Telegram Web Link
ይገምቱ ይሸለሙ

የማንችስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 8:30 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@neaea_gov_et_student_results
👍61
Forwarded from Lij Mani
8👍4
3036799
👍82
#በአዲስ_አበባ_የመሬት_መንቀጥቀጥ_ተከሰተ !!🌟

በአዲስ አበባ ከምሽቱ 2:10 ሰዓት ላይ በዓደይ አበባ ኖህ ሪል ስቴት አራብሳ መንገድ ላይ ፣ ሃያት፣ ሲኤሚሲ በንዝረቱ ሰዎች ከቤታቸው ወጥተዋል ።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአዲስ አበባ ብዙ ቦታዎች እንደተከሰተ እየተነገረ ነው፣ በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ #ምስራቅ_ኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጡ እንደተከሰተ ከሚደርሱን መረጃዎች ተመልከተናል።
👍51
የጥንቃቄ መልዕክት ‼️

የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ የሚገባቸዉ የጥንቃቄ ርምጃዎች፦

📌  ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንጻዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሰሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እንዲሁም ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

📌  በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

📌  በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ - ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

📌  መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ - የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሰሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽከርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።
👍42
You inivist only a minimum 350birr to get started
ከትምህርት ሚኒስትር የተሰጠ መግለጫ ለሪሜዲያል‼️

የ2017 የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅምን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የRemedial Program የመግቢያ ነጥብ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ፈተናዉን የወሰዱና ከ50% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም

1ኛ. በሁሉም አማራጮች (በግልና በመንግስት ተቋማት) የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ና ከዚያ በላይ የተቆረጠ ሲሆን

2ኛ.በመንግስት ተቋማት የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ።

1)የተፈጥሮና የማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች

👉204 ከ600

2)የተፈጥሮና የማሀበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች

👉 192 ከ600

3)ታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮና ማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች

👉192 ከ600

4)ታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮና ማሀበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች

👉186 ከ600

5)ማህበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ወንድ ተማሪዎች

👉160 ከ500

6)ማህበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ሴት ተማሪዎች

👉155 ከ500

7)በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች

👉238 ከ700

8)በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች

👉224 ከ700

የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋምና የት/ት መስክ ምርጫችሁን በየት/ት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት የምትችሉ መሆኑን ት/ት ሚንስቴር ገልጿል።https://youtube.com/@aberagasare?si=y_BPf93mqw68UzBa
👍3510
የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ‼️

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት : https://placement.ethernet.edu.et 
➡️ በቴሌግራም : https://www.tg-me.com/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።https://youtube.com/@aberagasare?si=y_BPf93mqw68UzBa
13🥰8
Live stream started
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
*****

የ2017 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ በመጪው ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።

በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ካሉ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እንዲመዘገቡ ያሳሰበው አገልግሎቱ፤ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ፈተናውን እንደማይፈተኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት አስጠንቅቋል።
👍64
ይመዝገቡ!

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና #በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ #የግል አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ አድርጉ!

ከዚህ ቀደም በመደበኛ ፕሮግራም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ያላመጣችሁና ፈተናውን በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ የግል አመልካቾች ምዝገባ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

https://register.eaes.et/Online ሊንክ ላይ በመግባት Apply Now የሚለውን ይጫኑ፤ የሚመጣላችሁን ቅፅ በጥንቃቄ ይሙሉ፤ አስፈላጊ ሰነዶችን ይጫኑ፤ የምዝገባ ክፍያ ብር 750 ክፍያ በመፈጸም ምዝገባዎትን ያከናውኑ፡፡

ምዝገባው የሚያበቃው 👇
ማክሰኞ ጥር 20/2017 ዓ.ም

በምዝገባ ሒደቱ ማንኛውም ድጋፍ ቢያስፈልግዎ ከላይ በምስሉ ላይ በተጠቀሱት የስልክ ቁጥሮች በመደወል ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡
3👎2
በኦሮሚያ ክልል በ2017 ዓ.ም ከ212 ሺህ በላይ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ - የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ

በኦሮሚያ ክልል በ2017 ዓ.ም ከ212 ሺህ በላይ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ሲሆን፤ 59 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ ቀሪዎቹ ደግሞ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን ይሰጣል ያሉት ኃላፊው፤ ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው ብለዋል፡፡ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱባቸው ማዕከላት እየተለዩ እንደሆነ ጠቁመዋል።  #FMC
👍2😍1
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ከታህሳስ 6 እስከ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም መከናወኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) አስታውሰዋል፡፡ 

በዚህም ከ608 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች መመዝገባቸውን ገልፀዋል። 

ሀገር አቀፍ ፈተናው በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፤ ክልሎች በኦንላይን እና በወረቀት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ እስከ የካቲት 25/2017 ዓ.ም ድረስ ለይተው እንዲያሳውቁ ይጠበቃል፡፡

የፈተና ዝግጅቱ ከኢኮኖሚክስ በስተቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት አይነቶችን ያካተተ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ኢኮኖሚክስ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የገባ በመሆኑ ለዚህ ዓመት ከ12ኛ ክፍል ብቻ እየተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል። #ENA
👍7
44A+ እና 40A+ ያሳኩት ተመራቂዎች 👏

ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የተመረቁት ተማሪ አስማማው እና ተማሪ ቤዛዊት ከ40 በላይ A+ በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚዎች ሆነዋል።

የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ተመራቂው ተማሪ አስማማው ሽፈራው CGPA 4.00 እና 44A+ በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል ተመራቂዋ ቤዛዊት ጌቱ CGPA 4.00 እና 40A+ በማምጣት በሁለተኝነት የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

ሁለቱም ተመራቂዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ ለትምህርታቸው ብቻ በመስጠታቸውና ጠንክረው በመስራታቸው ለዚህ ውጤት መብቃታቸውን ገልፀዋል።

https://www.tg-me.com/neaea_gov_et_student_results
👍8
በጸጥታ ችግር ምክንያት ከ7 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ7 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ የክልሉ የትምህርት ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ7 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ ገልጸዋል።

ግጭቶች የሕጻናትና ወጣቶችን አዕምሮ በመመረዝ የወደፊት ዕድላቸውን የሚያሰናክሉ በመሆናቸው፤ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚገባ በአጽንኦት አንስተዋል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ በበኩላቸው፥ በክልሉ በትምህርት ላይ የደረሰውን የከፋ ጉዳት በመቀልበስ ወደነበረበት የመማር ማስተማር ሁኔታ ለመመለስ ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በክልሉ በጸጥታ ችግር ምክንያት በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 7 ሚሊየን ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ቢታቀድም፤ የተመዘገቡት ተማሪዎች 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ በትምህርት ዘመኑ በሁለት ዙር በተደረጉ ኢ-መደበኛ ምዝገባዎች የተመዘገቡት 76 ሺህ ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡

መድረኩ በትምህርት ዘርፍ በደረሰው ጉዳት ላይ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ@neaea_gov_et_student_results
👍3🖕2
2025/07/14 14:25:10
Back to Top
HTML Embed Code: