Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«ማነው ግን ተክፊሩ»

የኢስላምን ጠላት #የአይሁዶች ወዳጅ ፡
የክርስቲያን ታማኝ ሙስሊሙን አሳዳጅ፡
የሁሉም ጥመቶች ንፁህ ቃል አቀባይ፡
የሽርክ ሙሒቦች ሐቅን አስተባባይ፡

መጁሳውን ሳይቀር ወደው የተጠጉ፡
ሙስሊሙን ነጥለው በውስጥ የሚወጉ፡
መረጃ ሲሰጡ የሚበረግጉ፡
አህባሽ እንደዚህ ነው በቃ ተረጋጉ፡

እስኪ ተመልከቱ ይህንን ዘመቻ፡
ክፋትና በደል የግ*ድያ ዛቻ፡
ከአህባሽ ነው የወጣው ግፍና ጥላቻ፡

ለነሱ ሀላል ነው ዘወትር ጫት መቃም፡
የተውሒድ ሰወች ግን ኒካሁም አይበቃም!?

ግፍ እየፈረዱ ወጥተው ከመስመሩ፡
ከሀዲያን ጋር ሆነው ሴራ እየቀመሩ፡
እስኪ ይፈተሹ እስኪ ይመርመሩ!?

ማነው እንደነሱ ጥላቻ ያወጀ፡
ማን አለ እንደ አህባሾች ሐቅን የፈረጀ፡
ማነው ሙስሊሞችን ደፍሮ ያከፈረው!?
ማነው ያለ ደሊል ግፍ የተናገረው⁉️
👍68
የዛ ሰፈር ሰወች
እስኪ የእውነት ሙስሊሙን የምትወዱ ከሆነና እንደምትሉት ለሙስሊሞች ፍቅር ክብር ካላችሁ አክሱም ላይ ሒጃብ ተከልክሏል፣
መስጅድም የለም፣
ይባስ ብለው #አክሱምን ለቃችሁ ውጡ እየተባሉ እየተሳደዱና እየታደኑ ነው።

… እስኪ የምትሉት እውነት ከሆነ ይህን ነገር ተማክራችሁ ተወያይታችሁ ፍቀዱና ውደታችሁን በተግባር አሳዩን እኛም እንመናችሁ..እ⁉️

ነው ወይንስ የአክሱም ሙስሊሞችም «#ውሃብያ» ተብለው ተፈርጀዋል⁉️

ሁሉም ሙስሊም ይህንን ነገር ባገኘበት ቦታ ሊጠይቃቸው ይገባል
👍74
"ወሃBያ ተከትሎ መስገድ አይቻልም፣ ያረ ^ዱት ስጋ አይብበላም፣ ኒካሕ የላቸውም"

#ማነው_ተKፊሩ?
#ክፍል_2
~
ሰሞኑን ኢኽዋንና አሕ ^ ባሽ በሰለፊያ ደዕዋ ላይ የጋራ ዘመቻ እንደከፈቱ እያየን ነው። በቀዳሚነት እያራገቡት ያለው ነጥብ ተKፊሪዮች ናቸው የሚል ነው። ሙስሊሞችን በጅምላ ከኢስላም በማውጣት ላይ የተሰማራው ማን እንደሆነ በተከታታይ በማስረጃ አቀርባለሁ። ክፍል አንድን አሳልፌያለሁ።

በዚህኛው ክፍል ያቀረብኩት መረጃ የአሕ ^ ባሹን ዑመር ይማምን ንግግር ነው። በቅድሚያ አንድ ነጥብ ላስቀድም። አላህ ከፍጡራን በላይ ነው የሚለው እምነት በቁርኣንም፣ በሐዲሥም የተረጋገጠ የሰለፎች ኢጅማዕ ያለበት ጉዳይ ነው። በዚህ ላይ ተደጋጋሚ መረጃዎችን ያቀረብኩ ቢሆንም ለቅምሻ ያክል ብቻ ጠቆም ላድርግ፦

1. ታላቁ ዓሊም ዐብዱላህ ብኑል ሙባረክ (181 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-

فَإِنَّ أَهْلَ الْإِثْبَاتِ مِنْ أَهْلِ السُّنَّةِ يُجْمِعُونَ ... وَأَنَّ اللَّهَ عَلَى عَرْشِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ

“የአላህን መገለጫዎች የሚያፀድቁት የሱና ሰዎች … አላህ ከፍጡሩ ተለይቶ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ኢጅማዕ አድርገዋል።” [አልኢባና፣ ኢብኑ በጧህ፡ ቁ. 694]

2. አቡ ዙርዐ አራዚይ (264 ሂ.) እና ሓቲም አራዚይ (277 ሂ.) የአህሉ ሱናን ዐቂዳ ሲተነትኑ እንዲህ ብለዋል፡-

أَدْرَكْنَا الْعُلَمَاءَ فِي جَمِيعِ الْأَمْصَارِ حِجَازًا وَعِرَاقًا وَشَامًا وَيَمَنًا فَكَانَ مِنْ مَذْهَبِهِمُ: … وَأَنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ عَلَى عَرْشِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ كَمَا وَصَفَ نَفْسَهُ فِي كِتَابِهِ , وَعَلَى لِسَانِ رَسُولِهِ ﷺ بِلَا كَيْفٍ

“በሁሉም ሃገራት - በሒጃዝ፣ በዒራቅ፣ በሻም፣ በየመን፣… ያሉ ዑለማዎችን አግኝተናል። ከመዝሀባቸው ውስጥ … አላህ - ዐዘ ወጀል - እራሱን በቁርኣኑ፣ እንዲሁም በመልእክተኛው ﷺ አንደበት እንደተገለፀው - ያለ እንዴት - ከፍጡሩ ተለይቶ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ማመን ነው። [ላለካኢ፡ ቁ. 321]

3. ታላቁ ኢማም ኢብኑ ቁተይባህ (276 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-

وَالْأُمَمُ كُلُّهَا - عَرَبِيُّهَا وَعَجَمِيُّهَا - تَقُولُ: إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى فِي السَّمَاءِ مَا تُرِكَتْ عَلَى فِطَرِهَا وَلَمْ تُنْقَلْ عَنْ ذَلِكَ بِالتَّعْلِيمِ

“ህዝቦች በሙሉ ዐረቡም ሌላውም አላህ በሰማይ ነው ይላሉ። በተፈጥሯቸው ላይ እስከተተውና ከዚህ ላይ በስብከት እስካልተወሰዱ ድረስ።” [ተእዊሉ ሙኽተሊፊል ሐዲሥ፡ 395]


በዚህ ላይ ያሉ የሰለፎች ንግግሮች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ድምፁን ያያያዝኩት ዑመር ይማም የተባለው አሕ ^ባሽስ ምን ይላል?

አላህን ከፍጡራን በላይ ከዐርሹ በላይ ነው የሚሉ ሙስሊሞችን በሙሉ ከኢስላም ያስወጣል። ሙስሊሞች አይደሉም፣ እነሱን በሶላት ተከትሎ መስገድ አይቻልም፣ ያረ ^ዱት ስጋ አይብበላም፣ ኒካሕም የላቸውም ይላል። ይሄ የሱ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው የአሕ ^ባሽ ቡድን አቋም ነው። ዛሬ ያሉ ሙስሊሞችን ከተራው ህዝብ አልፈው እስከ ዑለማእ ከእስልምና ያስወጣሉ። ለሐጅ እና ለዑምራ ወደ ሳዑዲ ሲሄዱ ኢማሞቹ ሙስሊሞች አይደሉም በሚል አብረው አይሰግዱም።

እንደ ዑመር ይማም ሃይማኖት አላህ ከዐርሹ በላይ ነው በማለት ከሶሐቦች ጀምሮ ያለፉ የጥንት ሰለፎች በሙሉ ሙስሊሞች አይደሉም ማለት ነው። እንግዲህ ተመልከቱ! ከዚህ በላይ ተKፊነት ኖሮ አይናቸውን በጨው አጥበው ሌሎችን በተK ፊርነት እየከሰሱ ነው። በሺርክ እየጨፈሩ ሌሎችን ከኢስላም ሲያስወጡ ማየት ስላቅ ነው መቼም። እኮ ማነው ተKፊሩ ?

በደንብ "ሼር" እያደረጋችሁ ባረከላሁ ፊኩም።

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍41
👉ማነው ተክፊሩ⁉️
🎙በኑረዲን አል-አረብ
👉ማነው ተክፊሩ⁉️

ፀሀፊ👉 ዑስታዝ ኢብኑ ሙነወር
አቅራቢ 👉ኑረዲን አል-ዓረቢ

ሸር በማድረግ አሰራጩት
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍53
ቻናሏን ብናሳድጋትስ...እ.
..አትጠቅመንም ይመስላችኋል..⁉️

የሱና ቤት አይጠብምና ሌሎችን እየጋበዝን ተሸጋሽገን ጠጋጠጋ ብለን ተቃቅፈን እንደግ....እ

ብናሳድጋት ለብዙ ነገር ትጠቅመን እንደሆነ ብዬ ነው «መቸም የሚዲያ ተፅኖ ይገባችኋል..ጮሌ ናችሁ...እና...

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍162
عاجل..
ትክክለኛ ሰው ከትክክለኛ ቦታ ላይ

አሏሁ አክበር
አሏሁ አክበር
‏أمر ملكي:

‏بناءً على ما عرضه ولي العهد.

‏يُعين فضيلة الشيخ الدكتور صالح بن فوزان بن عبدالله الفوزان مفتيًا عامًا للمملكة العربية السعودية ورئيسًا لهيئة كبار العلماء ورئيسًا عامًا للرئاسة العامة للبحوث العلمية والإفتاء بمرتبة الوزير

‏ ታዋቂው ሸይኽ ዶ / ር ሳሊህ ቢን ፋውዛን ቢን አብዱላህ አል ፋውዛን ሀፊዞሁሏህ

የሳውዲ አረቢያ ግዛት ታላቅ ሙፍቲ ፣ የከፍተኛ ምሁራን ምክር ቤት ሊቀመንበር እና የጄኔራል የሳይንሳዊ ምርምር ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

አሏህ እድሜያቸውን ያርዝምልን አሚን

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍180
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉ለምን ፈራን...⁉️

የሙፍቲን መቃብር ለምን እንደፈራን፡
ከዚህ ዘግናኝ ድርጊት ቀድመን እንደጠራን፡

.....ለምን እንደሆነ አስተውላችኋል...!?
....የሽርክ ክብደቱ በርግጥ ገብቷችኋል..!?

የሽርክን አደጋ ግፉን ስለቀራን፡
የምናየው ነገር በጣም ነው ያስፈራን?!

ኮልፌ ገብተው ለፈድሉ ምንጣፍ አንጥፈውና ጫት ይዘው ከገቡ፤ ለሐጂ ዑመር ደግሞ ቀብራቸውን ለብቻ ሲያገኙት ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መገመት ቀላል ነው። ወሏሁ-ል-ሙስተዓን!
👍83
👉አይዟችሁ አሏህ ከኛ ጋር ነው።

አብሽር የሱናው ሰው
------------------

አህባሽ ምንም ቢጮህ
ኢኽዋን ምን ቢንጫጫ፡
ሱፍይ ምን ቢፎክር
ምን ቢሰጥ መግለጫ፡
ተብሊግ ምን ቢዞረን፤
ቢቀርብም ለምርጫ፡
ቀላል ስለማይሆን፤
መረጃ እንደ በርጫ፡

የሐቅ ሰወችን አይችሉም መጋፈጥ፡
ካልሆነ በስተቀር ወድቆ ለመፈጥፈጥ፡
የሱና ሰው ጉዞው ደምቋል በመረጃ፡
የተድበሰበሰ የለም መጋረጃ፡
አህባሽ ግን በጫት ነው የሚያወጣው ሀጃ!

ሐጃው እንድወጣ የጫት ቀርጥ ይቅማል፡
መቃብር ያመልካል ሽርክን ይፈፅማል፡
በየደረሰበት ቢዲዓን ይለቅማል፡
እንደዚህም ሆኖ ይሰግዳል ይፆማል⁉️
አስተውሎ ላየው እጂጉን ይገርማል‼️

የሱና ሰወች ግን ቁርዓን ነው ዳኛቸው፡
የነብዩ ፈለግ ሐዲስ ነው መሪያቸው፡
የሶሀባ አረዳድ ይህ ነው ቀኖናቸው፡
ለሌላው ቲወሪ ጉዳይም የላቸው፡

.....ታዲያ...

በጌታ ቃል ኪዳን ፍፁም የታዘዘ፡
በአዳዲስ ፈጠራ ሐቁን ያልበረዘ፡
ማን ያሸንፈዋል አሏህን የያዘ ?⁉️

አትፍራ ሴራውን ማንም ይጠንስሰው፡
አንተ ሐቅን ስበክ ቢዲዓን አፍርሰው፡
አሏህ ከኛ ጋር ነው አብሽር የሱና ሰው፡

አሏሁ አክበር

«ከወንጀላችንም ቢሆን ሰለፍይ ያደረገን ጌታ ምስጋና ይገባው ወላሒ...እህህህህ ረፍቱኮ»

.....በኑረዲን አል-ዓረብ



http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍109
Forwarded from Fuad Mohammed
أعز الله السعودية بلاد يعز فيها أهل السنة ويذل فيها أهل البدع وأبقاها ذخرا للإسلام والمسلمين
👍27
(❷)نواقض الإسلام
🎙አቡ-ፋሩቅ حفظه الله
ነዋቂዱል-ኢስላም

ክፍል =❷

👉ከአሏህ ውጭ አምልኮ እና አማላጆችን መጣራት ያለው መዘዝ

🎙በአቡ-ፋሩቅ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍21
(➌)نواقض الإسلام
🎙አቡ-ፋሩቅ حفظه الله
ነዋቂዱል-ኢስላም

ክፍል =➌

➥ሙሽሪክን የማያከፍር
➥በኩፍራቸው የሚጠረጥር
➥እምነታቸው ትክክል ነው የሚል#ካፊር ነው።


👉ከሰሞኑ የአህባሽ አቋም ምን ተረዳን⁉️

🎙በአቡ-ፋሩቅ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍22
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአማላጅ ሰበብ ሙታኖችን መጣራት
~
"የሁዳውንም፣ ነሷራውንም፣ መጁሳውንም እንቀበላለን" ብሏል ዑመር ይማም። ከሰሞኑም እርስ በርስ ሲሞጋገሱ፣ በጋራ "ወሃ ^ ብያ " በሚሉት ላይ ሲዘምቱ ነበር። የእውነትም ቀላል የማይባል የጋራ እምነት አላቸው። ለምሳሌ ያክል ሁለቱም ደጋጎች ወይም ፃድቃኖች የሚሏቸውን በመማፀን፣ በመጣራት ላይ ይመሳሰላሉ። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ሲፋጠጡ የነበሩት አጋሪዎችም የማሻረካቸው ሰበብ ይሄው ነበር። አላህ እንዲህ ይላል :-

{ وَیَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا یَضُرُّهُمۡ وَلَا یَنفَعُهُمۡ وَیَقُولُونَ هَـٰۤؤُلَاۤءِ شُفَعَـٰۤؤُنَا عِندَ ٱللَّهِۚ قُلۡ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا یَعۡلَمُ فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَلَا فِی ٱلۡأَرۡضِۚ سُبۡحَـٰنَهُۥ وَتَعَـٰلَىٰ عَمَّا یُشۡرِكُونَ }

"ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ 'እነዚህም አላህ ዘንድ #አማላጆቻችን ናቸው' ይላሉ፡፡ 'አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን' በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም።" [ዩኑስ፡ 18]

{ وَٱلَّذِینَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦۤ أَوۡلِیَاۤءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِیُقَرِّبُونَاۤ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰۤ }
"እነዚያም ከእርሱ ሌላ ረዳቶች የያዙት 'ወደ አላህ ማቃረብን #እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም' (ይላሉ)።" [አዝዙመር፡ 3]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍61
«መስሏችሁ እንጂ አይወዳችሁም»

....ተመልከቱ...‼️

ሱፍዩን በአጭር ጊዜ አጋር አድርገን ውሀብያ ላይ እንደ አርጩሜ ከተጠቀምንበት በኋላ ተፍተን እንረግጠዋለን።


http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍50
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉ከእነዚህ ጋር አማኝ ይወዳጃልን⁉️

...አሏህ ያሳያችሁና ተመልከቱ...‼️

ሐቂቃ እነዚህ ሰወች ለማንስ ይጠቅማሉ ብላችሁ ታስባላችሁን አይሳካላቸውም እንጂ ቢሳካላቸው ከሙስሊም የፀዳች ሀገር ነው የሚፈልጉት #ፀባቸው ከሁሉም ሙስሊም ነው ግን #ለጥቃት እንድመቻቸው አንዱን ወዳጅ አድርገው አንዱን ያጠቃሉ ከዛ ተራው ይደርስሀል።

➥በዚህ ልክ #ኢስላምን የሚጠሉ ሰወች #ሸሁን ተገን አድርገው ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ምንድን ነው⁉️

👉አህባሽን ይዘው ማጥቃት የፈለጉት ማንን ነው⁉️

ይህንን ነው እንግዲህ አጋርና ወዳጃቸው አድርገው አሕባሾችና መሰሎቻቸው ህብረት ይዘው የሚያሸረግዱት ተመልከቱ‼️

ልጁ ግን ህግ ካለ በአስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ አለበት


http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍86
አህባሽ +ሱፍያ+ኢኽዋን

«የሰለፍያን ስም»
---------------------------
በነገራችን ላይ፤
አህባሽና ዒኽዋን ለሱና አያስቡም፡
በስሜት ካልሆነ፤
በቁርዓን በሀዲስ አይሰበሰቡም፡
ፖለቲካን እንጂ፤
በመረጃ ጠቅሰው ፍፁም ዲን አይክቡም፡
ከፊርቀቱ-ናጂያ፤
ከሀቀኞች ተርታም በፍፁም አይገቡም፡

ኢኽዋን በስልጣን ሱስ የተተበተበ፡
አህባሽ በሽርክ አለም አፍርቶ ያበበ፡
ሱፍያ በጥመት ካባ የደረበ፡
ተብሊግ በጂልነት ኖቬል ተሸላሚ፡
ሁሉም የጥመትን ኮተት ተሸካሚ፡
በተራ አሉባልታ ንፁህ ህዝብ አጥማሚ፡
ቃላት በመሰንጠቅ፤
ሀቅን በመቃረን እውቅና ለቃሚ፡
ይህ ነው ፀባያቸው፤
ደግሞም ይጠበቃል ሁሌም ከጫት ቃሚ!!

ታዲያ ከዚህ ሁሉ ማን በማን ይስቃል!?
ማን ሀቀኛ ሆና ማን ከማን ይልቃል፡
ማን ጤነኛ ሆኖ ማንስ ሊያክማቸው!?
አንድ ነን ማለት ነው ብቸኛው ግባቸው፡
ግንኮ በእውነቱ ብዙ አይነቶች ናቸው!!

ከማታሸንፉት ጦርነት ገጥማችሁ፡
ከጋዜጠኝነት ድንገት ተነስታችሁ፡
ከሱፍይ ከአህባሽ ጋር በጀርባ መክራችሁ፡
ምነዋ የመንሀጅ ስም ታጠፋላችሁ!?

እርግጥ ነው መረጃ ከናንተ አንጠይቅም፡
ሽርክ የፈፀመ ደፍሮ ጫት መሚቅም፡
እንኳን ለእምነቱ ለራሱም አያውቅም፡
ስለ እምነት ለማሰብ አቅል ያስፈልጋል፡
በእናንተ ምርቃና ሲጨልም ይነጋል፡
በተቃራኒው ነው እናንተ ጋ ደግሞ፡
ለሌሎች ሲነጋ ይመሻል ፈፅሞ፡

ታዲያ በዚህ መልኩ አዕምሮው የዛገ፡
በቲክቶክ ላይ ቀርቦ ማበድ ከፈለገ፡
ስላለመደብን ካበደው ጋር ማበድ፡
ስለማናውቅበት መቅለልም መካበድ፡
እዛው ካንፓችሁ ላይ ጥመትን ስትሰብኩ፡
ባለቤት ስላለው #መንሐጄን አትንኩ፡

....እኛ....

ከቢዲዓ ኮተት ከውሻሸት ካዝና፡
ከአሻዒራ ፊክራ ከኢኽዋን ቀኖና፡
ምን እንጠይቃለን ምን ይገኛልና!?

የተውሒድ የሱና ሳይወስዱ ክትባት፡
በዚህች ንፁህ መንሀጅ ነጋደ በዝቶባት፡
ስንቶቹ ሞከሩ ክብሯን ለማዛባት፡

ከራሱ ላይ ደፍቶ የትዕቢትን ክምር፡
አንድት ሪሳላ አቂዳ ሳይጀምር፡
ወደ ገጠር ወጥቶ ተውሒድ ሳያስተምር፡
አንድም ቀን ሳያደርግ እውቀት ላይ ምርምር፡

አላህ የትም ቦታ ይገኛል እያለ፡
ጫት እያላመጠ ህዝብ እያታለለ፡
በሽርክ የሚጫወት ስንት ደዩስ አለ፡
የመቃብር አፈር ደፍሮ የሚበላ፡
ኢስላም አሰዳቢ የመረጃ አተላ፡
የአሏህን ንግግር የሚቀይር ደፍሮ፡
ሱፍያና ኢኽዋን አሹቅና ንፍሮ፡

በቲክቶክ አዳራሽ ብቅ ብሎ ድንገት፡
አሊም ነኝ ይለናል የቢዲዓው ዳገት፡
ቁርዓን ሀዲሱ ገብቶት ሳይረዳ፡
በየሚዲያው ላይ ነገር እየነዳ፡
ለቀብር አምላኪው ውሸት እየቀዳ፡
ሀቅን እየወጋ ባጢል እየረዳ፡
የሚፈፅመው ግፍ ጥመቱ ሳይፀዳ፡
ጭራሽ ደፋር ሆኖ ሊያደርገን ባለ-እዳ፡
በሽርክ የጨቀየ እጁን ሲከነዳ፡
መዳኺላ እያለ በአፉ ሲፀዳዳ፡
ግድ ነው መናገር ይህን ቆረቆንዳ፡

ከፖለቲከኞች👉ተሞክሮ ወስዶ፡
እየጠመዘዘ👉 ቃላትን ሸምድዶ፡
የምላስ ላይ አሊም👉 ጭንቅላተ-ባዶ፡
የዋርካ ላይ እሾህ👉 የድንጋይ ላይ ሰርዶ፡
ያው እያመሰን ነው👉ሒዝብያ ስር ሰዶ፡
እስከሚተነፍስ ሀቅ እውነት ተፈርዶ፡

በየሚዲያው ላይ ፊትና ከማራገብ፡
ነገር እንደ ቆሎ ሁሌ ከማንገርገብ፡
ተውሒድን መስበክ ነው እያ'ሰሩ ወገብ፡

ህዝብ ላይ ለመጫን የመውሊድን ኮተት፡
ስንቱ ተጋጋጠ ከስንቱ አየን ስህተት፡
ከሸህ-ሱራ አንስቶ እስከ ገታው ዜና፡
በደገር በሾንኬ በከረም በዳና፡
ሸይጧንን በሚያስንቅ ስንቱን ጉድ አሰሙን፡
ታጥቀው ተደራጅተው ተውሒድን ሊቀሙን፡

ፊት ለፊት ግንባር ላይ ውሸት ከመቀንደብ፡
ስሜት እየነዳን ሁሌ ከመደደብ፡
ከሀቁ ጎዳና ሰውን ከመገደብ፡
ዝም ብሎ መኖር ይሻል ነበር አደብ፡

አውቃለሁ ኢኽዋኖች ስልጣን ከታያችሁ፡
ነሷራ ይወዳል ቀጣፊው ልባችሁ፡
አይሁድ ይታቀፋል አለ ታሪካችሁ፡
ሽዓ ነው ዛሬም ላይ ዋናው አለቃችሁ፡
....ግን ቢሆንም...ደግሞ..
የነቃሁኝ መስሎህ ፈጥነህ እንዳትከስም፡
ከዱንያ ላይ ዝና የአሏህ ፀጋ አይብስም!?
ስሜት እየነዳህ ብ'ትወሰወስም፡
ከአህባሽ ጋር አታንሳት የሰለፍያን ስም፡

«በኑረዲን አል-አረብ»

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍33
በዚህ ግለሰብ የቀረበው) በእስልምና ላይ የተሰነዘረ የጥላቻ ሰበካ፣ I*S*IS*ን (አ*ይ ኤ*ስ ኤ*ስ) እንደ ዋና ማስረጃ ተጠቅሞ፣ አጠቃላይ እስልምናን ለመጥላት ሲሞክር ታይቷል።

ይህ ተንኮል የተሞላበት አካሄድ፣ በሙስሊሞች ዘንድ ያለውን የውስጥ የአመለካከት ልዩነት (የሱናውን አካል ከአህባሽ ጋር በማነፃፀር) ከዓለም አቀፍ የሽ*ብ*ር ቡድን ጋር በማጣመር፣ የጥላቻን ትርክት በ"እውነታ" ሽፋን ለማስተላለፍ የተሞከረ እጅግ አደገኛ እርምጃ ነው።

የግለሰቡ ዋነኛ ዓላማ እስልምናን መጥላት ነው። ይህንን የጥላቻ ስሜት ለማስረዳትና ሕጋዊ ለማድረግ ደግሞ I*S*I*Sን እና ሌሎች የጥፋት ቡድኖችን ይጠቀማል።

➥ተንኮሉንና ሴራውን ልብ ይበሉ‼️

ይህ እኩይ ግለሰብ ወሃቢያ ብሎ የፈረጀውን አካል አቂዳ በከፊል ይጠቅሳል፣ ወዲያውኑ ደግሞ I*S*ISን እንደዚያው አመለካከት ትክክለኛ ተወካይ አድርጎ ያቀርባል።

ይህ ንግግር በስህተት የተፈፀመ አይደለም።
ይልቁንም ተንኮል አዘል ስሌት ነው!
*I*S*ISን ጨምሮ የሃይማኖትን ሽፋን ቢጠቀምም፣ እውነተኛ የእስልምና ተወካይ አይደለም።
እነሱ ሙስሊሞችን ጨምሮ የብዙሃንን ሕይወት የሚነጥቅ የጥፋት ቡድን እንጂ የሙስሊሞችን አቂዳ አይወክልም።

ይህ ግለሰብ በእስልምና ውስጥ ያሉትን የውስጥ አቂዳ እና መንሀጅ ልዩነቶች የመተንተን ዕውቀትም ሆነ መብት የለውም።
ይልቁንም እነዚህን ልዩነቶች ከዓለም አቀፍ ሽ*ብ*ር*ተ*ኝ*ነት (I*S*IS) ጋር በማገናኘት፣ ከውጭ ሆኖ የመከፋፈልንና የጥላቻን አጀንዳ ማስፈፀሙን ያሳያል።
➥ይህ የልጁ እብሪተኛ ንግግር የግል ጥላቻ ሽፋን እንጂ፣ የሃይማኖት እውነት አይደለም።
የኛ የአመለካከት ልዩነቶች የውስጥ ጉዳዮቻችን ናቸው፤ ሁለቱን አጣምሮ ለእስልምና ጥላቻን መግለጽ ግልጽ የሆነ ተንኮልና ተልዕኮ ነውና ሁሉም ሙስሊም በህግ ይጠይቀው ።
👍35
ሙስሊሞች ሆይ እባካችሁ‼️

እናስተውል በአሏህ እንንቃ
የጠላት መጠቀሚያ ከመሆን እንጠንቀቅ መረጃ እንለዋወጥ

➥ትክክለኛ መረጃ የሚሰጡንን ሰወች እንከታተል ‼️

በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የጠላትን ሴራ በማጋለጥ ህዝባችንን እንጠብቅ

የሐቅ ድምፅ እናሰማ
ሚዲያውን ለእምነታችን ለሐቅ እንስራበት

የተደቀነብን ፈተና ከባድ ነው በፅናት እንታገላቸው ይህ አሁን እየሆነ ያለው በግልፅ የነገሩን ሲሆን በልባቸው ያቀዱትና በድብቅ የሚሰሩት ከዚህ የከፋ ነው ።

በመሆኑም እንንቃ
👉አብሽሩ አሏህ ከኛ ጋር ነው።

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍45
«ትላንትም ዛሬም ጀግናዬ ነህ»

         «ሳዳት ከማል»

ያለ ምንም ፍርሀት ያለ ድንበር ማለፍ፡
አልሸማቀቅም አብሬህ ብሰለፍ፡
በደዕዋ መፅናትን ፈፅሞ ለረሳን፡
አስታዋሻችን ነህ የኔ ዘመን ልሳን፡
ብርቱ ፅኑ ቆራጥ የሱና ውብ ድርሳን፡

ስንቱን ተቋቁመህ ዛሬ እዚህ ደርሰሀል፡
አሁንም ሳትሰለች ሐቅ ላይ ቆመሀል፡
አሏህ ይጠብቅህ ክብር ይገባሀል፡

ምንም ቢፈራረቅ ክረምትና በጋ፡
ቢመች ባይመች ቢደቀን አደጋ፡
ሳዳት አቋሙ ላይ ቆሟል እንደረጋ፡

የሒዝብያ መንጋ ሁሌ ሲሽመደመድ፡
አንተ ግን በፅናት ወደፊት ተራመድ፡
ጨብጠሀልና የሱናውን ገመድ፡

በተቻለው አቅም የነብያት ወራሽ፡
ያወቃትን እውነት ሐቋን ለህዝብ አድራሽ፡
ድሽቃ ነው ቃላቱ ሒዝብዮችን አፍራሽ፡

መረጃውን ታጥቆ በሚናገረው ቃል፡
በሳዳት ንግግር ስንት አሳብ ይወድቃል፡
አሏህ አመላክቶት የኢስላምን ዳና፡
ሰበብ ሆኖልናል ለተውሒድ ጎዳና፡

ደግሞ በፊትና ወቅት ስንቱ ሲጉረመረም፡
ስንቱ በሆይሆይታ በጥመት ሲፈረም፡
ሳዳት ጀግኖቹ ጋር አቋም አልቀየረም።


ከትላንት አቋሙ ያልተነቃነቀ፡
ተውሒድና ሱናን ሐቁን የሰነቀ፡
በሐቅ ላይ ፀንቶ ባጢል ያስጨነቀ፡
ስንቱ ስንት ሲለው ደክሞ ያሎደቀ፡
ስሜት ተከትሎ እውነትን ያልናቀ፡

ዛሬም በተውሒድ ላይ ተውቦ እንዳማረ፡
የሚያውቃትን እውነት ፀንቶ ያስተማረ፡
አሉባልታ ወሬ የማያሸንፈው፡
ጥመት ተመልክቶ ፈፅሞ እማያልፈው፡

ሰወች በሌለበት ስሙን ቢያጠፉትም፡
ሱና ነው አላማው ከኋላም ከፊትም፡
ሳዳት በሐቅ ላይ አይዘባበትም።

ስንቱ ጀግና ነኝ ባይ ሲገባ አሰንሰራ፡
በወሬኞች አለም ተግቶ የሚሰራ፡
ጀግናችን ነው እሱ የብርሀን ጮራ፡

አለ እየታገለ በተውሒድ ጂማሬ፡
አንድ ነው አቋሙ ትላንትናም ዛሬ፡
እወቁት ይሔ ነው የኔ መምህሬ፡

በንፁህ ልብ ላይ ተውሒድ የሚዘራ፡
አንገቱን ሳይደፋ ታጥፎ እንደ ከዘራ፡
ሒዝብያ ቢገፋው የማይገፈተር፡
ቀድሞ የታጠቀ የሱና ድሞፍተር፡

ንፁህ የሱና-ዘብ ጀግና ነው ለሚያውቀው፡
ለዛም ነው ጥመትን የሚያስጠነቅቀው፡
እስኪ ሁላችንም እንተዋወቀው‼️
ይህን ውድ ታጋይ አሏህ ይጠብቀው፡

ከተውሒድ መስመር ላይ የሌለበት ክዳት፡
ያምራል በገባው ልክ ሱናን ሲያሰናዳት፡
ንፁህ አብሪ ኮከብ ጀግናዬ ነው ሳዳት።

በቅርበት ለሚያውቀው ፈፅሞ አያስፈራም፡
እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ ለሰከንድ አይኮራም፡
ሰውን ለሐቅ እንጂ ለጥመት አይጠራም፡
እኔ ብሎ ራሱን ጭራሽ አያብራራም፡
ተውሒድ ሱናን እንጂ ተረት አያወራም፡

ግን ሲወነጂሉት እጂጉን ይገርማል፡
ብዙ መሀይማን ሲከሱት ይሰማል፡
ከሚሉት ግን ጠርቷል ዳዒ ሳዳት ከማል፡

     «ትላንትም ዛሬም ጀግናዬ ነህ»

        «በኑረዲን አል አረብ»

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍95
2025/10/23 17:55:29
Back to Top
HTML Embed Code: