Forwarded from ጰላዲዎስ (🤔)
ሰቆቃወ ድንግል
እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች
     ➛ ትዕቢተኛ ዓይን፥
     ➛ ሐሰተኛ ምላስ፥
     ➛ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
     ➛ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
     ➛ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
     ➛ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
     ➛ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

ምሳሌ 6፥16-19
ወደ ቅዳሴ ምዕመናን የምን ተዘርፍቶ ማፍጠጥ ነው 😡
"እየጾማችሁ ነውን?"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

እንግዲያስ መጾማችሁን በተግባር አሳዩኝ፡፡ "እንዴት
አድርገን እናሳይህ?" ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስላችኋለሁ፡- ድኻው እርዳታችሁን ፈልጎ እንደሆነ ቸርነትን አድርጉለት፤ የጠላችሁትን ሰው ካያችሁት ከእርሱ ጋር ፈጥናችሁ ታረቁ፤ ባልጀራችሁ ተሳክቶለት ስታዩት በእርሱ ላይ ቅናት አትያዙ፤ ቆነጃጅትን በመንገድ ሲያልፉ ስታዩ በዝሙት ዓይን አትመኙ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያደረጋችሁ በትክክል መጾማችሁን አሳዩኝ፡፡

በሌላ አገላለጽ አፋችሁ ብቻ ሳይሆን ዐይናችሁ፣ እግራችሁ፣ እጃችሁ፣ በአጠቃላይ የሰውነታችሁ ሕዋሳቶች በሙሉ መጾም አለባቸው፡፡
       + እጆቻችሁ ከመስረቅና የእናንተ ያልሆነውን
          ከመውሰድ ይጹሙ፤
       + እግሮቻችሁ የኃጢአት ሥራን ለመፈፀም
           ከመፋጠን ይጹሙ፤
       + ዐይኖቻችሁ ውጫዊ በሆነ ውበት ምክንያት
          ከመቅበዝበዝ ይጹሙ፡፡

ጥሉላትን (የፍስክ ምግብ) እየበላችሁ አይደለም አይደል? እንግዲያስ በዐይኖቻችሁም ክፉ ነገርን አትብሉ፡፡ የሚታዩ ነገሮች ለዐይን ምግቦች ናቸውና፡፡ ጀሮዎቻችሁም ይጹሙ፡፡ የጀሮ ጾም ሐሰተኛ ወሬንና ሐሜትን አለመስማትና ይህን የመሳሰለ ነው አንደበታችሁም ከከንቱ ንግግር ይጹም፡፡ ዓሣንና ሌሎች ጥሉላትን ከመብላት ተከልክለን ሳለ ነገር ግን ወንድሞቻችንን በሐሜት የምናኝካቸውና የምንበላቸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው?

ወንድሙን የሚያማና የሚነቅፍ ሰው እርሱ የወንድሙን አካል ያቆስላል፤ ሥጋውንም ይበላል፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ይህን አስመልክቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "እርስ በእርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በእርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" /ገላ.5፡15/፡፡ ስታሙ በጥርሳችሁ የወንድማችሁን ሥጋ አትነክሱም፡፡ በክፉ ንግግራችሁ ግን የወንድማችሁን ነፍስ ትነክሳላችሁ፤ ታቆስሉትማላችሁ፡፡ እንዲህ በማድረጋችሁ ራሳችሁን፣ ወንድማችሁንና ሌሎች ብዙ ሰዎችን ትጎዳላችሁ፡፡

አንደበታችሁ ክፉ ነገርን ከመናገር ካልጾመ ጉዳቱ
በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በሐሜታችሁ እናንተን የሚሰማ ወንድማችሁም የሐሜታችሁ ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርጉታላችሁ ማለት ነው፡፡ እርሱም የራሱን ኃጢአት እንዳይመለከት ስላደረጋችሁት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ በዚህም የሌሎች ወንድሞቹን ድካም እየተመለከተ እርሱ ግን በመጾሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል ስለዚህ አንደበታችሁም ክፉ ከመናገር ይጹም፡፡
ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።

ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።

አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።

ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።

የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤
ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!

(ማቴዎስ 6፥14-23)
''እውነተኛ ጿሚ ራሱን ከክፉ ምግባራት የከለከለ፤ ከንቱ የሆኑ ንግግሮችን ከመናገር የተቆጠበ፣ ሐሰትን የማይናገር፣ ሐሜተኛ ያልሆነ፣ በማንም ላይ የማይፈርድ፣ሽንገላን የማይወድና እኒህንም ከመሰሉ ነገሮች ራሱን የተጠበቀ ፣የማይቆጣ፣ የማይበሳጭ ፣ተንኮለኛ ያልሆነ ፣ ቂመኛ ያልሆነና፣ እነዚህን ከመሳሰሉ ክፋቶች ሁሉ የራቀ ሰው ነው፡፡

ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ ከስድብ፣ ከውሸት ፣ከማታለል፣ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡''
#ቅዱስ_ኤፍሬም

እኛስ እውነተኛ ጿሚ መባል ይገባን ይሆን?
ጾም በአንተ ውስጥ የሆነ አንድ ነገር መለወጡን ተመልከት።

ከጾም የምታገኝው ነገር የምግብ ለውጥ መሆኑን ብቻ አትመልከት። ለተሻለ ህይወት የሚደረግ ለውጥ መሆኑን ተመልከት። ይህም ማለት በአንተ ውስጥ ያለ ጉድለትንና በውስጥህ እንዳለ የሚሰማህን ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር የሚሆን ድክመት ተመልከት ማለት ነው። ይህ ሳይሆን ከቀረ በሃምሳ አምስቱ የሁዳዴ ጾም ቀናት ውስጥ ራስህን አሸንፈህ ከቆየህ በኋላ ከእግዚአብሔር  ጋር የፍቅር ዝምድና እና የተረጋጋ ግንኙነት ሳትፈጥር ከጾሙ አስቀድሞ የነበረህን አቋም ሙሉ ለሙሉ ይዘህ ለመውጣት ከሆነ የነፍስህ ጥቅም ምን ሊሆን ነው? አንተ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳታመጣና አስቀድመህ በነበርህበት ሁኔታ ውስጥ እያለህ እስከ አሁን ድረስ ስንት አጽዋማት እንዳለፉህ አስብ!

በሁሉም አጽዋማት ውስጥ ፈቃድህ ደካማ ጎንህን ለማሸነፍ ስኬታማ እንድትሆን አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር እንድትታረቅ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም የእርሱን ፈቃድ ጣፋጭነት እንድትቀምስ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ከእግዚአብሔር። ጋር የሚኖርህ ዝምድና እስከ አሁን ድረስ እንደምን የሰፋና የጠለቀ ይሆን ነበር!

ስለዚህ ንስሃ በመግባት ጾምህን ጀምር። ጾምህን በጸሎት በምጽዋት በስግደት በመንፈሳዊ ንባባት በቅዳሴ በኪዳን ጸሎቶች አጅበው። እነዚህን ሁሉ በማድረግህ ከእግዚአብሔር ጋር ትወዳጃለህ የሁዳዴ ጾም የያዛቸው በረከቶች ብዙ ናቸውና። እኒህን ካደረክ በመጨረሻ ላይ ውጤቱን ከአምላክህ ትቀበላለህ።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!'

መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም 'ለሰው ፊት የማያዳላ' እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም። (ሐዋ 10፥34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡

'የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ' ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው።

(Deacon Abel Kassahun Mekuria)
"እግዚአብሔርን የምትወዱ ክፋትን ጥሉ!"

መዝ. 97÷10
"የቂመኛ ሰው ጸሎት፣ በእሾህ መካከል እንደ ወደቀ ዘር ነው"

#ማር_ይስሐቅ
ለደሴዎች አድርሱልን
#ምጽዋት በአበው አንደበት

"አንተ ልትበላው ያልፈለግኸው እንጀራ የተራቡት ሰዎች እንጀራ ነው። በቁም ሳጥንህ ውስጥ ሰቅለህ የተውከው ልብስ ዕርቃኑን የሆነው ሰው ልብስ ነው። የማታደርጋቸው ጫማዎችህ ባዶ እግሩን የሚሔድ ሰው ጫማዎች ናቸው። የቆለፍክበት ገንዘብ የደሃው ገንዘብ ነው። የማትፈጽማቸው የቸርነት ሥራዎች ሁሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችህ ናቸው።"
#ቅዱስ_ባስልዮስ

"አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምነው ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው ጽዋ ላይ አታገኘውም።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ወንድምህ ዕርቃኑን ወድቆ እያለቀሰ ነው ፣ አንተ ግን የሚያምር የወለል ንጣፍ ለመምረጥ ተቸግረህ ቆመሃል።"
#ቅዱስ_አምብሮስ

"አባት ሆይ ወጪውን ሳናሰላ እንድንመጸውት አስተምረን።"
#ቅዱስ_አግናጥዮስ
#በእንተ_ጸሎት_ሐሙስ
"ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ  ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ዠመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡"  (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

"በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው"
(ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡

ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው።

በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።"

የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን

(Orthodox and Bible fb page)
#የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር

በቤተ ክርስቲያናችን ትዉፊት መሰረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡

ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ፣ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣ እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡ እኛም ከእንደነዚህ ዓይነት አሰናካዮች በመለየት ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረዉ እና ራሳችንን መልዕክቴ ነው፡፡
ለዚህም የእመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡
👉=>ውበትን ደስታ አታድርጉት
የረገፈና የቆሰለ ዕለት ታዝናላችኹ!

👉=>ሐብታችኹን ደስታ አታድርጉት
ሲቀሟችኹ ታዝናላችኹ!

👉=>ዘመድን የደስታ ምንጭ አታድርጉት
ሲታመም ሲሞት ትጎዳላችኹ!

👉=>ባልንጀራን የደስታ ምንጭ አታድርጉት
ሲለያችኹ ሲከዳችኹ ታዝናላችኹ!

👉=>ጉልበታችኹን የደስታ ምንጭ አታድርጉት
ስትታመሙ ስትደክሙ ኹሉም ይቀራል!

የደስታ ምንጭ ክርስቶስ ነው።
      ደስታም ክርስቶስ ነው

ከየኔታ ስብከት የተወሰደ
2024/06/16 13:03:01
Back to Top
HTML Embed Code: