Forwarded from Islam mindset
   " ጥንካሬ ሲተረጎም!"

ብዙዎቻችን በብዙ መልክ ጥንካሬን የምንለካበት ሚዛን ይኖረናል። አንዳንዶች ተሳስተን, ሌሎቻችን ደግሞ ልክ ልንሆን እንችላለን። በብዙ እይታዎች አንፃር!.. አንዳንዶች ጥንካሬን ባልተረጋገጠ ታሪክ ስንለካ፤ ሌሎች ደግሞ ባለንበት ዘመን በሚከወነው እውነታ ይመዝኑታል።ጥንካሬን ከሀብት እና ከማጣትም ጋር የሚመዝኑም አይጠፉም። ከዚህም ባስ ሲል... ጥንካሬን ከጀግንነት ጋር በማያያዝ... ክብረትን እና ዝናን ማገኘት የመጨረሻው ቁንጮ ነው ብለው የሚያስቡ ሙስሊሞችም ከምንግዜውም በላይ ተበራክተዋል። ይሄ ሁሉ አስተሳሰብ ከእምነታችን መላላት መሆኑን ሙስሊሞች ልብ ልንል ይገባል።በተለይ ወጣቶች! የሰው ልጅ በእምነት የሚኖር ፍጡር ነው።ሌሎች ፍጡሮች ለአላህ ተገዢነትን ብቻ እንጂ የኔ እምነት ይሄ ነው ብለው አይናገሩም አይወያዩም ብሎም በዕምነታቸው ምክንያት አይጋደሉም፣ መስዋት አይከፍሉም። የሰው ልጅ ግን ለዚህ ታድሏል።ጥንካሬ የሚመዘነው በእምነት ብቻ ነው። እኛ ሙስሊሞች በኢማናችን ልክ ነው ጥንካሬያችን!  ለአላህ ባለን ቅርበት እና ርቀት ብቻ ነው የምንለካው። የዘር እና የቀለም፤የጎሳና የጎጥ፣የተራነት እና የባለስልጣንነት በኢስላም ላይ ቦታ እንደሌለው ምሳሌ አድርገን ልንወስድ የሚገባን, የነብይነት ህይወታቸው የ23 አመት ጉዞ ብቸኛ መመዘኛችን መሆኑን እንወቅ፣እንገንዘብ። ከጥቃቅን እስከ ትላልቅ የእለት ከእለት ዉሏችን በቁርአን አንቀፆች እና በሀዲሶች ይለካ! ዉስጣችንንም እንመርምር ፣የማይነጥፍ እና የማይዛነፍ ሚዛን ለጥንካሬያችን እናስቀምጥ። እንደ ተምሳሌታችን ነብዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) ጥንካሬን በወህይ እውቀት እንገንባ! እምነታችን፣ኑሮአችን፣ትምህርታችን፣መረዳዳታችን፣ሰራችን፣ትግላችን ሁሌም በዲነል ኢስላም ይመዘን።ያኔ ጠንካሮች እንሆናለን። የተረሳውንም ጥንካሬን ለትውልድ እናስተምራለን እናሳያለን!..
www.tg-me.com/@mind_islam
youtube.com/@islam_mindset
tiktok.com/@islam_mindset
fb.com/@islam_mindset
#ፎሎው_ያድርጉ
#ቻናሉን_እናሳድገው
#ቤተሰብ_እንሁን
#እንጠቀማለን_ኢንሻአላህ
Forwarded from Islam mindset
ግዜ ሰጥተህ የምታሳልፋቸው ,የምትፈፅማቸው ,እንዲሁም የምትጨነቅለት አልያም የምትደሰትበት ነገር ሁሉ ስላንተ ይናገራል።ከዚህ ሁሉ ነገር ግን አንተ በምትሰራቸው ነገሮች ምን ያህል ደስተኛ ነህ ,ምን ያህሉስ ፈልገኸው ትፈፅመዋለህ፤ ምን ያህሉስ ደስ ብሎህ ትከውነዋለህ። የራስህን ማንነት የምታውቀው በዚህ ምልክት ነው። ምክንያቱም አላህ ስለ ሙናፊቆች በቀላሉ ሲገልፅልን ሶላትን ሲሰግዱ እንኳ ዉስጣቸውን እየደበራቸው ነው ብሎ አይደል! ...ሁሌም ቢሆን አስታውስ!
www.tg-me.com/@mind_islam
#join
#ቤተሰብ_እንሁን
Forwarded from Islam mindset
ረመዳን ግዜውን ጠብቆ ለሚጠቀምበት ብዙ ትሩፋቶችን በውስጡ ይዞ ሊገባ ሰዓታቶችን እየቆጠረ ይገኛል። ይሄ ሁሉ ግን በህይወት ለደረሰ ብቻም ሳይሆን ለሚጠቀምበት መሆኑን እንገንዘብ። ረመዳንን ከሚጠቀሙበት እንዲሁም ከሚጠቅማቸው ውስጥ አላህ ያድርገን!....አሚን.
www.tg-me.com/@mind_islam
Forwarded from Islam mindset
ረመዳን - 1
በረመዳን ለመጠቀም ዘንድ ረመዳንን የእውነት በውስጣችንን ልናውቀው በአዕምሯችን ልናስተነትነው ይገባል።

ረመዳን ብሎ ማለት.. በደማችን ውስጥ የሚዘዋወረውን ዋና ጠላታችን የሚታሰርበት ወር ነው!..

ረመዳን ብሎ ማለት ከሱ በፊትም ሆነ በኋላ ምንም አይነት መመሪያ የማይበልጠው የአላህ ንግግሩ ቁርአን የወረደበት ቀን ነው...

ረመዳን ማለት ውስጣችንን በጠንካራ ጉትጎታ የምታሳስተን ነፍስያችን በረሀብ የምትከስምበት ወር ነው...

ረመዳን ብሎ ማለት አላህ በእያንዳንዱ ለሊት በሱ የእውነት ላመኑ ባሮቹን ከጀሀነም እሳት ነፃ የሚልበት ቀን ነው...

ረመዳን ብሎ ማለት አላህ ከወራቶቹ ሁሉ ያላቀው ወር ሲሆን አላህ ዘንድ ከፍ ማለት ከፈለክ በረመዳን ደረጃህን ከፍ አድርግ!...

ረመዳን ብሎ ማለት በውስጡ የቀናቶች ንጉስ የሆነችን ቀን ለይለቱል ቀድርን በውስጡ የያዘ ወር ነው...
...እናም ይሄንን ሁሉ መጠቀም ካልቻልክ ከተረገሙት ውስጥ መሆንህ አረጋግጠሀል...አላህ የረመዳን ትሩፋቶችን ከሚጠቀሙት ያድርገን......

www.tg-me.com/@mind_islam
#remedan
#Remedan
Forwarded from Islam mindset
ረመዳን - 1 (part 2)

የረመዳን የመጀመሪያው ቀን ሊያልፍብን ሰዓታቶች ቀርተውታል። ይበልጥ በዱዓ,በዚክር እንዲሁም ቁርአን በመቅራት ከአሱር እስከ መግሪብ ያለውን ግዜ እንጠቀምበት። ምክንያቱም ይቺ ግዜ አላህ ዘንድ ትልቅ ቦታ አላት። የማታ አዝካሮችን በማለት ዛሬ እንጀምረው፣ ዱዓ አድርጉልን ያሉ ወንድሞችን እና እህቶችን ዱዓ እናድርግላቸው፣ ቁርአን ቢያንስ አንድ ጁዝ እንቅራበት እንዲሁም በጥሩ እንሰናበተው...አደራ በመዳከም እና በማይጠቅሙ ነገሮች በነዚህ ሰዓቶች እንጠንቀቅ። ምክንያቱም ስራዎች የሚመዘኑት በመጨረሻ መሆናቸውን አንርሳ!

(ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቤተሰብ እንሁን!)
www.tg-me.com/@mind_islam
Forwarded from Islam mindset
ረመዳን - 3 (part-1)

የረመዳን ጉዞ

ረመዳን አይቆምም ይጓዛል! ነገር ግን እኛ አለመቆማችንን እርግጠኛ እንሁን። ምክንያቱም ረመዳን የመጨረሻይቱ ቀን ላይ አብረነው መጓዛችንን ይመሰክርልናል አልያም አለመጓዛችንን ይመሰክርብናል። በቀላሉ እንዳንሸወድ አብዘሀኞች እንደተሸወዱት ማለት ነው... ገና ነው ረመዳን ብለው ሳያስቡት እንዳለቀባቸው ማለት ነው። ከሰዓታቶቹ እና ከቀናቶቹ ጋር አብረን ከረመዳን ወር በኢባዳ እንጓዝ, ያኔ ነው ረመዳን እኛን የሚለውጠን...ካልሆነ ግን ረመዳንን በማይረባ ነገር ለውጠነዋል!
www.tg-me.com/@mind_islam
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
#ቤተሰብ_ይሁኑ
Forwarded from Islam mindset
የሰራነውን መገምገም

ከአሱር ሶላት እስከ መግሪብ ሰዓት ባሉት ግዜያቶች ስራችንን የለሊቱን እና የቀኑን ዘወር ብለን መመልከትን ልምድ ይኑረን። ምክንያቱም  የተሳሳትነው ነገር ካለም እስከ መግሪብ ኢስቲግፋር የምንለበትን የተዋቡ ሰዓታቶች አሉን። የምናስታውሰው ስህተት ከሌለም ይበልጥ በኢባዳ ቀኑን መጨረስ ትልቅ ትሩፉት እናገኝበታለን። ራሳችንን በረመዳን መገምገም የምንችልበት ወር እንዲሁም እኛም ራሳችንን በመገምገማችን ትልቅ እድለኞች መሆናችንን እናስተንትን።

www.tg-me.com/@mind_islam
Forwarded from Islam mindset
የማይጠገበው የሸይክ ሙሐመድ አንሲ ዳዕዋ ነገ ማለትም ጁሙዓ ረመዳን-5-1445 ዓ.ሒ ከቀኑ 7:30 youtube.com/@Islam_mindset ዩቲዩብ ቻናላችን ላይ ገብተው በጥሞና ብታዳምጡ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
Forwarded from Islam mindset
ነገ ቅዳሜ ማለትም ረመዳን-6 ከቀኑ 8:00 ላይ በዩትዩብ ቻናላችን የሼኽ ሙሐመድ አንሲ ትምህርት ይውሰዱ።
youtube.com/@islam_mindset ያገኙናል!
Forwarded from Islam mindset
" የድግግሞሽ ፀጋ"

በህይወት እስካለን ድረስ ፍጥረተ አለሙ ሲደጋገም እንመለከታለን። ለሊት ከቀኑ እንዲሁም ቀኑ ከለሊት፤ ብርዱ ከሙቀቱ እንዲሁም ሙቀቱ ከብርዱ፤ አመት ከአመት አንዳይነት ወራቶች በኛ ላይ ይመላለሳሉ። የአላህ ድንጋጌዎችም እንደዚሁ ናቸው። በየቀኑ አምስት አውቃት ሶላቶችን ሰዓታቸውን ጠብቀን እንሰግዳቸዋለን፣ በየአመቱ ዘካ ግዴታ የሚሆንበት ሰው የአመቱን ግዜ ጠብቆ ይሰጣል፣ እንዲሁም ረመዳን በየአመቱ ይመላለሳል። ሀጅም ወሩን ጠብቆ ይመጣል። ይሄ ግን የሚሆነው በህይወት ላለ ሰው ብቻ ነው። ምክንያቱም የሞቱ ሰዎች በነሱ ላይ የመጨረሻይቱን ቀን መጠባበቅ ብቻ ነው ስራቸው! የስራ መዝገባቸውም ተጠቅሎ ተቀምጧል። መጥፎ የሰሩትን ነገር ሊያካክስ የሚችል ስራ መስራት አይችሉም፤ ጥሩ የሆነውንም ስራ ይበልጥ እንስራ ብለው አይንቀሳቀሱም። ከዚህ የምንረዳው አላህ በኛ ላይ ከዋላቸው ፀጋዎች መሀል የጊዜ ድግግሞሽ ፀጋ መሆን ነው። ምክንያቱም አላህ አንድን ፀጋ ደጋግሞ ሰጠን ማለት ምናልባችም ደጋግሞ እድል እየሰጠን ነው ካለንበት ወንጀላችን እንድንመለስ አልያም ወደሱ ይበልጥ እንድንቃረብ!

www.tg-me.com/@mind_islam
#ቤተሰብ_ይሁኑ
Forwarded from Islam mindset
እሁድ 7:30(ረመዳን-7) የሼኽ ሙሐመድ አል-አንሲ ትምህርት ይከታተሉ።
Forwarded from Islam mindset
ረመዳን -8 ሰኞ ከቀኑ 7:15 በዩትዩብ ቻናላችን ትምህርቱን ይከታተሉ።

"ዱዓ ስታደርግ..." በሚል ዝግጅት ወደናንተ የቀረበ ሲሆን ዝግጅቱ በረመዳን 7 - 1445ዓ.ሒ በሼኽ ሙሐመድ አል-አንሲ አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን ሰፊ ነጥቦችን ሼኹ ይዳስሳሉ። በዋናነት ስለ ዱዓ ሚስጥራቶች እና እስከዛሬ አስበናቸው የማናቃቸውን ነጥቦችን ከህይወታችን ጋር በማያያዝ የዱዓ ሚስጥራቶችን ያብራርሉናል። ፕሮግራሙን ሼር እና ላይክ እንዲሁም ፔጃችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
http;//youtube.com/@UCf1l3HUhbvYevpMWRDPVhjg
http;//tiktok.com/@islam_mindset

----------------------------------------------------
Forwarded from Islam mindset
ረመዳን-15-1445 ዓ.ሒ

ህይወት ትጠቀለላለች...ያውም ሳናስብበት ሳንጨነቅለት..ሳናስተነትነለት! ለዚህም ማሳያ እስካሁን ያሳለፍነውን ዘመናቶች እና ግዜያቶችን ዘወር ብለን መመልከት ብቻ በቂ ነው።ከህይወት ግን የሚያስፈራው ነገር ቢኖር መቼ ከሞት ጋር እንደምንላተም አለማወቃችን ነው። ምክንያቱም ሞት ለመምጣቱ መስፈርት የለውም። ከዚህም አለፍ ስንል ደግሞ አለመዘጋጀታችን እና ዘላለም እንደምንኖር ማስመሰላችን አሰፈሪ ያደርገዋል። ጠንቃቃዎች እንሁን ..ወደ አላህ በቻልነው አቅም እንቃረብ!

@islam_mindset
Forwarded from Islam mindset
ያንተ ማንነት ለነገሮች ቦታ በምትሰጠው ነገር ይወሰናል።ለጊዜውም ቢሆን...!
ለነገሮች ቦታ መስጠት ማለት ደግሞ ውድ የሆነውን ሰዓትህን በምሰጠው ነገር ማሳለፍ ማለት ነው። ምንድን ነው የምታሳልፈው ሰዓትህን ራስህን ጠይቅ...!?

@islam_mindset
2024/05/02 19:19:18
Back to Top
HTML Embed Code: