Telegram Web Link
የዒድ ሥነ-ሥርዓቶች

1- ገላን መታጠብ፣
2- አዲስ የሆነ ልብስ (ንፁህ ባይሆን እንኳን) መልበስ፣
3- ሽቶ መቀባት፣
4- ዘካት አልፊጥርን ከሶላት በፊት መስጠት፣
5- የተወሰኑ ተምሮችን በልቶ መውጣት፣
6- ለዒድ ሶላት ማልዶ መውጣት፣
7- ልጆችን ጨምሮ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ወደ ዒድ አደባባይ እንዲወጡ ማድረግ፣
8- ሰብሰብ ብሎ በብዛት መስገድ፣
9- ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ በእግር መሄድ፣
10- ከፍ ባለ ድምፅ ተክቢራ እያደረጉ መሄድ፣
11- አላህን አብዝቶ ማመስገን፣
12- በዒድ ሶላት ቦታ ላይ ከዒድ ሶላት በፊት ሱንና ሶላት አለመስገድ፣
13- በዒድ መስገጃ ቦታ ላይ አዛንም ሆነ ኢቃማ አለማድረግ፣
14- ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ፣
15- በዒድ ቀን መደሠት፣ መጫወትና መዝናናት፣
16- የእንኳን አደረሣችሁ መልዕክቶችን ማስተላለፍና መጨባበጥ፣
17- ወደ ዒድ ሜዳ በሄዱበት መንገድ አለመመለስ፣
18- ዚያራ ማድረግ፡፡ ወላጆችን፣ ዘመዶችን፣ ዑለሞችን፣ አቅመ ደካሞችን፣ ድሆችን፣ ወዳጆችን መዘየር፡፡
19- ድሆችን መርዳት፣ የዒድን ቀን በደስታ እንዲያሳልፉ ማገዝ፣
20- ሶደቃ ማብዛት፣
21- በዒድ ቀን ወንጀል አለመሥራት፣
©ነጃሺ ማተሚያ ቤት
@nidatube @nidatubebot
«መጅሊስ ዋጋ የከፈልኩበት ተቋሜ ነው»

ነገ ጠዋት ከ 3 ሰዓት ጀምሮ «መጅሊስ ዋጋ የከፈልኩበት ተቋሜ ነው» በሚል በርካታ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ከጦርሃይሎች በላይ ሆላንድ ኢንባሲ ጋር በሚገኘው የፌደራል መጅሊስ ቅጥር ጊቢ በመገኘት የመጅሊስ አመራሮች የተሰጣቸውን ህዝባዊ አማና በተመለከተ ጥያቄ ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ታውቋል። ከሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ሀሳቦች መካከል:

1) «አማናችሁን በ6 ወራት እንድትወጡ ተሰጥቷችሁ ከ 2 ዓመታት በላይ ባለመወጣት ህዝበ ሙስሊሙን የበደላችሁበት ምክንያት በግልጽ ንገሩን»፣

2) «የመጅሊስ ምርጫ ቁርጥ ቀኑ ይነገረን»፣

3) «መጅሊስ የህዝበ ሙስሊሙ እንጂ የግለሰቦች አይደለም»

4) ፣«ሕዝበ ሙስሊሙን የበደሉት የመጅሊስ አባላት በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ»፣

5) «የጠቅላላ ጉባኤውን ዉሳኔ ያደናቀፉ አካላት በአስቸኳይ ለህግ ይቅረቡልን»

6) ፣«የፌደራል መጅሊስ የክልል መጅሊሶችን ተወካይ ሆኖ ሳላ ስለምን ከነርሱ ፍላጎት በተቃራኒ ቆመ?»

7) በ2004 ህዝበ ሙስሊሙ ለመብቱ ሲታገል የትግሉ መነሻ የሆነውን የአወሊያ ተቋምን መጅሊስ በማዳከም ለማፈራረስ የጀመረው ተግባር በአስቸኳይ ይቁም»

8) ፣ «እኛ ሙስሊሞች ነን።ሱፊ-ሰለፊ ጫወታ አይመለከተንም። መጫወት የፈለገም አካል ዋጋ በከፈልንበት ተቋማችን ሳይሆን በቤቱ ሄዶ ይጫወት»፣

9)«ህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየደረሰ ላለው ትንኮሳ የፌደራል መጅሊስ ሚናውን ካለመወጣት አልፎ ተባባሪ ነው እስክንል ድረስ እየበደለን በመሆኑ ከተጠያቂነት አያመልጥም»፣

10) «በሀጅና በፋይናንስ ክፍል ሆነው ህዝበ ሙስሊሙን ለዓመታት የዘረፉ የቀድሞ የመጅሊስ አባላትን በህግ ተጠያቂ ማድረግ ሲገባችሁ ከተባረሩበት መልሳችሁ እንዴት ሾማችሁ?»፣

11) «ከህወሃት መራሹ መንግስት ጋር ዉድ ዋጋ ከፍለን የታገልነው መጅሊስ የናንተ መጫወቻ እንዲሆን አይደለም»፣

12) «ዑለማ ሆናችሁ በቃል በመገኘትና አማናን በመጠበቅ ለህዝቡ ምሳሌ መሆን ሲገባችሁ እንዴት የዑለማን ስም የሚያሰድብ ተግባር ትፈጽማላችሁ? »፣

13) አህለል ከይሮች እንስራ በማለት እየለመኑ ጭምር ሲጠይቁ መስጊዱ እንዲሰራ ፈቃደኛ ባለመሆን የነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከልን መሬት ለማስነጠቅ የጀመራችሁት አካሄድን በአስቸኳይ በማቆም እንዲገነባ ይደረግ።

14) የተሰጣችሁን አማናንን ቶሎ እንወጣ በማለታቸው በሌላችሁ ስልጣን ቦርዱን በማገዳችሁ በይፋ ይቅርታ ጠይቁ። ወደ መጅሊስ እንዳይገቡ ያዘዘው አካል ላይ በአስቸኳይ እርምጃ ይወሰድበት።

15) «መጅሊስ በአስቸኳይ ህወሃት ካሰማራቸው ካድሬዎችና ተላላኪዎች ነፃ የሆነ ህዝባዊ ተቋም እንዲሆን እንጠይቃለን»፣«የሚሉ ይገኙበታል።

የዑለማ ምክር ቤት አባላት ነገ ወደ ቢሮ እንደሚገቡ የታወቀ ሲሆን በቢሮዋቸው ሳይገኙ የሚቀሩ ከሆነ ሰኞ እለት ጀምሮ በመጅሊስና በመኖሪያ ቤቶቻቸው በመመላለስ ጥያቄ ለማቅረብ መታሰቡ ታውቋል። የመጅሊስ ጉዳይ ይመለከተኛል፣ «ተቋሜን አሳልፌ አልሰጥም» የሚል የአዲስ አበባ ሙስሊም በስፍራው ሲገኝ ጥያቄዎቹን በኢስላማዊ አደብ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ማቅረብ እንደሚገባው አሳስበዋል።
«የሀገር ጉዳይ ይቀድማል»

T.me/ahmedin99

አንዳንዶች የምታነሳቸውን ጥያቄዎችህን እንድታቆም በመፈለግ፣ሌሎች ደግሞ ጉዳዩ ሳይገባቸውና ለሀገራቸው የእውነት ከማሰብና ከመጨነቅ የተነሳ «የሀገር ጉዳይ ይቀድማል» ሲሉ ይደመጣሉ። እውነት ነው የሀገር ጉዳይ ይቀድማል። ሀገር ሕዝበ ሙስሊሙን አያካትትም ካልተባለ በቀር የሕዝበ ሙስሊሙን ችግርም የሀገር ችግር ነው። የህዝበ ሙስሊሙን ቁልፍ ችግርም መፍታት የሀገርን ችግር መፍታት ነው። ችግሩንም አለመፍታትም የሀገር ችግር እንዲቀጥል መፍቀድና መስማማት ነው።

የመጅሊስን ተቋማዊ ችግሮች በተቋማዊ አሰራር እንዲፈታ የሰባት ክልሎች እስልምና ጉዳዮችና ከሁለት ሦስተኛ በላይ የሆኑ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በፊርማቸው የጠቅላላ ጉባኤ ሲጠሩ ፖሊስ ስራዉን መስራት ትቶ ህጋዊ የሆነና 33 ሰዎች የሚሳተፉበትን የመጅሊስን ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባን ለማደናቀፍ ሲሯሯጥ፥የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በራሳቸው ተሰብስበው? በጉዳዩ ላይ በመነጋገር ችግር እንዳይፈቱ ካደረጉ በኋላ ደግሞ ከመንግስት አካላት ጋር ለስብሰባ ተቀመጡ ተባለ። በተድበሰበሰ መልኩ ችግሩ ሳይፈታ «ተፈታ» ተብሎ የተሸፋፈነ መግለጫ እንዲሰጥ ተደረገ። ወዲያው የክልል መጅሊሶችና ቦርዱ ችግሩ እንዳልተፈታ ይፋ ማድረግ ጀመሩ። ችግሩ ሳይፈታ «ተፈቷል» ያሉት አካላትና ሽማግሌዎችም ጭምር ሳምንት ሳይቆይ እንዳልተፈተ ማሳወቅ ጀመሩ።

የ60 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መሪ ተቋም የሆነው መጅሊሱ ፕሬዝዳንቱ በየመድረኩ እየዞሩ በመናገራቸው ብቻ ምንም አይነት እቅድና ሪፖርት ሳይኖረው ለሁለት ዓመታት ያክል ያለምንም፣ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ፣ ዓመታዊ እቅድ፣ተግባርና ሪፖርት በሴራ እንዲመክን ሲደረግ የሀገር ጉዳይ ካልሆነ የሀገር ጉዳይ የሚሆነው የቱ ነው?

ይህን ሁሉ በቅርበት እያየ ያለ ሕዝብ «ጥያቄዬ አልተመለሰም» ብሎ መንገድ ሳይዘጋ ከፊል የህዝበ ሙስሊሙ አካላት ወደ መጅሊስ ቢሮ በመሄድ ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዳያቀርቡ ፖሊስ ራሱ በድንጋይ ጭምር መንገድ ሲዘጋና ሌሎች እየሆኑ ያሉትን ሁኔታዎችን ስታይ የሀገርን ጉዳይ ያላስቀደመው ማን ነው? ሀገርስ የሚቀድመው ህዝበ ሙስሊሙን ወደ ኋላ በማስቀረት ነውን? መፈታት የሚችልን ጉዳይ «የሀገር ጉዳይ ይቀድማል» ስም እንዲድበሰበስ ተፈለገ? ብለህ ለመጠየቅ ትገደዳለህ።
ለዓመታት በሴራ እንዲቋረጥ የተደረገውን የአፋሩን ፕሮጀክት ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ላይ የየበኩላችንን እንወጣ!


ለዓመታት እንደቆመ እንዲቀር የተደረገው ኢስላማዊ ተቋም
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
ትናንት በአፋር ከጎበኘዃቸው ስፍራዎች አንዱ በአሳይታ አቅራቢያ የሚገኘው የሱልጧን ዓሊ ሚራ መስጊድ፣ ኢሰላማዊ ኮሌጀና ቤተመንግሥት ይገኝበታል። ይህ ተቋም እንደመረጃ ምንጮቻችን ገለፃ ከሆነ ግንባታው የተጀመረው በ1980ዎቹ መጨረሻ ገደማ በቀድሞው የአፋር ሱልጧን በነበሩት ሱልጧን ዓሊ ሚራህ ጠያቂነት እና በሸህ ሙሀመድ አሊ ሁሰይን አልአሙዲ የግንባታ ወጪ ሸፋኝነት ነበር። ግንባታው 70% ከተጠናቀቀ በዃላ ነው በህወሃት መራሹ መንግስት ትዕዛዝና ቀጥተኛ ጫና ግንባታው ሳይጠናቀቅ ባለበት እንዲቀር የተደረገው። መስጂዱ ሰፊና በ2ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን ተጀምሮ የነበረው ኢስላማዊ ኮሌጀ ደግሞ ከ50 በላይ መማሪያ ክፍሎች፣ አደራሾችና ክሊኒኮችና ሌሎች ለተለያዩ ግልጋሎት የሚውሉ ክፍሎች አሉት። በማዕከሉም አጠገብ ያረጀው የቀድሞው የሱልጧን አሊሚራህ ቤተመንግስት ያለ ሲሆን በርሱ አቅራቢያም ሱልጧን አሊሚራህ በህይወት እያሉ ለርሳቸውና ለአፋር ሱልጧኖች ዘመናዊ ቤተመንግስት ግንባታ ተጀምሮ የማጠናቀቂያ(ፊኒሺንግ) ሥራ ሲቀረው እንዲቋረጥ ተደርጓል። ቤተመንግስቱ በምስሉ ላይ እንደሚታየው በርካታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ቤተመንግስቱ ተጠናቆ ሱልጧን አሊ ሚራህ በዉስጡ መኖር ሳይችሉ ሲሞቱ በአቅራቢው ተቀብረው ቀብራቸው ይገኛል።

የአካቢው አዋቂዎች እንደሚሉት ሼህ ሙሀመድ ሁሴን አልአሙዲ ኮንትራት ለተሰጠው ተቋራጭ በተዋዋሉት መሠረት ቀሪ 49 ሚሊየን ብር እንኳ እንዳይከፍሉ ጫና ተደርጎባቸው ኮንትራክተሩ ለዓመታት ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ ቢያቀርብም ምላሽ ሳያገኝ ህይወቱ እንደለፋ(ራሱን አጠፋ የሚሉ አሉ) ይገልፃሉ።

የአከባቢው አዛውንቶች እንደሚሉት የአፋር ህዝብ ይህ ኢስላማዊ ኮሌጅ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በዲኑ ላይ ይጠነክራል በሚል ምክንያት የህወሃት አመራርና የአንድ ምዕራብ ሀገር ኢምባሲ ተማክረው እንዳስቆሙ ይገልፃሉ። ዋቢ የሚያደርጉት ደግሞ የዚያ ሀገር ኢምባሲ ሰራተኞች አጠያይቀው ቦታው ላይ መጥተው በጎበኙ በሳምንቱ ግንባታ እንዲቆም መታዘዙን ይጠቅሳሉ። 100% ሙስሊም የሆነው የአፋር ህዝብ ሃይማኖቱን የሚማርበትን ኢስላማዊ ኮሌጅ እንዳይኖረው ማሰናከል የተፈለገውና መልዕክቱ ግልፅ ነው።

በአሁኑ ጊዜ የዚህ ተቋም ግንባታ ለበርካታ ዓመታት ተቋርጦ ቢቆይም በጥሩ የይዞታ ደረጃ ይገኛል። የሚመለከተው አካል ተረባርቦ ሊጨርሰው ይገባል። አንድ አባት እንደገለፁልኝ ሱልጧን ዐሊ ሚራህ በሽግግር መንግስት ጊዜ የኤርትራን መገንጠልን በዃላ ላይም በክልል የህወሃት ሰዎች ጣልቃ ገብነትናና ጫናን በመቃወማቸው ምክንያት በህወሃት ሰዎች ጥርስ ዉስጥ እንደገቡና ከዚህ ጊዜ በዃላ ማንኛውም ሱልጧኑ የደገፉትን ነገር የህወሃት ሰዎች መቃወምና ማደናቀፍ እንደቀጠሉ ገልፀውልኛል። ይህ መስጊድ፣ቤተመንግስትና ኮሌጅ በጊዜ ብዛት አርጅቶ እንደፈራርስ ቢፈለግም ይዞታው ደህናና በአሁኑ ጊዜ ከተጀመረ 20 ዓመታት የቆ ሳይሆን በቅርቡ የተጀመረ ይመስላል።(በድጋሚ የተለጠፈ)
***************

ዛሬ ሰኔ 6 ለአፋሩ ፕሮጀክት መቀጠል በያሉበት ሆነው በዚህ ውብ ታሪክ ላይ አሻራዎን ያኑሩ።
Via Ahmedin Jebel official - አህመዲን ጀበል
@nidatube @nidatubebot
ግዙፉን የሱልጣን አሊሚራህ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ለማጠናቀቅ በአፋር ክልል በአሳይታ ከተማ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ በመካሄድ ላይ ይገኛል::

ሁላችንም ባለንበት ሆነንም ያቅማችንን ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል የባንክ አካውንት ይፋ ተደርጓል።

በዚህ ታሪክ ላይ የአቅማችንን ለማበርከት:-

የአካውንት ስም: የስልጣን አሊ ሚራህ መድረሳ
የኢትዪጵያ ንግድ ባንክ 1000380109828
ዳሽን ባንክ 2936722484811
@nidatube ,@nidatubebot
« #በሴራ ያቆሙት የታላቁ ሱልጣን አሊሚራህን ማዕከል #በስራ እንጨርሰዋለን!!»
ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
@nidatube @nidatubebot
በሰላሳ አመቴ ወሊድ የተባለ ወጣት የትዳር ጥያቄ አቀረበልኝ።በጣም ውብና አማላይ የሚባል ወጣት ነበር።ሁሉ ነገሩን ወድጄ አንድ ነውር ብቻ ነበር ያገኘሁበት።ወሊድ ከኔ በፊት ሌላ ሰው አግብቶ ነበር።በዚያም ትዳር የወለደው አንድ ልጅ አለው።ሚስቱ ህፃኑን በወለደችበት ሰዓት ነበር ያረፈችው።ከሚስቱ ያላለቀ ፍቅር ያለው ወሊድ በእናቱ ግፊት እኔን ለማግባት ወሰነ።እኔም ከጥቂት አመታት በኃላ ከመንደሩ ሰው የሚወረውርብኝን የ"ለምን አታገባም?" ጥያቄ ለመመለስ አገባሁት።
በሰርጋችን ምሽት መጀመሪያ አደራ ያለኝ:-"አሏህ ላንቺ መልካም እንዲያረግልሽ ከሻሽ ለሁሳም መልካም ሁኚ።"ይህ ነበር አደራው።ሁሳም ካለፈ ትዳሩ ያፈራው ልጁ ነው።
ከተጋባን ከአንድ አመት በኃላ ጨረቃ የመሰለ ልጅን አላህ ሰጠኝ።ነገር ግን ልጄ ከልብ ህመም ጋር ነበር አብሮ የተወለደው።በዚህም የተነሳ ለባለቤቴ እሰጠው የነበረውን ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ለህመምተኛው ልጄ መስጠት ጀመርኩ።ይህም በመካከላችን ክፍተትን ፈጥሮ እኔ ወደእናቴ ቤት ሄድኩ።ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ወሊድ በመኪና አደገ ደረሰበት።
አደጋው ከባደ ስለነበር የመትረፍ አድል እንደሌለው ያወቀው ወሊድ በብዙ ነገራት አደራ አለኝ።የመጨረሻው አደራ ግን "አሏህ መልካም እንዲሰራልሽ ከፈለግሽ ለሂሳም በጎ አድርጊ።እሱ አሁን አባቱንም ማጣቱ ነው።" የሚል ነበር።
ይህን ካለ ብዙም ሳይቆይ ወሊድ ጥሎኝ ሄደ።ፍቅሩን በምላስ ብዙ ጊዜ ባይገልፅም እጅግ አዛኝ፣ምግባረሰናይና ርሁሩህ ነበር።
ከዚህ ወዲህ የባሌን አደራ ለመጠበቅ ነብሴን አሳልፌ ሰጠሁ።ቤተሰቦቼ ሁሳምን ለህፃናት ማሳደጊያ አንድሰጥ ቢወተውቱኝም አሻፈረኝ ብዬ እንደልጄ አድርጌ አሳደግኩት።ችግሩን፣ናፍቆቱን ሃሳቡን ሁሉ በጫንቃዬ ተሸክሜ አሳደግኩት።
በሌላ በኩል የኔው ልጅም ከህመሙ ጋር እየተታገለ አስራ አምስት አመታትን ከቆየ ወዲያ እስከ ወዲያኛው አሸለበ።ከሁሳም ውጭ አጫዋችም ሆነ አፅናኝ የሌለኝ ብቸኛ ሆኜ ቀረሁ።
ታዲያ ሁሳምም አድጎ ተመረቀልኝ።በተመረቀልኝም ቀን በሁሉም ፊት ዝቅ ብሎ እግሬን ስሞ ስጦታን አበረከተልኝ።በህይወቱ አንድም ቀን "ጀነቴ" ብሎኝ አንጂ ጠርቶኝ አያውቅም።የኔን መተኛት ሳያረጋግጥ ወደመተኛ ክፍሉም ገብቶ አይተኛም።
ይህ ልጄ ትናንት የራሱን ሆስፒታል ገምብቶ አስመረቀ።በሁሉም ፊትም አንድ ቃል ገባ።በሳምንት ጁሙዓ እለት ሁሉም ሰው በነፃ ህክምና አንዲያገኝ እንደሚያደርግ ቃል ገባ።ይህም ለወንድሙ ሰደቃ እንዲሆን በመሻት እንደሆነም ገለፀ።

ሳራህ አል-ዓቃሪ
Umer Yasin Yusuf 🙏
@nidatube @ndatubebot
ሰበር ዜና
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ራሳቸውን ከምርጫ አገለሉ።

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በፌቡክ ገፁ

ለጅማ ከተማ ነዋሪዎች

ዘንድሮ በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጅማ ከተማ እንድወክላችሁ ሽማግሌ ከመላክ አንስቶ በተለያዩ መንገዶች እጩ እንድሆን በመጠየቅና ለእጩነት የሚጠበቀውን ፊርማ በራሳችሁ ተነሳሽነት በመፈረምና በማስፈረም የምርጫ ቅስቀሳ እንድጀምር፣ ለቅስቀሳውም «የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመወጣት ከጎንህ ነን» በማለት ላሳደራችሁብኝ እምነትና አክብሮት ከልብ እያመሰገንኩ፤ በግል እጩነት ተመዘግቤ በነበረው በምርጫው በራሴ የግል ምክንያት
ልቀጥል አለመቻሌን ላላሳወቅኳችሁ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ሳሳውቃችሁ ከታላቅ አክብሮት እና ይቅርታ ጋር ነው።
@nidatube @nidarubebot
በዚህ መርጫ ቢያንስ ፓርላማ ውስጥ ለኛ ድምፅ መሆን የሚችል ጥቂት ተወካይ ካገኘን ትልቅ ድል ነው።
ሰለዚህ በድምፃችን እንጠቀምበት
@nidatube @nidatubebot
አስቸኳይ መረጃ !

"ምርጫው እስከ ምሽቱ 3:00 ሰአት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ይቀጥላል ።"
ስብራቶች ሁሉ የነገር መጨረሻዎች አይደሉም፤ እንዲያውም አንዳንድ ስብራቶች የመልካም ጅማሬ ብስራቶች ይሆናሉና ተስፋ አትቁረጥ!
©abu kudama

@nidatube @nidatubebot
🐺 ቀበሮው ዶሮውን «የአባትህ ድምፅ በጣም ደስ ይለኝ ነበር» አለው።
🐓 ዶሮውም « ታዲያ የኔም ድምፅ እኮ እንደ አባቴ ነው» በማለት መለሰ።
🐺 ቀበሮውም «እንደዛ ከሆነ እባክህ ልታሰማኝ ትችላለህ ??» በማለት ተማጸነው።
🐓 ዶሮው «ምን ችግር አለው !» በማለት ጩኸቱን ለማሰማት ዓይኑን ሲጨፍን ቀበሮው ይዞት ተፈተለከ።

ውሾች ሁሉ ዶሮውን ከቀበሮው አፍ ለማስጣል እየጮኹ እግር በእግር ተከታተሉት።

🐓 ዶሮው ለቀበሮው «ከውሾቹ ለመዳን ከፈለግክ ዶሮው የእናንተ ሰፈር አይደለም !!» በላቸው አለው። ቀበሮውም የተባለውን ለመናገር ሲሞክር ዶሮው ከአፉ አመለጠው።
🐺 ቀበሮውም በፀፀት ተውጦ «ዝም ማለት ሲገባው የተናገረ አፉ ይረገም ፤ ይኮነን» አለ።
🐓 ዶሮም በበኩሉ «መንቃት ሲገባው የተጨፈነ አይን ይረገም፤ ይኮነን» አለ።

( ط أ /Aumar Alaa)

® Awwal Hamza Hamza

@nidatube @nidatubebot
የኡዱሒያ ቅድመ መስፈርቶች የትኞቹ ናቸው?

ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል‐ዑስይሚን አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ብለዋል:‐

1⃣ የሚታረደው እንስሳ "በሂመት አል‐አንዓም" በመባል ከሚታወቁት ግመል፣ ላም ወይም በሬ እና በግ አልያም ፍየል መሆን አለበት።

2⃣ በሸሪዓ የተገደበለት የእድሜ ወሰን ላይ የደረሰ መሆን አለበት። ማለትም:‐

📌 በግ ከሆነ፥ ስድስት ወር የሞላው መሆን አለበት።

📌 ፍየል ከሆነ፥ አንድ አመት የሞላው መሆን አለበት።

📌 ላም ወይም በሬ ከሆነ፥ ሁለት አመት የሞላው መሆን አለበት።

📌 ግመል ከሆነ፥ አምስት አመት የሞላው መሆን አለበት።

3⃣ የሚታረደው እንስሳ በሸሪዓ የኡዱሒያን ብቁነት ለማረጋገጥ ከተጠቀሱት ጉድለቶች እና እንከኖች ነፃ መሆን አለበት። እነሱም:‐

📌 ግልፅ ከሆነ ሸውራራነት ነፃ መሆን አለበት።

📌 በግልፅ ከሚታወቅ በሽታ ነፃ መሆን አለበት።

📌 በጉልህ ከሚታይ አንካሳነት ነፃ መሆን አለበት።

📌 በከፍተኛ ሁኔታ ከመክሳት እና ከመድከሙ የተነሳ መቅኒ የሌለው ከመሆን ነፃ መሆን አለበት።

🔖የኡድሒያን ቆዳ መሸጥ ይቻላልን?

ኡድሒያ የሚታረደው ወደ አላህ ለመቃረብ ነው!
ስጋውን ለሶስት ከፍሎ፥ አንድ ሶስተኛውን ለቤት፣ አንድ ሶስተኛውን በስጦታ መልኩ ለዘመድ፤ለጎረቤትና ለጓደኛ፣ አንድ ሶስተኛውን ሳይበስል ለአቅመ-ደካሞች መስጠቱ የጠበቀ ሱና ነው

የኡድሒያውን ቆዳም ይሁን ሌላ ነገር ሽጦ ገንዘቡን መጠቀም ወይም በገንዘቡ ፋንታ ለሰራተኛ መስጠት አይቻልም!

ቆዳውን ሳይሸጡ ለራስ መጠቀም ወይም ለአቅመ ደካማ በነጻ-ሰደቃ- መስጠት ግን ይቻላል

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

ኡስታዝ ጣሀ አህመድ

@nidatube @nidatubebot
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ግብዣ ወደ ቱርክ ሊጓዙ ነው

ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ቱርክ የሚጓዙት በአገሪቱ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ግብዣ መሆኑን የቱርክ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬትን ጠቅሶ አናዱሉ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ቱርክ ለኢትዮጵያ የትኛውንም አይነት ድጋፍ ታደርጋለች በማለት ወዳጅነታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

ፕሬዝደንቱ ይህን ማለታቸው የተሰማው ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት እንደነበር ተገልጾ ነበር።

ሁለቱ መሪዎች ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም በስልክ በተወያዩበት ወቅት ቱርክ ለኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ ፕሬዝደንት ኤዶጋን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ቱርክ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ካደረጉ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን የጨርቃ ጨርቅ እና የኤሌክትሪክ ማስተላላፊያ ገመዶች ማምረቻዎችን ጨምሮ የቱርክ ኩባንያዎች 2.5 ቢሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ፈሰስ ማድረጋቸውን ከዚህ ቀደም የቱርኩ ዜና ወኪል አናዱሉ ዘግቧል።

ቱርክ በመካከለኛው ምሥራቅ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ ነች።

Bbc

@nidatube @nidatubebot
ስድስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል።
የወንድማችን ሙሐመድ ሳልህ ልጆች ልጆቻችን ናቸው።
ቤተሰቦቹ ቤተሰቦቻችን ናቸው። እርሱን ማጣት ሃዘኑ ከባድ ነው። ከወንድማችን ቤተሰቦች ጎን በመቆም የአላህን ውዴታ እንፈልግ።

በቤተሰቦቹ ፈቃድ የቤተሰብ እድር አባላት በሆኑ ሶስት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000427892232
ይማም አህመድ
ኢስማዒል ይስማው
ሙሐመድ ተስፋዬ

@nidatube
2024/06/09 01:40:05
Back to Top
HTML Embed Code: