Telegram Web Link
👉ጥያቄ ለእኔ ወንድሞች⁉️

ከሱናው ሰው የሙስሊሞች ድምፅ የሚሆነው ዑስታዝ ኢብኑ ሙነወር ብቻ ነው⁉️

ማነው የሁሉንም ሙስሊም በደልና ግፍ አንድ ሰው ብቻ ይተንፍስ ብሎ እዳ ያሸከመው ⁉️

ሌሎቻችንስ እ‼️

የሱና ወጣቶች ለምንድነው የሚደርሰውን ግፍና መከራ መናገርና ለህዝቡ በቻላችሁት አቅም ድምፅ የማቶኑት...እ...⁉️

👉ከሸሪዓ ባልተጋጨ መልኩ የህዝብን ብሶት ማሰማት ነውር ነውን⁉️

በደሉ እናንተን አይሰማችሁምን⁉️
ነው ወይስ .......⁉️

ይቅርታ ሁሌ ስለሚገርመኝ ነው ወላሒ

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍169
አልቡኮ ወረዳ ነጢ የፋኖ ግፍ

«የአረብ ሀገር ልጆቻችን ሆይ ለምን⁉️
-----------------------------------
በድጋሜ ላልፅፍ ወስኘ ነበረ፡
በህዝቤ መከራ ልቤ ተሰበረ፡
ለቅሶውን ስሰማ ቃሌን አፈረስኩት፡
ድምፅ ልሁን ብዬ ሁሉን ነገር ተውኩት፡


በአልቡኮ ወረዳ ፋኖ በገባባቸው ቀበሌወች እየተሰራ ያለው ግፍና በደል እጂግ የሚዘገንን ለመናገር የሚያሳዝን ግፍ ነው።

ማንኛውም አባወራ በሬ ያለው
በበሬው ግብር ይከፍላል።
ሶላር ያለው በሶላሩ ይከፍላል።
ይህ ፋኖ የሚባል ቡድን የህዝብ ጠላት ነው ስንል የምትቃወሙ ሙስሊሞች ግን ...በምን ቋንቋ እንንገራችሁ።

እነሆ ደቡብ ወሎ በአልቡኮ ወረዳ #ነጢ በሚባል አካባቢ #ፋኖ ማህበረሰቡን እየዘረፈ እያሰቃዬው ነው።

ገበሬዉን በግዳጅ/ አንድ ቁና ስንደ እና
ባቄላ ብሎም ከእያንዳንዱ ማህበረሰብ
1000 ብር አምጡ እያለ ሚስኪን ገበሬ  መሬቱን መዝራቱን ትቶ የልጆቹን ቂጣ #ለፋኖ ታጣቂ ሀይል አስረክቦ ፆሙን እያደረ የቆየ ቢሆንም አማራጭ ስላጣ ችሎ ነበር።

አሁን ላይ ደግሞ በእያንዳንዳችኔ ➌⓪ ሽ ብር አምጡ
ከፋኖ ጎን ሁኑ እያለ አስቸግሯል ሲሉ የአካባቢው ተወላጆች ነግረውኛል::

ይህ እየሆነ ያለው #ነጢ ከምትባል ቦታ ነዉ::
የሚገርመዉ ነገር 
👉አረብ ሀገር ልጁ ያላቸዉን ሰወች ሰብስቦ ደግሞ
አንድ ልጅ ያለዉ ➌❺ሽ  
ሁለት ልጅ ያለዉ ❼⓪ሽ
አምጡ እያለ ፋኖ እየቀማ ይገኛል።

የክፍያ ማጠናቀቂያዉ ጥቅምት ➍ ነው ከዚያ ቀን ካለፈ ያልከፈለ ሰው ደግሞ ❶⓪⓪ ሽ እስከ ➌⓪⓪⓪ ሽ ቅጣት ይቀጣል እየለ ህዝቡን እየረበሸ እያተራመሰ ይገኛል።

መረጃውን ያደረሱኝ ሰወች እንደነገሩኝ ከሆነ




ነገር እየደረሰብን ያለው አረብ ሀገር ያሉት አንዳንድ ልጆች #ከፋኖ_ጎን_እንቆማለን ብለዉ
የጀመሩት የገንዘብ ድጋፍ ነውና እነዚህ ሰወች የህዝባቸውን ነፍስ ቀብድ አሲዘው #መቆመሩን አሏህን ፈርተው ያቆሙ ዘንድ ንገርልን ብለዋል።

 አስከትለውም እናንተ አዋጥታችሁ መሳሪያ ያስታጠቃችሁት ፋኖ ዛሬ የእናንተን ዘላጆች ሲያስፈራራበትና መስጂድ ውስጥ ሲረሽንበት ምን ተሰማችሁ ሲሉም የሀዘን ግርምታቸውን በብሶት አጋርተውኛል።

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍110
በወረኢሉ እና ካቤ መሰል አካባቢ ያላችሁ ሙስሊሞች ጥንቃቄ አድርጉ‼️
አሏህ ይጠብቃችሁ ወገኖቼ
አብሽሩ ሊነጋ ሲል ይጨልማል በየቦታው መከራችን መብዛቱ የድል ብስራት ጂማሮ ሊሆን ይችላል ኢንሻ አሏህ አብሽሩ በአሏህ ተመኩ አሏህም ህዝባችንን ይጠብቅልን አሚን
👍233
ጀግናዬ

ህይወት ቀልድ ብትሆን ኖሮ ብዙ ከልባቸው የሚስቁ ሰዎች ታይ ነበር።
👍63
አልሀምዱ ሊላህ

የታገተው ተርፏል!!
------------------
የአማራ ነፃ አውጭ ሀይል ነኝ የሚለው ፋኖ የሚያግተው አማራን፣
የሚቆጣጠረው አማራን፣
የሚገድለው ሙስሊምን፣
የሚያፈርሰው መስጂድን ግን ደግሞ የአማራ ነፃ አውጭ ታጋይ...ከማን ነው ነፃ የሚያወጣው⁉️

ለማኔኛውም #በመካነ-ሠላም #መስጅደ-ኑር በነበረው #በፋኖ በተደረገ ጭፍጨፋ ወቅት የሸሂድ ወጣት አብዱሶመድ ሙሐመድ የአጎት ልጅ አስከሬን ለማንሳት ወደ መስጅድ ሲመጣ በፋኖ ሃይሎች ታግቶ ተወስዶ ነበር።

ይህን ወደ ሚዲያ ማውጣት የልጁን ህይዎት አደጋ ላይ መጣል ስለነበር ለሚዲያ ፍጆታ አልቀረበም ከአጋቾቹ ጋር በተደረግ ድርድር #በሶስት_መቶ_ሺህ ክፍያ ማስለቀቅ ተችሏል።

የአማራ ነፃ አውጭ ነኝ የሚል አካል አማራ ነኝ የሚልን ሙስሊም ገድሎ የሟችን ቤተሰብ አግቶ 300ሽ ብር የሚቀበል ነፃ አውጭ ቡድን...አይደል⁉️


ለአማራ ህዝብ ነው የምታገለው የሚል ሃይል መልሶ ያንኑ ህዝብ አግቶ ገንዘብ የሚቀበልበት ትግል መቼም ልዩ ትግል መሆን አለበት የምለውክ በምክንያት ነው⁉️

እንጂማ ህሌና ያለው አካል የአጎትን ልጅ ገድሎ የአጎቱን ልጅ አግቶ ብር የሚቀበል "የአማራ ነፃ አውጪ" ትግል እንደት ሊሆን ይችላል⁉️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍147
ለጦለበተል ዒልም
~
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደምን ተጠቀሙባቸው። የምትችሉ በአካል እየተገኛችሁ፣ ካልቻላችሁ የተቀዱ ትምህርቶቻቸውን ብትከታተሉ ትጠቀማላችሁ ኢንሻአላህ።

ዱሩሶቻቸው የሚቀርቡበት የቴሌግራም ቻናል ይሄ ነው :-

ቴሌግራም - https://www.tg-me.com/Sheikhmuhammedzainadam
https://www.tg-me.com/SheikhMuhammedZainAdam


ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም።
👍32
(❽)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎

     👉ክፍል =❽

«ግዙፍ የሆነው ተዓምር ቁርዓን»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍24
ስልጤነት ይለምልም‼️
🎙ኑረዲን አል-ዓረብ
ስልጤነት ይለምልም

ወሎዬው ሲረሸን በእምነቱ ሲገለል፡
አንዳንዱ አስመሳይም በጥቅም ሲደለል፡
ድምፅ ስናሰማ ጠንቶብን መከራ፡
ስልጤ ነው የሚሉን ነጥለው ከአማራ፡


መስጂዱ ተደፍሮ በማንም ወጠጤ፡
በስንቱ ሰካራም መንጋና ሰገጤ፡
መግለጫ ሲሰጡ ሽብሩና ዳምጤ፡
የጥፋት ማርከሻው የአብጤና አናውጤ፡
ስንኖር ሙስሊሞች ስንገደል ስልጤ፡


የእምነት ጠላት ሆኖ ሁሉም ህልሙን ሲያልም፡
በጥላቻ ሰክሮ ሰው ገዳይ ሲሸልም፡
ሙስሊምነት ይፍካ ስልጤነት ይለምልም፡


🎙በኑረዲ አል_ዓረብ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍97
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«እኔ ምንም አልላችሁም ስሙት‼️»

👉ሙስሊሞቹ የዚህ መንጋ ተከታዮች አሏህ ልባችሁን ይመልሰው ሌላ ምን እላለሁ መቼስ‼️

ልብ ያለው ልብ ይበል

የሚገርመው ይህ ሰውዬ ጎጃም ውስጥ የፋኖ ጦር መሪ መሆኑን ስትሰሙ ነው እና የዚህ ሰውየ ጦርና ይህን አቅፎ የያዘው #ፋኖ ለብሔር ነው የሚታገለው ነው ብላችሁ ነው የምታስቡት⁉️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍73
«የሴት ልጅ አይን ማረፊያ»

እሷ ተውሒድ እንጂ አትሻም ቤሳቢስት፡
ታጋሽ የመርህ ሴት ጀግና ነች ኒቃቢስት፡
ከባጢል አፅድቶ ሐቅ የሚሞሽርሽ፡
ንግስት ነሽ ለኔ ዘመን የማይሽርሽ፡

قرة عين المرأة ؛

زوجٌ يملك من القوامة ما يكفي ليحميها من الحرج ، ويُعفيها من همٍّ لم تُكلَّف به ، وينهي عنها الصراعات قبل أن تبدأ..

ከሀፍረት የሚጠብቃት ፣
ከጭንቀት የሚገላገልላት እና ግጭቶችን ከመጀመራቸው በፊት ለማስቆም የሚያስችል በቂ አመራራዊ ጥበብ ያለው ባል ነው...።

أبهى الرجال في عين المرأة :
القوي العادل ، لا الغني ولا الوسيم!

በሴት ዓይን ውስጥ በጣም ቆንጆው ወንድ ጠንካራ እና ፍትሃዊ እንጂ ሀብታም ወይም መልከኛው አይደለም። #እንዳትሳሳት!!

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍84
«ኒቃቢስት»

ንፁህ ወንድምሽ ነኝ አልልም ደክሜ፡
ግን አስብሻለሁ ጥፋቴን አክሜ፡
ስላንች እፅፋለሁ መፃፍ እስኪሳነኝ፡
ጠላትሽ ሲበዛ ጠበቃሽ እኔ ነኝ፡

...አይዞሽ...

አሸርጋጁ በዝቶ ቢሆን አመድ-አፋሽ፡
ለጠላቶች ሴራ ፈፅሞ እንዳይከፋሽ፡
ከቶ እንዳያስፈራሽ የሚያደርጉት ነገር፡
አንች መርህ አለሽ በሁለቱም ሀገር፡

....አይዞሽ...

በጠላቶች ሴራ እንዳትሳቀቂ፡
ለነሱ ዘመቻ ኒቃብ አታውልቂ፡
አንች ልዩ ሴት ነሽ ይህንን እወቂ፡

ያንችን ልብ ለብሶ ኬንያ ቢጓዝም፡
ምንም ቢያጭበረብር ደምሳሽ ፍቅሪዝም፡
በዘመናት ጠላት በተንኮል ተልኮ፡
ምን በደል ቢሰራም በኒቃብሽ ሾልኮ፡
ያንችን ግርማ-ሞገስ አያውቀውምኮ፡

...እና አይዞሽ እሽ....!!

ሔለንና ቅድስት ስምሽን ሊያጠፉት፡
ሙስሊም ነን እያሉ ምንም ቢሰለፉት፡
ምን ዘመቻው በዝቶ በስምሽ ቢነገድ፡
አደራ እንዳትለቂ #የኒቃቡን መንገድ፡
የተጋለጡ ቀን እውነታው ይጠራል
ፍሬና ገለባው ያኔ ይበራል፡
የነሱ ሲጨልም ያንች ግን ይበራል፡

ከባጢል አፅድቶ ሐቅ የሚሞሽርሽ፡
ንግስት ነሽ ለኔ ዘመን የማይሽርሽ፡
እሷ ተውሒድ እንጂ አትሻም ቤሳቢስት፡
ታጋሽ የመርህ ሴት ጀግና ነች ኒቃቢስት፡

«የወንድምነት ክብር በኒቃቢስት እህቶች ይደምቃል»
«ባል የመሆን ሞገስ በኒቃቢስት ሚስት ይፀድቃል።»


.....ኑረዲን አል-ዓረብ....

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍111
ወላጆች፣ ት/ቤቶች ጥንቃቄ አድርጉ
~
ሰው እያገቱ፣ ህፃናት እየሰረቁ ከፍተኛ መጠን ያለው ብር መጠየቅ በጣም የተንሰራፋ ባህል እየሆነ ነው። ሰላም ሲጠፋ፣ ጠንካራና አስተማሪ ቅጣት ሳይኖር ሲቀር የሰው ልጅ እንዲህ አይነት የተደበቀ አመሉን ያወጣል።

ብቻ ልጆቻችንን እንጠብቅ። ለራሳችንም ቢሆን አጉል ሰዓት ላይ ወይም ራቅ ያለ አካባቢ ብቻችንን አንጓዝ። እንዲሁ ሰበብ ለማድረስ ያህል እንጂ አንዳንድ አካባቢ ቤት ሰብረው፣ ተሳፋሪ አስወርደው ነው ሰው እያገቱ ያሉት። የሃገራችን ነገር እጅግ አሳዛኝ ደረጃ ደርሷል። አላህ ሰላማችንን ይመልስልን።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍72
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍68
(➒)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎

     👉ክፍል =➒

«በመጨረሻ ቀን ማመን»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍30
እህታችን نعيمة جمال أم عيناية በብዙ ፈተና ተፈትናለች። በስደት፣ በትዳር መፍረስ፣ በህመም፣ አግኝቶ በማጣት ይሄው አሁን ደግሞ ብዙ የደከመችበት ልጇን በሞት አጣች። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!

ህመሟን እንድትታከም ለችግሯም በተወሰነ ለመደጎም ከጎና እንቁም። ትንሽ ትልቅ ሳንል በቻልነው እናግዛት። ወገን ለዚህ ካልሆነ ለምን ሊሆን ነው? ለነገ ለኣኺራችን ይሆነናል፣ ኢንሻአላህ። አካውንቷ ይሄውና


1000391550728
ነይማ ጀማል
ንግድ ባንክ

ሌሎችን ያነሳሳል ካላችሁ የላካችሁበትን ላኩልኝ። አላህ ከጭንቅ ከመከራ ያውጣችሁ።
ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም።
👍63
ክንፍ ተሰብሮ ብረር እንጂ አይባልም የምትናገሩትን እያስተዋላችሁ።
👍100
➨ሙሀመድ ይባላል....ﷺ

አሏህ ብሎ ያለው ቀና በል አትዘን፡
የሰላም የፍትህ አርማና ማዕዘን፡
ደግነት ብቻ ነው ሙሀመድ ያዘዘን፡

....የኛ ነብይ..ﷺ

ራሱን ለአሏህ ሽቅብ ቀና አድርጎ፡
ከረሒሙ ጌታ እዝነቱን ፈልጎ፡
በሙሽሪኮች በደል እየደረሰበት፡
ስሙ እየጎደፈ ዋሽተው ቀጥፈውበት፡
ፍፁም በሌለበት እየተወቀሰ፡
ጌታዬ ህዝቦቼን ብሎ ያለቀሰ፡

ሙሀመድ ይባላል።

የስልጣኔ አርማ የእድገት የከፍታ፡
ስሙ እማይረሳ ለሰከንድ ለአፍታ፡
እንኳን ላመነበት በመንገዱ ፀንቶ፡
አያውቅም ጠላቱን በክፋት አንስቶ፡

ከመጥፎ ከልክሎ መልካሙን ያሳያል፡
ከማንም ከምንም ሙሀመድ ይለያል፡
መከራው ሲጠና በአሏህ ይወከላል፡
ችግር ሲደራረብ ሀስቢየሏህ ይላል...
መደምደሚያው ነብይ ይባላል...

«እስኪ ሶለዋት እናውርድ⁉️

....✍️በኑረዲን አቡል-ፋሩቅ

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍123
«ተሰውረህ እደግ»

ከሰወች አይን ተሰውረህ እደግ
እድገትህ ስውር ከሆነ ግልፅ የወጣህ ሰዓት ማንም አይቋቋምህም።
ለጠላቶችህ ዱብዳ ሁንባቸው Background ሳታሳውቅ ድንገት የምትጋፈጥ ክስተት ሁን ያኔ ታሪክህ ሙሉ አሸናፊነት ይሆናል።

.....ኑር

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍129
የሰለምቴወችን ፅናት ያየሁበት ፖስት ነው።

«ለካ ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም»

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍210
2025/10/25 01:19:26
Back to Top
HTML Embed Code: