Telegram Web Link
«ደም እየፈሰሰ»

አንባ-ገነንነት ካልተገረሰሰ፡
የሰራውን ሰርቶ ሰው ካልተከሰሰ፡
ሁሉም በልቡ ላይ ቂም ከጠነሰሰ፡

ሰላምና ፍትህ ፍቅር ካልነገሰ፡
ነገን ተስፋ ካጣ ህልም ካልደገሰ፡
ለውጥን በአይኑ እያዬ ሰው ካልገሰገሰ፡

ከንፁህ ህዝባችን ስቃይ ከታፈሰ፡
የመከራ ንፋስ ሌት ቀን ከነፈሰ፡
ዳኛው ለእውነት ፍርድ ከተልፈሰፈሰ፡

ታው ባይ ሽማግሌ ተሰሚነት ካጣ፡
ወንድ ልጅ ተከፍቶ ካገሩ ከወጣ፡
ትላንት ያልነበረ ዛሬ ላይ ከመጣ፡

ወንድም በወንድሙ እሳት ከለኮሰ፡
ሁሉም ቡድን ሰርቶ ከተተራኮሰ፡
አንደኛው ተከብሮ አንዱ ከኮሰሰ፡
አብረን እንዘልቃለን ደም እየፈሰሰ፡

....ኑረዲን አል-ዓረብ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍52
#ማሽላ_ጠባቂ__!!
-------------------------
እርሻውን ሲያሳምር ሲያስተካክል ከርሞ፡
ምርጥ ዘሩን ዘርቶ ሁለት ሶስቴ አርሞ፡
ምርቱን ይጠብቃል ከማማው ላይ ቆሞ፡
የልፋቱን ውጤት ወፍ እንዳይለቅምበት፡
ከርከሮ እንዳይገባ እንዳያጠፋበት፡
ደንቀሌ ወንጭፉን በደንብ አሳምሮ፡
ለጣቱ ማስገቢያ ከጫፉ ላይ ቋጥሮ፡
ከማሽላው መሀል እያንጎራጎረ፡
ሞገሱን ደርቦ አለ እንደነበረ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
#ማሽላ_ጠባቂ___!!
ፍየሎቹን ከቤት ከብቶቹን ከበረት፡
ፍቅር እየዘመረ ሳይሰማው ክስረት፡
ይህ ነው በቃ ለርሱ ሰላማዋ ኑረት፡
የደስታው ፍፃሜ ውድ ቀሪው ንብረት፡
እንግዳ ሲመጣ ለማየት አክብሮ፡
ወተቱን ከጓዳ እሸቱን ከጓሮ፡
ያለውን ፈልጎ ያመጣል ቆፍሮ፡
እውነትም ፍቅር ነው የገጠሩ ኑሮ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ቤቱ ያፈራውን ያገኘውን ሁላ፡
ይደሰትበታል ለእንግዳ እያበላ፡
አብሽር እግረኛየ አይዞህ እያለ፡
በፈገግታ ደምቆ ፈክቶ እያባበለ፡
ብሉልኝ ጠጡልኝ ብሎ የሚደሳ፡
ምንም የማይፈግ ከሰው ልጅ ሙገሳ፡
እርሱም ተሸክሞ ልጁን አሳዝሎ፡
እሸት የሚያመጣ አጋም አስመስሎ፡
ይህ ነው ያገሬ ልጅ ማሽላ ጠባቂው፡
ከማማው ላይ ቆሞ ያ ቅኔ ሰባቂው፡
አንተም ተዋወቀው አንችም ተዋወቂው፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
መልከ መልካም ቆንጆ የደግነት ቃና፡
ማሽላ ጠባቂው ያ የገጠር ጀግና፡
ይህ ነው የርሱ እውነታ ግሩም ማንነቱ፡
ክፋት ምቀኝነት አያውቅም በእውነቱ፡
ካመነ እምን ነው አያሸገሽግም፡
ሲናገር ሀቅ ነው  ፈፅሞ አይሸሽግም፡
በቻለው ይለፋል ሲሰራም አይለግም፡
ያለውን ይሰጣል ለዘመድ ለባዳ፡
አዛኝ አስተዋይ ነው ተቀባይ እንግዳ፡
የጃምዮ መቃ ይመስላል አንገቱ፡
ሲራመድ ደስ ይላል መለሎ ነው ባቱ፡
የተመረቀ ነው በናቱም በአባቱ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
የሰውነት ወዙ ከርሱ ይጨመቃል፡
ፀባይ ስርአቱ ፈጥኖ ልብ ይሰርቃል፡
የብዙወችን ልብ በፍቅር ያፈዛል፡
በክፋት የመጣን በፀባይ ይገዛል፡
ከማሽላው መሀል ጎስ እየመረጠ፡
ፍሬው እንዳይረግፍ ፈጥኖ እየጋጠጠ፡
ከዳር ላይ ለበሬው ወስዶ እየመገበ፡
ከማሽላው ቆርጦ ደግሞ እየቀለበ፡
ወተት ሲያስፈልጠው ላሙን እያለበ፡
ጥንቅሽ ሲያሰኘወሸ ከማማው ላይ ወጥቶ፡
ሲፈልግም ቁሞ ሲፈልግ ተኝቶ፡
ደስታን ከፈጣሪ ከላይ የተሰጠ፡
በልፋት በእንግልት ተስፋ ያልቆረጠ፡
ንግግሩ ጣፋሽ ፀባዩ ጥም አርኪ፡
ከተንኮለኞች ጋር የሌለው ንክኪ፡
በክፉ ለነካው ጠላት አንበርካኪ፡
ሽጉጥ ሚኒሽሩን በጀርባው ታጣቂ፡
ገና በሩቅ ሲታይ ሞራሉ አነቃቂ፡
ትዕግስቱ የፀና ፍቅሩም አስረቅራቂ፡
ደስ ይለኛል በጣም ማሽላ ጠባቂ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በኑረዲን አል አረቢ 19/02/1443

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍40
👉አልናፈቃችሁም በአሏህ⁉️
👍89
.....እስኪ አትነካኩኝ.....⁉️

👉#እሸት__
--------------------------
ማኛና ሰርገኛ ነጭ ጤፍ ምስሩ፡
ሽንብራና ጓያ ባቄላና አተሩ፡
አረንጓደ ለብሶ ሲታዩት ማማሩ፡
ገጠር ሁሉም አለ ቀፎ ሞልቷል ማሩ፡
----------------------------------
ከዘንጋዳው መሀል ይመረጣል ጥንቅሽ፡
የትውልድ መንደሬ እስኪ ላስተዋውቅሽ፡
ገጠር ነሽ እያለ ማንም እንዳይንቅሽ፡
አዝመራሽን አይቶ ማንም እንዳልቅሽ፡
ሁሌ እሸት እንደሆንሽ ፈጣሪ ያዝልቅሽ፡
ከደግነትሽ ጋር ሰላም ላይ ያፅድቅሽ፡
------------------------------------
ከማሽሎች መሀል ጥንቅሽ ይመረጣል፡
ልጦ ለማላመጥ ሁሉም ይቋምጣል፡
ከገጠሩ ህዝቤ እሸት መች ይታጣል ፡
ባህሉ ነውና ሳትጠይቅ ይሰጣል፡

.....ገጠሬ ነኝ እሽ...

እናቴ ''ባለ አገር'' አባቴ ገበሬ፡
አንሸምትም እኛ ሽሮና በርበሬ፡
ሁሉም ከጓሮው ነው ፀጋ አለው ገጠሬ፡
እኔም ደስ ይለኛል እዚያ መፈጠሬ፡
---------------------------------

ተራራና ሜዳው አልባብ አልባብ ሲሸት፡
ገጠር ደስ ይለኛል ያለ ምንም ውሸት፡
መስከረም ጥቅምትን ይቀጠፋል እሸት፡
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
#በኑረዲን_አል_አረብ
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍83
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማሻአሏህ ተጋበዙ በትዝታ ሰፈር ሆናችሁ
👍87
የሶሪያው ንጉስ

አላሁ አክበር
አላሁ አክበር

ሺዓዎችና ኢኽዋኖች የሚፈሩት ጀግናውና ወጣቱ የሶሪያ መሪ..
ከኺሊፋዎች በኋላ የመጀመሪያዉ የሙስሊም ንጉስ በሆነው በሙዓዊያህ ቢን አቢ ሱፍያን(ረዲየላሂ አንሁ) ስም
በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ መንገድ ተሰይሞለታል።

ይህ ዛሬ በይፋ የተቀየረው መንገድ የቀድሞው ስሙ «የኢራቆች ጎዳና» ሲሆን

አሁን ደግሞ

ወደ ሙዓዊያ ኢብኑ አቢ ሱፍያን ተቀይሯል ይህ እጂግ የሚበረታታ ነው።

አላህ አዲሱ የሶሪያ መሪንም ለዑማዉ የሚጠቅም መሪ ያድርገዉ።አሚን።
👍193
2025/10/20 10:17:04
Back to Top
HTML Embed Code: