Telegram Web Link
ተፈናቃይ አርሶ አደሮች የተሰጠን የጋራ መኖሪያ ቤት የለም አሉ

አዲስ አበባ አከባቢ ያሉ ገበሬዎች
"እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም ገበሬ ባዶ እጁን ነው ያለው። ይህ ፈጣሪ የሚያውቀው እውነት ነው" በማለት ለቢቢሲ የተናገሩት ከመሬታቸው ተፈናቅለው የጋራ መኖሪያ ቤት ይሰጣቸዋል ከተባሉት ግለሰብ መካከል አንዱ ናቸው።

በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ አርሰው ያድሩ የነበሩ ገበሬዎች፣ በከተማዋ መስፋፋት እና ለልማት በሚል ምክንያት ከእርሻ መሬታቸው የተፈናቀሉ በርካቶች መሆናቸው ይነገራል።

ከእርሻ መሬታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው የአዲስ አበባ ከተማ የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ኮሚሽን በተጠናቀቀው 2012 ዓ.ም ብቻ መሬት ከተወሰደባቸው እና ለችግር ከተጋለጡ ከ67 ሺህ አርሶ አደሮች ላይ መረጃ ተሰብስቧል ብሏል።

ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ በ2012 ዓ.ም መሬታቸው ከተወሰደባቸው ገበሬዎች መካከል 1655 የሚሆኑት መጠለያ እና ገቢ ምንጭ በማጣታቸው በእምነት ተቋማት እና መንገድ ላይ በልመና ህይወታቸውን እየገፉ ነው።

https://www.bbc.com/amharic/news-54078495?at_medium=custom7&at_custom1=%5Bpost+type%5D&at_custom2=facebook_page&at_campaign=64&at_custom4=8C2E21BE-F4BB-11EA-A48F-B8334D484DA4&at_custom3=BBC+News+Amharic
አፋር የመንግስትን እና የህዝብን አስቸኳይ ድጋፍ እና እርዳታ ይሻሉ

ይህን ከባድ የተፈጥሮ አደጋ በቸልታ የሚታለፍ አይደለም:

አፋር የሃገራችን ዳርድንበር ለዘመናት ሲጠብቁ የቆዩ ፣ የሰው ልጆችን ሁሉ በእኩልነት እና በክብር ተቀብለው የሚያስተናግዱ እንግዳ ተቀባይ እና ከሌሎች ጋር ተካፍለው መብላት ህይወታቸው የሆነ የኢትዮጵያ ውድ ህዝቦች ናቸው::

እነዚህ ወገኖቻችን ባጋጠማቸው ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ ከ200ሺህ ህዝብ በላይ ተፈናቅሎ የመንግስትን እና የህዝብን ድጋፍ እየጠበቁ ነው

ሰብዓዊነት ሁሉም ሊሰማው ይገባል:: አንድ አካላችን ሲታመም ሁሉም አካላችን እንደሚታመም ሁሉ የአፋር ወገኖቻችን ጉዳት እና ህመም እኛንም ሊያመን ይገባል::

ትኩረት ለአፋር

http://www.tg-me.com/nidatube
ኢትዮጵያ የብር ኖቶችን ልትቀይር ነው

ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ገልጸዋል።

ይህም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ ይጨምራል። እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ ይረዳሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት እንደሚያግዙ ገልጸዋል።
ፎቶ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ገጽ
Al ain

http://www.tg-me.com/nidatube
ለአዲሱ ገንዘብ ህትመት ከ3.7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ሆኗል፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

አሮጌው በአዲሱ ብር በ3 ወር ጊዜ ውስጥ እስከሚቀየር ድረስ ሁለቱም ጎን ለጎን ስራ ላይ እንደሚውሉ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል፡፡አሁን ላይ ግን አሮጌውንና አዲሱን የብር ኖት ጎን ለጎን መጠቀም እንደሚቻልም የብሔራዊ ባንክ ገዥው አስታውቀዋል፡፡
http://www.tg-me.com/nidatube
ከታቀደለት ግዜ 3 ወራት የዘገየው የብር ኖት መቀየር ሂደት በ3.7 ቢሊየን ብር ወጪ ይፋ ሆነ

-እንዲቀየር ታስቦ የተዘጋጀው የብር ኖት መጠን በዋጋ 262 ቢሊየን ብር ሲሆን

-የኖቶቹ ብዛት 2.9 ቢሊየን ነው

-በባንኮች አካባቢ ለሚፈጠር የትኛውም ህገወጥነት የባንኮችን ህልውና እስከማሳጣት የሚደርስ ቅጣት እንደሚኖር ተነግሯል

ዛሬ መስከረም 4፣ 2013 ዓ/ም ይፋ እንዳደረገው የብር ኖቶች 5 ብርን ሳይጨምር በሶስት ወራት ግዜ ይጠናቀቃል ተብሎ ታቅዷል፡፡

ሆኖም ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ማለትም ከ 100 ሺ ብር በላይ ገንዘብ በእጃቸው የሚገኝ ዜጎች የገንዘብ ለውጡን በ አንድ ወር ግዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በከፍተኛ ሁኔታ የጥሬ ገንዘብ በኢኮኖሚ ውስጥ ታትሞ መሰራጨቱን ያስታወቁት ጠ/ሚ አብይ አህመድ ለዚህም ማሳያ አሁን የታተመው የ10 ብር የገንዘብ ኖት ብቻ በ1990 ዓ/ም ለነበረው የብር ኖት መቀየሪያ ከታተሙት ሁሉም አይነት ኖቶች የሚበልጥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በአዲሶቹ ኖቶች ላይ ከፍተኛ የደህንነት ማረጋገጫዎች የተካተቱበት ሲሆን አሁን ይፋ ለተደረገው የ 200 ብር ኖት ደግሞ ስፓርክ የሚያደርግ እና በርካታ የሰለጠኑ አገራት የሚጠቀሙበት የደህንነት መጠበቂያ እንደተካተተበት የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ አስታውቀዋል፡፡

ባንኮች ቀደም ሲል ሲወተውቱት ነበር እሁን መሆኑ ያስደሰታቸው ቢመስልም የመቀየሪያ ግዜ እርዝማኔ ግን ተገቢ እንደልሆነ ሃሳባቸውን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የባንኮች ማህበር የወቅቱ ፕሬዝደንት አቶ አቤ ሳኖ ውሳኔው ለባንኮች ትርጉሙ ብዙ መሆኑን አውስተው ሆኖም የመቀየሪያው ግዜ ከ 1 ወር መብለጥ የለበትም ሲሉ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

በ 1990 ዓ/ም በነበረው የኖት ወቅት የባንኮች ተደራሽነት ዝቅተኛ በመሆኑ ሰፊ ግዜ አስፈልጎ ነበር አሁን ግን ይህ የሚያስፈልግ አይመስለኝም ብለዋል፡፡

አቶ አቤ ሌላ ያቀረቡት ሃሳብ ከፍተኛ ገንዘብ የያዙ ግለሰቦች የሚቀይሩበት ግዜ ከ 1 ወር ወደ 15 ቀን ዝቅ ቢል የሚል ሃሳብ አቅርበው፤ በተጨማሪም የገንዘብ መጠኑ ለ 100ሺ ወደ 50 ሺ ዝቅ ቢል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ብር ለመቀየር የሚመጣ ከ 10 ሺ ብር በላይ የያዘ ሰው ሂሳብ ከፍቶ እዛው እንዲያስቀምጥ ይደረጋል የሚለውን የመንግስት እቅድ ወደ 5 ሺ ቢወርድ የሚል ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

ጠ/ሚ አብይ ሃሳቡን ወስደው ባንኮች ላይ ጫና እንዳይፈጥር የተያዘ የግዜ እቅድ መሆኑን በማስታወስ ባንኮች ከብሄራዊ ባንክ ጋር በሚኖራቸው ንግግር ለውጦች ሊደረጉ እንደሚችል ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

ሆኖም እስከ 95 በመቶ የሚሆነው የገንዘብ ለውጥ በአንድ ወር ግዜ መጠናቀቅ እንዳለበት መታቀዱን አስታውሰዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የብር መቀየር ስራው 10 ወራት የወሰደ ሲሆን ከሶስት ወራት በፊት ቅያሬውን ይፋ ለማድረግ ታስቦ ኮሮና ተህዋስ በፈጠረው ተፅእኖ ተግባራዊ የማድረጊያው ግዜ መዘግየቱን የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ ለካፒታል ተናግረዋል፡፡

ኖቶቹ የታተሙባቸውን አገራት ግን ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ ለገንዘብ ህትመቱ ብቻ 3.7 ቢሊየን ብር የወጣበት ይህ ቀደም ሲል ፕሮጀክት X ተብሎ ይታወቅ እንደነበር የገለፁት ጠ/ሚ አብይ በመቀየር ሂደቱ ተጨማሪ ወጪ መኖሩን አስታውሰዋል፡፡

የብር ኖት የመቀየር ሂደት ላይ ባንኮች ከፍተኛ ሃላፊነት እንዳለባቸው በአፅንኦት የተናገሩት ጠ/ሚኒስትሩ መንግስት በሚመለሱ አሮጌ ኖቶች ላይ ሃሰተኛ ገንዘብ መኖሩን እያንዳንዱን ኖት በሰው ሃይል እና በማሽን በመፈተሽ የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከየትኛውም ባንክ የሚመጡ ህገወጥ ኖቶች ባንኮቹን ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆኑን አስጠንቅቀዋል፡፡
ህገወጥ እንቅስቃሴዎች አንዳንድ ባንኮች አካባቢ እንዳለ መረጃ እየደረሰን ነው ያሉት ጠ/ሚ አብይ በዚህ የብር ኖት የመቀየር ሂደት ይሄ የሚቀጥል ከሆነ ዋነኛ የባንክ ሃላፊዎችንም ሆነ እራሱ ባንኩን ህልውና የሚያሳጣ እርምጃ የሚወሰድ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

የብር መቀየር ሂደቱ በአብዛኛው ከኢኮኖሚ ምክንያቶች ጋር የሚያየዝ መሆኑን የተናገሩት ይናገር ሕገወጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በዋንኛ ምክንያትነት አንስተዋል፡፡
አብይ የፀጥታ መዋቅሩ ከዛሬ ጀምሮ ከአገር ውስጥ የሚወጡ እና የሚገቡ የገንዘብ ኖቶች ላይ ከፍተኛ ስራ እንዲሰራ አዘዋል፡፡

Capital

http://www.tg-me.com/nidatube
የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት የወከሏቸውን ጠበቆች አሰናበቱ።

አቶ ልደቱ እርምጃውን የወሰዱት ከዚህ በኋላ በከተማው ፍርድ ቤት የህግ ክርክር ማድረግ ባለመፈለጋቸው እንደሆነ ዛሬ ረቡዕ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል።

ከዚህ በኋላ የሚካሄደውን ክርክር “ትርጉም የሌለው” ሲሉ የጠሩት አቶ ልደቱ፤ “ህግ የፖለቲካ መሳሪያ በሆነበት ሁኔታ በህግ ክርክር መብትን ማስከበር ስለማይቻል ከአሁን በኋላ ግዴታዬን ለመወጣት ቀጠሮ ሲሰጠኝ በችሎት ፊት ከመገኘት ባለፈ የህግ ክርክር የማድረግ ፍላጎት የለኝም” ሲሉ በፓርቲያቸው በኩል ባሰራጩት ደብዳቤያቸው አስፍረዋል።

(ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

http://www.tg-me.com/nidatube
'ግርግር ለጭልፊት ይመቻል' እንዲሉ …
(በጋዜጠኛ ዘከሪያ ሙሀመድ )
.
የብር ኖቶች እየተቀየሩ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት፣ ሕገ ወጥ ገንዘብን ወደ ሕጋዊነት የመቀየር ሙከራን በማክሸፍ ዓላማ የሚካሄድ የዘፈቀደ ብርበራ፣ ሕጋዊ ጥሬ ገንዘብ ይዘው በሚንቀሳቀሱ ዜጎች ላይ ችግር እየፈጠረ ነው።
.
ከመሸ በደረሰኝ መረጃ፣ ዛሬ ከሰዓት በኋላ፣ በግል መኪናው ውስጥ 200 ሺህ ብር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ አንድ ነጋዴ፣ ሉካንዳ አካባቢ ትራፊክ እና አንድ ፖሊስ ለፍተሻ ያስቆሙታል። ከዚያም ፖሊሱ፣ የዳሽ ቦርዱን ኪስ እንዲከፍት ይጠይቀዋል። ከፈተለት። 20 የአሥር ሺህ ብር እስሮች ያየው ፖሊስ፣ "ይሄ ገንዘብ በሕገ ወጥ ያስጠይቃል፤ ከሚወረስብህ 2 ሺህ ብር አስቀምጥ" ይለዋል። ነጋዴውም፣ "ለምንድነው የሚወረሰው? የራሴ ገንዘብ'ኮ ነው" ብሎ ለመከራከር ቢሞክርም፣ "ወንድሜ ክርክር አያዋጣህም፣ ይልቅ አፍጥነው" አለው ትራፊክ ፖሊሱ። ነጋዴውም፣ የትራፊክ ፖሊሱ መደረብ አስደንግጦት፣ 200 ሺህ ብሩን ከእነዚህ ጭልፊቶች በማዳን ለመገላገል ሲል፣ የተጠየቀውን ቆጥሮ ለማስረከብ ተዳርጓል።
.
የንግድ ልውውጡም ሆነ የፋይናንስ ሥርዓቱ እጅግም ባልዘመነባት አዲስ አበባ፣ በ100 ሺህዎች የሚቆጠር ብር ይዞ መንቀሳቀስ፣ መክፈል፣ መቀበል፣ ባንክ ማስገባት፣ ከባንክ ማውጣት፣ በከተማችን የንግዱ ኀብረተሰብ አባላት ዘንድ፣ በተለይ መርካቶ አካባቢ፣ በጣም ተራ ነገር ነው። … በተጨማሪም፣ ብዙ ነጋዴዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ጥሬ ብር፣ በመኖሪያ ቤት ወይ በንግድ ሱቃቸው ካዝና ውስጥ ያስቀምጣሉ። ከባንክ ውጪ በቤት ውስጥ በሚቀመጥ የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ከተጣለ ገና አንድ ወሩ ነው። … የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነሐሴ 12 ቀን 2012 ይፋ ያደረገው አዲስ መመሪያም ቢሆን፣ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር ማስቀመጥን አልከለከለም። ስለዚህም፣ ከተለምዷዊው የንግድ እንቅስቃሴ በተጨማሪ፣ በዚህ ወቅት ብዙ ሰዎች በቤትም ይሁን በሱቅ ካዝና ውስጥ ያስቀመጡትን በዛ ያለ ጥሬ ብር ለመቀየር፣ በካኪ ወረቀት፣ በቦርሳ አልያም በፌስታል ሞልተው ወደ ባንክ መኳተናቸው የሚጠበቅ ነው። … ሲኾን ሲኾን ዜጎች አሮጌውን ብር ሸክፈው ወደ ባንክ ሲኳትኑ ለዘራፊዎች እንዳይጋለጡ ሲቪል እና ባለ መለዮ ፖሊሶች ነቅተው ጥበቃ ሊያደርጉላቸው የሚገባ ይመስለኛል። በተቀረ፣ መቶ ሺህዎች የያዘን ሰው ሁሉ "ሕገ ወጥ!" እያሉ ማሸማቀቅ፣ አያሌ ዜጎችን የጭልፊቶች መጫወቻ ሊያደርግ እንደሚችል ማሰብ ዲየግ ነው።
.
ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ወደ ሕጋዊነት ለመቀየር የሚሞክሩ የመኖራቸውን ያህል፣ በወፋፍራሙ የታሰረ፣ በዛ ያለ ጥሬ ገንዘብ ይዞ የተገኘን ሁሉ በደፈናው በሕገ ወጥነት የማሰብ ዝንባሌ፣ የሕዝብን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸውን ፖሊሶች ወደ አጉል ክጃሎት ከመግፋትም በላይ፣ ይህን ዓይነቱን ውዥንብር ለ"ቢዝነስ" በመጠቀም ለተካኑት ዘራፊዎች መልካም አጋጣሚ ነው የሚፈጥረው።
.
እናም፣ ይታሰብበት ለማለት ነው።
No photo description available.
ሰበር ዜና፦
ዛሬ ዕለተ ዐርብ መስከረም 8 ቀን 2013 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባኪያሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፤
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ስድስተኛው ዙር አገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ሲሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት አመለከቱ።

http://www.tg-me.com/nidatube
ኢንና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን!

የታላቁ ቢላል መስጂድ ኢማም እና ኸጢብ
#ሸይኽ_አህመድ_ሙሐመድ_አደም ወደ አኼራ ሄደዋል።

ሸይኽ አህመድ ሙሐመድ አደም በደቡብ ወሎ ክፍለ ሃገር ቦረና ውስጥ ቡሪ በምትባል መንደር ተወልደው ከተለያዩ ታላላቅ የቦረና እና የአካባቢው መሻይኾች ኢስላማዊ እውቀቶችን ከቀሰሙና ኢጃዛ ካገኙ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከእውቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ እና ሌሎችም ዑለማኦች ጋር በመሆን በታላቁ አንዋር መስጂድ ከ15 ዓመታት በላይ የቁርአን ተፍሲር አቅርተዋል።

ከዚያም ወደ ቢላል መስጂድ በመምጣት ከ30 ዓመታት በላይ በኢማምነትና ኸጢብነት፣ የዒልም ሃለቃዎችን በመመስረትና በርካታ ቁጥር ያላቸውን ደረሶች በማቅራት እንዲሁም ማህበረሰቡን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በማንቃት ከፍተኛ ተጋድሎ አሳይተዋል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ዑለሞች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ለረጅም አመታት ያሰግዱበትና ያቀሩበት ከነበረው የቢላል መስጂድ መድረክ በኩላሊት ህመም ምክንያት ከቤት እስከቀሩበት ድረስ ሙስሊሙን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለዋል።

ለ5 ዓመታት በኩላሊት ህመም በህክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 ቀን 2013 (ሰፈር 2 ቀን 1442 ዓሂ) ወደ ጌታቸው እዝነት ተሻግረዋል።

አላህ በጀነተል ፊርደውስ እንዲያበስራቸው እንለምነዋለን!

http://www.tg-me.com/nidatube
👍1
ከሂጅራ ባንክ የተላለፈ የባለ አክሲዮኖች የፊርማ ጥሪ
*******************************************
ለውድ የሂጅራ ባንክ መስራቾች በሙሉ

የባንካችን የምስረታ ሂደት ማጠናቀቂያ የሆነው የፊርማ ስነስርዓት ከመስከረም 19 ቀን 2013 ጀምሮ ፍልውሃ አካባቢ በሚገኘዉ የአምባሳደር ቲያትር አዳራሽ ይከናወናል::
ዝርዝሩን ለእያንዳንዱ ባለአክሲዮን በስልክ የምናሳውቅ ሲሆን በተለያየ ምክንያት በቦታው መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዎኖች በውክልና የሚስተናገዱ ይሆናል::
ባለአክሲዎኖች ለፊርማ ስነስርዓቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች አሟልተዉ እንዲቀርቡ እናሳሰባለን።

- የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ኮፒ፣
- ወኪል ከሆኑ፣ የራስዎን የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ኮፒ እንዲሁም የውክልና ደብዳቤ ዋናውንና ኮፒውን፣
- አባት/እናት/ሞግዚት ከሆኑ ደግሞ የራስዎን የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ኮፒ እንዲሁም የህፃኑን የልደት ሠርተፊኬት ዋናውንና ኮፒውን

::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::

Kabajamtoota Hundeessitoota Baankii Hijraa,

Adeemsi Mallattoo Hundeessummaa Aksiyoona Baankichaa Fulbaana 19, 2013 kan eegalamu yoo ta'u iddoon Mallattoon itti adeemsifamu Magaalaa Finfinnee. Gamoo Tiyaatira Ambaasaaddar Naannawa Filowihaa jedhamee beekkamu
Fuuldura Ministeera Ittisa Biyyaatti.
Kanaafuu, Hangasii Namoonnii biyya keessa hinjirre
አልሃምዱሊላህ ከስንትጊዜ ቡኃላ አዲስ አበባ ኑር መስጅድ በዚህ መልኩ ጁምዓ ሰላት ተሰግዷል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሆስፒታል ገቡ

የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሆስፒታል ገቡ፡፡

ከነጩ ቤተ መንግስት የወጡ መረጃዎች ፕሬዚዳንቱ መጠነኛ የድካም ስሜት እንዳለባቸው ያመላክታሉ፡፡

ይሁን እንጅ ትራምፕ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የጠቀሰው መረጃው ለተሻለ ክትትልና ጥንቃቄ ሲባል ሆስፒታል መግባታቸውን አመላክቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከነጩ ቤተ መንግስት በሄሊኮፕተር ወደ ዋልተር ሪድ ሆስፒታል አቅንተዋል፡፡

በወቅቱም ለወትሮው የሚሳለቁበትን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ አድርገው የታዩ ሲሆን፥ አውራ ጣታቸውን በማንሳት ደህና ነኝ የሚል ምልክት አሳይተዋል፡፡

በቪዲዮ በለቀቁት መልዕክትም “ደህና ነኝ ብየ አስባለሁ፤ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እንደሚሄዱም እገምታለሁ ባለቤቴም ደህና ናት” በማለት ከጎናቸው ለሆኑት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የተወሰነ የቫይረሱን ምልክት ከማሳየታቸው ውጭ በመልካም ጤንነት ላይ በመሆናቸው በሆስፒታሉ ውስጥ ሆነው ሀገራቸውን እየመሩ ይቀጥላሉም ነው የተባለው፡፡

ትራምፕ በሙከራ ላይ የሚገኝ መድሃኒት የወሰዱ ሲሆን ተጨማሪ ቪታሚኖችን ጨምሮ ከቫይረሱ ለማገገም የሚረዱ ቀላል መድሃኒቶችን ወስደዋል ተብሏል፡፡

በህዳሩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የእርሳቸው ተቀናቃኝ የሆኑት ጆ ባይደን ትራምፕና ባለቤታቸው ከቫይረሱ በቶሎ ያገግሙ ዘንድ ተመኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ/ (ኤፍ ቢ ሲ)
በተቋም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦሮሚያ መጅሊስ ለ35 መሻኢኮች የሙፍቲህነት ማዕረግ ሰጠ።

1) ሙፍቲህ ዶ/ር ጄይላን ኸድር ገመዳ
2) ሙፍቲህ ዶ/ር ከማል ገለቱ ማሜ
3) ሙፍቲህ ዶ/ር ጄይላን ገለታ ማሜ
4) ሙፍቲህ ሼኹል መሻይኽ፣ ሼኽ አህመድ ዑስማን (ሼኽ አህመድ ወተር)
5) ሙፍቲህ ሼኹል መሻይኽ፣ ሼኽ ኣደም ቱላ
6) ሙፍቲህ ሼኹል መሻይኽ፣ ሼኽ ዪሱፍ ጪሮ
7)ሙፍቲህ ሼኽ ዐብዱል ቃድ ዐብደሏህ (ከቄለም ወለጋ)
8) ሙፍቲህ ሼኽ ዐብዱል ሐኪም ሙሀመድ (ከምራቅ አርሲ)
9) ሙፍቲህ ሼኽ ሙሀመድ ዐሊ ( ከምስራቅ ባሌ)
10) ሙፍቲህ ሼኽ ጄይላን ኣደም አየለ
11) ሙፍቲህ ሼኽ ሻፊ ያሲን ሲራጅ
12) ሙፍቲህ ሼኽ ሙሳ ሀሰን አብዲ ( ሼኽ ሙሳ ሱኣላ)
13) ሙፍቲህ ሼኽ ሀምዛ ሙ/ኑር ዐብደሏህ
14) ሙፍቲህ ሼኽ ዐሊ ሙሀመድ (ሼኽ ዐሊ ጂማ)
15) ሙፍቲህ ሼኽ ኢብራሂም ዪሱፍ (ከምዕራብ ወለጋ)
16) ሙፍቲህ ሼኽ ጅብሪ ኢብራሂም ሮባ
17) ሙፍቲህ ሼኽ ሙ/ዘቡር ዪሱፍ ከጄሎ
18) ሙፍቲህ ሼኽ ዐሊ ቡታ (ከምዕራብ አርሲ)
19) ሙፍቲህ ሼኽ አህመድ ሻሚል (ከምስራቅ አርሲ)
20) ሙፍቲህ ሼኽ ሸረፉ ሙ/ኑር (ከምስራቅ ወለጋ)
21) ሙፍቲህ ሼኽ ሲራጅ ሙሀመድ (ከሰሜን ሸዋ)
22) ሙፍቲህ ዶ/ር ሙሀመድ ከማል ቲልሞ
23) ሙፍቲህ ሼኽ ሙ/ዘይን ሙ/ጠይብ
24) ሙፍቲህ ሼኽ ዐብዱል መናን ዐብደሏህ (ከምስራቅ አርሲ)
25) ሙፍቲህ ሼኽ አህመድ ሰዒድ
26) ሙፍቲህ ሼኽ ሙደሲር ሼኽ ሻሚል
27) ሙፍቲህ ሼኽ ሙሀመድ ዐብዱረህማን አህመድ
28) ሙፍቲህ ሼኽ ሙሀመድ አስራር ኢብራሂም
29) ሙፍቲህ ሼኽ ዐብደሏህ ጀማል አባሚልኪ
30) ሙፍቲህ ሼኽ መዕሸር ሁሴን ኸድር
31) ሙፍቲህ ሼኽ አህመድ ሀሰን ሙሀመድ
32) ሙፍቲህ ሼኽ ሙ/ኑር ሐጅ ጉዮ
33) ሙፍቲህ ሼኽ ሰዒድ ሙሀመድ አባይ
34) ሙፍቲህ ሼኽ ሙሀመድ አባ ድጋ
35) ሙፍቲህ ሼኽ ዐብዱልገፋር
እና ሁሉም የመጅሊስ ምክር ቤት አባላት (ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ ሼኽ ጀማል ዐሊዪ፣… ጨምሮ) የዐለማዖች ምክር ቤት አባላት ናቸው።

Via- አዱኛ ሙጬ
@nidatube @nidatubebot
በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ክልል ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ በሙሉ ድምጽ ጸደቀ

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ በሙሉ ድምፅ ጸደቀ።

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት ቀደም ሲል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ አቅርበው ነበር።

በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ ሰፋ ያለ ውይይት ካደረገ በኋላ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈፃሚነት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ጥያቄውን ያቀረቡት የከፋ፣ ቤንች፣ ሸኮ ፣ምእራብ ኦሞ፣ዳውሮ፣ ሸካ ዞኖችና የኮንታ ልዩ ወረዳ ናቸው።

ዞኖቹ ተቀራራቢ ቋንቋ፣ ባሕል፣ ታሪክና መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ስላለን አንድ ላይ ብንሆን የተሻለ ነው በማለት ጥያቄያቸውን ማቅረባቸው ተገልጿል።

@nidatube @nidatubebot
ኢና ሊላሂ ወ ኢና ኢለይሂ ራጂኡን

የ17ቱ ኮሚቴ አባል የነበሩት ሼይኽ ዩሱፍ ሙዘሚል ወደ አኼራ ሄዱ

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊኮሚቴ አባል እና የሼይኽ ሆጀሌ ሰፈር መስጂድ የረጅም አመታት የመስጂደዱ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ሼይኽ ዩሱፍ ሙዘሚል ወደ አኼራ ሄደዋል፡፡

ሼይኽ ዩሱፍ ሙዘሚል በኮሚቴው ውስጥ ህዝበ ሙስሊሙ የሰጣቸውን አማና ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት ሲያደረጉ የነበሩ አባት ሲሆኑ ሼህ ሆጀሌ መስጂድም ከአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ አልፎ ለከተማው ህዝበ ሙስሊም የሚጠቅም እንዲሆን በማድረግ ትልቁን ሚና ከተጫወጡት ሰዎች መካከል እሳቸው ቀዳሚው ነበሩ፡፡

ሼህ ሆጀሌ መስጂድ አሁን ለደረሰበት ትልቅ ደረጃ በማድረሱ ረገድ የመስጂዱ ኮሚቴ በመሆን ትልቅ ሚና የተጫወቱ ሲሆን ከምስረታው ጀምሮ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የሳቸውን አስተዋፅኦ የጎላ ነበር፡፡

ሼይኽ ዩሱፍ ሙዘሚል በፌደራል የሸሪዓ ፍርድ ቤትም ቃዲ በመሆን ህዝበ ሙስሊሙን አገልግለዋል::

ሼይኽ ዩሱፍ ሙዘሚል የ17ቱ ኮሚቴ አባል በመሆን የሙስሊሙን አማና በመወጣት እና በሼህ ሆጀሌ መስጂድም የአመራር ሃላፊነታቸውን በመወጣት ለወጣቱም አርዓያ መሆን የቻሉ አባት ነበሩ፡፡

ህዝበ ሙስሊሙን በማገልገል ህይወታቸውን ባሳለፉት ሼይኽ ዩሱፍ ሙዘሚል ስርዓት ቀብር ላይም ህዝበ ሙስሊሙ በመገኘት አሸኛኝ ሊያደርግላችቸው ይገባል

ሼይኽ ዩሱፍ ሙዘሚል ትግላቸውን አላህ ይቀበላቸው፣ ከሸሂዶች ይመድባቸው
ማረፊያቸውንም በጀነት ያድርግላቸው

ለመላው ቤተሰቦቻቸው እና ለሙስሊሙ ማህበረሰብም አላህ ሰብሩን ይለግሰን

@nidatube @nidatubebot
2025/07/14 09:48:49
Back to Top
HTML Embed Code: