላደረጋቸው መልካም ነው ይላሉ።
"Millennial" ትውልዶች ብዙ መገለጫዎች አሏቸው! ዋናው መገለጫቸው ግን "ስንፍና" ነው። የስንፍና ጥጎች ናቸው ይባላል! ቁጭ ብለው ደሞዝ ቢበሉ አልያም ቁጭ ብለው ከጓደኞቻቸው ጋር ጌም እየተጫወቱ ቢውሉ ደስታቸው ነው። ስራ አይወዱም! ጉልበታቸው የሚያልቅ ይመስላቸዋል።
በጣም ትንሽዬ ነገር ሰርተው ነገር ግን ትልቅ ነገር እንደሰሩ(እንዳሳኩ) እንዲታሰብላቸው ይፈልጋሉ። ትንሽ ሰርተው ኒዩክለው እንዳበለፀገ ሰው ሊጀነኑ ይችላሉ። ስለ ሁሉም ጉዳይ አዋቂ መስለው መታየት ይወዳሉ። ስለ ሙዚቃ፣ ኪነ ጥበብ፣ ፖለቲካ፣ ሳይንስ፣ አስትሮኖሚ፣... ብቻ ምን አለፋህ ሁሉም ነገር ላይ አዋቂዎች ነን ብለው ያስባሉ። ለምሳሌ አንድ ስለ "አንደኛው የዓለም ጦርነት" ብዙ መፅሃፍትን ካነበበ ሰው ጋር እኩል ሊያወሩ ይችላሉ። ነገር ግን እውቀቱን ያመጡት ከ "Google" ላይ እየቀነጫጨቡ ካገኟች መረጃ ተነስተው ነው። ብዙ ነገራቸው ከላይ ከላይ ነው! ጠለቅ ብለው ማንበብ አይመቻቸውም!
መረጋጋት ወይም ትኩረት መስጠት ላይ እንብዛም ናቸው። አንድ ነገር ላይ ትኩረት ሰጥተው መቆየት የተራራ ያህል ይከብዳቸዋል! እያወራሃቸው ነው። እነሱም ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ እየሰሙህ ነው! ነገር ግን እያዳመጡህ አይደለም።
ስልክ ማውራት አይወዱም! አንዳንዴ ስልክ ማውራት ከመጥላታቸው የተነሳ ለራሳቸው ጉዳት እንኳን መደወል አይፈልጉም! በተቻላቸው መጠን ሀሉንም ነገር በ "Chat" ወይም በ "Text" መጨረስ ይመቻቸዋል። የሰዎችን አይን እያዩ ማውራት አይደፍሩም! አካላዊ ተግባቦት ላይ ደካሞች ናቸው! ሁሌም "vertual" ህይወትን ይመርጣሉ!
ሌላስ!
ወቀሳ አይወዱም። ሞታቸው ነው። የሚሰሩትን መልካም ተግባር ስታደንቅላቸው እንጂ ክፍተት ወይም ድክመታቸውን ስትነግራቸው ፈፅሞ ውስጣቸው ደስተኛ አይሆንም። በመልካም ጎን ለመቀበል ይተናነቃቸዋል! ብልጠታቸው ድክመታቸውን እየነገርክ ስትወቅሳቸው "...ልክ ነው! ሁላችንም ድክመታችንን የሚነግረን ሰው ያስፈልገናል!..." ምናምን እያሉ ፈገግ ብለው ሊሰሙህ ይችላሉ! ከዛ በኃላ ግን ድጋሚ አያገኙህም፣ ጠላታቸው ትሆናለህ።
ያደጉት "...ሁሉንም ነገር ማድረግ ትችላለህ! የፈለከውን መሆን ትችላለህ!. " እየተባሉ ነው። ለትንንሽ ስኬታቸው እየተሸለሙ የመጡ ትውልዶች ናቸው። እየተሳሳቱ እንኳን መምህር እና ቤተሰቦቻው "ጎበዝ...በርታ...ጀግና!..." እያሉ ነው ያሳደጓቸው። የፈተና ወረቀታቸው ሲታረምላቸው "Excellent, smart, very good" እየተባለ ነበር። ይህንን የሚባሉት እየተሳሳቱም ጭምር ነው! ከ 30 ተማሪ 20ኛ ወጥተው ሳይቀር ተሸልመዋል፣ ተበረታትተዋል። ይህ የውሸት አስተዳደጋቸው እጅግ ስሜታዊ እና በትንሽ ነገር የሚከፉ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። "....አትችልም፣ ሰነፍ ነህ፣ ይሄንን አሻሽል..." ስለተባሉ ብቻ ሊቆዝሙ፣ ሲያለቅሱ ወይም እራሳቸውን ማጥፋት ሊያምራቸው ይችላል። ብዙዎቹ "Millennial" ትውልዶች ችግሮቻቸው የሚጀምሩት ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ስራ ሲገቡ፣ ትክክለኛዋን ቀፋሪ ዓለም ሲጋፈጡ፣ የውሸት የሚያደንቃቸው ሲጠፋ እና ለትንንሽ ስኬታቸው የሚሸልማቸው ሲያጡ ነው። ያኔ ህይወትን ማማረር እና ዓለምን መርገም ይጀምራሉ!
ሌላስ ባህሪያቸው!
አብዛኛዎቹ ከማንም ሰው በተሻለ ደስተኛ ህይወት እየኖሩ እንደሆነ እንዲታወቅላቸው ይፈልጋሉ። ሲበሉ፣ ሲጠጡ፣ ሲዝናኑ፣ ሲጓዙ፣ ሲርባቸው፣ ሲታመሙ፣ ሲጠብሱ፣ ሲያገቡ እና ሲፈቱም ጭምር ሃገር ይወቅልኝ ማለት ይወዳሉ። "Approval seekers" ናቸው። የማህበራዊ ሚድያ ገፃቸው ሁሉም የሚያነበው የግል ዲያሪያቸው ነው።
ወጣ ያለ ነገር መስራት፣ ጫካ ለጫካ ካሜራ ይዞ መዞር፣ ተራራ መውጣት እና ሃገራትን/ቦታዎችን መጎብኘት ይወዳሉ። ይህንን ሲያደርጉ ግን ሁሌም የማህበራዊ ሚድያ ተከታዮቻቸው እንዲያዩላቸው ይፈልጋሉ። ፎቶ መነሳት አብዝተው ይወዳሉ። ነገር ግን ፍፁማዊነትን አጥብቀው ስለሚሹ የተነሷቸው ፎቶዎች ላይ አይረኩም! ሁሌም እንዳጠፉት አልያም አቃቂር እንዳወጡ ነው።
ስልካቸው አጠገባቸው ከሌለ ችግሮችን መፍታት ይከብዳቸዋል። ለሁሉም ችግሮቻቸው መፍትሄ የሚያገኙት ከስልካቸው ላይ ነው። ሲታመሙ ሳይቀር ለመፍትሄው ሆስፒታል ከመሄድ ይልቅ መዳኛ መፍትሄዎችን "google" ማድረግ ይቀላቸዋል።
ያዩት ነገር ሁሉ ያምራቸዋል። በየቀኑ ልብስ እና ጫማ ቢገዙ ውስጣቸው ነው። ነገር ግን በቂ ገንዘብ የላቸውም። ሁሌም እንደተበደሩ ነው። ደሞዛቸውን ከወር እስከ ወር አይደርስም። ከየትኛውም ትውልድ ያነሰ ቆጣቢዎች ናቸው። ስራ ይዘው ደሞዝ እየተከፈላቸው ሳይቀር ከቤተሰቦቻቸው እርዳታን ይፈልጋሉ! ሁሌም የሚከፍሉት ብድር አይጠፋቸውም! ቤት የመግዛት እድላቸው ጠባብ ነው። "Nomadic(ዘላን)" ናቸው። ከሃገር ሃገር ወይም ከቦታ ቦታ እየተዟዟሩ ተከራይተው መኖርን ይመርጣሉ።
አብዛኛዎቹ ተቀጥረው መስራትን ይጠየፋሉ። ሁሌም የራሳቸው አለቃ መሆንን ያልማሉ! "... ብር ሳገኝ ወይም ሲሳካልኝ የራሴን ቢዝነስ እጀምራለሁ!.." ሲሉ ትሰማቸዋለህ። መታዘዝ፣ ዝቅ ማለት፣ መላላክ ምናምን አይመቻቸውም። በጎነቱ ከየትኛውም ትውልድ በበለጠ ስራ ፈጣሪዎች ናቸው። ቢሮ በመቀመጥ፣ ጠዋት 2 ሰዓት ገብቶ 11 ሰዓት በመውጣት እና በቁጥጥር አያምኑም፣ አይመቻቸውም። "...በዚህ ሰዓት ወጣህ፣ በዚህ ሰዓት ገባህ!..." የማይባሉበት መስሪያ ቤት መግባትን ይመርጣሉ።
ሲቀጥል!
"Libral" ናቸው። ያን ያህል ወግ አጥባቂዎች አይደሉም! ነፃነታቸውን እስካገኙ ድረስ ማንም መራቸው ማንም አይጨነቁም!
ከየትኛውም ትውልድ የተሻለ በራስ መተማመን አላቸው! አንዳንዴ እንደውም በራስ መተማመናቸው ጣራ ይነካና ይቀብጣሉ። በ "Multi tasking" ወይም "በተመሳሳይ ሰዓት ብዙ መተግበር" ላይ የተካኑ ናቸው። "Text" እያደረጉ፣ በጆሮዋቸው ሙዚቃ እያዳመጡ በዚህ ጋር ደግሞ ሌላ ስራ ሲሰሩ ልታያቸው ትችላለህ።
ችግራቸው አንድን ነገር ትኩረት ሰጥተው ማንበብ አይችሉም! ለምሳሌ የስራ ማስታወቂያዎችን ተረጋግተው ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው እንኳን አያነቡም። የሚያዩት የቅጥር መስፈርት የምትለውን ቦታ ብቻ ነው። መፅሃፍ ማንበብ ጀምረው እስከ ግማሽ እንኳን አይዘልቁም። በአመት ከአንድ መፅሃፍ በላይ ላያነቡ ይችላሉ። አብዛኛዎቹ "Self centered" ናቸው። ከአንድ ከሃገራዊ ችግር ይልቅ "facebook" ላይ "block" ስላደረጋቸው ሰው አብዝተው ይጨነቃሉ። የጋራ ችግር አይገባቸውም! ምንም ነገር በራሳቸው ላይ እስካልደረሰ ድረስ "I don't care!" በሚል "Mentality" መኖርን ይመርጣሉ!
ማጠቃለያ!
ይህንን ፅሁፍ የምታነቡ ወዳጆቼ እድሜያቹ ከ 25 እስከ 40 ከሆነ ""Millennial Generation" ወይም "ሚሊኒያል ትውልድ" ትባላላችሁ። አብዛኛዎቹ ጥናቶች የተደረጉት ምዕራባዊያኖቹ ጋር ቢሆንም ዓለም እየተሳሰረች ከመምጣቷ ጋር ተያይዞ እኛም ጋር የምናስተውላቸው የጋራ ባህርያት ይኖራሉ ። እንደውም አንዳንዶቹ ባህርያት በደንብ ይገልፁናል! አባዬ! ይሄንን ትውልድ የወለዱት ቤተሰቦቻችን "Baby boomers" ሲባሉ ከእኛ በኃላ (እ.ኤ.አ ከ 2000) በኃላ የመጡት ትውልዶች ደግሞ "Generation Z" ይባላሉ።
ጌታዬ! "Generation Alpha", "Silent Generation" እና "Generation X" ብለው የሚከፍሏቸው ትውልዶችም ጭምር አሉልህ። ለማንኛውም ማወቁ አይከፋምና ስለነዚህ ውስብስብ የትውልድ የጋራ ባህሪያት እረፍትህን እያነበብክ አሳልፍ የኔ "Millennial"!
መልካም ምሽት! መልካም የእረፍት ሳምንት! ፍክት ያለች ቅዳሜ ይሁንላችሁ!

@monhappy
፡ አረቄ ቤት…ከእስዋ ጋር 👫

ወይንዋ አረቄ ቤት ነን…ዛሬ እና ትላንት በጣም ይለያያሉ…ልቤን እሚያሸንፈው ፍቅር ብቻ…ሰላም ለእናተ ይሁን…




💍 @monhappy 🌴
🍷 @BINC90
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ደህና ለመሆን እየሞከርኩ ነው😞
እንደተቀየርኩ ይገባኛል…ግን ፈልጌውም አደለም💔
የአና ማስታወሻ ክፍል 01
📙 የ መጻሕፍት ትረካ 🎙
●●◦የአና ማስታወሻ ክፍል 01◦●●
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
➲ ተርጓሚ አዶኒስ, ተራኪ ዩሐንስ የዝና

➲ የ15 ዓመት ልጃገረድ የሆነችው የአና ፍራንክ ዳየሪ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @monhappy
@BINCJ90
የአና ማስታወሻ

✏️ ባለታሪክ - አና ፍራንክ
👉 ትርጉም - አዶኒስ
👉ህትመት - 1996 ዓ.ም
👉 ይዘት - ዲያሪ
👉 ቻናል - 📙 የ መጻሕፍት ትረካ 🎙

👍
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @monhappy
@BINCJ90
የአና ማስታወሻ ክፍል 02
📙 የ መጻሕፍት ትረካ 🎙
●●◦የአና ማስታወሻ ክፍል 02◦●●
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
➲ ተርጓሚ አዶኒስ, ተራኪ ዩሐንስ የዝና

➲ የ15 ዓመት ልጃገረድ የሆነችው የአና ፍራንክ ዳየሪ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @monhappy
@BINCJ90
የቅዳሜ ቀደዳ-22(፳፪)
እንዴት ሰነበትሽ የኔ እናት? እንዴት ይዞሃል ጌታዬ? እንደተለመደው የፀዳው፣ የፈካው እና ያማረው የቅዳሜ ቀደዳችንን ይዘን ተከስተናል!
አንዳንዴ እራሴን እንዲህ ብዬ እጠይቃለሁ! የምሬን ነው!
ፑሉቶ ላይ ያለው ቅዝቃዜ ምን ያህል ነው? ሳተርን ላይ ያንን የሚያክል ቀለበት ምን ይሰራል? ፀሃይን ከቧት ያለውን ክፍል "Corona" ብሎ የሰየመው ማን ነው? "Steven Hawkins" ሲሞት የመጨረሻ ቃሉ ምን ነበር? "Albert Einstein" ምን ታይቶት ነው "Theory of relatively" የሚባል ቀመርን የጠነሰሰው?
እሺ እሱን ተወው!
አንድ "Asteroid" ምድርን ቢመታን ምን ይውጠናል?
ፀሃይን የሚዞሯት ስምንቱ ፕላኔቶች አያድርገውና አቅጣጫ(orbit) ስተው ቢጋጩ ሁላችንም ለማለቅ ምን ያህል ደቂቃ ይፈጅብናል? ሜርኩሪ ምን ልትሰራ እንደዛ ወደ ፀሃይ ተጠጋች?
በፀሃይ እና በምድር(Earth) መካከል ያለው ርቀት 150 ሚልዮን ኪሎሜትር ከሆነ ፀሃይ የምትሰጠን ብርሃን በምን ፍጥነት ወደኛ ይደርሳል? ቬነስ ለምን እንደዛ እንደ እሳተ ጎመራ ትንቦለቦላለች?
ፀሃይ ካላት እጅግ ከፍተኛ ክብደት አንፃር ዙሪያዋ ያሉትን 8 ፕላኔቶች፣ ከአስር በላይ ጥቃቅን(dwarf) ፕላኔቶችን፣ 170 ጨረቃዎችን እና ተቆጥረው የማያልቁ ኮሜቶችን እና አስትሮይዶችን በ "gravitation force" ስባ ትይዛለች! ሁላችንም እሷን ከበናት እንዞራለን፣ እንጨፍራለን!
እንደዛ ትንሽ ስታቃጥልህ የምትረግማት ፀሃይ ከሌለች ሙቀት እና ብርሃን የለም። ሙቀት እና ብርሃን ከሌለ እፅዋት አያድጉም፣ ምድር ላይ ያለው ውሃ ሁሉም ወደ በረዶነት ይቀየራል።በጥቂት ግዜያትም የመኖር ህልውናችን ያበቃል። የሚገርመኝ ፀሃይን ከ 4.6 ቢልዮን አመታት በፊት ሃይድሮጂን እና ሂልየም ተሰባጥረው እንዴት ፈጠሯት? እሺ ፀሃይ ብትፈነዳስ? "Big bang theory" ምን ያህል እውነት ነው? ማን አሰላው?
ከአጠቃላይ የፀሃይ ስርዓት(solar system) ክብደት ውስጥ ፀሃይ ብቻዋን 99.86% የሚሆነው ክብደት ትይዛለች። እኛን ጨምሮ ሌሎች ፕላኔቶች ተደማምረን እንኳን በአጠቃላይ 0.14% የሚሆን ክብደት የለንም! 300 ሺህ እጥፍ ከምድር የምትበልጠው ፀሃይ ጋር ብትሄድ 15 ሚልዮን ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያክል ትንተከተካለች። ምድር ላይ ከፍተኛው ሙቀት ተብሎ የተመዘገበው አሜሪካ ውስጥ "Death Valley" የሚባል ቦታ ሲሆን መጠኑ 57 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ብቻ ነው። የፀሃይ 15 ሚልዮን ዲግሪ ሴንቲግሬድን እንድታስበው ብዬ ነው!
እሱን ተወው እሺ!
የመኖራችን ህልውና የሆነችው ጨረቃ ከምድር በአማካይ በዓመት 4 ሴንቲሜትር እየራቀች ነው። ይህ ማለት ጨረቃ እየራቀችን ከሄደች የመሬት እሽክርክሪት(rotation) እየቀነሰ ይሄዳል። በዚህ ከቀጠለ ከሆነ ግዜ በኃላ ምድር ወይም "planet earth" ላይ አንድ ቀን አንድ ወር ያህል ሊረዝም ይችላል። "...ነገ እንገናኝ!..." ብዬህ ከወር በኃላ መገናኘት "Normal" ይሆናል ማለት ነው።
ሳይንሱ እንደሚለው!
እነዚህ በቢልዮን የሚቆጠሩ ኮከቦች፣ እነዚህ ሁሉ ማለቂያ የሌላቸው ፕላኔቶች፣ አስትሮይዶች፣ ኮሜቶች እና ፀሃይ አንድ ላይ ሆነው አንድ "Galaxy" ይባላሉ! ልክ እንደኛ አይነት "galaxy" ደግሞ ሌሎች በቢልዮን የሚቆጠሩ "ጋላክሲዎች" አሉ። እያንዳንዱ ጋላክሲ ውስጥ ደግሞ ሌሎች በቢልዮን የሚቆጠሩ ከዋክብቶች አሉ። የኛ "galaxy" ውስጥ ያሉት ከዋክብት ብቻቸውን ምድር ላይ ካለው ቅንጣት አሸዋ ቁጥር በላይ ናቸው። ነገር ግን አንዷ ኮከብ ከምድር(Earth) በብዙ ትበልጣለች። ምድር ወይም "Earth" በዚህ ሰፊ "Galaxy" ውስጥ የአንዲት ቅንጣት ጤፍን ያህል እንኳን ዋጋ የላትም! ከቢልዮን ኩንታል ጤፍ ውስጥ አንድ ዘለላ ወይም አንድ ፍሬ ጤፍን ማውጣት እንደማለት ማለት ነው።
ግን...ግን
ይህ ሁሉ በቢልዮን የሚቆጠር ክዋክብት፣ ይህ ሁሉ ጨረቃ፣ ይህ ሁሉ ጋላክሲ፣ ይህ ሁሉ ፕላኔት እና ይህ ሁሉ ሚልኪ ዌይ(Milkly way) ባለባት "Universe" ውስጥ "ህይወት(life)" የምንለው ነገር ያለው "ምድር" ላይ ብቻ ነው? እዚች ቅንጣት የምታክል ነገር ውስጥ እንዴት ህይወት ተፈጠረ? ይህ ሁሉ ፕላኔት፣ አስትሮይድ፣ ጨረቃ እና ክዋክብት እጅግ እጅግ እጅግ ፍፁም በሆነ መንገድ ከተፈጠረ በኃላ እንዴት ሳይዛባ ሊቀመጥ ቻለ? በርግጥ ለህይወት አስፈላጊ የሆኑት አየር እና ውሃ እስካሁን የተገኙት ምድር(earth) ላይ ነው። ነገር ግን እነዚህ በቢልዮን የሚቆጠሩ ጋላክሲዎችን ገና የቅንጣት ታህል እንኳን ምርምር አላደረግንባቸውም።
አብዛኛዎቹ በዚህ ዙርያ ምርምር ያደረጉ ሳይንቲስቶች፣ አስትሮፊዚሲስቶች እና ኮስሞሎጂስቶች "... አንድ የሆነ ቦታ ላይ እዚህ ምድር ላይ ከምናውቀው ህይወት የተለየ ሌላ ህይወት(ፍጡራን) ቢኖሩስ? የላቀ ስልጣኔ፣ የላቀ ማንነት እና የላቀ ስብዕና ያላቸው ከሰው ልጆች ፍፁም የተለዩ ፍጡራን እያዩን ሙድ እየያዙብን ቢሆንስ?..." ብለው ይጠይቃሉ።
ይህንን ለማረጋገጥ/ለማጥናት ሙከራዎች መደረግ ከጀመሩ ግማሽ መቶ ክፍለ ዘመን በላይ ተቆጥሯል። እስካሁን ግን ወይ እነሱ እንዳሉ እንድናውቅ አልፈለጉም፣ ወይ እኛ መኖራቸውን ለማረጋገጥ የሚበቃ የስልጣኔ ደረጃ ላይ አልደረስንም፣ ወይ ደግሞ ህይወት ያለው ምድር ላይ ብቻና ብቻ ነው!
እዚህ ተቆጥሮ የማያልቅ "Universe" ውስጥ ከሰው ልጅ ውጪ ይኖራሉ ተብለው የሚገመቱ ፍጥረታትን "Aliens" ወይም "በአዳን" እያልን እንጠራቸዋለን።
አሜሪካ እ.ኤ.አ ከ 1960ዎቹ በኃላ "Search for Extraterrestrial Intelligence(SETI)" በሚባል ተቋም አማካኝነት "Aliens" ይኑሩ አይኑሩ የሚለውን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥናት እና ምርምር እያደረገች ነው። የተለያዩ ግዙፍ ሳተላይቶችን ተክለው ሌት ተቀን የኤልያኖችን "Signal" ካገኘን ብለው ይተጋሉ! "NASA"ም ተመሳሳይ ስራ ይሰራል!
አንዳንድ ፍንጮች አንድ!
እነዚህ ፍጥረቶች ይጓዙበታል ተብሎ የሚታሰብ ዲስክ የሚመስል በራሪ መጓጓዣ አለ! እነሱ "Unidentified Flying Objects (UFO)" ብለው ይጠሩታል። እነዚህን በራሪ መጓጓዣዎች አይተናል ያሉ ብዙ የጦር ፓይለቶች አሉ። እሱ ብቻ ሳይሆን በተንቀሳቃሽ ምስልም ጭምር መቅረፅ የቻሉ ፓይለቶች ይገኛሉ። አንዳንዶች ደግሞ የነዚህ በራሪ መጓጓዣዎች ቅርፅ የፒራሚድ ቅርፅ ያለው ነው ይላሉ። 2019 ላይ አንድ ፓይለት የቀረፃቸው እነዚህ በራሪ መጓጓዣዎች "edit" ያልተደረጉ እውነተኛ ምስሎች እንደሆኑ የአሜሪካ መንግስትም በመጨረሻ አረጋግጣል። በ 2004 ተቀርፆ የተለቀቀ ሌላ ተንቀሳቃሽ ምስልም "እውነት ነው!" ብሎናል!
አንዳንድ ፍንጮች ሁለት!
እነዚህ ፍጥረቶች የሰው ልጆች ላይ ምርምር እና ጥናት ለማድረግ በአሳቻ ሰዓት ሰዎችን ጠልፈው ወደ ሌላ ዓለም ይወስዳሉ ይባላል! እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች በ "Aliens" ተጠልፌ ተወስጄ ነበር ብለው ለተለያዩ የሚድያ ተቋማት ቃለ መጠይቆችን ይሰጣሉ። አብዛኛዎቹ ተጠልፈናል(Abduct) ተደርገናል የሚሉ ሰዎች ደግሞ በፆታ ሴቶች ናቸው። አንዳንዶቹ ሴቶች "ለዓመታት ወደማናውቀው ምድር ወስደውን ልጆች ሳይቀር አስወልደውናል!" ብለው በሚገርም የራስ መተማመን መንፈስ ምስክርነት ይሰጣሉ። አንዳንዶቹ ለዓመታት ተወስደናል የሚሉ ሴቶች ላይ ጥናት ሲደረግ ተወስደናል ባሉባቸው ግዜያት ውስጥ ምድር (earth) ላይ እውነትም ምንም "record" አልተገኘባቸውም!
ከዚህ በተጨማሪ አብዛኛዎቹ ተጠልፈን ተወስደናል የሚሉ ግለሰቦች የወሰዷቹ ሰዎች ምን ይመስላሉ? ተብለው ሲጠየቁ "....ረጃጅም፣ ከሰው ልጅ የተለየ የቆዳ ቀለም ያላቸው እና አይናቸው ትላልቅ የሆነ ለየት ያሉ ፍጥረቶች ናቸው!..." ይላሉ!
የፍንጩ ውድቅ ማድረጊያ!
"....ተጠልፌያለው፣ ተወስጄያለው፣ ልጅ አስወልደውኛል..." የመሳሰሉትን የሚሉ ሰዎች የአዕምሮ በሽተኞች ናቸው! አንዳንዶቹ ትኩረት ለመሳብ እና ለመታወቅ ሲሉ ያደርጉታል! አብዛኛዎቹ ይህንን የሚሉ ግለሰቦች ደግሞ ከአሜሪካ መሆናቸው "ኤልያኖች አሜሪካውያንን ብቻ ነው እንዴ የሚጠልፉት?..." የሚል ጥያቄን እንዲያስነሳ አድርጓል። እነዚህ ተጠልፌያለው የሚሉ ግለሰቦች በሽተኞች ስለሆኑ የሚያስፈልጋቸው የሚድያ ሽፋን ሳይሆን የስነ ልቦና ድጋፍ ነው የሚሉ አሉ!
አንዳንድ ፍንጮች ሶስት!
"....የሰው ልጅ ከ 4500 ዓመታት በፊት ራቁቱን ጫቃ ለጫካ እንስሳትን እያደነ ኃላ ቀር ሆኖ ይኖር በነበረበት ዘመን እንዴት የግብፅ ፒራሚዶችን ሊሰራ ይችላል?..." የሚል ጥያቄ አለ! በርግጥ አንዳንድ የኪነ ህንፃ ባለሙያዎች እንደሚሉት የግብፅ ፒራሚዶች አይደለም ከ 4500 ዓመታት በፊት አሁን ላይ ባለው የሰው ልጅ ስልጣኔ እንኳን ሊሰሩ አይችሉም። ፍፁማዊነታቸው፣ አደራደሩ፣ ቀመሩ፣ ሚስጥሩ እና ከኦርዮን ኮከብ ጋር ያለው ስብጥር ድንቅ ስለሆነ ብዙዎች እነዚህን ፒራሚዶች የሰሩት "ኤልያኖች" ናቸው!" እንዲሉ አስገድዷቸዋል። "Elon Musk" ሳይቀር "The pyramids are built by Aliens obviously!" የሚል ፅሁፍ ለጥፎ ወዳጅ ሃገር ግብፅ ልትበላው ደርሳ ነበር! ብዙ ሰዎች ኤልያኖች ፒራሚድን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ከአስር በላይ ድንቅ ግንባታዎችን ዓለማችን ላይ ሰርተዋል ብለው ይከራከራሉ!
አንዳንድ ፍንጮች አራት!
እጅግ ድብቅ የሆነው እና አሜሪካ "Nevada" ውስጥ የሚገኘው "Area 51" የሚባለው የአሜሪካ አየር ሃይል ዋና ቅጥር ግቢ ውስጥ የተከሰከሰ የኤልያን መጓጓዣ ፕሌን እንዳለ እና መጓጓዣ ውስጥ የነበሩ የኤልያኖች ቅሪተ አካል እንደሚገኝ ይነገራል። በርግጥ ቦታው እጅግ ሚስጥራዊ፣ ከፍተኛ ምርምር የሚደረግበት፣ አሜሪካ አዳዲስ የምታመርታቸው የጦር ጀቶች እና የስለላ መሳርያዎች የሚሞከሩበት ነው! የቦታው ሰራተኞች ሳይቀር የሚወጡት እና የሚገቡት በድብቅ ነው። ነገር ግን የአሜሪካ መንግስት እዚህ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከኤልያኖች ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ምርምር አይደረግበትም ይላል! ጌታዬ! ግዜ ካለህ "Google map" ላይ ፈልገህ ማየት ትችላለህ! በርግጥም ቦታው ይገርማል!
ማጠቃለያ!
በቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ወቅት እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ ቅድም ያልኩህ "Area 51" የተሰኘው ቦታ ላይ አሜሪካ ራሽያን ለመሰለል "U2" እና "SR-71" የሚባሉ ጥቋቁር ጀቶችን ታመርትበት ነበር። እነዚህ የስለላ ጀቶች ከራዳር ውጪ ሆነው ከ 80 ሺህ ጫማ ከፍታ በላይ መብረር ይችላሉ! በወቅቱ እነዚህን የስለላ ጀቶችን ያዩ ሰዎች የ "UFO/Alien" መጓጓዣዎች ናቸው ብለው እንዲገምቱ አድርጓል! ጌታዬ! ታድያ ብልጧ አሜሪካ በነዚህ ጀቶች ራሽያን እየሰለለች እንደሆነ እንዳይባነንባት ከህዝቡ ጋር አብራ "አዎ! የኤልያን መጓጓዣዎች ናቸው!" ብላ ጨረር መልቀቅ ጀመረች! የሚገርመው በወቅቱ እነዚህን ጀቶች የሰሩ እና በዚህ "operation" የተሳተፉ አሜሪካዊ ፓይለቶች አሁን ላይ ይህ ታሪክ እውነት እንደሆነ እና የወቅቱ ኤልያኖች የአሜሪካ የስለላ ጀቶች እንደነበሩ ይመሰክራሉ።
ለማንኛውም እነ "SETI" እና "NASA" ...."....ህይወት ከምድር ውጪ እንዳለ እና እንደሌለ ለማረጋገጥ አስር አመት ብቻ ስጡኝ፣ እስካሁን ባለን ጥናት የመኖሩ እድል ከ 60% በላይ ነው!..." እያሉን ነው።
እኛም እድሜ ይስጠን እና ለማየት ያብቃን!
ቅዳሜን ፈታ፣ ዘና ብላችሁ አሳልፉ!

@monhappy
@BINCJ90
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኮኮቦቹን ስቆጥር ለካ ጨረቃዋን አላየሁዋትም :)
ከጠፋሁበት መንገድ እባክህ መልሰኝ😔🙏🏽
Cross @BINCJ90
2025/07/01 15:03:26
Back to Top
HTML Embed Code: