Telegram Web Link
Forwarded from ኑ እናመስግን (l๏ɠคฬ)
አብሳሪው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል
http://www.tg-me.com/nu_enamasgin
፣ " ቅዱስ ገብርኤል ይቁምላችሁ ፤ የመልአኩ ጥበቃ አይለያችሁ " አሜን‼️
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
👉 እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!
••••
❤️ እንዲህ አለ #ገብርኤል ለካህኑ #ዘካርያስ :-

👉 " እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ " ሉቃ.1:18
••••
❤️ እንዲህ አለ #ነብዩ_ዳንኤል

👉 " ስለ ህዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል " ት.ዳን.12፡1
••••
❤️ እንዲህ አለ #መዝሙረኛው1ዳዊት:-

" የተመረጠው ሙሴ በመቅሰፍት ጊዜ
በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ " መዝ.105:23
••••
❤️ #ሙሴ ምን ብሎ #ቆመ

👉 " አሁን ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ አለ " ዘፀ.32፡32
••••
❤️ #መጽሐፈ_ኢዮብ ደግሞ የቁሳን መላእክትን መቆም እንዲህ ይገልጽልናል:-

👉 " ከዕለታት አንድ ቀን የአምላክ ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ " መ.ኢዮብ 1:6
••••
👉 ሰይጣን ከሳሽ ለክስ ይመጣልና ቆመ ሲል አልገለጸውም የእግዚአብሔር ልጆች መላእክቱን ግን ለመቆም መጡ ሱል ገለጻቸው።
••••
🌺 ካዲያ #መቆም ምንድን ነው⁉️
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
👉 መቆም በአካለ ስጋ ፊት ለፊት መገተር ማለት ሳይሆን ይልቁንም ቅዱሳን መላእክት ቅዱሳን ሁሉ በምልጃ ብልመና በእግዚአብሔር ፊት መቆማቸውን ያሳየናል።
••••
👉 ይህን ትርጉም አጉልቶ የሚያሳየን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ደግሞ እነሆ •••• ሉቃ.13፡6-9 #የበለሷ+ምሳሌ+ላይ:-
••
1ኛ. የበለሷ ባለቤት አለ
2ኛ. በለሷ አለች
3ኛ. የወይን አትክልት ሰራተኛው አሉ።
••••
👉 የበለሷ ባለቤት ከአንዴም ሶስት ጊዜ ከበለሷ ፍሬ ሽቶ ቢመጣም ምንም ፍሬ ባለማግኘቱ ትቆረጥ ሲል ያ የወይን አትክልት ሰራተኛ ግን እንዲህ ነበር ያለው:-
••••
" ጌታ ሆይ ዙሪያዋን እስክኮተኩትላትና ፋንድያ እስካፈስላት ድረስ በዚህ ዓመት ደሞ ተዋት " በማለት በለሷ እንዳትቆረጥ በመማጸን የቆመላት ያ የወይን ስራተኛ ነበር።
••••
👉 በተጨማሪም " የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቆጣሀቸውን ኢየሩሳሌምና የይሁዳ ከተሞች የማትምራቸው እስከመቼ ነው? አለ " ት.ዘካ.1:12
••••
👉 " የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል " መዝ.33:7
••••
👉 ቅዱሳን መላእክት ለተልእኮ የሚፋጠኑ ስለኛ ምህረት የሚለምኑ ይቅርታን የሚጠይቁ የሚቆሙ የሚጠብቁን ከመከራ የሚታደጉን ናቸው።
••••
🌺 #ሐምሌ_19 በአረማዊው ንጉስ አለ እስክንድሮስ ፈተና የጸናባቸው በኋላም በእሳት እንዲጣሉ ተፈርዶባቸው በእምነታቸው ጽናት ወደ እሳት የተጣሉት ቅድስት ኢየሉጣና ልጃ ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ በሊቀ መልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ከእሳት የዳኑበት የእግዚአብሔር አምላክነት የመልአኩ ጥበቃ የተገለጠበት ልዩ በዓል ነው።
••••
👉👉 #በምርቃት እንደጀመርነው #በምርቃት_እንቋጨው 🙏🙏🙏
••••
📌 የመልአኩ ጥበቃ ምልጃ ረዳትነት ከሁላችን ጋር ይሁን‼️
📌 አገራችንን ሠላም ያድርግልን‼️
📌 ክፉን አርቆ መልካሙን ደዌን አርቆ ጤናውን ጥልን አርቆ ፍቅርን መለያየትን አስወግዶ አንድነትን ቸር አምላክ ያድለን አሜን‼️
••••
ዲ/ን ሩፊኖስ ዘደብረ ኃይል
••••
━━━━⊱✿⊰━━━━
🀄️🀄️ሉን
New photo competition💵💸
ሰላም ወዳጆቼ ጨዋታው (በካርድ) ነው አሸንፍበታለው የምትሉትን ፎቶ በመላክ ያሸንፋ
መስፈርት
መላክ ያለባቹ የምትወዳደሩበትን ፎቶ
ስማቹን እና ምትወዳዳሩ በትን 5ብር
በዚ ይላኩ
@Bisre_man10
@Bisre_man10
ለበለጠ መረጃ 0925878995
https://www.tg-me.com/photo_competition
#ፆመ_ፍልሰታ🙏
✝️ ፍልሰታ ለማርያም ✝️

…… #እንኳን_አደረሳችሁ……
የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን አሜን አሜን መልከም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን ።

join us @nu_enamasgin
ነሐሴ 3/12/2013 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ 1 ተሰሎ 3÷1-ፍ.ም
ንፍቅ ደያቆን፦1 ጴጥ 3፥10-15
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 14÷20-ፍ.ም

ምስባክ ፦ መዝ 44፥12-14
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ ብዑላነምድር
ኩሉ ክብረ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን

ትርጉም ፦
የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻ ይዘው ይሰግዱለታል
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ
ለሐሴቦን ንጉስ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው

ወንጌል ፦ ሉቃ 18÷9-18
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ)
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
ሃሌ-ሉያ አንተ ሰው ሆይ

ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ (4)
ቡሄ መድረሱን ሰምተሃል ወይ
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
መስማቱንማ ሰምቼ ነበር
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
ከዚያ ቢያደርሰኝ ልዑል እግዚአብሔር
ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ

እናቴ ሆይ.......... ሆ
ይህን ባየሻ ........ሆ
በቁርማ ዳቦ .......ሆ
ሲጥለኝ ውሻ........ሆ
ደጓ ጫማዋን ......ሆ
አውልቃዋለች.......ሆ
ውሃ ሲጠማ.........ሆ
አጠጥታዋለች......ሆ
የስዋ ውዳሴ .......ሆ
ሆኖኛል ውይን ......ሆ
ዘሬም ብዘምር ......ሆ
እኖራለሁኝ ...........ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4)

በእምነት እንውጣ .ሆ
ከተራራው ላይ......ሆ
ይታይ ብርሃኑ........ሆ
ክብሩ ኤልሻዳይ....ሆ
ሙሴን እንጠይቅ...ሆ
የጥንቱን ነገር .......ሆ
ምን እንደሚለው ...ሆ
ጌታን ሲያናግር......ሆ
ድምጹን እንስማ ....ሆ
እንደ ትሁትነቱ.......ሆ
እንቀበለው ..........ሳ
እኛም በትሩን .......ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (2)
ተቁኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2)

ተራራውማ ..........ሆ
ነውና አምሳል.......ሆ
ለቤተ ክርስቲያን...ሆ
መንበረ ልዑል........ሆ
ወጥተን እንጠይቅ .....ሆ
ኤልያስን.............ሆ
እንድንዳስሰው.....ሆ
ጸጓራር ክንዱን....ሆ
ሰማይ በትለጉም...ሆ
ባህር ቢከፍል.......ሆ
እሳት ብታወርድ.....ሆ
ጠላትም ቢርድ......ሆ
በሰረገላ ..............ሆ
የተነጠከው...........ሆ
ይህ ሁሉ ክብር .....ሆ
በማን ስልጣን ነው....ሆ
ለሁላችን መልካም ነው በዚህ መኖር(4)

የእመብርሃን .........ሆ
የምዬ ልጅ............ሆ
ተጥሎ ላይቀር .....ሆ
ተረስቶ ደጅ...........ሆ
ሰአሊ ለነ .............ሆ
ባለበት አፉ...........ሆ
የጭንቁን እለት.....ሆ
ተሰብሮ ሰልፉ......ሆ
እንዳባቶቹ ............ሆ
ቅኔን ተቀኘ.............ሆ
ድንግል ስትረዳው....ሆ
አይኑ ስላየ..............ሆ
ተፈስሂ ደብረ ታቦር(2)
ተፈስሂ አርሙኒየም (2)
ባንቺ ላይ ታየ እግዚአብሔር
ተፈስሂ አርሙንየም

ሙሴ ስላለ ............ሆ
መና ያውርዳል........ሆ
ቅዱስ ኤልያስ.........ሆ
ስጋ ያመጣል..........ሆ
ዮሃንስንም............ሆ
ጌታ ይወዳል.........ሆ
መድኃኒታችን........ሆ
ፈውስ ይሆነናል.....ሆ
በዚህ እንድንኖር ...ሆ
ዳሱን ጥለናል .....ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4)

አባቴም ቤት..........ሆ
አለኝ ለከት.............ሆ
እናቴም ቤት ...........ሆሆ
አለኝ ለከት...,..........ሆ
ፍልሰታ ስትሆን.......ሆ
የቆምኩባት............ሆ
በድብረ ታቦር .........ሆ
ያጌጥኩባት...........ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ(2)
ተቀኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2)

አመት አውዳመት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ያባብዬን ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ይግባ በረከት "ድገምና" አመት "ድገምና"
የማምዬ ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ይትረፍረፍ በእውነት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ነሩ በሀይማኖት
ጽኑ በጸሎት
በተዋህዶ ቤት(4)

የሰማይ ሰራዊት "በእምነት" ያድርጋችሁ "አሜን"
አማኑኤል በጸጋ "በእምነት" ያኑራችሁ "አሜን"
ከስጋ ወደሙ "በእምነት"
ያድላችሁ "አሜን"
ዘርን እደ አብርሃም "በእምነት"
ያብዛላችሁ "አሜን"
ይባረክ በእግዚአብሔር በእምነት ዘመናችሁ "አሜን"/2/
እድሜና ጤናውን በእምነት ያድላችሁ "አሜን" (2)

✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
አምላካችን ናና
ዝማሬ ዳዊት
#አምላካችን_ናና

አምላካችን ናና በአምደ ደመና
አማኑኤል ናና ብርሀን ነህ እና/2


ታቦር አርሞንያም ሆ
የታዳለች መካን ሆ
የተገለጠባት ሆ
የመለኮት ብርሀን ሆ

አዝ

አብም መሰከረ ሆ
በደመናሳለ ሆ
የምወደው ልጄ ሆ
ይሄነው እያለ ሆ
እሱን ስሙትብሎ ሆ
ቃልን ተናገረ ሆ

አዝ

ከሞቱት ሙሴ ሆ
ኤሊያስ ከህያዋን ሆ
ቆመው መሰከሩ ሆ
በቀኝ በግራ ሆ
ጴጥሮስ ዮሀንስ ሆ
የቆመላቸው ሆ
ያምላክጌትነቱን ሆ
ገልጦ ያሳያቸው ሆ
የከበሩ ናቸው ሆ
ያዩት አይኖቻቸው ሆ

አዝ
ታቦር አርሞንያም ሆ
የታደለች መካን ሆ
የተገለጠባት ሆ
የመለኮት ብርሀን ሆ

አዝ

እኔም እመኛለው ሆ
የጴጥሮስንምኞት ሆ
አምኖ ለመኖር ሆ
በሰማይህም ቤት ሆ
ደግሞ ለመመገብ ሆ
የቃሉን ወተት ሆ

አመት አውዳመት ድገምና አመት ድገምና
ፀጋበረከት ድገምና አመት ሰቶናል በእውነት ድገምና አመት
በብራኑ ፀዳል ድገምና አመት
ህይወታችን በራ ድገምና አመት
ሁሉም በዘመኑ ድገምና አመት
ታሪክ እየሰራ ድገምና አመት
በቤተክርስቲያን ድገምና አመት
ይኖራል ሲዘከር ድገምና አመት
የጌታችን ስራ ድገምና አመት
በታቦር ተራራ ድገምና አመት
ላመቱ ያድርሰን ድገምና አመት
ሁላችን በደና ድገምና አመት
ሰላም ያገናኘን ድገምና አመት
ጌታችን በጤና ድገምና አመት
አመት አውዳመት ድገምና አመት ✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱✥
ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ
በአቦጊዳ አፌን የፈታውብሽ
በመልእክት መንፈሴ ተደሰተ
በዳዊቱ ብዙ ነው በረከቱ (2)
ተዋህዶ ኧኸ ሀይማኖቴ
የእውቀት ምንጭ ኧኸ መሰረቴ

አለኝ ትዝታ ከዛፉ ስር 2
የኛ የኔታ ዱላ በትር 2

ሀሁ ብዬ ስጮህ ሀ
ድምፄን እያሰማው ሁ
አንዷን ቃል ስገድፋት ሂ
የኔታን አስቆጣው ሃ
ሀ ማለት እግዚህ ነው ሄ
እያሉ ሲቀኙ ህ
የኔታን አንደበት ሆ
ማር ይንጠፍጠፍበት ሆ
አዝ
አቦጊዳ ብዬ መልእክተን ሳልወጣ 2
የኔታ ደከሙ እንቅልፋቸው መጣ 2

ፊደል ገበታዬን ሀ ግዕዝ
ጥያት ከመሬት ሁ ካዕብ
አቧራዬን ማቡነን ሂ ሣልስ
ያዝኩኝ መላፋት ሃ ራብዕ
ሲነቁ የኔታ ሄ ኃምስ
ልምጯን አነሱ ሆ ሳብዕ
ቁጣ ቃል አሰሙ ሀ ግዕዝ
አዝ
ተማሪ እና ውሻ ሁል ጊዜ አይስማሙ 2
እስከ እድሜ ልካቸው አሉ እንደ ተዳሙ 2

አቆፋዳ አንግቦ ሀ
ገመሎውን ለብሶ ሁ
በእንተ ስሟ ሲል ሂ
ድምፁን አለስልሶ ሃ
አንዲት እፍኝ ጥሬ ሄ
የቁራሽ እንጀራ ህ
ውሻ ሲያባርረው ሆ
አይ ያለው መከራ ሆ
አዝ
አለኝ ትዝታ ቅኔ ቤት 2
በእንተ ስሟ ለማርያም ማለት 2

የዜማው መለኪያ ሀ
ጭረት ምልክቱ ሁ
እዝልና ግዕዙ ሂ
ቅናቱ ድፋቱ ሃ
ጣቢዘር ጥሬዘር ሄ
ደግሞም ቅኔ ቤት ህ
አገባብ ሚስጥሩ ሆ
ሰባት ስምንት ቤት ሆ
አዝ
አለኝ ትዝታ ከመቅደሱ 2
ሌሊቱን ሙሉ ማወደሱ 2

መፃሃፍን ዘርግቶ ሀ
ከጉባኤ ውሎ ሁ
መሪ ዜማ አጥንቶ ሂ
ስምአኒ ብሎ ሃ
ተፈስሂ እያልን ሄ
እሱን ስደረድር ህ
ሳዜመው ይነጋል ሆ
ቅኔ ስደረድር ሆ
አዝ
አለኝ ትዝታ ከጎጆዬ 2
ተሰቅላ አቆፋዳዬ 2
ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ
በአቦጊዳ አፌን የፈታውብሽ
በመልእክተ መንፈሴ ተደሰተ
በዳዊቱ ብዙ ነው በረከቱ


✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
ሀሁ ብዬ
<unknown>
✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
ሃሌ ሉያ
ቤተ አብርሃም
✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
​ቡሄ._.በሉ

ቡሄ በሉ /2/ ሆኦ ልጆች ሁሉ ሆ
የኛማ ጌታ ሆኦ የዓለም ፈጣሪ ሆ
የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ
በደብረ ታቦር ሆ የተገለጠው ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ
ልብሱ እንደብርሃን ሆ ያንፀባረቀው ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

ያዕቆብ ዮሐንስሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ
አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ
አባቱም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ
ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ


ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ
ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ
ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ


በተዋህዶ ሆ ወልድ የከበረው ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወልደማርያም ነው ሆ
ቡሄ በሉ ሆ ቡሄ በሉ ሆ
የአዳም ልጆች ሆ ብርሃንን ሆ ተቀበሉ ሆ


አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ከአጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
አክስቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ


የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣው ሆ
ከተከመረው ሆ ከመሶቡ ይውጣ ሆ
ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ሰለመጣ ሆ
የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይምጣ ሆ


ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ ያላችሁ ሆ
ባህላችሁን ሆ ያዙ አጥብቃችሁ ሆ
ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ
ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ


አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ
የቡሄን ትርጉም ሆ ያሳወቁን ሆ
እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን ሆ
ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ


ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ
በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ
ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ


ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነጽ ሆ
በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ
በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችንይድረስ ሆ

ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና


እንዲሁ እንዳላችሁ በምነት አይለያችሁ በምነት
ላመቱ በሰላም በምነት ያድርሳችሁ በምነት
ክርስቶስ በቀኙ በምነት ያቁማችሁ በምነት
የመንግስቱ ወራሽ በምነት ያድርጋችሁ በምነት
እንዲሁ እንዳለን በምነት አይለየን በምነት
ለዓመቱ በሰላም በምነት ያድርሰን በምነት
አማኑኤል በቀኙ በምነት ያቁመን በምነት
የመንግስቱ ወራሽ በምነት ያድርገን በምነት


የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት/2/ ይግባ በረከት/2/
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት /3/


✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
ቡሄ በሉ
<unknown>
✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
ለደብረ ታቦር ፕሮፋይል ለምትፈልጉ

✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚
@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
​​ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው

ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ
ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ/2/
አዝ.........
ተገለጠ------------ሆ
በታቦር ላይ---------ሆ
ብርሐኑን-------------ሆ
ለእኛ ሊያሳይ---------ሆ
የምሥራች--------------ሆ
እልል በሉ---------------ሆ
ለሁሉ አባት-------------ሆ
ለአዳኙ-------------------ሆ
በሥምኽም ደሥ አላቸው
ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/
አዝ...........
ጽልመት ጠፍቶ------------ሆ
ብርሐን ሆነ-----------------ሆ
በክርስቶስ------------------ሆ
ተከወነ----------------------ሆ
ያን ጨለማ------------------ሆ
በአንተ አልፈናል-------------ሆ
አምላክ ክበር-----------------ሆ
ውብ ሆነናል------------------ሆ
በሥምኽም ደሥ አላቸው
ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/
አዝ............
ጴጥሮስ ያዕቆብ----------ሆ
ዮሐንስ----------------------ሆ
ሙሴ ኤልያስ---------------ሆ
ኢየሱስ---------------------ሆ
ተመርጠው ነው------------ሆ
ለሥደት---------------------ሆ
ይኽን ክብር------------------ሆ
ለማየት---------------------ሆ
በሥምኽም ደሥ አላቸው
ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/
አዝ...........
ለእኛ በእዚኽ-------------ሆ
ብንኖር----------------------ሆ
መልካም ነበር-------------ሆ
ያውም ክብር---------------ሆ
ሦስት ዳስ-------------------ሆ
እንስራና---------------------ሆ
በእዚኽ እንኑር---------------ሆ
በምሥጋና-------------------ሆ
በሥምኽም ደሥ አላቸው
ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/
አዝ..........
ተገለጠ------------ሆ
በታቦር ላይ---------ሆ
ብርሐኑን-------------ሆ
ለእኛ ሊያሳይ-------ሆ
የምሥራች------------ሆ
እልል በሉ-------------ሆ
ለሁሉ አባት------------ሆ
ለአዳኙ-------------------ሆ
በሥምኽም ደሥ አላቸው
ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/

ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት
ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት
ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት

✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
Audio
✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
2024/06/11 17:20:49
Back to Top
HTML Embed Code: