የጋዛውና በሰይጣናዊቷ አይሁድ ጦርነት ያየሁት ሁለት ነገ ቢኖር
❶ «የአለም አቀፍ ህግ»የሚባል ነገር እንደሌለ ነው።
ብቻ በጌታህ ተማምነህ የፈረጠመ ሀይል ኖሮህ እስከ ጥግ ጠላትህን ተፋለም...እንጂማ #ሰይጣኗ አይሁድ ያላፈረሰችው የአለም አቀፍ ህግ አለ እንዴ⁉️
➋አሏህ እየጠበቀን እንጂ የያዝነው #ስልክ #ፈንጅ የተቀበረበት እንደሆነ እና የሰሩት ሰወች የሆነ ሰዓት ወይም የሆነ ቀን የደበራቸው ለት በሆነ ሲስተም ተጠቅመው በገዛ ስልካችን እንደሚገድሉን ተገንዝቤያለሁ።
......ጋዛ ላይ ያልፈነዳ ነገር ምን አለ....⁉️
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
❶ «የአለም አቀፍ ህግ»የሚባል ነገር እንደሌለ ነው።
ብቻ በጌታህ ተማምነህ የፈረጠመ ሀይል ኖሮህ እስከ ጥግ ጠላትህን ተፋለም...እንጂማ #ሰይጣኗ አይሁድ ያላፈረሰችው የአለም አቀፍ ህግ አለ እንዴ⁉️
➋አሏህ እየጠበቀን እንጂ የያዝነው #ስልክ #ፈንጅ የተቀበረበት እንደሆነ እና የሰሩት ሰወች የሆነ ሰዓት ወይም የሆነ ቀን የደበራቸው ለት በሆነ ሲስተም ተጠቅመው በገዛ ስልካችን እንደሚገድሉን ተገንዝቤያለሁ።
......ጋዛ ላይ ያልፈነዳ ነገር ምን አለ....⁉️
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍64
እናት ስል ትዝ...የሚለኝ..
«በእንጀራ እናት አድጋችኋል⁉️
ገና በለጋ እድሜ ላይ ያለ አንድ ህፃን #እናቱ ትሞትበትና .....አማራጩ #አባቱ ካገባት የእንጀራ እናት ጋር ህይወትን ለመግፋት ይገደዳል።
......ይህ ታሪክ የኔና የመሰሎቼም ነው።
ከእንጀራ እናቱ ጋር ህይወቱን እየገፋ ያለውን ብላቴና ከእለታት አንድ ቀን አባቱ ይጠይቀዋል⁉️
➥አባት ይጠይቃል👉
በቀድሞዋ እናትህ እና በአሁኗ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው ሲል ይጠይቀዋል⁉️
➥ልጁም በመልሱ👉
እውነተኛዋ እናቴ ትዋሸኛለች አዲሷ ግን እውነተኛ ነች አለው ።
➦አባት ግራ ገባውና እንደት⁉️ሲል ጠየቀ!?
➦ልጅ ሲመልስ‼️
...እውነተኛዋ እናቴ ውጭ ወጥቼ ስጫወትና እንደ ልጅ ስረብሽ «ከረበሽክ ምግብ አልሰጥህም»ትለኛለች .....እኔ ግን እንደምሰጠኝ ብቻ ሳይሆን አልበላም ብዬ ከጠፋኋት ..መንደሩን ዙራ ልጄ ምግብ አልበላም ይርበዋል ብላ እንደምትፈልገኝ ስለማውቅ #ጨዋታየን እቀጥላለሁ።
......አዲሷ እናት ግን #እውነተኛ_ነችና.....
«ከረበሽክ ምግብ አልሰጥህም ካለችኝ እውነትም አትሰጠኝም #ይሔው ዛሬ ሁለተኛ ቀኔ ነው ምግብ ከበላሁ በማለት ነገረው ይባላል።
«ይህ ሚስጥር የሚገባችሁ በእንጀራ እናት ካደጋችሁ ብቻ ነው....አውቃለሁ መልካም የእንጀራ እናቶች አሉ ....አብዛኞቹ ግን ....ልቦና ይስጣችሁ!!
....ኑር....✍️
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
«በእንጀራ እናት አድጋችኋል⁉️
ገና በለጋ እድሜ ላይ ያለ አንድ ህፃን #እናቱ ትሞትበትና .....አማራጩ #አባቱ ካገባት የእንጀራ እናት ጋር ህይወትን ለመግፋት ይገደዳል።
......ይህ ታሪክ የኔና የመሰሎቼም ነው።
ከእንጀራ እናቱ ጋር ህይወቱን እየገፋ ያለውን ብላቴና ከእለታት አንድ ቀን አባቱ ይጠይቀዋል⁉️
➥አባት ይጠይቃል👉
በቀድሞዋ እናትህ እና በአሁኗ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው ሲል ይጠይቀዋል⁉️
➥ልጁም በመልሱ👉
እውነተኛዋ እናቴ ትዋሸኛለች አዲሷ ግን እውነተኛ ነች አለው ።
➦አባት ግራ ገባውና እንደት⁉️ሲል ጠየቀ!?
➦ልጅ ሲመልስ‼️
...እውነተኛዋ እናቴ ውጭ ወጥቼ ስጫወትና እንደ ልጅ ስረብሽ «ከረበሽክ ምግብ አልሰጥህም»ትለኛለች .....እኔ ግን እንደምሰጠኝ ብቻ ሳይሆን አልበላም ብዬ ከጠፋኋት ..መንደሩን ዙራ ልጄ ምግብ አልበላም ይርበዋል ብላ እንደምትፈልገኝ ስለማውቅ #ጨዋታየን እቀጥላለሁ።
......አዲሷ እናት ግን #እውነተኛ_ነችና.....
«ከረበሽክ ምግብ አልሰጥህም ካለችኝ እውነትም አትሰጠኝም #ይሔው ዛሬ ሁለተኛ ቀኔ ነው ምግብ ከበላሁ በማለት ነገረው ይባላል።
«ይህ ሚስጥር የሚገባችሁ በእንጀራ እናት ካደጋችሁ ብቻ ነው....አውቃለሁ መልካም የእንጀራ እናቶች አሉ ....አብዛኞቹ ግን ....ልቦና ይስጣችሁ!!
....ኑር....✍️
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍149
..ልቤ በትዝታ...ዘመተ..
....ልጅነትኮ...‼️
ያኔ ገጠር ነው
ለጋ ገና ጮርቃ ህፃን ሳለን
ስንደባደብ ውለን ማታ እንደ ዶሮ
በጊዜ ገብተን..ራታችንን በእንቅልፍ ሰክረን እየተወዛወዝን...አይናችንን ጨፍነን በልተን..
አትገለጥ ብርድ ይመታሀል ...
ትራስ ካላደረኩ አይወስደኝም...የሚባል ነገር የለም ...እንቅልፍ ከመጣ መንገድ ዳር ይጥልሀል በቃ ከመጣ ትዕዛዝ ተቀብለህ .#ለሽሽሽሽ ብቻ ነው።
እና ያኔ...በዚህች ውብ የእንቅልፍ ክኒን በሆነች #ብርድ_ልብስ ውስጥ «ጭልጥ»ያለ እንቅልፍ እንዳላጣጣምን ...ዛሬ ሁሉም ትዝታ ሆነ.....➥እሽ ልጂነቱስ ይቅር እድሜ ነው።
...እንቅልፉ የት ገባ⁉️
እስኪ የዚህች ብርድ-ልብስ ውለታ ያለባችሁ..ሹክ በሉኝ⁉️
....የኔ ዛሬም ገጠር አለች ዘሯ አልጠፋም...
ወይ ትዝታ ዛሬማ አለቀቀኝም...ስንቱን አስታወስኩት...⁉️
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
....ልጅነትኮ...‼️
ያኔ ገጠር ነው
ለጋ ገና ጮርቃ ህፃን ሳለን
ስንደባደብ ውለን ማታ እንደ ዶሮ
በጊዜ ገብተን..ራታችንን በእንቅልፍ ሰክረን እየተወዛወዝን...አይናችንን ጨፍነን በልተን..
አትገለጥ ብርድ ይመታሀል ...
ትራስ ካላደረኩ አይወስደኝም...የሚባል ነገር የለም ...እንቅልፍ ከመጣ መንገድ ዳር ይጥልሀል በቃ ከመጣ ትዕዛዝ ተቀብለህ .#ለሽሽሽሽ ብቻ ነው።
እና ያኔ...በዚህች ውብ የእንቅልፍ ክኒን በሆነች #ብርድ_ልብስ ውስጥ «ጭልጥ»ያለ እንቅልፍ እንዳላጣጣምን ...ዛሬ ሁሉም ትዝታ ሆነ.....➥እሽ ልጂነቱስ ይቅር እድሜ ነው።
...እንቅልፉ የት ገባ⁉️
እስኪ የዚህች ብርድ-ልብስ ውለታ ያለባችሁ..ሹክ በሉኝ⁉️
....የኔ ዛሬም ገጠር አለች ዘሯ አልጠፋም...
ወይ ትዝታ ዛሬማ አለቀቀኝም...ስንቱን አስታወስኩት...⁉️
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍173
(⓭)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎
👉ክፍል =⓭
«ሙስሊም መሪዎችን ማመፅ»
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👉ክፍል =⓭
«ሙስሊም መሪዎችን ማመፅ»
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍25
እናት ለልጇ....!!
«የኔ ሳቅ እና ያንተ ሳቅ ልዩነቱ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ?
አንተ የምትስቀው ደስታ የተሰማህ ጊዜ ሲሆን.......
........እኔ... የምስቀው ግን አንተ ስትደሰት ባየሁ ጊዜ ነው።»
............
እማማዬ
የእዝነት ጥግ ወደር አልባ፡
የጥበብ ምንጭ ውብ መክተባ፡
የኔነት ውል ልዩ አርማዬ፡
ሰላም ላንች እማማዬ፡
--------------------------------
ኑር ነኝ (የለይላ ልጅ)
--------------------------------
https://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
«የኔ ሳቅ እና ያንተ ሳቅ ልዩነቱ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ?
አንተ የምትስቀው ደስታ የተሰማህ ጊዜ ሲሆን.......
........እኔ... የምስቀው ግን አንተ ስትደሰት ባየሁ ጊዜ ነው።»
............
እማማዬ
የእዝነት ጥግ ወደር አልባ፡
የጥበብ ምንጭ ውብ መክተባ፡
የኔነት ውል ልዩ አርማዬ፡
ሰላም ላንች እማማዬ፡
--------------------------------
ኑር ነኝ (የለይላ ልጅ)
--------------------------------
https://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍111
ትዳርን አሰልች የሚያደርጉት ጉዳዮች
----------------------------------
«እውነተኛና ምክንያታዊ የሆነ ፍቅር ታጋሽ ነው በውስጧ ፍቅር ያላት ሴት ታጋሽና ታዛዥ ነች።»
ከማግባትሽና ለምታገቢው ሰው ፈተና ከመሆንሽ በፊት መጀመሪያ ትዕግስት ይኑርሽ
አወ የማንም ከመሆንሽ በፊት መጀመሪያ የራስሽ በመሆን የተረጋጋ ስክነት ይኑርሽ የራስሽ እንደሆንሽ ሲሰማሽ የሌሎች ለመሆን ደርሰሻል።
......ፈገግ የሚያደርግ ቁም ነገር!!
👉እሱ.....‼️
እንደ ነቢዩ ሱለይማን ስልጣን ቢሰጠኝ ኖሮ የተወሰኑ ጅኖችን ልኬ ነበር የምወስድሽ አላት!!
...👉እሷ...!!
ጉረኛ! እስቲ የጅኑን ነገር እርሳና
የተወሰኑ ሽማግሌዎችን ብቻ ልከህ ውሰደኝ::
አለችው ይባላል።
«ዞሮ ትዳርን የሚያሰለቹት የሚከተሉት ናቸው
❶አለመደማመጥ የዘወትር ንትርክና ጭቅጭቅ‼️
❷በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ስህተቶችን መፈፀም።
❸ለረጂም ጊዜ መኮራረፍና እልህ መጋባት ለችግሮች ፈጥኖ መፍትሔ አለመስጠት።
❹በቂ የሆነ የፍቅር ጊዜ አብሮ አለማሳለፍ
❺ሁልጊዜ ራስን እንደተበዳይ መመልከት ማማረርና ደስተኛ አለመሆን ናቸው።
.....አቡ-ፋሩቅ ኑረዲን.....✍️
https://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
https://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
----------------------------------
«እውነተኛና ምክንያታዊ የሆነ ፍቅር ታጋሽ ነው በውስጧ ፍቅር ያላት ሴት ታጋሽና ታዛዥ ነች።»
ከማግባትሽና ለምታገቢው ሰው ፈተና ከመሆንሽ በፊት መጀመሪያ ትዕግስት ይኑርሽ
አወ የማንም ከመሆንሽ በፊት መጀመሪያ የራስሽ በመሆን የተረጋጋ ስክነት ይኑርሽ የራስሽ እንደሆንሽ ሲሰማሽ የሌሎች ለመሆን ደርሰሻል።
......ፈገግ የሚያደርግ ቁም ነገር!!
👉እሱ.....‼️
እንደ ነቢዩ ሱለይማን ስልጣን ቢሰጠኝ ኖሮ የተወሰኑ ጅኖችን ልኬ ነበር የምወስድሽ አላት!!
...👉እሷ...!!
ጉረኛ! እስቲ የጅኑን ነገር እርሳና
የተወሰኑ ሽማግሌዎችን ብቻ ልከህ ውሰደኝ::
አለችው ይባላል።
«ዞሮ ትዳርን የሚያሰለቹት የሚከተሉት ናቸው
❶አለመደማመጥ የዘወትር ንትርክና ጭቅጭቅ‼️
❷በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ስህተቶችን መፈፀም።
❸ለረጂም ጊዜ መኮራረፍና እልህ መጋባት ለችግሮች ፈጥኖ መፍትሔ አለመስጠት።
❹በቂ የሆነ የፍቅር ጊዜ አብሮ አለማሳለፍ
❺ሁልጊዜ ራስን እንደተበዳይ መመልከት ማማረርና ደስተኛ አለመሆን ናቸው።
.....አቡ-ፋሩቅ ኑረዲን.....✍️
https://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
https://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍95
«ደም እየፈሰሰ»
አንባ-ገነንነት ካልተገረሰሰ፡
የሰራውን ሰርቶ ሰው ካልተከሰሰ፡
ሁሉም በልቡ ላይ ቂም ከጠነሰሰ፡
ሰላምና ፍትህ ፍቅር ካልነገሰ፡
ነገን ተስፋ ካጣ ህልም ካልደገሰ፡
ለውጥን በአይኑ እያዬ ሰው ካልገሰገሰ፡
ከንፁህ ህዝባችን ስቃይ ከታፈሰ፡
የመከራ ንፋስ ሌት ቀን ከነፈሰ፡
ዳኛው ለእውነት ፍርድ ከተልፈሰፈሰ፡
ታው ባይ ሽማግሌ ተሰሚነት ካጣ፡
ወንድ ልጅ ተከፍቶ ካገሩ ከወጣ፡
ትላንት ያልነበረ ዛሬ ላይ ከመጣ፡
ወንድም በወንድሙ እሳት ከለኮሰ፡
ሁሉም ቡድን ሰርቶ ከተተራኮሰ፡
አንደኛው ተከብሮ አንዱ ከኮሰሰ፡
አብረን እንዘልቃለን ደም እየፈሰሰ፡
....ኑረዲን አል-ዓረብ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
አንባ-ገነንነት ካልተገረሰሰ፡
የሰራውን ሰርቶ ሰው ካልተከሰሰ፡
ሁሉም በልቡ ላይ ቂም ከጠነሰሰ፡
ሰላምና ፍትህ ፍቅር ካልነገሰ፡
ነገን ተስፋ ካጣ ህልም ካልደገሰ፡
ለውጥን በአይኑ እያዬ ሰው ካልገሰገሰ፡
ከንፁህ ህዝባችን ስቃይ ከታፈሰ፡
የመከራ ንፋስ ሌት ቀን ከነፈሰ፡
ዳኛው ለእውነት ፍርድ ከተልፈሰፈሰ፡
ታው ባይ ሽማግሌ ተሰሚነት ካጣ፡
ወንድ ልጅ ተከፍቶ ካገሩ ከወጣ፡
ትላንት ያልነበረ ዛሬ ላይ ከመጣ፡
ወንድም በወንድሙ እሳት ከለኮሰ፡
ሁሉም ቡድን ሰርቶ ከተተራኮሰ፡
አንደኛው ተከብሮ አንዱ ከኮሰሰ፡
አብረን እንዘልቃለን ደም እየፈሰሰ፡
....ኑረዲን አል-ዓረብ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍52
#ማሽላ_ጠባቂ__!!
-------------------------
እርሻውን ሲያሳምር ሲያስተካክል ከርሞ፡
ምርጥ ዘሩን ዘርቶ ሁለት ሶስቴ አርሞ፡
ምርቱን ይጠብቃል ከማማው ላይ ቆሞ፡
የልፋቱን ውጤት ወፍ እንዳይለቅምበት፡
ከርከሮ እንዳይገባ እንዳያጠፋበት፡
ደንቀሌ ወንጭፉን በደንብ አሳምሮ፡
ለጣቱ ማስገቢያ ከጫፉ ላይ ቋጥሮ፡
ከማሽላው መሀል እያንጎራጎረ፡
ሞገሱን ደርቦ አለ እንደነበረ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
#ማሽላ_ጠባቂ___!!
ፍየሎቹን ከቤት ከብቶቹን ከበረት፡
ፍቅር እየዘመረ ሳይሰማው ክስረት፡
ይህ ነው በቃ ለርሱ ሰላማዋ ኑረት፡
የደስታው ፍፃሜ ውድ ቀሪው ንብረት፡
እንግዳ ሲመጣ ለማየት አክብሮ፡
ወተቱን ከጓዳ እሸቱን ከጓሮ፡
ያለውን ፈልጎ ያመጣል ቆፍሮ፡
እውነትም ፍቅር ነው የገጠሩ ኑሮ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ቤቱ ያፈራውን ያገኘውን ሁላ፡
ይደሰትበታል ለእንግዳ እያበላ፡
አብሽር እግረኛየ አይዞህ እያለ፡
በፈገግታ ደምቆ ፈክቶ እያባበለ፡
ብሉልኝ ጠጡልኝ ብሎ የሚደሳ፡
ምንም የማይፈግ ከሰው ልጅ ሙገሳ፡
እርሱም ተሸክሞ ልጁን አሳዝሎ፡
እሸት የሚያመጣ አጋም አስመስሎ፡
ይህ ነው ያገሬ ልጅ ማሽላ ጠባቂው፡
ከማማው ላይ ቆሞ ያ ቅኔ ሰባቂው፡
አንተም ተዋወቀው አንችም ተዋወቂው፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
መልከ መልካም ቆንጆ የደግነት ቃና፡
ማሽላ ጠባቂው ያ የገጠር ጀግና፡
ይህ ነው የርሱ እውነታ ግሩም ማንነቱ፡
ክፋት ምቀኝነት አያውቅም በእውነቱ፡
ካመነ እምን ነው አያሸገሽግም፡
ሲናገር ሀቅ ነው ፈፅሞ አይሸሽግም፡
በቻለው ይለፋል ሲሰራም አይለግም፡
ያለውን ይሰጣል ለዘመድ ለባዳ፡
አዛኝ አስተዋይ ነው ተቀባይ እንግዳ፡
የጃምዮ መቃ ይመስላል አንገቱ፡
ሲራመድ ደስ ይላል መለሎ ነው ባቱ፡
የተመረቀ ነው በናቱም በአባቱ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
የሰውነት ወዙ ከርሱ ይጨመቃል፡
ፀባይ ስርአቱ ፈጥኖ ልብ ይሰርቃል፡
የብዙወችን ልብ በፍቅር ያፈዛል፡
በክፋት የመጣን በፀባይ ይገዛል፡
ከማሽላው መሀል ጎስ እየመረጠ፡
ፍሬው እንዳይረግፍ ፈጥኖ እየጋጠጠ፡
ከዳር ላይ ለበሬው ወስዶ እየመገበ፡
ከማሽላው ቆርጦ ደግሞ እየቀለበ፡
ወተት ሲያስፈልጠው ላሙን እያለበ፡
ጥንቅሽ ሲያሰኘወሸ ከማማው ላይ ወጥቶ፡
ሲፈልግም ቁሞ ሲፈልግ ተኝቶ፡
ደስታን ከፈጣሪ ከላይ የተሰጠ፡
በልፋት በእንግልት ተስፋ ያልቆረጠ፡
ንግግሩ ጣፋሽ ፀባዩ ጥም አርኪ፡
ከተንኮለኞች ጋር የሌለው ንክኪ፡
በክፉ ለነካው ጠላት አንበርካኪ፡
ሽጉጥ ሚኒሽሩን በጀርባው ታጣቂ፡
ገና በሩቅ ሲታይ ሞራሉ አነቃቂ፡
ትዕግስቱ የፀና ፍቅሩም አስረቅራቂ፡
ደስ ይለኛል በጣም ማሽላ ጠባቂ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በኑረዲን አል አረቢ 19/02/1443
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
-------------------------
እርሻውን ሲያሳምር ሲያስተካክል ከርሞ፡
ምርጥ ዘሩን ዘርቶ ሁለት ሶስቴ አርሞ፡
ምርቱን ይጠብቃል ከማማው ላይ ቆሞ፡
የልፋቱን ውጤት ወፍ እንዳይለቅምበት፡
ከርከሮ እንዳይገባ እንዳያጠፋበት፡
ደንቀሌ ወንጭፉን በደንብ አሳምሮ፡
ለጣቱ ማስገቢያ ከጫፉ ላይ ቋጥሮ፡
ከማሽላው መሀል እያንጎራጎረ፡
ሞገሱን ደርቦ አለ እንደነበረ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
#ማሽላ_ጠባቂ___!!
ፍየሎቹን ከቤት ከብቶቹን ከበረት፡
ፍቅር እየዘመረ ሳይሰማው ክስረት፡
ይህ ነው በቃ ለርሱ ሰላማዋ ኑረት፡
የደስታው ፍፃሜ ውድ ቀሪው ንብረት፡
እንግዳ ሲመጣ ለማየት አክብሮ፡
ወተቱን ከጓዳ እሸቱን ከጓሮ፡
ያለውን ፈልጎ ያመጣል ቆፍሮ፡
እውነትም ፍቅር ነው የገጠሩ ኑሮ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ቤቱ ያፈራውን ያገኘውን ሁላ፡
ይደሰትበታል ለእንግዳ እያበላ፡
አብሽር እግረኛየ አይዞህ እያለ፡
በፈገግታ ደምቆ ፈክቶ እያባበለ፡
ብሉልኝ ጠጡልኝ ብሎ የሚደሳ፡
ምንም የማይፈግ ከሰው ልጅ ሙገሳ፡
እርሱም ተሸክሞ ልጁን አሳዝሎ፡
እሸት የሚያመጣ አጋም አስመስሎ፡
ይህ ነው ያገሬ ልጅ ማሽላ ጠባቂው፡
ከማማው ላይ ቆሞ ያ ቅኔ ሰባቂው፡
አንተም ተዋወቀው አንችም ተዋወቂው፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
መልከ መልካም ቆንጆ የደግነት ቃና፡
ማሽላ ጠባቂው ያ የገጠር ጀግና፡
ይህ ነው የርሱ እውነታ ግሩም ማንነቱ፡
ክፋት ምቀኝነት አያውቅም በእውነቱ፡
ካመነ እምን ነው አያሸገሽግም፡
ሲናገር ሀቅ ነው ፈፅሞ አይሸሽግም፡
በቻለው ይለፋል ሲሰራም አይለግም፡
ያለውን ይሰጣል ለዘመድ ለባዳ፡
አዛኝ አስተዋይ ነው ተቀባይ እንግዳ፡
የጃምዮ መቃ ይመስላል አንገቱ፡
ሲራመድ ደስ ይላል መለሎ ነው ባቱ፡
የተመረቀ ነው በናቱም በአባቱ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
የሰውነት ወዙ ከርሱ ይጨመቃል፡
ፀባይ ስርአቱ ፈጥኖ ልብ ይሰርቃል፡
የብዙወችን ልብ በፍቅር ያፈዛል፡
በክፋት የመጣን በፀባይ ይገዛል፡
ከማሽላው መሀል ጎስ እየመረጠ፡
ፍሬው እንዳይረግፍ ፈጥኖ እየጋጠጠ፡
ከዳር ላይ ለበሬው ወስዶ እየመገበ፡
ከማሽላው ቆርጦ ደግሞ እየቀለበ፡
ወተት ሲያስፈልጠው ላሙን እያለበ፡
ጥንቅሽ ሲያሰኘወሸ ከማማው ላይ ወጥቶ፡
ሲፈልግም ቁሞ ሲፈልግ ተኝቶ፡
ደስታን ከፈጣሪ ከላይ የተሰጠ፡
በልፋት በእንግልት ተስፋ ያልቆረጠ፡
ንግግሩ ጣፋሽ ፀባዩ ጥም አርኪ፡
ከተንኮለኞች ጋር የሌለው ንክኪ፡
በክፉ ለነካው ጠላት አንበርካኪ፡
ሽጉጥ ሚኒሽሩን በጀርባው ታጣቂ፡
ገና በሩቅ ሲታይ ሞራሉ አነቃቂ፡
ትዕግስቱ የፀና ፍቅሩም አስረቅራቂ፡
ደስ ይለኛል በጣም ማሽላ ጠባቂ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በኑረዲን አል አረቢ 19/02/1443
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍40
شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
#ማሽላ_ጠባቂ__!! ------------------------- እርሻውን ሲያሳምር ሲያስተካክል ከርሞ፡ ምርጥ ዘሩን ዘርቶ ሁለት ሶስቴ አርሞ፡ ምርቱን ይጠብቃል ከማማው ላይ ቆሞ፡ የልፋቱን ውጤት ወፍ እንዳይለቅምበት፡ ከርከሮ እንዳይገባ እንዳያጠፋበት፡ ደንቀሌ ወንጭፉን በደንብ አሳምሮ፡ ለጣቱ ማስገቢያ ከጫፉ ላይ ቋጥሮ፡ ከማሽላው መሀል እያንጎራጎረ፡ ሞገሱን ደርቦ አለ እንደነበረ፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️…
በተለይ ማማ ላይ ወጥታችሁ ጥንቅሽ የበላችሁና «ማሽላ ጠባቂ»የሆናችሁ ሰወች አንብቡት
👍58